Ethiopian Construction Vacancy & Tender
18.1K subscribers
4.57K photos
56 videos
536 files
3.78K links
Ethiopian Construction Vacancy & Tender
Daily updates on construction Engineering Works, job vacancies, tenders,News,Technology and bid announcements in Ethiopia & World

Buy ads: https://telega.io/c/ETCONpWORK

📩 @Philemona7
Download Telegram
👉የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የወጣበት ቀን መስከረም 3, 2019

@etconp
❤3
👉በአዲሱ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሰራር ለመወሰን በወጣው መመሪያ 1147/2018 ድንጋጌዎች መሠረት የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዳይሆኑ የሚያግዱ ወንጀሎች እና በባለቤትነት ሊይዟቸው የማይችሏቸው የቤት ዓይነቶች ተለይተዋል።

🚥ዝርዝሩን ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ!

🌟ለድርጅታቹ እድገት እና ስራቹ በቀላሉ ማስተዳደር እንድትችሉ የሚያግዝ ሙሉ የ በ EXCEL የተገነባ ሲስተም ፋይል አዘጋጅተንላቹዋል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aaa29dcad3b0_etconp
🥰2👏1🙏1
👉የግንባታና የምህንድስና Drawing ዓይነቶች

🌟በ Construction & Engineering ፕሮጀክት ውስጥ የሚዘጋጁ Drawing ዓይነቶች እንደ ፕሮጀክቱ ዓይነትና መጠን ይለያያሉ።

1️⃣ Architectural Drawings
የሕንፃውን አቀማመጥ፣ ተግባራዊ አጠቃቀምና ገጽታ የሚያሳዩ Drawings።
🔹 Site Plan – ሕንፃው በመሬቱ ላይ ያለበትን ቦታ፣ የመሬት ወሰን፣ መንገድ፣ ፓርኪንግ፣ Landscaping እና Utilities ያሳያል።
🔹 Floor Plan – የክፍሎች፣ ግድግዳዎች፣ በሮች፣ መስኮቶችና Dimensions አቀማመጥን ያሳያል።
🔹 Roof Plan – የጣሪያ አቀማመጥ፣ Slope፣ Drainage እና Parapet ያሳያል።
🔹 Elevation Drawing – ሕንፃውን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲታይ ያለውን ውጫዊ ገጽታ ያሳያል።
🔹 Section Drawing – ሕንፃውን በቁመት ቆርጦ Foundation፣ Floor፣ Slab፣ Ceiling፣ Roof፣ Levels እና ሌሎች ክፍሎችን ያሳያል።
🔹 Reflected Ceiling Plan (RCP) – የCeiling፣ Lighting፣ Access Panel ወዘተ አቀማመጥ ያሳያል።
🔹 Door & Window Schedule – የበርና መስኮት ዓይነት፣ Size፣ Material፣ Number እና Location ያሳያል።
🔹 Finishing Schedule – የFloor፣ Wall እና Ceiling Finishes ዓይነቶችን ይገልጻል።
🔹 Detail Drawing – እንደ Staircase፣ Door፣ Window፣ Parapet እና Wall Junction ያሉ ክፍሎችን በተለየ ዝርዝር ያሳያል።

2️⃣ Structural Drawings
የሕንፃውን Load-Bearing Elements እና Reinforcement ዝርዝሮች የሚያሳዩ Drawings።
🔹 Foundation Plan – የFoundation ቦታ፣ Size፣ Type እና Level ያሳያል።
🔹 Column Layout – የColumns ቦታ፣ Size እና Identification ያሳያል።
🔹 Beam Layout – የBeams ቦታ፣ Size እና Identification ያሳያል።
🔹 Slab Layout – የSlab Type፣ Thickness፣ Level እና Arrangement ያሳያል።
🔹 Reinforcement Drawing – የRebar Diameter፣ Spacing፣ Location፣ Shape እና Anchorage/Development ዝርዝሮችን ያሳያል።
🔹 Bar Bending Schedule (BBS) – የReinforcement Bars መቁረጫ፣ መታጠፊያ፣ Shape፣ Length እና Quantity መረጃ ይይዛል።
🔹 Retaining Wall Drawing – የRetaining Wall Geometry፣ Foundation፣ Reinforcement እና Drainage ያሳያል።
🔹 Structural Detail Drawing – የBeam-Column Connection፣ Joint፣ Reinforcement እና ሌሎች Structural Details ያሳያል።

3️⃣ Plumbing & Sanitary Drawings
🔹 Water Supply Layout – የWater Pipes፣ Valves፣ Tanks፣ Pumps እና Fixtures አቀማመጥ።
🔹 Sanitary/Drainage Layout – የWastewater እና Soil Pipes አቀማመጥ።
🔹 Stormwater Drainage Plan – የዝናብ ውሃ መሰብሰቢያና ማስወገጃ ስርዓት።
🔹 Plumbing Isometric Drawing – የPlumbing Network በIsometric እይታ የሚያሳይ Drawing።
🔹 Riser Diagram – የቧንቧ ስርዓትን በVertical አቀራረብ የሚያሳይ Diagram።
🔹 Manhole/Inspection Chamber Detail – የManhole እና Inspection Chamber መጠን፣ Level እና Construction Details።

4️⃣ Electrical Drawings
🔹 Lighting Layout – የLighting Fixtures እና Switches አቀማመጥ።
🔹 Power Layout – የSockets፣ Outlets እና Electrical Equipment Connections።
🔹 Single-Line Diagram (SLD) – የElectrical Distribution System በቀላል አቀራረብ የሚያሳይ Diagram።
🔹 Distribution Board Schedule – የElectrical Circuits፣ Breakers እና Loads መረጃ።
🔹 Earthing/Grounding Drawing – የEarthing/Grounding System አቀማመጥ።
🔹 Lightning Protection Drawing – የLightning Protection System አቀማመጥ።
🔹 Cable Routing Drawing – የCables መንገድና Routing ያሳያል።

5️⃣ Mechanical & HVAC Drawings
🔹 HVAC Layout – የHeating፣ Ventilation እና Air Conditioning Equipment አቀማመጥ።
🔹 Ductwork Drawing – የAir Ducts መንገድ፣ Size እና Fittings።
🔹 Mechanical Piping Drawing – የMechanical Piping Network አቀማመጥ።
🔹 Equipment Layout – የMechanical Equipment ቦታና Arrangement።
🔹 HVAC Schematic – የHVAC System አሰራርና Connections የሚያሳይ Diagram።

6️⃣ Civil / Site Development Drawings
🔹 Topographic Survey Plan – የነባሩን Ground Elevation፣ Contours እና Existing Features ያሳያል።
🔹 Grading Plan – የታቀደውን Ground Level እና Slope ያሳያል።
🔹 Road Layout – የRoad Alignment፣ Width እና Geometry ያሳያል።
🔹 Longitudinal Profile – በRoad Alignment አቅጣጫ የGround እና Proposed Levels ለውጥን ያሳያል።
🔹 Cross-Section Drawing – በተወሰኑ Chainages የRoad/Earthwork ክፍልን ያሳያል።
🔹 Earthwork Plan – የExcavation፣ Filling እና Grading መረጃ ያሳያል።
🔹 Pavement Drawing – የPavement Layers እና Thicknesses ያሳያል።
🔹 Drainage Drawing – የCulverts፣ Ditches፣ Channels እና Stormwater Systems አቀማመጥ።
🔹 Culvert Drawing – የCulvert Dimensions፣ Reinforcement እና Construction Details።

7️⃣ Survey Drawings
🔹 Topographical Survey Drawing – የExisting Terrain እና Ground Features መረጃ።

🌟Complete Guide to Reading Building Drawings

📐መፅሃፉ የህንፃን ድሮዊንግ በተግባር ለመረዳት እና ስለ ጠቅላላ አርክቴክቸር ሳይነስ የሚዳስስ ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውሩዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aa7c4a30b34d_etconp
❤12👍1🥰1
ማስታወቂያ

ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ

የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://forms.gle/3y6E2EmAZSbboRg8A

@etconp
👍4
👉በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ፣ የአንድ ኮለም (column) ቱምቢው የተወሰነ ሲኖረው "5 ሚ.ሜ ብቻ እኮ ነው፤ ምንም አያመጣም በልስን ይስተካከላል" የሚለውን የተለመደ አባባል እንሰማለን።

ይህ የ "5 ሚ.ሜ ህግ" በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ የተለመደ ነው። ነገር ግን ይህ 5 ሚ.ሜ ከየት መጣ? የህንፃ ኮዱስ በእርግጥ ምን ይላል? እስኪ አብረን እንየው....

በኮንስትራክሽን execution ወቅት በሳይት ላይ የሚፈጠሩ የአሰራር ጉድለቶችን (workmanship errors) ታሳቢ ለማድረግ፣ የEBCS code (EBCS EN 1992-1-1:2013) አንቀጽ 5.2 ለጂኦሜትሪክ መዛባት (geometric imperfection) በdesign stage ታሳቢ እንዲደረግ በግልፅ አስቀምጧል። እውነታው ሲመረመር የሳይቱ "5mm" ህግ የመጣው ከነዚህ የኮድ እሴቶች የመነጨ ነው::

🚥1. የቱምቢ ችግር (Verticality/Plumbness): ኮዱ አንቀጽ 5.2(5) ላይ መሰረታዊ የማጋደል መጠንን/inclination (1/200) በማለት ያስቀምጣል።
ይህ ማለት በየ 1 ሜትር ቁመት 5 ሚ.ሜ ማጋደል በdesign ወቅት ታሳቢ መደረግ አለበት ማለት ነው::
ለምሳሌ የተለመደውን 3 ሜትር ቁመት ያለው ኮለም ብንወስድ፣ Design ሲደረግ ታሳቢ የሚደረገው አጠቃላይ ማጋደል 15 ሚ.ሜ (3000/200) ነው።

በሳይት ላይ የምናገኘው "5mm" ከ 15mm ስለሚያንስ እጅግ በጣም ጥብቅ (Conservative) ሆኗል ማለት ነው so ተቀባይነት አለው ማለት ነው።

🚥2. የሊኛ ችግር (Horizontal Shifting/Eccentricity): ኮዱ አንቀጽ 5.2(7)(a) ላይ braced systems ላሉ ኮለሞች የኤክሴንትሪሲቲ መጠንን (Lo/400) በማለት ያስቀምጣል, lo ማለት የኮለሙ clear height ነው።
ለ 3 ሜትር (3000 ሚ.ሜ) ኮለም፣ የሚፈቀደው የHorizontal Shifting 7.5 ሚ.ሜ (3000/400) ነው።

እዚህም ጋር የሳይቱ የ 5 ሚ.ሜ ልማድ በdesign stage ከታሰበው የ 7.5 ሚ.ሜ ገደብ በታች በመሆኑ ስህተቱን በአስተማማኝ ሁኔታ (safely) ያስተናግደዋል።

እዚህ ጋር ልንገነዘበው የሚገባው ዋና ነጥብ፣ እነዚህ 1/200 እና Lo/400 አሃዞች የሳይት ላይ ስህተት መለኪያ ሳይሆኑ፣ ገና በዲዛይን ደረጃ (Design Stage) በስትራክቸራል መሃንዲሱ ስሌት ውስጥ የገቡ ታሳቢዎች መሆናቸውን እና ከቻልን zero error ካልቻልን ግን ለzero የቀረበ ሥራ እንድንሰራ ነው::

🗂መዛባቱ ትክክለኛውን የኮድ ገደብ (Actual Code Limits) ቢያልፍስ ምን ይፈጠራል??

🌟አንድ ኮለም ከላይ ከተጠቀሱት የኮድ ገደቦች ውጭ ሲያፈነግጥ፣ በኮለሙ ላይ የሚከተሉት ከባድ ስትራክቸራዊ ችግሮች ይፈጠራሉ እነሱንም እንደሚከተሉት አቀርብላችኋለሁ

🚥1. ያልታሰበ የጎንዮሽ ሞመንት መፈጠር (Unintended & Biaxial Bending): ኮለሙ ከሴንተር ላይኑ ሲያፈነግጥ ከላይ የሚመጣው ሸክም (axial load) በቀጥታ በኮሎሙ የክብደት ማዕከል (centroid) ላይ አያርፍም።
ይህ eccentricity በዲዛይን ወቅት ያልታሰበ ተጨማሪ ሞመንት (additional moment) በኮሎሙ ላይ ይፈጥራል(M=N*e)።
ኮሎሙ በሁለቱም አቅጣጫዎች (x እና y) ካጋደለ ደግሞ፣ ስትራክቸሩን ለበለጠ ጫና የሚያጋልጥ የሁለት አቅጣጫ ሞመንት (Biaxial Bending) ይፈጠራል ማለት ነው።

🚥2. የሁለተኛ ደረጃ እና የ P-Delta ተፅዕኖ (Second-Order & P-Delta Effects): መዛባቱ በጨመረ ቁጥር የኮሎሙ የጎንዮሽ ዝንበሌ (Deflection) ይጨምራል። ከላይ የሚያርፈው ሸክም በዚህ ያጋደለ ኮሎም ላይ ሲያርፍ፣ ሸክሙ እና Deflection ተባዝተው ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ ሞመንት ይፈጥራሉ (P-Delta effect)።
ይህ ተፅዕኖ በተለይ ለቀጫጭን እና ረዣዥም ኮለሞች (slender columns) የኮሎሙን ሸክም የመሸከም አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እንዲቀንስ ያደርገዋል።

🚥ሌላኛው የስትራክቸር መጎዳት እና የመሰበር አደጋ (Structural Distress & Failure): በመዛባቱ ምክንያት የተፈጠረው አጠቃላይ ሞመንት ኮለሙ design ከተደረገበት አቅም (design capacity) በላይ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ያለው ኮንክሪት መሸርሸር እና መሰንጠቅ (concrete crushing/spalling) ይጀምራል።

▶️በሌላ በኩል ያለው ብረት (reinforcement) ከአቅም በላይ በመወጠር (yielding) ውሎ አድሮ ኮለሙ buckling failure ሊያጋጥመው ይችላል ማለት ነው።

▶️ይህን ከገደብ በላይ የሆነ መዛባት የሚያስከትለውን ከባድ የስትራክቸር አደጋ ከተረዳን "መቻቻል (tolerance) አለ" ብለን በስራችን ላይ ፈፅሞ መዘናጋት የለብንም።

⏺ይልቁንም በሳይት ላይ ስራዎችን ስንሰራም ሆነ ስናሰራ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና የጥራት ቁጥጥር በማድረግ፣ እንዲህ አይነት አደገኛ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ የቻልነውን ሁሉ ማድረግ የሁላችንም የሙያ ግዴታ መሆኑን ላስታውሳቺሁ እወዳለሁ።

🏛የQuantity Surveying እና Building Construction Estimation ከ ሀ አስከ ፐ ችሎታዎን በተግባራዊ ምሳሌዎች የሚያሳድጉበት ምርጥ መፅሐፍ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8dd294cbaa9_etconp
❤3👍1🥰1
🏛ምርጥ ቤዝመንት ያለው G+5 ህንፃ ማለትም አርክቴክቸራል፣ስትራክቸራል፣ኤሌክትሪካል እና ሳኒተሪ ያካተተ በ Auto Cad የተሰራ ዲዛይን ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a75638f22910_etconp

@etconp
🥰4👏1😢1
👉የሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ሳይጠብቁ በሚሠሩ አልሚዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ!

🌟​በአዲስ አበባ ከተማ የሕንፃ ደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟሉ እና ለአደጋ አጋላጭ በሆነ መልኩ ግንባታዎችን ሲያካሂዱ በተገኙ አልሚዎች፣ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ላይ የገንዘብ ቅጣትና አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

​የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር አመለወርቅ አሰፋ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በተከናወኑ የመስክ የቁጥጥርና ክትትል ሥራዎች ሕግን እና የደህንነት ደንቦችን አፍንጫቸው ስር ጥሰው የሚገኙ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።

🚥​በዚህም መሠረት፡-

​በአልሚዎች ላይ፦ ሕጋዊ የደህንነት መስፈርቶችን ባላሟሉ አካላት ላይ የገንዘብ ቅጣት ተጥሏል።

​በኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ላይ፦ ተገቢው ጥንቃቄና ቁጥጥር ሳያደርጉ ቀርተዋል ተብሎ የታመነባቸው ላይ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎች ተወስደዋል።

​የደህንነት ጥንቃቄ ለሕይወትና ለንብረት ዋስትና ነው!

​እንደ ኢ/ር አመለወርቅ ማብራሪያ፣ የሕንፃ ደህንነት መስፈርቶችን ሳይከተሉ የሚከናወኑ ግንባታዎች በሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች፣ በአካባቢው ማህበረሰብ እና ነዋሪዎች ላይ ሕይወት የማጥፋት፣ የአካል ጉዳት የማድረስ እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት የማስከተል አደጋቸው ከፍተኛ ነው።

​"የሕንፃ ግንባታ ደህንነትን ማስጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ነው፤ ሕግን ማክበር ሕይወትን ይጠብቃል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፣ መሰል የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል። በመሆኑም ሁሉም አልሚዎች፣ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች ሕንፃዎችን ሲገነቡ የደህንነት ጥንቃቄዎችን ሙሉ በሙሉ አሟልተው እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቧል።
​
─────────────────
👉Construction Safety & Compliance Kit – ፕሮፌሽናል Safety Templates ጥቅል ይፈልጋሉ?🦺

📋 Safety Checklists
🗣️ Toolbox Talk Templates
📝 Incident Report Forms
⚠️ JSA Templates
🥾 PPE Inspection Sheets

✅ Editable Word Document👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a88471586c15_etconp
❤5👏2🥰1
👉ደቡብ ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ አዲስ ግድብ ልትገነባ መሆኑን አስታወቀች፡፡

የደቡብ ሱዳን የሀይልና ግድብ ሚኒስትር የሆኑት አጎክ ሙካር አገራቸው አዲስ የግድብ ፕሮጀክት ልትጀምር መሆኑን ገለፁ፡፡

ይህ ግድብ ‹‹ፉላ›› የሚባል ሲሆን የፕሮጀክቱ መጠሪያ ደግሞ ‹‹የታላቁ ፉላ ሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክት›› የሚል ነው፡፡ እንደዘገባዎች ከሆነ ግድቡ በነጭ አባይ ወንዝ የሚገነባ ነው፡፡

1080 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው ይህ ግድብ የሚገነባውም ኡጋንዳ ድንበር አቅራቢያ ነው፡፡

ሚኒስትሩ የግድቡ እቅድ አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረት የተነሳ ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱን አውስተዋል፡፡

አሁን ግን ከአለም አቀፍ የልማት ፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ማግኘታቸውን ጠቅሰው በፕሮጀክቱ ላይ የአዋጪነት ጥናት ተሰርቶ መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

በግድቡ ግንባታ ዙሪያ ከግብፅ በኩል የተለያዩ ስጋቶችና ማስፈራሪያዎች እየደረሷቸው መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ በአባይ ተፋሰስ አገራት ሚኒስትሮች ምክር ቤት በኩል መፅደቁን አስረድተዋል፡፡ በንግግራቸው ማጠቃለያም ‹‹የፉላ ግድብን ለመስራት ዝግጅት እያደረግን ነው ግብፅንም አንፈራም›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

@etconp
👍7❤3🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ  እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል የተባለዉ አዲስ የፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ከሰሞኑ ይፋ ተደርጓል።

🌟ይህ ስታንዳርድ ለዘርፉ ምንድነዉ?  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ በዚህ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

📉ለድርጅታቹ እድገት እና ስራቹ በቀላሉ ማስተዳደር እንድትችሉ የሚያግዝ ሙሉ የ በ EXCEL የተገነባ ሲስተም ፋይል አዘጋጅተንላቹዋል ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aaa29dcad3b0_etconp
❤4👏2👍1
👉በኮንስትራክሽን ዘርፍ የኳንቲቲ ሰርቬየር ሚና ምንድ ነው?

🏷Quantity surveyor ማናቸውም በግንባታ ዙሪያ ለተካተተ ሥራ የሚያስፈልገውን የቁጥር ብዛት በማስላት ወጪውን ያሰላል፤በእቅድ እና በተዛማጅ ሥራ በዋናነት በግንባታ ወጪ ስሌት ውስጥ ይሳተፋል።

⭐️የ Quantity surveyor ሚና ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦
‎    
1.ዋጋ መገመት
‎   
2. ወጪ ማዕቅድ
‎    
3. ወጪዎችን ማዘጋጀት, መካፈል እና መተንተን ጨረታዎች እና ኮንትራቶች
‎    
4. የግዥ ምክር /Procurement advice
‎    
5. የክፍያ መጠየቂያዎችን ማዘጋጀት(BOQ)
‎    
6. በጀት የመቆጣጠር
‎    
7. የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ እና የምስክር ወረቀት ዝግጅት
‎    
8. የእለት  ግምገማ ማድረግ
‎    
9. ግጭትን መፍታት/Dispute resolution
‎   
10. የአዋጭነት ጥናቶችን በማዘጋጀት
‎   
11. የወጪ ቁጥጥር
‎   
12. የዋጋ ምህንድስና/Value engineering.
‎   
13. በዋጋ ገደቦች እና በጀቶች ላይ ምክር
‎   
14. የህይወት ዑደት ወጪ/Whole life cycle costing
‎   
15. ለዋስትና ዓላማዎች የሚውል የዋጋ ትመና/Valuation for insurance purposes
‎   
16. የፕሮጀክት አስተዳደር

17. በውል ክርክር ላይ ምክር/Advice on contractual disputes

18. የመጨረሻውን መለያ ዝግጅት

19. የሳይት ጉብኝቶች, ግምገማዎች እና ትንበያ ለወደፊት ሥራ

20. የተጠናቀቀ ሥራን መተንተን እና ያመቻቻል ለኮንትራክተሮች ክፍያ

21. መጪውን ሥራ ለኮንትራክተሮች መመደብ/ከእነዚህ በተጨማሪ quantity surveyors በግንባታው በተወሰነ ቦታ ውስጥ ልዩ እንደ ወጪና ምክር ባሉ ኢንዱስትሪ እና ትኩረት ያድርጉ የንብረት ግብር፣ትግበራ ምንጮችን፣ነባር ሕንፃዎችን ለመጠገን.......ወዘተ ስራዎችን ኳንቲቲ ሰርቬየሩ ያስተገብራል።

🏛በነገራችን ላይ ሙሉ የ Quantity Surveying Full Course በቅናሽ ዋጋ በ ኦንላይን መማር ለምትፈልጉ 👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a5e233a9c5e0_etconp
❤5🥰4
🌉የBridge Design Excel Template ይፈልጋሉ?

🌟የድልድይ ዲዛይንና ስሌት ስራዎን በቀላሉ፣ በፍጥነትና በተደራጀ መልኩ ያከናውኑ።

✅ Bridge Geometry
✅ Deck & Girder Design
✅ Girder Calculations
✅ Bearing Calculations
✅ Automated Excel Calculations የያዘ 👷‍♂️ለCivil & Structural Engineers፣ Bridge Designers፣ Contractors እና Engineering Students ተስማሚ የሆነ ፋይል ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aa299412b4e4_etconp
🥰2👏2
👉በመንገድ Construction ላይ BM/Benchmark ሲቋቋም በየተወሰነ ርቀት GPS Control Point የሚወሰደው ለምንድን ነው❓
━━━━━━━━━━━━━━━
🚥በመንገድ (Road Construction) ላይ BM (Benchmark) ሲቋቋም በየተወሰነ ርቀት GPS Control Point የሚወሰደው ምክንያቶች አሉ።

1. BM (Benchmark) ምንድን ነው?
━━━━━━━━━━━━━
✅Elevation (RL) የሚያሳይ ቋሚ መመዘኛ ነጥብ ነው።
✅በLevel instrument ተጠቅመው የከፍታ ሥራዎችን ለመጀመር ያገለግላል።

2. GPS Control Point ምንድን ነው?
━━━━━━━━━━━━━
✅X, Y እና Z (Easting, Northing, Elevation) በትክክል የሚያሳይ ቋሚ ነጥብ ነው።
✅Total Station እና GNSS/GPS ሥራ ለማስጀመር ያገለግላል።

3. ለምን BM ብቻ አንጠቀምም?
━━━━━━━━━━━━━
✅ምክንያቱም BM ከፍታ (RL) ብቻ ይሰጣል፤ አቀማመጥ (Coordinates) አይሰጥም። ነገር ግን GPS Control Point ሙሉ Coordinate (X, Y, Z) ይሰጣል።

4. GPS Control Point ጥቅሙ
━━━━━━━━━━━━━
✅የመንገዱን Centerline እና Alignment በትክክል ለማስቀመጥ።
✅Total Station ለማስተካከል (Setup)።
✅BM ቢጠፋ ወይም ቢጎዳ እንደገና ለመመስረት።
✅የSurvey ስህተት ለመቆጣጠር።
✅ፕሮጀክቱን ከብሔራዊ ኮኦርዲኔት ሲስተም ጋር ለማገናኘት።

5. ሁሉንም BM ማድረግ አንችልም?
━━━━━━━━━━━━━
መደረግ ይቻላል፣ ነገር ግን BM ብቻ በቂ አይደለም። ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክቶች ሁለቱንም (BM እና GPS Control Points) በአንድነት ይጠቀማሉ። BM ከፍታን ይቆጣጠራል፣ GPS ደግሞ አቀማመጥንና ከፍታን በአንድ ላይ ይሰጣል።

🌟በእርስዎ የመንገድ ሥራ ላይ እንደ Surveyor ወይም Site Engineer የሚጠቀሙበት BM → TBM → GPS Control Point → Total Station Setup የሥራ ፍሰትን በስዕል አብራርቶ ማሳየት ይቻላል።
━━━━━━━━━━━━━━━
👉የመንገድ ስራ BOQ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aa4f7a526f13_etconp
3❤6👏1
👉የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ዲዛይን ሃይማኖታዊ ይዘቱ ጠብቆ ከመሠረታዊ የሕንፃ አካላት እስከ የተለያዩ ክፍሎችና የሕንፃ ቅርፆች በቀላልሉ ለመረዳት የተዘጋጀ ምርጥ የአማርኛ ኮንስትራክሽን መፅሐፍ ከፈለጉ ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6a8a873add2d7_etconp
❤3🥰2
📢 JOB VACANCY ANNOUNCEMENT

🏗️ BM Technology PLC is seeking qualified and experienced professionals for the following roles:

👷 Senior Office Engineer – 4 Positions
• BSc/MSc in Civil Engineering or related field
• 6 years general experience, including at least 4 years as an Office Engineer

📋 Project Manager – 2 Positions
• BSc/MSc in Civil Engineering or related field
• 8 years general experience, including at least 4 years as a Project Manager

🏗️ Senior Site Engineer – 2 Positions
• BSc/MSc in Civil Engineering or related field
• 4 years general experience, including at least 2 years as a Senior Site Engineer

🔧 Construction Engineer – 2 Positions
• BSc/MSc in Civil Engineering or related field
• 6 years general experience, including at least 2 years as a Construction Engineer

📝 Office Engineer – 2 Positions
• BSc/MSc in Civil Engineering or related field
• 4 years general experience, including at least 2 years as an Office Engineer

👷 General Foreman – 3 Positions
• Level IV Diploma in Building Construction or related field
• 6 years general experience, including at least 4 years as a General Foreman

Total Vacancies: 15

📩 How to Apply:
Interested and qualified candidates should send their CV and relevant credentials to:
📧 merony1992@gmail.com

⏰ Deadline: October 3, 2026
Only candidates meeting the stated requirements will be considered.

@etconp
👍5❤4🥰1
👉የግንባታ ፕሮጀክትዎን BOQ፣ ወጪ፣ የሥራ አፈጻጸም፣ ክፍያ፣ Cash Flow እና Profit/Loss በአንድ ፕሮፌሽናል Excel System በቀላሉ ለማስተዳዳር የሚጠቅም Editable Microsoft Excel System ለContractors፣ Engineers፣ Quantity Surveyors፣ Construction PLCs፣ Consultants፣ Project Owners እና Project Managers ይጠቅማል ከታች ባለው ሊንክ ያውርዱት👇

https://ye-buna.com/etconp?ref=product_detail&product=6aaf8ac262672_etconp
❤4👏2
👉የሳምንቱ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽንና ቴክኖሎጂ ዜናዎች 🏗️🌍

​ለዚህ ሳምንት የዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን፣ ሪል ስቴት እና መሠረተ ልማት ዘርፍ ትኩረትን የሳቡ ዋና ዋና ክስተቶች እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦

​አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በግንባታ ደህንነት ቁጥጥር ላይ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ግንባር ቀደም የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች የደህንነት ካሜራዎችን ከ AI ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት በግንባታ ቦታዎች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ የሚጠቁም ሥርዓት በስፋት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

ቴክኖሎጂው ሠራተኞች የግንባታ እቃዎችን በትክክል ማጥለቃቸውን በራስ-ሰር በመከታተል የሥራ ላይ አደጋዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ችሏል።

​የካርቦን ልቀት ቅነሳ እና 'ግሪን ሲሚንቶ' (Green Cement)
ዓለም አቀፍ የሲሚንቶ አምራቾች ማህበር ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት፣ በግንባታ ግብአቶች ዘርፍ የሚወጣውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

በተለይ እንደ ቮልካን አሽ እና በኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች ላይ የተመሰረቱ የሲሚንቶ ማምረቻ ቴክኖሎጂዎች በፈረንሳይ እና ጀርመን በስፋት ወደ ሥራ እየገቡ ናቸው።

​የዲጂታል መንታ (Digital Twin) እና አውቶሜትድ የከርሰ ምድር መሠረተ ልማት
በእስያ እያደጉ ባሉ መካከለኛ እና ታላላቅ ከተሞች፣ የትራፊክ መጨናነቅን እና የቧንቧ መስመር ጥገና ፈተናዎችን ለመቅረፍ ባለ ብዙ ደረጃ የከርሰ ምድር መሠረተ ልማት ኔትወርኮች እየተገነቡ ይገኛሉ።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ በሮቦቲክስ እና በዲጂታል መንታ ቴክኖሎጂዎች የሚታገዙ ሲሆን፣ የከተሞችን የረጅም ጊዜ ዘላቂነት እያረጋገጡ ይገኛሉ።

​በሞጁላር እና ቅድመ-ግንባታ (Prefabrication) ሕንፃዎች ላይ የሚታየው ዕድገት በአሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሪል ስቴት ገበያ የጊዜ እና የወጪ ቆጣቢነቱን ከፍ ለማድረግ በፋብሪካ ተጠናቀው የሚገጠሙ የሞጁላር ህንፃዎች ፍላጎት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው። ይህ አሰራር የግንባታ ጊዜን እስከ 40 በመቶ መቀነስ እንደቻለ የዘርፉ ጥናቶች ያመለክታሉ።

Via Ethio Con

​ለተጨማሪ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን መረጃዎች እና ጥናቶች ከታች ባለው ዋናው ቻናላችን ይቀላቀሉ👇

───────────────────

https://t.me/ETCONp
❤5🥰1👏1