Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.61K photos
56 videos
538 files
3.84K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለመሶብ ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት
414 ሠራተኞችን በዜሮ ዓመት ልምድ መቅጠር ይፈልጋል

ኤክሲኪዩቲቭ ሴክሬታሪ    ብዛት    9
የመልእክት ሠራተኛ         ብዛት    9
ሹፌር 1                     ብዛት    9
የአገልግሎት ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ብዛት     18
የቅሬታ አፈታት ክትትል ባለሙያ     ብዛት    9
የአይቲ ሰፖርት ኦፊሰር      ብዛት    18
ሃርድዌር ኢንጂነር 1         ብዛት    9
ኔትወርክ አስተዳዳሪ 1       ብዛት    9
ሶፍትዌር አስተዳዳሪ 1       ብዛት    9
የተገልጋይ መስተንግዶ ሠራተኛ 1 (ሪሴፕሽን)    ብዛት    36
ዩኒቨርሳል አገልግሎት ባለሙያ 1      ብዛት    54
የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያ 1      ብዛት    36
የገቢ አገልግሎቶች ደንበኞች መስተንግዶ ባለሙያ 1      ብዛት    36
የሥራ ፈላጊ ምክር፣ግንዛቤ፣ምዝገባ እና ማደራጃ ባለሙያ 1         ብዛት    9
የኤጀንሲ ፍቃድ እና የሙያ መልመጃ ውል ባለሙያ 1    ብዛት    9
የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ 1      ብዛት    27
መብት መዝጋቢ እና የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ 1    ብዛት    27
የሊዝ እና የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ 1      ብዛት    18
የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ 1      ብዛት    18
የትራፊክ ማኔጅመንት ደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ 1    ብዛት    9
የቤት አስተዳደር አገልግሎት ባለሙያ 1         ብዛት    18
የጋራ መኖሪያ ቤት እና የንግድ ቤት ማስተላለፍ አገልግሎት ባለሙያ 1        ብዛት    18

@etconp
❤14👍4
👉የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በ2018 ኣ.ም በሁለተኛው ዙር የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

@etconp
❤3
👉ከተፈቀደላቸው የግንባታ ፈቃድ ውጪ የሕንፃ አዋጅ፣ ደንብና መመርያ በመጣስ የሕንፃቸውን የመኪና ፖርኪንግ ቦታዎች ለሌላ አገልግሎት ባዋሉ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

🚧ከተፈቀደላቸው የግንባታ ፈቃድ ውጪ  የሕንፃ አዋጅ፣ ደንብና መመርያ በመጣስ የሕንፃቸውን የመኪና ማቆሚያ ወይም ፖርኪንግ ቦታዎች ለሌላ አገልግሎት ባዋሉ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ባለሥልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

በባለሥልጣን መ/ቤቱ የሕንፃ መጠቀሚያ ፈቃድና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢ/ር ጌታሁን አበራ እንዳስታወቁት፤ በማዕከልና በክፍለ ከተማ መዋቅሮቻችን ጋር በመቀናጀት ባለፋት 6 ወራት ጊዜ ውስጥ በከተማዋ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙት ሕንፃዎች መካከል በ2420 ሕንፃዎች ላይ በተደረገ መደበኛና ድንገተኛ የሕንፃ መጠቀሚያ ኢንስፔክሽን ሥራዎች 187 የሚሆኑት የሕንፃ መጠቀሚያ ፈቃድ ሳያወጡና ሳያሳድሱ አገልግሎት ሲሰጡ እንዲሁም የአገልግሎት ለውጥ በማድረግ የመኪና ማቆሚያ ወይም ፓርኪንግ ቦታዎችን በከፊልና ሙሉ ለሙሉ ለተለያዩ አገልግሎት ሲያውሉ ተገኝተዋል፡፡

በመሆኑም ባለሥልጣን መ/ቤቱ በሕንፃ አዋጅ፣ደንብና መመርያ መሠረት አጣርቶ በመለየት በአስቸኳይ እንዲያስተካክሉ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ጊዜ ገደብ በመስጠት 163 የሚሆኑት እንዲያስተካክሉና ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን፤ ቀሪ 24 ሕንፃዎች ውስጥ ማስጠንቀቂያውን ችላ ብለው ማስተካከያ ባለማድረጋቸውና የማስተካከያ ስራ ለመጀመር ፍቃደኛ ባልሆኑት ላይ በቅንጅት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል፡፡

ይህም እንደየ ጥፋታቸው ዓይነትና ሁኔታ በማየት ከማሸግ ጀምሮ የአገልግሎት ማሻሻያ ተመን ክፍያ ላይ በተቀመጠው የቅጣት እርከን መሠረት ከዘጠኝ ሚሊየን አንድ መቶ ሃምሳ ሺሕ ብር በላይ እንዲቀጡ ተደርጓል ሲሉ  የሕንፃ መጠቀሚያ ፈቃድና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኢ/ር ጌታሁን አስታውቀው፡፡

በቀጣይም ይህ ዓይነቱ እርምጃ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጾ የሕንፃ ባለቤቶችም ይህን አውቀው ዳግም ስሕተት ውስጥ እንዳይገቡና ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ባለሥልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል፡፡

@etconp
❤7
👉ዕለታዊ የኮንስትራክሽን እና መሠረተ ልማት አጫጭር ዜናዎች

1. ☀️ á‹¨á‹“áˆˆáˆ›á‰˝áŠ• ግዙፉ የፀሐይ ኃይል ማከማቻ ግንባታ መጠናቀቅ

በታዳሽ ኃይል ዘርፍ፣ በዩናይትድ ስቴትስ (ካሊፎርኒያ) የዓለማችን ትልቁ ተብሎ የሚታሰበው የባትሪ ኃይል ማከማቻ ፕሮጀክት ወደ ሼል መግባቱ ተሰምቷል። ፕሮጀክቱ ከ 800 ሜጋ ዋት á‰ áˆ‹á‹­ ኃይል የማከማቸት አቅም ያለው ሲሆን፣ ይህም ለታዳሽ ኃይል መሠረተ ልማት ትልቅ ምዕራፍ ተብሏል።

2. 🏗️ á‹¨áˆŽá‰Śá‰˛áŠ­ "Exoskeletons" በግንባታ ሳይት ላይ

በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ትልልቅ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው Exoskeleton á‹¨á‰°á‰Łáˆ‰ ሜካኒካል ልብሶችን ማቅረብ ጀምረዋል። እነዚህ ሮቦቲክ ልብሶች ሠራተኞች ከባድ ዕቃዎችን ያለ ድካም እንዲያነሱና በሥራ ላይ የሚደርስን አደጋ (Back injuries) ለመቀነስ የሚረዱ ዘመናዊ መሣሪያዎች ናቸው።

3. 🪵 "Mass Timber"፦ ከእንጨት የሚሰሩ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች

ከአረብ ብረት እና ከሲሚንቶ ይልቅ ጠንካራ በሆኑና በልዩ ሁኔታ በተዘጋጁ እንጨቶች (Mass Timber) የሚገነቡ ረዣዥም ሕንጻዎች አዝማሚያ እየጨመረ ነው። በቅርቡ በሲንጋፖር እና በአውሮፓ የተመረቁት እነዚህ ሕንጻዎች የካርቦን ልቀትን በከፍተኛ መጠን የሚቀንሱ በመሆናቸው እንደ "አረንጓዴ ኮንስትራክሽን" ተመራጭ ሆነዋል።

4 🌊 á‰°áŠ•áˆłá‹áŠ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች (Floating Solar Farms)

በውኃ አካላት (እንደ ግድቦች እና ሐይቆች) ላይ የሚንሳፈፉ የፀሐይ ኃይል ፓነሎች ግንባታ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ መሬት እንዳይባክን ከማድረጉም በላይ፣ ውኃው ፓነሎቹን ቀዝቃዛ ስለሚያደርጋቸው የኃይል ማመንጨት አቅማቸው ከተለመደው በ 15% እንደሚጨምር አዳዲስ ጥናቶች አረጋግጠዋል።

5. ⚡ "ስማርት ግሪድ" (Smart Grid) እና የታዳሽ ኃይል ውህደት

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማትን ዘመናዊ ለማድረግ የSmart Grid á‰´áŠ­áŠ–áˆŽáŒ‚ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ የፀሐይ እና የንፋስ ኃይልን ከባህላዊው የኃይል መሾመር ጋር በቀላሉ በማገናኘት፣ የኃይል ብክነትን በዲጂታል መንገድ ይቆጣጠራል። ይህም ለታዳሽ ኃይል መስፋፋት ዋነኛው ኢንጂን ሆኗል።

6. 🛣️ á‹¨á•áˆ‹áˆľá‰˛áŠ­ መንገዶች (Plastic Roads) ቴክኖሎጂ

ለአካባቢ ጥበቃ እና ለዘላቂ መሠረተ ልማት ሲባል፣ እንደገና ጥቅም ላይ የዋሉ ፕላስቲኮችን (Recycled Plastic) አስፋልት ውስጥ በመቀላቀል መንገድ የመሥራት ቴክኖሎጂ ትኩረት አግኝቷል። እነዚህ መንገዶች ከተለመደው አስፋልት የበለጠ ጥንካሬ ያላቸውና ለከፍተኛ ሙቀት የማይበገሩ በመሆናቸው ለታዳጊ ሀገራት ተመራጭ እየሆኑ ነው።


Via Infracon Media

@etconp
❤15👍3
👉ቻይና በአቡጃ ናይጄሪያ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት (ECOWAS) ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ አጠናቃለች።

💫ቻይና የዚህን ፕሮጀክት ግንባታ ያከናወነችው ያለምንም ክፍያ በዕርዳታ መልክ ነው። ለግንባታው ወደ 32 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ በየካቲት ወር 2026 ዓ.ም. ርክክብ ይደረጋል።

🚧ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ቤጂንግ በአፍሪካ ውስጥ 200 ለሚደርሱ የመንግሥት ሕንፃዎች ግንባታ ወይም እድሳት የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች።

ለዚህም እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱት፦ እ.ኤ.አ በ2012 በ200 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የአፍሪካ ህብረት (AU) ህንፃ፣ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ በ80 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና መስሪያ ቤት ናቸው።

በተጨማሪም በ200 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የዚምባብዌ የፓርላማ ህንፃ እና በ20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የጋና የውጭ ጉዳይ እና ቀጣናዊ ውህደት ሚኒስቴር ህንፃ ይጠቀሳሉ።


@etconp
❤6👍1
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤

በዓሉ የሰላም የፍቅር ያድርግልን🙏

@etconp
❤8👍4
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤4🔥1🥰1
👉የሬዲ ሚክስ ኮንክሪት አለም አቀፍ አዝማሚያዎች (Global Trends)

💫የሬዲ ሚክስ ኮንክሪት (Ready-Mix Concrete - RMC) ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ያለ ዘርፍ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን አዝማሚያ እና በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የሬዲ ሚክስ ኮንክሪት ገበያ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ሲሆን፣ ዋና ዋና አዝማሚያዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦

• ዘላቂነትና "አረንጓዴ" ኮንክሪት (Sustainability)፦ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ሲባል የሲሚንቶን መጠን የሚቀንሱ ግን ጥንካሬያቸው የማይቀንስ ግብዓቶችን (ለምሳሌ Fly Ash, Slag) መጠቀም ተለምዷል።

• ዲጂታላይዜሽን፦ በኮምፒውተር የታገዘ ምርት (Automation) እና የጂፒኤስ (GPS) ክትትልን በመጠቀም ኮንክሪቱ ሳይበላሽና ሳይደርቅ በወቅቱ ለደንበኛ ማድረስ፤

• ከፍተኛ ጥንካሬ ያላቸው ኮንክሪቶች፦ እጅግ ረጅም ህንፃዎችን ለመገንባት የሚያስችሉ እጅግ ከፍተኛ ጥንካሬ (High-Performance Concrete) ያላቸው ምርቶች ላይ ትኩረት ተደርጓል።

• የከተሞች መስፋፋት (Urbanization)፦ በታዳጊ ሀገራት የከተሞች መስፋፋት ለዘርፉ እድገት ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

♦️በኢትዮጵያ ያለው መልካም አጋጣሚ (Opportunities)

በኢትዮጵያ ከ50 በላይ ኩባንያዎች ወደዚህ ዘርፍ መግባታቸው የኢንዱስትሪውን ተፈላጊነት ያሳያል። ዋና ዋና አጋጣሚዎች፦

• የጊዜና የጥራት ቁጥጥር፦ በግንባታ ቦታ ላይ ኮንክሪት ከማቡካት ይልቅ በፋብሪካ ተዘጋጅቶ መምጣቱ የግንባታ ፍጥነትን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል። ጥራቱም በላቦራቶሪ ስለሚፈተሽ አስተማማኝ ነው።

• የቦታ ጥበት መፍትሄ፦ በተለይ በአዲስ አበባና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች የግንባታ ቦታዎች ጠባብ በመሆናቸው፣ ግብዓቶችን ለማከማቸትና ለማቡካት ቦታ ስለማይኖር የሬዲ ሚክስ አቅርቦት ብቸኛ መፍትሄ እየሆነ ነው።

• የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፦ የመንገድ፣ የድልድይ እና የባቡር መስመሮች ግንባታ ለዘርፉ ሰፊ ገበያ ፈጥረዋል።

• ብክነትን መቀነስ፦ በግንባታ ቦታ ላይ የሚባክነውን አሸዋ፣ ጠጠርና ሲሚንቶ በማስቀረት ወጪን ይቀንሳል።

♦️ተግዳሮቶች (Challenges)
ዘርፉ እያደገ ቢሆንም፣ ኩባንያዎቹንና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን የሚፈታተኑ ነጥቦች አሉ፦

• የትራፊክ መጨናነቅ፦ ኮንክሪት ተቦክቶ በ2 ሰዓት ውስጥ መፍሰስ አለበት። በአዲስ አበባ ያለው የትራፊክ መጨናነቅ ኮንክሪቱ መኪና ውስጥ እንዳይደርቅ ትልቅ ስጋት ይፈጥራል።

• የግብዓት አቅርቦት መዋዠቅ፦ የሲሚንቶ እጥረትና የዋጋ መናር፣ እንዲሁም ጥራት ያለው አሸዋና ጠጠር በቅርብ ርቀት አለማግኘት የምርት ወጪን ይሰቅላል።

• የውጭ ምንዛሬ እጥረት፦ ለሬዲ ሚክስ የሚያስፈልጉ ዘመናዊ መኪናዎች (Agitators)፣ ፓምፖችና መለዋወጫዎች ከውጭ የሚገቡ በመሆናቸው በምንዛሬ እጥረት ምክንያት አቅርቦቱ ይስተጓጎላል።

• አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፦ የምርት ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ በመሆኑ፣ የኃይል መቋረጥ የምርት ጥራትና ፍጥነት ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል።

• የባለሙያ እጥረት፦ ዘመናዊ የኮንክሪት ቴክኖሎጂን (Chemical Admixtures) በሚገባ የተረዱ ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ።

♦️የወደፊት እጣ ፈንታ
በኢትዮጵያ የከተማ እድገትና የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እስከቀጠሉ ድረስ፣ የሬዲ ሚክስ ኮንክሪት ኢንዱስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ የግዴታ ምርጫ እየሆነ ይሄዳል። ኩባንያዎች በትራንስፖርት ዘርፍ (ለምሳሌ በምሽት በረራ ወይም ቅድሚያ በማግኘት) እና በግብዓት አቅርቦት ላይ ከመንግሥት ጋር ተቀራርበው መሥራት ከቻሉ፣ ዘርፉ የሀገሪቱን የግንባታ ጥራት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል።

ďťż
Via Infrancon

@etconp
❤13🔥1
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን አዲስ የ YouTube ቻናል ከፍተን ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ቪድዮዎች እየለቀቅን ነው ከታች ባለው ሊንክ እየገባቹ Subscribe በማረግ አግዙን🙏

💫Here Is Our YouTube Channel👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
👏3🔥1
JCB
በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ኢንዱስትሪ የገዘፈ የልህቀት ምልክት


🚧በዘመናዊው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደ JCB (Joseph Cyril Bamford) ስም ዝነኛ የሆነ ኩባንያ ማግኘት አዳጋች ነው። እ.ኤ.አ. በ1945 በብሪታንያ የተመሰረተው ይህ ኩባንያ፣ ዛሬ በዓለም ዙሪያ በቢጫ ቀለሙና በጥንካሬው የሚታወቅ ዓለም አቀፍ ምልክት ሆኗል። JCB ከቀላል የግንባታ ስራዎች እስከ ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ድረስ የሚሳተፉ ማሽኖችን በማምረት የዘርፉ ግንባር ቀደም ተዋናይ ነው።

🏷የJCB ማሽኖች ልዩ ባህሪና ጥቅሞች 

JCBን ከሌሎች ተወዳዳሪዎቹ (እንደ Caterpillar ወይም Komatsu) ለየት የሚያደርገው ዋናው ነጥብ የፈጠራ ውጤት የሆነው Backhoe Loader áˆ›áˆ˝áŠ• ነው። ይህ ማሽን በአንድ ጊዜ የመቆፈርና የመጫን አቅም ያለው በመሆኑ፣ ለኮንስትራክሽን ድርጅቶች ወጪ ቆጣቢና ሁለገብ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል።


⭐️ከጥንካሬያቸው በተጨማሪ፣ የJCB ማሽኖች በነዳጅ ቆጣቢነታቸውና በቴክኖሎጂ ምጥቀታቸው ይታወቃሉ። የራሳቸው የሆነው የJCB DieselMax ሞተር ማሽኑ ሳይዝል ለረጅም ሰዓታት እንዲሰራ ያደርገዋል። እንዲሁም የሾፌሩ መቀመጫ (Cabin) የተሰሩበት ergonomics እና ሰፊ እይታ ኦፕሬተሩ ሳይዝል በደህንነት ስራውን እንዲያከናውን ያስችለዋል።

🎲ዓለም አቀፍ የገበያ ሁኔታ 

በዓለም አቀፍ ደረጃ JCB በሦስት ትልልቅ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ አምራቾች ውስጥ ይመደባል። በተለይም በሕንድና በአውሮፓ ገበያ ላይ ከፍተኛ የበላይነት አለው። ኩባንያው ዛሬ ላይ ወደ "አረንጓዴ ቴክኖሎጂ" በመሸጋገር የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ባክሆ ሎደር (Electric Backhoe) በማስተዋወቅ ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት እያሳየ ይገኛል። ይህ ተለዋዋጭነቱና ለገበያ ፍላጎት ፈጣን ምላሽ የመስጠት ብቃቱ በዓለም ዙሪያ ተመራጭነቱ እንዲቀጥል አድርጎታል።


🔰የJCB ሁኔታ በኢትዮጵያ እና የኢትዮ ኒፖን ሚና 

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ፣ የJCB ስም ከመንገድና ከህንፃ ግንባታ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው። ለዚህ ደግሞ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ብቸኛ ወኪሉ የሆነው áŠ˘á‰ľá‹Ž ኒፖን ቴክኒካል ካምፓኒ (Ethio Nippon Technical Co.) áŠá‹á˘

ኢትዮ ኒፖን ማሽኖቹን ከማስመጣት ባለፈ፣ ለሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ትልቅ እገዛ የሚያደርጉ አገልግሎቶችን ይሰጣል፦

• የመለዋወጫ አቅርቦት፦ á‹¨JCB ማሽኖች በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ከፍተኛ "Resale value" (ተመልሶ የመሸጥ ዋጋ) እንዲኖራቸው ያደረገው የመለዋወጫ ዕቃዎች በኢትዮ ኒፖን በኩል በቀላሉ መገኘታቸው ነው።

• ከሽያጭ በኋላ ያለው አገልግሎት፦ á‹¨áŒĽáŒˆáŠ“ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ማሽኖቹ ለረጅም ዘመን እንዲያገለግሉ ያደርጋል።

• ተስማሚነት፦ á‹¨áŠ˘á‰ľá‹ŽáŒľá‹Ť መልክዓ ምድር ወጣ ገባ በመሆኑ፣ እንደ JCB ያሉ ጠንካራ ማሽኖች ለሀገሪቱ የመሰረተ ልማት ግንባታ እጅግ ተመራጭ ሆነዋል።

በአጠቃላይ፣ JCB በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የቴክኖሎጂ የበላይነት ከኢትዮጵያ ተጨባጭ የሥራ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ረገድ ስኬታማ የሆነ ኩባንያ ነው። በኢትዮ ኒፖን በኩል የሚቀርቡት እነዚህ ማሽኖች፣ የሀገሪቱን የልማት ጉዞ በማፋጠን ረገድ የማይተካ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። የወደፊቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍም የቴክኖሎጂና የጥንካሬ ውጤት በሆኑት በእነዚህ ማሽኖች ላይ መደገፉን እንደሚቀጥል ጥርጥር የለውም።


Via Infranco Media

@etconp
❤8👍1🔥1
👉የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

💫በአብክመ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ

ANRSMETAL INDUSTRY AND MACHINE TECHNOLOGY DEVELOPMENT ENTERPRIS

⚡️ማሳሰቢያ፡-

* የቅጥር ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ

* የምዝገባ ቦታ  ቦታ ቀበሌ 17 በድሮው ግብርና ሜካናይዜሽን በመስከረም 16 ት/ቤት እና በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያው መካክል ካለው in መ/ቤት የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 25

* የፈተና መስጫ ቀን ወደፊት በማስታወቂያ ይገለጻል።

* ተወዳደሪዎች የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ይዛቸሁ በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ!

@etconp
❤5👍2🔥1
👉የኮንዶሚኒየም ቤት ቆጣቢዎች ዕጣ ፈንታ

ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች የ20/80 510 ሺሕ፣ የ40/60 ተመዝጋቢዎች 9ዐ ሺሕ በድምሩ 600 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ ለ370 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ቤት ተረክበዋል።

በኢትዮጵያ የነዋሪዎችን የቤት ተደራሽነት ለማሟላት ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ አዋጅ ቁጥር 370/1995 በጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤትነት መሠረት ተደንግጎ በተጀመረው የኮንዶሚኒየም ቤት ቁጠባ ፕሮግራም፣ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበው የቤት ቁጠባ እንደጀመሩ፣ ዛሬም ድረስ እየቆጠቡ እንዳሉና ዕጣ ደርሷቸው የቤት ባለቤት የሆኑ እንዳሉም ይታወቃል፡፡

በ1997 ዓ.ም. እና 2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት ለዓመታት መሥፈርቱን አሟልተው በመመዝገብ ሲቆጥቡ የነበሩ ቆጣቢዎች ቤት የማግኘታቸው ነገር የውኃ ሽታ እንደሆነባቸውም ሲገልጹ ይስተዋላል፡፡

በ1997 ዓ.ም. የ20/80 የኮንዶሚኒየም ባለ አንድ መኝታ ቤት ቁጠባ ተመዝጋቢ ሲሆኑ፣ ለ21 ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ እንደቆጠቡ፣ ነገር ግን አሁንም የቤት ዕጣ እንዳልደረሳቸው አንድ ተመዝጋቢ ነግረውናል፡፡

አክለውም ‹‹በቤት ኪራይ ለዓመታት ተንከራትቻለሁ፣ ቤት በማግኘት ተስፋ ያለመሰልቸት ብቆጥብም ከእኔ በኋላ የተመዘገቡ ሲደርሳቸው ታዝቤያለሁ፡፡ አሁንም ቢሆን ከየትም አምጥቼ በቆጠብኩት ገንዘብ መንግሥት ቤቴን እንዲያስረክበኝ ስል እጠይቃለሁ፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችን ተመዝጋቢ፣ የ2005 የ40/60 ኮንዶሚኒየም ቤት ቆጣቢ ስትሆን፣ ለ13 ዓመታት ያህል ቆጥባ ዕጣው እንዳልደረሳ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/150500/

@etconp
❤3👍2
👉የግንባታ ላይ ደህንነት

🚧የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትኩረት አንዱና ዋነኛው ትኩረት ማድረግ የሚገባው በሰው ልጆች ደህንነት ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

💫ግንባታዎች በሚገነቡበት በዋናነት ለሰውልጆች አገልግሎት ለመስጠት በመሆኑ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስራዎች የስራ ላይ ደህንነት ሥጋት የሌለባቸው እንዲሁም ለአገልግሎት በሚውሉበት ጊዜ ለአካባቢ የተመቹ እና ደህንነታቸው  የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

💫የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ የደህንነት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡

🏷ደህንነቱ የተረጋገጠ የኮንስትራክሽን ሾል እንዲኖር ቁጥጥር በማድረግ ሂደት ትኩረት እንደሚሰጥ ቢነገርም ደህንነት በቁጥጥር ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ሁሉም የግንባታው ዘርፍ አካላት በየራሳቸው ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ነጥብ  ነው፡፡

👷‍♀የግንባታ ሂደት ውስጥ የሰራተኞች ደህንነት እንዲጠበቅ በግንባታ ስራው ላይ የሚሰማሩት የመስክ ሰራተኞች በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ ሆኖ እንዲሰሩ የሚያስፈልጋቸውን የግል የአደጋ መከላከያዎችን  በማቅረብ ሰራተኞቹም የስራ ላይ ትጥቃቸውን በመጠቀም በስራ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡

⏺በህንጻ ግንባታ ሆነ በሌሎች ግንባታዎች ደህንነቱ የተጠበቀ በማድረግ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ ይቻላል፡፡

⏺የህንጻ ግንባታዎች ላይ በተለይም የግንባታ ስራ የእቃ መስቀያ፣ መወጣጫዎች እንዲሁም ወደ መንገድ እና ወደ አጎራባች ህንጻዎች፤ መኖሪያዎች፣መተላለፊያዎች የሚወርዱ የግንባታ ተረፈ ምርቶች የግንባታ ግብዓቶች በሰው እና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል አደጋ ያደርሳሉ፡፡

⏺ሆኖም በእነዚህ አደጋዎች የሚፈጥሩትን ኪሳራ የግንባታ ጊዜ ማስታወቂያዎች መከላከያዎች በማድረግ እንዲቀነሱ ማድረግ ይቻላል፡፡

🚧በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ ሙያተኞች ወደስራ ቦታቸው ሲገቡ አስፈላጊውን የደህንነት መጠበቂያ ባለማድረጋቸው የሚደርሱ የአካል እና የመንፈስ ስብራቶች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ የራስ (የአናት) መከላከያ ቆብ፣ ጓንት፣ አስፈላጊ የደህንነት ጫማዎች፣ የመለያ አልባሳት ወ.ዘ.ተ ለደህንነት ዓላማ የተዘጋጁ ቁሶች እንደመሆናቸው ቅድሚያ ለደህንነት በመስጠት መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በቀላል የሚቀረፉ እና የሚስተካከሉ ጉዳዮች በብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

⏺ግንባታ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ጥቅሞች ቢኖሩትም በግንባታ ወቅት የሚደርሱ ኪሳራዎች ደግሞ በግለሰብ በማህበረሰብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ ታሳቢ ቢያደርገውና ቅድሚያ ለደህንነት በማለት የመጀመሪያውን እርምጃ ለደህንነት ማድረግ ይኖርበታል፡፡

https://t.me/ETCONp

@etconp
                                   
❤8
ADVERTISMENT

ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

✅የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

🔅 ፕሌት any Size & thickness
🔅 ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

🔅 የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

♦️ ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

☎️ስልክ 0904040477 ወይም 0911016833 ደውለው ያግኙን
📱ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
❤3