Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.78K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ብዝዎች በጠየቃቹን መሰረት የ ETABS ቲቶርያል ቪድዮ በአማርኛ ቋንቋ ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ኣዘጋጅተንላቹዋል።

🫵እንሆ ዛሬ ክፍል 2 ይዘንላቹ መጥተናል👇

https://youtu.be/nI-r7Tbcba4
❤4
👉የኮንስትራክሽን ኮንትራት ህጎች፦ PPA 2011 vs FIDIC 2017 ዋና ዋና አንቀጾች (Clauses) 

🌟​በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለምትሰሩ ባለሙያዎች፣ ተቋራጮችና መሐንዲሶች በኢትዮጵያ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው PPA 2011 (የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ) እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰራበት FIDIC 2017 ዋና ዋና አንቀጾች ልዩነትና ንፅፅር፦

​📌 1. የኮንትራቱ ሰነዶች ቅደም ተከተል (Priority of Documents)
​ሰነዶች ቢጋጩ የትኛው ቅድሚያ ያገኛል?

​PPA 2011 (GCC Clause 2):

​የኮንትራት ስምምነት (Agreement)
​የይሁንታ ደብዳቤ (Letter of Acceptance)
​የተቋራጩ ጨረታ (Bid submission)
​የልዩ ውል ሁኔታዎች (SCC)
​የአጠቃላይ ውል ሁኔታዎች (GCC) 
​ቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን፣ ዲዛይን እና BOQ

​FIDIC 2017 (Sub-Clause 1.5):

​Contract Agreement
​Letter of Acceptance
​Letter of Tender
​Particular Conditions - Part A & Part B
​General Conditions (GCC)
​Specification & Drawings

​📌 2. የመሐንዲሱ/የሱፐርቫይዘሩ ሚና (The Engineer / Supervisor)

​PPA 2011: Engineer ወይም Supervisor የአሰሪው (Employer) ወኪል ሆኖ ይሰራል፤ በዋናነት የአሰሪውን ጥቅም ይወክላል።

​FIDIC 2017 (Clause 3): Engineer ገለልተኛ (Neutral) ሆኖ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውሳኔ እንዲሰጥ ይጠበቃል።

Sub-Clause 3.7 አዲስ አሰራር አስቀምጧል፦ በመጀመሪያ መስማማት (Agreement) ላይ ለመድረስ ይሞክራል፣ ካልተቻለ ብቻ ነው ውሳኔ (Determination) የሚሰጠው። 

​📌 3. የጊዜ ማራዘሚያ እና ክሌም (EOT & Claims)

​PPA 2011 (GCC Clause 27 & 44):
​ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ (Extension of Time) መጠየቅ የሚችለው በቂ ምክንያት (የአየር ሁኔታ፣ የአሰሪው መዘግየት፣ የተለየ ልዩነት/Variation) ሲኖር ነው።
​ጥያቄው በፅሁፍ መቅረብ አለበት፣ ነገር ግን እንደ FIDIC በጥብቅ የተወሰነ "የቀን ገደብ (Time-bar)" ላይኖረው ይችላል።

​FIDIC 2017 (Clause 20):
​Strict Time-Bar Clause (28 Days): ተቋራጩ ወይም አሰሪው ጉዳቱ/መዘግየቱ በታወቀ በ 28 ቀናት ውስጥ ማሳወቅ (Notice) ካልላከ፣ መብቱ ፈጽሞ ይቃጣል (Claim drops)!
​በ FIDIC 2017 ሁለቱም ወገኖች (Employer & Contractor) እኩል የክሌም ስርዓት ይከተላሉ። 

​📌 4. የዋጋ ማስተካከያ (Price Adjustment)

​PPA 2011 (GCC Clause 47): የፕሮጀክቱ ጊዜ ከ 18 ወራት በላይ ከሆነ እና በልዩ ውሉ (SCC) ከተፈቀደ ብቻ የዋጋ ማስተካከያ (Price Adjustment Formula) ይተገበራል።

​FIDIC 2017 (Sub-Clause 13.7): በውሉ ማلاحጫ (Contract Data) ከተገለፀ በማንኛውም ጊዜ በምንዛሬ ወይም በቁሳቁስ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል።

​📌 5. አለመግባባቶችን መፍታት (Dispute Resolution)

​PPA 2011 (GCC Clause 24 & 25):
​በመጀመሪያ በ Adjudicator (አስታራቂ) ይታያል። 
​ካልተስማሙ ወደ Arbitration (ግልግል ዳኝነት) ይሄዳል። 

​FIDIC 2017 (Clause 21):
​DAAB (Dispute Avoidance/Adjudication Board): አለመግባባት ከመፈጠሩ በፊት ቋሚ DAAB ይቋቋማል። ዋና አላማው አለመግባባቶችን አስቀድሞ "ማስቀረት" (Avoidance) ነው።
​ከ DAAB ውሳኔ በኋላ ካልተስማሙ ወደ ICC Arbitration ይሄዳል።

🚥ማጠቃለያ፦ PPA 2011 ለሀገር ውስጥ የመንግስት ፕሮጀክቶች ቀለል ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ FIDIC 2017 ደግሞ ጥብቅ የጊዜ ገደብና የክሌም ህጎች ያሉት የዓለም አቀፍ ፕሮጀክቶች መመሪያ ነው። 

☄ዋናው የ ኮንስትራክሽን ጉዳዮች የሚዳሰስበት መፅሃፍት ቪድዮዎች እና ትምህርቶች ምናጋራበት ቻናላችን ካልተቀላቀሉ ብዙ ነገር ኣምልጦታል እና ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ጆይን ኣርገው ቤተሰብ ይሁኑ ለወዳጅዎ ይጋብዙ👇

https://t.me/ETCONp
❤7👍2
👉የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ዲዛይን ሃይማኖታዊ ይዘቱ ጠብቆ ከመሠረታዊ የሕንፃ አካላት እስከ የተለያዩ ክፍሎችና የሕንፃ ቅርፆች በቀላልሉ ለመረዳት የተዘጋጀ ምርጥ የአማርኛ ኮንስትራክሽን መፅሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8a873add2d7_etconp
🙏2❤1
የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ መታቀዱ ተገለጸ።

የኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድብ አጠቃላይ አፈጻጸም ከ77 በመቶ በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

201 ሜትር ርዝመት ያለው የግድብ ግንባታው 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የአፈር ቁፋሮ በማካሄድ አጠቃላይ ግድቡ ከሚፈልገው 7 ነጥብ 72 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ውስጥ 81 ነጥብ 2 በመቶው ማለትም 6 ነጥብ 27 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት (RCC) ሥራ መከናወኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መብራቱ ተሾመ ተናግረዋል።

የኃይል ማመንጫ ቤቱ የቁፋሮ ሥራ እንዲሁም የሲቪል ሥራው የመጀመሪያ ደረጃ የኮንክሪት ሙሌት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁንና የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራውን በታቀደው ጊዜ ለማጠናቀቅ ዕቃዎች በበርካታ ፋብሪካዎች እንዲመረቱ መደረጉንም ጠቁመዋል።

የፋይናንስ አቅርቦት በተለይም የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና ተያያዥ ችግሮች በግንባታው ሂደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮ መቆየቱን ያስታወሱት ኢንጂነር መብራቱ፣ አሁን ላይ ተቋሙ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ በራሱ በመሸፈኑ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል ብለዋል።

የግድብ ግንባታውን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ በጥቅምት 2021 ዓ.ም የመጀመሪያውን ተርባይን ወደ ኦፕሬሽን ለማስገባት እየተሠራ ነውም ተብሏል።

Via EBC

@etconp
❤4👍2
👉ከስራ ተቋራጮች ጋር ሲሰሩ ማወቅ የሚገቡዎት 10 ወሳኝ ነጥቦች:-

​በግንባታው ዓለም ስኬታማ ጉዞ ለማድረግ እና ገንዘብዎን ከብክነት ለመታደግ ከስራ ተቋራጮች (Contractors) ጋር ሲያደርጉት የሚገባውን ውልና ጥንቃቄዎች በዝርዝር ተመልከቱ፦

​1. ህጋዊ ፈቃድ እና ምዝገባ 📄

ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ማረጋገጫ መጠየቅ የመጀመሪያው እና ትልቁ የጥንቃቄ እርምጃ ነው።

​2. የብቃት ማረጋገጫ (Grade) ⭐️

ተቋራጮች በምን ያህል አቅም እና ካፒታል እንደሚሰሩ የሚገልጽ ደረጃ (ከደረጃ 1 እስከ 10) አላቸው። ለሚሰሩት ፕሮጀክት የሚመጥን ደረጃ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

​3. የስራ ልምድ (Portfolio) 🏢

ከዚህ በፊት የሰሩዋቸውን ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች፣ የተጠናቀቁ ህንፃዎች ወይም ሌሎች ግንባታዎች በአካል በመሄድ ወይም በምስል ማየት የብቃታቸው ትልቁ ማሳያ ነው።

​4. ውል እና ስምምነት (Contract) ✍️

በቃል የሚደረግ ንግግር በግንባታ ላይ ቦታ የለውም። የዋጋ ዝርዝር፣ የቁሳቁስ ጥራት፣ የሚጠናቀቅበት ጊዜ እና የክፍያ ሁኔታ በግልጽ የሰፈረበት ውል በህግ ባለሙያ መዘጋጀት አለበት።

​5. የዋጋ ግምት እና ክፍያ (Budget) 💰

ክፍያዎች በሂደት (በደረጃ) እንጂ በአንዴ መፈጸም የለባቸውም። ስራው ሲሰራ እና የጥራት ምርመራ ሲያልፍ ብቻ ክፍያ እንዲለቀቅ ማድረግ ገንዘብን ከብክነት ይታደጋል።

​6. የጊዜ ሰሌዳ (Timeline) ⏳

ግንባታው የሚጀምርበትን እና የሚጠናቀቅበትን ቀን በግልጽ የሚያሳይ የጊዜ ሰሌዳ (Schedule) ከውሉ ጋር መያያዝ አለበት። ዘግይቶ የሚጠናቀቅ ስራ ከፍተኛ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል።

​7. የቁሳቁስ ጥራት (Quality Control) 🧱

በውሉ ላይ የተስማሙባቸውን የኮንክሪት መጠን፣ የብረት ዓይነት እና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ጥራት በባለሙያ ማስመረመር ለህንፃው ጽናት ዋስትና ነው።

​8. የሰራተኞች ዋስትና እና ደህንነት (Safety) 🦺

በግንባታ ቦታ ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች ተቋራጩ ኃላፊነት አለበት። የኢንሹራንስ ሽፋን ያላቸው እና የደህንነት እቃዎች (Safety materials) የሚጠቀሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።

​9. የባለሙያ ቁጥጥር (Supervision) 📐

እርስዎ ራስዎ ኢንጂነር ካልሆኑ፣ የስራውን ሂደት የሚከታተል ገለልተኛ አማካሪ (Consultant) ወይም መሐንዲስ መቅጠር ተቋራጩ ጥራቱን የጠበቀ ስራ እንዲሰራ ይገፋፋል።

​10. የዋስትና ጊዜ (Defect Liability Period) 🔑

ስራው ተጠናቆ ከተረከቡ በኋላም እንኳ ለተወሰነ ጊዜ የሚፈጠሩ ስንጥቆች ወይም ጉድለቶች በባለቤቱ ወጪ ሳይሆን በተቋራጩ እንዲስተካከሉ በውሉ ላይ መካተት አለበት።

@etconp
❤12👍4
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦቻችን

🏷Ms Project Full Online Course
25% Discount አርገናል

🪧ከ ETABS እና Quantity Surveying በተጨማሪ Ms Project ኦንላይን ኮርስ እያሰተማርን አዳዲሶችም አየመዘገብን ነው🙏

📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን ወይም ለበለጠ መረጃ በ 0925446661 ይደውሉልን❤️

@etconp
👌4
📐 CONVERSION TABLE – Essential Units for Civil Engineering

Accurate unit conversion is extremely important in construction, surveying, quantity estimation, structural design, and site execution. Using the wrong units can lead to serious calculation errors, material wastage, and incorrect dimensions.

1️⃣ Metric Conversions

• 1 cm = 10 mm
• 1 m = 100 cm = 1000 mm
• 1 km = 1000 m

2️⃣ Standard/Imperial Conversions

• 1 ft = 12 in
• 1 yd = 3 ft = 36 in
• 1 mile = 1760 yd

3️⃣ Metric → Standard Conversions

• 1 mm = 0.0393701 in
• 1 cm = 0.393701 in
• 1 m = 39.3701 in
• 1 m = 3.28084 ft
• 1 m = 1.09361 yd
• 1 km = 1093.6133 yd
• 1 km = 0.621371 mi

4️⃣ Standard → Metric Conversions

• 1 in = 2.54 cm = 25.4 mm
• 1 ft = 30.48 cm = 0.3048 m
• 1 yd = 91.44 cm = 0.9144 m
• 1 mi = 1609.344 m = 1.609344 km

✅ Important Notes

✔ Always check the units before starting calculations.
✔ Use consistent units throughout design and estimation.
✔ Convert units properly before calculating area, volume, loads, or quantities.
✔ Verify dimensions shown on drawings and measurements taken at the site.
✔ Accurate unit conversion helps ensure precision and confidence in engineering work.

Quick Check:
📏 1 meter ≈ 3.28084 feet
📏 1 foot = 0.3048 meter

@etconp
❤7👏1
👉ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን ብዝዎች በጠየቃቹን መሰረት የ ETABS ቲቶርያል ቪድዮ በአማርኛ ቋንቋ ከ introduction ጀምሮ Analysis እና Design ኣካተን ምርጥ ቪድዮ ኣዘጋጅተንላቹዋል።

🫵እንሆ ዛሬ ክፍል 4 ይዘንላቹ መጥተናል👇

https://youtu.be/iYTyYlebxjU
❤4
⚠️የኮንክሪት መላጥ (Spalling) እና የRebar Corrosion አደጋና መፍትሄዎቹ! 🏗️

በምስሉ ላይ እንደምናየው፣ የህንፃው ኮንክሪት ተላጦ በውስጡ ያለው የRebar ብረት በከፍተኛ ሁኔታ ዝገት ያሳያል። ይህ ችግር በቀላሉ የሚታይ የውበት ጉድለት ብቻ ሳይሆን፣ የኮንክሪት ጥንካሬንና የStructural Member አቅምን ሊቀንስ የሚችል ከባድ የStructural Defect ሊሆን ይችላል⚠️

🔹 ለምን ኮንክሪቱ ይላጣል?

የRebar ብረት ሲዝግ የዝገቱ ምርት ከመጀመሪያው ብረት የበለጠ መጠን ይይዛል። ይህም በኮንክሪቱ ውስጥ የExpansion Pressure በመፍጠር ኮንክሪቱን ከውስጥ ወደ ውጭ ይገፋል፤ በመጨረሻም Cracking, Delamination እና Spalling ሊያስከትል ይችላል።

🔹 ዋና ዋና መንስኤዎች፦

1️⃣ Inadequate Concrete Cover
በግንባታ ወቅት በቂ Concrete Cover አለመኖር ወይም በቂ Cover/Spacer Blocks አለመጠቀም ብረቱን ለእርጥበትና ለአካባቢያዊ ንጥረ ነገሮች በቀላሉ እንዲጋለጥ ያደርጋል።

2️⃣ Water Leakage & Moisture Exposure 💧
የውሃ መስረግ፣ የWaterproofing ችግር ወይም ቋሚ እርጥበት የRebar Corrosion እድልን በእጅጉ ይጨምራል።

3️⃣ High Water-Cement Ratio
ከፍተኛ Water-Cement Ratio ያለው ኮንክሪት የበለጠ Permeable ስለሚሆን ውሃ፣ ኦክሲጅን እና ክሎራይድ ያሉ ንጥረ ነገሮች ወደ Rebar በቀላሉ ሊደርሱ ይችላሉ።

4️⃣ Carbonation
CO₂ ወደ ኮንክሪቱ ውስጥ በመግባት የConcrete pH እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህም የRebar የተፈጥሮ መከላከያ ሲዳከም ዝገት ሊጀምር ይችላል።

🛠️ የጥገና መፍትሄ (Repair Procedure)

✅ የተላጠውንና የላላውን ኮንክሪት እስከ Sound Concrete ድረስ በጥንቃቄ ማስወገድ።

✅ የዛገውን Rebar በWire Brush, Mechanical Cleaning ወይም Sandblasting በተገቢው ማፅዳት።

✅ የብረቱ ዲያሜትር ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ከቀነሰ በStructural Engineer ግምገማ መሰረት የRebar Replacement/Doubling ወይም ሌላ የStrengthening መፍትሄ መውሰድ።

✅ አስፈላጊ ከሆነ ተገቢ የCorrosion Protection System/Primer መጠቀም።

✅ ቦታውን በተገቢ Polymer-Modified Repair Mortar, Micro-Concrete ወይም በEngineer የተመከረ የRepair Material መልሶ መሙላት።

✅ የውሃ መስረግን እና የMoisture ምንጩን ማስወገድ፤ ካልሆነ ግን ጥገናው እንደገና ሊበላሽ ይችላል።

⚠️ አስፈላጊ ማስታወሻ: ከባድ Spalling ወይም የRebar Section Loss ከታየ በቀጥታ መሙላት ብቻ በቂ አይደለም። የStructural Engineer ግምገማ አስፈላጊ ነው።

🏗️ የግንባታ ጥራት ከመጠገን ይሻላል!

👉 በእርስዎ ሳይት ላይ ለRebar ምን ዓይነት Concrete Cover / Cover Block ትጠቀማላችሁ? የምትጠቀሙትን የCover መጠንም አብራችሁ በኮሜንት ያካፍሉን!

@etconp
❤2🥰2
👉የ ህንፃ Quantity Surveying ከ Introduction ጀምሮ ችሎታዎን በተግባራዊ ምሳሌዎች የሚያሳድጉበት ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8dd294cbaa9_etconp
👏2❤1🥰1
🪜በደረጃ ኮንክሪት ስራ (Staircase Reinforcement & Formwork Preparation) ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች🏗️👷‍♂️

📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት እና ለደህንነት ቁጥጥር ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

1️⃣ የፎርምወርክ እርጋታ እና ድጋፍ (Formwork & Scaffolding Support):
የደረጃው የእንጨት ፎርምወርክ ከስር የተደገፈበት ፕሮፕስ/ስካፎልዲንግ የኮንክሪቱን ክብደት እና የሰራተኞቹን ንዝረት መቋቋም የሚችል ጠንካራ መሆኑን ማረጋገጥ።

2️⃣ የብረት አሰራር እና ማደራረብ (Waist Slab & Landing Rebar Detail):
የደረጃው ዋና ብረቶች (Main Bars) እና የማቋረጫ ብረቶች (Distribution Bars) በዲዛይኑ መሠረት መታሰራቸውን፣ እንዲሁም ደረጃው ከወለሉ/ላንዲንግ (Landing) ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ ተገቢው የብረት መቆላለፍ (Development Length / Anchorage) መኖሩን ማረጋገጥ።

3️⃣ የኮንክሪት ከቨር (Concrete Cover Spacers):
በብረቱ እና በፎርምወርኩ መካከል ተገቢው የኮንክሪት ከቨር (ከ 2.5cm - 3cm) እንዲኖር የስፔሰር ፓድ (Concrete Spacer Blocks) ማድረግ፤ ይህ ካልሆነ ብረቱ ከስር ክፍት ሆኖ ለዛግ ይጋለጣል።

4️⃣ የደረጃዎች እኩልነት እና ጽዳት (Step Dimensions & Cleaning):
የራይዘር (Riser) እንጨቶች እኩል ከፍታ እና ስፋት መያዛቸውን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ኮንክሪት ከመፍሰሱ በፊት በደረጃው ውስጥ ያሉ የእንጨት ፍቅፋቂዎችና ቆሻሻዎችን በደንብ ማፅዳት እና ፎርምወርኩን በውሃ ማረስ።

​🌐ለተጨማሪ መረጃ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዜናዎች የ YouTube ገፃችን ከታች ባለው ሊንክ በመግባት SubScribe አርገው ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG
‎
‎@etconp
👍3❤1
👉የኮንስትራክሽን ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ እና በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/.

በኮንስትራክሽን ውል ውስጥ የስራ መጀመሪያ ቀን እና ውል የተደረገበት ቀን የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ይሄውም የሆነበት ውሉ በተደረገበት እለት የግንባታ ስራ ይጀመራል ተብሎ ስለማይታሰብ ነው፡፡

*በኮንስትራክሽን ውል የስራ መጀመሪያ ቀን/Commencement date/

በመርህ ደረጃ የውል የግንባታ ስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ነው፡፡ ስለዚህ የውሉ የግንባታ ጊዜ ተብሎ የሚጠቀሰውን ቀን ውሉ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ መቁጠር ስህተት ነው፡፡

ምክንያቱም የኮንስትራክሽን ውል በአሰሪና ተቋራጭ መካከል ከተፈረመ በኋላ የግንባታው ተጨባጭ ስራ በተለያየ ምክንያት ሊዘገይ ይችላል፡፡ለምሳሌ ግንባታው የሚከናወንበት ቦታ የይገባኛል ጭቅጭቅ ቢነሳበት ጭቅጭቁ እስኪፈታ ድረስ አሰሪው የግንባታውን ሳይት ለተቋራጩ ማስረከብ ያልቻለ እንደሆነ ግንባታው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ ሳይጀመር መቆየቱ የማይቀር ይሆናል፡፡

*ለተቋራጩ የሳይት ርክክብ/site handover/

ለግንባታ የተወሰነው ቦታ ከጥያቄ ነጻ ከሆነና አሰሪው ሙሉ ባለይዞታ ለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ውል ላዋዋለው ሥራ ተቋራጭ የሥራ ቦታውን ያስረክባል ወይም የሳይት ርክክብ ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡

ይህ ከሆነ በኋላ አሰሪው ሥራ ተቋራጩ የግንባታ ሥራውን የሚጀምርበትን ቀን
- በርክክብ ወቅት በቃለ ጉባዔ ይወስናል፡፡
- ወይም አስቀድሞ በውሉ ልዩ ሁኔታዎች(Special condition of contract) ላይ በተቀመጠው ቀን እንደሆነ ታውቆ በተባለው ቀን ሥራ ይጀመራለረ ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ሥራ ተቋራጩ ሳይት ሳይረከብ የግንባታው ጅማሬ ቀን ሊቆጠር አይችልም ማለት ነው፡፡
ሳይት ርክክብ ከተደረገ በኋላ እንደፕሮጀክቱ ዓይነት ወይም መጠን ስፋት የሞቢላይዜሽን ቀን ተጨምሮ ዋና የግንባታ ሥራ ማስጀመሪያው ቀን ይወሰናል፡፡ ስለዚህ ተቋራጩ የግንባታ ቁሳቁስ እና የሰው ሀይል ሞቢላይዝ እስከሚያደርግበት ምክንያታዊ ጊዜ ድረስ የስራ መጀመሪያ ቀን ሊጀምርበት አይገባም፡፡

በዚህ ረገድ በተግባር አልፎ አልፎ ስህተት ሲሰራ ይስተዋላል፡፡ይሄውም አሰሪዎች አንዳንዴ የግንባታውን ጊዜ ውሉ ከተደረገበት ቀን ጀምረው በመቁጠር እና ተቋራጩን በቂ ምክንያት ካለህ የጊዜ ማራዘሚያ/Time extension/ ጠይቅ የሚሉበት የተሳሳተ ሁኔታና አጋጣሚ አለ፡፡

በዚህ ረገድ በሀገራችን እና በአለም ሀገራት እየተሰራባቸው ያሉ የዳበሩ የፊዲክ ጀኔራል ኮንዲሽኖች እና በሀገራችን ተጣጥመው የተቀረጹ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ምን ይዘት አላቸው የሚለውን እና የፍትሀብሄር ህግ ድንጋጌዎችን ደግሞ ቀጥለን እንዳስሳለን፡፡

1. FIDIC RED BOOK 1999

በፊዲክ ሬድ ቡክ 1999 ቨርሽን ክሎስ 8.1 ላይ ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ስራ እንዲጀምር ማስታወቅ እንዳለበት እና ከ7 ቀን ያላነሰ ጊዜ መስጠት እንደሚገባው ይጠቅሳል፡፡

እንደዚሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር የስራ መጀመሪያው ቀን/ Commencement date/ ተቋራጩ በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ42 ቀናት ውስጥ መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

በተጨማሪም ተቋራጩ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ወዲያውኑ እና ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡ተቋራጩ/contractor/ ከስራ መጀመሪያ ቀን በኋላ ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ምክንያት ሳይኖረው ያለመዘግየት የግንባታ ስራ መጀመር እንዳለበት በክሎስ ላይ የተቀመጠውን ግዴታውን ያልተወጣ እንደሆነ ደግሞ አሰሪው/client/ውሉን ለማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 15.2(c) ላይ ተቀምጧል

2. FIDIC 1987

በኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ፎር ወርክስ ኦፍ ሲቪል ኢንጅነረንግ ኮንስትራክሽን ፊዲክ 1987 ቨርሽን ክሎስ 41.1 ላይ ስለ ኮመንስመንት ዴት/የስራ መጀመሪያ ቀን ተቀምጧል፡፡ይዘቱም መሀንዲሱ የስራ መጀመሪያውን ቀን በጨረታ ሰነዱ አፔንዴክስ ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለተቋራጩ ማስታወቅ እንዳለበት የሚገልጽ ነው፡፡ተቋራጩም የስራ መጀመሪያው ቀን በመሀንዲሱ ከተገለጸለት በኋላ ያለመዘግየት እና በተቻለ ፍጥነት የግንባታ ስራውን መጀመር እንዳለበት ይገልጻል፡፡

የግንባታ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቆጠር የሚጀምረውም ከኮመንስመንት ዴት ጀምሮ ስለመሆኑ ክሎስ 43.1 ላይ ተቀምጧል፡፡

እንግዲህ ተቋራጩ በቂ ምክንያት ሳይኖረው በክሎስ 41.1 ላይ በተመለከተው አግባብ የግንባታ ስራውን ሳይጀምር የቀረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለማቋረጥ እና ተቋራጩን ከሳይት ለማስወጣት መብት/expel right/ እንዳለው ክሎስ 63.1 ያስቀምጣል፡፡

3. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር  አቋም/MoWUD 1994

ይህ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1994 ስራ ላይ አውሎት የነበረው የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/MoWUD 1994 በተለይ ከፊዲክ/FIDIC 1987 ቨርሽን የተወሰደ ሲሆን ስለኮመንስመንት ዴት በሁለቱም ጀኔራል ኮንዲሽኖች ላይ ተመሳሳይ ይዘት ባለው ሁኔታ ያስቀምጣሉ፡፡
ስለዚህ ማብራሪያውን መድገም አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም፡፡

4. የመንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ/PPA 2011

በፒፒኤ 2011 ቨርሽን ክሎስ 71 ላይ የስራ መጀመሪያ ቀን በስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ላይ ሊቀመጥ እንደሚችል ወይም ደግሞ በአስተዳደራዊ መንገድ በኢንጅኒየሩ በሚሰጥ ትእዛዝ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠቅሳል፡፡

እንዲሁም በሌላ ሁኔታ በውሉ ላይ ካልተገለጸ በስተቀር ለተቋራጩ የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ ታስቦ ከ120 ቀናት ለማለፍ አይችልም፡፡

5-የፍትሀብሄር ህግ

የስራ ማከናወኛ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 2610 - 2637) በሚመለከት በውሉ ላይ የጊዜ ጉዳይ በግልጽ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ተቋራጩ ወዲያውኑ ስራ መጀመር እንደሚኖርበት በአንቀጽ 2619 ላይ ተደንግጓል፡፡የግንባታ ጊዜ በተገለጸባቸው ውሎች ደግሞ ስራ ተቋራጩ ስራውን ወዲያው ያልጀመረ እንደሆነ እና በጊዜ ገደቡ የግንባታ ስራውን ለመፈጸም የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ አሰሪው ለተቋራጩ ስራውን የሚጀምርበትን ጊዜ ሊወስንለት እንደሚችል በአንቀጽ 2618 ላይ ተቀምጧል፡፡

ሌላው እነዚህ ደንቦች ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ስራ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3019-3040) በሚመለከተው የግል የስራ ተቋራጭነት ውል ላይ ጭምር ተፈጻሚነት እንደሚኖራቸው ከአንቀጽ 3019(2) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

የአስተዳደር መስሪያ ቤት የኮንስትራክሽን ውል ማለትም የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውል(የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3244 እና ተከታዮቹ) በሚመለከት እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን ግዴታዎቹን በውሉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡

በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ስምምነት የሌለ እንደሆነ ደግሞ ግዴታው በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ መፈጸም እንደሚኖርበት በአንቀጽ 3174 ላይ ተቀምጧል፡፡

ይህ ድንጋጌ ስለአስተዳደር መስሪያ ቤት ውሎች በጠቅላላው የተደነገገ ሲሆን የመንግስት ስራዎች መቋረጥ ውልን በሚመለከተው ልዩ ክፍል ላይም በግልጽ ስለስራ ጊዜ ተደንግጓል፡፡

@etconp
❤11👏3
🏗️በሳይት ላይ የኮንክሪት ድብልቅ (Site Concrete Mixing & Quality Control) ሲከናወን ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች!

🏛​በምስሎቹ ላይ እንደሚታየው በሳይት ደረጃ በሞተር በሚሰራ ሚክሰር (Concrete Mixer) ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠር እና ውሃ ተጨምረው ለስትራክቸር ስራ የሚሆን ኮንክሪት በመደባለቅ ላይ ይገኛሉ።

​📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት እና ለኮንክሪት ጥንካሬ (Concrete Strength) ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​1️⃣ የተመጣጠነ ስብጥር (Proper Mix Proportions): በዲዛይኑ መሠረት (ለምሳሌ C25 ወይም C30) የተቀመጠውን የሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር መጠን በጥብቅ መከተል። የቁሳቁሶቹን መጠን በድምፅ (Volume Batching/Gauge Box) ወይም በሚዛን (Weight Batching) በትክክል መስፈር ተገቢ ነው።

2️⃣ የውሃ እና ሲሚንቶ- (Water-Cement Ratio): የውሃ መጠን ከመጠን በላይ መጨመር የኮንክሪቱን ጥንካሬ (Strength) በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚቀንስና ስሊት/ክራክ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ አስፈላጊውን የመስሪያ ምቹነት (Workability) ብቻ በሚሰጥ መጠን ማስተካከል ያስፈልጋል።

3️⃣ የመደባለቂያ ጊዜ (Mixing Duration): ቁሳቁሶቹ በሚክሰሩ ውስጥ ከተጨመሩ በኋላ ኮንክሪቱ አንድ አይነት ቀለም እና ስብጥር (Uniform Consistency) እስኪያገኝ ድረስ በቂ ጊዜ (ከ 1.5 እስከ 2 ደቂቃ) መደባለቅ አለበት።

4️⃣ የሰራተኞች ደህንነት (PPE & Safety): ሲሚንቶ እና አቧራ ለሳንባ እና ለቆዳ ጎጂ በመሆናቸው ሰራተኞች የአፍ መሸፈኛ (Dust Mask)፣ ጓንት እና ተገቢውን የደህንነት አልባሳት መጠቀም አለባቸው።

​@etconp
❤8👍3
🏗️RCC & Masonry Structural Design Guide 📘

የRCC እና Masonry ዲዛይን በተግባር ይማሩ!

📚 Beams • Slabs • Columns • Footings • Staircases • Masonry • Retaining Walls

🎯 ለCivil Engineering ተማሪዎች፣ Engineers እና Construction Professionals 👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a951fc24c62a_etconp
❤3🙏2
👉JOB VACANCY

🌟Bill of Quantity (BoQ) surveyor

Addis Ababa, Ethiopia

Deadline: September 15, 2026

Vacancies: 1

Education Qualification: á‰´áŠ­áŠ’áŠ­áŠ“ ሙያ

Skills

Furniture Design
CADWork

Address:-Kality

Job Description

Prepare detailed Bills of Quantities (BOQs) based on drawings, specifications, and project

requirements-Coordinate with designers, architects, project managers, and store and work center managers-must have previous experience in preparing BOQ is a plus-CAD knowledge is a plu-knowledge about wood works Raw materials-Responsible for preparing accurate BOQs, cost estimates, and supporting cost control throughout furniture manufacturing process.

waryt wood works telegram support services - @warytwoodworks_support (send cv only as optional )

call 0932298929 or 0999289093

@etconp
❤3👍1