Forwarded from Mizan Law / ሚዛን ሎዉ⚖️ (Mesfin assefa)
ከባድ_አካል_ጉዳት_ማድረስ_ወንጀልየወህቁ_555.pdf
963.6 KB
ከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል(የወ/ህ/ቁ.555)
Vs.
ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል (የወ/ህ/ቁ.556)
በአንዋር መሀመድ
ቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ከከባዱ የአካል ጉዳት ማድረስ (Grave wilful injury Vs. Common willful injury) የሚለየው በሚደርሰው አካላዊ ጉዳት መጠን መሆኑን የወንጀል ህግ ድንጋጌዎቹን በማንበብ መገንዘብ ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ በወንጀል ህጉ ከተቀመጠው የቀላልና ከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ዝርዝር በራሱ ግልጽ ባለመሆኑ- ለማድረግም ስለማይቻል፡፡ ብዙ ግዜ በባለሙያዎች ዘንድ ቀላሉን ከከባድ አልፎ አልፎም ቀላል የአካል ጉዳት ማድረስን ከእጅ እልፊት ለመለየት ልዩነቶች ይፈጠራሉ፡፡
የወ/ህ/ቁ. 555 ከባድ የአካል ጉዳትን በመዘርዘር ከመተርጎም (Illustrative) የሞከረ ቢሆንም በመጨረሻው ንዑስ አንቀጽ 555(ሐ) ስር “በሌላ መንገድ ከባድ የሆነ ጉዳትን…” የሚል ጥቅል (ሰፊ) ሀረግ ያስቀምጣል፡፡ በዚህም የተሰጠው ትርጉም ለሰዎች ግላዊ ቀላልና ከባድ እይታ ውስጥ መውደቁ አይቀርም፡፡ ቀላል አካል ጉዳት ማድረስን ደግሞ “ከከባዱ ውጭ ..” በማለት አሁንም ለልዩነት በር በሚከፍት መልኩ አስቀምጦታል፡፡
በወንጀል ህግ ላይ በተጻፈ ጽሁፎች ውስጥ ቀላል የአካል ጉዳት ለመባል የቆዳ ውስጠኛ ክፍል መሰንጠቅ ጭምር የሚይዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ (A complete breaking of all layers of the victims’ skin)
ይበልጥ በተብራራ መልኩ ሲቀመጥ ፡- (the continuity of the whole skin must be broken; ….including not merely the outer skin of the body but the skin of an internal cavity….) (ይመልከቱ፤ Dr. Roger Geary,

Forwarded from De Z Habesha
የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ ጸደቀ
*
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ ደንብ አጽድቋል።
ደንቡ በጸደቀበት ወቅት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ እንደተናገሩት የዳኝነት አከፋፈል ሥርዓቱን ለማዘመን፣ ሥርዓቱም አጭር፣ ቀልጣፋና ለከፋዩ ያመቸ እንዲሆን ለማስቻል ሕጉን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች እስከ አሁን ድረስ ሲጠቀሙበት የነበረው የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል የህግ ክፍል ማስታወቂያ ደንብ በ1945 ዓ.ም የወጣና ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በደንቡ ያልተሸፈኑ በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው ወቅቱን ያገናዘበ የዳኝነት ክፍያን መወሰኛ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በተጨማሪም የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁን ከደረሱበት ወቅታዊ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃና ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር ተመጣጣኝ የሆነ የዳኝነት ክፍያ ለማስከፈል የሚያስችል ሕግ በማስፈለጉ ደንቡ ተዘጋጅቷል።
ደንቡ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቂ ውይይት የተደረገበትና የሀገር ውስጥን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባትና የሌሎች ሀገራትንም ልምድ ታይቶ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል ። መረጃዉ የኢትጵያ ፕሬስ ድርጅት ነዉ፡፡👇👇👇👇
© ዳንኤል ፈቃዱ

Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu √)
ሰሞኑን በፓርላማ የፀደቀው የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ?
➡️ የዘር ፍሬ በመለገስ ልጅ መውለድ እንዲቻል ለመፍቀድ ቀርቦ የነበረው የአዋጅ ድንጋጌ የለበትም።
➡️ በመሣሪያ ላይ የተመሠረተ አተነፋፈስ ማቋረጥ ተፈቅዷል።
" የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ " ለ3 ወር ያህል ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ ከቀናት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ9 ድመጸ ተአቅቦ ፣ 1 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።
የዘር ፍሬን በመለገስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ልጅ መውለድ እንዲቻል እንዲፈቅድ በረቂቅ ሕጉ ተካቶ የነበረው አንቀጽ እንዲወጣ ተደርጓል።
ለጤና፣ ማኅበራዊና ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ውይይት ሲደረግበት በነበረው ረቂቅ አዋጅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት የሚፈቅደው ድንጋጌ እንዲወጣ ተጠይቆ ነበር።
ድንጋጌው እንዲወጣ ያደረገው " ልጅ እንዲኖረው የፈለገ ምን ይሁን ? " ለሚለው ጥያቄ፣ የጉዲፈቻ ልጅ በበቂ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ተነጋግሮበት በመወሰኑ ነው።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
" ድንጋጌው ከረቂቁ እንዲወጣ የተደረገው ወላጆች ልጅ ለመውለድ ያላቸውን ፍላጎት ሳይሆን፣ ሕግ አውጪው የሚወለዱ ልጆች የማኅበረሰብ ቀውስ እዳያጋጥማቸው በማሰብ፣ ከእምነትና ከማኅበረሰብ መስተጋብር ጋር የተጣጣመ ሕግ መውጣት እንዳለበት ታስቦ ነው።
በተጨማሪም ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ ድንጋጌ ማውጣት ስለማይፈቀድ ነው።
ለተጋቢ ባለትዳሮች ፍላጎት ሲባል ይህ ሕግ ወጥቶ የሚወለደውን ሕፃን መብት መጋፋት አያስፈልግም።
ይሁን እንጂ የፀደቀው ሕግ በጋብቻ የተጣመሩ ባለትዳሮች ያለ ልገሳ የራሳቸውን የዘር ፍሬ ብቻ በመውሰድ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዷል " ብለዋል።
ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው ረቂቅ ሕግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ ወይም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆናቸው በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ እንደሆነ ይል ነበር፡፡
የምክር ቤት አባላት የዘር ፍሬን በሕጉ ከተፈቀደው ውጪ አሳልፎ የሰጠ አካል ከተገኘ በወንጀል ሕግ ተጠያቂ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል ፤ በአዋጁ አንቀጽ 14 በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡
በዚህ ድንጋጌ በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓትን ማቋረጥ የሚቻለው፣ የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
አፈጻጸሙ አግባብነት ባላቸው ሶስት ባለሙያዎች ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
#ሪፖርተር

Forwarded from JURIS PODCAST
በፍትሐብሔር ጉዳይ ሕግ ወደ ኋላ ሄዶ ይሰራልን ?
እንደሚታወቀው በወንጀል ጉዳይ አንድ የወንጀል ድርጊት በኢፌድሪ የወንጀል ህግ መሠረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው የወንጀል ሕግ ግን እንደወንጀል ካልተቆጠረና የተፈፀመው ይህ ሕግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ እደማይችል በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 5(2) ላይ የወንጀል ህግ ወደኃላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑን ይደነግጋል፡፡የኢፌድሪ ህገ-መንግስትም በአንቀፅ 22(1) ላይ ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ በህግ የተደነገገ ካልሆነ በስተቀር ሊቀጣ አይችልም፡፡ሲል ይደነግጋል፡፡ይህ የወንጀል መርህ ለፍትሐብሔር ተፈፃሚነት ይኖረዋልን ?ይህን አከራካሪ ጭብጥ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 229940 (ባልታተመ) ውሳኔው ላይ ህግ ወደኃላ ተመልሶ አይሰራም በሚል የሚታወቀው መርህ መሰረት ሀሳቡ አንድ ህግ በሥራ ላይ መዋል ያለበት ሕጉ ከፀና በኃላ በተፈጠረ መብትና ግዴታ ወይም ፍሬ ነገር ላይ ተፈፃሚ መሆን እንዳለበት እና ዜጎች በሚያውቁት ህግ መተዳደር አለባቸው የሚለውን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡እንዲሁም አንድ ህግ የሚፀናበትን ጊዜ አስመልክቶ በህግ አውጪው ከተደነገገበት ቀን በፊት ለተፈጠሩት ክስተቶች ወይም መብትና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አይኖረውም የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡የዚህ መርህ ተግባራዊነት የህግ የበላይነት ከሚረጋገጥባቸው መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ስለሆነም በተለይም አንድ መሠረታዊ ህግ(substantive law) ወደ ኃላ ተመልሶ እንዲሰራ ህግ አውጪው በህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካላመለከተ በስተቀር ፍርድ ቤት ወይም ሌላ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ለያዘው ጉዳይ ተፈፃሚነት ያለውን መሠረታዊ ህግ ሲመርጥ መሠረት ሊያደርግ የሚገባው ወይም መሠረት እንዲያደርግ የሚጠበቅበት ለክርከሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ በተፈጠረበት ጊዜ ተፈፃሚ ሲሆን የነበረውን ህግ ሊሆን ይገባል፡፡ሲል በፍትሐብሔር ጉዳይ አንድ ህግ ወደኃላ ሄዶ የሚሰራው በህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካመላከተ ብቻ ነው ካልሆነ አንድ ህግ ወደኃላ ሄዶ አይሰራም ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
ፕሌይ ስቶር በመግባት ሌጋልቴክ/LegalTech ብላችሁ በቀላሉ በመፈለግ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ !
አፕሊኬሽኑን ለማውረድ በዚህ ሊንክ ግቡ 👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli
ጠበቆች የሕግ ባለሙያዎች ና ተማሪዎች በዚህ የሕግ ሶፍትዌር
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው አድራሻ መግባትና መመዝገብ ትችላላችሁ
#share #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግምክር #የኢትዮጵያ
https://t.me/Ethiopianlegalinsight

Google Play
ClauseBit - Apps on Google Play
ClauseBit is a application that revolutionize the legal industry in Ethiopia.
Forwarded from አለ ሕግ
#እንድታውቁት
ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦
➡ ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።
➡ አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።
➡ ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።
🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።
➡ ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።
➡ አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።
➡ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።
➡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።
➡ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።
(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
#tikvahethiopia
🔴 Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:
✅ Website & Social Media⌛
✅ Linktree:📱 📱 📱 📱 📱 📱 📱 📱
https://linktr.ee/alehig
📱 Facebook:✅
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
📱 Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig
🌐 📱 📱 📱 📱 Website: alehig.com
Direct Contact🔈 ⬇️ ✉️
📱 WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱 Telegram: ✉️ @MikiasMelak
Our Commitment
alehig.com
📊 አለሕግ🔽
🔠 🔠 🔠 🔠 🔠 🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼 ⭐️
We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.
Feel free to reach out anytime‼️
ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦
➡ ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።
➡ አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።
➡ ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።
🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።
➡ ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።
➡ አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።
➡ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።
➡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።
➡ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።
➡ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።
➡ መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።
(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
#tikvahethiopia
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:
https://linktr.ee/alehig
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/
https://t.me/AleHig
Direct Contact
Our Commitment
alehig.com
Alternative Legal Enlightenment & Services
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.
Feel free to reach out anytime
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Mizan Law / ሚዛን ሎዉ⚖️ (Mesfin assefa Ali)
የህፃናት_መብት_dna_የፌደሬሽን_ምክር_ቤት.pdf
509.5 KB
1. ሕፃናት በፍ/ቤት ለማስረጃነት የሚውል የዘረ መል (DNA) ምርመራ ለማድረግ አይገደዱም፤ ምርመራውን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ብቻውንም እንደ በቂ ማስረጃ ተቆጥሮ "ሕፃኑን DNA ለማስመርመር ፈቃደኛ ያልተሆነው ልጁ የባልዬው ባይሆን ነው" የሚል የሕግ ግምት [የፍ/ሕ/ቁ. 22ን ልብ ይሏል] በመያዝ ባልዬው የልጁ አባት አይደለም ብሎ መወሰን ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ነው::
2. በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ ልጄ አይደለም በማለት (አባትነትን ለመካድ) የሚቀርብ ክስ በጠባቡ ሊታይ የሚገባና የክስ ማቅረቢያ ጊዜውም ባልዬው የልጁን መወለደ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ ባሉት 180 ቀናት ውስጥ የመሆኑ ይርጋ የሕፃናትን ሕገ መንግሥታዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከሌሎች ይርጋዎች የተለየ ስለሆነ በአንድነት ሊታይ የማይገባ እና ተከራካሪ ወገኖች ባያነሡትም እንኳን ፍ/ቤቶች በራሳቸው አንሥተው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ ነው::
ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 94/13
ግንቦት 30/2013 ዓ.ም

Forwarded from Guyita Guna
የእምነት ማጉደል ወንጀል እና የአደራ ውል ሰ/መ/ቁ.209733 / Daniel Fikadu Law Office?
የእምነት ማጉደል ወንጀል ምን ማለት እንደሆነ እና የወንጀሉማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 675 ስር ተመልክቷል፡፡ በዚሁ አግባብ አንድ ሰው የእምነት ማጉደል ወንጀልፈፅሟል ተብሎ በወንጀል የሚቀጣው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግናን ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰውየሆነውን እና ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይምበከፊል ለራሱ ያደረገ፣ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ወይም ይህንን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት የፈፀመ እንደሆነ እናይህንኑ በእምነት ወይም በአደራ የተቀበለውን ንብረት ወይም ጥሬ ገንዘብ እንዲመልስ ወይም እንዲከፍል ሲጠየቅ ንብረቱያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግሎት ያዋለው ለመሆኑ ማስረዳት ያልቻለ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆን ከዚሁድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 3 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ የእምነት ማጉደል ወንጀል ማቋቋሚያ
83መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ውስጥ አንዱ በአደራ የተቀበሉትን ንብረት እንዲመልስ ሲጠየቅ አለመመለስ እንደሆነ በዚሁ ድንጋጌ ስርበግልፅ ተመልክቷል፡፡
በህገ ወጥነት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለውን ንብረት በአደራፈርመው መቀበላቸው በግራ ቀኙ መካከል ያለው ግኑኝነት የውል የሚያስመስለው ቢሆንም እንዲያስቀምጡ የተሰጣቸውንንብረት ሲጠየቁ አለማቅረብ ንብረቱን የእምነት መጉደል ወንጀል አንጂ የውል ግዴታን አለመፈፀምን የሚመለከት ፍትሐ-ብሄራዊኃላፊነት አይደለም። /በአደራ አሰቀማጩ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።/ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በዳንኤል ፍቃዱ /ጠበቃ/

Forwarded from Federal Law and Justice Institute የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት (kenean X)
• የቅጣት አላማዎች በጠቅላላ
ቅጣት ሊያሳካ ከተነሳለት አላማ በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የተለያዩ አላማዎችን ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህ አላማዎች በወንጀል ቅጣቶች ውስጥ በተናጥል ወይም በጣምራ ተካተው የሚገኙበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ቅጣት የሚከተሉት ዓላማዎች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡
1. ቅጣት እንደ በቀል ማስፈፀሚያ (Retribution)
የዚህ የቅጣት ዓላማ አራማጆች ወንጀለኛው ማህበረሰቡ ተው አታድርግ ያለውን ነገር ተላልፎ በማህበረሰቡ ህይወት፣ አካል፣ ጤና፣ ሞራል፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ፋይዳ ላይ ጥቃት ስለፈፀመ ለዚህ ተገቢ ያልሆነ ድርጊቱ የጁን ማግኘት አለበት የሚል መነሻ ያላቸው ሲሆን መሠረቱም የሀሙራቢ አይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ መርሆ ነው፡፡ የዚህ ቅጣት አላማ ተቃዋሚዎች ቅጣት እንደዚህ ከሆነ ለሁሉም ወንጀሎች ተመሳሳይ አቻ ቅጣት ልናገኝላቸው አንችልም ለምሳሌ በሀገር ክደት ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ወንጀለኛ አቻ ቅጣት ምንድ ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እንዲሁም እንዲህ አይነቱ አካሄድ ዓለምን የአይነ ስውራንና የአካል ጉዳተኞች መነሃሪያ ያደርጋታል የሚል መከራከሪያ አላቸው፡፡ ይህ አይነቱ የበቀል አስተሳሰብ በዘመናዊው አለም የጎለበተውን ሰብአዊ መብት የሚቃረን በመሆኑ በአሁኑ ዘመን በአንዳንድ ሀገሮች ካልሆነ በስተቀር እንምብዛም አይገኝም፡፡
2. ቅጣትን እንደ ወንጀል መከላከያ (Deterrence)
በሌላ በኩል ደግሞ የቅጣት ግብ ወደ ፊት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል እንጂ ወንጀለኛውን መበቀል ሊሆን አይገባውም፡፡ የፈሰሰ ውሃ ስለማይታፈስ ወንጀለኛው ላደረገው ነገር የምንቀጣው ላደረገው ነገር እንደ ቅጣት ሳይሆን ወደ ፊት ቅጣት ፈርቶ ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፅሙ ለመከላከል ነው የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወንጀለኛው ወንጀል እንዲፈፅም ያነሳሳው ምክንያት ከቅጣት ፍርሃቱ ሊበልጥ ስለሚችል እንዲሁም ሰዎች ወንጀል በሚፈፅሙበት ቅፅበት ቅጣት ትዝ ስለማይላቸው ቅጣት ሁል ጊዜ ይህን ግቡን ላይመታ ይችላል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ በተጨማሪም በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን ወንጀልና የወንጀለኞችን ደጋጋሚነት በማውሳት ቅጣት የማስተማር ግቡን እንዳልተወጣ ያሳያል የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡
3. ቅጣት እንደ ወንጀለኛውን ማግለያና መለያ (Incapacitation)
በዚህኛው አላማ ደግሞ ቅጣት ወንጀለኛውን ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለዘላለሙ (በሞት ቅጣት) ወንጀል ከሚፈፀምበት ማህበረሰብ በማግለል ወይም በመለየት በማህበረሰቡ ላይ ድጋሜ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል ይቻላል የሚሉ ወገኖች ያሉ ሲሆን ወንጀለኛው እስር ቤት በሚሆንበት ጊዜ ማህበረሰቡ ከወንጀል ይገላገላል፤ እንደ ሞት ያሉ ቅጣቶች በሚጣልባቸው ወንጀሎች ደግሞ ወንጀለኛው በድጋሜ ወንጀል የመፈፀም እድል ስለሌለው ማህበረሰቡ ከወንጀለኛው ድጋሚ ጥፋት መታደግ ይቻላል የሚል ነው፡፡ እንደ ሌሎቹ ቅጣት ሁሉ በዚህ የቅጣት አላማ ላይም ትችቶች ያሉ ሲሆን ከሞት ቅጣት ውጭ ባሉ ቅጣቶች ላይ ወንጀለኛው እስር ቤትም ሆኖ እንደ ስርቆት፣ ግብረሰዶም፣ ግድያና የአካል ጉዳትን የመሳሰሉ ወንጀሎችን መፈፀሙ አይቀርም ወይም ከእስር ሲፈታ ጠብቆ መልሶ ወንጀል ሊሰራ ይችላል፣ እንዲያውም በእስር ቤት ቆይታው ወንጀል ተምሮ እንዴት በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ እንደሚፈፅመው፣ እንዴት የመያዝ እንድሉን እንደሚቀንስ ተምሮ ሊወጣ ስለሚችል ይህ የቅጣት አላማ ብዙ ርቀት አያስጉዝም፣ እንዲሁም የቅጣቱ ግብ እስረኛውን በማህበረሰቡ ላይ ይበልጥ በቀለኛ ስለሚያደርገው በወንጀል ተግባሩ የመግፋት ዝንባሌ ሊኖረው ይችላል የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡
4. ቅጣት ወንጀለኛውን እንደ ማረሚያ (Rehabilitation)
የዚህ ቅጣት ግብ መሠረት አጥፊውን ከመረዳት የሚጀምር ሲሆን ወንጀለኛው ወንጀል ውስጥ የገባው ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ወንጀል እንዲፈፅም ገፍተውት ስለሆነ እነዚህ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች በማከም ወንጀለኛውን ከድጋሜ ጥፋት ማረም ይቻላል የሚል ነው፡፡ ወንጀለኞች ተወልደውም ይሁን ተሰርተው ወንጀለኛ እንዲሆኑ ያደረገ ሳይኮሎጂካል፣ ባዮሎጂካል፤ ኢኮኖሚካል ወይም አካባቢያዊ አሊያም ማህበራዊ ምክንያት ስለሚኖር ወንጀለኛው ወንጀል ለመፈፀም ያነሳሳውን ምክንያት በመመርመር ምክንያቱ አክሞ በማዳን ወንጀለኛውን ጤነኛ አምራች ወንጀልን የሚጠየፍ ለማህበረሰቡ ርህራሄ የሚያሳይ አድርጎ መመለስ ስለሚቻል የቅጣት ግብ ይህ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ያለው ነው፡፡
• የቅጣት አላማና ግቦች በኢ.ፊ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ
የወንጀል ህጉ አላማና ግቦች በህጉ አንቀፅ 1 እንደዚሁም በመግቢያው ላይ በዝርዝር ተገልፀው ይገኛሉ፡፡ በዚህ መሰረት የወንጀል ሕጉ ዓላማ ስለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎችን፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ ስርዓት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ሲሆን የሕጉ ግብ ደግሞ ወንጀል እንዳይፈፀም ለመከላከል የሚያስችል ስለወንጀሎችና ስለሚያስከትሉት ቅጣት በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ይህ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀለኞቹ ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ፣ ለሌሎችም ማስተማሪያ እንዲሆኑ፣ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሆነ በወንጀል ህጉ አንቀፅ አንድ ተገልፀዋል፡፡ በዚህ መሰረት የወንጀል ህጉ ከላይ ከተዘረዘሩት የቅጣት አላማና ግቦች ውስጥ በተለይ ችሎታ ማሳጣትን፣ ማስጠንቀቂያ መስጠት እና እርማትን ወይም መልሶ ማቋቋምን አዋህዶና አካቶ ይዟል ለማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የወንጀል ሕጉ የቅጣት ዓላማና ግቦች በሕጉ በጠቅላላም ሆነ ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ ስለቅጣት አወሳሰን በሚደነግጉት አንቀፆች ስር ተንፀባርቆ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ የወንጀል ዓይነቶች ላይ ተፈፃሚ እንዲሆኑ የተደነገጉት የቅጣት አይነቶችና መጠን ተቀባይነት ያላቸውን የቅጣት አላማና ግብ ለማሳካት የተደነገጉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በወንጀል ህጉ ጠቅላላ ክፍል በአንቀፅ 117 የተደነገገው የሞት ፍርድ፣ በአንቀፅ 123 ስር የተደነገገው ከቤተሰባዊ፣ ሙያዊና ተመሳሳይ ከሆኑ መብቶች የመሻር ቅጣት፣ በአንቀፅ 127 ስር የተገለፀው ከወታደራዊ መዓረግና የሥራ ገበታ መቀነስ ወይም ማስለቀቅ እንዲሁም ከአንቀጽ 142-150 የተገለፁት የተለያዩ ፍቃድ የመንጠቅ ቅጣቶች የወንጀል ሕጉ የቅጣት ዓላማ ወንጀል የመፈፀም ችሎታን ማሳጣት እንደሆነ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ እንዲሁም በወንጀል ህጉ አንቀፅ 98 ስር እንደተደነገገው የፅኑ እስራት ግብ ተቀጪው እንዲታረምና ወደ ማህበራዊ ኑሮው እንዲመለስ ከማድረግ በተጨማሪ በተለይ ለህብረተሰቡ ደህንነት ጥብቅ ቁጥጥር ሥር እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡

👍1
ህገ-ወጥ የስራ ውል መቋረጥ የሚያስከትለው ውጤት
የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ለተዋዋይ ወገኞች ፈቃድ ብቻ እንዳይተውና ህግ ጣልቃ እንዲገባ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ከስራ ውል መቋረጥ ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህም የስራ ውል በዘፈቀደ ሳይሆን በበቂ ምክንያቶች ላይ ተመስርቶ የተቋረጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ሕግ አስፈላጊውን ጥበቃ ያደርጋል፡፡ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያለ የስራ ውል በአሰሪው አነሳሽነት፣በሠራተኛው አነሳሽነት፣በህግ በተደነገገው መሰረት እና በህብረት ስምምነት በተቀመጠው መሰረት ሊቋረጥ የሚችል ሲሆን በህግ ተቀባይነት ያለው የስራ ውል መቋረጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ከአንቀፅ 23 ጀምሮ እና ዝርዝር ምክንያቶቻቸውና ሁኔታዎቻቸው ደግሞ ከዚሁ አንቀጽ ቀጥለው በሚገኙት አንቀጾች ተደንግገዋል፡፡
• በአሰሪው አነሳሽነት የሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ እንደየ ሁኔታው በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማሰጠንቀቂያ ሊደረግ የሚችል ሆኖ የምክንያቶቹ ዝርዝር እና አፈጻጸሙ ከአንቀጽ 26 እስከ 30 ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሕብረት ስምምነት መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ለማቋረጥ የሚያበቃ ምክንያት ተደርጎ የተወሰደ ጉዳይም በአሰሪው አነሳሽነት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ሊያቋርጥ የሚችል መሆኑ በአንቀጽ 27/1/ተ/ ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የስራ ውል በአሰሪው አነሳሽነት ሊቋረጥ የሚችለው የሰራተኛውን ጠባይ ወይም የሰራተኛው የመስራት ችሎታን ከሚመለከቱ ግልጽ ሁኔታዎች ወይም ከድርጅቱ ድርጅታዊ አቋም ወይም የስራ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት ባላቸው ምክንያቶች ብቻ ነው፡፡
• በሰራተኛው አነሳሽነት የሚደረጉት ደግሞ ልክ በአሰሪው አነሳሽነት ሊደረግ እንደሚችለው በማስጠንቀቂያ እና ያለማሰጠንቀቂያ ውሉን የሚያቋርጥበት መንገድ ሲሆን ( ለምሳሌ የስራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ከሚቻልባቸው ምክንያቶች ውስጥ አሰሪው የሰራተኛውን ክብርና ሞራል የሚነካ ወይም በወንጀል የሚያስቀጣ ሌላ አድራጎት የፈፀመበት እንደሆነ) ሁኔታዎቹና ምክንያቶቹ ከአንቀጽ 31 እስከ 33 ተደንግነው ይገኛሉ፡፡
• ውሉ በሕግ የሚቋረጥበት ምክንያቶች በአብዛኛው ከሁለቱም ወገን ቁጥጥር ውጭ ያሉ ሲሆን( የሰራተኛው መሞት፣በጡረታ መገለል፣የድርጅቱ መክሰር ወይም መዘጋት ወ.ዘ.ተ አንቀጽ 24)፤ የስራ ውል ሁለቱም በፈቃደኝነት የሚገቡበት እንደመሆኑ ሁሉ ሁለቱም በፈቃኛነት ከተስማሙ ውሉን ሊያቋርጡ የሚችሉበት ሁኔታም በአንቀጽ 25 ስር ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ከላይ በተገለጹት ቁጥሮች በተደነገጉት ምክንያቶችና ሁኔታዎች የሚፈጸም የስራ ውል መቋረጥ ሕጋዊ የስራ ውል መቋረጥ ሲሆን ከነዚህ ውጭ የሚደረጉ የስራ ውል መቋረጥ በሕገወጥነት የሚፈረጁ ናቸው (አንቀጽ 42 ድረስ በዝርዝር ተቀምጧል)፡፡
ሰራተኛው የስራ ውሉን በህገ ወጥ መንገድ ሲያቋርጥ የሚያስከትለው ውጤት
በሠራተኛው አነሳሽነት የሚፈጸም የስራ ውል መቋረጥ ሕገወጥ ሊሆን የሚችለው ሠራተኛው ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ከሚችልባቸው በአንቀጽ 32 ስር ከተደነገጉት ውጪ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች ሆኖ ነገር ግን ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ማስጠንቀቂያ ለአሰሪው ሳይሰጥ ውሉን ያቋረጠ ከሆነ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የስራ ውሉን ያቋረጠ ሠራተኛ ለአሰሪው አሰሪው ለሱ ከሚከፍለው ቀሪ ክፍያ ውስጥ ከሠላሳ ቀናት ያልበለጠ ክፍያን በካሳ መልክ መክፈል ይኖርበታል (አንቀጽ 45)፡፡
አሰሪው የስራ ውሉን በህገ ወጥ መንገድ ሲያቋርጥ የሚያስከትለው ውጤት
አንድ አሰሪ ሰራተኛውን በህገ-ወጥ መንገድ ከስራ ቢያሰናብት ሰራተኛው ሊያገኛቸው የሚችላቸው መፍትሔዎች ምንድናቸው ወይም ውጤቱ ምን ይሆናል ለሚለው በአዋጁ ክፍል 4 አንቀፅ 43 መሰረት እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ሠራተኛው ወደ ስራ እንዲመለስ አልያም የስራ ስንብት ክፍያን ጨምሮ ካሳ እና ሌሎች ተያያዥ ክፍያዎች ተከፍለውት የስራ ውል መቋረጡ እንዲፀና ሊደረግ ይችላል፡፡ የሰራተኛው ወደ ስራ መመለስ የስራ ከባቢውን የሚረብሽ ከሆነ እና በአሰራው እና በሰራተኛው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሻክር ከሆነ ወደ ስራ ከመመለስ ይልቅ በህጉ የተቀመጡትን ክፍያዎች ፈፅሞ ማሰናበት የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ህጉ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ሁለቱን አማራጮች ያስቀመጠ ሲሆን ይህንንም በማጠናከር የፌ/ጠ/ፍ/ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 18581 ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡

ስለአመክሮ አንዳንድ ነገሮች
አመክሮ ማለት አንድ ታራሚ የእሥራት ጊዜውን ሙሉ በሙሉ ከመፈጸሙ በፊት በገደብ ወይም በሁኔታ ላይ ተመስርቶ ከእስር የሚለቀቅበትና ገደቡን ተላልፎ ሲገኝ እንደ አስፈላጊነቱ ወደነበረበት ማረሚያ ቤት እንዲመለስ የሚደረግበት አሠራር ሲሆን በአመክሮ መለቀቅ ሙሉ በሙሉ ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ሳይሆን ይልቁንም የቀረውን 1/3ኛ ቅጣት ታራሚው በገደብ ወይም ሥልጣን በተሰጠው አካል ክትትል ሥር ሆኖ እንዲፈጽም የሚደረግበት የቅጣት አፈጻጸም ሥርዓት ነው፡፡
በአመክሮ ለመለቀቅ መሟላት ያለባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች
1ኛ፣ በፍርድ ቤት ከተላለፈው ቅጣት 2/3ኛውን መፈጸም፣ የእድሜ ልክ እስራት በሚሆንበት ጊዜ ቢያንስ 20 ዓመት እስር ሲፈጽም፣
2ኛ፣ ከተበዳይ ጋር በተደረገ ስምምነት (እርቅ) ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ሊከፍል የሚገባውን ካሳ መክፈል፣
3ኛ፣ በማረሚያ ቤት ቆይታው በሥራውና በጠባዩ መሻሻል ማሳየትና
4ኛ፣ ተቀጪው “ልማደኛ ደጋጋሚ” አለመሆን ናቸው፡፡
እነዚህና መሰል የህግ ግንዛቢያችንን የሚጨምሩ ጉዳዮችን፣ አዳዲስ የሚወጡ ህጎችን፣ አዳዲስ ህግ-ነክ መረጃዎችን ለማግኘትና ለየትኛውም የህግ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/getuasnakew ሳብስክራይብ የቴሌግራም ግሩፓችንን https://t.me/debgzv174 ደግሞ ጆይን ያድርጉ።
አስተማሪ መልእክቶቻችንን ሼር በማድረግና የቴሌግራም ግሩፓችንንና ቻናላችንን ደግሞ ተደራሽ እንዲሆን ጓደኞቻችሁን አድ በማድረግና በመጋበዝ አጋርነተዎን ያሳዩን፤ ያበረታቱን።
በስልክ ልታገኙን የምትፈልጉ ወዳጆቻችን 0913771324 ላይ መደወል ይቻላል።
ምርጫዎት በአካል ቢሮ መምጣት ከሆነ ደግሞ መገናኛ የካ ክ/ከተማ አጠገብ ከሚገኘው ሰላም ታወር ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፊትለፊት እንገኛለን።

Telegram
ጌቱ አስናቀው የጥብቅናና የህግ ማማከር አገልግሎት
ይህ ቻናል አነጋጋሪ የህግ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግበት፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከህግ አንጻር ሙያዊ ምልከታዎች የሚቀርብበት ማንኛውም ሰው አባል ሆኖ የሚጠቀምበት አሳታፊና መማማሪያ ገጽ ነው። በመሆኑም እባከዎ ሼርና አድ እንድያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
☎️ስልክ ቁጥር 0913771324
getu.asn@gmail.com
☎️ስልክ ቁጥር 0913771324
getu.asn@gmail.com
ስለስመዎት አስበው ያውቃሉ?
የፍትሀ ብሔር ህጋችን ስለስም ዘርዘር ያሉ ድንጋጌዎችን ይዟል። አንድ ሰው አንድ የቤተዘመድ እና የአባት ስም ሊኖረው፤ አንድ ወይ ሁለት የግል ስሞች ሊኖሩት እንደሚችል ደንግጓል። የግል ስም አሰጣጥን በሚከተለው መንገድ እንዲሆን ደንግጓል።
1. የአንድን ልጅ የግል ስም የሚመርጠው አባቱ ነው፡፡ አባቱ በሌለ ጊዜ የአባቱ ቤተዘመዶች ይመርጣሉ።
2. ለልጁ ሁለተኛ የግል ስም እናቱ ወይም እርሷ የሌለች እንደሆነ የእናቱ ቤተዘመዶች መርጠው ሊያወጡለት ይችላሉ።
3. የልጁ አባት ያልታወቀ በሆነ ጊዜ ወይም የልጁ አባት ወገን የሆኑ ቤተዘመዶች የሌሉት የሆነ እንደሆነ የልጁ እናት ወይም እርሷ ባትኖር የእናቱ ቤተዘመዶች ለልጁ ሁለት የግል ስም ሊሰጡት ይችላሉ።
4. ከላይ የተጠቀሱት ቤተሰቦች በሌሉበት ወቅት ለልጁ በጣም ቅርብ የሆነ ወደ ላይ የሚቆጠር ወላጅ ወይም የጎን ዝምድና ያለው ሰው የቤተዘመድ እንደራሴ በመሆን የግል ስም ሊያወጡለት ይችላሉ፡፡ በአጋጣሚም በቤተዘመድ እንደራሴዎች እንደራ በመሆን የዝምድና ደረጃ እኩል በሚሆኑበት ጊዜ የልጁን የግል ስም የሚመርጠው በእድሜ ከፍ ያለው ወደላይ የሚቆጠር ወይም የጎን ዝምድና ያለው ሊሆን ይችላል።
5. በመጨረሻም ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በሙሉ የሌሉ እንደሆነ የልጁን የግል ስም የሚያወጣው የክብር መዝገብ ሹም መኮንን በአካባቢው ከሚገኙ ልማዳዊ ስሞች መካከል መርጦ ይሆናል።
ይህንን ካነበቡ በኋላ የርሰዎ ስም እንዴት እንደወጣና ህጉንስ እንዴት እንደተመለከቱት አስተያየተዎትን እንዲሰጡን በክብር ጋብዘነዎታል።