Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.58K photos
56 videos
536 files
3.79K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
JOB VACANCY

1. Position: Project Coordinator 📋
2. Project Manager 🚀
Company: Assem PLC 🏢

Education: BSc in Civil, CoTM or related fields 🎓

Experience:
- 0 year for Project Coordinator
- Above -1 years for Project Manager ⏳

Additional Requirements:
- Communicate with team members, clients, and stakeholders 🗣️
- Organize meetings, documentation, and project files 📂
- Assist in budget tracking and resource allocation 💰
- Ensure projects are completed on time and within scope ✅
- Strong organizational and multitasking skills 🧠
- Excellent written and verbal communication skills ✍️
- Proficiency in Microsoft Office and project management tools 💻

Salary: As per company scale 💸

Work Location: Lideta, Addis Ababa 📍

Deadline: May 26, 2026 📅

How to Apply:
- Email: Asseminfo1@Gmail.com 📧
- Telegram: +251981546461 📱

@etconp
❤8👍2
👉በዓለማችን ላይ የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ብክለት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አዳዲስ አማራጮችን እንዲፈልግ እያስገደዱት ባሉበት በዚህ ዘመን፣ ተፈጥሮ ሌላ አስደናቂ የምሥራች ይዛ ብቅ ብላለች።

ዘላቂና አረንጓዴ የህንፃ ግንባታ ቁሳቁሶችን ለማምረት ሌት ተቀን የሚተጉ ተመራማሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት የካክተስ (የቁልቋል) ተረፈ ምርትን ወደ ዝቅተኛ ወጪ የሕንፃ ግንባታ ግብዓትነት መለወጥ የሚያስችል አዲስ የቴክኖሎጂ ብልሃት ማግኘታቸውን "Earth.com" ይፋ አድርጓል።

ይህንን አዲስ የተፈጥሮ ስጦታና የምህንድስና ውህደት በዚህ መልክ እንደሚከተለው እንቃኘዋለን፦

የቁልቋል ምስጢርና የአረንጓዴው ግንባታ አብዮት 🌵🏗️

ďťż
ቁልቋል በአብዛኛው በደረቅና ውኃ አልባ በሆኑ አካባቢዎች፣ ያለምንም እንክብካቤ በራሱ ተፈጥሯዊ ጥንካሬ የሚበቅል ተክል ነው።

ሳይንቲስቶች አሁን የደረሱበት ግኝት የሚያሳየው፣ ይህ ተክል ጥቅም ላይ ውሎ የሚጣለው ተረፈ ምርቱ (Cactus Waste) በውስጡ እጅግ ጠንካራና ተለጣጭ የሆኑ የተፈጥሮ ፋይበሮችንና ባዮ-ፖሊመሮችን የያዘ መሆኑን ነው።


ይህንን ተረፈ ምርት በልዩ አሰራር በማቀነባበር ከባህላዊ የግንባታ ቁሳቁሶች ጋር ሲቀላቅሉት፣ የሚመረቱትን ጡቦችና የድንጋይ መዋቅሮች ክብደት በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ፣ ነገር ግን ጥንካሬያቸውን እጅግ የሚያሳድግ ሆኖ ተገኝቷል።

ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ቁሳቁስ ሙቀትና ቅዝቃዜን በራሱ የመቆጣጠር (Thermal Insulation) ከፍተኛ ብቃት ስላለው፣ በውስጡ የሚገነቡ ቤቶች ሰው ሰራሽ ማቀዝቀዣ ሳይፈልጉ የተመጣጠነ የአየር ንብረት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ከተራ ወጪ ቅናሽ ባለፈ፣ ባህላዊው የሲሚንቶ ማኑፋክቸሪንግ በዓለም ላይ ለሚለቀቀው የካርቦን ጋዝ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ በመሆኑ፣ ይህንን የቁልቋል ተረፈ ምርት እንደ አማራጭ ማጠናከሪያ መጠቀም የኮንስትራክሽኑን ዘርፍ የካርቦን አሻራ ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ያወርደዋል።


የኢትዮጵያ ቁልቋልና ያልተነካው የወርቅ ማዕድን 🇪🇹✨

ታዲያ ይህ ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ ግኝት ወደ እኛ አገር ስንመጣ ፍጹም የተለየና የላቀ ትርጉም ይኖረዋል።

ኢትዮጵያ—በተለይም ሰሜናዊው፣ ምሥራቃዊውና ደቡባዊው የሀገራችን ክፍሎች—ይህ የካክተስ ወይም የቁልቋል ዝርያ (በተለይ በሀገር ውስጥ "በለስ" የምንለውና መሰል የቁልቋል ዓይነቶች) በሰፊውና በቶን የሚቆጠር በብዛት የሚገኝባት ምድር ናት።

እስካሁን ድረስ ቁልቋልን የምናውቀው ለጊዜያዊ ፍራፍሬነት፣ ለአጥር ጥበቃ ወይም በድርቅ ወቅት ለከብቶች መኖነት ብቻ ነበር።

ከጥቅም ውጭ ሆኖ የሚደርቀውና የሚጣለው ተረፈ ምርቱ ግን ሜዳ ላይ ዝም ብሎ የሚበሰብስ አልያም የሚቃጠል ነበር።

አሁን ግን ይህ የሳይንስ ብልሃት በሀገራችን በብዛት የሚገኘውን የቁልቋል ተረፈ ምርት ወደ ታላቅ የኢኮኖሚና የኮንስትራክሽን ዕድል መቀየር እንደምንችል ትልቅ በር ከፍቶልናል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከተሞች እየታየ ያለውን ከፍተኛ የቤት እጥረትና የቤት መሥሪያ ቁሳቁስ (የሲሚንቶና የጡብ) ዋጋ መናር ለመቅረፍ፣ እንዲህ ያሉ በቀላሉ ከሀገር ውስጥ ተፈጥሮ የሚገኙ የቁልቋል ተረፈ ምርቶችን ወደ ግንባታ ማገዶነት መቀየር የሀገር በቀል መፍትሔዎች ቁንጮ ነው።

ይህንን የቴክኖሎጂ ፍልስፍና የሀገር ውስጥ መሐንዲሶቻችንና የዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቻችን መሬት ላይ አውርደውት በተግባር ቢተረጎም፣ በገጠሪቱና በከተማዋ ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ርካሽ፣ ጠንካራና ከአየር ንብረት ጋር የሚስማሙ ውብ መኖሪያዎችን በጥቂት ወጪዎች መገንባት ይቻላል።

የነገው የኢትዮጵያ ኢንፍራስትራክቸር ውበቱና ጥንካሬው የሚቀዳው ከውጭ ከሚመጣ ውድ ዕቃ ሳይሆን፣ በገዛ ምድራችን ላይ በቀላሉ በቀለው ጥቅም አጥቶ ከሚጣለው የቁልቋል ተረፈ ምርት በስተጀርባ ያለውን የተፈጥሮ ምስጢር በፈጠራና በብልሃት መግለጥ ስንችል ብቻ ነው።

ፍለጋው በሲሚንቶ ማገዶዎች ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በመንገድ ዳር በበቀሉት አረንጓዴ ቁልቋሎች ውስጥም ጭምር ነው።


@etconp
❤13
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ሊጠናቀቁ ይገባል -- ቋሚ ኮሚቴው

በሕዝብ  ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ፣ በተመደበላቸው በጀት እና የጥራት ስታንዳርድ ሊጠናቀቁ እንደሚገባ አሳስቧል።

ቋሚ ኮሚቴው ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን በሚከታተላቸው የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ ከአካሄደ በኋላ ለተቋሙ አመራሮች ግብረ መልስ በሰጠበት ወቅት ነው።

ቋሚ ኮሚቴው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ፣ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች ተዘዋውሮ ከጎበኘ በኋለ እነዚህ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሁለንተናዊ ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፈሰር መሐመድ አብዶ áˆ˜áŠ•áŒáˆľá‰ľ ለኮንስትራክሽን ዘርፉ በሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አስታውሰው፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው በወቅቱ እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የበለጠ ክትትልና ቁጥጥሩን ሊያጠናክር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የህንጻ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ያለበቂ ምክንያት  በሚያዘገዩ እና በዘርፉ ተያያዥ ጥፋት የሚፈጽሙ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኳሊቲ ሰርቬይ እና የዲጂታይዘችን ሰራዎች ላይ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴው አባላት አሳስበዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባልና የኮንስትራክሽን ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ገነት ከተማ በበኩላቸው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ከለውጡ በፊት ከነበሩባቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተላቀው በተሻለ ደረጃ ለይ የሚገኙ ቢሆኑም፤ አሁንም ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ፣ በጀት እና ጥራት መጠናቀቅ እንዲችሉ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ.ር)  በበኩላቸው ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው ጊዜና የጥራት ስታንዳርድ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የተቋሙን ስራዎች የሚያቀላጥፋ ሲስተሞች በማልማት እና በሳይቨር ሴኩሪቲ ደህንነት ላይ በልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ተቋሙ በመሶብ አንድ ማእከል ከ84 በላይ የሚሆኑ  አገልገሎቶች በኦን ላይን መስጠት መቻሉ ፤ በዘርፉ የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት እገዛ ማድረጉን የተቋሙ áŠ áˆ˜áˆŤáˆŽá‰˝  አብራርተዋል።

ተቋሙ የተገልጋይ እርካታን በ2018 በጀት ዓመት  በ10 ወራት ወስጥ 97 በመቶ ማድረስ እንደቻለም ተገልጿል።

Via ፓርላማ

@etconp
❤7
የባንክ አካውንታችሁን ከ Fayda መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የእያንዳንዱን ባንክ link ማስታወስ አይጠበቅባችሁም።

ይህን link በመጠቀም የሁሉም ባንኮችን link ማግኘት ትችላላችሁ👇

https://id.et/connect

ጊዜና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ ለወላጅ ዘመዶቻችሁ share አድርጉላቸው።

@etconp
❤5👏3
ዘለቀ በላይ አሁን ደግሞ  ወደ መንፈሳዊ ሕንፃ ንድፍ (ecclesiastical design) ፊቱን አዙሯል።

ለፍልውሃ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ-ክርስቲያን የሰራው አዲሱ የሕንፃ ኮምፕሌክስ፣ ጭምት  ለሆነው የ1950ዎቹ  የቀደመ ታሪካዊ ቤተክርስትያን ሕንፃ ደማቅ እና ተጫዋች የሆነ ዳራ (background) ሰጥቶታል።

​ዘለቀ ሊደፈር እስከሚችለው ድረስ  የሚሄድ  ደፋር ባለሙያ ነው። እንደ ማዕቀፍ እና እንደ ሊፍት ሆኖ የሚያገለግለውን  ድፍረት የተሞላበት ቀጥተኛ (vertical) አካል የሕንፃውን አጠቃላይ ገጽታ አንደኛው  መለያ  አድርጎታል።

​በሕንፃዎች ላይ የሚሰሩ የአየር ላይ ድልድዮችን (sky bridges) የመፈተሽ ሙከራውን ደግሞ ጥቂት ወደፊት ፈቀቅ አድርጎታል። ስቴርስ ህንጻ ላይ ያለውን የመጀመርያውን ኪውቦክታ (Cubocta) የሰማይ ድልድዩን አንረሳውም። ፍጹም አስገራሚ የሆነው ባለ መስታወት ማገናኛ ድልድይ የዚህ የጥበብ ሾል ሌላው  መለያ (signature) ነው። ለመሆኑ ልክ  እንዳለመው ይህ መስታወት ድልድይ በተግባር ይገነባ ይሆን? ይሄንን ግዜ የሚመልሰው ይሆናል።  ግን ግን ቤተክርስትያኑ ወጪ አውጥቶ ምንም ብረት እና የሚጋርድ ነገር ሳይኖር በመስታወት ብቻ ቢገነባው ሳያስደስት አይቀርም።

​እንዲህ ሁሌ የድፍረት አድማሱን የሚያሰፋ  አስተዋይ ባለ ተሰጥኦ እና ምናበ-ሰፊ አርክቴክት በኢትዮጵያ በመኖሩ ኩራት ሊሰማን ይገባል።

ግን ማህበረሰባችንስ ድምጻዊውን፣ ሙዚቀኛውን ፣ጸሀፊውን፣ ተውኔተኛውን፣ ሯጩን፣ ሰአሊውን እንዲሁም ቀራጺውን ሲያደንቅ እንደዚህ ያለውን ህንጻ ነዳፊ አላደንቅ አለሳ!

አገራችን ሆይ ህንጻ ነዳፊዎችሽን አድንቂ! 

Via ዳዊት በንቲ

@etconp
❤22🔥2
👉JOB VACANCY

💫Position: Design Group — Civil Works Design Architect

⏺Company: Ethiotelecom

⏺Education: BSc in Architecture or Architecture and Planning

⏺Experience: 0 years (Graduated since 2015 E.C — fresh graduates only)

Additional Requirements:
- Excellent skills in 3D modeling, rendering, and presentation
- Strong knowledge of AutoCAD and architectural drafting tools
- Understanding of engineering and architectural concepts
- Project scheduling and coordination ability
- Knowledge of building sector standards and maintenance practices
- Problem-solving, communication, and teamwork skills

📍Work Location: Addis Ababa, Ethiopia

⚡️Deadline: May 23, 2026

📩How to Apply:Apply online via Ethiotelecom's recruitment portal👇

https://erp.ethiotelecom.et/OA_HTML/OA.jsp?page=/oracle/apps/irc/candidateSelfService/webui/VisVacDispPG&OAHP=IRC_EXT_SITE_VISITOR_APPL&OASF=IRC_VIS_VAC_DISPLAY&akRegionApplicationId=821&transactionid=537538459&retainAM=N&addBreadCrumb=RP&p_svid=40018&p_spid=121006&oapc=7&oas=TzORJbJdMFEXtg4xmQXFGg

@etconp
❤7
ጨረታ

አዲስ ዘመን áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 14 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1🙏1
ጨረታ

አዲስ ዘመን áŒáŠ•á‰Śá‰ľ 14 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👏1
ጨረታ

አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍3
👉ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

@etconp
🙏4