የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ07/03/2014 ዓ.ም በአስቸኳይ አዋጁ እና በጊዜያዊ መታወቂያ መመሪያው ላይ የተጀመረው የአደባባይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ብቻ የተዳሰሱት ቦታዎች 5 ሲሆኑ እነሱም ገርጂ ሮባ፣ጎሮ፣ቦሌ መዳኒዓለም፣ጎላጎል እና ሃያ አራት ናቸው፡፡ በነዚህ ቦታዎች በጊዜያዊ መመሪያው ላይ የተዘጋጀውን 4538 እንዲሁም ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተዘጋጀውን 2642 በራሪ ጽሑፍ ባጠቃላይ 7180 (ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሊሰራጭ ችሏል፡፡
ቸር ያሰማን!
ጤና ይስጥልኝ!!
ዓለማቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በየአመቱ ሕዳር 24 (December 3) በተለያዩ መሪ ቃላት ይከበራል፡፡
በዚህም መሰረት ዘንድሮ በዓለም ለሰላሳኛ በሀገራችን ደግሞ ለሃያዘጠነኛ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ በሱማሌ ክልል ይከበራል፡፡ ይህንን ምክንያት በማድረግ እኔም ስለአካል ጉዳተኞች በወጡ ስምምነቶችና የራሳችን ሕጎች ዙሪያ ተከታታይ መልዕክቶችን በዚህ መገናኛ መስመር አደርሳለሁ፡፡
ለዛሬ ከስራ ስምሪት መብት ጋር በተያያዘ በዓለማቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት የሰፈረውን ቅድሚያ በልቶ ማደር ይቀድማልና አንቀጽ 27 ምን እንደሚል አቀርባለሁ፤ መልካም ምንባብ፡፡
ውድ ተከታያችን በሀገራችን ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በ2013 ዓ.ም ከተገኘው ሪፖርት መረዳት እንደተቻለው ጠቅላላ አካልጉዳተኛ ተቀጣሪዎች 6000 አይሞሉም፤ ለነገሩ የተማሩትም 10000 ስለመሙላታቸው መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡
አንቀጽ 27
1. ተዋዋይ መንግሥታት አካል ጉዳተኞች ከሌሉች ጋር በእኩል ደረጃ ላላቸው የመሥራት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ፡፡ ይኸውም በነፃ የተመረጠን ወይም ግልፅ፣ ሁሉንም አካታችና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት ባለው የስራ ገበያና ቅጥር የተገኘንና ተቀባይነት የተሰጠውን ሥራ ሰርቶ መተዳደሪያ የማግኘት መብትን ይጨምራል፡፡ ተዋዋይ መንግሥታት ይልቁንም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በስራ ላይ ለማዋል ይቻል ዘንድ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ በስራ ሂደት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በሚያካትት መንገድ የሰዎች የመስራት መብት እንዲጠበቅና ተሻሽሎ እውን እንዲሆን የሚያደርጉ ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ፡-
ሀ) ምልመላን፣ ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ቅጥርን፣ በቋሚ ስራ ላይ መቀጠልን፣ የሙያ እድገትን ደህንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የስራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ሁሉ አስመልክቶ በአካል ጉዳት ላይ የተመሰረተ ማናቸውም አይነት አድልዎ እንዳይፈፀም መከላከል!
ለ) ከወከባ መጠበቅንና ለቅሬታዎች የመፍትሄ ምላሽ ማግኘትን ጨምሮ እኩል ዋጋ ላለው ስራ እኩል ዕድልዎችንም ሆነ እኩል ክፍያ የማግኘት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ጤናማ የስራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩል ደረጃ ለአካል ጉዳተኞች ትክክለኛና ምቹ የስራ ሁኔታ የማግኘት መብትን መጠበቅ!
ሐ) አካል ጉዳተኞች ከሌሎች ጋር በእኩል ደረጃ በስራና በሙያ ማኀበራት የመደራጀት መብት እንዳላቸው ማረጋገጥ!
መ) አካል ጉዳተኞች የአጠቃላይ፣ የቴክኒክና ሙያ ነክ የአመራር መርሃ ግብሮች እንዲሁም የምደባ አገልግሎት፣ የሙያዊና ተከታታይነት ያለው ስልጠና ውጤታማ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ማስቻል!
ሠ) ለአካል ጉዳተኞች በሥራ ገበያ ውስጥ የቅጥርና የሙያ እድገት እድሎችን ከፍ ማድረግና እንዲሁም ሥራ ፍለጋ፣ ግኝት፣ ቆይታና የመልሶ ቅጥር ሁኔታዎች ረገድ ድጋፍ ማድረግ!
ረ) በግል ሥራ የመፍጠር ፣ ገቢ በሚያስገኝ ተግባር የመሰማራት፣ የሕብረት ሥራ ማሕበራትን የማሳደግና የራስን ሥራ የመጀመር ዕድሎችን ከፍ ማድረግ!
ሰ) በመንግሥት የሥራ ዘርፎች አካል ጉዳተኞችን በሰራተኝነት መቅጠር!
ሸ) የድጋፍ መርሀ ግብሮችን፣ ማበረታቻዎችንና ሌሎች እርምጃዎች ሊያካትቱ በሚችሉ ተገቢ ፖሊሲዎችና እንቅስቃሴዎች አማካኝነት በግሉ ዘርፍ በኩል የአካል ጉዳተኞችን የስራ ቅጥርና ስምሪት ማሻሻል!
ቀ) በሥራ ቦታ ለአካል ጉዳተኞች ምክንያታዊ ተቀባይነት ያለው ማስተካኪያ የቀረበላቸው መሆኑን ማረጋገጥ!
በ) ክፍት በሆነው የሥራ ገበያ ዘንድ የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ተሞክሮ ግኝት ማሻሻልና
ተ) የአካል ጉዳተኞችን የተለየ ስልጠና፣ ሙያዊ ተሃድሶ፣ ስራ ይዞ መቆየትና ወደ ስራ የመመለስ መርሃ ግብሮችን ማስፋፋት፡፡


ሲሳይ ሰማኝ
ኢትዮጵያ ከፍ ትበል!!!!
ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ክቡራን ሰላማችሁ ይብዛ!!
የዓለማቀፉ አካልጉዳተኞች መብቶች ስምምነት ስለተደራሽነቱ የደነገገውንና ሀገራችን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 በማጽደቅ የሕጎቿን አካል በማድረግ ለተፈጻሚነቱ ግዴታ የገባችለትን እንደሚከተለው ይድረስልኝ፡!
ተደራሽነት የሚመለከተው አንቀጽ 9 ነው፡፡
አካል ጉዳተኞች ኑሯቸውን በነፃነት እንዲመሩና በየትኛውም የሕይወት መስክ ያልተገደበ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል ተዋዋይ መንግሥታት እነዚሁ ወገኖች ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር ባልተናነሰ ሁኔታ ቁሳዊ አካባቢን የመድረስም ሆነ በመጓጓዣ ዘዴዎች፣ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችንና ስርዓቶችን ጨምሮ በመረጃና መገናኛ አውታሮች እንዲሁም በከተማም ይሁን በገጠር ለሕዝብ ክፍት በተደረጉ ተቋማትና አገልግሎቶች የመጠቀም ዕድል የተመቻቸላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተገቢነት ያላቸውን እርምጃዎች ይወስዳሉ፡፡
በተደራሽነት ላይ የተጋረጡትን መሰናክሎችና ገደቦች መለየትና ማስወገድን የሚያጠቃልሉት እነዚህ እርምጃዎች ከሁሉ በፊት ቀጥሎ በተመለከቱት ላይ ተፈፃሚዎች ይሆናሉ፡፡
ሀ) ሕንፃዎች፣ መንገዶች፣ የመጓጓዣ ዘዴዎችና እንደ ትምህርት ቤቶች፣ የመኖሪያ ሥፍራዎች፣ የሕክምና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶችና የስራ ማከናወኛ ቦታዎች ያሉ የቤት ውስጥና የቤት ውጭ መገልገያ ተቋማት!
ለ) የኤሌክትሮኒክስና የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎቶችን ጨምሮ የመረጃ፣ የመገናኛና ሌሎች አገልግሎቶች፡፡
2. ተዋዋይ መንግስታት በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን በስራ ላይ ለማዋል ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ፡፡
ሀ) ለሕዝብ ክፍት የተደረጉ ወይም የተመቻቹ ተቋማትንና አገልግሎቶችን ለመድረስ የሚያስችሉ ዝቅተኛ መስፈርቶችንና መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ በይፋ ማውጣትና ተግባራዊነታቸውን መቆጣጠር!
ለ) ለሕዝብ ክፍት የሆኑ አገልግሎቶችን በማመቻቸትና በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ የግል ድርጅቶች እነዚሁ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች ጭምር ተደራሽነት እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች ሁሉ ግምት ውስጥ ማስገባታቸውን ማረጋገጥ!
ሐ) አካል ጉዳተኞችን በሚገጥሟቸው የተደራሽነት ችግሮች ዙሪያ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ወገኖች ስልጠና መስጠት!
መ) ለሕዝብ ክፍት በሆኑ ሕንፃዎችና ሌሎች መገልገያ ተቋማት ውስጥ በግልጽ የሚታዩ ምልክቶችን፣ ብሬሎችንና በቀላሉ አንብቦ ለመረዳት የሚያስችሉ ቅጾችን ማስቀመጥ ወይም ማቅረብ!
ሠ) የቀጥታ ድጋፍ ዓይነቶችንና መሪዎችን፣ አንባቢያንንም ሆነ በምልክት ቋንቋ አጠቃቀም የሰለጠኑ አስተርጓሚዎችን ጨምሮ ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ሕንፃዎችንና ሌሎች መገልገያ ተቋማትን ተደራሽነት የሚያመቻቹ አማካዮችን ዝግጁ ማድረግ!
ረ) አካል ጉዳተኞች መረጃ የማግኘት ዕድል የተጠበቀላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሌሎች ተገቢነት ያላቸውን የእርዳታና የድጋፍ ዓይነቶችን ማስፋፋት!
ሰ) አካል ጉዳተኞች የመረጃን መረብን ጨምሮ በአዳዲስ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችና ሥርዓቶች የሚጠቀሙበትን ዕድል ከፍ ማድረግና!
ሸ) ለወደፊቱ በዝቅተኛ ዋጋ ሊቀርቡ የሚችሉበት ዕድል እስኪፈጠር ድረስ ምቹና ተደራሽነት ያላቸውን የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችና ሥርዓቶች ዝግጅት፣ ልማት፣ አመራረትና ሥርጭት ከመነሻው ጀምሮ ማስተዋወቅ
የሚል ዝርዝር ካስቀመጠው በመነሳት ይመስላል ኢትዮጵያም የህንጻ አዋጅ 624/2001በአንቀጽ 36 ማንኛውም ህንጻ ለአካል ጉዳተኞች በተሽከርካሪ ወንበር መንቀሳቀስ በሚያመች መለኩ እንዲገነባ፣ መጸዳጃቤቶችም ለአጠቃቀም በሚያመች መልኩ መሰራት እንዳለባቸው፤
ደንግጋ ትገኛለች፡፡
ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን ለኛ!!!
ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ሲሳይ ሰማኝ
በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 5 መሠረት የሚከተሉት አካላት የጥብቅና ፍቃድ ሳያስፈልጋቸው የጥብቅና አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡-
1. ስለራሱ ጉዳይ የሚከራከር ሰው፤
2. ያለክፍያ ለትዳር ጓደኛው፤ ለወላጁ፤ ለልጁ፤ ለአያቱ፤ ለእህቱ፤ ለወንድሙ፤ ለትዳር ጓደኛው ወላጆች፤ እንዲሁም ሞግዚት ወይም አሳዳሪ ለሆነለት ሰው የሚከራከር ሰው፣
3. ከሥራው ጋር በተያያዘ ጉዳይ የሚከራከር ዐቃቤ ሕግ፣
4. ሕጋዊ ሰውነት ባለው የንግድ ድርጅት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት፤ ሕዝባዊ ድርጅት፣ የሃይማኖት ተቋም፣ የሙያ ማኅበር፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት ወይም በሌላ አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት በተቋቋመ ድርጅት ተቀጥሮ የተወከለ ሰው፣
5. የመንግስት መሥሪያ ቤትን ወይም የልማት ድርጅትን በሚመለከት የሚከራከር ማንኛውም የመንግስት መሥሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ባለስልጣን ወይም ኃላፊ ወይም በእርሱ የተወከለ ሰው፣ ወይም
6. ማንኛውም የሠራተኛ ማኅበር መሪ ወይም ማህበሩ የሚወክለው ሰው፡፡
ኦምኒኤል (ህዳር 30/03/2014 ዓ.ም)
በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 7 መሠረት ማንኛውም ሰው የጥብቅና ፍቃድ የማይሰጠው፡-
1. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ (1) ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች ያላሟላ ከሆነ፤
(ማንኛውም በጥብቅና ሙያ መሰማራት የሚፈልግ ሰው የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡- ሀ) የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ ለ) እውቅና ካለው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው፣ ሐ) ለመጨረሻ ጊዜ ይሰራበት ከነበረበት ተቋም ድርጅቱን ከመልቀቁ በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በከባድ ዲስፕሊን ጥፋት ያልተቀጣ እና የመልካም ሥነ-ምግባር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ እና መ/በሕግ ሙያ የሚፈለገውን የሥራ ልምድ ያሟላ እና እንደ አስፈላጊነቱ ፍቃድ ለማግኘት የሚሰጠውን የሙያ መግቢያ ፈተና ያለፈ፡፡ )
2. ታስቦ በሚፈጸምና ከሙያ ሥነ-ምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ ጽኑ እስራት በሚያስቀጣ ወንጀል ተከሶ ጥፋተኛ ከተባለ እና አግባብነት ባለው ሕግ ያልተሰየመ ከሆነ፤
3. በሕግ አገልግሎት እንዳይሰማራ በሕግ ወይም በፍርድ ቤት የተከለከለ ከሆነ ነው፡፡
ኦምኒኤል (ህዳር 30/03/2014 ዓ.ም)
በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 22 መሠረት ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት፡-
1. በደንበኛ፣ በፍርድ ቤት ወይም በማንኛውም አግባብ ባለው አካል የጥብቅና ፍቃድን እንዲያሳይ ሲጠየቅ የማሳየት ግዴታ አለበት፤
2. የጥብቅና ፍቃዱን በማንኛውም ሁኔታ ለሌላ ሰው መጠቀሚያ ወይም መገልገያ አሳልፎ መስጠት የለበትም፡፡
ኦምኒኤል (ህዳር 30/03/2014 ዓ.ም)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን አደረጃጀትና አሠራርን ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 71/2008 መሰረት የትራንስፖርት ባለስልጣን የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት አሉት፡-
o በከተማው የብዙሀንና የጭነት ትራንስፖርትን በተመለከተ ተገቢውን መረጃ ማደራጀትና ማሰራጨት፤
o በከተማው የሚንቀሳቀሱ የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት አጠቃላይ የኦፕሬሽን ሥርዓታቸውን በበላይነት መቆጣጠር፣ ፈቃድ መስጠት እንዲሁም ማገድ፤
o የከተማውን የተማከለ የብዙሃን ትራንስፖርት ሥርዓት እንዲፈጠር ማድረግ፣ የስምሪት ድልድል ማዘጋጀት፣ ታሪፍ አጥንቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፣ ሲጸድቅ ለተፈፃሚነቱም መስራት፣ ለአፈጻጸም የሚረዱ የቴክኖሎጂ አውታሮችንም መዘርጋት፤
o የከተማውን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ማለትም ለሕዝብና ለጭነት ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ መናኸሪያዎችን፣ ፌርማታዎችን፣ መጋዘኖችና ዴፖዎችን መገንባትና ማስተዳደር፤
o አጠቃላይ የከተማው የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርትን በተመለከተ መመሪያዎችን ማውጣት፣ ሲፈቀድለትም መተግበር፤
o የከተማውን የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት ማጥናት፣ አማራጭ መፍትሔዎችን በማቅረብ ለአቅርቦት መጣጣም ፕሮግራሞችን በመቅረፅ መስራት፤
o ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሆነ የትራንስፖርት መረጃ አገልግሎት ማደራጀት፣ ማሰራጨት፣ የከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት በቅንጅት እንዲሰሩ እቅድ ማውጣት፤
o የከተማውን የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት መመዘኛ መስፈርቶች፣ ማኑዋሎች ደረጃዎች ማውጣትና ለተፈፃሚነቱ መስራት፤
o ለሚሰጠው አገልጎሎት ክፍያ መሰብሰብ፤
o ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በብዙሃንና በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ኦፕሬተሮች፣ ማሕበራት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች እንዲደራጁና እንዲጠነክሩ ተገቢውን ድጋፍ መስጠት፣ ለከተማው ትራንስፖርት ቅልጥፍናና ደህንነት መስራታቸውን ማረጋገጥ፡፡ ናቸው


ፌናን ተጊበሉ
ታህሳስ 04/2014 ዓ.ም
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1) መሠረት አንድ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሀ) ሠራተኛው የሥራ ሰዓት ለማክበር የማይችልባቸው ሁኔታዎች ተብለው በኅብረት ስምምነት በሥራ ደንብ ወይም በሥራ ውሉ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጭ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ በጠቅላላው ለስምንት ጊዜ የስራ ሰዓት አለማክበር፤
ለ) በአዋጁ ከተመለከቱ እረፍቶች እና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ ለአምስት ቀናት ከስራ መቅረት፤
ሐ) በሥራው ላይ የማታለል ተግባር መፈፀም፤
መ) የራሱን ወይም የሌላ ሰው ብልጽግናን በመሻት በማንኛውም የአሠሪው ንብረት ወይም ገንዘብ አለአግባብ መጠቀም፤
ሠ) ሠራተኛው ሥራውን ለመሥራት ችሎታ እያለው የሥራ ውጤቱ ባለማቋረጥ በኅብረት ስምምነት ወይም በሥራ ደንቡ ወይም በሁለቱ ወገኖች መግባባት ከተወሰነው የምርት ጥራትና መጠን በታች ሲሆን፤
ረ) እንደጥፋቱ ክብደት በሥራው ቦታ አምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆን፤
ሰ) በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና በጥፋቱም ምክንያት ለያዘው ሥራ ብቁ ሆኖ አለመገኘት፤
ሸ) በአሠሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ሥራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤
በ) በሠራተኛው ላይ ከሰላሳ ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የእሥራት ፍርድ ተወስኖበት ከሥራ ሲቀር፤
ተ) ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ለማቋረጥ ያስችላሉ ተብለው በኅብረት ስምምነት የተወሰኑ ሌሎች ጥፋቶችን መፈፀም፡፡ ናቸው

ፌናን ተጊበሉ
ታህሳስ 11/2014 ዓ.ም
የነጻ የጥብቅና ፈቃድ አገልግሎት
የነጻ የጥብቅና ፈቃድ አገልግሎት ማለት፡-
• የመክፈል አቅም ለሌላቸዉ ሰዎች
• ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ ለሲቪክ ማሕበራት፤ እና ለማሕበረሰብ ተቋማት
• ፍርድ ቤት የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ ለሚጠየቅላቸዉ ሰዎች
• ሕግን፤ የሕግ ሙያን እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ለሚሰሩ ኮሚቴዎች እና ድርጅቶች እና በሌሎች አግባብነት ባላቸዉ ሕጎች ለተመለከቱ ሰዎች በአነስተና ክፍያ ወይም ያለምንም ክፍያ በጠበቃ ወይም በጥብቅና ድርጅት የሚሰጥ የጥብቅና አገልግሎት ነዉ
1249/2013 አን 2(11)፤ 31(1)
ህድአት ጌታቸዉ ታህሳስ/2014 ዓ.ም
ነጻ ጥብቅና አገልግሎት ስለመምራት
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ (ፍትህ ሚኒስቴር) እያንዳንዱ ጠበቃ በዓመት መስጠት ከሚጠበቅበት የነጻ የጥብቅና አገልግሎት መጠን ሳያልፍ በነጻ የጥብቅና አገልግሎት መጠን ሳያልፍ በነጻ የጥብቅና አገልግሎት ሊስተናገዱ የሚገባቸዉን ጉዳዮች እያጣራ ለጠበቆች ይመራል የመራለትንም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት በዚህ አዋጅ እና በጠበቆች ሥነ-ምግባር ደንብ መሠረት መፈጸሙን መቆጣጠር እና መከታተል አለበት፡፡ የተመራለት ጠበቃም የነጻ ጥብቅና አገልግሎት ተቀብሎ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡
ጠበቃዉ በራሱ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎ መሰጠት ያለበት ሰዉ አግኝቶ አገልግሎቱን በነጻ ሰጠ በሆነ ጊዜ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ (ፍትህ ሚኒስቴር) የአገልግሎቱን ትክክለኛነትና አዉነተኛነት አረጋግጦ እዉቅና ሊሰጠዉ ይችላል፡፡
1249/2013 አን 32
ህድአት ጌታቸዉ ታህሳስ/2014 ዓ.ም
በጠበቆች ወይም የጥብቅና ድርጅት የሚፈጸሙ ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶች እና የሚያስከትሏቸዉ ተጠያቂነቶች
1. የጥብቅና ፈቃድን ለደንበኛ፤ ለፍርድ ቤት ወይም ለሚመለከተዉ አካል እንዲያሳይ በተጠየቀ ጊዜ ለማሳየት ፈቃደኛ ያለመሆን
2. ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታና የደረሰበትን ደረጃ በደንበናዉ ሲጠየቅ በአግባቡ ያለማሳወቅ ደንበኛን ማመናጨቅ ወይም ክብሩን መንካት
3. ያለበቂና አሳማኝ ምክንያት በቀጠሮ ቀን መዘግየት እና ፍርድ ቤት ያለመገኘት
4. ለጠበቆች ማኅበር መክፈል የሚጠበቅበትን ክፍያ ወይም መዋጮ በተደጋጋሚ እና በወቅቱ ያለመክፈል
5. የጥብቅና ፍቃድን በወቅቱ አለማሳደስ
6. ባልታደሰ የጥብቅና ፍቃድ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት
7. የጥብቅና ፍቃዱን ለጥብቅና ፍቃድ ሰጪው ተቋም ሳይመልስ በሌላ ቋሚ ሥራ ተሰማርቶ መገኘት
በተራ ቁጥር 1 እና 2 ከተደነገጉት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ጠበቃ ዌም የጥብቅና ድርጅት የቃል ማስጠንቀቂያ በዲስፕሊን በዲስፕሊን ጉባዔው ይሰጠዋል፤ ለሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ጥፋት ከፈጸመ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል
በተራ ቁጥር 3 እና 4 የተደነጉትን ጥፋቶች የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡
በተራ ቁጥር 5--7 የተደነገጉትን ጥፋቶች የፈጸመ ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት እንደነገሩ ሁኔታ ከብር አምስት ሺህ እስከ ብር ሰባት ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
1249/2013 አን 83 እና 84
ህድአት ጌታቸዉ ታህሳስ/2014 ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ ፡-
ግለሰቦች ከሕግ ወይም ከውል በመነጨ ግንኙነታቸው መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ወይም የፍርድ ቤት ውሣኔ የሚያስፈልገው ጉዳይ ቢያጋጥማቸውና በዚሁ መሠረትም ፍ/ቤቱ ቢወስን ለውሣኔው ማስፈጸሚያ የሚሆን ንብረት ካለ ይህው ንብረት ተከብሮ የሚያዝና በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት የሚወስድ ሲሆን ሆኖም ግን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 404 ተከብረው ስለማይያዙና በአፈጻጸም ወቅት ስለማይወሰዱ ንብረቶች እንመልከት፡-
መልካም ምንባብ፡-
- ለፍርድ ባለዕዳውና ለቤተሰቡ የዕለት አገልግሎት የሚጠቅሙ ልብሶች ፣ የምግብ ማብሰያ፣አልጋ፣
- ለዕለት ሙያ ሥራና ለንግድ ሥራ ማከናወኛ ተገቢ የሆነ ዕቃ፣
- የፍርድ ባለዕዳው ገበሬ ወይም በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ከሆነ የዘር እሕልን ጨምሮ ለግብርና ሥራ አገልግሎት በቂ የሆነው፣
- ለራሱና ለቤተሰቡ ለሦስት ወራት መተዳደሪያ ገንዘብና ለዕለት ምግብ የሚሆን ፣
- ለጡረታ የሚከፈል ገንዘብ፣
- በባሕር ሕግ በቁጥር 121 የተመለከተው ድንጋጌ (የመርከበኛ ደመወዝ ከ1/4ኛ በላይ አይያዝም )
እንደተጠበቀ ሆኖ ከወር ደመወዝ ላይ ከ1/3ኛ በላይ ወይም በቀን ከሁለት ብር የማይበልጥ ሆኖ ሌላ ገቢ የሌለው እንደሆነ ፣
- በሕግ የተወሰነ እንደሆነ፣
- እንደዚሁም በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚው ችሎት የሰ/መ/ቁጥር 10489 እና 25019 በሆኑ አስገዳጅ ውሣኔዎች በበጀት የሚተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤት የፍርድ ባለዕዳ ሆኖ ሲገኝ በበጀት የተያዘውን እና የሠራተኛ ደመወዝን የሚያካትተውን ገንዘብ ከባንክ ወጪ ሆኖ ለአፈጻጸም እንዲውል ማድረግ እንደማይቻልም ግንዛቤ እንያዝበት፡፡
መልካም ቀን
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!!!
ታህሳስ 13 2014ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ