Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.2K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.78K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚኒሱ ማንኛው ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት እንዳለባቸው ተገለፀ

🪧የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር  የኮንስትራክሽን ዘርፍ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆንና ዘርፉ ሰፊ እና ውስብስብ እንዲሁም ብዙ ሀብት የሚንቀሳቀስበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የሚኒሱ ጥያቄዎችን ምላሽ መስጠት የሚያስችል   ውይይት ተካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት ክቡር ሚ/ዲኤታ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በዘርፉ የወጡ አዋጆች ደንቦች እና መመሪያዎች በማጣራት ተመጋጋቢ እና ተናባቢ በማድረግ ወጥነቱን አስጠብቆ መሬት በማውረድ ከጥያቄ ባለፈ ተግባራዊ ማድረግ እንደምገባ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ሙሉዓለም ደበበ ለህንጻ ስራ ተቋራጮች፣ ለሙያ ማህበራትና ለአማካሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የስራ ክፍሉ በሰጠው ስልጠና የተነሱ ጥያቄዎች፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የኮንስትራክሽን የምዝገባና የብቃት ማረጋገጫ መመሪያ ረቂቅ እንዲሁም ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የመወያያ ሰነዶች አቅርበዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት በማፋጠን የመሰረተ ልማት አውታሮችን በመዘርጋትና ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ያለው ከፍተኛ ድርሻ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዘርፉ የሚከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች የሚጠበቅባቸውን ጥራት፣ ደህንነት እና የወጪ ቆጣቢነት መርህ ተከትለው እንዲከናወኑ ለማድረግ ዘመናዊ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

የኮንሰትራክሽን ኢንዱስትሪ መረጃዎችን እና ግብዓቶችን በአንድ ቋት ማግኘት የሚያስችል እና የዘርፉ ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ችግር የሚፈታ ሲስተም በሚዲያ ላይም ዘርፉ ከማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች እና የዘርፉ አመራሮች ተሳትፈዋል።

Via መልሚ

@etconp
❤3👍3
🏗️ የክፍያ ሰርተፊኬት (Payment Certificate) እና የመጠን ቆጠራ (QTO) መሠረታዊ ቃላት

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚሰሩ ሲቪል ኢንጅነሮች፣ ኮስት ኢንጅነሮች፣ ኳንቲቲ ሰርቬየሮች እና ፕሮጀክት ማኔጀሮች ሊያውቋቸው የሚገቡ አስፈላጊ የክፍያ እና የኮንትራት አስተዳደር ቃላት! 📐📋

✅ Cumulative Work Executed – እስከ አሁን ድረስ የተጠናቀቀው ጠቅላላ የሥራ መጠን።

✅ Advance Payment – ሥራው ከመጀመሩ በፊት ለኮንትራክተሩ የሚሰጥ ቅድመ ክፍያ።

✅ Interim Payment – በተከናወነ የሥራ መጠን መሠረት በየጊዜው የሚከፈል ክፍያ።

✅ Final Payment – ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚፈጸም የመጨረሻ ክፍያ።

✅ Retention – ለጉድለቶች ዋስትና ተብሎ ከክፍያ የሚቀነስ መጠን።

✅ Rebate – ቅናሽ ወይም ከኮንትራቱ ዋጋ የሚቀነስ መጠን።

✅ Provisional Acceptance – ፕሮጀክቱ በጊዜያዊ ሁኔታ የሚቀበልበት ደረጃ።

✅ Final Acceptance – ሁሉም ግዴታዎች ከተሟሉ በኋላ የሚሰጥ የመጨረሻ ቅበላ።

✅ Defects Liability Period (DLP) – ኮንትራክተሩ የታዩ ጉድለቶችን የሚያስተካክልበት የዋስትና ጊዜ።

✅ Addition & Deduction – በኮንትራቱ ላይ የሚጨመሩ ወይም የሚቀነሱ መጠኖች።

✅ Advance Repayment – ቀድሞ የተከፈለው ቅድመ ክፍያ በኋለኛ ክፍያዎች የሚመለስበት ሂደት።

✅ Materials on Site – በሳይት ላይ ያሉ እና ለክፍያ ብቁ የሆኑ ግንባታ ቁሳቁሶች።

✅ Liquidated Damages (LD) – በፕሮጀክት መዘግየት ምክንያት በኮንትራቱ መሠረት የሚከፈል ቅጣት።

✅ Previous Payment – በቀደሙት የክፍያ ሰርተፊኬቶች የተከፈለ መጠን።

📊 Quantity Take-Off (QTO) ዋና ዓላማው፦

🔹 የኮንትራት መጠን (Contract Quantity) እና የተፈጸመ መጠን (Executed Quantity) ማነፃፀር

🔹 የኮንትራት ዋጋ (Contract Amount) እና የተፈጸመ የሥራ ዋጋ (Executed Amount) ማረጋገጥ

💡 እነዚህን ቃላት በጥልቀት መረዳት ትክክለኛ የክፍያ ሰርተፊኬት ዝግጅት፣ የፕሮጀክት ወጪ ቁጥጥር እና የኮንትራት አስተዳደር ላይ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። 🏗️📈💰

👷‍♂️ ለማንኛውም ሲቪል ኢንጅነር፣ ኳንቲቲ ሰርቬየር ወይም ኮንስትራክሽን ባለሙያ የግድ ሊታወቁ የሚገቡ መሠረታዊ የኮንትራት እና የክፍያ አስተዳደር ቃላት ናቸው። 🚧📋

🏗️ Payment Certificate & Quantity Take-Off (QTO) Basics for Construction Professionals

Understanding payment certificates and quantity take-off (QTO) is essential for every Civil Engineer, Quantity Surveyor, and Construction Professional. 📐📋

This note highlights key terms commonly used in construction contract administration:

✅ Cumulative Work Executed – Total value of work completed to date.
✅ Advance Payment – Initial payment made before work starts.
✅ Interim Payment – Periodic payment based on completed work.
✅ Final Payment – Last payment issued after project completion.
✅ Retention – Portion of payment withheld as security against defects.
✅ Rebate – Discount or reduction in contract value.
✅ Provisional Acceptance – Temporary acceptance before the defects liability period ends.
✅ Final Acceptance – Official handover after all obligations are fulfilled.
✅ Defects Liability Period (DLP) – Period during which the contractor must rectify defects.
✅ Additions & Deductions – Adjustments made to the contract amount.
✅ Advance Repayment – Recovery of advance payments from subsequent certificates.
✅ Materials on Site – Approved materials stored on-site and eligible for payment.
✅ Liquidated Damages (LD) – Compensation for delays as specified in the contract.
✅ Previous Payment – Amount certified and paid in earlier certificates.

📊 Quantity Take-Off (QTO) compares:

* Contract Quantity vs. Executed Quantity
* Contract Amount vs. Executed Amount

Mastering these concepts helps ensure accurate valuation, payment certification, cost control, and successful project delivery. 🚧💰📈

#CivilEngineering #QuantitySurveying #ConstructionManagement #PaymentCertificate #QTO #ContractAdministration #ProjectControl #ConstructionIndustry #EngineeringEducation #CostManagement

@etconp
❤18
Forwarded from Kelemat Ads
🚀 Need Content That Gets Results?

Meet Abrham Alemu — a creative specialist helping brands grow through powerful content and high-performing TikTok videos.

✅ TikTok Content Creation
✅ Content Strategy
✅ Brand Positioning
✅ Motion Graphics

Check out his work:
https://vt.tiktok.com/ZSQmDMqkf/
https://vt.tiktok.com/ZSQmdrMJg/
https://vt.tiktok.com/ZSQmUdBJK/

📞 +251942065130
📲 @Rasab_7

Ready to elevate your brand? Contact Abrham today.
❤2
🌆 ከተሞች ስሜታችንን እንዴት ይቀይሩታል?

• ​የ90 ሰከንድ ህግ (The 90-Second Rule)

የስነ-ልቦና ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ አንድ ሰው አሰልቺና ረጅም የኮንክሪት ግድግዳ ብቻ ባለው መንገድ ላይ ሲራመድ በ90 ሰከንድ ውስጥ የደካማነትና የጭንቀት ስሜት ማሳየት ይጀምራል።

በአንጻሩ ግን ሱቆች፣ ዛፎችና የተለያዩ የስነ-ህንፃ ውበቶች (Facades) ባሉበት መንገድ ላይ ሲራመድ አእምሮው ይነቃቃል፣ የደስታ ሆርሞንም ያመነጫል።

• ​የአረንጓዴ ቦታዎች ምትሃት (The Green Effect)

በከተማ ፕላን ውስጥ ፓርኮችና አረንጓዴ ስፍራዎች ዝም ብለው ለውበት ብቻ አይደሉም።

በጥናት እንደተረጋገጠው፣ በሳምንት 2 ሰዓት ብቻ በአረንጓዴ ቦታዎች ውስጥ ማሳለፍ የሰዎችን የፈጠራ አቅም (Creativity) በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል።

አሁን ከተማችን አዲስ አበባ ላይ እየተሰሩ ያሉትን የኮሪደር ልማቶችና ፓርኮች ስናይ፣ ከህንፃ ውበት ባለፈ የህዝቡን ምሽትና የኑሮ ስሜት እንዴት እየቀየሩት እንደሆነ መገመት ትችላለህ።

• ​የመብራት (Lighting) ሳይንስ፦ የምሽት ከተማ ውበት የሚወሰነው በመብራት ዲዛይን ነው።

ቢጫና ሞቅ ያሉ መብራቶች (Warm lights) ሰዎችን ዘና እንዲሉና እንዲረጋጉ ሲያደርጉ፣ ነጭና ደማቅ መብራቶች (Cool lights) ደግሞ ንቃትንና የስራ ስሜትን ይፈጥራሉ።

Via National Magazine

@etconp
❤5👏5
ይህንን ያውቃሉ ?😁

☕️1 ዶላር በ ኢራን rial 1.8 million ነው 👑እዛ ሄደን billionaire እንሁን እንዴ?😀

መልካም እሁድ 🫡

@etconp
🤣5❤3
👉የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ የተራዘመ
መሆኑን ለማሳወቅ የቀረበ ማስታወቂያ

ተቋማች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ያስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ህንጻ ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን እና በካፒታል ፕሮጀክት የተገነቡ ንግድ ቤቶችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ 8ኛ ዙር እና 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ በተመሳሳይ ቀን በአንድ የጨረታ ሰነድ ማውጣቱ እና የጨረታው 1ኛ ደረጃ አሸናፊዎች ከግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም የሽያጭ ውል ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከሲስተም መቆራረጥ እና ተጫራቾች ካነሱት ከባንክ የገንዘብ ዝውውር መዘግየት አንፃር የባከኑ የስራ ቀናትን ታሳቢ በማድረግ ለተጨማሪ 5 ( አምስት ) ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ በመሆኑ ቀደም ሲል በተገለፀላችሁ የመዋዋያ ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ በኩል የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በተገለጸው የሽያጭ ውል ጊዜ ገደብ ውስጥ ውል መፈጸም እንድትችሉ ጥሪ የቀረበላችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

@etconp
❤6👍1
👉JOB VACANCY

Project Manager at Compass Construction

Deadline: 2026-06-26
Experience: 8+ yrs

Oversee high‑rise construction projects as a Project Manager, coordinating teams, managing timelines and budgets, and ensuring technical and regulatory compliance.

• Lead and oversee high‑rise building projects
• Coordinate project activities with stakeholders
• Manage schedules and budgets
• Ensure compliance with engineering standards

How to Apply
Interested applicants who meet the above criteria are invited to apply within 10 working days from the date of this advertisement by submitting non-returnable copies of original documents at the office found at Gorgorios Roundabout, Welosefer Road, Amanuelwa Building, 2nd floor.
For More information: Telephone: +251 0114 70 12 87 // +251 907 71 72 73

@etconp
❤3👍2
Forwarded from Kelemat Ads
ብቁ አስጠኚ ሆነው ተከፋይ ይሁኑ

በኤክስትሪም እየሰለጠኑ ሥራ ይጀምሩ👌

በኤክስትሪም ለአስጠኚዎች የሚሰጠዉን የProfessional_Tutors ስልጠና በመዉሰድ የነገዉን ትዉልድ ትርጉም ባለዉ መንገድ የመቅረጽ ሂደቱን በብቃት እና በልበ ሙሉነት ይቀላቀሉ✅

ሰርተፍኬት በነጻ🥰
ባሉበት ሆነዉ በOnline ይማሩ

🎯 ማን ማመልከት ይችላል?

📌 መምህራን (ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል)
📌 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ተመራቂዎች
📌 ልምድ ያላቸው አስጠኚዎች እና ባለሙያዎች
📌 በቂ የማስተማር እውቀት እና ጥሩ የመግባባት ችሎታ ያላቸው።

ሰልጥነዉ ዉጤታማነትዎን ያሳድጉ❗️
እያስጠኑ ገቢዎትን ይጨምሩ👌

የመመዝገቢያ ሊንክ 👇
https://forms.gle/VAzHytRx7V8av6hR8

ጥያቄ ካለዎት በ @extremeconsultancy በኩል ያናግሩን።

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+KcrwCu8eoDUxZTM0
❤3
JOB VACANCY

Sanitary Engineer at EF Architects And Engineers Consulting Plc

Deadline: 2026-06-26
Experience: 5+ yrs

Responsible for designing and overseeing sanitary engineering projects in Addis Ababa, ensuring compliance with regulations and client requirements.

• Design sanitary systems for construction projects
• Prepare technical drawings and specifications
• Coordinate with clients and contractors
• Ensure compliance with local regulations
• Supervise installation and commissioning

Contact Details:

Address:- Lamberet Lame Dairy (Shola Milk) Building first floors 108. Yeka, Addis Ababa, Ethiopia.
📩Email Us :-efheadoffice1@gmail.com
Call Us
+251 116 677479
+251 911 240283

@etconp
❤9👍2🥰1
👉JOB VACANCY

Construction Engineer at Compass Construction

Deadline: 2026-06-26
Experience: 5+ yrs

Responsible for managing high‑rise building construction projects, ensuring technical quality, safety, and schedule adherence while coordinating site operations.

• Oversee high-rise construction projects
• Manage site activities and contractor coordination
• Ensure compliance with design specifications and safety regulations
• Maintain project schedules and budgets

How to Apply
Interested applicants who meet the above criteria are invited to apply within 10 working days from the date of this advertisement by submitting non-returnable copies of original documents at the office found at Gorgorios Roundabout, Welosefer Road, Amanuelwa Building, 2nd floor.
For More information: Telephone: +251 0114 70 12 87 // +251 907 71 72 73

@etconp
❤6
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦቻችን

🪧4ኛ ዙር ኦንላይን ስልጠናዎቻችን ምዝገባ ጀምረናል

⛈ክረምት እውቀትዎ እና ሞያዎ ማዳበር ይፈልጋሉ?

💫እንግድያውስ የ ETABS እና QUANTITY SURVEYING ሙሉ ኦንላይን ኮርስ በ 25 % ቅናሽ ምዝገባ ጀምረናል እንዲሁም ሁለቱም ኮርሶች በአንድ ላይ ለሚወስዱ ከ እያንዳንዱ የ 40% ቅናሽ ይደረግላቹዋል🙏

📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ይደውሉልን❤️

@etconp
❤4👏2
📢 Vacancy Announcement for fresh graduate 🎓

🏗️ Company: Macro General Contractor and Trading P.L.C

📋 Positions:
1. Site Engineer
2. Civil Engineer
3. Junior Office Engineer

🎓 Education: First degree in Civil Engineering or construction management
💼 Experience: 0 years & above
💰 Salary: Negotiable and Attractive
👥 Required qty: 15 total for 3 positions
📍 Work location: Addis Ababa & Project
📅 Deadline: June 26, 2026

📝 How to apply:
Interested applicants shall submit a copy of non-returnable documents in person or electronically.

🏢 Address: Addis Ababa around Hilegarment behind My wish Enterprise
📞 Phone no.: +251 11 471 0591
📧 Email: hr@macrogc.com
✈️ Telegram: +251986073396

@etconp
❤12👍1
የደቡብ ሱዳን መንግሥት የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ ከተማ ለሚያከናውነው  የዘመናዊ ቤቶች ግንባታ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገለጸ

ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን ስምምነት ያደረገ ሲሆን፣ የህንጻ ግንባታ ሳይቶች መረጣ እና ተያያዥ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አፈጻጸምም በግዛቱ የኮንስትራክሽን እና ቤቶች ኮርፖሬሽን በቀረበየጥናት  ሪፖርት  አማካኝነት  በዝርዝር  ተገምግሟል።

​ቀደም ሲል በአዲስ አበባ የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባር የሚያስገባው ይኸው አዲስ ውል በጁባ ከተማ ተፈርሟል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በዶክተር ረሻድ ከማል እና በደቡብ ሱዳን ሴንተራል ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ በክቡር ኢማኑኤል አድል ስምምነቱን ፈርመዋል፡።

በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ በጁባ ከተማ ዘመናዊ የንግድና የመኖሪያ ሕንጻዎችን የሚገነባ ይሆናል።

​ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል ከደቡብ ሱዳን መንግስት ልዩ መልዕክተኛ ከክብርት አዱት ኪር ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር ደሊል ከድር እና በደቡብ ሱዳን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩት ታዋቂው ባለሀብት ዶክተር አይሸሽም ተካ ተገኝተዋል።

​በመድረኩ ላይ ክብርት አዱት ኪር ኮርፖሬሽኑ በጁባ ከተማ ለሚያካሂደው የቤት ልማት ፕሮግራም የደቡብ ሱዳን ፌዴራል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

ይህ የቤት ግንባታ መጀመር በሁለቱ እህትማማች ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራና ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ያላቸውን ሙሉ እምነት በመግለጽ፣ የደቡብ ሱዳን መንግስት ለስምምነቱ ተግባራዊነት ያለውን  ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የፌቤኮ ​ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ረሻድ ከማል በበኩላቸው፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን የቤት ልማት ዘርፍ የተሰማራው የጋራ ተጠቃሚነትን፣ አብሮነትን እና ወንድማማችነትን መርህ አድርጎ መሆኑን ገልጸው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ ግንባታው በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ረሻድ ከማል እና በርሳቸው የሚመራው የሥራ ልዑካን ቡድን ለአራት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጉብኝት አጠናቆ  ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡

@etconp
❤4👍1
በኢትዮጵያ በበርካታ ከተሞች ዕውን እየሆነ ያለው የፕሪፋብ ቴክኖሎጂ የቤት ግንባታ ጥበብ

ለሰው ልጆች መሠረታዊ ፍላጎቶች ከሆኑት ከምግብና አልባሳት ቀጥሎ መጠለያ አንዱ ነው፡፡ መንግስት መሠረታዊ ፍላጎት የሆነውን የቤት ልማት አቅርቦትን ለማሳደግ በርካታ የቤት ልማት አማራጮችና ቴክኖሎጂዎችን ለማላመድ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከእነዚህ ስራዎች መካከል አንዱ የሆነውን የፕሪፋብ ቴክኖሎጂ የቤት ልማት ግንባታን ማፋጠን ደግሞ የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት ያስችላል፡፡

ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ለመጣው የህብረተሰብ ክፍል የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሻሻል በአጭር ጊዜ ተመርተው የሚገጣጠሙ ቤቶችን መስራት ተገቢ ነው፡፡

በእነዚህ የተገጣጣሚ የህንጻ አካላት የሚገነቡ ቤቶች የሀገር ውስጥ ግብአቶችን በብዛት የሚጠቀሙ፤ ብክነትንና ብክለትን የሚከላከሉ፤ ወጪ ቆጣቢ እና የዜጎችን የመክፈል አቅም ያገናዘቡ ከመሆናቸው ባሻገር ባለሙያዎችን በአጭር ጊዜ አሰልጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችሉ መሆናቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል፡፡
ከእነዚህ የመፍትሄ አማራጮች አንዱ ደግሞ የፕሪፋብ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትክሽን ኢንዱስትሪ ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ያዘጋጀውና በዱከም ከተማ መግቢያ ላይ በፕሪፋብ ቴክኖሎጂ የተገነባው 48 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት የቤት ግንባታ ለዚህ ማሳያ ነው፡፡

በቅርቡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች የተገነባውን የኮሪደር ልማት ተከትሎ የገጠሩን ነዋሪ የኑሮ ዘይቤ ለማሻሻል እየተሰሩ ካሉ ስራዎች መካከል አንዱ በሆነው የገጠር ኮሪደር እየተተገበረ ያለው የፕሪፋበ ቴክኖሎጂ የቤት አሠራር ጥበብ በይበልጥ ከታወቁት በብረት፣ በሲሚንቶ እና በብሎኬት ከሚገነቡ ቤቶች በተለየ በቃጫ፣ በጠጠር፣ በአሸዋ እና በሲሚንቶ ብቻ ተመርቶ የሚገነባው ቤት በቀላሉ ተመርቶ አገልግሎት ላይ ለማዋል የሚቻልበትን ዘዴ ያስተዋወቀ ነው፡፡

ቴክኖሎጂውን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ያላመዱት ኢንጂ.ብርሃኑ ካሣ በጉብኝቱ ሂደት እንደገለጹት ከዛሬ 8 ዓመት በፊት የባለቤትነት መብት ዕውቅና ያገኘው የፕሪፋብ ቴክኖሎጂ በአሁኑ ሰዓት ስታንዳርድ ወጥቶለት በሀገራችን ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በስፋት እየተተገበረ በመሆኑ የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎችን ለማሰልጠን ካሪኩለም ተቀርጾለት ቴክኖሎጂውን በስፋት መጠቀም የሚቻልበትን ዕድል ለማስፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ቴክኖሎጂው በተግባር ተፈትኖ በስፋት እየተሰራበት ያለ በመሆኑ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው ቴክኖሎጂው እያደገ የሚሄድ በመሆኑ ጅምሩ መስፋት እንዳለበትና በየጊዜው ማሻሻያዎች ሊደረጉበት እንደሚገባ፤ የህንጻ አካሉ የሚመረትበት የተለየ የማምረቻ ቦታ ቢኖረው፤ የላቦራቶሪ ፍተሻ የሚረጋገጥበት ሁኔታ ቢፈጠር፤ የገበያ ትስስር ቢኖር፤ በጋራ አብሮ ለመስራት የሚቻልበት ዕድል ቢፈጠር እና በዘርፉ ከተቋቋሙ ማህበራት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ቢመቻቹ የሚሉ ምክረ-ሀሳቦችን ለግሰዋል፡፡

@etconp
❤2👍1
🏥የላፍቶ ሆስፒታል – የልብና ነርቭ ህክምና የላቀ ማዕከል

📍 አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👤 ባለቤት፦ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ
🏢 የህንፃው ከፍታ፦ G+2
📐 ዲዛይን፦ OTT Architects & Engineers PLC
🏗️ የዲዛይን እና ግንባታ አስተዳደር፦ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ስራዎች ቢሮ

🔄 በመጀመሪያ በEthiopian Construction Works Corporation (ECWC) እንደ Turnkey Project የተከናወነ
📋 የዲዛይን ግምገማ፣ ሱፐርቪዥን እና የኮንትራት አስተዳደር፦ Ethiopian Engineering Corporation (EEC)
👷 ኮንትራክተር፦ TNT Construction PLC
🌍 የፕሎት ስፋት፦ 5.4 ሄክታር

የላፍቶ ሆስፒታል የልብና ነርቭ ህክምና የላቀ ማዕከል በኢትዮጵያ ከተገነቡ እጅግ ዘመናዊ እና የላቀ የጤና ተቋማት መካከል አንዱ ነው።

🏥 500 አልጋዎችን የያዘ እና 17 ህንፃዎችን ያካተተው ይህ ግዙፍ የጤና ኮምፕሌክስ፣ ዜጎች ለልዩ ህክምና ወደ ውጭ አገር የሚጓዙበትን ፍላጎት ለመቀነስ እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ የላቀ የህክምና ማዕከል ለማድረግ ታስቦ ተገንብቷል።

🫀🧠 ማዕከሉ በሚከተሉት ዘርፎች ልዩ ህክምና ይሰጣል፦
✔️ የልብ ህክምና (Cardiology)
✔️ የነርቭ ህክምና (Neurology)
✔️ የካንሰር ህክምና (Oncology)

🔬 የተቋሙ ዘመናዊ መሳሪያዎች፦
• AI የተደገፈ የምርመራ ስርዓት
• በኢትዮጵያ የመጀመሪያው Total Laboratory Automation (Robotics) System
• 640-Slice CT Scanner
• በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው PET Scanner

@etconp
👍4❤1
ጨረታ

ሪፖርተር ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤4