Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
549 files
3.87K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ውስጥ ያደረገው IC Publisher ስር የሚታተመው AFRICAN BUSINESS መጽሔት "Are Ethiopia's ambitious mega projects grounded in realiy?" በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ በመጪዎቹ አስር አመታት ውስጥ ስለሚተገበሩ የ30 ቢሊዮን ዶላር ሜጋ ፕሮጀክቶች አነጋጋሪ ሃሳብ ይዞ ወጥቷል።

የህዳሴውን ግድብ ምርቃት ዋና አጀንዳ አድርጎ በቀጣዮቹ አመታት ስለሚተገበሩት ግዙፍ የኤርፖርት ከተማ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና ሌሎቹንም ሜጋ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ ፈታሽ መጣጥፍ ያቀረበው አፍሪካን ቢዝነስ በኢትዮጵያ በቀጣይ ስለሚካሄዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ኤክስፐርቶችን አነጋግሮ ዘርዘር ያለ ጽሑፍ አቅርቧል።


💫አሁን ኢትዮጵያ ስሟ ከግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ጋር መያያዙ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የፈጠረው በጎ አንድምታ ነው ሊባል ይችላል።

⏺በተጨማሪም ተጽዕኖ አድራጊ ፕሮጀክት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው።

⏺የአለም ሚዲያ ኢትዮጵያን ሁልጊዜ ከችግር ጋር አያይዞ የሚዘግብበት ታሪክ እየተዘጋ የመጣ ይመስላል።

🏷በአለም አቀፍ ጀረጃ ታዋቂ የሆነው IC publishers ከአፍሪካን ቢዝነስ ሌላ፣ New African እና African Banker የተባሉ መጽሔቶችን የሚያሳትምና ከ100 በላይ ሀገሮች ሰፊ የስርጭት ሽፋን ያለው ስመ ጥር ድርጅት ነው።


@etconp
❤5
#ADVERTISEMENT

🔧📐📐ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት 📐📐  
                 መማምረቻ ድርጅት⚙🔧🛠


🛠🛠🛠የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🛠🛠🛠

1 መገለጫችን የሆነው የሞደፊክ ስራዎች

2 እዲሁም ፕሌት ከ 1ሚሊም እስከ 30 ሚሊም እንቆርጣለን እበሳለን

3 በመቀጠል ጄቦልት 12ሚ እስከ 32ድረስ ጥርስ አውጥተን አጥፈን እናቀርባለን

4 የተለያዩ ቦልቶች በፈለጉት መጥን


📍 አድራሻ መገኛችን


ቁ1. በእጆት ባለ ስልክ ለናተ ቅርብ

ቁ2. በታታሪዎች መገኛ ኮርቻ ተራ

ቁ3. አየር ጤና ኪዳን ምህረት ጊቢ ማንኛውም ልሜራ እዛው በዘመናዊ ማሽን እቆርጣለን

ቁ4. ሴሚት ፍየል ቤት በቅርባ ባራቱም አቅጣጫ

ማሳሰብያ

ከጊዜው አንፃር የዋጋ ንረት ካሳሰቦት እኛጋ እሚገርም መፍትሄ አለ በማያስቡት መልክ ስራዎን ይሰራሉ ይደውሉ

ስልክ ቁጥር☎️
📞0939180889
📞0912492727
📞0944064945

መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ ፀግሽ   
ፕሌት እና ጄቦልት!
❤2
👉JOB VACANCY

🏷Senior Architect

#gift_real_estate

#Addis_Ababa


💫Master’s or Bachelor’s Degree in Architecture or in a related field of study with relevant work experience

🌟Duties and Responsibilities:

- Lead the design of residential, commercial, and mixed-use developments.
- Prepare and review conceptual, schematic, and detailed architectural drawings.
- Ensure designs are functional, aesthetically appealing, sustainable, and aligned with company brand standards.
- Conduct feasibility studies and site analysis to guide design decisions.

⏺Quanitity Required: 1

⏺Minimum Years Of Experience: #5_years

⚡️Deadline: October 2, 2025

📩How To Apply: Submit your application, updated CV and supporting credentials via email: giftrealestatehr2020@gmail.com

@etconp
❤2
👉JOB VACANCY

⭐️Quality Assurance Supervisor

#gift_real_estate

#Addis_Ababa

💫Bachelor’s Degree in Architecture, Civil Engineering, Construction Management or in a related field of study with relevant work experience

📜Duties and Responsibilities:

- Review architectural, structural, and MEP design documents to ensure compliance with company standards, local building codes, and project requirements.
- Coordinate with architects, engineers, and consultants to address design inconsistencies and quality issues before project execution.
- Develop and maintain QA/QC checklists and inspection procedures for ongoing projects.

⏺Quanitity Required: 1

⏺Minimum Years Of Experience: #5_years

⚡️Deadline: October 2, 2025

📩How To Apply: Submit your application, updated CV and supporting credentials via email: giftrealestatehr2020@gmail.com

@etconp
❤3👏2
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦች

💫3ኛ ዙር የ "Quantity Surveying" Full Course ኦንላይን ላይ በ አማርኛ ቋንቋ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች እና የ ኮንስትራክሽን ባለሞያዎች 3ኛ ዙር በተመጣጣኝ ዋጋ ለጥቂት ተማሪዎች ምዝገባ ጀምረናል
               
🔥 ይህ ስልጠና ምን ምን ትምህርቶችን ያካትታል?
💫Takeoff sheet
💫Bill of Quantity(BOQ)
💫Payment Certificate

🏷በዘርፉ ብዙ አመታትን ባስቆጠሩ መምህራን ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅቶቻችንን ጨርሰን እርሶን በመጠባበቅ ላይ እንገኛልን ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳይሉ ፈጥንው በመመዝገብ እራሶዎትን በትምህርት አዳብረው በቀላሉ ወደ ስራው እንዲቀላቀሉ አንርዳዎት እንላለን።

📍ታዲያ ምን ይጠብቃሉ ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ቀድመው ቦታ በመያዝ ይመዝገቡ                       

📩መመዝገብ የምትፈልጉ @Philemona7 ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ደውለው ያግኙን🙏

@etconp
👍4👌3❤2
👉JOB VACANCY

⭐️QUANTITY SURVEYER

⏺የሥራ ዓይነት: On-site - Permanent (Full-time)

⚡️ቀነ ገደብ: October 3, 2025

▶️ክፍት የስራ ቦታዎች: 1

⏺የትምህርት ደረጃ: Bachelors Degree

💫Education : Bsc in civil Engineering, COTM, Quantity surveying or related fields.

▶️EXPERIANCE : 2+ YEARS

🕹work location: addis abeba

📌How to apply: BY REFERING FOR WHAT JOB YOU APPLY

⏺interested applicants who meet the criteria can submit their cv, credientials and supporting documents via telegram @EMAROSHsales

@etconp
❤6🎉2
👉ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ ደመራ በዓል በሠላም አደረሳችሁ❤

💫በዓሉ የሠላም ፣ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የአንድነትና የእድገት እንዲሆን ፈጣሪ አምላክ ፍቃዱ ይሁን!"

@etconp
🥰7❤5
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤4
👉አሁናዊ ኪነህንጻ

🏷ናይል ሶርስ ህንጻ : በ ዘለቀ በላይ

📍አፍሪካ ጎዳና፣ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ

🚧ይህ ዘለቀ በላይ የነደፈው ህንጻ ከሀዋሳና ከአዳማ ውጪ ለመጀመሪያ ግዜ በአዲስ አበባ ውስጥ በትልቅ ደረጃ የንድፍ ጥበቡን ሰከን ነገር ግን ጠለቅ አድርጎ የገለጠበት ህንጻ ነው።

⏺በክፍተት ጨዋታው (playful openings)፣ በእይታ ሚዛን ተጽእኖው (scale manipulation)፣ በ ንጽጽር ቁጥጥሩ (proportion control)፣ በቁሳዊ ባህርይው (materiality)፣ ከሁሉ በላይ በሚወደው ሰያፍ የቁሳቁስ እና የጥላ መስመሮች ... የበለጸገ ንድፉን አቅርቦልናል።

⏺ዘለቀ እንደ ጎበዝ ደራሲ በንድፎቹ መደራደርን እንደማያውቅ የታወቀ ነገር ነው።

▶️ሆኖም ግን አጠቃላይ የንድፍ እይታው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳረፈ አንድ ትልቅ ዲጂታል ስክሪን በህንጻው በግራ መግቢያው አናት ላይ ተቀምጧል።

🎲የተሳካለት የእይታ ውበት ያላቸው ህንጻዎች ላይ የሚደረጉ ትላልቅ "እይታ ቀይር" ድርጊቶች እርምት ያስፈልጋቸዋል።

Via Ethiopian architecture and urbanism

@etconp
❤5👍2🔥2
👉የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ባለፈው መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዮት ጋር በግንባታ ደህንነት እና ጤና ላይ አብሮ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ  ሰነድ ተፈራርመዋል።

@etconp
❤8👍1
በቢሾፍቱ የአየር ማረፊያ ግንባታ የተነሱ ገበሬዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በያዝነው ወር ይጠናቀቃል"

በቢሾፍቱ የአየር ማረፊያ ግንባታ የተነሱ ገበሬዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በዚህ ወር ይጠናቀቃል ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለፁ።

አቶ መስፍን ጣሰው ከዘመን ኢኮኖሚ ጋር ባደረጉት ቆይታ አዲሱ ኤርፖርት ሊገነባ የሚችልበትን ቦታ በፈረንሳይ ኩባንያ እንዲጠና ተደርጓል።

ጥናቱም ቢሾፍቱ አጠገብ አቡሴራ የሚባል ቦታ ከሁሉም የተሻለ ቦታ እንደሆነ የጠቆመ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ደረጃ ማስተር ፕላንና ያዋጭነት ጥናትም ተሰርቶለታል ብለዋል።

አዋጭነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በኮቪድ ምክንያት ፕሮጀክቱ መቀዛቀዙን ገልጸው፤ ከዚያ ግን ጥናቶቹ ተከልሰው ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት።

እንደ አቶ መስፍን ገለፃ ግንባታው በሚከናወንበት አካባቢ ያሉ ገበሬዎች ሲነሱ ዳግም ማቋቋም እንደሚገባ በማመን ከቢሾፍቱ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ምን አይነት ቤት እና ሥራ ይገባቸዋል ተብሎ ግንባታ ተጀምሯል። ግንባታውም በያዝነው መስከረም ወር ይጠናቀቃል።

ሰዎቹም ወደ አዲሱ መኖሪያቸውና አዲሱ ሥራቸው የሚዘዋወሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የኤርፖርት ግንባታ የሚካሄድበትን ቦታ ከክልሉ መንግሥት መረከባቸውንና ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳነሱ ሕዳር መጨረሻ አካባቢ አዲሱ ኤርፖርት ግንባታው እንደሚጀመርም ጠቁመዋል።

@etconp
👍8❤7
👉CIRCULAR COLUMN OR SQUARE COLUMN ?

📌Which column is preferred for Housing ?

💫Let’s rise 6 criteria which column to choose

⭐️Stress distribution

⏺Circular column - Load spreads evenly in all radial directions so there is no weak points (no sharp corners)

⏺Rectangular Column - Stress is also uniform under pure axial load (theoretically) But sharp corners make it less efficient in practice (stress concentrations may develop under combined loading).

⭐️Strength & Efficiency

⏺Circular column - Stronger in axial compression for the same cross-sectional area and More economical in concrete use for resisting axial load and it has better resistance to buckling.

⭐️Bond with HCB block

⏺Circular columns protrude out from mansonary wall creating unaligned surface between the column and the wall.

@etconp
❤16👍7👏1
🫵ውድ ቤተሰቦቻችን ባለፈው እንዲሰራላቹ ምትፈልጉት ቲቶርያል ጠቁሙን ባልነው መሰረት ከ መቶ በላይ መልእክቶች Ms Project የሚል ስለበዛ ይህ ቲቶርያል ቪድዮ በ አማርኛ ሰርተንላቹዋል❤

💫የ Youtube ቻናላችንም Subscribe በማረግ አበርቱን🙏

📌እንሆ የመጀመርያ ክፍል Scheduling Using Ms Project ክፍል 1👇

https://youtu.be/MfMqqUPXxNI?si=vqU6CgVVs_T1V2At

@etconp
❤12👏4🥰1🙏1
Microsoft Project Professional 2016 x86x64 Full.rar
746.4 MB
ከላይ ላለው የ Scheduling Ms Tutorial የሚሆን Ms Software Set Up እና Sample BOQ እዚህ ኣለላቹ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤13👍11
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤5👍1
👉How to select suitable type of foundations?

🚧1. ADEQUATE DEPTH

*⃣The foundation must have an adequate depth to prevent frost damage. For such foundations as bridge piers, the depth of the foundation must be sufficient to prevent undermining by scour.

🚧2. BEARING CAPACITY FAILURE

*⃣The foundation must be safe against a bearing capacity failure.

🚧3. SETTLEMENT

*⃣The foundation must not settle to such an extent that it damages the structure.

🚧4. QUALITY

*⃣The foundation must be of adequate quality so that it is not subjected to deterioration, such as fromsulfate attack.

🚧5. ADEQUATE STRENGTH

*⃣The foundation must be designed with sufficient strength that it does not fracture or break apart under the applied superstructure loads.

🌟The foundation must also be properly constructed in conformance with the design specifications.

🚧6. ADVERSE SOIL CHANGES

*⃣The foundation must be able to resist long-term adverse soil changes.

🌟An example is expansive soil, which could expand or shrink causing movement of the foundation and damage to the structure.

🚧7. SEISMIC FORCES

*⃣The foundation must be able to support the structure during an earthquake without excessive settlement or lateral movement.

@etconp
👍9❤2
👉የኮንስትራክሽን ዘርፉ ቀዳሚ ችግር ሙስና ነው ተባለ!

💫በኮንስትራክሽን ዘርፍ ካሉ ችግሮች መካከል ሙስና በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

🚧የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ/ር) ይህን ያስታወቁት፣ ‹‹የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ነባራዊ ሁኔታና ተግዳሮቶች›› በሚል መሪ ሐሳብ ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡

⏺የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በርካታ ገንዘብና ሀብት የሚፈስበት በመሆኑ በሰፊው ሙስና የሚፈጸምበት ነው ብለዋል፡፡

የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም እ.ኤ.አ. በ2019 ይፋ ባደረገው ሪፖርት፦ በአውሮፓ ሙስና ከሚፈጸምባቸው ዘርፎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ 46 በመቶ እንደሚይዝ፣ በኢትዮጵያ በጥናት የተደገፈ አይሁን እንጂ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለው ሙስና ‹‹ሰፊና ጥልቅ ነው፤›› ብለዋል፡፡


‹‹የሕግ ማዕቀፍ ችግር ሌላው በዘርፉ የሚስተዋል ተግዳሮት ነው፡፡ ሕጉ በራሱ ቢኖርም አስቻይ ከመሆን ይልቅ ከልካይ የሆነበት፣ እንዲሁም አስፈለጊና ጠቃሚ የሚባሉ የሕግ ማዕቀፎች የጎደሉበት ነው፤›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡

መስፍን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የክህሎት እጥረት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ሌላው ማነቆ ነው፡፡ ከ15 ዓመታት በፊት ዘርፉ የተማረ የሰው ኃይል እጥረት የነበረበት ቢሆንም፣ አሁን ግን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዘርፉ ተመርቀው የሚወጡ በርካቶች መሆናቸውን፣ ሆኖም አሁንም ድረስ የክህሎት ማነስና የሙያዊ ሥነ ምግባር ችግር በሰፊው ይስተዋላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ዘርፉ በተጨማሪ የአቅም ክፍተት ያለበት፣ የፈጠራ ችግር ጎልቶ የሚታይበትና ባህላዊ የኮንስትራክሽን አሠራር የሚከተል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡


‹‹እንደ አገር የተቋማት ግንባታ ስብራት አለብን፡፡ ረጅም ዕድሜ አስቆጥረው የሚገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ናቸው፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚመሠረቱ ተቋማትም ብዙ ሳይጓዙ የሚፈርሱ ናቸው፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ለዚህም ምክንያቱ በዘርፉ የሚመሠረቱ ተቋማት የጋራ ግብ የሌላቸውና የጋራ ጉዳያቸውን የሚያዩበት ዕይታ ትክክል ባለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

በሌሎች አገሮች የሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት ትርፍን መሠረት አድርገው የሚሠሩ ቢሆንም በአገር ጥቅም የማይደራደሩ መሆናቸውን፣ በእዚህ አገር ግን የአስተሳሰብ ችግር በሰፊው ስላለ የአገርን ጥቅም ከማስቀደም ይልቅ በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚደረግ ሙከራ ጥቂት በማይባሉ ተቋማት የሚስተዋል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹እነዚህና ሌሎች መሰል በዘርፉ ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ መንግሥት በቅርቡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ይፋ አድርጓል፤›› በማለት የጠቆሙት መስፍን (ዶ/ር)፣ ትራንስፎርሜሽኑ የ25 ዓመታት ዕድሜ ያለውና በየአምስት ዓመታት እየተሸነሸኑ የሚከናወኑ ሥራዎች የተካተቱበት እንደሆነ፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያለበትን ችግር በመፈተሽና በመለየት ዘርፉን የማሻገርና የላቀ አፈጻጸም እንዲኖረውም የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።


በተጨማሪም የተቆጣጣሪ ተቋማትን አቅምና ተደራሽነት በማጠናከር፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዲጂታላይዝ በማድረግና ሕጎችንና ደንቦችን በማሻሻል ኢንዱስትሪው የአገርን ፍላጎት ማሟላት የሚችሉና ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠርታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

‹‹የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከሲስተም ጋርተያይዞ በመጣ ችግር ለዘመናት ተጎጂ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዘርፉ ሕጎች ቢወጡም ለትውልድ ተሻጋሪ የሚሆኑ አልነበሩም፤›› ያሉት ደግሞ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ እሸቱ ተመስገን ናቸው፡፡

‹‹የሚወጡ ሕጎች ለመጣው ሥርዓት በሚበጅ መንገድ የሚቀረፁ እንጂ አገር ለመጥቀም የሚዘጋጁ ባለመሆናቸው ዘርፉ በበርካታ ችግሮች እንዲተበተብ ተደርጓል፤›› ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፣ በተጨማሪም ዘርፉ የጨረታ አወጣጥ፣ የበጀት አያያዝ፣ የጥራት ቁጥጥር፣ የፕሮጀክት ማኔጅመንትና የመሳሰሉት ሌሎች በርካታ ችግሮች ያሉበት ነው ብለዋል፡፡

‹‹በመሆኑም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት፣ ከምንደግፋቸውና ከምንቆጣጠራቸው ተቋማት ጋር በጥምረት በመሥራት ላይ እንገኛለን፤›› ሲሉም አስረድተዋል።


‹‹የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ነባራዊ ሁኔታና ተግዳሮቶች›› በሚል መሪ ሐሳብ በተዘጋጀው መድረክ፣ በዘርፉ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ግለሰቦች ሽልማትና ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል፡፡

@etconp
❤15