Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.77K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ለጠቅላላ እውቀት

💫ስለ CGPA እና GPA አሰራር ማብራሪያ

🚧ብዙዎች እንደሚሳሳቱት፣ Cumulative GPA (CGPA) ማለት የ-1st Semester እና የ-2nd Semester Gpaን ደምሮ ለሁለት ማካፈል ማለት አይደለም❌

🏷የትኛውም የGPA ስሌት የሚሰራው ተማሪው በወሰዳቸው አጠቃላይ Credit Hours ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው።

📚 የሴሚስተር GPA አሰራር

🧷የአንድን ተማሪ የሴሚስተር ውጤት (GPA) ለማስላት፣ እያንዳንዱ ትምህርት ያለው የ Credit Hour በዛው ትምህርት የመጣው Grade Point ይባዛል። ከዚያም የሁሉም ትምህርቶች ውጤት በአንድ ላይ ተደምሮ፣ በሴሚስተሩ ለተወሰዱት አጠቃላይ የ Credit Hour ድምር ይካፈላል።

🔖ምሳሌ፦ አንድ ተማሪ በሴሚስተሩ 3 ትምህርቶችን ቢወስድ፡

1ኛ ትምህርት፦ Grade A (4.0) እና Credit Hour 5 ቢሆን ➔ 4.0 x 5 = 20

2ኛ ትምህርት፦ Grade A- (3.75) እና Credit Hour 5 ቢሆን ➔ 3.75 x 5 = 18.75

3ኛ ትምህርት፦ Grade B (3.0) እና Credit Hour 3 ቢሆን ➔ 3.0 x 3 = 9

🚧የተማሪውን GPA ለማግኘት፦

የውጤቶች አጠቃላይ ድምር፦ 20 + 18.75 + 9 = 47.75

የአጠቃላይ Credit Hour ድምር፦ 5 + 5 + 3 = 13

🔗በመጨረሻም፣ የውጤቱን ድምር ለአጠቃላይ ክሬዲት ሰዓቱ ስናካፍለው የሴሚስተሩን GPA እናገኛለን፦
47.75 ÷ 13 = 3.67

❇️ስለዚህ፣ ይህ ተማሪ በሴሚስተሩ 3.67 GPA አመጣ ይባላል።

🪧CGPA ሲሰላም በተመሳሳይ መንገድ የሁሉንም ሴሚስተሮች(የሁሉንም ኮርሶች) አጠቃላይ የውጤት ድምር ለአጠቃላይ የክሬዲት ሰዓት ድምር በማካፈል ነው የሚገኘው።

📌 የ CGPA አሰራር ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፦

🚧ለምሳሌ የአንድን ተማሪ የሁለት ሴሚስተር የCGPA ውጤት ለማስላት፦

• 1st Semester ላይ፦
የውጤት ድምር = 47.75
የ Credit Hour ድምር = 13
(GPA = 3.67)

• 2nd Semester ላይ፦
የውጤት ድምር = 52.00
የCredit Hour ድምር = 15
(GPA = 3.46)

❌ የተሳሳተው አሰራር፦ የሁለቱን ሴሚስተር GPA ደምሮ ለሁለት ማካፈል (3.67 + 3.46) ÷ 2 = 3.56 (ይህ ስህተት ነው!) የምትወስዱት ኮርስ በጨመረ ቁጥር የተሳሳተ Result ነው የምታገኙት

🔗ትክክለኛው አሰራር (CGPA)፦
የሁለቱንም ሴሚስተር አጠቃላይ የውጤት ድምር ለአጠቃላይ የክሬዲት ሰዓት ድምር ማካፈል፦

• አጠቃላይ የውጤት ድምር፦ 47.75 + 52.00 = 99.75
• አጠቃላይ የCredit Hour ድምር፦ 13 + 15 = 28

🔗ስለዚህ CGPA = 99.75 ÷ 28 = 3.562 (ወደ ሁለት Digit ሲጠጋ 3.56 ይሆናል።)

📎ውጤቱ ተመሳሳይ ሊሆን የቻለው የሁለቱ ሴሚስተሮች የክሬዲት hr በጣም ስለሚቀራረብ ብቻ ነው፤ የምትወስዷቸው ኮርሶች በበዙ ቁጥር የ ሁለቱ አሰራር ልዩነት ይፈጥራል።

@etconp
❤15👍1
👉Job Vacancy Announcement 🏗️

💫Aser Construction

🚧30 different job titles 📋

💫Applicants are instructed to submit applications within 10 working days from the announcement date. ⏳

Engineering & Technical Roles 🔧

Senior Project Office Engineer (2 open positions)
Senior Engineer / Real Estate (2 open positions)
Office Engineer / Real Estate (2 open positions)
Asphalt Plant Site Engineer (2 open positions)
Senior Laboratory Technician (2 open positions)

Maintenance & Operations 🔨

Maintenance Planner (2 open positions)
Maintenance Coordinator (1 open position)
Maintenance Forman
Excavator Operator
Industrial Electrician

Procurement & Logistics 🚚

Project Supply Head
Procurement Officer
Local Purchaser Section Head
Transport Coordinator
Project Store Keeper

Drivers & Heavy Equipment

Heavy Truck Driver
Truck Mixer Driver
Bulk Load Driver
Low bed Driver
Concrete Pump Operator and Driver

📆 Deadline: June 27, 2026

@etconp
👍4❤1
🏗️ በዓለማችን የመጀመሪያው የሶላር ስታዲየም አስደናቂው የብረት መዋቅር ዝርጋታ ተጀመረ!

​በአረንጓዴና ዘላቂ ግንባታ (Sustainable Construction) ረገድ በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ ሊሰራ የተቃረበው ግዙፉ ስታዲየም፣ እጅግ ወሳኝና ውስብስብ የተባለውን ምዕራፍ አሳክቷል።

​የግንባታው ኃላፊ የሆነው የቻይና ኩባንያ፣ የስታዲየሙን ግዙፍ የጣራ ብረት መዋቅር (Steel Structure) የመጀመሪያ ዙር ወደ ላይ የማንሳትና የመግጠም ስራ (First Lift) በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን አስታውቋል።

​💡 ይህ ስታዲየም ለምን ልዩ ሆነ?
• ​ሙሉ በሙሉ በሶላር ኃይል የሚሰራ፦ ስታዲየሙ በዓይነቱ የመጀመሪያውና ሙሉ በሙሉ በፀሐይ ብርሃን በሚያገኘው ታዳሽ ኃይል እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ነው እየተገነባ ያለው።
• ​የምህንድስና ጥበብ፦ በ "ፎቶ ላይ እንደምትመለከቱት፣ ክብ ቅርጽ ያለውና እጅግ ግዙፍ የሆነውን የጣራ መዋቅር በትክክለኛ ሚዛን ወደ ላይ የማንሳቱ ሂደት (Lifting operation) ከፍተኛ የምህንድስና ጥበብና ጥንቃቄ የተሞላበት ነው።
• ​ለአካባቢ ተስማሚ (Eco-friendly)፦ ፕሮጀክቱ በግዙፍ ግንባታዎች ላይ የሚወጣውን የካርቦን ልቀትን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ አዲስ አቅጣጫ አመልካች እየሆነ ይገኛል።

​የአለምን የግንባታ ቴክኖሎጂ አንድ እርምጃ ወደፊት ያሻገረው ይህ ፕሮጀክት፣ በዘላቂ ምህንድስና (Sustainable Engineering) ረገድ ለወደፊቱ ትልቅ ማሳያ የሚሆን ነው።

​እናንተስ በሃገራችን መሰል ግዙፍ ስታዲየሞችና መሰረተ ልማቶች ላይ ታዳሽ ኃይልን (የፀሐይ ብርሃንን) አቀናጅቶ መጠቀም መቼ በስፋት ይጀመራል ብላችሁ ታስባላችሁ? አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን!

@etconp
❤9👍2
👉የመንገድ ግንባታ ዋና ደረጃዎች (Main Stages of Road Construction)

🚧መንገድ ግንባታ በየደረጃው በጥንቃቄ የሚከናወን ሥራ ሲሆን እያንዳንዱ ደረጃ ለመንገዱ ጥንካሬ፣ ዘላቂነት እና ደህንነት ትልቅ ሚና አለው።

1. የሳይት ዝግጅት (Site Preparation)

ዛፎች፣ቁጥቋጦዎች እና ሌሎች እንቅፋቶችን ማስወገድ (Clearing & Grubbing)

የመንገዱን አቅጣጫ እና ወሰን በሰርቬይ መወሰን (Setting Out)

የግንባታ ቦታውን ለስራ ዝግጁ ማድረግ

2. የመሬት ሥራ (Earthwork)

ከፍ ያለ ቦታ መቆፈር (Cut)

ዝቅተኛ ቦታ በአፈር መሙላት (Fill)

አፈሩን በኮምፓክተር ማጠናከር (Compaction)

የመንገዱን Formation Level ማዘጋጀት

3. ሳብግሬድ (Subgrade)

ይህ የመንገዱ መሠረታዊ የአፈር ክፍል ነው።

ሁሉንም የላይኛ ንብርብሮች የሚሸከም መሠረት ነው።

በትክክል ካልተኮምፓክት መንገዱ በፍጥነት ሊበላሽ ይችላል።

4. ሳብ-ቤዝ (Sub-base)

በ Subgrade ላይ የሚቀመጥ የጠጠር ወይም የተፈጨ ድንጋይ ንብርብር ነው።

ጭነትን በስፋት ያሰራጫል።

የውሃ ፍሳሽን ያሻሽላል።

5. ቤዝ ኮርስ (Base Course)

የመንገዱ ዋና ጭነት ተሸካሚ ክፍል ነው።

የተሽከርካሪዎችን ክብደት ወደ ታችኛው ንብርብር ያስተላልፋል።

ከተፈጨ ድንጋይ (Crushed Aggregate) ይሠራል።

6. ባይንደር ኮርስ (Binder Course)

በBase Course እና Wearing Course መካከል ያለ የአስፋልት ንብርብር ነው።

ንብርብሮቹን እንዲጣበቁ ያደርጋል።

ተጨማሪ ጥንካሬ ይሰጣል።

7. ዌሪንግ ኮርስ (Wearing Course)

ይህ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ የሚንቀሳቀሱበት የመንገዱ የላይኛው ክፍል ነው።

ለስላሳ ጉዞ ይፈጥራል።

የጎማ መንሸራተትን ይቀንሳል።

መንገዱን ከፀሐይ፣ ከዝናብ እና ከሌሎች የአየር ሁኔታዎች ይጠብቃል።

8. ሾልደር እና ድሬኔጅ (Shoulder and Drain)

ሾልደር (Shoulder) በመንገዱ ጎን የሚገኝ ክፍል ነው።

ለአደጋ ጊዜ ማቆሚያ ይሆናል።

የመንገዱን ጠርዝ ይደግፋል።

ድሬኔጅ (Drainage) ደግሞ የዝናብ ውሃን ከመንገዱ ለማራቅ ይጠቅማል።

9. የመንገድ ምልክቶች እና መሳሪያዎች (Road Markings and Furniture)

የመስመር ምልክቶች (Lane Markings)

የትራፊክ ምልክቶች (Traffic Signs)

ጋርድሬል (Guardrails)

የመንገድ መብራቶች (Street Lights)

እነዚህ ሁሉ ለመንገድ ተጠቃሚዎች ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር አስፈላጊ ናቸው።

💫አጠቃላይ የRoad Pavement Layer ቅደም ተከተል

Wearing Course ⬇️
Binder Course ⬇️
Base Course ⬇️
Sub-base ⬇️
Subgrade (Compacted Soil)

@etconp
❤17👍7
👉JOB VACANCY

📈Junior Cost Control Engineer

✂️Vacancy code - Hahu Commercial 011/2026


📍Jimma

📖Bachelor's Degree in Civil Engineering or with related field of study with relevant work experience

- Generate cost & productivity reports accurately & timely
- Generate productivity evaluation reports according to the company productivity norm
- Generate loss reports covering material, labor, and equipment usage
- Generate cost related risk management report & the mitigation required.                                     
- Conduct market assessments to support cost analysis and decision-making
- Ensure compliance with company cost control procedures and guidelines

Quanitity Required: 5

Minimum Years Of Experience: #0_years
Maximum Years Of Experience: #2_years

Deadline: June 26, 2026

Note: Applicants should be residents of Jimma and only graduates of 2025/2026 academic year are eligible to apply.

📩How To Apply: Click the apply button below👇

https://application.eecproducts.com/

@etconp
❤8
ውጤትዎን ይመልከቱ!

ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት መታየት ጀምሯል።

ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et

ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

@etconp
❤4🙏1
JOB VACANCY

Position: Data Collector 📊

Company: Compass Construction 🏗️

Education: BSc degree in Civil Engineering or other related fields of study 🎓

Experience: 0 Years (Fresh Graduates) 🌱

Additional Requirements: 📝

Basic understanding of data collection and reporting principles, good communication and organizational skills, ability to work in field environments when required, and basic computer literacy (MS Office is an advantage) 💻

Work location: Addis Ababa - Ethiopia 📍

⚡️Deadline: Jun. 26, 2026 🗓️

📩How to apply: Interested applicants who meet the above criteria are invited to apply by submitting non-returnable copies of original documents at the office found at Gorgorios Round about to, Welosefer road Amanuelwa Building, 2nd floor 🏢

@etconp
❤9🙏3🥰1👏1
👉ማስታወቂያ

🪧ለ 70/30 የጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት በ online በተጠባባቂነት ለተመዘገባችሁ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤11🙏2
👉ብዝዎች እባካቹ ቅናሹ አራዝሙልን ባላቹት መሠረት ኦንላይን ስልጠናዎቻችን ምዝገባ ድጋሜ ጀምረናል

⛈ክረምት እውቀትዎ እና ሞያዎ ማዳበር ይፈልጋሉ?

💫እንግድያውስ የ ETABS እና QUANTITY SURVEYING ሙሉ ኦንላይን ኮርስ በ 25 % ቅናሽ ምዝገባ ጀምረናል እንዲሁም ሁለቱም ኮርሶች በአንድ ላይ ለሚወስዱ ከ እያንዳንዱ የ 40% ቅናሽ ይደረግላቹዋል🙏

📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ይደውሉልን❤️

@etconp
❤7🙏1
JOB VACANCY

Position: Junior Construction Supervisor 👷‍♂️🏗️

Company: Menschen fuer Menschen Foundation

Education: B.Sc. in Civil Engineering (CGPA ≥ 3.5; Fresh Graduate of 2024/25 Academic year) 🎓

Experience: 0-1 years (Entry Level / Fresh Graduate) 🌱

Additional Requirements: Good command of spoken & written English; skills in teamwork, problem-solving, and construction technologies; 🛠️🤝

Salary: Negotiable 💰

Required qty: 1

Work location: Gambela 📍

Deadline: June 29, 2026 📅

How to apply:

Interested applicants fulfilling the requirements can send a non-returnable application mentioning the job title and duty station in the subject line, CV, and copies of relevant credentials to the following address: 📬

Menschen fuer Menschen
P. O. BOX 2568
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Must submit a Civil Engineering Degree, Student Copy, High School Transcript, Application Letter, and CV. 📄✨

@etconp
❤7🙏3
👉የመሠረተ-ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በሠው ሠራሽ አስተውሎት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጠ

የመሠረተ-ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዲጅታላይዝ ለማድረግ ታስቦ በሠው ሠራሽ አስተውሎት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ  ዲጅታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተራቀቀና እየዘመነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ከዘመኑ ጋር ራሳቸውን ፈጥነው በእውቀትና በክህሎት ቀድመው በመገኘት በሀገራችን የሚከናወኑ የመሠረተ-ልማቶች በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ስልጠናው እጅግ የጎላ ነው ያሉት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሠረተ-ልማት ዘርፍ አማካሪ አቶ ቃሲም ጃቢር መድረኩን በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡

የሰው ሠራሽ አስተውሎት ያለው ፈፈዳ  በዓለማችንና በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ እጅግ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ  መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያው የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በማቀላጠፍ አዳዲስ ፈጠራዎችን እውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በተለይ በከተማ ልማት እና መሠረተ ልማት  ዘርፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ያለው ጠቀሜ ባለሙያው እንዳብራሩት ዘመናዊ የከተማ ፕላን (Smart City Planning): ሳተላይት እና ድሮኖች የሚሰበስቡትን መረጃ በመጠቀም ከተሞች እንዴት እንደሚያድጉ አስቀድሞ መተንበይ ይቻላል።

ይህም መሬትን በአግባቡ ለመጠቀምና ህገ-ወጥ ሰፈራዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል።

የትራንስፖርትና መንገድ አስተዳደር (Traffic Optimization): በትራፊክ መብራቶችና ካሜራዎች አማካኝነት የትራፊክ መጨናነቅን መቆጣጠር እና ተሽከርካሪዎች ያለ ምንም እንከን እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ይቻላል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊነት (E-Governance): እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሉ አካላት የነዋሪዎችን መረጃና አገልግሎት (ለምሳሌ የሲቪል ምዝገባ) ለማቀላጠፍ በ AI የተደገፉ ዲጂታል ሲስተሞችን እንደምጠቀሙ በስልጠናው ተገልጿል።

Via ከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር

@etconp
❤10