Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.78K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
🏗️ Bid & Contract Document Package

🌟ለኢትዮጵያ የግንባታ Bid, Tender & Contract ዝግጅት የሚያግዝ ፕሮፌሽናል ፓኬጅ።

📦 4 Editable MS Word Documents
📁 One ZIP File

🇪🇹 ለኢትዮጵያ ግንባታ ፕሮጀክቶች

🏛ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a7fed4a173ec_etconp
👌3❤2
የግንባታ ስራ ጨረታ ማስታወቂያ፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን " Construction Works of Package 8 Condominium Road, Lot 2 (Fanuel, Bereket & Wotader Sefer) Asphalt Road Project; Bridge Construction @ Station 0+420" ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ፍላጎት ያላቸው ተቋራጮች በሙሉ ከታች ባለው የeGP system ሊንክ በመግባትና አስፈላጊውን መረጃ በመሙላት መሳተፍ ይችላሉ።

Construction Works Tender Notice:

The Addis Ababa City Roads Authority invites eligible contractors through an Open Tender for the Construction Works of Package 8 Condominium Road, Lot 2 (Fanuel, Bereket & Wotader Sefer) Asphalt Road Project; Bridge Construction @ Station 0+420.

Qualified firms can participate by registering and submitting all required information through the official eGP System link below.

Procurement Reference No.: AACRA-NCB-W-0008-2019-BID-Open
eGP System Link:  https://production.egp.gov.et/egp/bids/report/tendering/26b595fb-fe03-46ae-873e-ad89a8d2b085/open

@etconp
👍2❤1
👉የኮንስትራክሽን ሥራ ውል አዘገጃጀት — ሙያዊ መመሪያ በአማርኛ

🏛የኮንስትራክሽን ሥራ ውል ከመዘጋጀቱ በፊት ሊታወቁና ሊካተቱ የሚገባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአማርኛ የሚያብራራ ሙያዊ መመሪያ።

👷 ሲቪልና ኮንስትራክሽን መሐንዲሶች
⚖️ የሕግ ባለሙያዎች
🏗️ ተቋራጮችና አማካሪዎች
📋 ፕሮጀክት ማኔጀሮች
🎓 የኮንስትራክሽን ተማሪዎች የሚጠቅም ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a9aa58c0b37b_etconp
❤2👏1🙏1
👉የግንባታ ሥራ  ውል አፈጻጸም ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ ዋና ዋና  ባለድርሻ አካላት፡

🌟የስራው ባለቤት/Client/Employer:-

ግለሰብ ወይም ማህበር ወይም ድርጅት ወይም የመንግስት ተቋም ሊሆን የሚችል ሲሆን የሥራው ባለቤት ከመሆኑ አንጻር ሥራውን ለማከናወን የሚችል ሥራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ መቅጠር እና ለግንባታ ሥራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ ሀብት የሚያዘጋጅና ዋጋ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት አካል ነው፡፡

🌟ሥራ ተቋራጭ:-

ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ግብዓቶች በሙሉ በሟሟላት የግንባታ ሥራውን  በተባለው ጊዜና በተቀመጠው የጥራት ደረጃ ለመስራት ተዋውሎ የሚሰራ ነው፡፡

🌟መሃንዲስ(አማካሪ):-

ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ውለታውን እንዲያስተዳድር የሚቀጠር ነው፡፡ምንም እንኳን አማካሪ መሃንዲሱን የሚቀጥረውና ክፍያ የሚፈጸምለት በአሰሪው ቢሆንም፤ አማካሪው ውሉን በማስተዳደር ሂደት ውስጥ በቅን ልቡና በፍጹም ፍትሃዊነት ለሁለቱም የሚሰራ ነው፡፡

🌟የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች (Insurance Companies):-

አንድ ሥራ ተቋራጭ በጨረታ ለመሳተፍ፣ ወደውል ለመግባት፣ ክፍያዎች ለማግኘትና በሌሎች አሰሪው ድርጅት ለደህንነቱ መጠበቂያ ከስራ ተቋራጩ እንዲቀርብለት የሚጠይቀውን የመተማመኛ የመድን ዋስትናዎች ለሥራ ተቋራጩ የሚያቀርብ አካል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ ለንብረቱ፣ ለገንዘቡ፣ ለስራውና ለሰራተኞቹ ደህንነት የሚጠይቃቸውን የመድን ዋስትናዎችንም (for Contractor’s all risks) የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ አንድ የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅት አይነቱ ተለይቶ ለታወቀ ጉዳይ ለሥራ ተቋራጩ የመድን ሽፋን ሰጠ ማለት በአሰሪው ድርጅትና በሥራ ተቋራጩ በኩል ሊኖር የሚችለውን የአደጋ ስጋት ለመሸከም ሃላፊነት የሚቀበል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለወደፊት ስለግንባታ ፕሮጀክቶች የመድን ዋስትናዎች (Construction Insurances) በተብራራ ሁኔታ በምናቀርበው ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡

🌟ባንኮች:-

ለስራ ተቋራጩም ይሁን ለስራው ባለቤት ለፕሮጀክቱ ማከናወኛ የገንዘብ ፍላጎቶችን በማመቻቸት የሚሰሩ ናቸው፡፡ ባንኮች እንደ የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትናም በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡ 

🌟አቅራቢዎች (Suppliers):-

እነዚህ ባለድርሻ አካላት ለግንባታ ሥራ ከመጀመሪያ እስከ ሥራው ፍጻሜ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ዓይነት የግንባታ ሥራ ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን ወይም የግንባታ ሥራ ቁሳቁሶችን በሽያጭና በኪራይ  የሚያቀርቡ ናቸው፡፡

🌟ፈቃድ ሰጪ አካላት (Permitting bodies):-

ለግንባታ ሥራው የግንባታ ቦታ በመፍቀድ፣ የግንባታ ፈቃድ በመስጠት፣ የግብዓት ማውጫ ካባዎችን ፣የማምረቻ የማከማቻና የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ፈቃድ በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡

🌟የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋማት (Public):-

ለግንባታ ሥራው እንደ ውሃ፣መብራት፣ስልክ የመሳሰሉ ለግንባታ ሥራዎች የመሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ አካላት ናቸው፡፡

@etconp
❤8👍5👏2
👉ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ የውል ተፈጻሚ ስላለመሆን /Privities of Contract/

🏛የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1952 “በህግ ተለይቶ የተመለከተ ካልሆነ በቀር ውሎች ውጤት ያላቸው በተዋዋሏቸው ወገኖች መካከል ብቻ ነው”

ውል ከተዋዋይ ወገኖች ውጭ ተፈጻሚነት እንደሌለው የታመነ ነው፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ፍትሃብሄር ሕግም በአንቀጽ 1952 ላይ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

በዚህም መሰረት ውሎች ልዩ ሁኔታዎች (exceptions) እንደተጠበቁ ሆነው በሦስተኛ ወገኖች ላይ ተፈጻሚ አይሆኑም ማለት ነው፡፡

ታዲያ! ከዚህ መርሆ ተቃርኖ በሚመስል መልኩ መሀንዲሱ እንዴት በአሰሪው እና በሥራ ተቋራጩ መካከል በተደረገ ውል ላይ ጣልቃ ሊገባ ይችላል ፣ ብሎም የተለያዩ ሚናዎች ሊኖሩት ቻሉ የሚሉ ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም ይስተጋባሉ፡፡

🌟መልሱ፦መሀንዲስ የአሰሪው ወኪል መሆኑ በራሱ የተለያዩ በሕግ ፊት ሊጸኑ የሚችሉ ተግባራትን (juridical acts) ሊፈጽም ይችላል እንደ ማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በወጥ ውሎች ላይ እንደተመለከተው የፕሮጀክቱ ተሳታፊ በመሆኑ የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ግልጽ ነው፡፡

ለሚወዱት ያጋሩ❤️

@etconp
🥰2🙏1
🕌ስለ መስጊድ አርክቴክቸር እና ግንባታ በተግባር ለመማር የሚረዳ 4 ምርጥ መፅሐፍ በአንድ ላይ አዘጋጅተናል📚

📐 የሚያካትተው፦
✅ Mosque Architecture
✅ Concept & Geometry
✅ Space Planning
✅ Design Synthesis & Form
✅ የአርክቴክቸራል እና Structural Drawings የምሳሌ ፕሮጀክቶች
✅ ለመማርና ለፕሮጀክት ማጣቀሻ የሚሆኑ ዝርዝር ማብራሪያዎች ያለው ነው🌙

💫እነዚህ መፅሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8fbfb8b8611_etconp
❤4👏1
👉Construction Engineering Abbreviation Tips

➡️The common abbreviation used in Construction Industry

👷 A.A.S.H.T.O – American Association of state highway Transport Official.

👷 A.C.I – American Concrete Institute.


👷 A.R.E.A – American Railway Engineering Association.

👷 A.B – Anchor  Bolt Or Asbestos Board

👷 AC – Asphalt Concrete

👷 A.S.C – Allowable Stress of concrete.

👷 A.S.T.M – American society for testing materials

👷 AC – Asbestos Cement.

👷 AE – Assistant Engineer

👷 APM – Assistant Project Manager

👷 B.M – Benchmark

👷 B.M – Bending Moment.

👷 BLK – Block Work

👷 BOQ – Bill Of Quantities

👷 BRW – Brick Retaining Wall

👷 BWK – Brick Work

👷 B.O.F – Bottom Of Foundation

👷 BHK – Bedroom, Hall, Kitchen

👷 C.I.Pipe – Cast iron pipe.

👷 C.I.Sheet – Corrugated Iron sheet.

👷CL- Centre Line

👷CRW – Concrete Retaining Wall

👷 CBW – Concrete Block Wall

👷 CIP – Cast In Place

👷 CMU – Concrete Masonry Unit

👷 CJ – Construction Joint

👷 CC – Centre To Centre

👷 CC – Cement concrete.

👷 CE – Chief Engineer

👷 CP – Cement plaster.

👷 CPM – Critical path method.

👷 CS – Comparative statement.

👷 D – Diameter

👷 DL – Development Length

👷 Dia – Diameter

👷 DIM – Dimension

👷 D.L – Dead load.

👷 DPC – Damp proof course.

👷 DPR – Daily Progress Report

👷 DRG – Drawings

👷 DWLS – Dowels

👷 EJ – Expansion Joint

👷 E.L – Environmental load.

👷 EL – Existing Load

👷 EGL – Existing ground level.

👷 ELCB – Earth Leak Circuit Breaker

👷 F.M – Fineness Modulus.

👷 Ft – Foot Or Feet

👷 FL – Floor Level

👷 FGL – Formation ground level.

👷 FOC – Factor Of Safety

👷 GL – Ground Level

👷 GL – Ground level.

👷 GP – Ground plane.

👷 HFL – Highest Flood Level.

👷 HAC – High Alumina Cement

👷 HP – Horizontal plane.

👷 IOM – Inter Office Memo

👷 ISI – Indian standard institute.

👷 JE – Junior Engineer

👷 JST – Joist

👷 Kg  – Kilogram.

👷 L.L – Live load.

👷 LW – Light  Weight

👷 LWC – light Weight Concrete

👷 LC – Lime concrete.

👷 M – Meter

👷 MM – Millimeter.

👷 MB – Measurement book.

👷 MCB – Miniature Circuit Breaker

👷 MEP – Mechanical Electrical Plumbing

👷 MFL – Maximum Flood Level

👷 MRC – Material Receipt Challan

👷 MT – Metric Tonnes

👷 N – Newton

👷 NCF – Neat cement finishing.

👷 OPC – Ordinary Portland Cement

👷 OGL – Original ground level.

👷 OSR – Open Soace Reservation Area

👷 PC – Pile Cap

👷 PC – Precast Concrete

👷 PCC – Plain Cement Concrete

👷 PERT – Programme Evaluation and Review Technique.

👷 PL – Plinth level.

👷 PM – Project Manager

👷 PO – Purchase Order

👷 PPE – Personal Protective Equipment

👷 PPR – Poly Propylene Random.

👷 PVC – Poly vinyl choloride .

👷 PVC – Polyvinyl Chloride

👷 PSF – Pound Per Square Foot

👷 PSI – Pound Per Square Inch

👷 PWD – Permanent Works Engineer

👷 QC – Quality control

👷 QS – Quantity Surveyor

👷 RC – Reinforced Concrete

👷 R.B.W – Reinforced brick work.

👷 RBC – Reinforced Brick concrete.

👷 RCC – Reinforced Cement Concrete

👷 RMC – Ready Mixed Concrete concrete.

👷 RL – Reduced level.

👷 SCC – Self Compacting Concrete

👷 STP – Sewage Treatment Plant

👷 SRC – Sulphate Resisting Cement

👷 SWG – Standard wire gauge.

👷 TB – Tie Beam

👷 TBM – Tunnel Boring Machine

👷 TDS – Total Dissolved Solids

👷 TOB – Top Of Beam

👷 TMT – Thermo Mechanical Treatment

👷 TOC – Top Of Concrete

👷 TOW – Top Of Wall

👷 U.S.C – Ultimate stress of concrete.

👷 UPVC – Unplasticized Polyvinyl chloride.

👷 USD – Ultimate strength design.

👷 VP – Vertical plane.

👷 W.C – Water closet.

👷 WL – Working Level

👷 W.S.D – Working stress Design

👷 WO –  Work Order
Source:from, etcon page

@etconp
❤15👏4🥰1
💧🏗️ የውሃ ሥራዎች ግንባታ | WATER WORKS CONSTRUCTION 🚰👷‍♂️

💡 የውሃ ሥራ ግንባታ የመጠጥ ውሃን ከምንጩ ወይም ከማጠራቀሚያ ቦታ በመነሳት ወደ ማህበረሰብ፣ ወደ ቤቶች፣ ወደ ድርጅቶች እና ወደ ሌሎች የውሃ ተጠቃሚዎች በአስተማማኝና በተቀጣጣይ ሁኔታ እንዲደርስ የሚያስችሉ የምህንድስና ሥራዎችን ያካትታል። 💦

በውሃ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ የሥራውን መጠን በትክክል ለመለካትና የፕሮጀክቱን ወጪ ለማስላት ተለያዩ የመለኪያ አሃዶች ይጠቀማሉ። 📐📋

🔹 የውሃ ምንጭ ልማት — No. / ቁጥር
የምንጭ ልማት፣ የጉድጓድ ሥራ ወይም የውሃ መያዣ መዋቅር እንደ አንድ የሥራ ክፍል ሲቆጠር። 💧

🔹 የውሃ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ — m / ML (ሜትር)
የተዘረጋው የቧንቧ መስመር ርዝመት። 🚰📏

🔹 የቧንቧ መስመር ቁፋሮ — m³ (ኪዩቢክ ሜትር)
የተቆፈረው የመሬት መጠን። ⛏️

🔹 የቧንቧ መስመር የአሸዋ አልጋ ዝግጅት — m³
በቧንቧው ስር የሚደረገው የአሸዋ ንጣፍ መጠን።

🔹 የቧንቧ መሙላት (Backfilling) — m³
ቧንቧው ከተተከለ በኋላ ቦዩን በመሬት ወይም በተመረጠ ቁሳቁስ የመሙላት መጠን።

🔹 የውሃ ማጠራቀሚያ ግንባታ — m³ / m²
የኮንክሪት ሥራ m³፣ የፕላስተርና የገጽታ ሥራ m² ሊለካ ይችላል። 🏗️

🔹 የፓምፕ ጣቢያ ግንባታ — m² / m³ / No.
የሕንፃ ሥራ m²፣ የኮንክሪት ሥራ m³፣ ፓምፕና መሣሪያዎች No. ሊሆኑ ይችላሉ። ⚙️

🔹 ቫልቭ እና ፊቲንግ መትከል — No. / ቁጥር
Valves, bends, tees, reducers እና ሌሎች ፊቲንጎች በቁጥር ይለካሉ። 🔧

🔹 የቫልቭ ቻምበር ግንባታ — No. / m³ / m²
ቻምበሩ እንደ አንድ የተጠናቀቀ ሥራ No. ሊሆን ይችላል፤ ኮንክሪት m³ እና ፕላስተር m² ይለካሉ።

🔹 የውሃ ማጣሪያ ሥራ — No. / LS
የማጣሪያ መሣሪያዎች በቁጥር፣ አንዳንድ የተሟላ የሥራ ክፍሎችም Lump Sum (LS) ሊሆኑ ይችላሉ። 🧪

🔹 የውሃ ግፊት ሙከራ — m / ML
የሚፈተነው የቧንቧ መስመር ርዝመት። 📏💦

🔹 የውሃ ጥራት ምርመራ — No. / Test
የላብራቶሪ ምርመራዎች በሚደረጉት የሙከራ ብዛት ሊለኩ ይችላሉ። 🧪

📌 በአጠቃላይ በውሃ ሥራ BOQ በብዛት የሚጠቀሙ መለኪያዎች፦

m/ML → ርዝመት 📏
m² → የገጽታ ስፋት
m³ → የድምፅ/የኩብ መጠን
No. → ቁጥር
kg → ክብደት ⚖️
LS → Lump Sum / የተጠቃለለ ዋጋ

💡 ትክክለኛ የሥራ መጠን + ትክክለኛ የመለኪያ አሃድ + ትክክለኛ BOQ = የተሻለ የወጪ ቁጥጥር! 📋💰🏗️

#WaterWorks #BOQ #CivilEngineering #HydraulicEngineering #Construction #የውሃ_ሥራ #የውሃ_ግንባታ #BOQ #ሲቪል_ኢንጂነሪንግ 🇪🇹

@etconp
👏5❤2
👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦች

🌟አዲስ አመት ምክንያት በማረግ ከ ጷግሜን 1 ጀምሮ እስከ ጷግሜን 5 የሚቆይ Quantity Surveying እና Ms Project ኦንላይን ኮርሶች ስልጠና የ 25% ቅናሽ አርገናል🙏

📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን

👊Qs ለሚወስዱ ETABS ቦነስ እንደተጠበቀ ነው👇
https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5e233a9c5e0_etconp

መልካም አዲስ አመት🙏

@etconp
🙏4❤3
👉አንድ ከፍተኛ የሳይት ኢንጂነር (መሃንዲስ) በተለይም ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የሳይት (የመስክ) እውቀት ሊያዳብር ይገባል?
========================
ከፍተኛ የሳይት ኢንጂነር ማለት በግንባታ ላይ ሠራተኞችን ብቻ የሚቆጣጠር ሳይሆን የግንባታ ሥራዎች በተፈቀዱ ስዕሎች፣ ቴክኒካዊ ዝርዝር መግለጫዎች፣ ደረጃዎች፣ የውል መስፈርቶች እና የቦታው ትክክለኛ ሁኔታ መሠረት በትክክል፣ በጥራት፣ በደህንነት፣ በተገቢው ወጪ እና በተወሰነው ጊዜ እንዲከናወኑ የሚያረጋግጥ የቴክኒክ ባለሙያ ነው።

1. የኢንጂነሪንግ ስዕሎችን ማንበብና መተርጎም

የሳይት ሲቪል ኢንጂነር የግንባታ ስዕሎችን በትክክል ማንበብ፣ መረዳት፣ መተርጎም እና በሳይት ላይ ተግባራዊ ማድረግ መቻል አለበት።

በተለይም፦
• የሳይት ሌይአውት ስዕሎች
• የአርክቴክቸር ስዕሎች
• የስትራክቸር ስዕሎች
• የሲቪል ስዕሎች
• የመንገድ ስዕሎች
• የውሃ ማፋሰሻ ስርዓት ስዕሎች
• የውሃ አቅርቦት ስዕሎች
• የቦይ፣ የካልቨርት እና የድልድይ ስዕሎች
• የግሬዲንግና የሌቨሊንግ ስዕሎች
• የዝርዝር ስዕሎች (Detail Drawings)
• የሱቅ ስዕሎች (Shop Drawings)
• የአስ-ቡልት ስዕሎች (As-Built Drawings)
• የኮንትራት ስዕሎች
• ቴክኒካዊ ዝርዝር መግለጫዎች
በስዕሎች ላይ ያሉ ዲሜንሽኖች፣ ከፍታዎች፣ ኮርዲኔቶች፣ ቻይኔጅ፣ አሊይንመንት፣ ሴክሽን፣ ኤሌቬሽን፣ የቁሳቁስ መስፈርቶች፣ የግንባታ ትክክለኛነት ወሰኖች (Tolerances) እና ሌሎች ቴክኒካዊ መመሪያዎችን መረዳት አለበት።
በተለይም በስዕሎች መካከል የሚኖሩ ልዩነቶችንና ግጭቶችን ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ማወቅ እና ማስተካከያ መጠየቅ አለበት።

ጥሩ የሳይት ኢንጂነር ስዕልን በዝምታ የሚከተል ብቻ አይደለም፤ ዲዛይኑ በእውነተኛው የሳይት ሁኔታ ላይ በተግባር ሊገነባ የሚችል መሆኑን ያረጋግጣል።

2. የሳይት ሰርቬይንግና ሴቲንግ-አውት
ሰርቬይንግ ለአንድ የሳይት ሲቪል ኢንጂነር እጅግ አስፈላጊ የሆነ ተግባራዊ እውቀት ነው።
እንደሚከተሉት ያሉ ጉዳዮችን መረዳት አለበት፦

• Benchmark እና Temporary Benchmark
• Reduced Level (RL)
• Coordinates
• Chainage
• Alignment
• Centerline
• Offset
• Profile
• Cross-section
• Existing Level እና Proposed Level
• Horizontal እና Vertical Control
• Gradient እና Slope
በተጨማሪም Auto Level፣ Total Station፣ Theodolite እና GPS/GNSS የመሳሰሉ የሰርቬይ መሳሪያዎችን አጠቃቀምና የሚሰጡትን መረጃ መረዳት አለበት።
የህንፃ፣ የመንገድ፣ የድልድይ፣ የካልቨርት፣ የውሃ መስመር እና ሌሎች ሲቪል ሥራዎች በትክክለኛ ቦታ፣ አሊይንመንት እና ከፍታ ላይ መገንባታቸውን ማረጋገጥ አለበት።

3. የመሬት ሥራና ቁፋሮ
የሳይት ኢንጂነር ስለ Earthwork ጠንካራ ተግባራዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል።
ይህም፦

• Site Clearance
• Topsoil Stripping
• Excavation
• Trench Excavation
• Foundation Excavation
• Rock Excavation
• Backfilling
• Filling
• Embankment Construction
• Cut and Fill
• Subgrade Preparation
• Soil Compaction
• Borrow Material
• Spoil Disposal
• Unsuitable Material Removal
• Slope Protection የሚያካትት ነው።

በተጨማሪም ስለ አፈር ምደባ፣ የአፈር እርጥበት፣ የአፈር ጥግግት፣ Bearing Capacity፣ Settlement፣ Compaction፣ CBR፣ Atterberg Limits፣ Soil Stabilization እና Groundwater መሠረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል።
እንዲሁም የመሬት ምርመራና የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤቶችን መረዳትና በግንባታ ውሳኔ ላይ መጠቀም መቻል አለበት።

4. ኮንክሪት ቴክኖሎጂና የኮንክሪት ሥራ
የሳይት ሲቪል ኢንጂነር የኮንክሪትን ቁሳቁሶች፣ አዘገጃጀት፣ አቀማመጥ፣ ማጠናከር፣ ማጠንከሪያ (Curing) እና የጥራት ቁጥጥር በደንብ ሊያውቅ ይገባል።
ይህም፦

• Cement
• Fine Aggregate
• Coarse Aggregate
• Water
• Admixtures
• Workability
• Slump
• Segregation
• Bleeding
• Setting
• Strength
• Durability
• Shrinkage
• Creep
• Curing
ያካትታል።
ከኮንክሪት መፍሰስ በፊት የFormwork፣ Reinforcement፣ Concrete Cover፣ Embedded Items፣ Construction Joints እና የሳይት ዝግጅት በትክክል መሆናቸውን መፈተሽ አለበት።
በኮንክሪት ሥራ ወቅት ደግሞ የኮንክሪት ጥራት፣ ማጓጓዝ፣ አቀማመጥ፣ ቫይብሬሽን፣ ፊኒሺንግ እና ኪዩሪንግ በተገቢው መከናወናቸውን ማረጋገጥ አለበት።
እንደ Honeycombing፣ Cold Joint፣ Cracking፣ Segregation፣ Bleeding፣ Poor Compaction እና Poor Curing ያሉ የኮንክሪት ጉድለቶችን መለየትና መንስኤያቸውን መመርመር አለበት።

5. የማጠናከሪያ ብረት ሥራ
በReinforced Concrete ሥራ ላይ የሚሰራ የሳይት ኢንጂነር የReinforcement መጫንና መመርመር በዝርዝር ሊያውቅ ይገባል።
ይህም፦

• የብረት ደረጃ
• የብረት ዲያሜትር
• የብረት ክፍተት
• Main Reinforcement
• Distribution Reinforcement
• Shear Reinforcement
• Stirrups
• Links
• Ties
• Chairs
• Spacers
• Concrete Cover
• Development Length
• Anchorage
• Lap Splicing
• Hooks
• Bends
• Curtailment ያካትታል።

ኮንክሪት ከመፍሰሱ በፊት የReinforcement ሥራው ከተፈቀደው Structural Drawing እና Specification ጋር መጣጣሙን ማረጋገጥ አለበት።
በተለይም የብረት ዲያሜትር፣ ብዛት፣ ክፍተት፣ ቦታ፣ Anchorage፣ Lap Location፣ Development፣ Concrete Cover እና የReinforcement ድጋፍ በትክክል መሆናቸውን መፈተሽ አለበት።

6. FORMWORK እና TEMPORARY WORKS
የሳይት ኢንጂነር Formwork እና Temporary Works በትክክል መጫናቸውን፣ መደገፋቸውንና ደህንነታቸውን መፈተሽ አለበት።
ለምሳሌ፦

• Dimension
• Alignment
• Level
• Plumbness
• Stability
• Support
• Bracing
• Shoring
• Reshoring
• Joint
• Surface Condition
• Cleanliness መፈተሽ አለበት።

Formwork ከመንቀሳቀስ፣ ከመጠማዘዝ፣ ከመፍሰስ፣ ከመዛነፍ ወይም ከበቂ ያልሆነ ድጋፍ የተነሳ የሚፈጠሩ ችግሮችን በጊዜ መለየት አለበት።

7. የመሠረት ግንባታ
የሳይት ኢንጂነር የተለያዩ የFoundation ዓይነቶችን እና የግንባታ ሂደታቸውን ሊያውቅ ይገባል።

እነዚህም፦

• Isolated Foundation
• Combined Foundation
• Strip Foundation
• Raft Foundation
• Pile Foundation
• Footing
• Ground Beam

@etconp
❤8🥰4👍3
Ethiopian Construction Vacancy & Tender pinned «👉አስደሳች ዜና ለዚህ ቻናል ቤተሰቦች 🌟አዲስ አመት ምክንያት በማረግ ከ ጷግሜን 1 ጀምሮ እስከ ጷግሜን 5 የሚቆይ Quantity Surveying እና Ms Project ኦንላይን ኮርሶች ስልጠና የ 25% ቅናሽ አርገናል🙏 📩ለመመዝገብ @Philemona7 ይፃፉልን 👊Qs ለሚወስዱ ETABS ቦነስ እንደተጠበቀ ነው👇 https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6…»