Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
538 files
3.86K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉የዓባይ ወንዝ ድልድዩች

@etconp 👇
❤5👍1
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Photo
👉የዓባይ ወንዝ ድልድዩች

ዓባይ(Abay) ማለት ታላቅ፤ ከወንዞች ሁሉ አብይ ማለት ነው ። ዓባይ የናይል ወንዝ ታላቁ ገባር ሲሆን መነሻውም ኢትዮጵያ ነው።

ďťż
💫ታላቁ ወንዝ 70 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱን ወንዞች የውሃ መጠን ይይዛል፡፡ የዓባይ ወንዝ 1450 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ ርዝመት አለው፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ርዝመት ውስጥ 800 ኪ.ሜ ያህሉን በሀገር ውስጥ ይጓዛል፡፡

ከደቡባዊ የጣና ሀይቅ በመነሳት የሀገሪቱን ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ እየተጠማዘዘ ወደ ሱዳን የሚገባው ዓባይ 400 ኪ.ሜ ያህሉን በሸለቆ ውስጥ ስለሚያልፍ ወንዙን ለመሻገር እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ከቀሪው ግማሽ የሀገሪቱ ክፍል ጋር ያለድልድይ መገናኘት አዳጋች ነው፡፡


⏺ምንም እንኳን ወደ ጣና ሀይቅ የሚገቡ ገባር ወንዞች ቢኖሩም ግሽ ዓባይ ተብላ የምትታወቅ አንዲት አነስተኛ ምንጭ የዓባይ መነሻ እንደሆነች ይታመናል፡፡ የዓባይ ወንዝ “ጥቁር ዓባይ” ወይም “ብሉ ናይል” እየተባለ ቆይቶ የኢትዮጲያን ግዛት ተሻግሮ ወደ ሱዳን በመግባት ካርቱም ከተማ ላይ ነጭ ዓባይ ከሚባለው አጋሩ ጋር እንደተቀላቀለ ናይል በሚል መጠሪያ ወደ ሜዲትራንያን ባህር ይገባል፡፡


በኢትዮጵያ የድልድይ ግንባታ አጀማመር መነሻን መለስ ብለን ስንቃኝ በ16ኛው መ.ክ.ዘ ከዓባይ ፏፏቴ አልፈን እንደተጓዝን በምናገኘው ጠባብ ገደል ላይ አባይ ወንዝን የሚያቋርጥ የመጀመሪያው የድንጋይ ድልድይ ተገነባ፡፡


⏺ይህ በ1612 ዓ.ም በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባው የመጀመርያው የእንቁላል ድልድይ ይባላል።

🚧ድልድዩ ልክ እንደዛሬው ቴክኖሎጂ በቅጡ ባልዳበረበት ዘመን በኢትዮጵያ የድልድይ ግንባታ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ተሰጥቶት በታሪክ ድርሳናት ተመዝግቦ የምናገኘው እንቁላልን እንደ ሲሚንቶ ግብአትነት በመጠቀም የተሠራ አሁንም ድረስ የእንቁላል ድልድይ ተብሎ የሚጠራው ድልድይ ነው፡፡ የ400 ዓመት እድሜ ባለጸጋው የእንቁላል ድልድይ ባለ 8 አፍ ወይም በእንግሊዘኛው አጠራር arch bridge የሚባለው ነው፡፡ በኢትዮጵያ እስከ አሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዞችን የሚያሻግሩ ድልድዮች መገንባታቸው ይታወቃል፡፡

🏷ከነዚህም ውስጥ ታላቁን አባይ ወንዝ የሚሻገሩ ድልድዮች ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡ እንግዲህ አባይ በትውልድ ሀገሩ በኢትዮጵያ 800 ኪ.ሜ ያህል ሲጓዝ ከ17ኛው ክፍለዘመን እስከ ቅርብ ድረስ አባይን ለመሻገር 10 ያህል ድልድዮች በተለያዩ ቦታዎች እንደተገነቡለት ታሪክ ይናገራል።

🚧የአባይ ሸለቆው፦ የዓባይ ወንዝ ድልድይ

⏺የዓባይ ድልድይ ያለበት እና ከጎሃ ጽዮን እስከ ደጀን ድረስ ያለውን 40 ኪሎ ሜትር ርቀት የአስፋልት ሥራ 320 ሚሊዮን ብር ፈጅቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የዓባይ ድልድዩ ግን ረቡዕ ጳጉሜን 5 ቀን 2000 ዓ.ም ነበር የተመረቀው።

⏺ጣሊያኖች የገነቡት የድሮውን ድልድይ የተካው ይህ የዓባይ ድልድይ ብቻውን 128 ሚሊዮን ብር (የጠቅላላ ፕሮጀክቱን 40 ከመቶ) የፈጀ ሲሆን፣ ሙሉ ወጪውን የሸፈነው የጃፓን መንግሥት መሆኑ ታውቋል።

⏺መሐንዲሶቹና ድልድዩን የሠራውም ጃፓናውያን እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

⏺ድልድዩ 300 ሜትር ርዝመት፣ ዘጠኝ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፣ የመሸከም አቅሙ 300 ሜትሪክ ቶን እንደሆነ ታውቋል።

⏺የላይኛው የድልድዩ ክፍል በጠንካራ ኬብል ተወጥሮ የተሠራ ሲሆን፣ በየጊዜው ተገቢው ጥገና ከተደረገለት ለአንድ መቶ ዓመታት ያገለግላል ተብሎ ይገመታል። ይኸው አዲሱ ድልድይ ሁለት መኪኖችን ጎን ለጎን ያሳልፋል። አሮጌው የአባይ ድልድይ አንድ መኪና ብቻ የሚያሳልፍ መሆኑ ይታወቃል።

⏺ከዚህ ቀደም ከአዲስ አበባ ደጀን ድረስ በመኪና ለመጓዝ 10 ሰዓታት ይፈጅ የነበረ ሲሆን፣ የድልድዩና የመንገዱ ሥራው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 4 ሰዓታትን ሊቀንሰው ችሏል።

⭐️(የድልድዮ የግንባታ ሂደት በፎቶ ይህንን ይመስላል)

@etconp
❤6
👉አልሚዎች ወደ ግንባታ ለመግባት በእያንዳንዱ የመንገድ አይነት ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸው ጉዳዮች።

💫በከተማዋ ውስጥ ያሉ የመንገድ አይነቶች (Type/Hierarchy) ፣ ስፋት (Street Width) ፣ ግንባታ ከመንገድ የሚኖረው ርቀት (setback) እንዲሁም በተሻሻለው የመሬት አጠቃቀም ፕላን መሰረት በግል ይዞታቸው ላይ በራሳቸው የማልማት ፍላጎት ያላቸው ባለይዞታዎች ወደግንባታ ለመግባት በእያንዳንዱ የመንገድ አይነት ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸውን ከሴትባክ በኋላ ቀሪ ዝቅተኛ የቦታ ስፋት(Plot Area) እና የፊት ገፅታ (Plot Frontage) በተመለከተ የሚከተለው ተወስኗል፤

Via ፕላንና ልማት ቢሮ፤ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም

@etconp
❤3
👉የዓለማችን ረጅሙ ሆቴል ሲኤል ዱባይ ማሪና  በዱባይ ተከፍቷል

💫364 ሜትር ከፍታ ያለው ይህ ህንፃ የመስታወት ግድግዳዎች ባሉት ክፍሎች፣ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ ባሉ ሁለት መዋኛ ገንዳዎች፣ ስምንት ሬስቶራንቶች፣ በ360° እይታዎች ባሉ ላውንጆች፣ በ24-ሰዓት አገልግሎት በሚሰጥ የአካል ብቃት ማእከል  እና በ61ኛው ፎቅ ላይ ባለው ስፓ ከተማውን እና ባህሩን የሚያይ አስደናቂ እይታዎችን ያቀርባል።

@etconp
❤11👍4
👉አልሚዎች ወደግንባታ ለመግባት በእያንዳንዱ የመንገድ አይነት ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸው ጉዳዮች እነሆ!

⭐️በከተማዋ ውስጥ ያሉ የመንገድ አይነቶች (Type/Hierarchy) ፣ ስፋት (Street Width) ፣ ግንባታ ከመንገድ የሚኖረው ርቀት (setback) እንዲሁም በተሻሻለው የመሬት አጠቃቀም ፕላን መሰረት በግል ይዞታቸው ላይ በራሳቸው የማልማት ፍላጎት ያላቸው ባለይዞታዎች ወደግንባታ ለመግባት በእያንዳንዱ የመንገድ አይነት ላይ ሊያሟሉ የሚገባቸውን ከሴትባክ በኃላ ቀሪ ዝቅተኛ የቦታ ስፋት(Plat Area) እና የፊት ገፅታ (Plot Frontage) በተመለከተ የሚከተለውን ተወስኗል፤

📜መልዕክቶች፡-  ለከተማችን ከፍታ የፕላን ህግን የተከተለ ህንፃ ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው!

⏺ደረጃቸውን የጠበቁ ግንባታዎች ለውብ የከተማ ገፅታ!
⏺ህግ አክባሪነት የስልጡን ከተሜነት ምልክት ነው!
⏺የሴት ባክ ህግ ለዘላቂና የተረጋጋ የከተማ ዕድገት መሰረት ነው!

❇️ከተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታዎች ከመንገድ የሚኖራቸውን ርቀት  እና ተያያዝ የግንባታ ፈቃድ መመሪያዎች ከተላላፈ ውሳኔ የተወሰደ

Via ፕላንና ልማት ቢሮ

@etconp
❤9
👉ከተሞች ምቹ እና ለኑሮ ተስማም እንዲሆኑ በመሠራቱ ከፍተኛ መነቃቃት ተፈጥሯል ፡ ክብርት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ

💫ከተሞች ምቹ እና ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ በመሠራቱ  በከተሞች የልማት ሾል ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን   የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሎ ጫልቱ ሳኒ ገለፁ።

🚧ሚኒስትሯ ይህን የተናገሩት ‘የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት’ በሚል መሪ ሀሳብ በአፋር ክልል ሠመራ-ሎጊያ ከተማ እየተካሄደ ያለውን 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ሁለተኛ ቀን ውሎ አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

⏺ክብርት ሚኒስትር እንዳሉት  ፎረሙ እንደሀገር  በከፍተኛ ማንሰራራት ዘመን  ላይ ባለንበት  ወቅት መከበሩ ለየት ያለ ትርጉም አለው።

⏺መንግሥት ከተሞችን አረንጓዴ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ያነሱ ሲሆን፣ ይህ ጥረት በከተሞች ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሮአል ብለዋል።

⏺የዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያጎለብቱ እና ተግዳሮቶችን የሚያቃልሉ ገንቢ የፓናል ውይይቶችም እየተካሄዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

🏷ሚኒስትሯ በመግለጫቸው፣ ከዚህ ቀደም የድህነት ማሳያ የነበሩ ከተሞች በመንግሥት በተሰጠው ልዩ ትኩረት የብልጽግና ማሳያ እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

⏺በተለይም በአዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ለዘርፉ በርካታ ትሩፋቶችን ማስገኘቱን ጠቁመዋል።

⏺የኮሪደር ልማት የኢንዱስትሪዎች መነቃቃትን፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል መፍጠርን ማስቻሉን እንዲሁም የሥራ ባህልን በጉልህ የቀየረ መሆኑን ተናግረዋል።

⏺ይህ ልማት የከተሞችን እንቅስቃሴ እና ገቢ በማሳደግ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን ማድረጉንም አብራርተዋል።

@etconp
❤6👍2
#ADVERTISEMENT

👉ለግንባታዎ ውበት እኛን ስለ ምናስፈልግዎ ከግንባታ በኋላ ወደ እኛ ይደውሉ።

💫AR Building Finishing & Water Proofing Works ለህንፃዎች ውበት ፈጣሪዎች ነን

🚧በልዩ ጥራት የፊኒሽንግ ስራውን አጠናቀን ቤትዎ ውበት አጎናፅፈን እናስረክብዎታለን።

🌟ከመኖሪያ ቤት እስከ ትልልቅ ህንፃዎች አሻራችንን አሳርፈናል።
▶️Contextra
▶️Fine quartez
▶️ Water Proofing Chemicals
▶️ Membranes በጥራት እንሰራለን።

🎲በተጨማሪ የ Sales ስራዎች እንሰራለን

📍አድራሻ:—ኡራኤል ሀይላለም ህንፃ
            ስልክ  0977 67 67 90
                      0912 23 04 71

💫AR Building Finishing & Water Proofing Works

📌ቴሌግራም👇

https://t.me/antearb
https://t.me/antearb
https://t.me/antearb
❤4
👉የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ጽሕፈት ቤቱን ወደ ቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንፃ አዘዋወረ‼️

💫ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አዲሱን ዋና መስሪያ ቤት ጎብኝተው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል፦

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ጽሕፈት ቤቱን ቀድሞ ከነበረበት በመለወጥ መሃል ከተማ ወደ ቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሕንፃ አዛውሯል።

በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አስደናቂ የግንባታ ለውጥ እና ዘመናዊ የመሥሪያ ሥፍራ ጥበብን በማሳየት ለሠራተኞቹ እጅግ ምቹ የሆነ ስፍራንም መፍጠር ችሏል።

ተቋሙ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሕይወታችንን በፍጥነት በመቅረጽ ውስጥ ያለውን ስፍራ በሚያንፀባርቅ እና ሀገራችንም በዚህ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር በንቁነት መሳተፏን በሚያረጋግጥ መንገድ ከፍታ ላይ ደርሷል።

ኢንስቲቲዩቱ በጤና፣ በግብርና፣ በአገልግሎት ዘርፍ እያደረገ ያለው የመሪነት አስተዋፅኦውን እየተወጣ ሲሆን በክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ትላልቅ የመረጃ ቋቶች፣ የመረጃ ፍለጋ፣ ሮቦቲክስ እና ኢመርሲቭ ቴክኖሎጂዎች አቅሙን በማጎልበት ላይ ይገኛል።

በቅርቡ የተጀመረው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርት አፕ መዐከል ደግሞ ይኽንን ከባቢ የበለጠ ያጠናክረዋል።

ዜጎች ሀሳብ ብቻ ይዘው በመምጣት ፕሮቶታይፕ ለመፍጠር፣ ለማባዛት ብሎም ከግሉ ዘርፍ ኢንቬስተሮች ጋር እንዲገናኙ እድል ያመቻቻል። እስከ አሁን 200 ሀሳብ ፈጣሪዎች በዚህ እድል ተጠቅመዋል።


@etconp
❤6🤩2👍1
👉በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ

🚧በመዲናዋ የመጀመሪያ የሆነውና ከፒያሳ እስከ ጀሞ-3 ኮንዶሚኒየም የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ፈጣን መንገድ ኮሪደር ግንባታ በታህሳስ ወር ይጀመራል።

🏷ፕርጀክቱ 15.64 ኪሎ ሜትር ሽፋን፣ 20 ዘመናዊ ጣቢያዎችን እና 12 ተጨማሪ አገልግሎቶችን ያካትታል።

⏺ግንባታው በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@etconp
❤10