Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
528 files
3.76K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉የምስራች ከ @ETCONp
ከታች ካሉት ሶፍትዌሮች በደንብ የምትችሉት አንዱ በመምረጥ በውስጥ ፃፉልን ስራ ልንፈጥርላቹ ነው👇

💻Ms Project
💻Civil 3D
💻 Etabs With Safe
💻Advanced Structural Design Using ETABS, SAFE and SAP2000
💻Structural Design in ProtaStructure Software
💻Autocad
💻Sap2000
💻Autodesk Revit Architecture
💻Primavera P6

📩 @Philemona7 ፃፉልን ወይም በ 0925446661 ይደውሉልን🙏

@etconp
👏5❤2
👉እናስተዋዉቃችሁ

​🌟 ቅዳሜን ከታላላቅ መሐንዲሶች ጋር፦
“ኒኮላ ቴስላ” የብርሃኑ እና የገመድ-አልባው ዓለም ጠቢብ
​
🪧ለዛሬው የቅዳሜ “እናስተዋውቃችሁ” ዓምዳችን፣ በአሁኑ ዘመን ለምንኖርበት ዘመናዊ የኢንጂነሪንግ እና የኤሌክትሪክ ስልጣኔ መሠረት የጣለውን፣ ነገር ግን በታሪክ ብዙም ሳይዘመርለት ያለፈውን ታላቅ ሳይንቲስት እና መሐንዲስ ኒኮላ ቴስላን (Nikola Tesla) ልናስተዋውቃችሁ ወደድን።

🔖​የቴስላን ሕይወት፣ ፈጠራዎች እና አስገራሚ ሚስጥሮች በአጫጭር ክፍሎች ከፋፍለን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦

​📌 ክፍል 1፦ ትውልድ፣ እድገት እና ያ አስፈሪ የልጅነት ትምህርት

• ​ልደቱ፦ ቴስላ የተወለደው እ.ኤ.አ. ጁላይ 10 ቀን 1856 በሰርቢያዊያን ቤተሰቦች ውስጥ (በአሁኗ ክሮኤሺያ) ስሚልጃን በተባለች መንደር ነው። በሚገርም ሁኔታ የተወለደው እጅግ ኃይለኛ የነጎድጓድና የመብረቅ ማዕበል በነበረበት እኩለ ሌሊት ላይ ነበር። አዋላጇ እናቱ “ይህ ልጅ የጨለማ ልጅ ይሆናል” ስትል፣ እናቱ ግን “አይደለም፣ የብርሃን ልጅ ነው የሚሆነው!” ብላ ተነበየችለት።
• ​ትምህርቱ፦ ቴስላ የሚገርም የማስታወስ እና የማሰብ ችሎታ (Photographic Memory) ነበረው። በኦስትሪያ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ትምህርቱን ሲከታተል፣ ውስብስብ የሂሳብ ቀመሮችን (Calculus) ያለምንም ስክሪፕት በጭንቅላቱ ብቻ ሰርቶ ይጨርስ ስለነበር መምህራኑ ያጭበረብራል ብለው ይጠረጥሩት ነበር። በቀን 2 ሰዓት ብቻ በመተኛት ትምህርቱን በጥልቀት ያጠና ነበር።

​📌  ዝንባሌ፣ ፈጠራዎቹ እና “የነዳጅ ፍሰት ጦርነት”
• ​መቼ፣ የት፣ ምን ፈጠረ? ቴስላ በ1884 ወደ አሜሪካ ተሰደደ። በወቅቱ ዝነኛው ቶማስ ኤዲሰን የዲሲ (Direct Current) ኤሌክትሪክን ይዞ ገበያውን ተቆጣጥሮት ነበር። ነገር ግን የኤዲሰን ዲሲ ኤሌክትሪክ ከአንድ ማይል በላይ መጓዝ አይችልም ነበር።
• ​የ-AC ሲስተም እመርታ (1887-1888፣ አሜሪካ)፦ ቴስላ ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ፍሰት (Alternating Current - AC) እና ኢንደክሽን ሞተርን ፈጠረ። ይህ ሲስተም ኤሌክትሪክን በከፍተኛ ቮልቴጅ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን በደህንነት ማጓዝ የሚችል ነበር። ይህ ፈጠራው ዛሬ መላው ዓለም፣ ፋብሪካዎችና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ለሚጠቀሙበት የኤሌክትሪክ ኃይል ዋናው መሠረት ነው።
• ​የቴስላ ኮይል (1891)፦ በገመድ አልባ መንገድ ኤሌክትሪክን ለማስተላለፍ የፈጠረው ማሽን ሲሆን፣ ለዘመናዊው ሬዲዮ፣ ኤክስሬይ (X-Ray) እና የርቀት መቆጣጠሪያ (Remote Control) መፈጠር በሩን ከፍቷል።

ይቀጥላል ...

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤7👏2
☄ውድ ቤተሰቦቻችን

👉ዋናው የ ኮንስትራክሽን ጉዳዮች የሚዳሰስበት መፅሃፍት ቪድዮዎች እና ትምህርቶች ምናጋራበት ቻናላችን ካልተቀላቀሉ ብዙ ነገር ኣምልጦታል እና ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ጆይን ኣርገው ቤተሰብ ይሁኑ ለወዳጅዎ ይጋብዙ👇

https://t.me/ETCONp
❤3🥰2👍1👏1
👉የ2018 በጀት ዓመት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የሴክተር ጉባኤ  ተካሄደ

የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም  ክልል የዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እና የተጠሪ ተቋማት የስራ  ሃላፊዎች  በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ  በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት  የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ጫልቱ ሳኒ  የሀገሪቱን ከተሞች ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ለማሻገር ከመቸውም ጊዜ በላይ መልካም ዕድልና አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል።

የከተሞች የመልማት ዕድል ተጠቅሞ የየትኛውም የከተማ አመራር ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል ክብርት ሚኒስትር።

የከተማ ልማት ሥራ ባለ ብዙ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ በመሆኑ የኢንዱስትሪ፣ የገበያ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረተ ልማትና አገልግሎቶችን በቅንጅት፣ በትስስርና በተመጋጋቢነት በውስጥም ሆነ ከአካባቢው በጋራና ትብብር በመፍጠር መምራትን የሚጠይቅ  ከፍተኛ ኃላፊነት ነው ብለዋል ክብርት ሚኒስትሯ፡፡

ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው በርካታ ስራዎች መካከል የከተሞችን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ፣ ግልፅነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት የመሬት ልማትና ማኔጅመንት በማጎልበት፣ ከከተሞች ገፅታ መቀየር፣ ነዋሪውን የቤት ባለቤት እንዲሆን ከማድረግ ጋር የተያያዘ የቤት ልማት ፕሮግራም በመተግበር፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ተወዳዳሪ ከተሞች መፍጠር ነው ብለዋል ክብርት ሚኒስትር።

በፕላን የሚመሩና ደረጃቸውን የጠበቁ ከተሞችና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እንዲኖሩና አገልግሎቶችን በአግባቡ እንዲቀርቡና እንዲዘምኑ እንዲሁም የነዋሪው እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር በማድረግ፣ የከተሞችን መሰረተ ልማት በማስፋፋት እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እንዲያፋጥኑ በማድረግ ረገድ ከባለፉት ዓመታት በተሸለ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ክብርት ሚኒስትሯ ገልጸዋል ፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ የሀገሪቱን ከተሞች ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ለማሻገር ከመቸውም ጊዜ በላይ መልካም ዕድልና አጋጣሚ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ይህንን መልካም የከተሞች የመልማት ዕድል ተጠቅሞ የየትኛውም የከተማ አመራር ትኩረት ሰጥቶ ሊተገብረው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ከቡር መስፍን መንዛ( ዶ/ር) የአርባ ምንጭ ከተማ  በተፈጥሮ መስህብ፣ ለቱርሲት ጎብኝዎች እጅግ የታደለች ከተማ ከመሆኗ በላይ የሰላምና የፍቅር ከተማ መሆኗን ጠቅሰው ዘመኑ የከተሞች የመልማት ዘመን በመሆኑ በሀገር ውስጥም ሆነ በሀገር ውጭ ያሉ ዜጎች ሀብታቸውን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ  አፈጻጸምና የቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫን የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን በዝረዝር አቅርበዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  ለሁሉም ክልሎች ባደረገው ክትትልና ድጋፍ ከተሞች ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገቡ እደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡
ለዚህም ማሳያው በኮሪደር ልማት፣ በሌማት ቱርፋት፣ በገበታ ለሀገር እዲሁም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እየተመዘገበ የመጣው ዕድገት በአጠቃላይ የከተማው አመራር ካለፉት ዓመታት በበለጠ ለከተማ ስራ ትኩረት ሰጥቶ መስራት በመቻላቸው ነው ብለዋል፡፡

አዲሱ የከተማ ልማት  ፖሊሲ በአማን አሰፋ (ዶ/ር) የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ(ዶ/ር) ቀርቦ  ዉይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም የ2019 በጀት ዓመት እቅድን የጋራ በማድረግ የመግባቢያ ሰነድ ክልሎች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በመፈራረም መርሀ ግብሩ ተጠናቋል።

@etconp
❤7
​🌐 የዓለማችን እጅግ አስገራሚ 4 ህንፃዎች

🔖ዛሬ በግንባታ ጥበብ ውስጥ የተፈጠሩ፣ የሰው ልጅን የፈጠራ ችሎታ ወደ ሌላ ደረጃ ያሸጋገሩ አስገራሚ ህንፃዎችን እናስጎበኛችሁ።

​1. ኩርባው ህንፃ (The Crooked House) - ፖላንድ 🇵🇱

​ይህ ህንፃ የካርቱን ምስል እንጂ እውነተኛ ህንፃ አይመስልም። የተገነባው በአርቲስቶች ስዕል ተመስጦ ነው።
ግድግዳዎቹ፣ መስኮቶቹና ጣሪያው ሁሉ የታጠፉ ይመስላሉ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አገልግሎት የሚሰጥ የገበያ ማዕከል ነው።

​2. የሎተስ ቤተ መቅደስ (Lotus Temple) - ህንድ 🇮🇳

​የሎተስ አበባን ቅርፅ በመያዝ የተገነባው ይህ ህንፃ፣ በዓለማችን እጅግ ውብ ከሆኑ የኪነ-ህንፃ ስራዎች አንዱ ነው።
27 ነጭ እብነበረድ የተሸፈኑ የ"ፔታል" ቅርጾች ያሉት ሲሆን፣ በማንኛውም ሃይማኖት ላለ ሰው ክፍት ነው። ይህ ህንፃ ምንም አይነት ቀጥተኛ ግድግዳ የለውም!

​3. የዳንሲንግ ሃውስ (Dancing House) - ቼክ ሪፐብሊክ 🇨🇿

​በፕራግ ከተማ የሚገኝ ይህ ህንፃ ሁለት አብረው የሚደንሱ ሰዎችን ይመስላል።
አንዱ ክፍል እንደ ወንድ፣ ሌላኛው ደግሞ እንደ ሴት ዳንሰኛ ተደርጎ የተሰራው ይህ የቢሮ ህንፃ፣ በዘመናዊው እና በጥንታዊው የከተማዋ የግንባታ ስልት መካከል ልዩ ድምቀት አለው።

​4. የቅርጫት ህንፃ (The Basket Building) - አሜሪካ 🇺🇸

​ኩባንያው የገነባው ይህ ህንፃ፣ ልክ እንደ ግዙፍ የእጅ ጥበብ ቅርጫት ይታያል። አምስት ፎቅ ያለው ሲሆን፣ የህንፃው እጀታዎች (Handles) እንኳን ሳይቀር በትክክል ተገንብተው የቅርጫቱን ቅርፅ በሚገባ አሳይተዋል።

የግንባታ ጥበብ ምን ያህል ፈጠራ ሊጨመርበት እንደሚችል ትልቅ ማሳያ ነው።

​💡 የተገነባው መቼ ነው? ለምን ዓላማ? የሚለውን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን!

​#Architecture #Engineering #AmazingBuildings #Construction #Design #EthioCon
​
@etconp
❤16👍2
👉ስለ ኮንስትራክሽን ስዕሎች ማብራሪያ (Construction Drawings Explained) ይፈልጋሉ?

👷‍♂የኮንስትራክሽን ስዕሎች የማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክት ቋንቋ ናቸው። ዲዛይኑን በግልጽ ሁኔታ በማስተላለፍ ፕሮጀክቱ በደህንነት፣ በትክክለኛነት እና በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲገነባ ያግዛሉ።

❇️ዋና ዋና የኮንስትራክሽን ስዕሎች/Main Types of Construction Drawings:

✏ፕላን (Plan)

• የሕንፃውን አቀማመጥ፣ መጠኖች፣ Grid Lines፣ ግድግዳዎች፣ አምዶች፣ ክፍተቶች፣ መሳሪያዎች እና የደረጃ መረጃዎችን ያሳያል።

✂️ሴክሽን (Section)

• ሕንፃውን በቁመት ተቆርጦ በሚታይበት መልኩ መሠረት፣ ወለሎች፣ መዋቅራዊ ክፍሎች እና ቁሳቁሶችን ያሳያል።

🪧ኤሌቬሽን (Elevation)

• የሕንፃውን ውጫዊ ገጽታ፣ ከፍታ፣ በሮች፣ መስኮቶች፣ ፊኒሽ እና የጣሪያ ቅርጽን ያሳያል።

📎ዲቴይል (Detail)

• የአስፈላጊ ክፍሎችን፣ ግንኙነቶችን፣ የብረት ዝርዝር፣ ቁሳቁሶችን እና የግንባታ ዘዴዎችን በትልቅ ስኬል ያቀርባል።

🏷ማስታወሻዎች (Notes)

• ደረጃዎች፣ ቴክኒካዊ መስፈርቶች፣ የስህተት ገደቦች፣ የደህንነት መመሪያዎች፣ የግንባታ ቅደም ተከተል እና ልዩ መመሪያዎችን ይይዛሉ።

💫ጥሩ የኮንስትራክሽን ስዕሎች/Why are they important?

✔️ ግራ መጋባትን ይቀንሳሉ/Reduce misunderstandings
✔️ የድጋሚ ሥራን ያስወግዳሉ/ Minimize costly rework
✔️ የፕሮጀክት መዘግየትን ይቀንሳሉ/Prevent construction delays
✔️ የጥራትና የደህንነት ደረጃን ያሻሽላሉ/Improve quality and safety
✔️ የፕሮጀክት ስኬትን ያረጋግጣሉ/Ensure successful project delivery

🔖ግልጽ ስዕሎች + ግልጽ ማስታወሻዎች = ቀላል ግንባታ + የተሻለ የፕሮጀክት ውጤት::

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤8👏2
👉የስራ ማስታወቂያ

🔖በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ ከዚህ በላይ ለተገለጹ የስራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

❇️የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
📍የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

💫ማሳሰቢያ

• የምዝገባ ሁኔታ፡ በኦን ላይን፡- https://tinyurl.com/IPDC-CDB-Vacancy6

• ለሥራ መደቡ የሚያስፈልጉ የትምህርት ፤ሥራ ልምድ እና ሌሎች  ማስረጃዎች ወደ ፒዲኤፍ/pdf በመቀየር በአንድ ፋይል ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
• በስራ መደቡ ላይ የልዩ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ ዋጋ ያሰጣል
• ደመወዝ ፡- በኮርፖሬሽኑ ደመወዝ ስኬል መሰረት
• የምዝገባ ቀን ፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ፡፡
• አመልካቾች ከስራ መደቡ ጋር ቀጥተኛ የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ከግል ድርጅቶች የሚቀርብ ስራ ልምድ ግብር መከፈሉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

📲ስልክ ቁጥር 011 658 22 11

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ

@etconp
🙏3❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 17 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1
ጨረታ

ሪፖርተር ሰኔ 17 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 19 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍1
JOB VACANCY

1. Position: Office Engineer I 🏢
2. Position: Office Engineer II 🏢
3. Position: Site Engineer I 🏗️
5. Position: Site Engineer II 🏗️

Company: EL-HADAR Engineering 👷‍♂️

Education: MSc/BSc in Civil Engineering, COTM, or related field 🎓

Experience: 2 years ⏳

Required Qty: 20 👥

Salary: Attractive 💰

Work Location: Project Site, Addis Ababa 📍

Deadline: July 7, 2026 📅

How to Apply: 📝

Submit comprehensive CV, cover letter, and copies of academic/professional credentials via:- Email: elhadarvacancy@gmail.com 📧

- In person: Addis Ababa, Saint Urael Church, Close to Justice Minister, Kidus Complex, 6th Floor 🏛️

🏷Please Subscribe Our Youtube Channel👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
👏6❤4
👉በግንባታ ላይ ያለው የቦሌው አዲሱ ፈርጥ፦ የሆራ ትሬዲንግ ባለ 25 ፎቅ ሕንፃ

💫የአዲስ አበባ ልብ በሆነውና ሌሊትና ቀን በማይተኛው የቦሌ መንገድ (Bole Avenue)፣ ፍሬንድሺፕ ሕንጻ አጠገብ፣ በአሁኑ ወቅት ገና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ አንድ ግዙፍና አስደናቂ ፕሮጀክት የብዙዎችን ቀልብ እየሳበ ነው፤

የሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ (Horra Corporate Group) በባለቤትነት የሚያስገነባውና ባለ 25 ፎቅ ቁመት የሚኖረው ይህ የሆራ ትሬዲንግ የገበያና የንግድ ማዕከል፣ አዲስ አበባ ወደ ዓለም አቀፍ የንግድና የቱሪዝም ማዕከልነት የምታደርገውን ፈጣን ምጥቀት በግልጽ የሚያሳይ እውነተኛ ማረጋገጫ ነው፤


📐 ታላቅ ስፋት እና የተራቀቀ የሕንጻ ጥበብ በቁጥር

ይህ ግንባታው በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ የሚገኘው ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በይዘቱና በስፋቱ ረገድ በከተማዋ ትልቅ አሻራ የሚያርፍ ነው፤

አጠቃላይ የግንባታ ስፋቱ 127,232 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ አጠቃላይ የወለል ስፋቱ (GFA) ደግሞ 80,933 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው፤


ይህም በውስጡ ፕሪሚየም የገበያ ማዕከል (Shopping Mall)፣ ዘመናዊ የኮርፖሬት ቢሮዎች፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ እንዲሁም የምግብና የመዝናኛ (F&B) ስፍራዎችን በአንድ ላይ አጣምሮ ለመያዝ አስችሎታል፤

የዚህን ማዕከል ዲዛይን የነደፉት HABAR Architects ሲሆኑ፣ ከዓለም አቀፉ የኮንሰፕት ዲዛይን አማካሪ WATG እና በሀገር ውስጥ ካለው KiT Studio PLC Partner Architect of Record ጋር በጋራ በመተባበር ነው፤


የሕንጻው ጥበብ የኢትዮጵያን ታላቅ ተፈጥሮ—ሰማይ ጠቀስ ተራሮቿንና ጥልቅ ሸለቆዎቿን—የሚዘክር ሲሆን፣ በአየር ላይ የተንሳፈፉ የሚመስሉ አካላትን (floating volumes) በማካተት የከተማዋን የስበት ማዕከል ወደላይ የሰቀለ ዲዛይን አለው፤

ሕንጻው በአራቱም አቅጣጫ ካሉት የተለያዩ የከተማዋ ገጽታዎች ጋር—ከኤርፖርት መንገድ ደማቅ የንግድ እንቅስቃሴ ጀምሮ እስከ ደቡባዊው ጸጥተኛ የመኖሪያ መንደር ድረስ—በጥንቃቄ ይዋሃዳል፤


🚀 አዲስ አበባን በዓለም መድረክ ከፍ የሚያደርግ የነገው አሻራ

ይህ ባለ 25 ፎቅ ሕንጻ ገና ተገንብቶ ባይጠናቀቅም፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እየታየ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስትራቴጂክ ዕድገት ተከትሎ የከተማዋን ገጽታ በአንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው አያጠራጥርም፤


ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ ወደ መሀል ከተማ ለሚገባ እንግዳ፣ በስትራቴጂክ ቦታ ላይ የተገነባው ይህ ማዕከል የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መነቃቃትና የወደፊት ራዕይ በኩራት የሚያበስር የመጀመሪያው ደማቅ መግቢያ (Gateway) ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ፣ የቢሮና የሆቴል አገልግሎቶችን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘው የሆራ ትሬዲንግ ማዕከል፣ አዲስ አበባ የኢንቨስትመንትና የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ መናገሻነቷን ይበልጥ የሚያጸናላት የነገው የከተማችን ድንቅ መታወቂያ ነው።

@etconp
❤6
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤5👍1
ጨረታ

አዲስ ዘመን 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤4👍3👏1