Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.59K photos
56 videos
536 files
3.81K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
ለገሃር አካባቢ ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት ጀርባ በመገንባት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) ባለ 36 ፎቅ ሕንፃ የግንባታ ሂደት እዚህ ደርሷል።

ይህ ግዙፍ የቢሮ እና የገበያ መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ምርት ገበያው የጀመረውን የዲጂታል ግብይት ሥርዓት ይበልጥ ለማሳለጥና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል።

@etconp
❤10
🏠 የመኖሪያ ቤት ግንባታ ወጪ ማጠቃለያ

📜ይህ ሰነድ ለአቶ በቀለ ባደ ገብሬ የመኖሪያ ቤት ግንባታ የተዘጋጀ የሥራ ዝርዝር እና የዋጋ ማጠቃለያ (Bill of Quantities) ነው።

🚧የግንባታው ጠቅላላ ወጪ 4,069,062.08 ብር መሆኑን ያሳያል።

🏠 Residence Building Construction Cost Summary

⏺This document presents the Bill of Quantities (BOQ) for the residence building of Ato Bekele Bade Gebre.

🏷The summary highlights the costs for both Sub-Structure and Super-Structure works, with a total grand summary of 4,069,062.08 Birr.

@etconp
❤10
👉Different Types Of Loads On Building

🚧External loads on a structure may be classified in several different ways. In one classification, they may be considered as static or dynamic.

🔵  Static loads are forces that are applied slowly and then remain nearly constant.

⏺One example is the weight, or dead load, of a floor or roof system.

🔵  Dynamic loads vary with time. They include repeated and impact loads.

🟠   Repeated loads are forces that are applied a number of times, causing a variation in the magnitude, and sometimes also in the sense, of the internal forces. A good example is an off-balance motor.

🟠 Impact loads are forces that require a structure or its components to absorb energy in a short interval of time. An example is the dropping of a heavy weight on a floor slab, or the shock wave from an explosion striking the walls and roof of a building.

🟠    External forces may also be classified as distributed and concentrated.

🟠   Uniformly distributed loads are forces that are, or for practical purposes may be considered, constant over a surface area of the supporting member. Dead weight of a rolled-steel I beam is a good example.

🟠  Concentrated loads are forces that have such a small contact area as to be negligible compared with the entire surface area of the supporting member. A beam supported on a girder, for example, may be considered, for all practical purposes, a concentrated load on the girder.

🟠   Another common classification for external forces labels them axial, eccentric, and torsional.

🟠 An axial load is a force whose resultant passes through the centroid of a section under consideration and is perpendicular to the plane of the section.

🟠 An eccentric load is a force perpendicular to the plane of the section under consideration but not passing through the centroid of the section, thus bending the supporting member.

🔵 Torsional loads are forces that are offset from the shear center of the section under consideration and are inclined to or in the plane of the section, thus twisting the supporting member.

🟠Also, building codes classify loads in accordance with the nature of the source.

🔵Dead loads include materials, equipment, constructions, or other elements of weight supported in, on, or by a building, including its own weight, that are intended to remain permanently in place.

🔵 Live loads include all occupants, materials, equipment, constructions, or other elements of weight supported in, on, or by a building and that will or are likely to be moved or relocated during the expected life of the building.

🔵Impact loads are a fraction of the live loads used to account for additional stresses and deflections resulting from movement of the live loads.

🔵  Wind loads are maximum forces that may be applied to a building by wind in a mean recurrence interval, or a set of forces that will produce equivalent stresses.

🔵Snow loads are maximum forces that may be applied by snow accumulation in a mean recurrence interval.

🔵 Seismic loads are forces that produce maximum stresses or deformations in a building during an earthquake.

@etconp
❤12👍1👏1
👉ከኢትዮጵያ መሀንዲሶች የቀረበ  ጥሪ
‎🙅‍♂️🙅‍♀️👷‍♂️🏫🏛

‎✅ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ስራና ክህሎት ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
‎✅ለኢትዮጵያ ከተማና ፕላን ሚኒስትር
‎✅ለኢትዮጵያ ሕዝብ እምባ ጠባቂ
‎✅እንዲሁም ለሁሉም የፌዴራል ሚኒስትሮችና የሚመለከታችሁ ባለድርሻ አካላት፡፡

‎       ✍️ መልዕክታችን
‎🙏እኛ የኢትዮጵያ መሀንዲሶች ለሀገራችን እድገት፣ ለቴክኖሎጂ ልማት፣ ለኢንፍራስትራክቸር ግንባታ እና ለኢኮኖሚ ጥንካሬ ቁልፍ ሚና እንዳለን በእምነት እንናገራለን።
‎🏠ከ17 ዓመት በላይ የትምህርት ቆይታ፣ ብዙ ትጋት፣ ከፍተኛ የስራ ጫና እና የሙያ ኃላፊነት በመሸከም እኛ የምንሰራው ስራ በሀገር ደረጃ የህዝብ ሕይወት እና ደህንነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። የምንወስደው ውሳኔ እና የምንፈጥረው ውጤት ለትውልድ የሚቀር ተፅእኖ አለው።
‎🙏ሆኖም ዛሬ በኢትዮጵያ የመሀንዲሶች ሁኔታ ከተጠበቀው ክብርና ከሚገባው የሙያ ደረጃ ጋር አይጣጣምም።

‎😭የስራ አጥነት መጨመር፣ የደመወዝ አለመመጣጠን፣ የሙያ እድገት እጥረት እና የኑሮ ውድነት ግፊት ሙያችንን እያዳከመ ነው።
‎📌 የእኛ ጥያቄዎች

‎👁 የመሀንዲሶች የስራ አጥነት መፍትሄ
‎🙏በየዓመቱ በሺዎች የሚመረቁ መሀንዲሶች ተገቢ የስራ እድል ያጣሉ ነው። ይህ ሀገር ለማበልፀግ የሚችል አእምሮ እና ክህሎት እንዲበላሽ ያደርጋል።
‎👉 ስለዚህ የሚመለከተው አካል ፈጣን፣ ተግባራዊ እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን።
‎የመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ የአገር ውስጥ መሀንዲሶችን ቅድሚያ መስጠት

‎➚የStart-up እና የInnovation ድጋፍ
‎➚የሙያ ምዝገባና የፈቃድ ሂደቶች ማሻሻል

‎👁 የደመወዝ እና የደረጃ (Grade) ማሻሻያ
‎👉የመሀንዲሶች የደመወዝ መጠን ከሚሸከሙት ኃላፊነት እና ከኑሮ ውድነት ጋር አይመጣጠንም።
‎👉 በሙያዊ ክህሎት፣ በልምድ እና በኃላፊነት መጠን የተመሰረተ የደመወዝ መዋቅር እንዲዘጋጅ እንጠይቃለን።
‎👁 የሙያ ጥቅማጥቅሞች ማሻሻያ
‎➚የሙያ ዋስትና (Professional Insurance)
‎➚ቀጣይ ስልጠናና ሙያ ልማት ድጋፍ
‎➚የቤት እና የብድር እድሎች
‎➚የስራ ደህንነት መደበኛ ስርዓት

‎🌍 መሀንዲስነት ምንድን ነው?
‎✍️መሀንዲስነት የሀገራችን አዲስ የፈጠራ ጥበብ እና የቴክኖሎጂ መሠረት ነው። ኢንፍራስትራክቸር፣ ኢነርጂ፣ ማዕድን፣ ኮንስትራክሽን፣ ኢንዱስትሪ እና ዲጂታል ልማት — ሁሉም በመሀንዲሶች ትእዛዝ ይቆማሉ።
‎መሀንዲስነት ዘመን የወለደው ፖለቲካ አይደለም፤
‎➚የሀገር ግንባታ መሠረት ነው።
‎➚የትውልድ ተስፋ ነው።
‎➚የልማት ልብ ነው።
‎
‎🤝 እኛ የኢትዮጵያ መሀንዲሶች የምንጠይቀው ልዩ ልዩ ጥቅም ለራሳችን ብቻ አይደለም፤
‎✅የሀገር እድገት እንዲፋጠን፣ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ መስክ እንዲበረታ እንጂ።
‎✅ዛሬ መሀንዲሶችን መጠናከር ማለት ነገ ኢትዮጵያን መጠናከር ማለት ነው።
‎ክቡር መንግስት፣
‎✅ይህን ድምፃችን በአክብሮት እንድትቀበሉና በተግባር እንድትመልሱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

‎#የኢትዮጵያ መሀንዲሶች ኑ… አብረን ፍትህን እንፈልግ!!

‎#ፍትህ ለኢትዮጵያ መሀንዲሶች!!!
‎#ፍትህ ለኢትዮጵያ መሀንዲሶች!!!
‎#ፍትህ ለኢትዮጵያ መሀንዲሶች!!!
‎
@etconp
❤102👏15✍6
የስራ ማስታወቂያ

@etconp
👍2
👉በአዲስ አበባ ሕንፃ አስገንቢዎች የሠራተኞችን ደኅንነት የሚቆጣጠር ባለሙያ እንዲመድቡ ሊደረግ ነው

💫በአዲስ አበባ ከተማ ሕንፃ የሚያስገነቡ የሠራተኞችን ደኅንነትን የሚቆጣጠር ባለሙያ እንዲመድቡ እንደሚገደዱ፣ የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

🚧የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አበበ እሸቱ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሥራ ላይ የሚያጋጥም ሞትን ለመከላከልና የግንባታ ደኅንነት መሠረታዊ አስፈላጊነትን ለማረጋገጥ የሕንፃ አስገንቢዎች በዘርፉ የሠለጠነ የደኅንነት ባለሙያ እንዲቀጥሩ ይገደዳሉ፡፡

🏷ይህን ለማድረግ የሚያስችል መመርያ እንደሚወጣ ገልጸው፣ እያንዳንዱ የግንባታ ቦታ በሕግ ተደግፎ የደኅንነት ባለሙያ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

Via Reporter

@etconp
❤11