👉የ አርክቴክት እና መሀንዲስ ልዩነቶች
💫የሚከተሉት ሰሌዳዎች ህንጻን በተመለከተ የአርክቴክቶች እና መሀንዲሶችን ልዩነት በዝርዝር ያስረዳሉ።
https://t.me/ETCONpWORK
@etconp

❤10👍3🌚1
👉NEW VACANCY
💫Interior design and 3D Visualization
🔰Addis Ababa, Ethiopia
⚡️Deadline: December 3, 2024
▶️Vacancies: 2
🚧Education Qualification: Bachelors Degree
🏷Job Description
⏺Job Title: Interior design and visualization
⏺Company: Leyu Design PLC
⏺Job Type: Permanent
Salary: Based on the company ⏺scale
⭐️Description: INTERIOR DESIGNER FOR HIRE
▶️Our company looking for employees With the following requirements
•BSc degree in Architecture
• 0-2 years experience
•good software skills (3DsMAX,lumion,revit,autoCad..)
•The person needs to be updated and upgraded with the latest trends in interior design.
•curious, proactive & needed to be able to complete any task on their own with minimum guidance.
❇️the interested applicants can send their updated portfolio and their payment expectation to on telegram📩👇
https://t.me/+251963698081

👍4❤1👏1
BIM Building Management Systems.pdf
9.8 MB
🎲ለማንኛውም አስተያየትዎ እና ሀሳብዎ ይጻፉልን!
📜ዋናው ቻናላችል ለመቀላቀል👇
👉https://t.me/ETCONp
@etconp
📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT
💫ቲክቶክ:👇
www.tiktok.com/@etconp7
@etconp
📜ዋናው ቻናላችል ለመቀላቀል👇
👉https://t.me/ETCONp
@etconp
📩ሊጽፉልን ካሰቡ @ETCONpBOT
💫ቲክቶክ:👇
www.tiktok.com/@etconp7
@etconp
👍19🙏4❤2
👉ባለ 13 ወለሉ የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደረገ።
በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገነቡ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በባለቤትነት የማከናወን ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት በማከናወን ለአገልግሎት እያበቃ ይገኛል።
ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነውና በስራ ተቋራጭ አፈፃፀም ውስንነት ተገምግሞና የቀደመ ውሉ ተቋርጦ ዳግም ከቆመበት እንዲቀጥል የተደረገው የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር 2B+G+11 ሕንፃ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።
ከ1.1 ቢሊየን ብር በላይ ተመድቦለት በ 3000 ካ.ሜ. ቦታ ላይ የተገነባው ይህ የክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ለተለያዩ ፅ/ቤቶች የሚውሉ ቢሮዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸው 1,224 እና 459 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ 30 ተሽከርካሪዎችን በቤዝመንት እንዲሁም 65 ተሽከርካሪዎችን በውጪ የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ፓርኪንጎች ፣ ጂምናዚየም ፣ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ ፣ ሬስቶራንት ፣ የመረጃ ክፍል ተሟልተውለታል።
ከዚህ በተጨማሪ አቅመ ደካማ እና የአካል ጉዳት ያለባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከግምት ያስገቡ 4 ዘመናዊ ሊፍቶች የተገጠሙለት ሲሆን ለአገልግሎት ሰጪውና ለአገልግሎት ፈላጊው ምቹ እና ሳቢ ከባቢን የሚፈጥር የአረንጓዴ ስፍራዎች የፕሮጀክቱ አካል ተደርገዋል።
ይህ ሕንፃ ከቀደሙት የክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃዎች ልምድ የተወሰደበትና የመዲናዋን የዕድገት ደረጃ እንዲሁም የስማርት ሲቲ ትልም ከግምት አስገብቶ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማካተት የተከናወነ ሲሆን በግንባታ ስራው ባማኮን ኢንጂነሪንግ በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኔማድ ኢንጂነሮችና አርክቴክቶች ኃ/የተ/የግ/ማ በአማካሪነት ተሳትፈውበታል።
የዚህ ህንፃ መገንባት የበርካታ ፋይናንስ ተቋማት መቀመጫ ለሆነው የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር አገልግሎት ትልቅ ዓቅም መፍጠር ከማስቻሉም ባለፈ አስተዳደሩ ለህንፃ ኪራይ የሚያወጣውን ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በማስቀረት ረገድ ትልቅ ፋይዳ የሚኖረው ይሆናል።

👍9
👍6
👉የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከ አሚጎስ ኢንስቲትዩት በመተባበር ከጀርመን ሀገር በተጋበዙ ዓለም አቀፍ አሰልጣኞች የፊታችን ሕዳር 24 እና 25/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ትኩረቱን በስራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት አመራር (health and safety leadership) ያደረገ ስልጠና በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አዘጋጅቷል ስለሆነም ስልጠናውን መውሰድ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከታች በተያያዘው ሊንክ በመግባት መመዝገብና ስልጠናውን ተካፍሎ ሰርተፍኬት መውሰድ እንደሚችል እንገልፃለን፡፡
💫ማስታወሻ:- ቀድሞ በተቀመጠው ሊንክ ገብታችሁ የተመዘገባችሁ የምዝገባ ቅፁ ላይ ማስተካከያ ስለተደረገበት ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንደ አዲስ ገብታችሁ በድጋሚ መመዝገብ ይኖርባችኋል።
🏷ለመመዝገብ ከታች የተያያዘውን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://forms.gle/J4ktYcejEXcKJsV8A

👍12🔥1
👉የከተማ መሬቶች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተጠቆመ‼️
🚧በኢትዮጵያ ከተሞች ያሉ መሬቶች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው ተሻሻሎ በቀረበው የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጠቆመ።
⏺በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረት ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ለመመዝገብ እና የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ ተሻሽሎ የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል።
▶️በተሻሻለው አዋጅ ውስጥም የከተማ መሬት ሊዝን በተመለከተ ከኅዳር 18/2004 በኋላ ያለፈቃድ የተያዙም ሆነ ፈቃድ ባላገኙ መሬት ላይ ያሉ ግንባታዎችን ጭምር በማፍረስ መንግስት የመሬት ይዞታዎቹን እንደሚረከብ ተመላክቷል።
💫እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ከተሞች በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሊዝ የመሬት ስርዓት ውስጥ መካተት እንዳለባቸው በተሻሻለው በረቂቅ አዋጅ ላይ መካተቱን ለሚመለከታቸው አካላት ተብራርቷል።

👍5❤1
Forwarded from Ethio Construction Engineering
Ethio Construction Engineering
Photo
👉የ አክሱም ሀወልቶች የ ግንባታ ታሪክ
የአክሱም ሀውልቶች ስቴልስ በመባልም የሚታወቁት በጥንታዊቷ የአክሱም ከተማ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የግራናይት ቅርፆች ናቸው።
እነዚህ ሐውልቶች ለጥንታዊው የአክሱም መንግሥት የመቃብር፣ የመታሰቢያ ሐውልት፣ የሀይል እና የሃይማኖት እምነት ምልክቶች ሆነው ያገለገሉ ጉልህ ታሪካዊ እና አርኪኦሎጂያዊ ቅርሶች ናቸው።
የአክሱም ሀውልቶች ግንባታ ታሪክ በቅድመ ክርስትና ዘመን የተጀመረ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ስቴሎች በ 4ኛው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደተገነቡ ይታመናል።
እነዚህ ከፍ ያለ ሕንጻዎች የተቀረጹት ከግራናይት ነጠላ ብሎኮች ሲሆን ብዙውን ጊዜ ውስብስብ በሆኑ ጽሑፎች፣ ምልክቶች እና የጂኦሜትሪክ ንድፎች ያጌጡ ነበሩ።
ሐውልቶቹ የተገነቡት የሞቱትን ገዥዎች፣ መኳንንት እና ሌሎች አስፈላጊ ሰዎችን ለማስታወስ እንዲሁም ጠቃሚ ክንውኖችንና ድሎችን ለመዘከር ነው።
እንዲሁም የመንግሥቱን ኃይልና ክብር እንዲሁም የአክሱማዊውን የአማልክት ጓዳ ለማክበር ምልክት ሆነው ያገለግላሉ ተብሎ ይታመን ነበር።
ታላቁ ስቲል በመባል የሚታወቁት የአክሱም ሀውልቶች ረጅሙ ከ 33 ሜትር (108 ጫማ) በላይ ነው
ቁመታቸው በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከመፍረሱ በፊት ነበር።
ሌላው ታዋቂው ሀውልት የአክሱም ሀውልት በ1930ዎቹ በጣሊያን ጦር ተወስዶ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በ2008 እንደገና ተተከለ።
የአክሱም ሀውልቶች ግንባታ የላቀ የምህንድስና እና የስነ-ህንፃ ክህሎት እንዲሁም ከፍተኛ የሰው ሃይል እና ግብአቶችን የሚጠይቅ ነበር።
የአክሱም ሐውልቶች ክብደት ይለያያሉ ትልቁ ሀውልት ታላቁ ስቴል ወይም የአክሱም ሀውልት ተብሎ የሚጠራው 160 ቶን (160,000 ኪሎ ግራም) ይመዝናል።
የእነዚህ ግዙፍ የድንጋይ ህንጻዎች ማጓጓዝ እና መገንባቱ የአክሱማውያን ስልጣኔ የቴክኖሎጂ ብቃቱን እና ድርጅታዊ አቅሙን የሚያሳዩ በጥንት ጊዜ የሚደነቅ ተግባር ነበር።
በአጠቃላይ የአክሱም ሀውልቶች ግንባታ ታሪክ የጥንታዊው የአክሱም መንግስት የበለፀጉ የባህል እና የስነ-ህንፃ ቅርሶች ምሳሌ ሲሆን የእነዚህን ሀውልት ህንጻዎች ዘላቂ ፋይዳ ከቀደምት ጋር የሚዳስሱ ግኑኝነቶች መሆናቸውን አጉልቶ ያሳያል።
#ConstructionHistory
መልካም በዓል❤🙏
Via FILA

👏7👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉በአዲሱ የከተማ መሬት አዋጅ መሰረት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የተገነቡ ሰነድአልባ ቤቶች ይወረሳሉ።
🚧በከተማ ውስጥ የተካለሉ በነባር/በ ውል የተያዙ ጭምር ወደ ሊዝ እንዲዛወሩ የሚፈቅድ ህግ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ተካቷል።

❤2👍1
👉NEW VACANCY
💫Our company SATCON CONSTRUCTION PLC has seeking Qualified Professionals in the following positions.
1 - IT Technician.
Work experience, minimum 2 years.
Required, 2
Educational Qualification, Diploma or BSC in IT or related fields. ( CGPA 3.4 and above)
2 - Office Engineer
Work experience, minimum 3
years in the industry.
Required, 4
Educational Qualification, BSC in -Civil Engineering or related fields. (CGPA 3.2 and above)
3-Senior Office Engineer
Work experience minimum 6 years in the industry.
( CGPA 3.2 and above)
📩How to apply,
🏷send your application with CV and academic credentials and Experience via Only Email engabiwow@gmail.com.
🚧For all positions, place of work Addis Ababa Head Quarter.
⏺experience out of construction companies are not acceptable.
Salary, attractive and negotiable.

👏6👍5❤1😁1
Forwarded from Ethio Construction Engineering
👉ይህ የ40/60 ህንፃ ቦሌ አያት 2 ብሎክ 38 ይባላል
ዕጣ ከወጣበት ሁለት አመት ሊሞላው ሲሆን ባለ 13 ፎቁ "ህንፃ" በሚያሳፍር እና አደገኛ በሆነ ሁኔታ ተሰርቶ ቆሟል።
እስካሁን ከ 8ኛ ወለል በላይ ያለው የውስጥ ለውስጥ partition የሌለው፣ መወጣጫ ደረጃው ያላለቀ፣ የውስጥ ልስን የሌለው እና ጣራው ያልተመታ ነው።
ህዝብ ግን የንግድ ባንክ ክፍያውን ቤት አገኝ ብሎ እየከፈለ ነው።
ህንፃው ውስጥ ሰው ገብቶ አስከፊ አደጋ ሳያደርስ በፍጥነት መፍትሄ ያስፈልገዋል።

🤔9😱1
👉የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር አዲሱ ረቂቅ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 02/2017 ከ"ባለሙያ ተኮር አዋጅነት" ወደ "ድርጅት ተኮር" ለመለወጥ የሚደረገው ጥረት እጅግ አንዳሳሰበው አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አርኪቴክቶች ማሕበር በረቂቅ አዋጁ ላይ አቋም የያዘባቸውን ሶስት ጉዳዮች በመግለጫው አብራርቷል።
(1ኛ) የ’’አማካሪ ድርጅት’’ የንግድ ተቋም እንደመሆኑ በንግድ ሕግ እንጂ በሕንጻ አዋጅ ውስጥ መካተት የለበትም ያለው ማሕበሩ፣ በተለይም ረቂቁ በአሁኑ ወቅት በአማካሪ ስም ብዛት ያላቸው ዘርፎች በመኖራቸው እና ሚናቸው በግልጽ ባልተቀመጠበት ሁኔታ፤ በተለይም “ትሩፋቶቹን” ለድርጅት በማድረግ “ተጠያቂነትን” ግን ለባለሙያ የተሰጠበትን አሰራር የተሳሳተ እና ከተዛማጅ አዋጆች ጋር የሚጣረስ ኢፍትሃዊ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የሃገርን ጥቅም የሚጎዳ እና የአዋጁ ዋና ዓላማ የሆነውን “የሕዝብን ጤንነት እና ደህንነት መጠበቅ”ን እንዳይረጋገጥ የሚያደርግ፣ በዘመናት ተፈትነው የተረጋገጡ ሃገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አሰራሮች ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ፈጽሞ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይገባ አበክሮ ገልጿል።
(2ኛ) የሙያ ጥሰት ተጠያቂነትን እና ቅጣትን በሚገባ እደግፋለሁ ያለው ማሕበሩ፣ የሙያ ጥሰት ገለልተኛ በሆነ እና ተጠሪነቱ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወይም ለክልል መስተዳድር በሆነ ገለልተኛ የባለሙያ ምርመራ ቦርድ ከተረጋገጠ በኋላ ክሱ አግባብ ባለው ፍርድ ቤት ሊታይ ይገባል እንጂ፤ ረቂቁ አዋጁ "ተቋም" እያለ ለሚጠራው “የአስተዳደር አስፈፃሚ አካል” የሰጠው ሥልጣን “ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ አጣሪ ቦርድ ሰያሚ፣ ራሱ ፈራጅ” የሆነበትን አሠራር ከህገ መንግስት እና ወንጀለኛ መቀመጫ ሕግጋት ጋር የሚጣረስ ከመሆኑም አልፎ በፍትህ ስርአቱ ላይ አላስፈላጊ ጫና የሚፈጠር እና የበቀል መሳሪያ ሊሆን እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።
(3ኛ) የሕንፃ የዲዛይን ስራ የአርክቴክቱ የፈጠራ ውጤት እንደመሆኑ የዲዛይን ማስተባበር ስራን ተገቢው እና የተሟላ የዲዛይን ትምህርት ዝግጅት ያለው አርክቴክቱ ብቻ ስለሆነ የማስተባበሩ ስራ በአርክቴክቱ ብቻ እንዲሆን ጠይቋል። ከሌሎች ሙያዎች በተለየ የአርክቴክቱ ስልጠና ሁሉንም በሕንፃ የዲዛይን እና ግንባታ ተያያዥ የምህንድስና ትምህርቶችን የሚያካትተው በዋናነት የሕንፃ የዲዛይን ስራን ለማቀናጀት እንዲረዳው ነው። የሕንጻ ዲዛይን ስራ እና ግንባታ ሂዳት የተለያዩ የአሰሪ ፍላጎቶችን ጨምሮ የብዙ የምህንድስና ባለሙያዎች ግብዓቶችን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ሁሉም ባለሙያ የሚያበረክተው ስራ አርክቴክቱ በምናቡ ከፈጠረው የሳይንስ እና ጥበብ ውህድ ለሆነው “ኪነ ሕንጻ” በመሆኑ የማስተባበር ሚና የአርክቴክቱ ብቻ እንደሆነ ገልጿል።
ማሕበሩ በህግ መወሰኛ ምክር ቤት መድረክ ላይ በአዲሱ ረቂቅ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 02/2017 ላይ ለቀናት በዘለቀው ውይይት ማጠቃለያ ቀን ስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዩች በይፋ በተገለፀው መሠረት ሳይሸራረፉ እና ሳይጨመርባቸው እንዲጸድቁ የጠየቀ ሲሆን፣ በተለይም ጥቂት ባለሙያዎች እና አንዳንድ ማህበራትን የወከሉ ግለሰቦች በስብሰባ እና በውውይት መድረኮች ላይ የወደቁ ከሀገራዊ እና አለም አቀፍ አሠራሮች የሚጣረሱ ሃሳቦችን መደበኛ ባልሆነ መንገድ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ውሳኔን ቀልብሶ ለማካተት የሚያደርጉት ከፍተኛ ግፊት መንግስት የሄደበትን አሳታፊ እና ሕዝባዊ አካሄድ ላይ ውሃ የሚቸልሱ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቦ፣ መንግስት ይህንን አደገኛ አካሄድ እንዲከላከልለት ጠይቋል ።
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማሕበር የዓለም አቀፉም ሆነ የአሕጉር አቀፉ አርክቴክቶች ማህበራት አባል ሲሆን ከ32 አመት በላይ ያስቆጠረ እና ባዳበረው ዓለም አቀፋዊ የልምድ ልውውጥ የኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ይሆን ዘንድ እየታገለ ያለ አንጋፋ የሙያ ማሕበር መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል ዋናው ቻናላችን ላይ ለቀነዋል።

👍11👏2😁1