የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰአት በ14ኛ ዙር ኮንደሚኒየም የደረሳቸው የ 11ዱም ክ/ከተማ ነዋሪዎች በቦሌ ክ/ከተማ ውል እየተዋዋሉ ይገኛሉ። ይህንም እድል በመጠቀም ስለ ውክልና ህግ የተወሠነ ለማለት በማሰብ ብሮሸር ስንበትን የሚያሳይ ምስል።
👍1
" የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ #እንዳይጨምሩ ተወስኗል "

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ 2ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ፦

1. የመኖሪያ ቤቶችን በመንግስትና የግል አጋርነት በ70/30 አሰራር መቶ ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀውን 35 ሄክታር መሬት ላይ ተወያይቶ ወስኗል።

2. ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና የስራ እድል የሚፈጥሩ የ373 ፕሮጀክቶች የመሬት ጥያቄ እነሱም ፦
2.1. ለኢንዱስትሪ ልማት
2.2 ሆቴሎችና ሞሎች ፣
2.3 የሀይማኖት ተቋማት ፣
2.4 ቀደም ሲል በካቢኔ ተወስነው የመሬት ለውጥ የቀረበባቸው ቦታዎች ፣ ለተለያዩ የግንባታ ግባዓት ማስቀመጫ የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠቀሚያ ቦታዎች ናቸው።

3. ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ መረጋጋት የዋጋ መናር መነሻ በማድረግ በአስቸኳይ ምርት ወደ ከተማ እንዲገባና እንዲሰራጭ ግብረ ኃይል አቋቁሟል።

4. ለተማሪዎች ምገባ የሚያቀርቡ እናቶች በአሁኑ ዋጋ ማቅረብ መቸገራቸውን መነሻ በማድረግ ለተማሪዎች ምገባ በወር 54,000,000 ብር (ሀምሳ አራት ሚሊየን) በዓመት 540,000,000 ብር (አምስት መቶ አርባ ሚሊየን) ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፤ ይህ ማለት ለአንድ ተማሪ በቀን ሃያ ብር የነበረው ወደ የሀያ ሶስት ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

5. ከወቅቱ ዋጋ መናር እና የገበያ አለመረጋጋት ጋራ ተያይዞ የነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ እንዳይጨምሩ ተውስኗል።

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
በቀን 21/06/2015 እና 22/06/2015 ዓ.ም ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ስለሚያወሳው አዋጅ ቁጥር 1183/2012 እና ስለ በሰዎች መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ጽንሰ ሀሳብ እና ገዢ ህጎቹ ዙርያ ለቦሌ ክ/ከተማ የምክር ቤት አባላት የተሰጠ ስልጠና የሚያሳይ ምስል። በነበረው ስልጠናም ብዙ ሀሳቦች ከተሰብሳቢው ተነስቷል። በተለይ ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔ አሠጣጥ ላይ በተሰጠው ስልጠና መሠረት ብዛት ያላቸው ሀሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን በዚህ ዙሪያም ከምክር ቤት አባላቱ ምን እንደሚጠበቅ አትኩሮት በመሥጠት ምላሽ ከአሰልጣኝ ተሠጥቷል።
145.2015 የመኖሪያ ቤት-.pdf
793.9 KB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ቀደም እንደሚታወቀው የቤት ኪራይ ክፍያ ላይ  ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ሲል ለ 90 ቀናት ማራዘሙ ይታወቃል። ይህንም መሠረት በማድረግ ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 145/2015 ከየካቲት 19/2015 ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ያጸደቀውን ለግንዛቤ እንዲውል እነሆ ብለናል። መልካም ቀን።