ሰላም ለእርስዎ ይሁን!
እርስዎ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በመጠቆም የዜግነት ግዴታዎትን ከመወጣት ባለፈ ጠቀም ያለ ማበረታቻ ሊያገኙ እንደሚችሉ ያውቃሉ? ይከተሉኝማ!
በሀገራችን የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ በህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3 እንደሰፈረው የህዝብና የመንግስት ሀብት ሲሆን መሸጥ ወይም መለወጥ እንደማይቻል ተደንግጎ ሳለ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ግን ሕገ-ወጥ የመሬት ይዞታና ግንባታ፣ እና የመሬት ወረራን ጨምሮ መሬት ነክ የሌብነትና የማጭበርበር ወንጀል ተስፋፍቶ ይገኛል።
በመሆኑም በከተማዋ እየተስፋፋ የመጣውን ህገ-ወጥነት ለማስቆምና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በህዝብ ተሳትፎ ወንጀሉን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር መከናወን እንዳለበት በመታመኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕገ-ወጥነትን ለሚጠቁሙ መረጃ አቅራቢዎች ስለሚሰጥ ማበረታቻ የሚደነግግ ደንብ ቁጥር 121/2013 አውጥቷል።
በቀደመው ልጥፋችን የጥቆማ አቀራረብ ስነ-ስርአቱን በአጭሩ አጋርተንዎት እንደነበር ይታወቃል። ለዛሬም ከዚህ ደንብ ላይ 3 ጥቆማ የሚቀርብባቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና የሚያስገኙትን ማበረታቻ እናጋራዎታለን፤ ሌሎቹን በቀጣይ ልጥፎቻችንን የምንመለስባቸው ይሆናል።
ማንኛውም ሰው፥-
1. ወደ መሬት ባንክ ቢገባም ባይገባም አግባብ ያለው አካል ሳይፈቅድ ማንኛውም የከተማ መሬት መያዙን ወይም መወረሩን ከጠቆመ በተጠቆመው ይዞታ ልኬት ስፋት ልክ በወቅቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ማበረታቻ ያገኛል፤
2. አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ በህጋዊነት ከተያዘ ይዞታ ጎን፣ (ከፊት ለፊቱ ወይም ከበስተ-ሗላው) ያለ የከተማ ቦታ ተስፋፍቶ መከለሉን፣ ጥቅም ላይ መዋሉን፣ መታጠሩን ወይም ከአዋሳኝ ይዞታ ጋር መቀላቀሉን ከጠቆመ ከተስፋፋው ይዞታ ልኬት ስፋት ልክ በወቅቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ማበረታቻ ያገኛል፤
3. በአካባቢ ልማት ፕላን መሰረት ለመንገድ አውታር፣ ለማህበራዊ ተቋማት፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ስፍራዎች፣ ለፓርክ፣ ለመንግስት ይዞታዎች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ተለይተው የተቀመጡ ባዶ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ መያዛቸውን ከጠቆመ ከተያዘው የይዞታ ልኬት ስፋት ልክ በወቅቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ማበረታቻ ያገኛል፤
ሰኔ 15 2014 ኣ.ም

👍2
ይህን ያውቁ ኖሯል?
ከጦር መሣሪያ በተጨማሪ በአወጁ ቁጥር 1177/2012 ዓ.ም በወጣው በአንቀፅ 2(13) መሠረት፤
ጉዳት አድራሽ ዕቃዎች ማለት
በስለታማነተቸው ምክንያት ወይም የኤሌትሪክ ሀይል በመጠቀም ወይም መርዛማ በመሆናቸው በሠው አካልና በህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ የሚችሉ እንደ ሳንዳ፣ገጀራ፣ሜንጫ፣ጦር፣ቀስት፣ጎራዴ፣ሴንጥ እና መሰል መሣሪያዎችን ያጠቃልላል፡፡
ቸር ይግጠመን!
አሊ ሣፊ(አቃቤ ሕግ)
ሓምሌ 28/2014ዓ.ም

👍1
ሰላም!
ለወረዳ ፎካል ፐርሰኖች:
ሀሙስ በ19/01/2015 በማስረጃ ሕግ ላይ ልንሰጥ የነበረውን ስልጠና በወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ መገደዳችንን እያሳወቅን ይህ ለሚፈጥረው ችግር አስቀድመን ይቅርታ እንጠይቃለን። ስልጠናው መቼና የት እንደሚካሄድ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።
(የቦሌ ክ/ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤት)

Forwarded from የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት (fasika aggena)
ሰላም!
ለወረዳ ፎካል ፐርሰኖች:
ሀሙስ በ19/01/2015 በማስረጃ ሕግ ላይ ልንሰጥ የነበረውን ስልጠና በወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ መገደዳችንን እያሳወቅን ይህ ለሚፈጥረው ችግር አስቀድመን ይቅርታ እንጠይቃለን። ስልጠናው መቼና የት እንደሚካሄድ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።
(የቦሌ ክ/ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤት)
ለወረዳ ፎካል ፐርሰኖች:
ሀሙስ በ19/01/2015 በማስረጃ ሕግ ላይ ልንሰጥ የነበረውን ስልጠና በወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ መገደዳችንን እያሳወቅን ይህ ለሚፈጥረው ችግር አስቀድመን ይቅርታ እንጠይቃለን። ስልጠናው መቼና የት እንደሚካሄድ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።
(የቦሌ ክ/ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤት)
ሰላም!
አንዳንድ ቃላትን በተደጋጋሚ ስለምንጠቀምባቸው ብቻ ትርጓሜያቸውን የምናውቅ የሚመስለን ስንቶቻችን ነን? እስኪ ከዚህ በታች በደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 1 “ደን” ለሚለው ቃል የተሰጠውን ትርጓሜ እንመልከት!
“ደን” ማለት በደን መሬት፣ በመንገዶች ዳርቻ፣ በወንዝ ዳርቻ፣ በእርሻና የግጦሽ መሬቶች ውስጥና በዙሪያቸው እንዲሁም በመኖሪያ አካባቢዎችና ፓርኮች ውስጥ በተፈጥሮ የበቀሉ ወይም ተተክለው ወይም በሌላ ዘዴ የለሙ የዛፎችና የዕፅዋቶች እንዲሁም ሌሎች ብዝሃ-ሕይወቶች ክምችት ነው።
ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ አንቀጽ ንኡሳን አንቀጾች 5፣ 6፣ 7፣ 8መሰረት ከባለቤትነት አንጻር ደን በ4 የሚከፈል ሲሆን እነርሱም፥-
“የመንግሥት ደን” ማለት በፌደራል እና በክልል መንግሥት ሥር የሚገኝ ማንኛውም ፍጹም ጥብቅ፣ ጥብቅ ወይም ምርት ሰጪ ደን ነው፤
“የግል ደን” ማለት የመንግስት እና የማህበረሰብ ያልሆነ በማንኛውም የግልና የተቋማት ይዞታ ላይ የሚገኝ ደን ነው፤
“የማሕበረሰብ ደን” ማለት የአንድ አካባቢ ህብረተሰብ የግል ወይም የወል ይዞታቸውን በጋራ በሚያወጡት ዕቅድ እና ሕገ-ደንብ መሠረት የለማ፣ የተጠበቀ፣ በጥቅም ላይ የሚውል እና የሚተዳደር ደን ነው፤
“የማሕበራት ደን” ማለት የደን አልሚዎች በማሕበር በመደራጀት የሚያለሙት፣ የሚጠብቁት፣ የሚጠቀሙበት እና የሚያስተዳድሩት ደን ነው፤
መስከረም 18 ቀን 2015 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት አቃቤ-ሕግ)

ስለደን ምንነትና አይነቶች የጀመርነውን ወግ ለመቀጠል ተመልሰናል!
በቀደመው መልእክታችን የደን ምንነትና ከባለቤትነት አኳያ የደን አይነቶችን ለመመልከት ሞክረናል። ዛሬ ደግሞ ደን ከሚሰጠው ጥቅምና ሊደረግለት ከሚገባው ጥበቃ አንጻር በደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀጽ 2 ንኡሳን አንቀጾች 11, 12, 13, 14 እና 15 የተዘረዘሩትን ልዩ ልዩ የደን አይነቶች እንመለከታለን!
“ጥብቅ ደን” ማለት ለተለያዩ የሥርዓተ ምህዳር ግልጋሎት የሚውል ደን ሲሆን በሚመለከተው አካል በሚዘጋጅለት የደን ማኔጅመንት ዕቅድ መሠረት የደኑን ዘላቂ ሥርዓተምህዳራዊ ዕሴቶች በማይጎዳ መልኩ በጥቅም ላይ እንዲውል የተለየ ደን ነው፤
“ፍፁም ጥብቅ ደን” ማለት ደኑን ከአደጋ ለመጠበቅ ካልሆነ በስተቀር ከማንኛውም የሰውና የቤት እንስሳት ጣልቃ ገብነት የተጠበቀ ደን ሲሆን ለብዝሀ ህይወት ጥበቃ፣ ለታሪካዊና ለምርምር የተለየ ደን ነው፤
“ምርት ሰጪ ደን” ማለት በዋናነት ለኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች የለማ ደን ነው፤
“ሰው ሰራሽ ደን” ማለት በሰው አማካኝነት የለማ ደን ነው፤
“የተፈጥሮ ደን” ማለት በአብዛኛው በተፈጥሮ የበቀሉ ዛፎች፣ ቁጥቋጦና ሌሎች የእንጨትነት ባሀሪ ያላቸውና የሌላቸው ተክሎችና ዕፅዋቶች ያሉበት ደን ነው፤
“ጥምር እርሻ ደን” ማለት ሰብልንና ዛፍን ወይም የእንስሳት መኖንና ዛፍን ወይም ሶስቱንም በአንድ መሬት ላይ በተመሳሳይ ጊዜ ወይም በማፈራረቅ በቅንጅት በማልማት የሚከናወን የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ስልት በመጠቀም የሚለማ ወይም የለማ ደን ነው፤
ደን ህይወት ነው!
መስከረም 20 ቀን 2015 ኣ.ም

ከኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆችና አላማዎች ውስጥ የኢኮኖሚ ነክ አላማዎች፥
አንቀፅ 89
ኢኮኖሚ ነክ አላማዎች
መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ የተጠራቀመ እውቀትና ሀብት ተጠቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት ፡፡
መንግስት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግና በሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት ፡፡
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጎጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ፡፡
በእድገት ወደኋላ ለቀሩ ብሔሮች፣ብሔረ ሰቦች፣ሕዝቦች መንግስት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
መንግስት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት ፡፡
የሀገር ልማት ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች በሚዘጋጁበት ወቅት መንግስት ሕዝቡን በየደረጃው ማሳተፍ አለበት፡፡ የሕዝብንም የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ አለበት፡፡
መንግስት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ለልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት፡፡
መንግስት የሰራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት፡፡
አቃቤ ሕግ አሊ ሳፊ
ጥቅምት 04/2015ዓ.ም

ይህንን ያውቁ ኖሯል?
በየጊዜው በምናደርገው የግብይት እንቅስቃሴ ውስጥ የውል ስምምነት እያደረግን ቢሆንም በፍትሀ-ብሔር ሕጎችን ለውል መመስረት አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ማወቅ አለብን ፡፡
1/ የተዋዋይ ወገኖች ችሎታ፡- (የተፈጥሮ ሠው ወይም የህግ የሰውነት መብት የተሠጠው አካል ) በህግ ፊት ውጤት ያለውን ተግባር ለማከናወን ያለውን ብቃት የሚመለከት ነው።
2/ የተዋዋይ ወገኖች ነጻ ፍቃድ፡- አንድ ውል በሕግ ፊት የሚፀና እንደሆነ ተዋዋይ ወገኖች ነፃ ፍቃዳቸውን የገለጹበት መሆን አለበት።
3/ የውለታው ጉዳይ ፡- ለውሉ መመስረት ምክንያት የሆነ ነገር ወይም ጉዳይ ሕጋዊ፣ ሊፈፀም የሚችል እና ለሞራል ተቃራኒ ያልሆነ መሆን ይገባዋል።
4/ የውሉ አቀራረፅ (ፎርም) ከሌሎች ውሎች በተለዬ ሁኔታ ሕጉ ልዩ አቀራረፅ (ፎርም)የሚጠይቅ ከሆነ በዛው መሠረት ብቻ መሆን አለበት።
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ መሰረታዊ ጉዳዮች በፍትሐ-ብሔር ሕግ አንቀፅ 1678 ላይ የተገለፁ ሲሆን በዚሁ መሠረት አውቀን መጠቀም አለብን።
ጥቅምት 17 ቀን 2015 ኣ.ም
አሊ ሳፊ የሕ/ስ/ም/መ አቃቤ ሕግ

Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከክ/ከተማው የክርክር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር መስከረም 30 ቀን 2015 ኣ.ም በማስረጃ ሕግና ከማስረጃ ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸውን አስመልክቶ ስልጠና የሰጠ ሲሆን በስልጠናው ከ300 በላይ ለሆኑ የወረዳ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች/መሪዎች ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎችን አጋራናችሁ።