Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
528 files
3.76K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉Job Vacancy Announcement

🪧Kidcon Engineering

📆Deadline : July 03, 2026

@etconp
👏4❤1
#ADVERTISEMENT

Construction safety net
Size 2×50
price=6800
Call ✅ 0912955969
✅ 0949434363

Telgram= https://t.me/fAR7957
👍5
🏗️  የወደፊቱ ኮንስትራክሽን አሁን ላይ ነው!

🏷የፈጠራ ማሽነሪዎች አዳዲስ አስገራሚ ታሪኮች


❇️​ሰላም የገጻችን ተከታታዮች ዛሬ በኮንስትራክሽኑ ዓለም ውስጥ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ እየቀየሩ ያሉ 3 አስገራሚና ወቅታዊ የማሽነሪ ቴክኖሎጂዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል።

🚧እነዚህ ማሽኖች ፍጥነትን፣ ደህንነትንና አካባቢ ጥበቃን በአንድ ላይ ያቀናጁ ናቸው።

​1. 🤖 በራሳቸው የሚሰሩ (Autonomous) ኤክስካቫተሮች
​አሁን ላይ ሹፌር የሌላቸው ኤክስካቫተሮች በብዛት ወደ ስራ እየገቡ ነው። በካሜራዎች፣ በሴንሰሮችና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዙት እነዚህ ማሽኖች፡
• ​ሰው በማይደርስባቸው አደገኛ ቦታዎች ላይ በራሳቸው ይቆፍራሉ።
• ​የሰውን ድካም ከመቀነስ ባለፈ የሳይት ላይ አደጋዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳሉ።
• ​ስራን ያለማቋረጥ 24 ሰዓት ሙሉ ማከናወን ይችላሉ።

​2. ⚡ የኤሌክትሪክ ከባድ ማሽነሪዎች (Electric Heavy Machinery)
​የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የኮንስትራክሽን ዘርፉም ትልቅ እመርታ እያሳየ ነው።
ታዋቂዎቹ አምራቾች (እንደ CAT፣ Komatsu እና Volvo ያሉ) ሙሉ በሙሉ በባትሪ የሚሰሩ ግዙፍ ዶዘሮችንና ሎደሮችን በስፋት እያመረቱ ነው።
• ​ጥቅማቸው፡ ጭስና ካርቦን ጨርሶ አይለቁም፣ ድምፅ ስለማያወጡ በከተማ መሀል ለሚሰሩ ስራዎች ተመራጭ ናቸው፣ እንዲሁም የነዳጅ ወጪን ሙሉ በሙሉ ያስቀራሉ።

​3. 🧱 ሮቦቲክ የጡብ ድራሽ ማሽኖች (Robotic Bricklayers)
​ግንብ ለመገንባት ሳምንታት የሚፈጅበት ጊዜ እያበቃ ይመስላል።
አዲሶቹ የሮቦት ግንበኞች በሰዓት እስከ 1,000 ጡቦችን የመደርደር አቅም አላቸው!
• ​ሰዎችን ከከባድና ደጋጋሚ ስራዎች በማረፍ፣ ይበልጥ ጥንቃቄ በሚያስፈልጋቸው የምህንድስና ክፍሎች ላይ እንዲያተኩሩ እያደረጋቸው ነው።

​💡የቴክኖሎጂው አለም በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የኮንስትራክሽን ሳይቶች ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተቆጣጠሩ ዲጂታል ማዕከላት መሆናቸው አይቀሬ ነው።

​📱 እናንተስ ምን ታስባላችሁ?

• እነዚህ ማሽነሪዎች ወደ እኛ ሀገር በስፋት ቢገቡ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ምን ያህል ያግዙታል?

ከታች በኮሜንት ሃሳባችሁን አካፍሉን!

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤10
👉የካሳ ክፍያን በተመለከተ የክልል እና የፌደራል መንግስት እርስ በእርሳቸው ‛ማን ይክፈል’ በሚለው ባለመስማማታቸው ካሳ ሊከፈላቸው የሚገባቸው አካላት እየተንገላቱ መሆኑ ተገለጸ

🚧ለልማት ሲባል በሃይል የሚነሱ ዜጎች የሚገባቸውን ካሳ እንደማይከፈላቸው የገለጸው የኢትዮጵያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ለዚህ ችግር አስፈፃሚ አካላት ህግን ተከተለው ባለመስራታቸው፣ የክልል እና የፌደራል መንግስት እርስ በእርሳቸው “አንተ ክፈል አንተ ክፈል” በመባባል ላይ እንደሆኑ አስታወቀ።

በቅርቡ የወጣው የካሳ አዋጅ ክልሎች እንዲከፍሉ የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ ቀደም ያለው ደግሞ የፌደራሉ እንዲከፍል የሚያዝ ነበር።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ2018 በጀት ዓመት የ11 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት አቅርቧል።

ተቋሙ በሪፖርቱ ላይ ባለፉት ወራት የደረሱትን በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

አክሎም ለተለያዩ የልማት ሥራዎች ሲባል ዜጎችን በኃይል የማንሳትና ተገቢውን ካሳ ያለመስጠት ድርጊት አሁንም አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለ ድርጊት ነው ማለቱን ለምክር ቤቱ  ካዘጋጀው ሪፖርት አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ዕንባ ጠባቂ ተቋም አክሎም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትንና የንብረት ካሳ የሚከፈልበት ሁኔታን አስመልክቶ አድርጌዋለሁ ባለው ስልታዊ ምርመራና መደበኛ ቁጥጥር በአስፈጻሚ አካላት በኩል ሰፊ የሕግ ጥሰት አለ ሲል ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ በግኝቱ ላይ እንዳመለከተው፣ በአዋጁ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ በቀጥታ እየተጣሰ ይገኛል።

በመሠረተ ልማት ግንባታ ምክንያት የሚነሱ ዜጎች ከመነሳታቸው ቢያንስ አንድ ዓመት በፊት ስለ ልማቱ ዓይነት፣ ጠቀሜታና አጠቃላይ ሂደት እንዲያውቁት  አይደረግም ብሏል።

ከዚህም በላይ በቦታው ላይ ከሚገኙ ተነሺዎች የንብረት ልኬትና መጠን መረጃ ሳይሰበሰብና ሊከፈላቸው የሚገባው የካሳ መጠን ሳይወሰን ዜጎች “በኃይል” ከይዞታቸው እንዲነሱ እየተደረገ መሆኑን ተቋሙ አረጋግጫለሁ ብሏል።

በዚህም ምክንያት ባለመብቶቹ መሬታቸውን በኃይል ከተቀሙ በኋላ መብታቸውን ለማስከበር በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ደጃፍ ለአቤቱታ ለመንከራተትና ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ገልጿል።

ሌላው የዕንባ ጠባቂ ተቋሙ  በሪፖርቱ ላይ የጠቀሰው ትልቅ ክፍተት፣ ካሳ ከተወሰነ በኋላም ለመክፈል ረዥም ጊዜ የሚወስድ መሆኑና አንዳንዶቹ ጉዳዮች ዓመታትን ማስቆጠራቸውን የተመለከተው ነው።

በተጨማሪም በ2016 በወጣው አዋጅ  ላይ ባለው የግልጽነት መጓደል ምክንያት የክፍያ ጥያቄዎች ሲቀርቡ ክልሎች ወደ ፌደራል፣ ፌደራል ደግሞ “የክልሎች ሥልጣን ነው” በሚል ኃላፊነትን እርስ በርስ በመገፋፋት በባለጉዳዮች ላይ መጉላላት እየፈጠሩ መሆኑን አንስቷል።

ተቋሙ ለማሳያ እንዲሆን አድርጌዋለሁ ባለው የቁጥጥር ስራ በአማራ ክልል የሚገኘው የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት ለልማት ተነሺዎች በሕግ ከተደነገገው በተቃራኒ 141.3 ሚሊዮን ብር ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች የሚገባውን ካሳ ሳይከፍል ቆይቷል ብሏል።

ተቋሙ ባለፉት 11 ወራት ውስጥ 1,715 የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን ተቀብሎ መመርመሩን አስታውቋል።

በእነዚህ መዝገቦች ላይ በተደረገው ማጣራትና ምርመራ በአጠቃላይ 44,901 ዜጎች “የአስተዳደር በደል ደርሶብናል” በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ከአቤቱታ አቅራቢዎቹ መካከል 17,002 ወንዶች ፤7,934 ሴቶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 19,965 ደግሞ በቡድንና በሌላ መልክ የቀረቡ በመሆናቸው በፆታ ያልተለዩ መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሳያል።

አቤቱታዎች ከቀረቡባቸው ዋና ዋና ዘርፎች መካከል 452 ጉዳዮች የአገልግሎት ዕጥረት፣ የ408 መሬት ይዞታ ክርክር፣ 306 የሥራ ቅሬታዎች እንዲሁም 197ቱ የካሳ ክፍያነ የተመለከቱ ናቸው።

ተቋሙ ወስጃዋለሁ ባለው የማስተካከያ እርምጃ እና  በሰጣቸው የመፍትሔ ሐሳቦች አማካይነት 82 ሠራተኞች ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ 1,319 ሠራተኞች ደግሞ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር መብታቸው ተከብሮላቸዋል ሲል አስታውቋል።

በተጨማሪም ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ የደመወዝና ጥቅማጥቅም ውዝፍ ክፍያ ለባለጉዳዮች እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን፣ 41 አቤቱታ አቅራቢዎች ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙና በአጠቃላይ 36,200 ካሬ ሜትር ምትክ ቦታ ለተነሺዎች እንዲሰጥ ተደርጓል ብሏል።

የዕንባ ጠባቂ ተቋሙ የምርመራ ሥራ ማካሄድ ብቻውን በቂ አለመሆኑን በመጥቀስ፣ የመፍትሔ ሐሳቦች ላይ ጥብቅ የክትትል ሥራ እየተከናወነ ቢሆንም አንዳንድ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ለተቋሙ ሥራ ፈቃደኛ አለመሆንና የሚሰጡ ምክረ ሐሳቦችን በተገቢው ፍጥነት አለመፈጸም እንደ ትልቅ ማነቆ ሆኖብኛል ብሏል።

በቀጣይ ለልማት የሚነሱ ዜጎች ሰብዓዊና አስተዳደራዊ መብቶች አስቀድመው እንዲከበሩና የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ለሕግ ተገዥ እንዲሆኑ ምክር ቤቱ የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ እና እንድከታተል ጥሪ አቅርቧል።

Via Addis Maleda

@etconp
❤5
Job Vacancy

Ovid Real Estate, a leading real estate construction company based in Addis Ababa and Jimma Housing Project, a proud member of Ovid Group, is dedicated to delivering residential, commercial, and mixed-use developments across Ethiopia.

We are excited to announce an opportunity with our Jimma Housing Project to work in a dynamic team and be part of this exciting journey.

Core Professional Skills
• Strong analytical and problem-solving skills 
• Excellent communication and documentation skills
• Ability to work under presser
How to Apply 
Interested and qualified applicants are required to submit the following documents through the link provided below.or through the email provided here.

mieraf.d@ovid-realestates.com
samrawitbarega@ovid-realestates.com hr@ovid-realestates.com 

https://forms.gle/QRCGiosMgwmnuUaF8

Application deadline: July 6 / 2026

• A Cover Letter
• An Updated Curriculum Vitae (CV)

@etconp
❤8
በከተማ አስተዳደሩ ዓመታዊ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መወሰኛ ጥናት ላይ የፖናል ውይይት ተካሄደ።

በእዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤናማ የቤት ኪራይ አሰራሮችን ለመዘርጋትና በህግ ማዕቀፍ ለመምራት የሚያስችል የግል መኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናትን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

የቀረበው ጥናት በከተማዋ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች እንዳሉት በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ እንደገለጹት፡- ጥናቱ አከራዩ ወቅቱን ያገናዘበ ፍትሃዊ ገቢ እንዲያገኝ የሚያረጋግጥ ተከራዩ ደግሞ ከገቢው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ እንዲከፍል ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዋጋ ትመና ጥናቱ በዘፈቀደ የተሰራ ሳይሆን የከተማችንን ነዋሪ የሆኑ ተከራዮች የመክፈል አቅም ያገናዘበ ነው ሲሉ የቢሮው ኃላፊዋ ገልጸዋል።

ይህ የኪራይ ዋጋ ማስተካከያ ጥናት በከተማችን የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም የቢሮው ኃላፊ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ገልጸዋል ።

መድረኩ ለ2019 በጀት ዓመት የተዘጋጀው የገበያ ዋጋ ጥናት ወደ ተግባር ከመሸጋገሩ በፊት ፣ ከሚመለከታቸው ተቌማት እና ከህዝብ ተወካዮች የጋራ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via Mayor Office of Addis Ababa

@etconp
❤7👍1
የጨረታ ማስታወቂያ-1.pdf
92.6 KB
ለመንገድ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚያገለግል የኮንክሪት ሚክስ ምርት ግዥ ጨረታ

Concrete ready mix C25 and C30

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
የጨረታ ማስታወቂያ-2.pdf
98.7 KB
👉ለባለሥልጣን መ/ቤቱ የጥገና ማዕከል የካፍቴሪያ አገልግሎት ግዥ ጨረታ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤4
🚧የሰማይ ጠቀሱ ግድብ ምረቃ 👇

@etconp
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
🚧የሰማይ ጠቀሱ ግድብ ምረቃ 👇 @etconp
የሰማይ ጠቀሱ ግድብ ምረቃ


የቅዳሜን እረፍት በምናጣጥምበት በዚህ ወቅት፣ በደቡብ ምዕራብ ቻይና ሲቹዋን ግዛት የሚገኘው የሹዋንግጂያንግኩ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ማመንጫ ክፍል ትናንት አርብ ዕለት ከዋናው የኃይል አውታር ጋር ተገናኝቷል፤

ይህ ክስተት በዓለማችን ላይ እጅግ ረጅሙ የሆነውን ግድብ የኃይል ማመንጨት ጉዞ በይፋ ያስጀመረ ሲሆን፣ በሰው ልጅ ምህንድስና ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፤


ይህ ግዙፍ ግድብ 315 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የከፍታውን ዘውድ ጭነው የነበሩትን የጂንፒንግ-1 (Jinping-I) እና ሊያንግሄኩ (Lianghekou) የውሃ ማጠራቀሚያዎችን በመብለጥ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ከአፈርና ከዓለት የተገነባው ይህ ግዙፍ መዋቅር፣ የሰው ልጅ በትጋትና በዕውቀት ተራራዎችን ማፍረስ ብቻ ሳይሆን አዲስ ተራራዎችንም መገንባት እንደሚችል ያሳየበት ህያው ምስክር ነው፤

ግድቡ 2 ሚሊዮን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ በዓመት በአማካይ 7.7 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት (kWh) ንጹህ ኃይል ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል። የሚገርመው ነገር፣ ይህንን ግድብ ለመገንባት የፈሰሰው የአፈርና የዓለት ድምር መጠን ከ46 ሚሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ሲሆን፣ ይህንን ቁስ አንድ ሜትር ከፍታና አንድ ሜትር ስፋት ባለው ግንብ ብንደረድረው፣ የምድርን ወገብ አንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መዞር ይችላል!

ከዚህ አስደናቂ ስኬት ጀርባ ለአሥርተ ዓመታት የዘለቀ የጽናት ታሪክ አለ። የፕሮጀክቱ ዲዛይነር የሆነው POWERCHINA Chengdu የውሃ ሀብት ጥናቱን የጀመረው ገና በ1950ዎቹ (እ.ኤ.አ.) የነበረ ሲሆን፣ በዳዱ ወንዝ ላይ ያለውን የሃይድሮሊክ ፕላን ያረቀቀው ደግሞ በ1977 ነበር። ትውልዶች አልፈው እቅዱ ዛሬ ላይ ፍሬ አፍርቶ ለዓለም ድንቅ ስራ ለመሆን በቅቷል፤


የጉዞው መንገድ አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ እ.ኤ.አ. በ2003 በነበረው የአከላለል ማሻሻያ ወቅት፣ መጀመሪያ ታስቦ የነበረው “ዱሶንግ” የተባለው ፕሮጀክት ከመጠን በላይ መሬትን በውሃ ስለሚያጥለቀልቅ እንዲሰረዝ ተደርጎ ነበር። ሆኖም መሃንዲሶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ ጥናታቸውን ወደ ላይኛው የወንዙ ክፍል በማሻገር የዙሙዙ እና የቹኦሲጂያ ወንዞች በሚገናኙበት ስፍራ ላይ የአሁኑን “ሹዋንግጂያንግኩ” (ትርጉሙም የሁለት ወንዞች መገናኛ) ግድብን መሰረቱ፤

የ315 ሜትር ከፍታውን ግድብ በዚያ አስቸጋሪ ስፍራ ላይ መገንባት ከባድ የተፈጥሮ ፈተናዎችን የጋበዘ ነበር። አካባቢው በከፍተኛ ከፍታ ላይ የሚገኝ፣ ብርድ የሚበረታበት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ያለበት እና የወንዙ ወለል የአፈር ንብርብር እጅግ ጥልቅ (እስከ 68 ሜትር) የሆነበት ቦታ ነው። ከዚህ ቀደም በዓለም ላይ በ250 ሜትር ጥልቀት ላይ እንዲህ ዓይነት ግዙፍ የአፈርና ድንጋይ ግድብ ተገንብቶ አያውቅም ነበር፤

በክረምት ወቅት ከ2,200 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ ስራን ለማቀላጠፍ የምህንድስና ቡድኑ በአይነቱ ልዩ የሆነ ትልቅ የአየር ድጋፍ ያለው ሽፋን (membrane structures) እና የፀሐይ ብርሃንን የሚያንጸባርቁ የማሞቂያ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሟል። ይህ ዘዴ የግንባታ ቁሳቁሱን ሙቀት በ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በመጨመር ስራው ያለ መቆራረጥ እንዲቀጥል ከማድረጉም በላይ፣ በዓለም የመጀመሪያውን ዘመናዊና ሙሉ ሰንሰለቱን የጠበቀ “የስማርት ቁጥጥር” ስርዓት ተግባራዊ አድርጓል፤


ይህ ፕሮጀክት በከፍታው ብቻ ሳይሆን በበርካታ የምህንድስና ዘርፎች የዓለምን ክብረ ወሰን ሰባብሯል። በውስጡ የያዘው ከመሬት በታች የተገነባው የሃይል ማመንጫ ዋሻ (underground powerhouse)፣ እጅግ ረጅሙ የቁሳቁስ ማጓጓዣ ስርዓት፣ የዓለማችን ትልቁ የውሃ መሳቢያ ክሬን (hydraulic hoist) እና ግዙፉ የጎርፍ መልቀቂያ ዋሻ ፕሮጀክቱን የቴክኖሎጂ ቁንጮ ያደርጉታል፤

ከመሬት በታች ያሉትን ውስብስብ የጂኦሎጂካል ፈተናዎች ለመቋቋም ቡድኑ የአካባቢውን ሁኔታ መሰረት ያደረገ አዲስ “የዓለት ፍንዳታ (rockburst) ምደባ ስርዓት” ዘርግቷል። ይህ የፈጠራ ስራ የድንገተኛ ዓለት ፍንዳታ አደጋን በ40 በመቶ የቀነሰው ሲሆን፣ በቁፋሮ ወቅት ሊፈጠር የሚችለውን ከፍተኛ መዛባት ወደ 30 ሚሊ ሜትር ብቻ በመቀነስ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ደህንነት አረጋግጧል፤

ይህ ግዙፍ የውሃ ማጠራቀሚያ በዓመት 2.9 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው። ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምር፣ በወንዙ ግርጌ የሚገኙትን ሌሎች የሃይል ማመንጫዎች አቅም በ6.6 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት ያሳድጋል፤ የሲቹዋንን የኃይል አቅርቦት ያረጋጋል፤ እንዲሁም በያንግትዜ ወንዝ ላይ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ በመከላከል ረገድ እንደ ታላቅ ጋሻ ሆኖ ያገለግላል።

መልካም ቅዳሜ


@etconp
👍7❤6👏1
👉የምስራች ከ @ETCONp
ከታች ካሉት ሶፍትዌሮች በደንብ የምትችሉት አንዱ በመምረጥ በውስጥ ፃፉልን ስራ ልንፈጥርላቹ ነው👇

💻Ms Project
💻Civil 3D
💻 Etabs With Safe
💻Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
💻Structural Design in ProtaStructure Software
💻Autocad
💻Sap2000
💻Autodesk Revit Architecture
💻Primavera P6

📩 @Philemona7 ፃፉልን ወይም በ 0925446661 ይደውሉልን🙏

@etconp
👏5❤2
👉እናስተዋዉቃችሁ

​🌟 ቅዳሜን ከታላላቅ መሐንዲሶች ጋር፦
“ኒኮላ ቴስላ” የብርሃኑ እና የገመድ-አልባው ዓለም ጠቢብ
​
🪧ለዛሬው የቅዳሜ “እናስተዋውቃችሁ” ዓምዳችን፣ በአሁኑ ዘመን ለምንኖርበት ዘመናዊ የኢንጂነሪንግ እና የኤሌክትሪክ ስልጣኔ መሠረት የጣለውን፣ ነገር ግን በታሪክ ብዙም ሳይዘመርለት ያለፈውን ታላቅ ሳይንቲስት እና መሐንዲስ ኒኮላ ቴስላን (Nikola Tesla) ልናስተዋውቃችሁ ወደድን።

🔖​የቴስላን ሕይወት፣ ፈጠራዎች እና አስገራሚ ሚስጥሮች በአጫጭር ክፍሎች ከፋፍለን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦

​📌 ክፍል 1፦ ትውልድ፣ እድገት እና ያ አስፈሪ የልጅነት ትምህርት

• ​ልደቱ፦ ቴስላ የተወለደው እ.ኤ.አ. ጁላይ 10 ቀን 1856 በሰርቢያዊያን ቤተሰቦች ውስጥ (በአሁኗ ክሮኤሺያ) ስሚልጃን በተባለች መንደር ነው። በሚገርም ሁኔታ የተወለደው እጅግ ኃይለኛ የነጎድጓድና የመብረቅ ማዕበል በነበረበት እኩለ ሌሊት ላይ ነበር። አዋላጇ እናቱ “ይህ ልጅ የጨለማ ልጅ ይሆናል” ስትል፣ እናቱ ግን “አይደለም፣ የብርሃን ልጅ ነው የሚሆነው!” ብላ ተነበየችለት።
• ​ትምህርቱ፦ ቴስላ የሚገርም የማስታወስ እና የማሰብ ችሎታ (Photographic Memory) ነበረው። በኦስትሪያ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ትምህርቱን ሲከታተል፣ ውስብስብ የሂሳብ ቀመሮችን (Calculus) ያለምንም ስክሪፕት በጭንቅላቱ ብቻ ሰርቶ ይጨርስ ስለነበር መምህራኑ ያጭበረብራል ብለው ይጠረጥሩት ነበር። በቀን 2 ሰዓት ብቻ በመተኛት ትምህርቱን በጥልቀት ያጠና ነበር።

​📌  ዝንባሌ፣ ፈጠራዎቹ እና “የነዳጅ ፍሰት ጦርነት”
• ​መቼ፣ የት፣ ምን ፈጠረ? ቴስላ በ1884 ወደ አሜሪካ ተሰደደ። በወቅቱ ዝነኛው ቶማስ ኤዲሰን የዲሲ (Direct Current) ኤሌክትሪክን ይዞ ገበያውን ተቆጣጥሮት ነበር። ነገር ግን የኤዲሰን ዲሲ ኤሌክትሪክ ከአንድ ማይል በላይ መጓዝ አይችልም ነበር።
• ​የ-AC ሲስተም እመርታ (1887-1888፣ አሜሪካ)፦ ቴስላ ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ፍሰት (Alternating Current - AC) እና ኢንደክሽን ሞተርን ፈጠረ። ይህ ሲስተም ኤሌክትሪክን በከፍተኛ ቮልቴጅ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን በደህንነት ማጓዝ የሚችል ነበር። ይህ ፈጠራው ዛሬ መላው ዓለም፣ ፋብሪካዎችና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ለሚጠቀሙበት የኤሌክትሪክ ኃይል ዋናው መሠረት ነው።
• ​የቴስላ ኮይል (1891)፦ በገመድ አልባ መንገድ ኤሌክትሪክን ለማስተላለፍ የፈጠረው ማሽን ሲሆን፣ ለዘመናዊው ሬዲዮ፣ ኤክስሬይ (X-Ray) እና የርቀት መቆጣጠሪያ (Remote Control) መፈጠር በሩን ከፍቷል።

ይቀጥላል ...

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤7👏2