Forwarded from ይግባኝ ምክረ ሕግ ⚖️
ሀ. ልጁ በተፀነሰ ወይም በተወለደ ጊዜ የመደፈር ወይም የመጠለፍ ተግባር ከተፈጸመ፤
ለ. አገባሻለውኝ በሚል የተስፋ ቃል በመስጠት በእናቲቱ ላይ የማሳት ተግባር ከተፈጸመ፤
ሐ. አባት ነው የተባለው ሰው በማያሻማ መልኩ አባት መሆኑ የሚገልጽ ደብዳቤ ወይም ጽሑፍ ከተገኘ፤
መ. በሕግ የታወቀ ግንኙነት ሳይኖራቸው ከእናቲቱ ጋር ቀጣይነት ያለው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ከተፈጸመ፤
ሠ. አባት ነው የተባለው ሰው ልጁን በማሳደግ ተግባር እንደአባት ከተሳተፈ ናቸው።
#እነዚህ ልብ ማለት የሚያስፈልገው አባትነትን የማረጋገጫ መንገዶች በቅደም ተከተል የሚተገበሩ ናቸው። ጋብቻ እያለ አባትነት መቀበል አይቀድምም ወይም በፍርድ ውሳኔ አባትነት ይታወቅልኝ አይባልም።
#ለምሳሌ አንዲት ሴት ጋብቻ እያላት አባትየው ልጁን ቢክድ ልትጠይቅ የምትችለው ዳኝነት በሕግ በታወቀ ጋብቻ እያለን ለተወለደ ልጅ አባቱ ነው በማለት የሕግ ግምት ውሳኔ ይሰጥልኝ እንጂ አባትነቱን ይቀበል ወይም በፍርድ ይታወቅልኝ የሚል አይሆንም።
👨🍼አባት የሌለው ልጅ🧒
#እዚህ ላይ የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 107ን መመልከቱ ለርዕሳችን ወሳኝነት አለው። ጋብቻ ሳይኖር ወይም ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት ከሚኖሩ ሰዎች ውጪ የሚደረጉ ግንኙነቶች በሕግ ፊት ተቀባይነት የላቸውም። በሕግ ፊት ስለጉዲፈቻና አባትነትን ስለመቀበል የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በሕግ ፊት እውቅና በሌለው ግንኙነት የተወለደ ልጅ ከእናቲቱ በስተቀር ከአባቱ ጋር ምንም ዓይነት ሕጋዊ ግንኙነት አይኖረውም።
ጭማሪ ትንታኔዎችን ለመቀጠል የእርስዎን ሃሳብ ያጋሩን።
ይግባኝ መብት ነው!!!

Forwarded from አለ ሕግ
ሰ/መ/ቁ/211987
ለግዴታ አፈጻጸም ዋስ የሆነ ሰው ባለዕዳው ግዴታውን ባለመፈጸሙ ምክንያት ዕዳውን ለባለገንዘቡ ሲከፍል ወለድ እና ወጪ ሊጠይቅ የሚችለው ከባለገንዘቡ ጋር ክርክር ተደርጎ ዋሱ ከዋናው ገንዘብ በተጨማሪ ወለድ እና ወጪ ጨምሮ መክፈሉ ሲረጋገጥ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ዋሱ የኪሳራ ጥያቄ ሊያቀርብ የሚችለው ለባለዕዳው ማስጠንቀቂያ መስጠቱ እንዲሁም በባለእዳዉ በኩል የተፈጸመ ጥፋት ወይም ቸልተኝነት መኖሩን ጭምር በማስረዳት ነው።
አብርሃም ዮሀንስ

Forwarded from የሕግ ዜና
የአስተዳደራዊ ዳኝነት ችሎት የዳኝነት ሂደት
በሁሉም ደረጃ ያሉ የአስተዳደራዊ የዳኝነት እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ዳኝነት ሲያዩ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እና ሰነዶችን ማንኛውም ሰው እንዲያቀርብላቸው የማዘዝ፣ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የማዘዝ፣ ያስተላለፏቸውን ውሳኔዎችና ትዕዛዞች የማስፈፀም፣ ፖሊስን ወይም አግባብ ያለውን ሌላ አካል የማዘዝ እና የንግድ ዕቃዎች እንዲታገዱ እንዲያዙና እንደሸጡ የማድረግ ሥልጣን አላቸው፡፡
በተጫማሪም የአስተዳደራዊው የዳኝነት ችሎት የአስተዳደር ቅጣት ወይም አስተዳዳራዊ እርምጃ በሚወስንበት ጊዜ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡-
• የተፈፀመውን ጥፋት ባህሪ፣ የቆይታውን ጊዜ፣ የጥፋቱን ክብደትና መጠን
• በተፈፀመው ጥፋት ምክንያት የደረሰውን የጉዳት መጠን፣
• ጥፋቱ የተፈፀመበትን የገበያ ሁኔታ፣
• ከተፈፀመው ጥፋት አጥፊው ያገኘውን ጥቅም፣
• የአጥፊውን የኢኮኖሚ ደረጃ፣
• በምርመራው ወቅት አጥፊው ያደረገውን ትብብር እና የአጥፊውን የቀድሞ ባህሪና የጥፋት ሪከርዶች ከግምንት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት በህጉ ተደንግገጎ ይገኛል፡፡
ሌላው ይግብኝን በተመለከተ በአዋጁ አንቅጽ 39 ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ውህደትን ለመከልከል ወይም የውህደት ፈቃድን ለመሰረዝ ወይም የንግድ ማስታወቂያውን ለማገድ በሰጠው ውሳኔ ወይም በማንኛውም የየዳኝነት ችሎት ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ለይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት በሚቀርብለት ይግባኝ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡ ሆኖም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 33(3) መሠረት ይግባኝ ሰሚው አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት የበሰጠውን ውሳኔ በሚመለከት የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚል ወገን ውሳኔው በተሰጠ በ30 ቀናት ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደ ሚችል በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
ማንኛውም መንግስታዊ አካል ያልሆነ ሰው ለአስተዳደራዊው የዳኝነት ችሎት ክስ ሲያቀርብ ወይም ለይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል እንዳለበት የተደነገገ በመሆኑ የዳኝነት ክፍያ መፈፀም አለበት፡፡ አስተደደራዊ የዳኝነት ችሎቶች ጉዳዮችን በሚያዩበት ወቅት እንደሁኔታው የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ እንደሚሆኑ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡
ማጠቃለያ
የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አስተዳደረዊ ዳኝነት ችሎት እና ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከላይ የተመለከቱ ስልጣንና ተግባራት ያላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ በአስተዳደራዊ ችሎቶቹ ስልጣን ሥር የሚታዩ ጉዳዮች ሲገጥሙ ጉዳዩን ለችሎቶቹ በማቅረብ ዳኝነት የመጠየቅ ልምዱን ሊያዳብር ይገባል፡፡
# በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

#አንዲት ወጣት ሴት በምሽት ከገበያ በምትመለስበት ወቅት የመኪና አደጋ ይደርስባታል። የመኪናው አደጋ ከደረሰባት በኋላ አደጋ አድራሹ ሕክምና ቦታ እሷን ከማድረስ ውጪ ምንም ያደረገው ነገር የለም። የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለፖሊስ በምታመለክትበት ወቅት ፖሊስም ዓቃቤ ሕግም ለምን አትታረቁም? ጉዳዩ እኮ ያን ያክል ወንጀል አይደለም። በማለት ጉዳዩን ያቃልሉባታል። እናም ለምክር ስትመጣ በቀጣይ ያለውን ሃሳብ አካፈልኳት ቢያንስ ለ1 ሰው ይጠቅማልና እነሆ#
🚘💥ዓቃቤ ሕግ አልከስም ቢል ምን ይደረጋል?🚘💥
📌ወንጀል ሁለት ዓይነት ነው።
#1. በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ እና
#2. በመንግሥት ከሳሽነት የሚያስቀጡ።
#በወንጀል ሕግ በአቤቱታ አቅራቢነት በሚያስቀጡ ወንጀሎች ላይ ክስ የማቅረብ ሥልጣንም ግዴታም የዓቃቤ ሕግ ነው። ይህን በማስመልከት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 40 (1) "ዓቃቤ ሕጉ በተከሳሹ ላይ ክስ ለማቅረብ በቂ ምክንያት መኖሩን የተረዳው እንደሆነ በቁጥር 42 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ክፍል ድንጋጌ በተመለከተው መሠረት ክስ ማቅረብ አለበት።" በማለት ይደነግጋል።
#ዓቃቤ ሕግ ክስ ከማይሰረትባቸው ምክንያቶች መካከል አንደኛው በቂ ማስረጃ ስለሌለ ክስ ለማቅረብ አያስችለኝም የሚለው ነው። ሙሉ ክስ የማይቀርብበቸው ምክንያቶች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 42 ላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል።
#ዓቃቤ ሕግ በአንድም በሌላም መልኩ በቂ ማስረጃ እያለው ክስ አላቀርብም ያለ እንደሆነ ምን ይደረጋል? የሚለውን በተመለከተ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በቁጥር 44 ላይ ተደንግጎ ይገኛል።

#ዓቃቤ ሕጉ ክስ ለማቅረብ አያስችለኝም ያለ እንደሆነ ክስ ለማቅረብ መብት ላለው ሰው በራሱ ክስ እንዲያቀርብ በጽሑፍ ይፈቅድለታል። ነገር ግን ይህ ፈቃድ ያልተሰጠው የግል ተበዳይ ዓቃቤ ሕጉ ክስ አይቀርብም በማለት ውሳኔ ከሰጠበት3️⃣0️⃣ቀናት አንስቶ በራሱ ክስ እንዲያቀርብ እንዲፈቀድለት ይጠይቃል።
#የግል ተበዳይ ክሱን የሚያቀርበው በራሱ ኃላፊነትና ወጪ ነው። የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 46
#የግል ክስ ለማቅረብ መብት ያላቸው ሰዎች
📌የተበደለው ሰው ወይም ተወካዩ ወይም
📌ባል ስለሚስቱ ወይም ሚስት ስለባሏ ወይም
📌ችሎታ ስለሌለው ሰው እንደራሴው ወይም
📌በሕግ የሰው መብት ስለተሰጠው ማኅበር ወኪሉ ናቸው።
#እንዲህ ከሆነ በኋላ ዓቃቤ ሕጉ የግል ተበዳዩ ወይም ተወካዩ በሚያቀርበው ክስ ላይ የበለጠ ከፍ ያለ ወንጀል ለመሠራቱ ለግል ኩ በቀረበው ማስረጃ የተገለጸ ሲሆን የግል አቤቱታው እንዲቋረጥ ለመጠየቅ ይችላል። ፍርድ ቤትም ክሱን ማስቆን አለበት። የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቁጥር 48

Forwarded from የህግ ማዕበል/ጠበቃ ውብአለም መስፍን (Wubalem Mesfin)
አንድ ጓደኛ በሰጠኝ አስተያየት መሠረት ተገዶ የመያዝ ህጋዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይ (habeas corpus) አስመልክቶ የዳኝነት ስልጣኑ ተለይቶ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያልተሰጠ በመሆኑ
የሚቀርብ አቤቱታን ተቀብሎ የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1(ኘ)) እና
11(1)፣ (3) በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 230167 ውሳኔ መሰጠቱን አመላከተኝ።
ይህም ውሳኔ አግባብነት ያለው ነው የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ የሰበር ውሳኔዎች አስገዳጅ መሆናቸውን ተከትሎ አካሌ ነፃ ይውጣልኝ አቤቱታ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሚቀርብ መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 17 በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ማንኛውም ሰው ነፃነቱን እንደማያጣ ይደነግጋል።
በተጨማሪም ማንኛውም ሰው በሕግ ከተደነገገው ሥርዓት ውጪ ሊያዝ፣ ክስ ሳይቀርብበት ወይንም ሳይፈረድበት ሊታሰር እንደማይችል በግልፅ ይደነግጋል።
ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችው የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (ICCPR) አንቀፅ 9 ማንኛውም ሰው ነፃነቱ እና ደህንነቱ ተከብሮ የመኖር መብት እንዳለው እና በዘፈቀደ ከሚደረግ እስር ሊጠበቅ እንደሚገባ ይደነግጋል።
ሕግ አስከባሪዎች ማንኛውም ሰውን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት የዜጎች ነፃነትን ለመጠበቅ የወጡ ሕጎች የጣሉባቸውን ግዴታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
ምስል-በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተቀናበረ
#AHRE( Association for Human Rights in Ethiopia)
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣🔴ሕግ
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

👍1
Forwarded from የህግ ማዕበል/ጠበቃ ውብአለም መስፍን (Wubalem Mesfin)
ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በመዝገቡ ተሳታፊ ለመሆን የሚቀርቡ አቤቱታዎች ስነ-ስርዓት
የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 78
በመዝገብ ላይ ተከሳሽ የነበረ ሰው(የተፈጥሮ/በህግ ሰውነት የተሰጠው) ለቀረበበት ክስ መልስ ሳይሰጥ ወይም ተገቢውን ክርክር ሳያደርግ ቀርቶ በሌለበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ የተሰጠበት እንደሆነ እነዚህ እንዲነሱለት ማመልከቻ ማቅረብ ወይም ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው:-
1. ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ እንደተሰጠ ባወቀ በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ከሆነ
2. የፍርድ ቤት መጥሪያ በአግባቡ እንዳልደረሰው ካስረዳ
3. ወይም ቀርቦ መከራከር ያልቻለው በበቂ ምክንያት መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ከቻለ ብቻ ነው።
ይህ አንቀፅ ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ሲነበብ ብቻ ላልተገኘ ሰው ተፈፃሚ አይሆንም።
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 358
በመዝገብ ላይ ተከራካሪ መሆን የሚገባቸው ሰዎች በተለያየ ምክንያት ተሳታፊ ሳይሆኑ ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል። ለዚህ መፍትሄ እንዲሆኑም የፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ የተለያዩ የመፍትሄ አንቀጾች አስቀምጧል። ከነዚህ ውስጥ አንዱም አንቀፅ 358 ነው። የዚህ አንቀጽ ተጠቃሚ ለመሆንም :-
1. ጣልቃ ለመግባት አቤቱታ የሚያቀርበው ሰዉ በክርክሩ ተሳታፊ መሆን የሚገባው/የሚችል
2. የተሰጠው ፍርድ መብቱን የሚነካው ሰው መሆን ያለበት ሲሆን በዋነኝነት መቃወሚያው መቅረብ የሚችለው መብቴን ይነካዋል ያለው ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት ነው።
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 418
አንድ ሰው የመዝገብ ተካፋይ/ተከራካሪ ባይሆንም ነገር ግን በክርክሩ ምክንያት የሱ የሆነ ንብረት እንደመያዣ/ ማስከበሪያ በተከራካሪ ወገኖች ቀርቦበት ሊሆን ይችላል። በዚህ ንብረት ላይ ያለውንም መብት ለማስጠበቅ በዚህ አንቀፅ መሠረት አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ሊያቀርብ ይችላል። አቤቱታውም:-
1. መዝገቡ አፈፃፀም እስኪደርስ የዘገየው በበቂ ምክንያት መሆኑን ማስረዳት
2. በፅሁፍ ሆኖ ፍርዱን ለሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት
3. በንብረቱ ላይ ያለውን የተቀዳሚነት መብት ወይም ባለይዞታነቱን የሚያረጋግጥ የፅሁፍ ማስረጃ አብሮ ማያያዝ አለበት።
አቤቱታውን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ቢያደርገው አቤት ባዩን በንብረቱ ላይ አዲስ ክስ ከመመስረት አያግደውም።

220042-3.pdf
916.8 KB
የካርታ ይምከንልኝ ጥያቄ መጀመሪያ በአስተዳደር አካል በአዋጅ ቁጥር 1183/12 መሠረት መታየት ያለበት እንጂ ለፍርድ ቤት ቀጥታ የሚቀርብ አይደለም። በመጨረሻው የአስተዳደር ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ሰው የተሰጠው ውሳኔ እንዲከለስለት ቅሬታውን ለከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረብ እንደሚችል ባልታተመ የሰበር ውሳኔ ተሰጥቷል።
👍1
Forwarded from የህግ ማዕበል/ጠበቃ ውብአለም መስፍን (Wubalem Mesfin)
የኑዛዜ አይነቶች
በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ
1. በተናዛዡ እየተነገረ በሌላ ማንኛውም ሰው የሚፃፍ ወይም በራሱ የሚፃፍ
2. በ 4 ምስክሮች ወይም ኑዛዜው ዳኛ ወይም በሌላ ስልጣን በተሠጠው ሰው ፊት በቢሮአቸው ውስጥ የተደረገ ከሆነ 2 ምስክር
3. ምስክሮቹ በህግ የተፈቀደ እድሜ እና የህግ ክልከላ የሌለባቸው መሆን። ማለትም አካለ መጠን የደረሱ እንዲሁም በጤና እክል ምክንያት ብቁ አይደሉም ተብሎ በህግ ክልከላ ያልተጣለባቸው። በተጨማሪም አካለ መጠን ሆነ ክልከላ ያልተደረገባቸው ቢሆንም እንኳን የተፃፈውን ኑዛዜ መረዳት የሚችሉ መሆን አለባቸው። ይሄም የተፃፈበትን ቋንቋ ማወቅ መስማት ወይም ማንበብን ያካትታል።
4. በተናዛዡ እና ምስክሮች ፊት የተነበበ ይህም እንደተደረገ እና ኑዛዜው የተፃፈበትን ቀን የሚያሳይ መሆን። ማለትም ኑዛዜው በግልፅ ባሉበት መነበቡን ኑዛዜው ላይ እስከተፃፈበት ቀን ጨምሮ መገለፅ አለበት።
5. ኑዛዜውም ወዲያውኑ መፈረም አለበት።
እነዚህ መስፈርቶች መሟላት እንዳለባቸው የፍትሐብሔር ህግ ከአንቀፅ 881 - 883 ይደነግጋል። ሰበር ችሎትም በቅፅ 8 መ/ቁጥር 36777 እነዚህን መስፈርቶች ዘርዝሮ ውሳኔ ሰቷል። በቅፅ 2 መ/ቁ 17429 ላይም ኑዛዜው ተናዛዡ እና ምስክሮች ፊት ስለመነበቡ ካመላከተ በቂ ስለመሆኑና "ተነቧል" የሚለው ቃል አልተገለፀም በሚል ኑዛዜውን ፈራሽ ማድረግ እንደማይቻል አስገዳጅ ውሳኔ ሰቷል።
በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ
1. ኑዛዜ መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሙሉ በሙሉ በተናዛዡ መፃፍ አለበት። ፅሁፉ በመፃፊያ መሳሪያ የተፃፈ ከሆነ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ በመሳሪያው መፃፋ በእጅ ፅሁፉ መገለፅ አለበት። ተናዛዡም የሚፅፍበትን ቋንቋ የማይረዳውና ቃላቶቹ ምንን እንደሚወክሉ የማያቅ ከሆነ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል።
2. እያንዳንዱ ገፅ ላይ የተናዛዡ ፊርማና ቀን መፃፍ አለበት
የቃል ኑዛዜ
1. ሟች የመሞቻው ግዜ ተሰምቶት ለሁለት አካለ መጠን የደረሱና በህግ ክልከላ ያልተደረገባቸው ሰዎች የሚሰጠው የመጨረሻ ፈቃድ ነው።
2. የቃል ኑዛዜ የቀብር ሁኔታን፣ ለእያንዳንዱ ከ500 ብር ያልበለጠ የኑዛዜ ስጦታን እና የልጅ አስተዳዳሪ ወይም ሞግዚት በተመለከተ የሚደረግ ነው። በዚህም በቃል ኑዛዜ ዋጋቸው ከፍ ያሉ ንብረቶችን ማስተላለፍ አይቻልም። ከተፈቀደው በላይ የተደረገም የቃል ኑዛዜ ትርፋ እንዲቀነስ ይደረጋል።
ማንኛውም ኑዛዜ ከላይ የተዘረዘሩትን ፎርማሊቲዎች መከተል ያለበት ሲሆን መስፈርቱን ሳያሟላ ከቀረ ፈራሽ ይሆናል። ኑዛዜም በማያሻማ መልኩ መፍረሱን የሚያሳይ ሰነድ በተናዛዡ ተፅፎ እያለ ኑዛዜው በተደረገበት ፎርማሊቲ መሠረት መፍረሱም አልተደረገም በሚል መፍረሱን ውድቅ ማድረግ አይቻልም ሲልም ሰበር ችሎት በመ/ቁጥር 96364 ውሳኔ አሳርፏል።

Forwarded from እንደ ❤️ (kidane M)
ወንጀልን አለማሳወቅ ወንጀል ነው!
****
አይበልባችሁና የቅርብ ዘመድ ወይም ወዳጅ ወንጀል መፈፀሙን ብታውቁ ለሕግ አሳልፋችሁ ትሰጡታላችሁ ወይስ ዝምድናው ወይም ወዳጅነቱ ይዟችሁ አይቶ እንዳላየ ሆናችሁ ትደብቃላችሁ? ጉዳዩ የህሊና እንዲሁም የሕግ ተጠያቂነትን የሚመለከት ነው። የህሊናውን ለየራሳችን ትተነው ሕጉ ምን እንደሚል እንይ።
በሞት ወይም በዕድሜ ልክ እስር ሚያስቀጣ ወንጀል
በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 443 ላይ ማንኛውም ሰው በቂ ምክንያት ከሌው በስተቀር በሞት ወይም በእድሜ ልክ የሚያስቀጣ ወንጀል መፈፀሙን ወይም የፈፃሚውን ማንነት እያወቀ ለሚመለከተው አካል (ለፖሊስ) ሳያሳውቅ ከቀረ ወንጀልን ባለማሳወቅ ወንጀል ይቀጣል። ይህ ሕግ ማናችንም ላይ የተጣለብን ግዴታ ነው።
ሙያዊ ኃላፊነት ያለበት ሰው
ሌላኛው ወንጀልን ለሕግ አካል የማሳወቅ ግዴታ የሚመነጨው ደግሞ ግለሰቡ ከተሰማራበት የሙያ ግዴታ ሲሆን ከዚህ አይነት ሙያዎች መከከል ለምሳሌ የጥበቃ፣የፍተሻ፣የመቆጣጠር፣ፍቃድ የመስጠት የመሳሰሉት ሙያዎች መጥቀስ ይቻላል። በነዚህ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለህብተረተሰቡ ሰላምና ደህንነት አስጊ የሆኑ ወንጀሎችን ወይም ከባድ ሁኔታዎችን የማሳወቅ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን የሙያ ግዴታቸውን በመጣስ ወይም በምንቸገረኝ ወንጀሉን ለሚመለከተው አካል ካላሳወቁ እሰከ ብር 1000 ወይም እስከ 6 ወር እስራት ሊያስቀጣቸው ይችላል።
በተለይም ደግሞ ከፍተኛ አደጋ በሚፈጥሩ የተወሰኑ የወንጀል አይነቶች ላይ ወንጀልን አውቆ አለማሳወቅ የሚያስከትለው ሀላፊነት ከፍ ያለ ነው። ከነዚህ መሀል ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
የሀገርና የሕዝብ ደህንነትን ሚመለከት ወንጀል
በሕገመንግስታዊ ስርዓቱ፣ በሉአላዊነታችን፣ በመከላከያ፣ በውስጥና በውጭ ደህንነታችን ላይ የተሞከሩ፣ የተሰናዱ፣ የተፈፀሙ ወንጀሎችን አውቆ አለማሳወቅ፣ አደጋው፣ አንዳይደርስ ወይም አድራሹ እንዳይያዝ የሚችለውን ያላደረገ ሰው ከአቅም በላይ በሆነ ወይም ግልፅ ምክንያት ግዴታውን ሳይወጣ መቅረቱን ካላስረዳ በወንጀል ይቀጣል።
በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 254 መሰረት ቅጣቱ ከ5 አመት የማይበልጥ ፅኑ እስር ሲሆን ወንጀሉ የተፈፀመው ያገራችን የውስጥ ወይም የውጭ ደህንነት አስጊ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከሆነ ቅጣቱ እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስር ይደርሳል።
ወታደራዊ ኩብለላ ወይም አመፅ
ወታደራዊ ኩብለላ ወይም አመፅ መዘጋጀቱን ወይም መፈፀሙን አውቆ ለሚመለከተው አካል ሳያሳወቁ መቅረት ፣እንዳይፈፀም ማድረግ ወይም አድራጊው አንዲያዝ አቅም የፈቀደውን አለማድረግም በቂ ምክንያት ከሌለ በቀር ያስቀጣል። በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 335(1) መሰረት ቢያንስ ወንጀሉ ከተሞከረ በቀላል እስራት ነገሩ ከባድ ከሆነ ደግሞ ከ3 ዓመት ማይበልጥ ፅኑ እስር ያስቀጣል።
የሽብር ወንጀል
በሽብርተኝነት አዋጁ 1176/2012 አንቀጽ 15 መሰረት የሽብር ድርጊት፣የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ማቀድና መሰናዳትን፣የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ማደምን፣ለሽብር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ድጋፍ የማድረግ ተግባርን፣ለሽብር የማነሳሳትና ከሽብር ወንጀል ጋር የተገናኘ ንብረት የመያዝ ወንጀሎች አንዱ ሊፈፀም፣እየተፈፀመ ወይም የተፈፀመ መሆኑን ወይም የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት እያወቀ በቂ ምክንያት ሳይኖረው ወዲያውኑ ለፖሊስ ወይም አግባብ ላለው የሕግ አስፈፃሚ ካላሳወቀ ከአንድ አመት እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።
የሽብር ወንጀልን ያለማሳወቅ ቅጣቱን የሚያከብደው ደግሞ የሚያውቀውን መረጃ አሳውቆ ቢሆን ኖሮ ወንጀሉን መከላከል ወይም ማስቀረት የሚቻል ዓይነት ከሆነ ቅጣቱ ከሦስት እስከ ሰባት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይሆናል።
በሽብር ድርጊት የተጠረጠረን ወይም የተከሰሰን ሰው አስቀድሞ በማስጠንቀቅ፣በመደበቅ ወይም ዱካውን በመሸሸግ ወይም በማጥፋት፣የሚደረግ ምርመራን በማሳሳት ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ተከሶ እንዳይቀርብ የረዳ ከሆነ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።ይህ ያለማሳወቅ ወይም በሽብር የተጠረጠረ ሰውን ተከሶ ለሕግ እንዳይቀርብ የመርዳት ድርጊት የወንጀል ተጠርጣሪውን መያዝ ወይም ማስቀጣት ቢቻልም እንኳን የሽብር ወንጀልን የማሳወቅና በሽብር የተጠረጠረ ሰውን በማንኛውም መንገድ በሕግ እንዳይጠየቅ ያለመርዳት ግዴታውን ያልተወጣ ሰው ለጥፋቱ መቀጣቱ እንደማይቀርለት አዋጁ ይደነግጋል።
ይህ የየሽብር ድርጊቶችን የማሳወቅ ኃላፊነት በሕግ ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ተፈፃሚ የማይሆን ሲሆን ወንጀሉ ሊፈፀም ወይም እየተፈፀመ ያለ ስለመሆኑ መረጃ ያለው ሰው ግን ይህን መብት ወይም ግዴታ እንደመከላከያ ሊያቀርብ አይችልም። ሚስጥር የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ የሽብር ወንጀልን ካለማሳወቅ ተጠያቂነት ሊያድን ሚችለው የሽብር ድርጊቱ የተፈፀም ወይም ድርጊቱ ካለፈና ጉዳቱን ለማስቀረት ወይም ለመከላከል ማይቻል ከሆነ ብቻ ነው።
ወንጀልን ላለማሳወቅ በቂ ሚባል ምክንያት
ወንጀልን አለማሳወቅ ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚያስቀጣ አንስተናል። ሆኖም ግለሰቡ ወንጀሉን ያላሳወቀው ‘‘በቂ ምክንያት’’ ኖሮት ከሆነ ላያስቀጣው እንደሚችል አይተናል።
"በቂ ምክንያት" የሚባለው ግለሰቡ ወንጀሉን ያላሳወቀው ‘‘ራሱን፣የቅርብ የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዱን ወይም በተለይም በጥብቅ ወዳጅነት የተሳሰረውን ሰው ለቅጣት ፣ለውርደት ወይም ለከባድ አደጋ ላለማጋለጥ’’ ከሆነ ነው። ከላይ የጠቀስነውን ወንጀልን ለሕግ አካል ያለማሳወቅ ምክንያት ከወንጀሉ አደገኛነትና ከሌሎችም ሁኔታዎች አንፃር መዝኖ በቂ ሆኖ ካገኘው በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 83(1) መሰረት ፍርድ ቤቱ ወንጀሉን ባለማሳወቅ ክስ የቀረበበትን ሰው ቅጣቱን በመሰለው መልኩ ያቀልለታል ወይም ከመነሻው የቅጣት መጠን ዝቅ አድርጎ ሊቀጣው ወይም ቅጣቱን በቀላል ሌላ ቅጣት ሊተካለት ይችላል።
ወዳጅነቱ ወይም ዝምድናው ከሚያስጠይቀው ወንጀል ክብደት ጋር ሲነፃፀር በጣም ጥብቅ ከመሆኑ የተነሳ ጭንቀት ፈጥሮበት ወንጀሉን ሳያሳውቅ የቀረን ሰው ፍ/ቤቱ በወቀሳ ወይም በማስጠንቀቂያ ሊያልፈው ይችላል።
በመሆኑም ሕጋችን ጥብቅ ዝምድና ወይም ወዳጅነት ለሚፈጥረው ትስስር እውቅና ቢሰጥም አጠቃላይ ህብረተሰቡ ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርሱ ከላይ የጠቀስናቸው አደገኛ ወንጀሎችን ግን አውቆ አለማሳወቅ በራሱ በወንጀል እንደሚያስጠይቅ ደንግጓል።
‘‘እንዴት ብዬ!? አብረን በልተን ጠጥተን፣ባለውለታዬን፣ዘመዴን ወይም ወዳጄን ወንጀል ፈፅሟል ብዬ አሳልፌ እሰጠዋለሁ?’’ በሚል ስሜት ወንጀልን እያወቁ ለሚመለከተው የሕግ አካል አለማሳወቅ ሕግ የጣለብንን ግዴታ አለመወጣት ነውና በወንጀል ያስጠይቃል።የዝምድናው ወይም የወዳጅነቱ ጥልቀት ከግንዛቤ ውስጥ ቢገባም የሚመጣውን ቅጣት የሚያቀል ‘በቂ ምክንያትነቱ’ በፍ/ቤቱ ይመዘናል እንጂ ከተጠያቂነት አያድንም።
በሕግ የሙያ ግዴታ ካለባቸው ሰዎች በስተቀር በሌሎች ሕጉ ወንጀልን አለማሳወቅ ጥፋት መሆኑን ባልደነገገባቸው ከላይ ካነሳናቸው ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ላይ ግን ዝምድናው ወይም ወዳጅነቱ ኖረም አልኖረ ወንጀሉን አውቆ እንዳላወቀ ዝም ማለት በግለሰቡ የህሊና ወቀሳ ያስጠይቅ ይሆናል እንጂ በሕግ አያስጠይቅም።

❤1
Forwarded from የሕግ ዜና
ማንኛውም #የመንግሥት ሠራተኛ ለጋብቻ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ሰባትም(7) የሥራ ቀናት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ 1064/2010 አንቀፅ 45
ማንኛውም #የግል ድርጅት ሠራተኛ ሕጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም ከክፍያ ጋር ለ ሶስት(3)የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 81 (1)(U)(ለ)
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
#NegereFej #ነገረፈጅ

❤🔥1
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ስለችሎታ እና ክልከላ ሕጉ ምን ይላል?
**************
ሁላችንም ሰው በመሆናችን መብት እና ግዴታዎችን የሚፈጥሩ ተግባራትን መከወን እንችላለን።መብት እና ግዴታን የሚፈጥሩ ተግባራት የሚባሉት ውል መዋዋል ፣ወኪል መሆን፣መክሰስ፣መከሰስ፣ንብረት ማፍራት በንብረት መብት መጠቀም፣ ጋብቻ መፈፀም ኑዛዜ ማድረግ እና የመሳሰሉት ናቸው።
እነኚህን መብቶችን ለመጠቀም ነፃ እና ምክንያታዊ ውሳኔ መወሰን የማንችልበት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሕግ ግምት ሲወስድ ከእነኚህ ሕጋዊ ውጤት ካላቸው ተግባራት ልንከለከል እንችላለን። እስኪ የፍትሐብሔር ሕጋችን ስለ ክልከላ ምን እንደሚል እንመልከት።
1. ስለችሎታ
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 192 ‘ሁላችንም በሕግ ተወስኖ ካልተገለፀ በቀር ማንኛውንም አይነት የማህበራዊ ኑሯችንን ተግባር ለመፈፀም ችሎታ አለን’ ይላል። ይህን ችሎታ የሚያሳጡት በዕድሜ ለአካለ መጠን አለመድረስ (ከ18 ዓመት በታች መሆን) የአዕምሮ ህመም፣ድርጊቱን ለመፈፀም ወሳኝ የሆነ የአካል ክፍል ጉዳት እና በፍርድ ቤት የሚጣል ከመብት የመሻር ቅጣት ናቸው፡፡
የተወሰኑ ነገሮችን ብቻ የማድረግ ችሎታ የሚያሳጣው ደግሞ የኢትዮጵያ ዜጋ አለመሆን ሲሆን፤ ለዜጎች ብቻ በተከለሉ ተግባራት ለምሳሌ መምረጥ ወይም መመረጥ፣በተወሰኑ የሥራና የንግድ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ በመገናኛ ብዙሀን፣ በብሮድካስት አገልግሎት እና በመሳሰሉት የተወሰኑ መስኮች ለመሰማራት የኢትዮጵያ ዜጋ ያልሆነ ሰው በሀገራችን ሕጎች ስለተከለከለ ለነዚያ ተግባራት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለመሆኑ ችሎታ ይጎለዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0hJJCeE4WH79TXYPvbzDUCqkrngJnR3WccZvqAY71NZnVMesZ1ZEc3ttvrDH66Bq3l

ለፍርድ_አፈጻጸም_የተያዘ_ንብረት_ለፍርድ_አፈጻጸም_የሚሸጥበት_ሥነሥርአት.pdf
160 KB
ተከራካሪ ወገኖች በመደበኛ ፍርድ ቤት ሆነ በሌላ ፍርድ ቤትን ተክተው ውሳኔ በሚያስተላልፉ ተቋማት ቀርበው በመከራከር ውሳኔ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህም ውሳኔ በህግ ለማስፈፀም ስልጣን በተሰጠው አካል ይፈፀማል። ከሚፈፀምባቸው መንገዶችም አንዱ ለፍርድ አፈፃፀም በሚያዝ ንብረት ነው። በዚህ ንብረት እና አፈፃፀሙ ዙሪያ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ረዳት ዳኛ በሆኑት ቁም ነገር ደጉ ይህ አጭር ፅሁፍ ተዘጋጅቷል።
Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu)
በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሲቀርቡ ቴምብር ቀረጥ ለሚከፈልባቸው ሰነዶች ተገልጋዮች ክፍያ መፈጸም የሚችሉባቸው የገቢዎች ማዕከላት፡፡
************************************************************
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ በፍርድ ቤት በማስረጃነት በሚቀርቡ ሠነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ ለማስለጠፍ እና ቀረጥ በተመን ለማስከፈል ባለጉዳዮች ክርክራቸውን በሚያቀርቡበት ምድብ ችሎቶች አቅራቢያ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በምድብ ችሎቶች አቅራቢያ የተደራጁ የቴምብር ቀረጥ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና የወረዳ ቢሮዎች ከዚህ በታች የተመለከቱት መሆናቸውን እናሳውቃለን፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት