የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
ከገቢ ግብር ነፃ የሆነ ገቢ
****************************
የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-
ሀ) ሚኒስትሩ በዚህ ፊደል ተራ በቁጥር (2) ፣ (3) ፣ (4) እና (6) በተመለከቱት ላይ በሚያወጣው መመሪያ የሚያደርገው ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተቀጣሪው የሚከፈሉ የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-
(1) ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
(2) በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
(3) በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤
(4) ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤
(5) የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤
(6) የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤
(7) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤
ለ) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
ሐ) ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመውዝ 15% (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
መ) በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
ሠ) የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤
ረ) በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
ስ) በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡-
(1) ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ፤
(2) ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፤
ሽ) በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት፤
ቀ) በተቀባዩ ላይ በደረስ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
በ) የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
ተ) በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
ቸ) ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
ን) ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
ነ) ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
ኘ) በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
አ) ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
ከ) በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ::
👍1
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
አንድ ሰው አስቦ ወደ ሌላ ሰው ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ ካስተላለፈ በስህተት ወይም ተጭበርብሮ መሆኑን ካላስረዳ ገንዘቡ እንዲመለስ የመጠየቅ መብት የሌለው መሆኑን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
Join👇
https://t.me/ethiolawtips
የወንጀል ህግ መርሆች

መግቢያ

ወንጀል ማለት በህግ አስቀጪነቱ የተደነገገውን ድርጊት በማድረግ ወይም ባለማድረግ የህግ ተጠያቂነት እና ቅጣትን የሚያከትል ድርጊት ነው። የወንጀል ህግ ደግሞ ወንጀል ስለሆኑ ድርጊቶች እና አለማድረጎች እንዲሁም ቅጣታቸውን የሚዘረዝር የህግ አይነት ነው። የወንጀል ህግ የራሱ የሆኑ መርሆች ያሉት ሲሆን በሀገራችንም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እና የወንጀል ህጉ አለማቀፋዊ ባህርይ ያላቸውን መርሆች አካተው የወጡ ናቸው። በዚህ ፅሁፍ በህገ መንግስቱ እና በወንጀል ህጉ የተደነገጉ የወንጀል ህግ መርሆች በአጭሩ እንመለከታለን።

• የወንጀል ህግ መርሆዎች

“መርህ” ማለት የአንድ ነገር ማጠንጠኛ መሰረት ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በቀላሉ የማይለወጥ፣ የማይሸረሸር፣ ሊጣስ የማይገባውና ከተጣሰ ግን ያ በሱ ላይ የተመሰረተው ፍሬ ሀሳብ ህልውናው ሊናጋ ስለሚችል መርሁ ወይም መሪው ሀሳብ በሚገባ ሊጠበቅና ሊያዝ የሚገባው ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ደስታ ተክለ ወልድ በአማርኛ የመዝገበ ቃላት መፅሐፋቸው “መርህን” “የመራ፣ የሚመራ፣ መሪ” በሚል የተረጎሙት። በመሆኑም ህጎች ሲወጡም ሆነ ሲተገበሩ የህግ መርሆችን መሰረት ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል። በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን ተቀባይነት ያላቸው እና በሥራ ላይ እየዋሉ የሚገኙ የወንጀል ህግ መርሆችን እንደሚከተለው እንመለከታለን።

1. የሕጋዊነት መርህ (Principle of Legality)፡- የህጋዊነት መርህ

መሰረታዊ ሀሳብ በህግ ከተደነገገው ውጪ ቅጣት ሊኖር አይችልም የሚል ነው። በመሆኑም ማናቸውም ሰው የተከሰሰበት ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑን የሚደነግግ ህግ ከሌለ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆንና ሊቀጣ አይገባውም የሚል ነው፡፡ አንድን ሰው ሆነ ብሎም ይሁን በቸልተኝነት አንድ ድርጊት ፈፅመሀል ወይም መፈፀም የሚገባህን አልፈፀምክም ብሎ ለመክሰስና በወንጀል እንዲቀጣ ለማድረግ የወንጀል ፈፃሚው ድርጊት ወይም ተዓቅቦ በወንጀልነት የሚፈርጅና የወንጀል ቅጣት የሚደነግግ አስቀድሞ የታወጀ ህግ መኖር አለበት፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ሕገ-ወጥነቱ በህግ ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት እንደወንጀል ሊቆጥረው እና ቅጣትን ሊወስን እንደማይችል በወንጀል ህጉ እንቀፅ 2(2) ስር ተደንግጎ ይገኛል። እንዲሁም ፍርድ ቤቱ በህግ ከተደነገገው በቀር ሌሎች ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን መወሰን አይችልም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ የተመሳሳይነት (analogy) ጉዳይ ሲሆን በህግ ላይ ከተደነገጉት ወንጀሎች ጋር ይመሳሰላል በማለት ወንጀልነቱ በግልፅ ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት እንደወንጀል ሊቆጠር እንደማይችል የወንጀል ህጉ አንቀጽ 2(3) ይደነግጋል።

2. የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑ (Non-Retroactivity of Criminal Law)

በዚህ መርህ መሰረት ህግ ሊተገበር ወይም ሊፈፀም የሚችለው ህጉ ከፀደቀ በኋላ በተፈፀሙ ድርጊቶች ላይ ነው። ይህ ማለት አዲስ ህግ ሲወጣ ህጉ ከመውጣቱ በፊት የተፈፀሙት ድርጊቶች በአዲሱ ህግ ወንጀል መሆናቸው ቢደነገግም ለበፊቱ ድርጊት ተፈፃሚ አይሆንም። አንድ ሕግ የዜጎችን መብትና ግዴታ የሚወስን በመሆኑ ሰዎች ሕጉ እስከሚለወጥ ድረስ ድርጊቶቻቸውን ወይም ግንኙነታቸውን ሕጉ በሚፈቅደው ወሰን ውስጥ ያካሂዳሉ፡፡ አንድን ሁኔታ የሚለውጥ ወይም የሚያሻሻል ሕግ ቢወጣ ሕጉ ተፈፃሚ መሆን ያለበት ቢያንስ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ወደፊት መሆን አለበት፡፡

ይህ መርህ በወንጀል ህግ አንቀፅ 5 እና በህገ መንግስቱ አንቀፅ 22 ስር ተደንግጎ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በአዲሱ ወይም በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ እና በተሻረው የወንጀል ህግ እንደወንጀል የተቆጠረ ድርጊት የተፈፀመው አዲሱ ህግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ፣ ጉዳዩ የሚታየው በተሻረው የወንጀል ህግ መሰረት ነው። ድርጊቱ በአዲሱ ህግ መሰረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው ህግ ግን እንደወንጀል ካልተቆጠረና የተፈፀመው አዲሱ ህግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ አይችልም። እንዲሁም የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈፀመ ወንጀል ሲኖር በአዲሱ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም፤ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ እንደሚቋረጥ በወንጀል ህጉ ተደንግጓል።

የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ሄዶ አይሰራም ሲባል በመሰረታዊ ሕጉ ላይ ሁለት ዓይነት ውጤቶችን ያስከትላል፡፡ አንደኛው አንድ ድርጊት በሚፈፀምበት ጊዜ ድርጊቱ በጊዜው የማያስቀጣ ከነበረ ይኸው ድርጊት ከጊዜ በኋላ በወጣ ሕግ ወንጀል ነው ሊባል አይችልም፡፡ ሁለተኛው ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ወንጀል ቢሆንም እንኳን ወንጀለኛው መቀጣት ያለበት ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ተፈፃሚነት የነበረው የወንጀል ሕግ በደነገገው ጣሪያ መሆን አለበት የሚሉ ናቸው፡፡ ስለዚህም ከድርጊቱ በኋላ የወጣው ሕግ የቅጣት ጣሪያውን ከፍ ቢያደርገው ይህ ቅጣት ሕጉ ከመታወጁ በፊት ለተፈፀመ ወንጀል ተፈፃሚ መሆን የለበትም፡፡ ይሁንና አዲሱ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ከድርጊቱ ኋላ የወጣው ህግ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 22(3) ይደነግጋል። በተጨማሪ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 6 ስር እንደተደነገገው አዲሱ የወንጀል ህግ እንዲፀና ከተደረገ በኋላ አድራጊው ህጉ ከመፅናቱ በፊት ላደረገው ወንጀል ሲፈረድበት፣ ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ በሥራ ላይ ከነበረው ሕግ ይልቅ ይሄኛው ሕግ ቅጣት የሚያቀልለት ሲሆን በአዲሱ ህግ ላይ የተመለከተው ቅጣት ይፈፀምበታል።

3. ለአንድ ጥፋት አንድ ቅጣት መርህ (Principle of Double Jeopardy)

የዚህ መርህ መሰረታዊ ሀሳብ ሰው በአንድ የወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ በተቀጣበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና መከሰስና መቀጣት የለበትም የሚለው ነው፡፡ በዚህ መርህ ላይ አግባብነት ያላቸው የሕገ-መንግስቱና የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 23 “ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነ-ሥርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም” በማለት ሲደነግግ የወንጀል ሕጉም በአንቀፅ 2(5) ስር “ማንም ሰው በሕግ መሰረት የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ ከዚህ ቀደም በተቀጣበት ወይም ሌላ ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም” በማለት ደንግጓል፡፡

4. የእኩልነት መርህ (Principle of Equality)
የእኩልነት መብት ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ከሚመነጩ እና ከማይገረሰሱ አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች አንዱ ነው። ሰዎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል ናቸው የሚለው መርህ የመጣውም ከዚሁ የእኩልነት መብት ነው። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 25 ስር እንደተደነገገው ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በመሆኑም በዘር፣ በብሄር፣ ብሄረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 4 ይህንን መርህ በተመሳሳይ ሁኔታ ያስቀመጠ ሲሆን
አድራጊዎች መሐከል ልዩነት የሚደረገው ምንጩ የአለም አቀፍ ህግ ወይም ህገ መንግስት ሆኖ በወንጀል ህጉ የተደነገገ መሰረታዊ መብት ሲኖር ወይም የወንጀሉ ከባድነት፣ የጥፋቱ ደረጃ ወይም የአድራጊው ዕድሜ፣ ሁኔታ ወይም ልዩ ግላዊ ጠባዩ ወይም ወንጀሉ በሕብረተሰብ ላይ ያስከተለው አደጋ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ህጉ ሲደነግግ እንደሆነ ያስቀምጣል።

ከላይ ከተዘረዘሩት የወንጀል ህግ መርሆች በተጨማሪ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እና ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ንፁህ ሆነው የመገመት (Presumption of innocence)፣ ዝም የማለት መብት (the right to remain silent) እና ሌሎችም የተያዙ እና የተከሰሱ ሰዎች መብቶች በህገ መንግስቱ ተደንግገው ይገኛሉ።

ማጠቃለያ

በህገ መንግስቱም ሆነ በወንጀል ህጉ የተመለከቱ የወንጀል ህግ መርሆች ከላይ የተብራሩት ሲሆኑ ህግ አስከባሪ አካላት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር ሥራዎችን ሲያከናውኑ እነዚህን የወንጀል ህጉን መርሆች በጥብቅ መከተል ይጠበቅባቸዋ::
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
የመንግስት ሰራተኞች የስነ-ምግባር ጥሰት እና የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ
መግቢያ
ድስፕሊን የሚለው ቃል ስርዎ ቃሉ እንግሊዝኛ ቢሆንም ለተመሳሳይ አላማ በአማርኛም ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ከቃሉ አግባብ መረዳት እንደሚቻለው፣ ለአንድ ጥፋት የሚወሰድ የቅጣት እርምጃ መሆኑን መገመት ይቻላል። ቅጣት ያለጥፋት አይኖርም ተብሎ ይገመታል። ምንም እንኳን ሁልጊዜ ይህ ግምት ባይሠራም፣ በአመዛኙ ትክክል ይሆናል። ነገር ግን ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ተፈጸመ የተባለው ጥፋት በማስረጃ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይህ ጠቅላላ አስተሳሰብ እንደተጠበቀ ሆኖ ከርእሱ አጻር፣ መታየት ያለበትን ጉዳይ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017  አንቀጽ 96 እና ተከታዮቹ የተደነገገውን ቀጥለን እንመለከታለን።
ዓላማ
የዲስፕሊን ቅጣት ዓላማ የመንግሥት ሠራተኛው በፈጸመው የዲስፕሊን ጉድለት ተፀፅቶ በአመለካከቱና በሥነ-ምግባሩ እንዲታረምና ብቁ ሠራተኛ እንዲሆን ለማስቻል ወይም የማይታረም ሆኖ ሲገኝ ለማሰናበት እንደሆነ በአዲሱ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 አንቀጽ 96 ላይ ተደንግጓል፡፡ የዲስፕሊን ጉድለት የፈፀመ የመንግስት ሰራተኛ እንደ ጥፋቱ ክብደት የቃል ማስጠንቀቂያ፤ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፤ እስከ አሥራ አምስት ቀን ደመወዝ የሚደርስ መቀጮ፤ እስከ ሦስት ወር ደመወዝ የሚደርስ መቀጮ፤ እስከ ሁለት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ በሥራ ደረጃ እና ደመወዝ ዝቅ ማድረግ፤ ከሥራ ማሰናበት ቅጣቶች ሊወሰንበት እንደሚችል በአዋጁ አንቀጽ 97 ላይ ተደንግጓል፡፡
የዲሲፕሊን ጥፋት አይነቶች
አዋጁ ሁለት አይነት የዲሲፕሊን ጥፋት አይነቶች እንዳሉ ያስቀመጠ ሲሆን  ይህም ቀላል እና ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ናቸው፡፡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ቅጣቶች ማለትም የቃል ማስጠንቀቂያ፤ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፤ እስከ አሥራ አምስት ቀን ደመወዝ የሚደርስ መቀጮ ለቀላል የዲሲፕሊን ጥፋቶች የሚጣሉ ሲሆን እስከ ሦስት ወር ደመወዝ የሚደርስ መቀጮ፤ እስከ ሁለት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ በሥራ ደረጃ እና ደመወዝ ዝቅ ማድረግ፤ ከሥራ ማሰናበት ቅጣቶች ለከባድ የዲሲፕሊን ጥፋቶች የሚጣሉ ቅጣቶች ናቸው፡፡ ከሥራ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ በማድረግ የተቀጣ የመንግሥት ሠራተኛ የቅጣት ጊዜውን ሲያጠናቅቅ ሠራተኛው ከሚሰራበት ሥራ መደብ እና ደረጃ ቀጥታ ግንኙነት ባለው ጥፋት ምክንያት ከስራ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ ብሎ እንድሰራ ተቀጥቶ ካልሆነ በስተቀር ከመቀጣቱ በፊት ይዞት ከነበረው የሥራ መደብ ጋር ተመሳሳይ ክፍት የሥራ መደብ ካለ ያለምንም ተጨማሪ የደረጃ ዕድገት ሥነ-ሥርዓት፣ ከመቀጣቱ በፊት ይዞት ከነበረው የሥራ መደብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ክፍት የሥራ መደብ ካልተገኘ ክፍት የሥራ መደቡ በተገኘ ጊዜ ያለምንም ተጨማሪ የደረጃ ዕድገት ሥነ-ሥርዓት፣ በሥራ መደቡ ላይ እንደሚመደብ ተደንግጓል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 97(5) መሰረት የመንግሥት ሠራተኛ በዲስፕሊን ከተቀጣ በኋላ ቅጣቱ በሪከርድነት ሊቆይና ሊጠቀስበት የሚችለው፣ ቀላል የዲስፕሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ዓመት፣ ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት ከሆነ ቅጣቱ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ዓመት እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች ምን ምን እንደሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 98 ላይ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ በዚህም፡- 
  ሕጋዊ ትዕዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመለገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤
  ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤
  ተቋምን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር መሠማራት ወይም ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤
  በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤
  በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነት መደባደብ፤
  በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤
  ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤
  በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤
  የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤
  የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤
  በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
  በሥልጣን አለአግባብ መገልገል፤
  በሥራ ቦታ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም፤
  ከላይ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸም ናቸው፡፡
በሌላ በኩል አዋጁ ከባድ የዲስፕሊን ቅጣት አይነቶችን ቢዘረዝርም ቀላል የዲስፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች ግን ምን ምን እንደሆኑ በግልፅ አላስቀመጠም፡፡
የዲስፕሊን እርምጃዎች አወሳሰድ ሥርዓት
ይህ አዋጅ በአንቀጽ 99 ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ ሥረዓትን ያስቀመጠ ሲሆን በዚሁም መሰረት ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት መደበኛ የዲስፕሊን ምርመራ የሚያካሂድና የውሳኔ ሀሳብ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የሚያቀርብ የዲስፕሊን ኮሚቴ ማቋቋም እንዳለበት አዋጁ ያስቀምጣል፡፡ የዲስፕሊን ቅጣት የማንኛውንም ፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ ወይም ሳይከተል ሊወሰን እንደሚችልም በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
በዚሁም መሰረት በተቋቋመ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አማካኝነት ተጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበለት የመሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ በበቂ ወይም አሳማኝ በሆነ ምክንያት የውሳኔ ሀሳቡን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመቀበል ወይም ውድቅ ለማድረግ ይችላል፡፡ ነገር ግን የማንኛውም መንግሥት መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 98 መሰረት ተቋምን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር መሠማራት ወይም ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤ ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤ የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤ የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤ ላይ የተመለከተውን ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት መፈፀሙን ካመነ በዲሲፕሊን ኮሚቴው ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት የፈጸመው ሠራተኛ ከስራ እንዲሰናበት የቀረበለትን ውሳኔ ሀሳብና ጉዳይ ለመሥሪያ ቤቱ የሥራ አመራር ጉባኤ በማቅረብ ማስወሰን አለበት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በዚህ መሠረት በአንድ መስሪያ ቤት የሥራ አመራር ጉባኤ አማካይነት የተሰጠ ከሥራ የማሰናበት ውሳኔ በዚህ አዋጅ ወይም በሌላ ሕግ በተቋቋመ ማንኛውም አስተዳደራዊም ሆነ መደበኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሊታይ አይችልም።
በአዋጁ አንቀጽ 101 መሠረት የመንግስት ሰራተኛ ላይ የዲስፕሊን ክስ ከቀረበ ሰራተኛው ከተጠረጠረበት ጉዳይ ጋር አግባብነት ያላቸው ማስረጃዎችን በማበላሸት፣ በመደበቅ ወይም በማጥፋት ምርመራውን ያሰናክላል ወይም በመንግስት ንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያደርሳል፣ ከተከሰሰበት ጥፋት ክብደት አንፃር የሌሎችን ሰራተኞች ሞራል የሚነካ ወይም ተገልጋይ ሕዝብ በመስሪያ ቤቱ ላይ ሊኖረው የሚገባውን እምነት ያዛባል ወይም ተፈፀመ የሚባለው ጥፋት ከስራ ያሰናብተዋል ተብሎ ሲገመት ከስራ ታግዶ እንዲቆይ የሚደረግ መሆኑን አዋጁ ደንግጓል፡፡ በዚህም አንድ ሰራተኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው ከሁለት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ሲሆን የመንግስት ሰራተኛው በተከሰሰበት የዲሲፕሊን ጉድለት ምክንያት ከስራ እንዲሰናበት ካልተወሰነበት በስተቀር በእግዱ ወቅት ሳይከፈለው የቀረው ደመወዝ ያለ ወለድ ልከፈለው እንደሚገባም ተደንግጓል፡፡
መጠነ ሰፊ የዲስፕሊን ችግር ያለበት መሥሪያ ቤት ላይ የሚወሰድ ልዩ የዲሲፕሊን እርምጃ ፡-
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ክስን ስለማሻሻል
"👇በክስን ስለማሻሻል ፍ.ስ.ስህ.ቁ. 91. መሰረት አንድ ፍ/ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ማንኛውም ጊዜ ተከራካሪዎች ሲያመለክቱ ወይም በራሱ ጊዜ አቤቱታ እንዲሻሻል ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ ድንጋጌ በጠባቡ ሊተረጎም የሚገባው ነው፡፡ ለምሳሌ በአዲስ ማስረጃ ለማቅረብ ማሻሻልን ነሚጠቀሙ አሉ፡፡
👇በክስ ማሻሻል ስርዓቱና ዓላማ ቀድሞ ዳኝነት ከተጠየቀበት ጉዳይ ፈጽሞ የተለየ ጥያቄ ለማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ አንቀጽ 91፣342 (መዝ.ቁ 100475(ቅጽ 19)
👇ለአንድ ክስ መሻሻል ወይም ለክርክሩ መለወጥ ቀደም ሲል የቀረብን የክስ ምክንያት በመቀየር ለመሞገት ማቅረብ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራሩ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ነው በሚል ክስ እንዲሻሻል የሚፈቅድበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ የፍ/ስ/ስ/ቁ. 91(1፣2)
👇 በመጀመሪያ በቀረበ የክስ መከላከያ መልስ ያልተካተትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መልስ አንዲሻሻል በሚል ፍ/ቤት በሰጠው ትእዛዝ መነሻነት ተካቶ ሲቀርብ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አንቀጽ 91፣244፣ መዝ.ቁ. 55973(ቅጽ 12)
👇 ከሳሽ ያቀረበው ክስ እና የክሱ ዝርዝር ይዘት የተለያየ ሆኖ የተገኘ ከሆነ ፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በማዘዝ ፤የክርክሩን ሂደት መምራት ያለበት ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91(1) (መዝ.ቁ 122249 (ቅጽ 20)."
Join
https://t.me/ethiolawtips
ክስ የማቅረብ መብት (Locus standi/the law of standing) የህዝብ ጥቅምን (public interest) በሚመለከቱ ጉዳዮች
#በዳንኤል ፍቃዱ የህግ ቢሮ
> በከሳሽ ተሰይሞ ክስ በችሎት (ፍርድ ቤት) የማቅረብ መብትን የሚመለከት ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብት አለዉ ለማለት የሚቻለዉ፡-
> ለክሱ ምክንያት የሆነዉ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተዉ መሆኑ፤
> ክሱ ለክሱ መነሻ የሆነዉ ጉዳት መከሰቱን የሚያሳይ፤
> በህግ ዕዉቅና የተሰጠዉ (ሊፈጸም የሚችል) መብት መኖሩ፤
> የባህላዊ ክስ የማቅረብ መብት (Traditional Locus Standi) በተለምዶ፣ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት (locus standi) የሚኖረው በቀረበው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ የግል ጥቅም ወይም ጉዳት (direct personal interest) ላለው አካል ብቻ ነው። ይህ አቀራረብና ዓላማው ግብረገብ ወይም የሕግ አጠቃቀምን የሚጠይቁ ጉዳዮች በተመለከተ ብቻ ነው።
• ይሁንና ክሱ የህዝብ ጥቅምን (public interest) የሚመለከት ሲሆን ለክሱ ምክንያት የሆነዉ በቀጥታ ከሳሽን የሚመለከተዉ ባይሆንም ክስ ማቅረብ እንደሚቻል በጊዜ ሂደት ተቀባይነት እያገኘ የመጣ አሠራር ነዉ፡፡
• በርካታ አገራት በህገ መንግስቶቻቸዉ ይህን አመላክተዋል፡፡
• ክስ የማቅረብ መብት ከአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 11(3) አንፃር፡-
> 11(4)- ማንኛዉም በጉዳዩ መብት ወይም ጥቅም ያለዉ ሰዉ ወይም ጉዳዩን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ ሰዉ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን ለማስከበር አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዉ፡፡
> ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ አንድ ሰዉ ለክሱ ምክንያት በሆነዉ ጉዳይ ላይ መብትና ጥቅም ያለዉ መሆኑን ማሳየት ሳይጠበቅበት ክሱን ለማቅረብ በቂ ምክንያት ያለዉ መሆኑን ካሳየ ክስ ማቅረብ የሚችል መሆኑን ነዉ፡፡
> ማንኛዉም ሰዉ በፍርድ ሊወሰን የሚገባን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በህግ የመዳኛት ስልጣን ላለዉ አካል የማቅረብ ዉሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለዉ፡፡አንቀጽ 37 የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብትን ተመላክቷል፡፡
> የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 11 (3) ነዉ፡፡ “…በዚህ አዋጅ ሌሎች ድንጋጌዎች እንዲሁም በሌሎች ህጎች የተመለከተዉ ቢኖርም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ ታይተዉ ሊወሰኑ የሚችሉ በሕገ መንግስቱ ምዕራፍ ሦስት (ከአንቀጽ 13 እስከ 44- ስር የተመለከቱ መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶችን ለማስከበር ለጉዳዩ ተገቢ የሆነ ፍርድ፣ ትዕዛዝ ወይም ዉሳኔ ለመስጠት ስልጣን አለዉ፡፡ (Notwithstanding the provisions of this proclamation and other relevant laws, the Federal High Court can render decisions, judgments or order in order to protect justiciable human rights specified under chapter three of the Constitution).
> በፍርድ ታይተዉ ሊወሰኑ የሚችሉ መብቶች የትኞቹ ናቸዉ? ሲቪል ወይም ፖለትካ መብቶች ነዉ ወይስ የትኖቹ ናቸዉ?በዚህ ላይ አዋጁ ላይ ምንም አልተባለም፡፡የሌሎች ሀገራትን ለምሳሌ በፍርድ ታይተዉ ሊወሰኑ የሚገቡት ጉዳዮች ተለይተዉ በህጋቸዉ ተደንግጎ ይገኛሉ፡፡
> በቂ ምክንያት ማለትስ ምንድን ነው? አከራካሪ ሃሳብ በመሆኑ ለፍርድ ቤት ትርጉም ክፍት ሆኗል፡፡
ተወካይ በውክልና የተሰጠው ንብረት ወካዩ አካል እንዲመልስለት ሲጠይቀው አልመልስም ማለት ይችላል? ሊጠየቅ የሚችለው በወንጀል ወይስ ፍትሐብሔር??
ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ግሩፕን ይቀላቀሉ!!

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 676/2/ አንድ ወኪል በውክልና ስልጣኑ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆነ በውክልና ስልጣኑ መሰረት አደራ የተቀበለውን ተዋዋይ ወገን እምነት አጉድሏል ተብሎ በወንጀል የሚጠየቅ ስለመሆኑ በግልፅ ያሳያል።

በመሆኑም በውክልና የተቀበለውን ንብረት ለወካዩ አልመልስም ማለቱ በማስረጃ ተረጋግጦ በወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ ቢቀጣ ጉዳዩ የፍትሃብሄር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በወንጀል ህግ 23 /2/ እና 676/2/ መሰረት የወንጀል ጉዳይ ጭምር በመሆኑ ተከሳሽ በፍትሃብሄር እንጅ በወንጀል አያስጠይቀኝም በሚል የሚያቀርበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ ወኪል ከወካዩ በውክልና ስልጣኑ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆነ በእምነት ማጉደል ወንጀል ሊያስጠይቀው ይችላል። ሰ/መ/ቁ 16408 ቅጽ/13 ላይ ውሳኔ ተሰጥቶበታል !!


📱  https://fb.me/tebekasamuel

🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel

👉 @tebekasamuel
                                        
👉 @tebeka

Contact @samuelgirma

☎️ 0911190299

#Ethiopia 🇪🇹 #samuelgirma

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ

☎️ 0911-190-299

⚡️
https://t.me/boost/tebekasamuel
https://t.me/boost/tebekasamuel
👍1
በፍትሐብሔር ክርክር የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች ማን መቼ ያነሳቸዋል?
በፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት እና በተከራካሪዎች
1. በተከራካሪዎች
ከሳሽ በተከሳሽ ላይ በቃል ክርክር ጭምር (በቅፅ 25 በሰ/መ/ቁ.222297)
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.358 መሰረት የመቃዎሚያ ከሳሽ የሆነ ተከራካሪ (በቅፅ 26 በሰ/መ/ቁ.196255)
ከሳሽ በጣልቃ-ገብ ላይ (ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.244 (1) (2) ማንኛውም ተከራካሪ)
ተከሳሽ በከሳሽ ላይ ፡-መርህ ነው 234 (1) (ሐ) እና ብዙ የሰበር ውኔዎቾ
ጣልቃ-ገብ በከሳሽ እና በተከሳሽ (በቅፅ 20 በሰ/መ/ቁ.108647)
አንዱ ተከሳሽ በሌላኛው ተከሳሽ ላይ (በቅፅ 12 በሰ/መ/ቁ.49295)
ባልተነጣጠለ ሃላፊነት በቀረበባቸው ክስ አንዱ ተከሳሽ ያነሳው የይረጋ መቃዎሚያ ሌሎች ተከሳሾች ባያነሱትም ክሱን ያቋርጣል (በቅፅ 4 በሰ/መ/ቁ.19081)
ፍርድ ቤት በራሱ አነሳሽነት የሚያነሳቸው መቃዎሚያዎች
ፍ/ቤቱ የሥረ-ነገር ሥልጣን የለውም (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9 እና 231 (1) (ለ) )
የክስ ምክንያት የለውም (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.9 እና 231 (1) (ለ))
ጉዳዩ በውሳኔ ያለቀ ነው (ቅፅ 13፣ ሰ/መ/ቁ.58119)
በፍሕብሔር የሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተቀመጡ ይርጋዎች (ቅፅ 1፣ ሰ/መ/ቁ.17361)
ዝርዝሩን ከመጽሐፉ በሰፊው ተዳሷሌ።
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የቀብድ ህጋዊ ውጤት


1 ቀብድ ሻጭና ገዥ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ ውል መፈፀማቸውን እርግጠኛ ሲሆኑ የሚቀባበሉት ገንዘብ በመሆኑ ይህን ማድረጋቸው ገንዘቡን ለመቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን ውሉን ለመዋዋላቸውም ማስተባበያ የማይቀርብበት ማስረጃ መሆኑን የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1883 ይደነግጋል።

ገዥና ሻጭ አንድን ቤት ሲሻሻጡ በፍትሀ ብሄር ህግ 1723(1) ስር የተመለከተውን ፎርም ባያሟሉም ሻጭ ለዚሁ የሽያጭ ውል ማስፈፀሚያ ቀብድ መቀበሉ ከተረጋገጠ በማያከራክር ሁኔታ ውሉ መደረጉን ያረጋግጣል። አንድ ውል የህጉን ፎርም ካላሟላ በህግ ፊት የማይፀና ይሆናል ነገር ግን በልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ ካለ ውሉ የህጉን ፎርም ያላሟላ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የማያከራክር ማረጋገጫ ስለሆነ ውሉ የፀና ይሆናል።

(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ መዝገብ/ቁ 56794 ቅፅ 12)

የተከፈለው ክፍያ ግን ቀብድ መሆኑ በውሉ ላይ ካልተገለፀ በቀር ቀብድ ነው ተብሎ ሻጭ አጠፌታውን እንዲከፍል የማያስገድድ ከመሆኑ በላይ ውሉ መኖሩንም ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

2 የቀብድ ክፍያ መኖሩ የውሉን መኖር የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ቢሆንም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማፍረስ ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ቀብድ ተቀባዩ የተቀበለውን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ፥ ቀብድ ሰጪው ደግሞ ይህንኑ የሰጠውን ገንዘብ ለተቀባዩ በመልቀቅ ያለሌላ ተጨማሪ ሁኔታ ውሉን የማፍረስና በመካከላቸው የተመሰረተውን ግዴታ ለማስቀረት መብት አላቸው። ይህም አሰራር በቀብድ የታሰረ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት ልዩ ባህሪ ነው። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1885)

ፍርድ ቤቶችም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሻጩ የቀብዱን አጠፌታ ከፍሎ ውሉን በማፍረስ የሸጠው ቤት እንዲመለስለት ከጠየቀ መወሰን የሚገባቸውና ተገዶ እንዲፈፅምም ማድረግ የሌለባቸው መሆኑ ግልፅ ነው።

የተደረገው ውል ሊፈፀም የማይችል (impossible)፣ ወደ ገዥ ሊተላለፍ የማይችል እና ህገ ወጥ (unlawful) ከሆነ ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከሚመላለሱ በቀር ሻጭም እጥፉን እንዲመልስና ገዢም የከፈለውን እንዲለቅ የሚጣልባቸው ግዴታ የለም።

3 ውሉ በአግባቡ ከተፈፀመ እና ለ ቀብዱ ገንዘብ ዕጣ ፋንታ በተዋዋዬቹ መሀል የተደረገ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የቃብድ ሂሳቡ ከጠቅላላው የሽያጭ ዋጋ ላይ የሚታሰብ ወይም እንዲመለስ የሚደረግ ይሆናል። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1884)👇👇
https://t.me/ethiolawtips
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሕገመንግስቱ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10
መሠረት የተሰጠው ስልጣን በአዋጁ በዝርዝር በተመለከቱት እና መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም
ነው፡፡ ይህን ስልጣኑን መሠረት በማድረግ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በበርካታ ጉዳዮች ላይ የሕግ ትርጉም ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በዚህም በአገሪቱ
ውስጥ ወጥ የሆነ የሕግ አረዳደር እና አተርጓጎም እንዲኖር በማድረግ ሕገመንግስታዊ ግድታውን ሲወጣ ቆይቷል፡ በሰበር ሰሚ ችሎቱ
ከአምስት ባላነሱ ዳኞች የተሰጠ የሕግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በየትኛውም ደረጃ በሚገኝ የፌዴራልም ሆነ የክልል ፍርድ
ቤት አስገዳጅነት ይኖረዋል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 26(1)እና(4) ላይ እንደተገለጸው አምስት ዳኞች የተሰየሙት የሰበር ሰሚ ችሎት
በባለጉዳዮቹ አመልካችነት ወይም በችሎቱ በራሱ አነሳሽነት ቀድሞ የተሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል
አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታይ በቂ እና አሳማኝ ምክንያቶችን ተንትኖ በመግለጽ
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡ በዚህ አግባብ በሰባት ዳኞች የተሰጠው ውሳኔም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ
አስገዳጅ ነው፤ በዚህ አግባብ መሠረት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የተሰየሙበት የሰበር ችሎት ቀድሞ የሰጠውን የሕግ ትርጉም ከሰባት ባላነሱ
ዳኞች በተመሳሳይ ጭብጥ በሌላ ጊዜ ሊሻሻል ይችላል በማለት የደነግጋል፡፡ ( አስቀድሞ የተሰጠው ውሳኔ በሰባት ዳኛ ሊለወጥ ይገባል
ወይስ አይገባል ለማለት የሚያስችሉ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው የሚለወ በአዋጁ ላይ አመላካች ነገር እንዳልተቀመጠ ልብ ይሏል )
ሰበር ሰሚ ችሎቱ በተለያዬ ጊዜ የውርስ ይርጋን አስመለክቶ የሰጣቸው ውሳኔዎች እርስ በእርስ ያላቸው መስተጋብር ምንድነው የሚለውን
ለመለየት ውሳኔዎቹን በአግባቡ ማየት ይጠይቃል፡፡ በዚህ ዓመት በሰባት ዳኞች በሰ.መ.ቁ 243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም
የተሰጠው ውሳኔም በአግባቡ ሊታይ የሚገባው ሌላው ውሳኔ ነው፡፡ በሰባት ዳኞች ታይቶ የውርስ ንብረት ክፍፍልን
አስመልክቶ ቀደም ሲል ተይዞ የነበረውን አቋም በመቀየር ውሳኔ ሲሰጥ ከውሳኔው ሰጪ ዳኞች አንዷ ነበርኩ፡፡ ይህ ውሳኔ
በሌላ ሰባት ዳኞች ታይቶ ሊለወጥ ይገባል ወይስ አይገባም ለማለት በተጨባጭ በማሕበረሰቡ ዘንድ ያለውን የኑሮ መስተጋብር
እና እያመጣ ያለውን ውጤት በአግባቡ ማጤን ይፈልጋል፡፡ ቀደም ሲል ሰበር ሰሚ ችሎቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 መሠረት
በተለያዩ መዛግብት ላይ የሰጣቸውን ውሳኔዎች እና በሰባት ዳኞች ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ አጭር ማጠቃለያ እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡
➢ በመሠረቱ ይርጋ መብቱ ወይም ጥቅሙ የተነካበት ሰው በሌላ ሰው ላይ የሚያቀርበውን ክስ፤ አቤቱታ ወይም የይገባኛል ጥያቄ
አስመልክቶ በሕግ ተለይቶ የተቀመጠ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ የይርጋ ጽንሰ ሐሳብ ሶስት መሠረታዊ ምክንያቶችን የያዘ
ነው፡፡ እነኚህም፡-
1. ከሳሽ በተገቢው ትጋት እና በቂ ምክንያት መብቱን እንዲጠይቅ ማስቻል እና ዳተኛ የሆነ ተከራካሪ ወገን እንዳይኖር
ማድረግ፤
2. ተከሳሽ በጣም ዘግይተው የሚመጡ ክሶችን ለመከላከል የሚያስችሉትን ማስረጃዎች እንዳያጣ ማድረግ፤
3. ዘግይው የሚቀርቡ ክሶች ዓላማቸው ፍትሕ ከማስገኘት ይልቅ ለበቀል እና ለማጥቂያ እንዳይውሉ ማድረግ ናቸው
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000(1) ድንጋጌ ከሳሹ መብቱን እና የውርስ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀ ሶስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለ ወራሽነት
ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ለማግኘት አይችልም በማለት ይደነግጋል፡፡ የዚሁ ሕግ ንዑስ (2) ድንጋጌ ደግሞ እንደዚሁም ሟቹ
ከሞተበት ወይም በመብቱ ለመሥራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት ዓመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የተባለው
የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት ማግኘት አይችልም በማለት ይደነግጋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ድንጋጌ መሠረት በማድረግ በፊቱ በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ላይ በውርስ ይርጋ ላይ
በርካታ የሕግ ትርጉም ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 25664 በሰጠው ውሳኔ ወራሽ የሆነ ሰው የውርስ ንብረቱን ለማስመለስ ወራሽ ባልሆነ ሰው ላይ የሚያቀርበው ክስ
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1677 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 1845 መሠረት በ10 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ነው በሚል ወስኗል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 44025 በሰጠው ውሳኔ ወራሾች በጋራ ይዘው ሲያስተዳድሩት ወይም ሲጠቀሙበት የነበረ የውርስ ንብረት ለመጠየቅ
የቀረበ ክስ ላይ የቀረበ የይርጋ መቃወሚያ ተቀባይነት የሌለው ነው በሚል ወስኗል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 120841 በሰጠው ውሳኔ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወራሽነት መብቱን ለአካለ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ
15 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የውርሱን ንብረት ለመጠየቅ በይርጋ አይታገድም በሚል ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 198
እና 100(2) ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ ነው፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 224271 ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፡- በሰ.መ.ቁ 171038 ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ሰው
መካከል ላለ የውርስ ንብረት ክርክር ተፈጻሚነት ያለው የ10 አመት ይርጋ እንደሆነ ይህ የአስር አመቱ የይርጋ ግዜ መቆጠር
ያለበት አካለመጠን ያላደረሰ ሰው አካለመጠን ካደረሰበት ግዜ አንስቶ መሆኑን፤ የመዝገቡ ተጠሪ አካለመጠን ካደረሰችበት ጊዜ
ጀምሮ ክስ እስካቀረበችበት ቀን ድረስ ያለው ጊዜ ሲታሰብ 10(አስር) አመት ያለፈው መሆኑን፤ ምንም እንኳ የወረዳው ፍርድ
ቤት የተጠሪን ክስ በይርጋ ቀሪ ሲያደርግ የ15 አመት ይርጋን መሰረት ማድረጉ አግባብ ባይሆንም ክሱ በይርጋ ቀሪ መደረጉ
ተገቢ ነው ሲል ወስኗል፡፡
➢ በሰ.መ.ቁ 44612 በሰጠው ውሳኔ የወራሽነት መብትን በሕግ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ያረጋገጡ ወራሾች የውርስ ንብረት
ክፍፍልን ማቅረብ ጥያቄ በማናቸውም ጊዜ ማቅረብ ይችላሉ በሚል ወስኗል
➢ በሰ.መ.ቁ 243973 ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም በ7 ዳኞች የተሰጠ ውሳኔ፡- በፍ/ሕ/ቁ. 1000 የተመለከተውን
የይርጋ ጊዜ ከወራሽነት የምስክር ወረቀት ጋር በማያያዝ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ መብቱን የሚያስከብር ሰው
የንብረት ጥያቄ ለማቅረብ ገደብ የሌለበት ተደርጎ የተሰጡ ውሳኔዎች አሉ፡፡ ይህን አቋም ለመፈተሽና ለተያዘውም
ጭብጥ ግልጽነት እንዲረዳ የወራሽነት የምስክር ወረቀትና የወራሽነት ጥያቄ ያላቸውን መስተጋብር ግልጽ ማድረግ
ይገባል፡፡ ሁለቱም ሐሳቦችን የያዙት ድንጋጌዎች በሕግ መድብሉ አንድ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የይርጋ ጊዜው
የተነሳው ግን ከወራሽነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በአጠቃለይ የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በተመለከተ
በተጠቀሰው በሕግ መድብሉ ክፍል የተደነገገ የይርጋ ገደብ የለም፡፡ አንቀጽ 1000 በግልጽ የሚናገረው የወራሽነት
ጥያቄ ተቀባይነት የማያገኝበትን ጊዜ ነው፡፡ ጊዜው ተፈጻሚ የሚሆንበትን ሁኔታ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ የወራሽነት
ጥያቄ ከወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠ ከሚቀርብ ማመልከቻ ያለውን ልዩነት ማየት ተገቢ ነው፡፡ የወራሽነት
የምስክር ወረቀት ስሙ እንደሚናገረው የምስክር ወረቀት ሲሆን በተግባር የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰ/መ/ቁ. 243973 ፍርድ ቤቶች አንድ ሰው ከሟች
ጋር ባለው ዝምድና ወይም በኑዛዜ መነሻነት ወራሽ መሆኑን በማረጋገጥ የሚሰጡት ውሳኔ ነው፡፡ ይህ ማስረጃ የህግ
ሁኔታን የሚያረጋግጥ በውጤቱም ሕጉ የሚወሰደውን ግምት የሚያረጋግጥ እንጂ በተከራካሪ ወገኖች መካከል ላለ
ክርክር መፍትሔ የሚሰጥ አይደለም፡፡
የወራሽነት ጥያቄ (petitio hereditatis) ጥንታዊ ጽንሰ ሐሳብ ሲሆን አንድ ሰው ከሟች ንብረት ለመውረስ
የሚያቀርበው ክስ ነው፡፡ የፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር 999 እንደሚያስቀምጠው ደግሞ አንድ ሰው ወራሽነ
ንዲታወቅለትና የተወሰዱት የውርስ ንብረቶች እንዲመለስለት የሚያቀርበው ክስ ነው፡ ፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው
ክሱ ሁለት ነገሮች የሚረጋገጥበት ነው፡፡ የመጀመሪያው የህግ ሁኔታ (status) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የንብረት
መብት ነው፡፡ የመጀመሪያውን ብቻውን ያየን እንደሆነ በቁጥር በፍ/ሕ/ቀ. 996 ሊስተናገድ የሚችል ሲሆን
የወራሽነት ጥያቄ ግን ከዚህም የሚዘል በመሆኑ የንብረት ክርክርም በውስጡ ይይዛል፡፡ የክሱን ውጤትም ተከሳሹ
በእጁ ያለውን ንብረት እንዲመልስ መደረጉ መሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 1001 መመልከቱ ትኩረቱ ንብረት ላይ መሆኑ
ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ እውነተኛ ወራሽ መሆንን ለማረጋገጥና የውርስ ንብረት ለማስለቀቅ የሚቀርብ ክስ ነው፡፡
የይርጋ ጊዜው ቅድመ ሁኔታ ስናይ ይህን ልዩነት ከግምት ያስገባ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ክሱ እንዲቀርብ
የተመለከተው ጊዜ መነሻ ከሳሽ መብቱንና የውርስ ንብረቶችቹ በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
የክሱ ይዘት ወራሽነት እና ንብረትን የሚመለከት የመሆኑን ያህል ይርጋውም እነዚህን መብቶች ከግምት የሚያስገባ
ነው፡፡ ከሳሽ ስለአንደኛው ፍሬ ነገር (ስለወራሽነት መብቱ እና ስለንብረቱ) እውቀት ኖሮት ስለሌላኛው ላያውቅ
ወይንም ስለሁለቱም ላያውቅ ይችላል፡፡ ስለመብቱ አውቆ ስለንብረቱ ላያውቅ የሚችልበት አጋጣሚ አንዱ
የወራሽነት ምስክር ወረቀት ይዞ ስለንብረቱ ወይም ንብረቱ በማን እጅ እንደተያዘ ላያውቅ ይችላል፤እነዚህ ፍሬ ነገሮች
ለስሌት መነሻ መሆናቸው የተመለከተ ቢሆንም ሕጉ ሟች ከሞተበት ወይም ከሳሽ ስለመብቱ መስራት ከቻለበት ቀን
አንስቶ በአስራአምስት ዓመታት ውስጥ የወራሽነት ክሱን ካላቀረበ ክሱ በይርጋ እንደሚታገድ በንዑስ 2 ደንግጓል፡፡
ስለዚህ የይርጋ ድንጋጌ ይዘትም የሚያወራው ስለምስክር ወረቀቱ ሳይሆን ስለወራሽነት ጥያቄ (petitio
hereditatis) ነው፡፡ ተቃራኒ ውሳኔ በተንጸባረቀባቸው ውሳኔዎች ለወራሽነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ውጤት
የተለያየ ሲሆን የዚህ ማስረጃ መኖር ወራሽ ተደርጎ ከመገመት ባለፈ የንብረት መብት የማይፈጥር በመሆኑ ሰነዱ በህጉ
ከታሰበለት ዓላማ ውጭ ውጤት መስጠት አይቻልም፡፡ በሌላ በኩል የወራሽነት ጥያቄ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ
ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰ/መ/ቁ. 243973 10 በጽንሰ ሐሳብም
ሆነ በውጤት የተለየ በመሆኑና በይዘቱ በተመለከተው አግባብ የሚቀርብ ጥያቄ የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት በመሆኑ
የይርጋ ጊዜው ተፈጻሚነት በወራሽነት ጥያቄ ላይ ነው፤ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ መያዝ አለመያዝ ልዩነት
ሳይኖረው በተጠቀሰው የሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የወራሽነት ጥያቄ ካልቀረበ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ይሆናል፡፡
የወራሽነት ጥያቄ በፍ/ሕ/ቁ. 1000 በተመለከተው የጊዜ ገደብ በይርጋ ይታገዳል፡፡ የውርስ ማጣራት ተጠናቆ
ንብረቱ የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የፍ/ሕ/ቁ. 1062 መሰረት በማድረግ
ያለጊዜ ገደብ የክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይችልም የሚል ትርጉም ተሰጥቷል፡፡
በኢትዮጲያ ባለው የማሕበረሰቡ መስተጋብር ቤተሰብ እርስ በእርሱ ከፍተኛ ቁርኝነት ያለው መሆኑ፤ በውጪ ሐገር የሚኖሩ
ውርሱ የሚገባቸው ሰዎች ውርሱን ለመጠየቅ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሊገኙ የሚችሉበት አጋጣሚ ያለ መሆኑ፤ ከሁለት
አንዱ ወላጆች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ በተለይም ታላላቅ ወንድሞች እና እህቶች በሕይወት ያለውን አንደኛውን ወላጃቸውን
ውርሱን ለመጠየቅ የሚቸገሩ መሆኑ፤ በተለይም በሕይወት ላለው ወላጅ ክብር ሲባል ውርሱን የማይጠይቁበት በርካታ
አጋጣሚዎች ያሉ መሆኑን፤ ሌሎች ትንንሽ እህት እና ወንድሞቻቸውንም በውርስ ሐብቱ እንዲጠቀሙበት እና እንዲያድጉበት
ሲባል የውርሱን ክፍፍል የማይጠይቁበት ሁኔታ ያለ መሆኑን፤ ይህም በማሕበረሰቡ የዳበረ ልምድ መሆኑ፤ ይህን ልምድ
ከግንዛቤ ሳያስገቡ መወሰን በተጨባጭ የውርስ ክፍፍሉን ባልጠየቁ እህት እና ወንድሞች ላይ በቀጥታ የወላጆቻቸውን ንብረት
በውርስ እንዳያገኙ የማድረግ ውጤት ያለው መሆኑን የምንገነዘበው ነው፡፡
ሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰ.መ.ቁ 224271 ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ.ም በሰባት ዳኛ በሰጠው ውሳኔ የውርስ ማጣራት ተጠናቆ ንብረቱ
የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የፍ/ሕ/ቁ. 1062 መሰረት በማድረግ ያለጊዜ ገደብ የክፍፍል
ጥያቄ ሊነሳ አይችልም የሚል አስቀድሞ ወራሽነታቸውን በጋራ ያረጋገጡ ሰዎች በማንኛውም ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ ተብሎ
የተሰጠውን የሕግ ትርጉም ለውጦታል፡፡
ሆኖም ከላይ በዝርዝር በጠየስኳቸው ነጥቦች ምክንያት በሰባት ዳኛ የተለወጠው የሕግ ትርጉም ጸንቶ ሊቀጥል ይገባል ወይስ በሌላ ሰባት
ዳኞች ወይም በሕገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ኮሚቴ አቅራቢነት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊለወጥ ይገባል የሚለው አሁንም አሳሳቢ ነው
የ 1 ብር ፌስታል 5000 ቅጣት‼️
ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡፡

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2 እስከ 5 ሺህ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ፤ ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው #የደረቅ_ቆሻሻ_አያያዝ_እና_አወጋገድ_አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2 እስከ 5 ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50 ሺህ ብር በማያንስና ከ200 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው #ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡
ሸገር ኤፍኤም
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
አዋጅ_ቁጥር_87_2017_የመንግስት_ሠራተኞች_አዋጅ.rtf
5.6 MB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር” 56/2010” በ “87/2017” በሚል የተሻረ ሲሆን ህጉ ይሄ ነው፡፡
Forwarded from Hermela Tilahun
Share copy
ሰላም አባላት
መልካም ዜና! በቢሮ ውስጥ ማማከር በስልክ እና በፍርድ ቤት ውክልና በመውሰድ  ሲሰጥ የቆየው የነጻ የህግ ምክር አገልግሎት በልዩ ሁኔታ  በነጻ የስልክ መስመር ቁጥር መሰጠት ተጀመረ።
አዲስ ነገር፤
በዘጠና አንድ አስር።
ከአንድ ሰአት እስከ አንድ ሰአት፤
በልዩ መስተንግዶ እና ጽናት።
እነሆ ማህበራችን በነጻ የስልክ ጥሪ ነጻ የህግ ምክር  አገልግሎት መስጠት  ጀመረ! በፍታሐብሄር,ማለትም በቤተሰብ፣ በውል፣ ከውል ውጪ በሚኖር ሀላፊነት፣ በንብረት፣ በውርስ በስራ እና በቅጥር የህግ ጉዳዮች፣  በአስተዳደር፣ በወንጀል  እንዲሁም አለም አቀፍ ሕግጋትን  በተመለከተ ለማማከር አካል ጉዳተኞች   በነጻ የስልክ ጥሪ የሚገለገሉበት ቁጥር ተበሰረ! ዘጠና አንድ አስር ካሉበት ሆነው ይደውሉ  ህግን በተመለከተ ያለበዎትን ክፍተት በነጻ ያሟሉ! ጠዋት የማለዳዋን ጀንበር ቀድመን ምሽት የምሽቱን ጀንበር ሸኝተን እርሶን እናገለግላለን። እባክዎን ተገደው በልመና ተግባር ላይ የተሰማሩ አካል ጉዳተኛ ከሆኑ  አልያም  አካል ጉዳተኞች ተገደው በልመና ላይ  ተሰማርተው  በሚመለከቱበት  ግዜ በዘጠና አንድ አስር በመደወል ያሳውቁ!
ዘጠና አንድ አስር አካል ጉዳተኞች ወደፍትህ የሚፈሱበት  ዥረት!
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር
👍1
Forwarded from SAMUEL GIRMA
የታክስ_አስተዳደራዊ_ቅጣት_አነሳስ_መመሪያ_189_2017.pdf
7.3 MB
የታክስ አስተዳደራዊ ቅጣት አነሳስ መመሪያ ቁ.189/2017

ገቢዎች ሚኒስቴር 🇪🇹

🌐  https://SamuelGirma.com

📱  https://fb.me/tebekasamuel

📱 https://t.me/tebekasamuel

🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel


👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

DM @samuelgirma
📻 0911190299

TAX
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law

Boost The Channel 👇
https://t.me/boost/tebekasamuel
https://t.me/boost/tebekasamuel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
DEMATERIALIZATION OF GOVERNMENT AND NBE SECURITIES.pdf
2.2 MB
DEMATERIALIZATION OF GOVERNMENT AND NBE SECURITIES
DIRECTIVE NO. MFAD/001/2025
Excise Tax Management System Directive No. 1071_2025.pdf
979.9 KB
የኤክሳይዝ ታክስ አስተዳደር ስርአት መመሪያ ቁጥር 1071/2017
 
DIRECTIVE NO. 1071/2025
DIRECTIVE ON EXCISE TAX MANGEMENT SYSTEM

🇪🇹

🌐  https://SamuelGirma.com

📱  https://fb.me/tebekasamuel

📱 https://t.me/tebekasamuel

🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel


👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

DM @samuelgirma
📻 0911190299

#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law
የከተማ_መሬት_ይዞታና_መሬት_ነክ_ንብረት_ምዝገባ_የፀደቀ_አዋጅ_ቁጥር_1381_2017_1.pdf
739 KB
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1381/2017
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1👍1