Forwarded from የህግ ማዕበል/ጠበቃ ውብአለም መስፍን (Wubalem Mesfin)
220042-3.pdf
916.8 KB
የካርታ ይምከንልኝ ጥያቄ መጀመሪያ በአስተዳደር አካል በአዋጅ ቁጥር 1183/12 መሠረት መታየት ያለበት እንጂ ለፍርድ ቤት ቀጥታ የሚቀርብ አይደለም። በመጨረሻው የአስተዳደር ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ሰው የተሰጠው ውሳኔ እንዲከለስለት ቅሬታውን ለከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረብ እንደሚችል ባልታተመ የሰበር ውሳኔ ተሰጥቷል።
👍1
Forwarded from የህግ ማዕበል/ጠበቃ ውብአለም መስፍን (Wubalem Mesfin)
የኑዛዜ አይነቶች
በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ
1. በተናዛዡ እየተነገረ በሌላ ማንኛውም ሰው የሚፃፍ ወይም በራሱ የሚፃፍ
2. በ 4 ምስክሮች ወይም ኑዛዜው ዳኛ ወይም በሌላ ስልጣን በተሠጠው ሰው ፊት በቢሮአቸው ውስጥ የተደረገ ከሆነ 2 ምስክር
3. ምስክሮቹ በህግ የተፈቀደ እድሜ እና የህግ ክልከላ የሌለባቸው መሆን። ማለትም አካለ መጠን የደረሱ እንዲሁም በጤና እክል ምክንያት ብቁ አይደሉም ተብሎ በህግ ክልከላ ያልተጣለባቸው። በተጨማሪም አካለ መጠን ሆነ ክልከላ ያልተደረገባቸው ቢሆንም እንኳን የተፃፈውን ኑዛዜ መረዳት የሚችሉ መሆን አለባቸው። ይሄም የተፃፈበትን ቋንቋ ማወቅ መስማት ወይም ማንበብን ያካትታል።
4. በተናዛዡ እና ምስክሮች ፊት የተነበበ ይህም እንደተደረገ እና ኑዛዜው የተፃፈበትን ቀን የሚያሳይ መሆን። ማለትም ኑዛዜው በግልፅ ባሉበት መነበቡን ኑዛዜው ላይ እስከተፃፈበት ቀን ጨምሮ መገለፅ አለበት።
5. ኑዛዜውም ወዲያውኑ መፈረም አለበት።
እነዚህ መስፈርቶች መሟላት እንዳለባቸው የፍትሐብሔር ህግ ከአንቀፅ 881 - 883 ይደነግጋል። ሰበር ችሎትም በቅፅ 8 መ/ቁጥር 36777 እነዚህን መስፈርቶች ዘርዝሮ ውሳኔ ሰቷል። በቅፅ 2 መ/ቁ 17429 ላይም ኑዛዜው ተናዛዡ እና ምስክሮች ፊት ስለመነበቡ ካመላከተ በቂ ስለመሆኑና "ተነቧል" የሚለው ቃል አልተገለፀም በሚል ኑዛዜውን ፈራሽ ማድረግ እንደማይቻል አስገዳጅ ውሳኔ ሰቷል።
በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ
1. ኑዛዜ መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሙሉ በሙሉ በተናዛዡ መፃፍ አለበት። ፅሁፉ በመፃፊያ መሳሪያ የተፃፈ ከሆነ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ በመሳሪያው መፃፋ በእጅ ፅሁፉ መገለፅ አለበት። ተናዛዡም የሚፅፍበትን ቋንቋ የማይረዳውና ቃላቶቹ ምንን እንደሚወክሉ የማያቅ ከሆነ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል።
2. እያንዳንዱ ገፅ ላይ የተናዛዡ ፊርማና ቀን መፃፍ አለበት
የቃል ኑዛዜ
1. ሟች የመሞቻው ግዜ ተሰምቶት ለሁለት አካለ መጠን የደረሱና በህግ ክልከላ ያልተደረገባቸው ሰዎች የሚሰጠው የመጨረሻ ፈቃድ ነው።
2. የቃል ኑዛዜ የቀብር ሁኔታን፣ ለእያንዳንዱ ከ500 ብር ያልበለጠ የኑዛዜ ስጦታን እና የልጅ አስተዳዳሪ ወይም ሞግዚት በተመለከተ የሚደረግ ነው። በዚህም በቃል ኑዛዜ ዋጋቸው ከፍ ያሉ ንብረቶችን ማስተላለፍ አይቻልም። ከተፈቀደው በላይ የተደረገም የቃል ኑዛዜ ትርፋ እንዲቀነስ ይደረጋል።
ማንኛውም ኑዛዜ ከላይ የተዘረዘሩትን ፎርማሊቲዎች መከተል ያለበት ሲሆን መስፈርቱን ሳያሟላ ከቀረ ፈራሽ ይሆናል። ኑዛዜም በማያሻማ መልኩ መፍረሱን የሚያሳይ ሰነድ በተናዛዡ ተፅፎ እያለ ኑዛዜው በተደረገበት ፎርማሊቲ መሠረት መፍረሱም አልተደረገም በሚል መፍረሱን ውድቅ ማድረግ አይቻልም ሲልም ሰበር ችሎት በመ/ቁጥር 96364 ውሳኔ አሳርፏል።

Forwarded from እንደ ❤️ (kidane M)
ወንጀልን አለማሳወቅ ወንጀል ነው!
****
አይበልባችሁና የቅርብ ዘመድ ወይም ወዳጅ ወንጀል መፈፀሙን ብታውቁ ለሕግ አሳልፋችሁ ትሰጡታላችሁ ወይስ ዝምድናው ወይም ወዳጅነቱ ይዟችሁ አይቶ እንዳላየ ሆናችሁ ትደብቃላችሁ? ጉዳዩ የህሊና እንዲሁም የሕግ ተጠያቂነትን የሚመለከት ነው። የህሊናውን ለየራሳችን ትተነው ሕጉ ምን እንደሚል እንይ።
በሞት ወይም በዕድሜ ልክ እስር ሚያስቀጣ ወንጀል
በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 443 ላይ ማንኛውም ሰው በቂ ምክንያት ከሌው በስተቀር በሞት ወይም በእድሜ ልክ የሚያስቀጣ ወንጀል መፈፀሙን ወይም የፈፃሚውን ማንነት እያወቀ ለሚመለከተው አካል (ለፖሊስ) ሳያሳውቅ ከቀረ ወንጀልን ባለማሳወቅ ወንጀል ይቀጣል። ይህ ሕግ ማናችንም ላይ የተጣለብን ግዴታ ነው።
ሙያዊ ኃላፊነት ያለበት ሰው
ሌላኛው ወንጀልን ለሕግ አካል የማሳወቅ ግዴታ የሚመነጨው ደግሞ ግለሰቡ ከተሰማራበት የሙያ ግዴታ ሲሆን ከዚህ አይነት ሙያዎች መከከል ለምሳሌ የጥበቃ፣የፍተሻ፣የመቆጣጠር፣ፍቃድ የመስጠት የመሳሰሉት ሙያዎች መጥቀስ ይቻላል። በነዚህ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለህብተረተሰቡ ሰላምና ደህንነት አስጊ የሆኑ ወንጀሎችን ወይም ከባድ ሁኔታዎችን የማሳወቅ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን የሙያ ግዴታቸውን በመጣስ ወይም በምንቸገረኝ ወንጀሉን ለሚመለከተው አካል ካላሳወቁ እሰከ ብር 1000 ወይም እስከ 6 ወር እስራት ሊያስቀጣቸው ይችላል።
በተለይም ደግሞ ከፍተኛ አደጋ በሚፈጥሩ የተወሰኑ የወንጀል አይነቶች ላይ ወንጀልን አውቆ አለማሳወቅ የሚያስከትለው ሀላፊነት ከፍ ያለ ነው። ከነዚህ መሀል ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
የሀገርና የሕዝብ ደህንነትን ሚመለከት ወንጀል
በሕገመንግስታዊ ስርዓቱ፣ በሉአላዊነታችን፣ በመከላከያ፣ በውስጥና በውጭ ደህንነታችን ላይ የተሞከሩ፣ የተሰናዱ፣ የተፈፀሙ ወንጀሎችን አውቆ አለማሳወቅ፣ አደጋው፣ አንዳይደርስ ወይም አድራሹ እንዳይያዝ የሚችለውን ያላደረገ ሰው ከአቅም በላይ በሆነ ወይም ግልፅ ምክንያት ግዴታውን ሳይወጣ መቅረቱን ካላስረዳ በወንጀል ይቀጣል።
በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 254 መሰረት ቅጣቱ ከ5 አመት የማይበልጥ ፅኑ እስር ሲሆን ወንጀሉ የተፈፀመው ያገራችን የውስጥ ወይም የውጭ ደህንነት አስጊ ሁኔታ ላይ ሆኖ ከሆነ ቅጣቱ እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስር ይደርሳል።
ወታደራዊ ኩብለላ ወይም አመፅ
ወታደራዊ ኩብለላ ወይም አመፅ መዘጋጀቱን ወይም መፈፀሙን አውቆ ለሚመለከተው አካል ሳያሳወቁ መቅረት ፣እንዳይፈፀም ማድረግ ወይም አድራጊው አንዲያዝ አቅም የፈቀደውን አለማድረግም በቂ ምክንያት ከሌለ በቀር ያስቀጣል። በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 335(1) መሰረት ቢያንስ ወንጀሉ ከተሞከረ በቀላል እስራት ነገሩ ከባድ ከሆነ ደግሞ ከ3 ዓመት ማይበልጥ ፅኑ እስር ያስቀጣል።
የሽብር ወንጀል
በሽብርተኝነት አዋጁ 1176/2012 አንቀጽ 15 መሰረት የሽብር ድርጊት፣የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ማቀድና መሰናዳትን፣የሽብር ወንጀል ለመፈፀም ማደምን፣ለሽብር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ድጋፍ የማድረግ ተግባርን፣ለሽብር የማነሳሳትና ከሽብር ወንጀል ጋር የተገናኘ ንብረት የመያዝ ወንጀሎች አንዱ ሊፈፀም፣እየተፈፀመ ወይም የተፈፀመ መሆኑን ወይም የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት እያወቀ በቂ ምክንያት ሳይኖረው ወዲያውኑ ለፖሊስ ወይም አግባብ ላለው የሕግ አስፈፃሚ ካላሳወቀ ከአንድ አመት እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።
የሽብር ወንጀልን ያለማሳወቅ ቅጣቱን የሚያከብደው ደግሞ የሚያውቀውን መረጃ አሳውቆ ቢሆን ኖሮ ወንጀሉን መከላከል ወይም ማስቀረት የሚቻል ዓይነት ከሆነ ቅጣቱ ከሦስት እስከ ሰባት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይሆናል።
በሽብር ድርጊት የተጠረጠረን ወይም የተከሰሰን ሰው አስቀድሞ በማስጠንቀቅ፣በመደበቅ ወይም ዱካውን በመሸሸግ ወይም በማጥፋት፣የሚደረግ ምርመራን በማሳሳት ወይም በሌላ በማናቸውም መንገድ ተከሶ እንዳይቀርብ የረዳ ከሆነ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።ይህ ያለማሳወቅ ወይም በሽብር የተጠረጠረ ሰውን ተከሶ ለሕግ እንዳይቀርብ የመርዳት ድርጊት የወንጀል ተጠርጣሪውን መያዝ ወይም ማስቀጣት ቢቻልም እንኳን የሽብር ወንጀልን የማሳወቅና በሽብር የተጠረጠረ ሰውን በማንኛውም መንገድ በሕግ እንዳይጠየቅ ያለመርዳት ግዴታውን ያልተወጣ ሰው ለጥፋቱ መቀጣቱ እንደማይቀርለት አዋጁ ይደነግጋል።
ይህ የየሽብር ድርጊቶችን የማሳወቅ ኃላፊነት በሕግ ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ተፈፃሚ የማይሆን ሲሆን ወንጀሉ ሊፈፀም ወይም እየተፈፀመ ያለ ስለመሆኑ መረጃ ያለው ሰው ግን ይህን መብት ወይም ግዴታ እንደመከላከያ ሊያቀርብ አይችልም። ሚስጥር የመጠበቅ ሙያዊ ግዴታ የሽብር ወንጀልን ካለማሳወቅ ተጠያቂነት ሊያድን ሚችለው የሽብር ድርጊቱ የተፈፀም ወይም ድርጊቱ ካለፈና ጉዳቱን ለማስቀረት ወይም ለመከላከል ማይቻል ከሆነ ብቻ ነው።
ወንጀልን ላለማሳወቅ በቂ ሚባል ምክንያት
ወንጀልን አለማሳወቅ ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚያስቀጣ አንስተናል። ሆኖም ግለሰቡ ወንጀሉን ያላሳወቀው ‘‘በቂ ምክንያት’’ ኖሮት ከሆነ ላያስቀጣው እንደሚችል አይተናል።
"በቂ ምክንያት" የሚባለው ግለሰቡ ወንጀሉን ያላሳወቀው ‘‘ራሱን፣የቅርብ የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዱን ወይም በተለይም በጥብቅ ወዳጅነት የተሳሰረውን ሰው ለቅጣት ፣ለውርደት ወይም ለከባድ አደጋ ላለማጋለጥ’’ ከሆነ ነው። ከላይ የጠቀስነውን ወንጀልን ለሕግ አካል ያለማሳወቅ ምክንያት ከወንጀሉ አደገኛነትና ከሌሎችም ሁኔታዎች አንፃር መዝኖ በቂ ሆኖ ካገኘው በወንጀል ሕጋችን አንቀፅ 83(1) መሰረት ፍርድ ቤቱ ወንጀሉን ባለማሳወቅ ክስ የቀረበበትን ሰው ቅጣቱን በመሰለው መልኩ ያቀልለታል ወይም ከመነሻው የቅጣት መጠን ዝቅ አድርጎ ሊቀጣው ወይም ቅጣቱን በቀላል ሌላ ቅጣት ሊተካለት ይችላል።
ወዳጅነቱ ወይም ዝምድናው ከሚያስጠይቀው ወንጀል ክብደት ጋር ሲነፃፀር በጣም ጥብቅ ከመሆኑ የተነሳ ጭንቀት ፈጥሮበት ወንጀሉን ሳያሳውቅ የቀረን ሰው ፍ/ቤቱ በወቀሳ ወይም በማስጠንቀቂያ ሊያልፈው ይችላል።
በመሆኑም ሕጋችን ጥብቅ ዝምድና ወይም ወዳጅነት ለሚፈጥረው ትስስር እውቅና ቢሰጥም አጠቃላይ ህብረተሰቡ ላይ ከባድ ጉዳት የሚያደርሱ ከላይ የጠቀስናቸው አደገኛ ወንጀሎችን ግን አውቆ አለማሳወቅ በራሱ በወንጀል እንደሚያስጠይቅ ደንግጓል።
‘‘እንዴት ብዬ!? አብረን በልተን ጠጥተን፣ባለውለታዬን፣ዘመዴን ወይም ወዳጄን ወንጀል ፈፅሟል ብዬ አሳልፌ እሰጠዋለሁ?’’ በሚል ስሜት ወንጀልን እያወቁ ለሚመለከተው የሕግ አካል አለማሳወቅ ሕግ የጣለብንን ግዴታ አለመወጣት ነውና በወንጀል ያስጠይቃል።የዝምድናው ወይም የወዳጅነቱ ጥልቀት ከግንዛቤ ውስጥ ቢገባም የሚመጣውን ቅጣት የሚያቀል ‘በቂ ምክንያትነቱ’ በፍ/ቤቱ ይመዘናል እንጂ ከተጠያቂነት አያድንም።
በሕግ የሙያ ግዴታ ካለባቸው ሰዎች በስተቀር በሌሎች ሕጉ ወንጀልን አለማሳወቅ ጥፋት መሆኑን ባልደነገገባቸው ከላይ ካነሳናቸው ውጭ በሆኑ ወንጀሎች ላይ ግን ዝምድናው ወይም ወዳጅነቱ ኖረም አልኖረ ወንጀሉን አውቆ እንዳላወቀ ዝም ማለት በግለሰቡ የህሊና ወቀሳ ያስጠይቅ ይሆናል እንጂ በሕግ አያስጠይቅም።

❤1
Forwarded from የሕግ ዜና
ማንኛውም #የመንግሥት ሠራተኛ ለጋብቻ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ሰባትም(7) የሥራ ቀናት ፈቃድ ከደመወዝ ጋር ይሰጠዋል፡፡
የመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ 1064/2010 አንቀፅ 45
ማንኛውም #የግል ድርጅት ሠራተኛ ሕጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም ከክፍያ ጋር ለ ሶስት(3)የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 81 (1)(U)(ለ)
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
#NegereFej #ነገረፈጅ

❤🔥1
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ስለችሎታ እና ክልከላ ሕጉ ምን ይላል?
**************
ሁላችንም ሰው በመሆናችን መብት እና ግዴታዎችን የሚፈጥሩ ተግባራትን መከወን እንችላለን።መብት እና ግዴታን የሚፈጥሩ ተግባራት የሚባሉት ውል መዋዋል ፣ወኪል መሆን፣መክሰስ፣መከሰስ፣ንብረት ማፍራት በንብረት መብት መጠቀም፣ ጋብቻ መፈፀም ኑዛዜ ማድረግ እና የመሳሰሉት ናቸው።
እነኚህን መብቶችን ለመጠቀም ነፃ እና ምክንያታዊ ውሳኔ መወሰን የማንችልበት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሕግ ግምት ሲወስድ ከእነኚህ ሕጋዊ ውጤት ካላቸው ተግባራት ልንከለከል እንችላለን። እስኪ የፍትሐብሔር ሕጋችን ስለ ክልከላ ምን እንደሚል እንመልከት።
1. ስለችሎታ
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 192 ‘ሁላችንም በሕግ ተወስኖ ካልተገለፀ በቀር ማንኛውንም አይነት የማህበራዊ ኑሯችንን ተግባር ለመፈፀም ችሎታ አለን’ ይላል። ይህን ችሎታ የሚያሳጡት በዕድሜ ለአካለ መጠን አለመድረስ (ከ18 ዓመት በታች መሆን) የአዕምሮ ህመም፣ድርጊቱን ለመፈፀም ወሳኝ የሆነ የአካል ክፍል ጉዳት እና በፍርድ ቤት የሚጣል ከመብት የመሻር ቅጣት ናቸው፡፡
የተወሰኑ ነገሮችን ብቻ የማድረግ ችሎታ የሚያሳጣው ደግሞ የኢትዮጵያ ዜጋ አለመሆን ሲሆን፤ ለዜጎች ብቻ በተከለሉ ተግባራት ለምሳሌ መምረጥ ወይም መመረጥ፣በተወሰኑ የሥራና የንግድ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ በመገናኛ ብዙሀን፣ በብሮድካስት አገልግሎት እና በመሳሰሉት የተወሰኑ መስኮች ለመሰማራት የኢትዮጵያ ዜጋ ያልሆነ ሰው በሀገራችን ሕጎች ስለተከለከለ ለነዚያ ተግባራት ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለመሆኑ ችሎታ ይጎለዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0hJJCeE4WH79TXYPvbzDUCqkrngJnR3WccZvqAY71NZnVMesZ1ZEc3ttvrDH66Bq3l

ለፍርድ_አፈጻጸም_የተያዘ_ንብረት_ለፍርድ_አፈጻጸም_የሚሸጥበት_ሥነሥርአት.pdf
160 KB
ተከራካሪ ወገኖች በመደበኛ ፍርድ ቤት ሆነ በሌላ ፍርድ ቤትን ተክተው ውሳኔ በሚያስተላልፉ ተቋማት ቀርበው በመከራከር ውሳኔ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህም ውሳኔ በህግ ለማስፈፀም ስልጣን በተሰጠው አካል ይፈፀማል። ከሚፈፀምባቸው መንገዶችም አንዱ ለፍርድ አፈፃፀም በሚያዝ ንብረት ነው። በዚህ ንብረት እና አፈፃፀሙ ዙሪያ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ረዳት ዳኛ በሆኑት ቁም ነገር ደጉ ይህ አጭር ፅሁፍ ተዘጋጅቷል።
Forwarded from ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️ (Daniel Fikadu)
በፍርድ ቤት በማስረጃነት ሲቀርቡ ቴምብር ቀረጥ ለሚከፈልባቸው ሰነዶች ተገልጋዮች ክፍያ መፈጸም የሚችሉባቸው የገቢዎች ማዕከላት፡፡
************************************************************
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ በፍርድ ቤት በማስረጃነት በሚቀርቡ ሠነዶች ላይ የቴምብር ቀረጥ ለማስለጠፍ እና ቀረጥ በተመን ለማስከፈል ባለጉዳዮች ክርክራቸውን በሚያቀርቡበት ምድብ ችሎቶች አቅራቢያ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በምድብ ችሎቶች አቅራቢያ የተደራጁ የቴምብር ቀረጥ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና የወረዳ ቢሮዎች ከዚህ በታች የተመለከቱት መሆናቸውን እናሳውቃለን፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት

Forwarded from Ethio Legal Hub
ከባንኮች የራሳችን ያልሆነን ገንዘብ ማውጣት፣ ማስተላለፍ ወይም ከሌላ ሰው መቀበል ያስጠይቃል?
በደንብ!!!
* * *
የወንጀል እና የፍትሐብሔር ተጠያቂነት ሊኖር ይችላል።
#የወንጀልን_ተጠያቂነትን_ በተመለከተ
በሳይበር ምህዳር መስፋፋት ምክንያት አዳዲስ ወንጀሎችና አዳዲስ የወንጀል አፈፃፀም ስልቶች በመፈጠራቸው እንዲሁም በሃገሪቱ የኮምፒውተር ወንጀልን የሚገዙ መሰረታዊም ሆነ የሥነ-ሥርዓት ሕጎች በበቂ ሁኔታ ባለመኖራቸው ምክንያት የኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ወጥቶ ሥራ ላይ ውሏል።
ይህ አዋጅ ታዲያ በኮምፒውተር አማካይነት የሚፈፀሙ የማታለል ወንጀል፣ ማለትም በተጭበረበረ መንገድ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት የኮምፒውተር ዳታን በመለወጥ፣ በማጥፋት ወይም ሌላ ማንኛውንም ጉዳት በማድረስ ሌላ ሰው ላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደረሰ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከብር 10,000 እስከ ብር 50,000 በሚደርስ መቀጮ ወይም ወንጀሉ ከባድ በሆነ ጊዜ እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 በሚደርስ መቀጮ እንደሚቀጣ ይደነግጋል።
ገንዘቡን ራሱ በተለያየ የኤሌክትሮኒክስ መንገዶች የፈፀመው ሰው በላይኛው ድንጋጌ ሊጠየቅ ይችላል። ገንዘቡ የተላለፈለት ወይም የተቀበለ ሰውስ?
የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ የወንጀል ፍሬ ወይም ውጤት የሆኑ ንብረቶችን መያዝ፣ መደበቅ ወይም ማስቀመጥ ኃላፊነት እንደሚያስከትል በግልፅ ይደነግጋል። ይህ የመሸሸግ ወንጀል በሁለት መንገዶች ሊፈፀም ይችላል። የመጀመሪያው ወንጀለኞቹን ለመርዳት ወይም በቀጥታ ከወንጀል ድርቲቱ ጥቅም ለማግኘት ታስቦ ሲፈፀም ሲሆን ሁለተኛው ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን ማወቅ ሲገባቸው በቸልተኝነት ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት ገንዘቡን ተቀብሎ ይዞ መገኘት ነው።
ገንዘቡ የሚላክበት ምክንያት መኖሩን እና አግባብነቱን እንዳጣራ ሕጉ ይጠብቅብናል። የራሱን ገንዘብ የሚልክበት ምክንያት የሌለው ሰው ገንዘብ ሲያስተላልፍልን መጠየቅ እንዲኖርብን ያደርጋል። በተለይ የአንድ ባንክ ሥርዓት መበላሸቱን የሚገልፅ ዜና በማህበራዊ ሚዲያ እና ሌሎች የዜና ምንጮች በስፋት ተወርቶ ሲገኝ ገንዘቡ ተሰርቆ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት የሚያስቸሉን አመላካች ነገሮች በመሆናቸው ከወንጀል ተጠያቂነት አናመልጥም። ገንዘቡ ከትክክለኛ ባለቤቱ በወንጀል ድርጊት አማካኝነት የተወሰደ መሆኑ ሲረጋገጥ እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል።
ድርጊቱ በኮምፒውተር ሥርዓት አማካኝነት የተፈፀመ እንደመሆኑ መጠን በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጁ ሊታይ ቢችልም፣ ከላይ ከተጠቀሱት ሁኔታዎች በተጨማሪ የአዋጁ ድንጋጌ ላይ ያለውን ቴክኒካል ቃላት አያሟላም የሚባልበት ሁኔታ ቢኖር ድርጊቱ መደበኛውን የስርቆት ወንጀልን ሊያቋቁም ይችላል።
በባንኩ የኮምፒውተር ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ያላደረሰ ሰው፣ ነገር ግን 2ሺ ብር ሊያወጣ ጠይቆ ኤቲኤም ማሽኑ 5ሺ ብር ቢሰጠው ግለሰቡ ልዩነቱን እና የርሱ ያልሆነውን 3ሺህ ብር የመመለስ ግዴታ አለበት። ያንን ባያደርግ አግኝቶ በመደበቅ ወንጀል ሊጠየቅ ይችላል። ይህ ወንጀል አንድ ሰው ከህጋዊ መንገድ ውጪ ንብረት አግኝቶ በዚሁ ንብረት ያለአግባብ ለመበልጸግ በማሰብ ንብረቱን ለመደበቅ የሚፈጽመው የወንጀል ተግባር ነው፡፡ ማንም ሰው የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን በስህተት ወይም ባልታሰበ ድንገተኛ አጋጣሚ ነገር፣ ከባለንብረቱ ፈቃድ ውጭ በሆኑ ማናቸውም ሁኔታ ከባለቤቱ እጅ ወጥቶ በእጁ የሚገኝን ንብረት ወይም እቃ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ካደረገ በወንጀል ያስጠይቀዋል፡፡ ይህንን የፈፀመ ሰው በመቀጮ ወይም በቀላል እስራት ያስቀጣል ሲል የወንጀል ህጉ ደንግጓል፡፡
#የፍትሐብሔር_ተጠያቂነትን_ በተመለከተ
ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ያለአግባብ መበልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡
ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እና ባለሀብቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ጥቅም ባገኘበት ልክ ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ሕጉ ያስቀምጣል፡፡ ያለአግባብ መበልፀግ በመሰረታዊነት ሶስት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን አንድን ሰው በዚህ የህግ ክፍል በመክሰስ ካሳ ለማስከፈል እነዚህ ሶስት ሁኔታዎች በድምር መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1ኛ. ተከሳሽ በገንዘብ ሊለካ የሚችል ጥቅም ያገኘ መሆኑ፤
2ኛ ይህ ጥቅም የተገኘው በከሳሽ ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መሆኑ እንዲሁም
3ኛ. የተገኘበት መንገድ አለአግባብ ወይም ምንም አይነት ህጋዊ መንገድ የማይቀርብበት መሆኑ ናቸው፡፡
©👉Ethio Legal shield.
___
Join us👇👇
https://t.me/ET_Legalhub
Join our discussion group👇👇
https://t.me/the_Legalhub

Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የወራሽነት ምስክር ወረቀት (certificate of heir)
የወራሽነት ምስክር ወረቀት(certificate of heir) ምንድነው?
# የወራሽነት ምስክር ወረቀት በአጭሩ ለመግለጽ ህጋዊ የውርስ ስርዓት ለሟላ የሟች ወራሽ ለሆነው ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ የሚገባውን ድርሻ በተመለከተ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ተረጋግጦ የሚሰጥ የጽሁፍ ማረጋገጫ ነው ለማለት ይቻላል።
✅♨️በቴሌግራም 👍👇✅ https://t.me/HenokTayeLawoffice
ወራሽ የሆነው ሰው ከውርሱ የሚያግኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት ምስክር ወረቀት እንዲሰጡት ዳኞችን ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህግ 996(1) ይደነግጋል።ከፍርድ ቤት የወራሽነት ምስክር ወረቀት መያዝ በወራሹ ሲጠየቅ የሚሰጥ እንጂ ህጉ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ማውጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም።
በዚህ ጉዳይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 22 መ/ቁ 130284 ለይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የውርስ ሰርተፊኬት አንድ ሰው የራሱን ወራሽነት ለማስረዳት የሚወስደው ማስረጃ እንጂ ሌሎች ወራሾች አለመኖራቸውን የሚያሳይ ሰነድ ስላለመሆኑ፣ እና በግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው በማረጋገጥ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ከማስረጃነት በዘለለ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ በሚያዘው መሰረት ከሌሎች ሰዎች ክርክር ተደርጎበት ውሳኔ ያገኘና በፍርድ ያለቀ መቃወሚያ የማይቀርብበት ተደርጎ ሊወሰድ የማይገባ ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጥቶበታል።በተመሣሣይ መልኩ በፌ.ጠ.ፍ.ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ14 መ/ቁ 73247 አንድ ወራሽ የወራሽነት መብት በሌለው ንብረት ላይ ከህግ ውጪ የወራሽነት ሠርተፍኬት መያዙ በተረጋገጠ ጊዜ ይኸው ማስረጃ እንዲሰረዝ አቤቱታ ሊቀርብ እንደሚችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
#በመሠረቱ የመወረስ መብት የሚገኘው በህግ ወይም በኑዛዜ ሲሆን ፍ/ቤት አስቀድሞ ለአመልካቹ ያለውን የውርስ መብቱ አረጋግጦ የሚሰጥ እንጂ ለአመልካቹ የውርስ መብትን የሚስጥ አይደለም።በፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 20 መ/ቁ 113529 ለይ በተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ ቡሃላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባያወጣም ለውርሱ አይገባም እስካልተባለ ድረስ የወራሸነት መብቶች ለእርሱ ወራሾች የሚተላለፍ ስለመሆኑ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል። የወራሽነት ሰርትፍኬት አስገዳጅ የሆነ ህጋዊ ውጤት ይኖረዋል።
# የወራሽነት ምስክር ወረቀት የያዘው ወራሽ የምስክር ወረቀቱ እስካልተሰረዘ ድረስ ህጋዊ የውርስ መብት እንዳለውና ከውርሱ ድርሻ የሚገባ እንደሆነ ተደረጎ ይቆጠራል።አሁን በተግባር ባለው ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት አንደ ሰው ከያዘ ቡሃላ ወራሹ በሰርተፍኬቱ መሠረት ህጋዊ ውጤት ያላቸውን(valid juridical acts) ተግባራት መፈጸም ይጀምራል ማለትም ስመ ንብረት የማዞር ከባንክ ገንዘብ የማውጣትና ሌሎች መብቶች ማከናወን ይችላል ማለት ነው።የውርስ ሰርተፍኬት ውርሱ ከመጣራቱ በፊት ነው ወይስ የውርስ መጣራቱ ሂደት ከተጠናቀቀ ቡሃላ ነው ሊሰጥ የሚገባው የሚለው ጥያቄ አከራካሪ ሲሆን ይታያል የውርስ ማጣራት ሂደት ከመጠናቀቁ በፊት የሚሰጠው ምስክር ወረቀት ህጋዊ ወራሾች ከመለየታቸው በፊት እና ከማነኛውም እዳ ነጻ የሆነ የውርስ ንብረት ተጣርቶ ባልተለየበት ሁኔታ የሚሰጥ በመሆኑ አግባብነቱ አጠያያቂ ይሆናል በዚሁ ጉዳይ ለይ የፌ.ጠ.ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ18 መ/ቁ110022 በሰጠው ውሳኔ ፍ/ቤቶች የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ብቻ አንዲሰጡ ማመልከቻ ሲቀርብላቸው ውርስ እንዲጣራ የሚሰጡት ትእዛዝ የማይገባና አላስፈላጊ ስለመሆኑ ትርጉም ሰጥቶት እናግኛለን።

https://t.me/ethiolawtips

የመቃወም አቤቱታ/የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 እስከ 360/ > ፍርድ ከተሰጠ በኋለ የሚቀርብ ሥርዓት
♨️♨️🛑🛑🛑🛑🛑⚖️👇
#Telegram ❤👇
https://t.me/HenokTayeLawoffice
1 • ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት አስቀድሞ ለአንድ ወገን የተሰጠውን ውሳኔ ለማሰረዝ በመቃወም አመልካች የሚቀርብ አቤቱታ
የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ክርክሩ የሚካሄደው በመቃወም አመልካች እና አስቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ተጠቃሚ በሆነው የመቃወም ተጠሪ በሚባለው ወገን መካከል ሲሆን የዚህ ዓይነቱ ክርክር የሚቀርብበት እና የሚመራበት ስርዓት እንዲሁም የዚህ ዓይነቱን ክርክር የሚሰማው ፍርድ ቤት ስላለው ስልጣን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ከቁጥር 358 እስከ 360 ተመልክቷል፡፡ የመቃወም አቤቱታው መቅረብ የሚገባው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 222 እና 223 ድንጋጌዎች መሰረት ክስ እና የማስረጃ መግለጫ የሚቀርብበትን ስርዓት መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በግልጽ ተደንግጎአል፡፡
የመቃወም አቤቱታው እና የማስረጃው ቅጂ የመቃወም ተጠሪ ለሆነው ወገን እንዲደርስ መደረግ የሚገባው መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር የመቃወም ተጠሪው የጽሁፍ መልስ እና የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚገባው በእነዚህ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ የተጻፈ ባይሆንም የመቃወም ተጠሪ የሆነው ወገን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234 ድንጋጌ መሰረት ለቀረበበት የመቃወም አቤቱታ ያለውን የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ከቁጥር 360(1) እና (2) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይም የመቃወሚያው ክርክር የሚሰማው የመጀመሪያው ክርክር በተሠማበት ስነ ስርዓት መሰረት ስለመሆኑ በቁጥር 360(2) የተመለከተው አስገዳጅ ድንጋጌ በቀጥታ የቀረበ ክስ እና ክርክር የሚስተናገድበትን ስርዓት በተመለከተ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት መሰረታዊ ድንጋጌዎች የመቃወሚያ ክርክርን በማስተናገድ ረገድም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ ሊደረጉ የሚገባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው የክርክር አመራር ስርዓት ዓይነተኛ ዓላማ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች እኩል ዕድል እንዲኖራቸው እና በተለይም የመቃወም አመልካች የሆነው ወገን የክርክሩ ተካፋይ ባልነበረበት ጊዜ የቀረበውን የመቃወም ተጠሪ ወገን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በመስቀልኛ ጥያቄ እና በማስተባበያ ክርክር ጭምር የመፈተን ዕድል እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86398 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 222፣ 223፣ 350-360
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አንድ የክርክሩ ተካፋይ መሆን የሚገባው ሰው የክርክሩ ተካፋይ ሳይሆን ውሳኔ ተሰጥቶ ከሆነ እና ውሳኔውም ያረፈው በአንድ የክርክሩ ምክንያት በሆነ ንብረት ላይ ሁኖ ይህንኑ የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ከተረጋገጠ ፍርዱ ይኸው ወገን ባለበት እንዲታይና በሕግና በማስረጃ የተደገፈ ሁኖ ሲገኝ እንዲነሳለት የሚደነግግ ነው፡፡ አቤቱታው የሚቀርብበት ሥርዓትም በቁጥር 359 ስር በተመለከተው መንገድ መሆን እንደአለበት የተቀመጠ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የመቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ በክስ አመሰራረት አይነት ሁኖ ማስረጃ ዝርዝር ሁሉ ይህንኑ ስርዓት ማሟላት እንደአለበት ያስገነዝባል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ ክርክሩ መኖሩን ከጅምሩ እያወቀ ውጤቱን በመጠበቅ ከፍርዱ በኋላ የፍርድ መቃወሚያ የሚያቀርበውን ወገን አቤቱታውን በመቀበል ለማስተናገድ አስፈላጊ ያለመሆኑን ሁሉ ያስገነዝባል፡፡
ይህም የክርክር አቀራረብ በቅን ልቦና የተመሰረተ ሁኖ በአነስተኛ ወጪ፣ ጉልበትና አጭር ጊዜ ፍትሐዊነት ያለውን ውሳኔ ለመስጠት የሚቻልበት አግባብ እንዲኖር እና ሕግ አውጪ ከፈለገበት አላማ ጋር መጣጣም ያለበት መሆኑም የሚታመን ነው፡፡ እንግዲህ አቤቱታውን የሚያቀርበው ወገን የቅን ልቦና ተከራካሪ ሁኖ መሰረታዊ መብቱን ማስከበር የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብ እንዲኖር ሕግ አውጪ የፈለገ ሲሆን ይህንኑ መመዘኛ የሚያሟላ አቤቱታ አቅራቢ የሚቃወመው ፍርድ ዋጋ ያለው፣ ያልተፈፀመ መሆን እንደአለበትም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌ ይዘት ያስረዳል፡፡ በሌላ አገላለፅ የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት ፍርድ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ያልተሻረና አፈጻጸሙም ያልተጠናቀቀ ሊሆን እንደሚገባ ሕጉ ያሳያል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 93987 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358፣ 359
የሟች ሀብት ተጣርቶ በክፍፍሉ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ውርሱ ሲጣራ ያልተሳተፈ የሟች ወራሽ ነኝ የሚል ወገን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ ማቅረብ ያለበት በውርስ አጣሪው ሪፖርትና ሪፖርቱን ባፀደቀው ፍ/ቤት ሳይሆን የክፍፍሉን ጥያቄ አይቶ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት ነው፡፡ የውርስ አጣሪ ሪፖርት በፍርድ ቤት መጽደቅ በራሱ ፍርድ ሁኖ ለአፈፃፀም የሚቀርብ ሣይሆን እንደማስረጃ የሚያገለግል ነው፡፡ በመሆኑም ሪፖርቱ የማስረጃነት ዋጋ አለው ከተባለ ደግሞ የክፍፍል ክርክር ሲቀርብ በማስረጃነቱ ላይ ክርክር ቢቀርብ ክርክሩ መቅረብ ያለበት በውርስ አጣሪና ሪፖርቱን በአፀደቀው ፍርድ ቤት ነው ተብሎ ውድቅ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 45905 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358፣ ፍ/ህ/ቁ. 944፣ 946፣ 956፣ 960
ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት የሚያካሂዱትን ሙግት በማቋረጥ የሚያደርጉት የእርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ተረጋግጦና ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ መባሉ የፍርድ ያህል አስገጃጅነት ያለው በመሆኑ እርቁን ያፀደቀው ፍርድ ቤት እርቁ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም በእርቁ መሠረት ይፈፀም በማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሰጠውን ትእዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358 መሰረት በእርቅ ስምምነቱ መብቴ ተነክቷል በሚል ወገን ተቃውሞ ሊቀርብበት የሚችል ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 83582 ቅጽ 15
2 • በአፈጻጸም ንብረት እንዳይያዝ፣ እንዳይታገድ በንብረቶቹ ላይ መብት አለኝ የሚል በክርክሩ ተሳታፊ ያልሆነ ሶስተኛ ወገን የሚያቀርበው አቤቱታ
የፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 ድንጋጌ አስፈላጊነት የክርክሩ አካል ያልሆኑና ፍርድ ያላረፈባቸው የ3ኛ ወገን ንብረት ሳይረጋገጥ ለፍርዱ ማስፈፀሚያነት እንዳይውሉ ለመከላከልና ባንጻሩ ፍርዱን የመፈፀም ለማስተጓጉል (እንዳይፈፀም ለሚቀርቡት በቂ ላልሆኑ አቤቱታዎችም) እልባት የሚሰጥ ነው፡፡ በመሆኑም በተያዙት ንብረቶች ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን የሚያቀርበውን መቃወሚያና አቤቱታ ተቀብሎ መመርመር እንዳለበት የተጠቀሰው ድንጋጌም በግልፅ ያሰፈረው ነው፡፡ ይህ ከሆነ የዚሁ አንቀጽ 418(3) የአራተኛው ቅጂ ባለይዞታነትን ለማስረዳት የፅሁፍ ማስረጃ መቅረብ እንዳለበት የሚደነግግ ቢሆንም የእንግሊዘኛው ቅጂ የስነ- ስርዓት ህጉ ደግሞ ይህንኑ አንቀጽ ሲገልጽ The Claimant or 0bjector Shall adduce evidence to Show that at the date of the attachment he had Some interest in, or was possessed of the property attached ይላል፡፡ እንግዲህ ከዚህኛው የእንግሊዘኛ ቅጂ የምንረዳው ማስረጃ በማቅረብ ለአፈጻጸም የቀረበውን ንብረት ማስረዳት እንደሚቻል የሚገልጽ ነው፡፡ የአማርኛው ቅጂም ቢሆን ከፍ/ህ/ቁ/1193 (1) እና (2) ድንጋጌዎች ጋር ተደምሮ ሲታይ ሌላውን የማስረጃ አይነት በግልጽ እንዳይቀርብ የከለከለው ሆኖ

አይታይም፡፡
ሰ/መ/ቁ 97094 ቅጽ 17፣ ፍ/ህ/ቁ. 1193(1) (2)፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 418
በዋናው ክርክር የሚሰጠው ውሳኔ እና በውሳኔው መሠረት ለማስፈጸም የሚደረገው ሂደት የተለያዩ በመሆናቸው በሚቀርቡት መቃወሚያዎች ላይ የሚሰጡት ውሳኔዎችም የተለያዩ ናቸው፡፡ መቃወሚያ አቅራቢው መብቱ የተነካው በአፈጻጸም ሂደቱ ከሆነ ከአፈጻጸም ሂደቱ ጋር የተያያዘ መፍትሄ ነው የሚሰጠው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418 መሠረት በሚቀርብ መቃወሚያ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 419 ተመልክቶአል፡፡ በዚህ መሠረት መቃወሚያው ተቀባይነት ያገኘ ከሆነ በአፈጻጸም የተያዘው ንብረት በከፊል ወይም በሙሉ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ከዚህ አልፎ በአፈጻጸም የተያዘው ንብረት ለአንድ ወይም ለሌላው ተከራካሪ ወገን ይገባል የሚል ዳኝነት አይሰጥም፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ በዋናው ክርክር የተሰጠውን ውሳኔ የሚሽር ወይም የሚያሻሽል ውሳኔ አይሰጥም፡፡ የዚህ አይነት ውሳኔ መስጠት የሚቻለው ዋናውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እራሱን የቻለ የአቀራረብ ሥርዓት እና የክርክር አመራር ሂደት ያለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ተገቢው ድንጋጌም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 የተመለከተው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 53607 ቅጽ 12 ፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358፣ 418፣ 419
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 አግባብ የተሟላ ክርክርና ማስረጃ ያቀረበ ወገን አቤቱታው በመደበኛ ሙግት እንዲከናወን እንዳይጠይቅ ሕጉ ግልጽ ክልከላ ያላደረገበት ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 421 ስር የተጠበቀው መብትም በሕጉ አግባብ የሚቀርቡ መቃወሚያዎች እንደተጠበቁ ሁነው አመልካቹ በምርጫው እንዲጠቀምበት የተቀመጠ እንጂ ይህንኑ ስርዓት እንዲከተል የግድ የሚደረግበት ያለመሆኑ ድንጋጌው በፈቃደኝነት የአቀራረፅ ስርዓት መቀመጡ አስረጂ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ 86133 ቅጽ 15
የቀዳሚነት መብት አለኝ በሚል መቃወሚያ አቅርቦ ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ሰው በድጋሚ ክስ ማቅረብ የተፈቀደለት በአፈፃፀም ችሎት የንብረቱ ባለመብትነት በጭብጥነት ተይዞ በመደበኛው የሙግት ስርአት አይነት ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ አንፃር ተመርምሮ ውሳኔ የሚሰጥበት ባለመሆኑ ይህንን እድል ለመስጠት ነው፡፡ አመልካቹ ይህንን መብት የሚያስከብርለት ሌላ ክስ የመሰረተ ከሆነ ግን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 421 ክስ ለማቅረብ ስለሚፈቅድ ብቻ በተመሳሳይ ጉዳይ ዳግመኛ ክስ ማቅረብ የስነ-ስርአት ህጉ አላማ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 37214 ቅጽ 9፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 421
#TelegramChannel 👇🛑

ከጋብቻ በፊት ስለተፈራ ንብረት
ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ የተፈራ ቤት በጋብቻ ውስጥ በልማት ምክንያት ፈርሶ በምትክ በተሰጠ ቦታ እና በካሳ ገንዘብ በጋብቻ ውስጥ ቤት ከተሰራ በፍርድ ቤት የግል ተብሎ ካልተመዘገበ የባል እና የሚስት የጋራ ሃብት ይሆናል።
በአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ በአንቀጽ 68 ባል እና ሚስት ጋብቻቸውን ሲፈጽሙ በግል የነበራቸው ንብረት የግላቸው ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን የተመለከተ ሲሆን በአንቀጽ 69 ደግሞ ባል እና ሚስት ከተጋቡ በኋላ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ በሆነ ንብረት ለውጥ ያገኘው ወይም በግል ገንዘቡ የገዛቸው ወይም የግል ንብረቱን ሸጦ የሚያገኘው ገንዘብ የግሉ ሊሆን የሚችለው በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ይባልልኝ በሚል አንደኛው ተጋቢ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ሲጸድቅለት ብቻ መሆኑ ተደንግጓል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው በአንደኛው ተጋቢ ከጋብቻ በፊት የተፈራ ንብረት የግል ሀብት ቢሆንም በጋብቻ ውስጥ በዚህ በግል ንብረት ለውጥ ወይም የግል ንብረት ተሸጦ የሚገዛ ሌላ ንብረት ወይም በግል ገንዘብ የተገዛ ንብረት ለፍርድ ቤት የግል ሆኖ እንዲቀጥል ጥያቄ ቀርቦ ካልጸደቀ የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት መሆኑ ቀርቶ የባል እና ሚስት የጋራ ንብረት የሚሆን መሆኑን ነው። በሌላ አባባል ከጋብቻ በፊት በአንደኛው ተጋቢ የተፈራ ንብረት በጋብቻ ውስጥ በማንኛውም ምክንያት ከተለወጠ የግል ሀብት ሆኖ መቀጠል የሚችለው በፍርድ ቤት የግል ሆኖ እንዲቀጥል ከተባለ ብቻ ነው። የዚህ ድንጋጌ አላማ በጋብቻ ውስጥ የሚገኝ(የተፈራ) ንብረት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት እንደሆነ የህግ ግምት የሚወሰድ በመሆኑ ይህንን የህግ ግምት ለማፍረስ የሚቻለው በፍርድ ቤት የአንደኛው ተጋቢ የግል ሆኖ እንዲቀጥል የተባለበትን ትእዛዝ ወይም ውሳኔ እንደማስረጃ በማቅረብ ብቻ ግምቱን ለማፍረስ እንዲቻል ሲሆን በዚህ መልኩ የግል ሆኖ መቀጠሉን ማስረዳት ካልተቻለ አንደኛው ተጋቢ ከጋብቻ በፊት ያፈራው ንብረት በጋብቻ ውስጥ ሲለወጥ የጋራ ሆኖ እንዲቀጥል መስማማቱን የሚያሳይ በመሆኑ ነው። በመሆኑም በፍርድ ቤት የግል ሆኖ እንዲቀጥል የወሰነበት/ያጸደቀበት ማስረጃ እስካቀረበ ድረስ በጋብቻ ውስጥ የተፈራው ንብረት ምንጭ የግል ሀብት በመሆኑ ብቻ የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብት ሆኖ መቀጠል አይችልም።
ስለሆነም ቤቱ የተሰራበት ገንዘብ እና ቦታ ምንጩ የአንደኛዉ ተጋቢ የግል ሀብት የነበረ ቤት መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ቢሆንም ከጋብቻ በፊት የሟች የግል ሀብት የነበረው ቤት በልማት ምክንያት ፈርሶ በምትክ በተሰጠ ቦታ እና በካሳ ገንዘብ በጋብቻ ውስጥ መሰራቱ ከጋብቻ በፊት የነበረው ቤት እንደተለወጠ የሚያስቆጥር ነው። ከጋብቻ በፊት የነበረው ቤት በጋብቻ ውስጥ ሲለወጥ የግል ሆኖ እንዲቀጥል የማድረግ ፍላጎት ከነበራቸው በፍርድ ቤት የግል እንዲባል ጥያቄ አቅርበው ማጸደቅ አለባቸዉ። በዚህ መልኩ በጋብቻ ውስጥ የተሰራው ቤት የግል ሆኖ እንዲቀጥልላቸው ጥያቄ አቅርበው ጥያቄያቸው ተቀባይነት ስለማግኘቱ በማስረጃ እስካልተረጋገጠ ድረስ አዲስ በምትክ የተሰራዉ ቤት የግል ሀብት ነው ሊባል የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ሰ.መ.ቁ. 228668 ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም