Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.78K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
🏛️🎬 የፒያሳው ሲኒማ አምፒር – ወርቃማ ትዝታዎች! ✨

በፒያሳ መልሶ ማልማት ምክንያት የፈረሰው ታሪካዊው ሲኒማ አምፒር፣ ለብዙ አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ ሲኒማ 🎥 እና የኪነጥበብ 🎭 መናኸሪያ ሆኖ አገልግሏል። ሕንፃው ዛሬ ባይኖርም፣ በሺዎች ልቦች ውስጥ የተቀረጹት ውብ ትዝታዎቹ ለዘላለም በታሪክ ማህደር ውስጥ ይኖራሉ። ❤️

🥰 ሲኒማ አምፒር ለብዙ ትውልዶች የፍቅር፣ የሳቅ እና የጓደኝነት መገናኛ ነበር። እነዚህን ውብ ቀናት ታስታውሳላችሁ?

🎟️ አዳዲስ ፊልሞች ሲመጡ በፒያሳ የሚታየው ረጅም የቲኬት ሰልፍ።
👨‍👩‍👧‍👦 የቅዳሜና እሁድ ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር የነበሩ የሲኒማ ቀጠሮዎች።
☕🍰 ከፊልም በኋላ በፒያሳ የሚደረጉ የቡናና የኬክ ጨዋታዎች።
🎬 የአንጋፋ ተዋናዮቻችንን ስራዎች በጉጉት የተከታተልንባቸው ውብ ምሽቶች።

🏛️ በ1930ዎቹ መጀመሪያ ዘመን (በጣሊያን ወረራ ወቅት) የተገነባው እና ለ86 ዓመታት ገደማ ያገለገለው ይህ ታሪካዊ ሲኒማ ቤት፣ በአዲስ አበባ የኪነጥበብ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበረው ሲሆን፣ የፒያሳም ዋና መለያ ምልክት ነበር። 🌟

💬👇 የእርስዎ የማይረሳው የሲኒማ አምፒር ትዝታ ምንድን ነው? በኮሜንት ያጋሩን! ❤️🎥

@etconp
❤6😢3👍2💯1
#ADVERTISEMENT

💫የቤቶዎን (የህንፃዎን) የፌንሽንግ ስራ ማሰራት ፈልገዋል? እንግዲያውስ ደሬ የፌንሽንግ ስራ አለን::

*የጅብሰም ስራ
*ዘመናዊ የዉጪ ግርግዳ ቅቦች
*የቀለም ስራዎች
*የመብራት ዝርጋታና ገጠማ(fitting)
*የሴራሚክ ስራ፤እንዲሁም ጠቅላላ የግንባታ የፊንሽንግ ስራዎን እንሰራሎታለን።

📍አድራሻ:  አዲስ አበባ እንዲሁም በሁሉም የክልል ከተሞች እንገኛለን።

📲 0935210071 ወይም 0960332429 ይደውሉልን🙏
❤1
👉​ለግንባታ ዘርፍ ባለሙያዎች እና አልሚዎች በሙሉ🏗️

​የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የኮንስትራክሽን ማዕድናት ቁፋሮና አስተዳደርን የሚመራ አዲስ መመሪያ አወጣ። "የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 191/2018" የተሰኘው ይህ ሰነድ በዘርፉ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለመ ነው።

🚧​ቁልፍ ነጥቦች፦

​📍 የማዕድን አይነቶች
ጥቁር ድንጋይ፣ ገረጋንቲ፣ ቀይ አሸዋ፣ ቀይ አፈር፣ ነጭ የግንብ ድንጋይ፣ የወንዝ አሸዋ፣ ጠጠር እና መሰል ማዕድናት።

​⏳ የፈቃድ ዘመን
​ጥቁር ድንጋይ፦ እስከ 5 ዓመት (በየዓመቱ ይታደሳል)።
​ገረጋንቲ፣ አሸዋና ነጭ ድንጋይ፦ እስከ 2 ዓመት (በየዓመቱ ይታደሳል)።

​🚫 ክልክል ቦታዎች (ቁፋሮ አይፈቀድም)
​ከመኖሪያ መንደሮችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች በ500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ።
​ከወንዝ ዳርቻዎች በ30 ሜትር ራዲየስ ውስጥ።

​ከከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ።

​መቃብር፣ ፓርክ፣ ሃይማኖታዊ ስፍራዎችና ብሔራዊ መታሰቢያዎች አቅራቢያ።

​📋 አልሚዎች ማሟላት ያለባቸው
​የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ (EIA) እና የአዋጭነት ጥናት ማቅረብ።
​ለአካባቢ ጥበቃ ዋስትና የሚሆን የገንዘብ ማስያዣ ማስቀመጥ።

​በየሦስት ወሩ የሥራ አፈጻጸም፣ በየወሩ የገቢ ሪፖርት ማቅረብ።
​የስፋት ማስፋፊያ የሚፈቀደው ቀደም ሲል ከተሰጠው ቦታ 70% ሲያለሙ ብቻ ነው።

​⚠️ ማሳሰቢያ
​ግለሰቦች ለንግድ ላልሆነ የግል ግንባታ በይዞታቸው ማምረት ይችላሉ።

​ለንግድ ዓላማ የሚሰማሩ በሽርክና ወይም በማህበር መደራጀት አለባቸው።

​ሕገ-ወጥ ድርጊት ሲፈጸም ወይም ግዴታን ሲያጓድሉ ፈቃድ ይሰረዛል።

​ለበለጠ መረጃ እና ዝርዝር መመሪያው ለማግኘት የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን ያነጋግሩ።

@etconp
❤4👍1
📢 VACANCY ANNOUNCEMENT


ENJEFO CONSTRUCTION invites qualified and experienced professionals to apply for the following positions for its ongoing building construction projects in Addis Ababa.

Available Positions
1. Site Engineer (2 Positions)
Minimum 6 years of relevant building construction experience.

2. Office Engineer (1 Position)
Minimum 4 years of relevant building construction experience.

3. Foreman (1 Position)
Minimum 10 years of proven building construction experience.

📍 Duty Station: Addis Ababa
💰 Salary: Negotiable, based on qualifications and experience.

How to Apply
Interested and qualified applicants are invited to submit their CV via Telegram to: @enjefo or 0963371366

Application Deadline: July 14, 2026

For future job opportunities and project updates, join our Telegram channel: @enjefocon
❤4
👉በገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የገጠር ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡- የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር

🚧የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፌደራልና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ “የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም” የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምን እየገመገመ ይገኛል።

በገጠር አካባቢዎች የመንገድና የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የግብርና ምርታማነትንና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተነደፈው ይህ ፕሮግራም፤ በአሁኑ ወቅት በ126 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፤ እስካሁን በድምሩ 1 ሺህ 123 የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። በእነዚህ ዘርፈ-ብዙ ሥራዎችም ከ3.4 ሚሊዮን በላይ የገጠሩ ማኅበረሰብ አባላት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

ይህ ተደራሽነት አርሶ አደሩ ምርቱን ያለ እንግልት ወደ ገበያ እንዲያቀርብ ከመደገፉም በላይ፤ እንደ ጤናና ትምህርት ያሉ ወሳኝ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በአቅራቢያው እንዲያገኝ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።

በተጨማሪም የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመኖሩ ምክንያት ከምርት ስብሰባ በኋላ የሚከሰተውን የሰብል ብክነት በከፍተኛ ደረጃ የሚገታው ይህ ፕሮጀክት፤ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል።

Via EBC

@etconp
❤4
@etconp 2018 4TH QUARTER CONSTRUCTION WORKS DIRECT COST.pdf
27.1 MB
🏷በ2018 ዓ.ም አራተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (4th Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።


🏷YouTube👇
https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

🌟Our Main Telegram Chanel👇

https://t.me/ETCONp

@etconp
❤4👍1🔥1
🚜 የከባድ ማሽኖች ንጉሥ፡ የInternational Harvester TD-25 የጀብዱ ታሪክ

🪧​በከባድ ማሽነሪዎች ዓለም ውስጥ አንዳንድ ማሽኖች ዝም ብለው አይሰሩም፤ ታሪክ ይጽፋሉ። International Harvester (IH) TD-25 ደግሞ ከእነዚህ አንዱ ነው።

​🛠 ከውድቀት ወደ ጥንካሬ
​የቀድሞው ሞዴል TD-24 በገበያ ላይ ስኬታማ ቢሆንም፣ የትራንስሚሽን ችግር እና የሲሊንደር ራስ መሰንጠቅ ችግሮች ስም አጥፍተውበት ነበር። IH ይህንን ትምህርት በጥንቃቄ ወሰደ። በ1959 ሲወለድ፣ TD-25 ተራ ማሽን አልነበረም፤ ከባድ ሚዛኖቹን Caterpillar D8H እና Allis-Chalmers HD-21ን ገጥሞ ለማሸነፍ የታለመ ነበር።

​⚙️ የዝግመተ ለውጥ ጉዞ
• ​የመጀመሪያው ብቃት: በ1962 የወጣው TD-25B፣ የፈረስ ጉልበቱን ወደ 240 በማሳደግ የገበያውን አመኔታ አተረፈ።
• ​የቀበጥ ጥግ (TD-25C - 1974): አብዛኞቹ ኦፕሬተሮች የሚያስታውሱት ይህንን የኃይል ማሽን ነው። በ DTI-817B ባለ ስድስት ሲሊንደር ተርቦቻርጅድ ሞተር 285 የፈረስ ጉልበት አቀረበ። የክብደት መጠኑ በሁለት ቶን ጨምሮ፣ ዘመናዊና ውብ ቅርጽን ተላበሰ።

​🏗 ለምን ይወደድ ነበር?
• ​የማይበገር አቅም: በአራት የፍጥነት ደረጃዎች (Powershift) እና በከባድ የሰሌዳ መዋቅር (Heavy tub frame) ለአሰቃቂ ስራዎች የተፈጠረ ነበር።
• ​የኦፕሬተር ምቾት: ሰፊው ካቢኔ፣ የታየው ጥሩ እይታ፣ እና ከሲ ሞዴል በኋላ የመጡት ማሞቂያና አየር ማቀዝቀዣ (AC) ስራን እንደ መዝናኛ አስቀሩት።
• ​ሁለገብነት: ከ18 ጫማ እስከ 13 ጫማ የሚደርሱ የቢላዋ (Blade) አይነቶች፣ እንዲሁም ሪፐር እና ዊንች በመጨመር በሁሉም የሥራ ዘርፍ ተመራጭ ነበር።

@etconp
❤8
🫵JOB VACANCY

📩How to Apply

⏺Interested and qualified applicants who meet the above requirements are invited to submit:
Via email mandbplc@gmail.com

⚡️Application Deadline: July 13, 2026
 
💫Note: Only shortlisted candidates will be contacted.

@etconp
👍6❤1
👉8ኛ ዙር የ40/60 እና 2ኛ ዙር ካፒታል ኘሮጀክት የንግድ ቤት ጨረታ 2ኛ ደረጃ አሸናፊዎች ሸያጭ ውል ጥሪ ማስታወቂያ

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

ሀምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

@etconp
👍3❤1
✅Construction safety net
Size 2×50=6650
✅belak wir 1.5m=245birr kg
✅belak wir 2.5m= 258birr kg
✅wire mesh 2×1 =2500birr

ለድርጅቶች የፕሮፎርማ አገልግሎት እንሠጣለን
   
ስልክ.  0912955969
           0949434363

Telgram = @FAR7957
❤3
ላፍቶ ሆስፒታል አካባቢ ለሚካሄድ አስቸኳይ ግንባታ ሲባል ከጀሞ 1 ወደ ጀሞ 3 የሚወስደው መንገድ ለ15 ቀናት ዝግ እንደሚሆን ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን አስቀድሞ ለመከላከል በላፍቶ ሆስፒታል አካባቢ አስቸኳይ የቦክስ ከልቨርት ግንባታ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።

ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ሲባል ከነገ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዝግ እንደሚደረግ ገልጿል።

በመሆኑም፦

- ከጀሞ አንድ መብራት ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ የሚወስደውን መንገድ የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች፤ በላፍቶ ሆስፒታል ጀርባ አድርገው ወደ ጀሞ ሦስት አደባባይ እንዲጓዙ፤

- ከጀሞ ሦስት አደባባይ ወደ ጀሞ አንድ ሚጓዙ አሽከርካሪዎች፣ በሀጫሉ ሁንዴሳ ጎዳና አድርገው በቫርኔሮ አደባባይ በኩል መጓዝ የሚችሉ መሆኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ ጠቁሟል።

@etconp
❤11
🪧ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ በውል እድሳት ወቅት ማሟላት ያለባቸው👇

👉 ቀደም ሲል የነበራቸውን የውል ስምምነት ሰነድ ፤

👉 ኪራይ ሲከፋሉበት የነበረው የኤሌክትሮኒክስ የክፋያ ሠነድ ፤

👉 የአከራይ እና የተከራይ ማንኛውም መታወቂያ
      
👉 የመኖሪያ ቤት ውሉን የሚያድሰው በወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና  ፤

🔖ኦርጅናል እና ኮፒ ይዘው  መገኘት አለባቸው

@etconp
❤8👍3
👋ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፣ብዙዎቻቹ በጠየቃችሁን መሠረት ብዙ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎች በ ቪዲዮ እንዲሁም በአገራችን ኮድ እና ስታንዳርድ መሰረት እንደ TAKE OFF SHEET፣BOQ፣ SURVEYING ፣ GENERAL KNOWLEDGE እና ሌሎች ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች እና አሰራሮች ይዘን በ YOUTUBE ለእናንተ ለማድረስ  ዝግጅታችንን  እያጠናቀቅ ሰለሆነ በተቻለ መጠን ቢያንስ ከ1000 SUBSCRIBER በላይ ሲጨምር የምንጀምር ይሆናል።

🌟እስከዛው ግን እናንተ ቤተሰቦቻችን የምንጠይቃቹ ከታች ያለውን YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE  በማድረግና ለጓደኞቻቹ በመላክ  ቤተሰብ  እንዲሆኑ ያግዙ።

💫ሊንኩ ይሄው 👇👇👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
👏4
👉የተጫራቹን ድህረ ብቃት ግምገማ (Post-qualification) ሳያደርጉ ለመንግስት ግንባታ ውል መስጠት (Award) በሕግ ፊት ተፈጻሚነት አልባ የሚያደርግ (Voidable) እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅን የሚጥስ ከባድ የአስተዳደር ጥፋት ነው።

💫በመንግስት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ግልጽነትን፣ ጥራትን እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የወጡ የሕግ ማዕቀፎች መጣሳቸውን ያመላክታል።

🚧ድህረ ብቃት ግምገማ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የውል ስምምነት ከመፈጸማቸው በፊት፣ በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ከተፈለገው የቴክኒክ አቅም፣ የሕግ ሰውነት፣ የፋይናንስ አቋም እና ያለፈው የስራ ልምድ አንጻር አሁንም ስራውን በአግባቡ ለመስራት ብቁ መሆኑን የሚያረጋግጡበት ወሳኝ የግምገማ ሂደት ነው።

🪧የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ አሰራሩ ግልጽ፣ ፉክክር የተሞላበት እና አገሪቱ ከምታወጣው ገንዘብ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ውጤት (Value for Money) የሚያስገኝ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት ይላል። የግምገማውን ሂደት አለማለፍ ማለት በመንግስት ግዥ መርሆች መሰረት ተጠያቂነትን የሚያስከትል አደገኛ ስህተት ነው።

🏷ድህረ ብቃት ግምገማ በአግባቡ አለማድረግ ማለት በመንግስት የግንባታ ጨረታዎች ሂደት ውስጥ የህግ የበላይነትን እና ግልጽነትን ለማረጋገጥ የወጡትን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ድንጋጌዎች መጣስ የሚያስከትለውን አስከፊ ውጤት ያሳያል።

#ሕጋዊ_ቅድመ_ሁኔታን_መጣስ፡- የግዥ ሕጉ አሸናፊ የሆነ ተጫራች በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚያስችል የገንዘብ(ፋይናንስ ሪፖርት)፣ የሰው ኃይልና የቴክኒክ አቅም እንዳለው ድህረ-ብቃት (Post-qualification) እንዲጣራ ግዴታ ይጥላል። ይህንን አለማድረግ መሠረታዊ የሆነ የግዥ ሥርዓት መጣስ ነው።

#ተፈጻሚነት_አልባ_መሆን_Voidable_Contract ማለትም በሕግ ፊት ተፈጻሚነት አልባ የሚሆን ውል(Voidable contract) ይሆናል፡- ሕጉ በሚያዘው መንገድና መስፈርት ሳይካሄድ የተሰጠ ውል በመሆኑ፣ ጉዳዩ በሚመለከተው አካል (ፍርድ ቤት ወይም የግዥ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን) ሲታይ ውሉ እንዲፈርስ(Void) ይደረጋል። ውሉ ሕገ-ወጥ ከመሆኑ አንጻር ምንም አይነት የሕግ ከለላ አያገኝም። የድህረ ብቃት ማረጋገጫ ሳይካሄድ የተሰጠ ውል ህጋዊ መሰረት ስለሚጎድለው፣ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል (ለምሳሌ ተወዳዳሪዎች ወይም የህግ አስከባሪ አካላት) ሲቃወሙት በህግ ፊት ውድቅ ሊደረግና የውል ስምምነቱም ሊፈርስ የሚችል (Voidable) ይሆናል።

#የአስተዳደር_ጥፋት_ተጠያቂነት_ወይም_የጥፋቱ_ክብደት፡- ውሳኔውን የሰጡት የመንግስት ግዥ ፈጻሚ አካላት ወይም ኃላፊዎች የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅን ሆን ብለው ወይም በቸልተኝነት በመተላለፋቸው ከባድ የአስተዳደር ቅጣት(እንደ ከሳራ መክፈል፣ ከሥራ መታገድ ወይም በወንጀል መጠየቅ) የሚያስከትል ጥፋት ፈጽመዋል ማለት ነው። ይህ ተግባር የመንግስትን ሀብት አደጋ ላይ የሚጥል፣ ሙስናን ሊጋብዝ የሚችል እና የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መርሆች (ፍትሃዊነት፣ ግልፅነት እና ወጪ ቆጣቢነት) የሚጥስ በመሆኑ በፈጻሚው አካል ላይ አስተዳደራዊ እንዲሁም የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ከባድ ጥፋት ነው።

#አሰራሩን_አላግባብ_መጠቀም_abuse_of_power:- የድህረ-ብቃት ግምገማ አስፈላጊነት ህጋዊነትን ማስጠበቅ ሲሆን ያለ ብቃት ማረጋገጫ የሚሰጥ ውል በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሰረት አሰራሩን አላግባብ መጠቀም (abuse of power) ተብሎ ይታወቃል።

#የሌሎች_ተጫራቾች_ወይም_የሌሎች_ዜጎች_መብት:-የተጎዳው አካል(ሌላ ተጫራች ወይም የመንግስት አካል ወይም ማንኛውም ዜጋ) ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ውሉ በህግ ፊት እንዲሰረዝ (Void) የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዋጁን ተላልፈው ውሉን የሰጡ የመንግስት ሰራኞችና ኃላፊዎች በሙስናና በህግ መተላለፍ ተጠያቂ ይሆናሉ።

@etconp
❤8👏1