Ethio Construction Engineering
32.3K subscribers
6.27K photos
359 videos
1.99K files
3.33K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
The best shape of aggregate for concrete workability
Anonymous Quiz
45%
Rounded
19%
Elongated
22%
Flaky
15%
Conical
❤10
Specific gravity of water is
Anonymous Quiz
21%
2.67
5%
0
36%
1
39%
1000
❤15🏆5👍2
# fire extinguisher
Fire extingusher supplier who has this type can contact us @etconpworks
👍2
👉የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት 75 በመቶ ያሟላል የተባለዉ የከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ ስራ ሊጀምር ነዉ

🚧በ 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘዉና ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ስራዉን እንጀሚጀምር የሚጠበቀዉ የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት 150 ቶን ከሰል የማምረት አቅም እንዳለዉ ተዘግቧል።

🌟ከኢፕድ የተገኘዉ መረጃ እንደሚያሳየው በዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ እየተገነባ የሚገኘዉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን 75 በመቶ የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ያሟላል ተብሏል።

@etconp
👏8❤2👍2
Maximum load that a structure member can bear
Anonymous Quiz
83%
Ultimate load
12%
Safe load
3%
Crippling load
2%
Curtail load
❤5👍3
One of the following has no measuring unit
Anonymous Quiz
9%
Stress
44%
Elasticity
35%
Strain
12%
Force
🏆7👍4
Under normal circumstance strength of concrete depends on
Anonymous Quiz
79%
Water cement ratio
8%
Shear strength
11%
Bond strength
2%
Native of bond
👍6🙏6❤2😁2🕊1
Short answer questions will be posted on our IG page and FB pages if you are interested to participate concrete technology join us we will be posting ‘give short answer questions’

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👏7❤1
🫵ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን🤚

🌟ቃል በገባነው እና ብዝዎች በጠየቁን መሰረት Basic Autocad Teutorial Video Introduction ዛሬ በ Youtube ቻናላችን ጀምረናል።

▶️በየቀኑ እየለቀቅን በ ኣንድ ሳምንት ብቁ ጀማሪ የ ኣውቶካድ ባለሞያ ይሆናሉ።

🖱ገና ጀማሪዎች እና ተማሪዎች የሆናቹ በጣም ይጠቅማቹዋል

✨Share,like እና Subscribe በማረግ አግዙን 👇

https://youtu.be/4YrAhC8QlJM?si=fSBqy7Fg4wteJ3lr
👍16👏1😢1
Given ETABS model of multi story building

How many basements are there ?

Facebook:- https://www.facebook.com/etconp/

Instagram:- https://instagram.com/etconp?igshid=YmMyMTA2M2Y=
👍7❤1
🖱AutoCad ገና ጀማሪዎች እና ተማሪዎች የሆናቹ በጣም ይጠቅማቹዋል

🌟Part One Is Uploaded

✨Share,like እና Subscribe በማረግ አግዙን 👇

https://youtu.be/Xfj-rDsfo1w?si=2Rxj_EEKFZlAoMoB
🙏22❤4👍4🏆1
🫵የቀጠለ

🖱AutoCad ገና ጀማሪዎች እና ተማሪዎች የሆናቹ በጣም ይጠቅማቹዋል

🌟Part Two Is Uploaded

✨Share,like እና Subscribe በማረግ አግዙን 👇

https://youtu.be/o1oWPAg-Faw?si=tivPr7zGqamFbg3C
🙏6👍2
Ethio Construction Engineering
🪡 Post tension ከቃሉ ስንነሳ post - ድህረ ማለት ነው። concrete ከተሞላ በኋላ ብረቱን ስንወጥር post tension (ድህረ መወጠር) concrete ከመሞላቱ በፊት ደግሞ ሲወጠር pre-tension ይባላል። ልዩነቱን ሌላ ጊዜ በሰፊው አብራራለው ዛሬ ስለ post tension እናውጋ! Post tension እዛው መስክ(site) ላይ የምናከናውነው የግንባታ ዘዬ ነው pretension…
👉PART 2

🚧post tension 👆

🌟ለ post tension የምንጠቀመው ultra high strength steel strand (እጅግ በጣም ጠንካራ ስትራንድ) ነው። በ አማካይ እስከ 1.8GPa ጥንካሬ አላቸው ግማሽ inch diameter ያላቸው እስከ 15kN ይወጠራሉ

🚧ጥቅሞቹ

⏺ይሄ የግንባታ ዘዬ ፍልስፍናው ሚነሳው ከመሰረታዊ የ RC concept ነው። ኮንክሪትን ስትወጥረው (under tension- two forces in opposite line of action) ይቀነጠሳል፣ስለዚህ ኮንክሪት ደካማ የመወጠር አቅም አለው በተቃራኒ ጠንካራ የመኮማተር አቅም አለው፣ ብረት ደግሞ በተቃራኒው ስለዚህ post tension (PT) ሁለቱን በተሻለ ቁመና ላይ በማድረግ እጅግ ጠንካራ RC መዋቅር መፍጠር ነው።

▶️ቅድም እንዳልኩት ስትራንድ እጅግ ጠንካራ ስለሆነ bending moment diagramኡን ይቀይረዋል ስለዚህ የተራራቀ bar spacing ለሶሌታችን እንጠቀማለን ስለዚህ ብረት ቀነስን ማለት አይደል በተመሳሳይ ጥንካሬ ካገኘ structureኣችን cross-section መቀነስ ይኖርብናል ይሄ ማለት ደግሞ concrete volume ቀነስን ማለት ነው።

▶️Post tension እጅግ ብዙ ጥቅም አለው spanኣችንን ለመጨመር፣ የብረት መጠን መቀነስ፣ የኮንክሪት መጠን መቀነስ፣ ለፈጣን ግንባታ፣ ለ architectኦች የተሻለ ነፃነት ይሰጣል ምክንያቱም flat slab ብዙ ጊዜ ስለሚያገኙ በኋላ ይሄን ሀሳብ አናብራራዋለው።

@etconp
👍14
👉የባሕር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ፕሮጀክት አስፓልት ንጣፍ ስራ ተጀመረ

🚧በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ  በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ግዙፉ የአባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አስፓልት ንጣፍ ስራ  ተጀመረ፡፡

🌟ከሄኒ ጋርደን አደባባይ እስከ ዘንዘልማ መገንጠያ ድረስ የሚዘልቀው 4.7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባሕር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት እንዲሁም የመፋሰሻ ቱቦ ዋና ዋና ስራዎች በአብዛኛው ተጠናቀዋል፡፡

⏺በተጨማሪም የሰብቤዝ ንጣፍ ፣ የቤስ ኮርስ ንጣፍ ፣ የቤዛዊት መንገድ መሿለኪያ እና መወጣጫዎች ሙሌት እንዲሁም የከርብስቶን ስራዎች በሰፊው ሲከናወን ቆይቶ ወደ አስፓልት ንጣፍ ስራ ተሸጋግሯል፡፡

▶️የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያለበት የአፈፃፀም ደረጃ 38.2% ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የአስፋልት እና የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ፤ የቀለም ቅብ ስራዎች ፤ የመንገድ ላይ መብራቶች ተከላ እንዲሁም የእግረኛ መንገድ ንጣፍ በስፋት ለመጀመር ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

🖱የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበውን 825,659,857 ብር ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።

🚧መንገዱ የእግረኛ እና አካፋይን ጨምሮ መደበኛ ቦታዎች ላይ 51 ሜትር  እንዲሁም የህዝብ ማጓጓዣ ማቆሚያ ቦታዎች ላይ 59 ሜትር ስፋት አለው፡፡ ከዚህም ባሻገር በአንድ ጊዜ በግራ እና በቀኝ 6 መኪናዎችን ማስተናገድ እንዲችል ተደርጎ በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፤ የመኪና ማቆሚያ ቦታንም ጭምር አካቶ በባህር ዳር ከተማ ፍኖተ ካርታ መሰረት የሚገነባ ሰፊ የመንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡

👷‍♀ግንባታው ሃፍኮን ኮንስትራክሽን እና ክሮስ ላንድ ኮንስትራክሽን በተባሉ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጮች በጥምረት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

🫶የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የውጭ ሀገር አማካሪ ድርጅት ከሀገር በቀሉ ስታዲያ ኢንጂነሪንግ ስራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ንዑስ አማካሪ መሃንዲስ ጋር በጋራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

🚧መንገዱ የኢትዮ ሱዳን ዋና መስመር የሆነው የአዲስ አበባ - ባህርዳር - ጎንደር-መተማ  መንገድ አንዱ ክፍል ነው፡፡

⏺ግንባታው ተጠናቆ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ሲሆን ፤ በአገልግሎት ብዛት የተጎዳውን  ነባር  የባህር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ የትራፊክ ጫና ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያስተነፍሳል ተብሎ እንደሚታመን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጀክቱ አስተዳዳሪ ኢንጅነር አዲስሕይወት ታደሰ ገልፀዋል፡፡

Via ERA

@etconp
👍9❤1😢1
🌟ማዘጋጃ ቤት ህንጻ

🚧የ ዛሬ 59 ዓመት ልክ በዛሬዋ ቀን ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተመርቆ ተከፈተ


⏺መሀል አራዳ ላይ የሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ህንፃ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገለት በ8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ህንፃ ነበር። ህንፃውን ዲዛይን ያደረገው አርክቴክት አርትሮ ሜዜዲሚ የሚባል ጣሊያናዊ ሲሆን ኢንጅነር መኮንን ሙላቱ የተባሉ ኢትዮጵያዊ የቁጥጥር ስራውን በመስራት ለአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ ውለታ ውለዋል።

▶️ቀኃስ ጥቅምት 23 ቀን 1942 ዓ.ም የሕንፃ ግንባታውን ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሲሆን (ህንፃው ዲዛይን ሲደረግ 600 መቶ ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲኖሩትና የመኪና ማቆሚያና መናፈሻ ቦታ ጨምሮ በ75 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ እንዲያርፍ ነው) ተመርቆ የተከፈተው ግንባታው ከተጀመረ ከ 15 ዓመት በኋላ ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ ነበር።

▶️ወደ ሕንፃው ሲገባ በሚታየው ሰሌዳ ላይ የሚከተለው ጽሁፍ ሰፍሯል፦

🖱«ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመናገሻው ከተማ ለአዲስ አበባ ሕዝባቸው፣ ለማኅበራዊ ኑሮው፣ ለኤኮኖሜውና ለባህሉ ዕድገት አማካይ የአገልግሎት ቤት ይሆን ዘንድ ፈቅደው ያሠሩትን ይህን ሕንፃ፣ በሠላሳ አራተኛው ዘመነ መንግሥታቸው መርቀው ከፈቱ።»

በ ጀማል አብዱልአዚዝ በኩል

#ConstructionHistory

@etconp
👍21❤4🏆1
👉በስምንት ሰዓት ውስጥ 47 ሺህ ብሎኬት የሚያመርት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

🌟በዱከም ከተማ በአንድ ፈረቃ ወይም በስምንት ሰዓት ውስጥ ብቻ 47 ሺህ የተለያዩ መጠን ያላቸውን ብሎኬቶችን የሚያመርት ፋብሪካ ሥራ መጀመሩ ተሰማ።

🚧ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ ኃ/ተ/ግ/ማ በዱከም ከተማ ያቋቋመው ፋብሪካ በከፍተኛ ጥራት የሚያመርታቸውን የብሎኬት እና ቴራዞ ምርቶች ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ታውቋል።

▶️የፋብሪካው ባለድርሻና ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ወንደሰን መንግሥቱ እንደገለጹት፣ ፋብሪካው  34 ሺህ ባለ (40*15*20 ሳ.ሜ)፣  እና 25 ሺህ ባለ (40*20*20 ሳ.ሜ)፣ ውፍረት/ስፋት ያላቸውን ብሎኬቶች የማምረት አቅም አለው፡፡

⏺ቢውልደርስ አፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኑፋክቸሪንግ 99 በመቶ የአገር ውስጥ ጥሬ ዕቃ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጥራት ያለው ምርት ማምረት የሚችል የግንባታ ግብአት አቅራቢ ፋብሪካ ነው።

🖱የፋብሪካ ግምባታ እና ማሽን ተከላ 18 ወራትን ወራትን የፈጀ ሲሆን፣  ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይወጣበታል ተብሏል።

🖱እንደ ፕሮጀክት ማናጀሩ ገለጻ፣ ፍላጎትን መሠረት አድርገን በተጨማሪ ፈረቃ ምርት ማምረት እንችላለን ብለዋል።

🖱በተመሳሳይ የቴራዞ ማምረቻው በተለያየ ሞልድ በቀን ከ 2500 ካ.ሜ በላይ የሚሸፍን ከፍተኛ ጭነት መቋቋም የሚችሉ የወለል ንጣፎችን ማምረት እንደሚችል ታውቋል።

🌟ፋብሪካው  ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከ150 በላይ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

@etconp
👍15❤3👌2
👉በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ እየተገነባ ያለው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በግንቦት ወር ወደምርት ይገባል ተባለ

🖱የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምክትል ስራአስኪያጅ አበባው በቀለ በቀጣይ እስከ ግንቦት ወር የኤሌክትሪክ ስራዎች ሲጠና ወደምርት ይገባል ብለዋል።

🚧ፍብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ በቀን ከ130 ሺህ እስከ 150 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ያመርታል ብለዋል።

🌟ሃያ ሺህ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ተገምቷል።

@etconp
👍11❤1