የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
25ቱ_የሙስና_ወንጀሎች

1. በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል (አንቀፅ 9)
2. ጉቦ መቀበል (አንቀፅ 10)
3. የማይገባ ጥቅም መቀበል (አንቀፅ 11)
4. አስታራቂ ሽማግሌዎችና ሌሎች ሰዎች የሚፈፅሙት ጉቦ የመቀበል ወንጀል (አንቀጽ 12)
5. የመንግስት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት (አንቀጽ 13)
6. አደራ በተሠጠው ዕቃ ያለአግባብ ማዘዝ (አንቀፅ 14)
7. በሥራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል (አንቀፅ 15)
8. በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ (አንቀፅ 16)
9. በህገወጥ መንገድ መሰብሳብ ወይም ማስረከብ (አንቀፅ 17)
10. ያለአግባብ ጉዳይን ማጓተት (አንቀፅ 18)
11. ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት (አንቀፅ 19)
12. ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀፅ 20)
13. ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ (አንቀፅ 21)
14. የሥራ ሚስጥርን መግለፅ (አንቀፅ 22)
15. መንግሥታዊ ወይም የህዝባዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት፣ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል (አንቀፅ 23)
16. መንግስታዊ ወይም የህዝባዊ ድርጅት ስነዶችን ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ (አንቀ8 24)
17. ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት (አንቀፅ 25)
18. ዋጋ ያለዉን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት (አንቀፅ 26)
19. ማቀባበል (አንቀፅ 27)
20. በሌለው ሥልጣን መጠቀም (አንቀፅ 28)
21. በግል ተሰሚነት መነገድ (አንቀፅ 29)
22. በምርጫ ላይ የሚሰጥ መደለያ (አንቀጽ 30)
23. ከባድ የእምነት ማጉደል (አንቀፅ 31)
24.ከባድ አታላይነት (አንቀፅ 32)
25. በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ ስለመርዳት (አንቀጽ 33
❤1👏1
ምንጭ:- የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 የተወሰደ ነው
Forwarded from Abe Shewa
#ቀልድ_መስለው_ነገር_ግን_ወንጀል_የሆኑ_ድርጊቶች ‼️
****
1. የሰውን ፎቶ/ቪዲዮ መለጠፍ
ድርጊቱ፦ መንገድ ላይ ያዩትን ጠብ ወይም አስቂኝ ነገር ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ቀርጾ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ።

ውጤቱ፦ የግል ነፃነትን መጣስ ተብሎ ያስከስሳል።

2. የሀሰት ወሬ ማሰራጨት
ድርጊቱ፦ "እውነት ይመስላል" ብለው መረጃን ሳያረጋግጡ "Share" ማድረግ።

ውጤቱ፦ ሀ, በሀሰተኛና ጥላቻ ንግግርን         የማሰራጨት ተጠያቂነት
ለ,የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን መጣስ እና የሰላም መታወክ ተጠያቂነት።

3. በኮሜንት መሳደብ
ድርጊቱ፦ በፖስት ስር ሰዎችን በብሄር፣ በሃይማኖት ወይም በግል ማንነታቸው መስደብ።

ውጤቱ፦ የጥላቻ ንግግር እና ስም ማጥፋት ወንጀል።

4. ያለፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ
ድርጊቱ፦ "ለታመመ ሰው እርዳታ" በሚል የባንክ አካውንት እየለጠፉ በሶሻል ሚዲያ ገንዘብ መለመን።

ውጤቱ፦ ያለፈቃድ የገንዘብ ማሰባሰብ እና የማጭበርበር ጥርጣሬ።

5. የሰው ዲዛይን መስረቅ
ድርጊቱ፦ የሌላ ሰውን ሎጎ ወይም የፈጠራ ስራ "የእኔ ነው" ብሎ መጠቀም።

ውጤቱ፦ የቅጂ መብት (Copyright) ጥሰት ክስ።

6. የግል መልዕክትን ማጋራት (Screenshot)
ድርጊቱ፦ በ "Inbox" የተላከልዎትን ሚስጥራዊ መልዕክት ያለ ሰውየው ፈቃድ ለሰው እንዲታይ ፖስት ማድረግ።

ውጤቱ፦ የግል ሚስጥርን ማባከን (Privacy violation)።

ማሳሰቢያ፦ በኢንተርኔት የምንለጥፈው ነገር ሁሉ "ዲጂታል አሻራ" ስላለው በሕግ ፊት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።
Http://t.me/lawabelethio
❤1