Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
528 files
3.76K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ስለ ኮንስትራክሽን ስዕሎች ማብራሪያ (Construction Drawings Explained) ይፈልጋሉ?

👷‍♂የኮንስትራክሽን ስዕሎች የማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክት ቋንቋ ናቸው። ዲዛይኑን በግልጽ ሁኔታ በማስተላለፍ ፕሮጀክቱ በደህንነት፣ በትክክለኛነት እና በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲገነባ ያግዛሉ።

❇️ዋና ዋና የኮንስትራክሽን ስዕሎች/Main Types of Construction Drawings:

✏ፕላን (Plan)

• የሕንፃውን አቀማመጥ፣ መጠኖች፣ Grid Lines፣ ግድግዳዎች፣ አምዶች፣ ክፍተቶች፣ መሳሪያዎች እና የደረጃ መረጃዎችን ያሳያል።

✂️ሴክሽን (Section)

• ሕንፃውን በቁመት ተቆርጦ በሚታይበት መልኩ መሠረት፣ ወለሎች፣ መዋቅራዊ ክፍሎች እና ቁሳቁሶችን ያሳያል።

🪧ኤሌቬሽን (Elevation)

• የሕንፃውን ውጫዊ ገጽታ፣ ከፍታ፣ በሮች፣ መስኮቶች፣ ፊኒሽ እና የጣሪያ ቅርጽን ያሳያል።

📎ዲቴይል (Detail)

• የአስፈላጊ ክፍሎችን፣ ግንኙነቶችን፣ የብረት ዝርዝር፣ ቁሳቁሶችን እና የግንባታ ዘዴዎችን በትልቅ ስኬል ያቀርባል።

🏷ማስታወሻዎች (Notes)

• ደረጃዎች፣ ቴክኒካዊ መስፈርቶች፣ የስህተት ገደቦች፣ የደህንነት መመሪያዎች፣ የግንባታ ቅደም ተከተል እና ልዩ መመሪያዎችን ይይዛሉ።

💫ጥሩ የኮንስትራክሽን ስዕሎች/Why are they important?

✔️ ግራ መጋባትን ይቀንሳሉ/Reduce misunderstandings
✔️ የድጋሚ ሥራን ያስወግዳሉ/ Minimize costly rework
✔️ የፕሮጀክት መዘግየትን ይቀንሳሉ/Prevent construction delays
✔️ የጥራትና የደህንነት ደረጃን ያሻሽላሉ/Improve quality and safety
✔️ የፕሮጀክት ስኬትን ያረጋግጣሉ/Ensure successful project delivery

🔖ግልጽ ስዕሎች + ግልጽ ማስታወሻዎች = ቀላል ግንባታ + የተሻለ የፕሮጀክት ውጤት::

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤8👏2
👉የስራ ማስታወቂያ

🔖በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ ከዚህ በላይ ለተገለጹ የስራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

❇️የቅጥር ሁኔታ ፤ ቋሚ
📍የስራ ቦታ ፤ አዲስ አበባ

💫ማሳሰቢያ

• የምዝገባ ሁኔታ፡ በኦን ላይን፡- https://tinyurl.com/IPDC-CDB-Vacancy6

• ለሥራ መደቡ የሚያስፈልጉ የትምህርት ፤ሥራ ልምድ እና ሌሎች  ማስረጃዎች ወደ ፒዲኤፍ/pdf በመቀየር በአንድ ፋይል ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
• በስራ መደቡ ላይ የልዩ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ ዋጋ ያሰጣል
• ደመወዝ ፡- በኮርፖሬሽኑ ደመወዝ ስኬል መሰረት
• የምዝገባ ቀን ፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ፡፡
• አመልካቾች ከስራ መደቡ ጋር ቀጥተኛ የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ከግል ድርጅቶች የሚቀርብ ስራ ልምድ ግብር መከፈሉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

📲ስልክ ቁጥር 011 658 22 11

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን ልማት ቢዝነስ ዘርፍ

@etconp
🙏3❤2
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 17 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤1
ጨረታ

ሪፖርተር ሰኔ 17 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 19 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 22 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 20 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
ጨረታ

አዲስ ዘመን ሰኔ 21 ቀን 2018
ዓ. ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
👍1
JOB VACANCY

1. Position: Office Engineer I 🏢
2. Position: Office Engineer II 🏢
3. Position: Site Engineer I 🏗️
5. Position: Site Engineer II 🏗️

Company: EL-HADAR Engineering 👷‍♂️

Education: MSc/BSc in Civil Engineering, COTM, or related field 🎓

Experience: 2 years ⏳

Required Qty: 20 👥

Salary: Attractive 💰

Work Location: Project Site, Addis Ababa 📍

Deadline: July 7, 2026 📅

How to Apply: 📝

Submit comprehensive CV, cover letter, and copies of academic/professional credentials via:- Email: elhadarvacancy@gmail.com 📧

- In person: Addis Ababa, Saint Urael Church, Close to Justice Minister, Kidus Complex, 6th Floor 🏛️

🏷Please Subscribe Our Youtube Channel👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp
👏6❤4
👉በግንባታ ላይ ያለው የቦሌው አዲሱ ፈርጥ፦ የሆራ ትሬዲንግ ባለ 25 ፎቅ ሕንፃ

💫የአዲስ አበባ ልብ በሆነውና ሌሊትና ቀን በማይተኛው የቦሌ መንገድ (Bole Avenue)፣ ፍሬንድሺፕ ሕንጻ አጠገብ፣ በአሁኑ ወቅት ገና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኝ አንድ ግዙፍና አስደናቂ ፕሮጀክት የብዙዎችን ቀልብ እየሳበ ነው፤

የሆራ ኮርፖሬት ግሩፕ (Horra Corporate Group) በባለቤትነት የሚያስገነባውና ባለ 25 ፎቅ ቁመት የሚኖረው ይህ የሆራ ትሬዲንግ የገበያና የንግድ ማዕከል፣ አዲስ አበባ ወደ ዓለም አቀፍ የንግድና የቱሪዝም ማዕከልነት የምታደርገውን ፈጣን ምጥቀት በግልጽ የሚያሳይ እውነተኛ ማረጋገጫ ነው፤


📐 ታላቅ ስፋት እና የተራቀቀ የሕንጻ ጥበብ በቁጥር

ይህ ግንባታው በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ የሚገኘው ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በይዘቱና በስፋቱ ረገድ በከተማዋ ትልቅ አሻራ የሚያርፍ ነው፤

አጠቃላይ የግንባታ ስፋቱ 127,232 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ አጠቃላይ የወለል ስፋቱ (GFA) ደግሞ 80,933 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው፤


ይህም በውስጡ ፕሪሚየም የገበያ ማዕከል (Shopping Mall)፣ ዘመናዊ የኮርፖሬት ቢሮዎች፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ እንዲሁም የምግብና የመዝናኛ (F&B) ስፍራዎችን በአንድ ላይ አጣምሮ ለመያዝ አስችሎታል፤

የዚህን ማዕከል ዲዛይን የነደፉት HABAR Architects ሲሆኑ፣ ከዓለም አቀፉ የኮንሰፕት ዲዛይን አማካሪ WATG እና በሀገር ውስጥ ካለው KiT Studio PLC Partner Architect of Record ጋር በጋራ በመተባበር ነው፤


የሕንጻው ጥበብ የኢትዮጵያን ታላቅ ተፈጥሮ—ሰማይ ጠቀስ ተራሮቿንና ጥልቅ ሸለቆዎቿን—የሚዘክር ሲሆን፣ በአየር ላይ የተንሳፈፉ የሚመስሉ አካላትን (floating volumes) በማካተት የከተማዋን የስበት ማዕከል ወደላይ የሰቀለ ዲዛይን አለው፤

ሕንጻው በአራቱም አቅጣጫ ካሉት የተለያዩ የከተማዋ ገጽታዎች ጋር—ከኤርፖርት መንገድ ደማቅ የንግድ እንቅስቃሴ ጀምሮ እስከ ደቡባዊው ጸጥተኛ የመኖሪያ መንደር ድረስ—በጥንቃቄ ይዋሃዳል፤


🚀 አዲስ አበባን በዓለም መድረክ ከፍ የሚያደርግ የነገው አሻራ

ይህ ባለ 25 ፎቅ ሕንጻ ገና ተገንብቶ ባይጠናቀቅም፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እየታየ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስትራቴጂክ ዕድገት ተከትሎ የከተማዋን ገጽታ በአንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው አያጠራጥርም፤


ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ ወደ መሀል ከተማ ለሚገባ እንግዳ፣ በስትራቴጂክ ቦታ ላይ የተገነባው ይህ ማዕከል የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መነቃቃትና የወደፊት ራዕይ በኩራት የሚያበስር የመጀመሪያው ደማቅ መግቢያ (Gateway) ሆኖ ያገለግላል፤ የንግድ፣ የቢሮና የሆቴል አገልግሎቶችን በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘው የሆራ ትሬዲንግ ማዕከል፣ አዲስ አበባ የኢንቨስትመንትና የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ መናገሻነቷን ይበልጥ የሚያጸናላት የነገው የከተማችን ድንቅ መታወቂያ ነው።

@etconp
❤6
ጨረታ

ኢትዮጵያን ሄራልድ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤5👍1
ጨረታ

አዲስ ዘመን 24 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም ላይ የተወሰደ

https://t.me/ETCONpWORK

@etconp
❤4👍3👏1
⚠️ የኮንስትራክሽን ኪሳራ ከየት ይጀምራል? ከአሰሪው “ቅበላ” ወይንስ ከኮንትራክተሩ ጥራት?

​በኢንጅነር ደሳለኝ ከበደ ፅሁፍ የጀመርነው ትንተና ሌላ ዋና ባለድርሻ እንድናስብ አደረገን።

አሰሪው (Client) ዝም ብሎ ተመልካች መሆን የለበትም፤ ኃላፊነት አለበት። በተለይ መቶ ሚሊዮን የተገመተን ፕሮጀክት በሰባ ሚሊዮን “ሲቀበል” (Underbidding ሲደረግ) ኪሳራው ገና ሳይት ሳይገባ በወረቀት ላይ ተፈርሟል ማለት ነው።

​ባለፈው በአማካሪዎች ድክመት ዙሪያ ያነሳነው ነጥብ እንዳለ ሆኖ፣ ሌላውና ትልቁ የዘርፉ በሽታ የሚጀምረው ከራሱ ከአሰሪው (Client) ነው። አሰሪው “ፕሮጀክቴ የት ላይ ነው? ምን እየተሰራ ነው?” ብሎ የመከታተል ብቻ ሳይሆን፣ ገና በጨረታው ወቅት የሚሰራው ስህተት ለፕሮጀክቱ መክሸፍ ትልቅ ምክንያት ነው።

​ለምሳሌ ያህል፦

​💰 በአግባቡ ተጠንቶ 100 ሚሊዮን ብር ይፈጃል የተባለውን ግንባታ፣ አሰሪው ወጪ ለመቀነስ ብቻ በማሰብ ወይም በጥናት ላይ ባልተመሰረተ ፉክክር በ70 ሚሊዮን ብር ተደራድሮ “ሲቀበለው” ችግሩ ከዚያው ይጀምራል!

​ይህ በምህንድስናው ዓለም "Underbidding" (ካለ አግባብ ዋጋን መስበር) የሚባለው አካሄድ የሚያስከትላቸው አስከፊ መዘዞች፦

1. ​📉 ጥራትን መበለዝ፦ ኮንትራክተሩ ከኪሳራ ለመዳን ሲል ማቴሪያልና የሙያ ጥራትን ለመቀነስ ይገደዳል።
2. ​⏳ የተጓተቱ ፕሮጀክቶች፦ በሂደት ላይ የገንዘብ እጥረት (Cash Flow) ስለሚገጥም ስራው ይቆማል፤ በመጨረሻም አሰሪው ካሰበው በላይ ለወጪና የጊዜ ብክነት ይጋለጣል ።
3. ​🤝 የ "Plan vs. Site" አለመጣጣም፦ ጥራቱ ያልተጠበቀ ጨረታ በመጨረሻም በወረቀት ላይ ያለው ፕላን እና ሳይት ላይ የሚሰራው ጉድኝት እንዳይገጥም ያደርገዋል::

​የናሽናል ኮንስትራክሽን ሚዲያ መልዕክት፦
አሰሪው ዝቅተኛ ዋጋ ስላገኘ ብቻ ያሸነፈ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል! ጥራት ያለው ግንባታ የሚገኘው ተገቢው ዋጋ ለተገቢው ባለሙያና ማቴሪያል ሲሰጥ ብቻ ነው። አሰሪዎች ዋጋ ከመቁረጥ ባለፈ “ፕሮጀክቴ የት ላይ ነው?” ብለው ጥራቱን የመቆጣጠር ትልቅ የቤት ስራ አለባቸው።

​📱 ባለሙያዎች ምን ትላላችሁ?
ይህ 100 ሚሊዮን የተገመተን ስራ በ70 ሚሊዮን ብር የመቀበል ልምድ በሃገራችን ኮንስትራክሽን ላይ ምን ያህል ጉዳት እያደረሰ ነው? መፍትሔውስ ምንድነው?
​ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇

@etconp
❤9👍7
👉የኮንስትራክሽን ኮንትራክት አስተዳዳሪ (Construction Contract Administrator / Contract Management Expert) ዋና ኃላፊነቱና የስራ ድርሻው ምንድን ነው?

💫የኮንስትራክሽን ኮንትራክት አስተዳዳሪ (Construction Contract Administrator / Contract Management Expert) ዋና ኃላፊነቱ የግንባታ ውል ከመዘጋጀት እስከ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ድረስ ውሉ በትክክል እንዲፈጸም ማስተዳደር ነው።

🚧ዋና ዋና የስራ ድርሻዎች
---------——------—---------
✏️የኮንትራት ሰነዶችን ማዘጋጀትና መገምገም።
✏️የጨረታ ሂደትን መደገፍ (Tender Administration)።
✏️ከተቋራጩ ጋር የተፈረመውን ውል መከታተል።
✏️የስራ ለውጦችን (Variation Orders) ማስተዳደር።
✏️የክፍያ ማመልከቻዎችን መመርመርና ማረጋገጥ።
✏️የጊዜ ማራዘሚያ (Extension of Time) ጥያቄዎችን መገምገም።
✏️የውል ግጭቶችንና ክርክሮችን መፍታት።
✏️የፕሮጀክት ሪፖርቶችን ማዘጋጀት።
✏️የውል ህጎችን፣ መመሪያዎችንና ደንቦችን ማስከበር።
✏️ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የመጨረሻ ሂሳብ (Final Account) ማዘጋጀትና ውሉን መዝጋት።

📎አብሮ የሚሰራቸው
-----------—-----—---
🎤የፕሮጀክት ማኔጀር
🎤የሳይት ኢንጅነር
🎤የቁጥር መሐንዲስ (Quantity Surveyor)
🎤የግዥ ባለሙያ
🎤የሕግ አማካሪ
🎤ተቋራጭ (Contractor)
🎤አማካሪ (Consultant)
🎤የፕሮጀክት ባለቤት (Client)

🔖ሊያውቃቸው የሚገቡ ክህሎቶች

✏️የኮንትራት ህግ
✏️የግንባታ አስተዳደር
✏️የዋጋ ግምትና ክፍያ
✏️ድርድር (Negotiation)
✏️ሪፖርት ጽሑፍ
✏️የፕሮጀክት መርሃ ግብር አስተዳደር

✂️በአጭሩ፦ የኮንስትራክሽን ኮንትራክት አስተዳዳሪ የፕሮጀክቱ ውል በጊዜ፣ በበጀት፣ በጥራት እና በህጋዊ መስፈርቶች መሠረት እንዲፈጸም የሚያስተዳድር ቁልፍ ባለሙያ ነው።

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp
❤11👏4
​👉የሀገራችን ኩራት፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ዋና መሥሪያ ቤት—የምሥራቅ አፍሪካው የሰማይ ጠቀስ አሻራ!

💫​በዋና ከተማችን አዲስ አበባ እምብርት ላይ ግርማ ሞገሱን ተላብሶ የሚታየው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ፣ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካን ዘመናዊ አርክቴክቸርና የኢንጂነሪንግ ዕድገት በጉልህ የሚያሳይ ግዙፍ መዋቅር ነው።

🚧​በፈረንጆቹ ፌብሩዋሪ 13፣ 2022 እ.ኤ.አ. በይፋ የተመረቀው ይህ የምህንድስና ውጤት፣ በኢትዮጵያና በምሥራቅ አፍሪካ ረጅሙ ህንፃ በመሆን ቀዳሚነቱን የያዘ ሲሆን፣ ከደቡብ አፍሪካ ውጭ ባለው ከሰሃራ በታች ባለው የአፍሪካ ክፍለ-ሀገር (Sub-Saharan Africa) ረጅሙ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ (Skyscraper) በመሆን በታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።

​📐 የዚህ ሜጋ ፕሮጀክት አስደናቂ የኢንጂነሪንግ እውነታዎች፦

• ​ቁመትና ይዘት፦ ህንፃው በድምሩ 209.15 ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን፣ 46 ወለሎችን (ፎቆችን) ከመሬት በላይ፣ እንዲሁም 4 የከርሰ-ምድር (Basement) ወለሎችን በውስጡ ይዟል።

• ​ጽኑ ንዑስ-መዋቅር (Massive Substructure)፦ እንዲህ ዓይነቱን ግዙፍና ረጅም ህንፃ በጽኑ መሸከም እንዲችል፣ ሳይት ላይ የተሠራው የኮንክሪት መሠረት (Raft Foundation) እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ብረትና ሲሚንቶ የተፈጀበት ሲሆን፣ በሀገራችን የሰብ-ስትራክቸር ግንባታ ታሪክ ትልቅ ልምድ የተገኘበት ፕሮጀክት ነው።

• ​የፊት ገጽታ አርክቴክቸር (Facade Engineering)፦ የህንፃው ውጫዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ ዘመናዊና ሃይል ቆጣቢ በሆኑ መስታወቶች (Curtain Wall) የተሸፈነ ሲሆን፣ ለአዲስ አበባ ከተማ ዘመናዊና ውብ ገጽታን ሰጥቷታል።

​🧠 ​ይህ የሀገራችን ታላቅ መዋቅር፣ እኛ በኮንስትራክሽንና በመሠረተ-ልማት ዘርፍ ላይ ያለን መሐንዲሶችና የስትራተጂክ መሪዎች የወደፊቱን የከተማ ዕድገት እንዴት መምራት እንዳለብን ትልቅ ማረጋገጫ ነው፦

• ​🎯 የ«Plan vs. Site» ስኬት፦ እንዲህ ያሉ ግዙፍ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን በሀገር ውስጥ ስንገነባ፣ ከንድፍ (Design) ጀምሮ ሳይት ላይ እስከሚተገበርበት ጊዜ ድረስ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የፕሮጀክት ማኔጅመንት እና የጥራት ቁጥጥር (Quality Control) የዲሲፕሊን ጥግን ይጠይቃል።

• ​👷‍♂️ የባለሙያዎቻችን አቅም ግንባታ፦ የዚህ ሜጋ ፕሮጀክት ግንባታ በሀገራችን መሐንዲሶች፣ አማካሪዎችና ፎርመኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ የቴክኖሎጂ ሽግግር (Technology Transfer) የፈጠረ በመሆኑ፣ ወደፊት ለሚገነቡት ሌሎች ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ትልቅ የመንደርደሪያ አቅም ሆኖ ያገለግላል።

​💬 ጥያቄ (Engagement Question)፦

​«የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ የምሥራቅ አፍሪካ የቁመት አክሊልን ተቀዳጅቷል።

⏺ለመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማችን እያደገ የመጣውን የሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ግንባታ (Vertical City Growth) ከሀገራችን የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣ የሳይት ሴፍቲ እና የከተማ መሠረተ-ልማት አቅም አንጻር እንዴት ይገመግሙታል? ወደፊትስ ከዚህ የተሻሉ ግዙፍ ህንፃዎችን ለመገንባት ምን ዓይነት የኢንጂነሪንግ ዝግጁነት ያስፈልገናል? ሃሳብዎን ያጋሩን!»


@etconp
❤8👏3
"አንድ መኪና አሸዋ 12ዐ፣ 130 ሺሕ  ገብቷል ፥ በቅርቡ 85 ፣ 90 ሺሕ፤ ከዛ በፊት ደግሞ 70 ሺሕ ነበር " - ህንፃ ገንቢዎች

" የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ብር ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል" - ማህበሩ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ ፈታኝ ከሆነው የነዳጅ ችግር ጋር በተያያዘ የኮንስትራክሽን ግብዓት ዋጋ ከ20 እስከ 40 ሺሕ በላይ መጨመሩን ህንፃ ገንቢዎች እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሃብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ከ60 እስከ 70 ሺሕ ብር ይሸጥ የነበረው አንድ መኪና አሸዋ አሁን ከ12ዐ ሺሕ እስከ 130 ሺሕ ብር መግባቱን ቲክቫህ ኢትየያ ከህንፃ ገንቢዎች ገለጻ ተረድቷል።

ከአሸዋ ባሻገር፣ ከወራት በፊት 60 ሺሕ ብር ሲሸጥ የነበረው አንድ መኪና ጠጠር አሁን ከ85 ሺሕ ብር በላይ መሆኑ ታውቋል።

የግንባታ ድንጋይ ደግሞ፣ በሺዎች የሚቆጠር ጭማሪ አሳይቷል። የሲሚንቶ ዋጋም እስከ ሦስት እጥፍ ጨምሯል።

ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ግብዓት አቅራቢዎች እና ማዕድናት ሀብት ሥራ አሰሪ ባለሃብቶች ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይለማርያም ገቢሳ፣ " በትክክል ጭማሪ አለ። የዛሬ ሦስት ዓመት 12 ሺሕ ይጫን የነበረው 15 ሜትርኩዩብ አንድ መኪና አሸዋ ዛሬ ወደ 90 ሺሕ ብር ገብቷል " ብለዋል።

ለዚህ ከፍተኛ የዋጋ ንረት " የነዳጅም፣ የቢሮ ክራሲም ሰንሰለት " ችግርን እንደ መንስኤ ጠቅሰው፣ እነዚህ ነገሮች ተደምረው አምራች ላልሆኑትም ዋጋ እንዲጨምሩ መንስኤ ስለመሆናቸው አስረድተዋል።

"ለምሳሌ እኛ አሸዋ እናመርታለን። ከሞጆ እና ከዚያም በታች የሚያመጡም በእንዲህ አይነት ዋጋ መሸጥ ግዴታ ሆኖባቸዋል" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

"ለጭማሪው የተለያዩ ችግሮች ይፈጠራሉ። ለምሳሌ በትራንስፖርቴሽን መንገድ ላይ ዝም ብለው ሚዛን ይጨምሩብሃል፤ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍሉሃል። 16 ሜትርኩዩብ መጫን ያለበትን መኪና 10፣ 9 ሜትር ኩዩብ መጫን አለብህ ብለው ያስቸግራሉ" ነው ያሉት።

"በዚህ፣ በዚህ ምክንያት ችግራችን እስከ ታች ድረስ ይወርዳል። ስለዚህ ሳንወድ በግድ ዋጋ እንጨምራለን" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ "የሠራተኛው ደመወዝ መክፈል፤ ነዳጅ መግዛት፣ ለመንግስት ግብር መክፈል አንችልም" ሲሉም ምክንያት ያሉትን አስረድተዋል።

"ነዳጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጣ ጣጣ ነው። አሁን ወደ ዓለም አቀፍ ጉዳይ እየሄደ ነው። የነዳጅ ጉዳይ እኛን ብቻ አይደለም የሚመለከተው" ብለው፣ ነገር ግን በተለያዩ አቅጣጫ የመሰረተ ልማቱን ለማስፋት በተለይ" የጠጠር አምራች ባለሃብቶች ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል ብለን ነው አቤቱታ የምናቀርበው" ብለዋል።

"እነሱን መንግስት ይይልን፤ ከመመሪያ ውጭ አንሆንም፤ ግን በመመሪያ እንዲሆንልን ነው፤ የመንግስት መመሪያ፣ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ አዋጅ ይከበር። በዛ መሰረት ሂደን ለመንግስት መክፈል የሚገባንን ዋጋ ከፍለን ወደ ሀገራችን ልማት እንግባ" ነው ያሉት።

Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ

https://t.me/ETCONp

@etconpwork
❤8😢3
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦቻችን

🏷Ms Project Full Online Course

⛈ክረምት እውቀትዎ እና ሞያዎ ማዳበር ይፈልጋሉ?

🪧ከ ETABS እና Quantity Surveying በተጨማሪ Ms Project ኦንላይን ኮርስ ለማስተማር 1ኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል

📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ይደውሉልን❤️

@etconp
❤4👏2