Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
photo_2025-09-01_10-49-04.jpg
211.1 KB
- አስፋልት ዊሪንግ ኮርስ ግዥ ጨረታ

- የተለያዩ ደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ ግዥ ጨረታ

- የተለያዩ የቆዳ ጫማዎች እና ሌሎች የቆዳ ውጤቶች ግዥ ጨረታ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤5😢1
👉JOB VACANCY

💫YOTEK looking for over 30

@etconp
❤4
ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

📌ፕሌትና ጄቦልት በፈለጉት አይነት የተዘጋጀ አለን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን


0904040477
0994941708
❤1
የ"Site Diary" ጥቅምና ይዘት
{The importance and Format of Site Diary}


📌በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል።

በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን። ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።  

ክፍል አንድ  ዋና ዋና ጥቅሙ፦


1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል።

2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦  በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው።

3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት  ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።

ክፍል ሁለት፡ ይዘቱ ምን መምሰል አለበት


ይቀጥላል .....

@etconp
❤18👍6
👉CONCRETE WORKABILITY

⏺The workability of Ready Mix Concrete (RMC) refers to how easy it is to mix, transport, place, compact, and finish the concrete without segregation or bleeding.

⏺It is a key property because RMC is often transported over some distance before being poured.

🏷Workability Tests:

1⃣ SLUMP TEST:  measures consistency. 

⚡️RMC Slump (mm): (Standard)

✅Slabs, beams, columns 75–100 Normal workability

✅Pumped concrete 125–175 High workability

✅Complex formwork 150–200 Very high, may need superplasticizers

✅Self-compacting concrete N/A (flow test 600–800 mm) No vibration required.

2⃣ COMPACTING FACTOR TEST:

⏺The compacting factor test is used to measure the workability of fresh concrete, especially for mixes with low workability (stiff concrete) where slump test is not very reliable.

💫Apparatus:

1. Compacting Factor Apparatus (consists of two conical hoppers and a cylindrical mould)

2. Tamping rod (16 mm diameter and 60 cm long)

3. Weighing balance (accuracy of 10 g)

4. Trowel and scoop

💫Procedure

1. Preparation of Apparatus:
Ensure the apparatus is clean and free from hardened concrete.

⏺Oil the inner surfaces lightly.

2. Filling Upper Hopper:
Fill the upper hopper with freshly mixed concrete without compaction.

3. Discharge to Lower Hopper:
Open the trap door and allow concrete to fall into the lower hopper.

⏺Do not apply any compaction.

4. Discharge to Cylinder:
Open the trap door of the lower hopper so concrete falls into the cylindrical mould.

⏺Level the top surface without tamping.

5. Weight Measurements:
Weight of partially compacted concrete (W1):

⏺Weigh the concrete in the cylinder.
⏺Weight of fully compacted concrete (W2):
⏺Fill the cylinder in layers and compact each layer thoroughly (e.g., by rodding or vibration) and weigh again.
⏺Weight of empty cylinder (W): Measure for reference.

6. Calculation

Compacting Factor(CF)={W1 - W} - {W2 - W}

W1 = weight of partially compacted concrete + cylinder

W2 = weight of fully compacted concrete + cylinder

W = weight of empty cylinder

🚧Typical Values:

⏺Very Low Workability (e.g., road construction): 70 – 80

⏺Medium Workability (e.g., reinforced concrete): 85 – 92

⏺High Workability (e.g., congested reinforcement): 95 – 100

@etconp
❤10👍2
#ADVERTISEMENT

🏭🏠TSEGAYE and YOHANNES J-ቦልት & PLATE 🏚🏗 🌁🌆

🧿 OUR SERVICES ⤵️

🔲Plate

⚙️  J-Bolt

⚓Anchor Bolt

➽Tie Rod

🏭🛖🌉scrap🚧🪝🔗
Phone : 🤳0938494506 
              🤳 0951087077
              🤳 0929044037
እናመሰግናለን::
👉አድራሻ፦  መርካቶ ምንአለሽ ተራ ከጭድ ተራ ከፍ ብሎ

https://t.me/tsegaye2016Jbolt
❤2
✨የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/SG-03/2018

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ የኦግዝለሪ(ጀነሬተሮች፣የውሃ ፓምፖች፣ቫይብሬተሮች፣ሚክሰር፣ኮምፓክተር እና የመሳሰሉት)መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1.በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

2.የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም ገዥ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው ፡፡

3.በጨረታዉ የተመዘገቡ ተጫራቾች ዕቃዎቹን ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጲያ ኮንስተራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀንና ሰዓት መመልክት ይቻላል፡፡

4.ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ(10%)የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

5.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በግዥ መምሪያ-1 ቢሮ ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን መስከረም 8 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡

6.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ቀን መስከረም 8 ቀን 2018ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

7.ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታ ማስከበሪያው ተወርሶ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል፤

8.አሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ በደረሰው በ5 ቀናት ውስጥ የዕቃውን ዋጋ ከፍሎ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት፤

9.የጨረታ አሸናፊው ክፍያውን ከፍሎ ንብረቱን በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት፤

10.ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

11.ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
         
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ ቢሮ
   አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ በስተጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ
                 
አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት-ለፊት
                   
  ስልክ ቁጥር 0118 96 29 91

@etconp
❤7
👉የኮለን ፎርምወርክ ቼክሊስት

💫1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/

⏺የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ነው።

💫2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/

⏺ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን

💫3.አቀባዊ ሊኛ/ቱምቢ/Vertical alignment/

⏺የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን

💫4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/

⏺ኮለምኑ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው መሆኑን

💫5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/

⏺የኮለኑ ወርድና ስፋት በዲዛይኑ መሰረት መሰራቱን ማረጋገጥ።

💫6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/

⏺አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን

💫7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/

⏺ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ

💫8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት
/Design cover/

⏺በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።

@etconp
👍20❤10
👉በ 14 ዓመታት የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጉዞ ውስጥ ከ15ሺ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል !!

💥ሕዳሴ የደም ዋጋም ተከፍሎበታል !

ሪፖርተር የእንግሊዘኛው መጽሔት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር ያደረገውን ቆይታ አውጥቷል።

በቆይታው ማብቂያ ጠያቂው ጋዜጠኛ በእውቀት አበበ ይህን ጠየቀ ...እርሳቸውም መለሱ

Is it true that as many as 15,000 people died while building the dam over the past 14 years?

Yes, that is true.

በገንዘብ በጊዜና በብዙ መስዋዕትነት ብቻ አይደለም ሕዳሴ በ15 ሺ የአገራችን ልጆች ደምም ጭምር ነው የተገነበው😢❤

©️ ኤርሚያስ በጋሻው ገሰሰ

📜ሪፖርተር ጋዜጣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃልመጠየቅ አንበቡ👇

https://thereportermagazines.com/4076/?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR5S6q17e_MubeBe6FwfpnOGpkMwpRxlipphXfneiSHIpYNitSAJ5MadMPygKg_aem_pDAw4-7glxVrzIgiOqC4SA

@etconp
❤5😢5👍1
👉JOB VACANCY

📌Yotek Construction PLC looking for over 30 personnel

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍5❤2
👉JOB VACANCY

⭐️Delta Bright General Construction PLC is hiring professionals with Junior Office Engineer

💥Job type : Junior Office Engineer

※ Qualification: BSc in Civil Engineering

※ Experience: 0-1 years

🕹Place of Work: Addis Ababa,

※ Salary: Negotiable/Attractive

※ Required No: 2

📩How to Apply: Applicants with the above mentioned criteria shall submit their application CV and credential and supportive documents to Delta Bright General Construction PLC. through telegram @Deltabright1254

@etconp
❤14👏1🎉1
👉የጨረታ ማስታወቂያ

የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የህንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ እና የተለያዩ የራስ አገዝ የልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ይፈልጋል።

ገዳሙ ከመንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ በአካባቢው ያለውን ማኀበረሰብ የሚጠቅም አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎችንም አካታለች፡፡

ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ያቀርባሉ።

በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/፣
የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል ሚገልፅ የጽሑፍ ማስረጃ (ጊዜ ያላለፈበት መሆን ይኖርበታል)፣
የተ.እ.ታክስ VAT/ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
ተጫራቾች በታክስ ባለሥልጣናት የተመዘገቡ እና የታከስ ማስረጃ ወረቀታቸውን ቅጂዎች ጨምሮ ትክክለኛ ሰነዶችን ማዘጋጀት መቻል አለባቸው።
2. ተጫራቾች ሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የግንባታ ሥራን ለማሰራት ቢያንስ GC–5/ BC 5 አና ከዚያ በላይ ሕጋዊ የተመዘገበ ተቋራጭ መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች የተናጠል ዋጋቸውን እና ጠቅላላ ዋጋቸውን ቫትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብር በግልጽ መግለጽ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1,000,000 በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የኢንሹራንስ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም።

5. ተጫራቾች ጥያቄ ካላቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል ፕሮፖዛል በሁለት የተለያች ማህደሮች በማዘጋጀት ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በታሸገ ቴክኒካል የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የቴክኒክ ምዘናውን በተሳካ ሁኔታ ያለፈ ኮንትራክተር ብቻ ለፋይናንስ ያለምዘና ግምት ውስጥ ይገባል። ቴክኒካል ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻው ዝርዝር መረጃ በመገኛ መረጃዎቻቸው ይነገራቸዋል።

8. ጨረታው ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ከታች በተቀመጠው አድራሻ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።

አድራሻ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ሾላ እልፍ ጸጋ ህንጻ 4ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- +251 93 864 4444/ +251 91 807 7957

በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በምስራቅ በስሳ ወረዳ ቤተ- ክህነት ጽ/ቤት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም

@etconp
❤14👍1
doc06739920250903063640_page-0001.jpg
779.1 KB
ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ኮንክሪት ቱቦ (RC-PIPI) ባለ 1000 እና ባለ 1200 ሚ.ሜ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
doc06740020250903063702_page-0001.jpg
885.5 KB
ግዥ  ጨረታ  ማስታወቂያ

ፊኖ (00) ጠጠር (Aggreagate fine 00) እና 01 ጠጠር (Aggregate 01)

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤7
👉ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤

@etconp
🙏3❤1
🏭🏠TSEGAYE and YOHANNES J-ቦልት & PLATE 🏚🏗 🌁🌆

🧿 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ⤵️

🔲Plate at any Size & thickness.

⚙️  J-Bolt height and diameter you want it.

🔩 anchor ⚓ bolt at any size

🏭🛖🌉scrap🚧🪝🔗
Phone : 🤳0938494506 
              🤳 0951087077
              🤳 0929044037
እናመሰግናለን::
👉አድራሻ፦  መርካቶ ምንአለሽ ተራ ከጭድ ተራ ከፍ ብሎ

https://t.me/tsegaye2016Jbolt
👉ጨረታ

💫ጉዳዩ፡ የተለያዩ ማሽነሪ መሳሪያ ለመከራየት በክፍት ጨረታ ስለመጋበዝ፡፡

🚧የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኮንስትራክሽን ዘርፍ ለአዲማ አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፣ለአዲስ አበባ፣ ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ከ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘርፍ ከተሰማሩ አቅራቢ ዴርጅቶች በክፍት ጨረታ አወዳድሮ በመምረጥ መከራየት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ' የተጨማሪ እሴት ታክስአ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናችውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ' ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን::
2.የዕቃው ዝርዝር እና አገልግሎቶቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች (specification)ተያይዟል።
3. ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ መስከረም 12 ቀን 2018ዓ.ም. ከጥዋቱ 4፡30ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡

4. ጨረታው የቴክኒክ ስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል
5. መ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

📍አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ኮንስትራክሽን ዘርፍ (ኢ.ኢ.ኮ/ኮንስትራ) ሕንጻ 1 ሶስተኛ ፎቅ፡ የግዥ ቡድን ቢሮ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05

📞ስልክ ቁጥር +251-960-041-951/+251-911-153-389/+251-934-932-921 አዲስ አበባ

📜Fourm ለመሙላት👇
https://forms.office.com/r/NYhvYi9Pw8

@etconp
❤4👍3