የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from ስለፍትሕ (Talk To Lawyer)
#ፍርድ ቤቶች ሚቀበሏቸው ሕጋዊ የቅጣት ገደብ ምክንያቶችን
#መሠረቱ
👉አንድ ቅጣት የሚገደበው ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ በተባለበት ውሳኔ በእስር ላይ ሳይደረግ ለጊዜው ቅጣቱ እንዳይፈጸምበት በማድረግ የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል ወደ መደኛ ማኅበራዊ ሕይወቱ ለመመለስ ጠቃሚ መሆኑን ፍርድ ቤት ሲያምንበት ነው።
👉ገደብ ከተሰጠ በኋላ የታሰበውን ውጤት ያላስገኘ እንደሆነ በማንኛውም ጊዜ ሊሻር ይችላል።
#ቅጣት የሚገደበው
1️⃣ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ከሆነ፤
2️⃣ጠባዩ አደገኝነት እንደሌለው ከታመነ፤
3️⃣ጥፋቱ በመቀጮ ወይም በግዴታ ሥራ ወይም ከሦስት ዓመት በማይበልጥ እሥራት የሚያስቀጣ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛው የሚወስንበትን ቅጣት ሳይፈጽም ለተወሰኑ ጊዜያት ጠባዩ ቢፈተሽ የሚታረም መሆኑን እምነት የጣለበት እንደሆነ የጥፋተኝነት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ቅጣቱ ሳይወሰን የተወሰነ የፈተና ጊዜ ይሰጠዋል።
4️⃣ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት እንደማያደርግ ፍርድ ቤቱ ካመነ ቅጣቱን ሊገድብለት ይችላል።
#ቅጣት የማይገደበው
1️⃣ጥፋተኛው ከዚህ በፊት በጽኑ እሥራት ወይም ከሦስት ዓመት የሚበልጥ እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት ከነበረ እና አሁንም በተከሰሰበት ጉዳይ እነዚህ ቅጣቶች የሚፈጸሙበት ከሆነ፤
2️⃣ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ አሁን በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት ዓመት የበለጠ የፅኑ አሥራት የሚፈረድበት ከሆነ፤
3️⃣ቅጣቱ ታግዶለት ለፈተኛ በተለቀቀበት ጊዜ ውስጥ አስቦ አንድ ወንጀል ከፈጸመ፤
4️⃣ቅጣቱ ቢገደብለት የሚታሰበውን ዓይነት መልካም ውጤት እንደማይገኝ ፍርድ ቤቱ ያመነ እንደሆነ።
ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመገደቡ በፊት ስለተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፣ የነበረው ጠባይ፣ የአኗኗሩና የሥራው ሁኔታ ምን እንደነበረ ምርመራ ተደርጎ ማስረጃ እንዲቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።
👉የሚወሰነው የቅጣት ገደብ ከ2 ዓመት ሊያንስ ከ5 ዓመት ሊበልጥ አይችልም።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
#laws2016

https://t.me/NegereFej
#ነገረ_ፈጅ
Forwarded from የሕግ ዜና
#በውርስ ክርክር ላይ ከሚገጥሙ እንግዳ ጉዳዮች መካከል ሟች ኑዛዜ አድርጎልኛል ወይም አድርጎልናል የሚሉ ተከራካሪዎች መቅረባቸው ነው።
#ልዩ የሚያደርግ ይህ አለ የሚባለው ኑዛዜ በውልና ማስረጃ ተደርጎ እንዲሁ በፍርድ ቤት ጸድቆ እንደማስረጃነት የሚቀርብ መሆኑ ነው።
በሌለ መብት ኑዛዜ ማድረግና ውጤቱ
#ሟች ኑዛዜ ማድረግ የሚችለው በሕግ ባለውና በተጠበቀለት መብት እና ድርሻ ልክ ብቻ ነው። ባልና ሚስት በትዳር እየኖሩ ባለበት ሁኔታ ባል ወይም ሚስት የአንዳቸውን ድርሻ ጠቅልለው ኑዛዜ ቢያደርጉበት በሌላቸው መብትና ድርሻ ላይ የተደረገ በመሆኑ የተናዘዙት ኑዛዜ ከድርሻቸውና ከመጠናቸው ያለፈውን ያህል ልክ ብቻ ፈራሽ ይሆናል።
#እንደዚህ ያለ ማስረጃ እንደመከራከሪያ ማስረጃ ሆኖ ሲቀርብ ሊሰጥ ከሚገባው ምላሽ ውስጥ ቀዳሚው መሆን ያለበት ሟች ፈጸመ የተባለው ኑዛዜ ከድርሻው በማለፍ በመሆኑ የሕግ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም መባል አለበት።
#በዚህ ረገድ የፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 8 በመዝገብ ቁጥር 32817 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ላይ "ተናዛዡ ከራሱ ንብረት ጋር የሌላ ሰውን ንብረትም ጨምሮ በመዘርዝር ኑዛዜ አድርጎ ይህ ኑዛዜ በፍርድ ቤህ ቢጸድቅም እንኳን የሌላ ሰው የሆነውን ንብረት በተመለከተ የተደረገው ኑዛዜ ዋጋ ሊሰጠው አይገባም። በራሱ ንብረቶች ላይ የተናዘዘው ግን ተለይቶ ዋጋ ሊሰጠው ይገባል።" በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ

https://t.me/NegereFej
Forwarded from Law forum (marye kasse)
የኮምፒውተር ወንጀል የሚያስከትለው ተጠያቂነት
መግቢያ

በአለማችን ቴክኖሎጂ እየረቀቀ እና ሥራዎችን እያቀላጠፈ ይገኛል፡፡ የኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአት ከነዚህ ቴክኖሎጂዎች በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ቴክኖሎጂ ለአለማችን አጋዥ ቢሆንም ለጥቃት ተጋላጭ ከመሆኑ አንፃር የራሱ ውስንነቶች ያሉት እና የጥንቃቄ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ የኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአትን እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀልን ምንነት አና የሚስከትለውን ተጠያቂነት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር ሥርአት ምንነት

በኮምፒውተር አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 2(3) መሰረት ኮምፒውተር ወይም የኮምፒውተር ሥርአት ማለት በሶፍትዌር እና ማይክሮቺፕ ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የዳታ ፕሮሰሲን፣ ክምችት፣ ትንተና፣ ሥርጭት፣ ግንኙነት ወይም ሌሎች ሂሳባዊ ወይም አመክንዮአዊ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም መሳሪያ እና የመሳሪያውን ተገጣሚ አካል የሚጨምር እንደሆነ ትርጓሜ ተሰጥቶታል፡፡

የኮምፒውተር ወንጀል ምንነት

በአዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀፅ 2(1) መሰረት የኮምፒዩተር ወንጀል ማለት በኮምፒዩተር፣ በኮምፒውተር ሥርአት እና በኮምፒዩተር ዳታ (ኔትዎርክ) ላይ የሚፈፀምን ወንጀል፣ እነዚህኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም የሚፈፀምን መደበኛ ወንጀል እንዲሁም ይህንኑ በመጠቀም ህገወጥ የኮምፒውተር ዳታ ማሰራጨትን የሚያከትት ነው፡፡ የወንጀሉ ዋነኛ ማጠንጠኛም በኮምፒዩተሩ ዳታ ላይ ያተኮረ ሆኖ በኔትወርክ አማካይነት ዳታውን ከመደበኛ አሰራሩ ውጭ ማበላሸት ወይም ማዛባትና ማሰራጨት ለዚህም አላማ ያለባለቤቱ ፍቃድ ኮምፕዩተሩን ማግኘት የሚመለከት ነው፡፡

የሳይበር ጥቃት መከላከል በአለምአቀፍ ደረጃ
የሳይበር ጥቃት የኮምፒውተር ሥርአት ወይም ኔትዎረክን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማግኘት ሲሆን አላማውም ጉዳት ማድረስ ነው፡፡ የሚያደርሰውም ጉዳት ብልሽት፣ ማዛባት፣ ማስወገድ ወይም የኮምፒውተሩን ሥርአት በመለወጥ ማጥፋት፣ በሥርአት ውስጥ ያለ መረጃን ማዛባት ወይም መስረቅን ይጨምራል፡፡ ይህ ጥቃት የማጥቃት እስትራቴጂ ባለው በማንኛውም ሰው ወይም ቡድን ከየትኛውም ቦታ ሊሰነዘር ይችላል፡፡ ጥቃቱን የሚፈፅሙ ሰዎች የሳይበር ወንጀለኞች ወይም በተለምዶ ሀከሮች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

የሳይበር ጥቃት አለማቀፍ ወንጀል መሆኑን መግባባት ያለ ቢሆንም ይህንኑ ድርጊት የሚያወግዝ ወጥ የሆነ አለማቀፍ ህግ ግን እስካሁን የለም፡፡ ይሁንና በጉዳዩ ላይ አህጉራዊ ስምምነቶች ያሉ ሲሆን ለአብነት ያክል በአፍሪካ ደረጃ በ2008 የወጣው የአፍሪካ ህብረት የሳይበር ደህንነት እና ግላዊ ዳታ ለመጠበቅ የወጣውን ስምምነት (African Union Convention on Cyber Security and Personal Data Protection) መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአውሮፓ ህብረት ደረጃ የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል እ.አ.አ በ2001 በሀንጋሪ የወጣው ስምምነት Convention on Cybercrime (በተለምዶ የቡዳፔስት ስምምነት እየተባለ የሚጠቀሰው) ተጠቃሽ ስምምንት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሀገራት በግዛታቸው የሚፈፀሙ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል ህግ በማውጣት ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የሳይበር ክልልን መቆጣጠር እና ማስተዳደር ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪ የሌሎች አካላትን ተሳትፎ ይፈልጋል፡፡ ይኸውም ለኢንተርኔት መፈጠር እና መስፋፋት መሪ ሚና የተጫወቱ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማለትም እንደ ጉግል፣ ፌስቡክ፣ የኢንተርኔት እስታንዳርድ እና ፕሮቶኮል አዘጋጆች፣ ሲቪል ማህበራት እና የመሳሰሉት የዘርፉ ቁልፍ ተዋናይ አካላት ዘርፉን በማስተዳደር እና የሳይበር ጥቃትን ከመከላከል አኳያ ከመንግስታት በተጨማሪነት ጉልህ ሚና አላቸው፡፡

የኮምፒዩተር ወንጀል በኢትዮጵያ

መረጃ የማግኘት እና የማሰራጨት መብት በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 29 ስር ጥበቃ የሚደረግለት መብት ቢሆንም የሀገር ደህንነት እና የህዝብን ሰላም እና ጤና ለመጠበቅ ሲባል በህግ ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል ከህገመንግስቱ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል። በዚሁ መሰረት በአገራችን የህግ ሥርአት በኮምፒዩተር ሥርአት አማካይነት የሚፈፀሙ ህገወጥ የመረጃ ተደራሽነት፣ ማዛባት፣ ጠለፋ እና ማጥፋት ተግባራት የተከለከሉ እና በወንጀልነት የተፈረጁ የሚያስቀጡ ድርጊቶች ጭምር ናቸው፡፡

የሳይበር ጥቃት የሀገራትን ሉአላዊነት የሚጥስ እና ከአንድ የአለማችን ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በቀላሉ የሚፈፀም እና የአለምን ሰላምና ደህንነት የሚነሳ አደገኛ አለማቀፍ ወንጀል ነው፡፡ ይህ የሳይበር ጥቃት በህጋችን የኮምፒዩተር ወንጀል ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደነገገውም በ1996 ዓ.ም. በወጣው የወንጀል ህግ ከአንቀጽ 706 እስከ 711 ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ድንጋጌዎች ብቻቸውን በየግዜው እየተወሳሰበ የመጣውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የወንጀል ተጋላጭነት በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ በአዲስ መልክ እራሱን ችሎ በአዋጅ እንዲሸፈን ለማድረግ በማሰብ በኮምፒዩተር ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 958/2008 በዝርዝር ተደንግጎ ወጥቷል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው ይሄው ህግ ሲሆን ቀጥለን ዋና ዋና የወንጀሉን ድንጋጌዎች ባጭሩ የምንቃኝ ይሆናል፡፡

• ህገወጥ ደራሽነት (አንቀጽ 3) ይኸውም ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ሥርዓት፣ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ኔትዎርክ ደራሽነት በከፊልም ሆነ በሙሉ ማግኘት ነው፡፡
• ህገወጥ ጠለፋ (አንቀጽ 4)- ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ ይፋዊ ያልሆነን የኮምፒዩተር ዳታ ወይም የዳታ ፕሮሰሲንግ አገልግሎት መጥለፍ ነው፡፡

• በኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ጣልቃ መግባት (አንቀጽ-5) -ያለ ፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን በማስገባት፣ በማሰራጨት፣ በማጥፋት ወይም በመለወጥ የኮምፒዩተር ሥርዓትን ወይም ኔትወርክን መደበኛ ተግባር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ማደናቀፍ፣ ማወከ፣ ማውደም ወይም እንዲቋረጥ ማድረግ ነው፡፡

• በኮምፒዩተር ዳታ ላይ ጉዳት ማድረስ (አንቀት 6)- ሆነ ብሎ ያለፈቃድ ወይም ከተሰጠው ፈቃድ ውጪ የኮምፒዩተር ዳታን መለወጥ፣ ማጥፋት፣ ማፈን፣ ትርጉም እንዳይኖረው ወይም ጥቅም እንዳይሰጥ ወይም ለሕጋዊ ተጠቃሚዎች ተደራሽ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው፡፡

• ከኮምፒዩተር መሣሪያና ዳታ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ወንጀሎች (አንቀጽ 7)- በኮምፒዩተር ሥርዓት በኮምፒዩተር ዳታ ወይም በኔትዎርክ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ እየታወቀ ለዚህ ዓላማ ተብለው የተመረቱ ወይም የተሻሻሉ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችን ሆነ ብሎ በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ነው፡፡

• የኮምፒዩተር ዳታን ወደ ሐሰት መለወጥ (አንቀጽ 9)- የሌላን ሰው ጥቅም ለመጉዳት ወይም ለራስ ወይም ለሌላ ሰው ያልተገባ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ ሕጋዊ ውጤት ያለውን ወይም ሊኖረው የሚችለውን የኮምፒዩተር ዳታ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም ሐሰተኛ የኮምፒዩተር ዳታ ማዘጋጀት ወይም በዚሁ መገልገል ነው፡፡

• በኮምፒዩተር አማካኝነት የሚፈፀም የማታለል ወንጀል (አንቀጽ 10)- አሳሳች የኮምፒዩተር ዳታዎችን በማሰራጨት፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት በመጠቀም፣ ሌላውን ሰው አታልሎ የራሱን ወይም የሶስተኛ ወገንን ማንኛውም ጥቅም የሚጎዳ ድርጊት እንዲፈፅም ማድረግ ነው፡፡
Forwarded from Law forum (marye kasse)
• የኤሌክትሮኒክ ማንነት ስርቆት (አንቀጽ 11)- የማታለል ወንጀል ለመፈፀም ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት የሌላን ሰው የኤሌክትሮኒክ ማንነት የሚያረጋግጥ ዳታ ያለባለቤቱ ፈቃድ በኮምፒዩተር ሥርዓት አማካኝነት ማምረት፣ ማግኘት፣ መሸጥ፣ ይዞ መገኘት ወይም ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡
እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች መፈፀም በህጉ ለየወንጀል አይነቶቹ የተደነገገውን በመደበኛ አፈፃፀም እስከ 5 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና በገንዘብ ቅጣት የሚያስቀጣ ሲሆን በከባድ ሁኔታ የተፈፀመ ሲሆን ማለትም ወንጀሎቹ የተፈፀሙት ፡-
• ለወታደራዊ ጥቅም ወይም ለዓለም አቀፍ ግንኙነት ሲባል በሚመለከተው አካል ጥብቅ ምስጢር ተብሎ በተሰየመ የኮምፒዩተር ዳታ ወይም ዳታው በሚገኝበት የኮምፒዩተር ሥርዓት ወይም ኔትዎርክ ላይ ከሆነ ወይም
• አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ወይም ሀገሪቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ በምትገኝበት ወቅት ከሆነ
• በቁልፍ መሠረተ ልማት ላይ ከሆነ
• በሕግ የሰውነት መብት ለተሰጠው ተቋም አገልግሎት ብቻ በሚውል የኮምፒዩተር ሥርዓት ላይ ከሆነ እና
በመሰል ሁኔታዎች በመፈፀሙ ወንጀሉ ከባድ በሆነበት ጊዜ ቅጣቱ እንደ ወንጀል አይነቶቹ ከብዶ እንዳደረስው ጉዳት እና አፈፃፀሙ እየታየ እስከ 25 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና እስከ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሚደርስ መቀጮ የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡

ማጠቃለያ
በጥቅሉ የኮምፒዩተር ወንጀል በአገር ሰላም እና ደህንነት ብሎም ምጣኔ ሀብታዊ እና ማህበራዊ አድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ወንጀል ስለሆነ ሁሉም ሰው ይሄን አውቆ ከዚህ ወንጀል እራሱን ማራቅ እና ተፈፅሞም ሲገኝ ከህግ አካላት ጋር በመተባበር ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ እና ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ፣ ምርመራ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተጠያቂነት ስርአትን ለመዘርጋት በወጣው ደንብ ቁጥር 143/2015 ዙሪያ በቀን 20/09/2016 ዐ.ም ስልጠና ሰጠ!!! በመድረኩም ከተለያዩ የሲቪክ ማህበራት፣ ማለትም፣ ከሴቶች፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ ከወጣቶችና ከአረጋውያን አደረጃጀቶች፣ የተወጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የደንቡን አላማና አስፈላጊነት፣ የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ፣ ምርመራ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተጠያቂነት ስርአትን እንዲሁም በደንቡ የተቋቋመውን የስራ ክፍል አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚ መሆኑ ገልጸው በቀጣይ መሰል ስልጠናዎች በስፋት እንዲሰጡ ሃሳብ ሰጥተዋል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!
የቦሌ ክ/ከተማ የህግ ስርፀት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከ ክፍለከተማው ምክር ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ስለ "የወንጀል ህግ ምንነት እና መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቦች በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ" በሚል እርእስ ዙሪያ ከቀን 19/09/2016 - 20/09/2016 ዓ.ም ስልጠና ሰጠ። በመድረኩም ከክፍለከተማው የተወጣጡ ወጣቶችና ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን ስለ ወንጀል ህግ ምንነት፡ አላማ፡ የተሳታፊነት ደረጃ፡ የወንጀል ህግ መሰረታዊ መርሆዎች አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን አስተማሪ ውይይቶ እና ምላሾች ተሰጥተዋል። ስልጠናው ቀጣይነት ያለው ሲሆን ተሳታፊዎችም ስልጠናው ጠቃሚ እንደነበር እና መሰል ስልጠናዎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።
Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ግንቦት 23 ቀን 2016 ዐ.ም በፌደራሉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ዙሪያ የንቃተህግ ስልጠና ሰጠ!!! በመድረኩ 300 ገደማ የሚሆኑ የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአረጋውያንና የወጣቶች ተወካይ የሆኑ የክ/ከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስለኪራይ ውል ምንነት፣ ዘመን፣ መታደስ፣ መቋረጥ እንዲሁም በአዋጁ ስለሚቋቋሙ ተቋማት ስልጣንና ሃላፊነት ግንዛቤ ተፈጥሯል። በተጨማሪም ተሳታፊዎች የነዋሪው ተወካይ እንደመሆናቸው መጠን ለአዋጁ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን ሚና ለመጫወት ከአሁኑ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተበረታትተዋል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!!!!!!