የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
በቤተሰብ ሕጋችን አንቀጽ 16 መሠረት በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነ ጊዜን በተመለከተ የሚከተሉት ነጥቦች ተቀምጠዋል፡-
1. አንዲት ሴት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ አንድ መቶ ሰማንያ ቀን ካላለፈ በስተቀር እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችልም፡፡
2. ከላይ የተደነገገው ቢኖርም፣ ሴቲቱ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ አንድ መቶ ሰማንያ ቀን ሳይሞላ
ሀ) የወለደች እንደሆነ፣ ወይም
ለ) ጋብቻ የምትፈጽመው ከቀድሞ ባሏ ጋር የሆነ እንደሆነ፣ ወይም
ሐ) እርጉዝ አለመሆኗ በሕክምና የተረጋገጠ እንደሆነ፣ ወይም
መ) በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነውን ጊዜ እንዳትጠብቅ ፍርድ ቤት የወሰነ እንደሆነ በብቸኝነት ለመኖር ስለተወሰነው ጊዜ የተደነገገው ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (ኦምኒኤል)
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ሕጋችን ቍ 17 መሠረት የወንጀል ክስ ወይም የክስ አቤቱታ መብት ለሌለው ባለሥልጣን ማቅረብን በተመለከተ የሚከተለው ነጥብ ሰፍሯል፡-
የወንጀሉ ክስ ወይም የክሱ አቤቱታ ለፖሊስ ወይም ለዐቃቤ ሕግ መቅረቡ ቀርቶ ለአንድ ሰው ወይም ለሌላ ባለሥልጣን ወይም ይህንኑ ጉዳይ ለመቀበል መብት ለሌለው ለፖሊሲ ባለሥልጣን ወይም ለዐቃቤ ሕግ የቀረበ እንደሆነ ይኸው ሰው ባለሥልጣን ወይም ዐቃቤ ሕጉ ሳይዘገይ በቶሎ ጉዳዩ ለሚመለከተው ሥልጣን ላለው ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ ይህንኑ ክስ ወይም የክስ አቤቱታ መላክ አለበት፡፡
መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (ኦምኒኤል)
በፍትሐብሔር ሕጋችን ቊ.4 መሠረት የሚኖር ወይም የማይኖር ልጅን በተመለከተ የሚከተለው ነጥብ ሰፍሯል፡-
1. አንድ ልጅ ተወልዶ 48 ሰዓት በሕይወት ከቈየ በሕይወት እንደ ኖረ ሆኖ ይቈጠራል፡፡
2. አንድ ልጅ ተወልዶ በሕይወት የቈየው ከ48 ሰዓት ያነሰ ጊዜ የሆነ እንደ ሆነ በሕይወት እንዳልኖረ ሆኖ ይቈጠራል፡፡
3. የልጁን መሞት ያስከተለው፤ በተፈጥሮው ጒድለት ምክንያት ያልሆነ ሌላ ሁኔታ መሆኑን ለማስረዳት የተቻለ እንደሆነ ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተውን አገማመት ቀሪ ለማድረግ ይቻላል፡፡
መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (ኦምኒኤል)
የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አላማና ግቦች
የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ ቀዳሚ አላማ
“ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፣ የህዝቦቹንና የነዋሪዎቹን ሰላም፣ ደህንነት፣ ስርአት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው”።
የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ ዋንኛ ግብ
• ወንጀል የሆኑ ድርጊቶችን ወንጀል ካልሆኑት ለይቶ በቅድሚያ በማሳወቅ፤
• ወንጀል የሆኑ ድርጊቶችን በፈጸሙ ወንጀለኞች ላይ የሚጣሉ ቅጣቶችን በቅድሚያ በማሳወቅና በማስጠንቀቅ፤
• ማስጠንቀቂያውን ችላ ብለው ወንጀል በሚፈጽሙ ወንጀለኞች ላይ ተመጣጣኝ ቅጣት በመጣል ሌላ ወንጀል ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፣ እንዲታረሙና ማስተማሪያ እንዲሆኑ በማድረግ
ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ነው።


ፋሲካ አጌና (ዐቃቤ ህግ)
ሚያዝያ 2014ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ!
የመንግስት መ/ቤቶችን ማህተሞች ወደ ሀሰተኛነት መለወጥ ወይም በማህተሞቹ ያለአግባብ መገልገል በጽኑ እስራት የሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት መሆኑን ያውቃሉ?
በወንጀል ህግ አንቀጽ 363 መሰረት፥-
1. ማንም ሰው፡-
ሀ) ለመንግስት ስራ ጉዳይ ብቻ በሚታተም የመንግስት ወይም ከመንግስት አካላት በአንዱ ማህተም ወይም ወደ ሀሰተኛነት በተለወጠ ወይም መስሎ በተሰራ ማህተም የተገለገለ እንደሆነ፤ ወይም
ለ) በእውነተኛው ማህተም ያላግባብ የሰራበት እንደሆነ
ከሶስት ዓመት እስከ አስር ዓመት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ይቀጣል።
2. ይህ የወንጀል ድርጊት በሀገር ጥቅም ወይም መብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ ከአምስት ዓመት እስከ ሀያ ዓመት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ይቀጣል።

በቦሌ ክ/ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት በህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

ፋሲካ አጌና (ዐቃቤ ህግ)
ሚያዝያ 2014ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ 1997 ዓ.ም
በሠው የግል ነጻነት ላይ የሚፈጸ ወንጃል አንቀጽ 580
ዛቻ-፡ ማንም ሠው በሌላ ሠው ላይ ድንጋጤን ወይም ፍርሃትን በሚቀሰቅስ ሁኔታ ከባድ አደጋ ወይም ጉዳት የሚያደርሱበት መሆኑን በመግለፅ የአስፈራረው እንደሆነ የግል አቤቱታ ሲቀርብበት ከአምስት መቶ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል ፡፡
የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው ለወደፊቱ በመልካም ጠበይ እንደሚመራ የማረጋገጫ ቃል እንዲገባ በቂ የሆነ ዋስ እንዲጠራ/አንቀፅ/ከማዘዝ የሚያግድ አይደለም፡፡

አሊ ሣፊ(አቃቤ-ሕግ)
ሚያዝያ 2014ዓ.ም
የኢትዮጵ የ 1997 ዓ.ም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 560
የእጅ እልፈት
1. ማንኛውም ሠው የአካል ጉዳትን ወይም የጤንነት ጉድለትን ሳያደርስ በሌላሰው ላይ የዕጅ እልፈት ወይም የመጋፋት ድርጊት የፈጸመ እንደሆነ፣
የግል አቤቱታ ሲቀርብበት ከሶስት መቶ ብር በማይበልጥ መቀጮ ፣ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን ከሦስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት የቀጣል ፡፡
ቀላል የሆኑ ሰንበሮች ፣የደም መቋጠር ምልክቶች ወይም በቶሎ የሚልፍ ሕመም ወይም ስቃይ እንደአካል ጉዳት ወይም እንደጤና ጉድለት አይቆጠሩም ፡፡
2. በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀፅ (1)ከአመለከተው ውጭ የሆኑ ጥፋቶች በዚህ ሕግ ሰለደንብ መተላለፍ በአንቀፅ 840 በተደነገገው መሠረት ያስቀጠሉ፡፡
3. ተበዳይ የተፈጸመበትን የእጅ እልፈት ወዲያውኑ በእጅ እልፈት የመለሠ አንደሆነ ፍ/ቤቱ ሌላ ቅጣት በመወሠን ፋንታ እንደአስፈላጊነቱ አንዱን ወይም ሁለቱንም ወገኖች በመገሰፅ ወይም በማስጠንቀቅ ልናልፋቸው እንችላለን፡፡

አሊ ሣፊ(አቃቤ-ሕግ)
ሚያዝያ 2014ዓ.ም
በፌደራል የአስተዳደር ስነ-ስርአት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስጣጥና አፈፃፀም ስነ-ስርአት ላይ የተደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
ሥራ ፈትነት እንደሚያስቀጣ የውቃሉ ?
አዋጅ ቁጥር 414/1996 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 477 አደገኛ የሆነ ስራ ፈትነት
1. ማንም ሰው ሙሉ አካል እያለው የተወሰነ መኖሪያ ወይም መደበኛ ስራ (ለኑሮው) አስፈላጊ የሆነ መደበኛ ወይም ጉልህ የሆነ የገቢ ምንጭ የሌለው ሆኖ የስራ ፈትነትን ወይም የመጥፎ አኗኗር አመልን ገንዘብ ለማግኘት ሲል ነቀፌታ ያለበትን መጥፎ ዘዴ አስቦ ልማድ አድርጎ የያዘና በዚሁ ኑሮው ለሕዝብ ደሕንነትና ጸጥታ አደገኛ የሆነ እንደሆነ፡፡
የግል ነፃነትን ከመቀነስ ጋር በሚወሰን የግዴታ ሥራ /አንቀጽ 104/ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እሥራት ይቀጣል ፡፡
2. ጥፋተኛው የጦር መሣርያ ወይም በጠባያቸው ወንጀልን ለመፈጸም የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ይዞ የተገኘ እንደሆነ በቀላል እሥራት የሚቀጣ ሲሆን ዛቻን ወይም የማሥገደድ ድርጊትን ወይም በግለሠቦች ላይ የኃይል ድርጊት ወይም የእጅ እልፈት የፈጸመ እንደሆነ ስለወንጀሎች መደራረብ የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
3. ሁኔታዎች ሲመዛዘኑ ተገቢሆኖ በታየ ጊዜ ፍ/ቤቱ የነፃነት መቀነስ የጥንቃቄ እርምጃዎችን /አንቀጽ 144/147/ ከዋናው ቅጣት ጋር አጣምሮ ለመወሰን ይችላል፡፡


አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ሚያዚያ 12/2014 ዓ.ም
ቸር ይግጠመን!!
በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813-2006 ዙሪያ የተዘጋጀ በራሪ ጽሁፍ