ሰላም!
አዲስ የታተሙ የኢትዮጵያ የብር ኖቶች ሥራ ላይ ለማዋል በወጣው መመሪያ ቁጥር ከማዳ/2/2013 አንቀጽ 6(4) መሠረት ከብር 5000 በላይ ገንዘብ የሚለወጠው በደንበኛው ስም በተከፈተ የተቀማጭ ሂሳብ በኩል ብቻ እንደሚሆን ተደንጓል።መመሪያዋን እንድታነቧት ከታች አስቀምጬላችኋለው።
ሰናይ 13/1/2013 ዓ.ም!

ወድ የቻናላችን ተከታታዮች በዛሬው እለት አዲሱን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ መመሪያ ቁጥር 30/2013ን በpdf አዘጋጅተናል፡፡ መመሪያውን አውርዳችሁ እንድታነቡት በአክብሮት እንጠይቃለን
ስለሕክምና ስህተት
በዚህ አጭር ጽሑፍ የሕክምና ስህተት ምን ማለት ነው በሀገራችን ሕግስ እንዴት ተካቷል የሕክምና ስህተት ተፈጽሟል የሚባለው ምን ምን ሲሟላ ነው የሚሉትን ነጥቦች ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
የሕክምና ስህተት ሕግ ምን ማለት ነው?
የሕክምና ስህተት ሕግ(MedicalMalpracticeLaw) ዶክተሮች ወይም ሌላ የሕክምና አገልግሎት ሰጪ አካላት የሕክምና አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በታማሚው ላይ በችልተኝነት ለሚያደርሱት ጉዳት ያለባቸውን ተጠያቂነት የሚገዛ ሕግ ነው፡፡ ይህ የሕግ ዘርፍ ከሀገር ሀገር የተለያየ ይዘት ቢኖረውም በአብዛኛው ሀገር ግን በሕክምና ስህተት ግለሰቦች ለሚደርስባቸው ጉዳት ጉዳቱን ያደረሰው አካል ተጠያቂ የሚሆንበት የአሠራር ሥነ ሥርዓት አላቸው፡፡ አንድ የሕክምና ባለሙያ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ በተመሳሳይ ጉዳይ ሌሎች የሕክምና ባለሙያዎች ሊያከብራቸው ወይም ሊፈጽሟቸው የሚገባውን መደበኛ ጥንቃቄ (“standard of care”) ሊያከናውን ወይም ሊከተል ባለመቻሉ ምክንያት በታማሚው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ የሕክምና ባለሙያው ለጥፋቱ ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር የሕክምና ስህተት ሕግ ይባላል፡፡
ሁሉም ስህተቶች የሕክምና ስህተት አይባሉም፡፡ አንድ ታካሚ የሚጠብቀውን የሕክምና ውጤት አላገኘሁም በማለት የሕክምና ባለሙያን ለመክሰስ አይችልም፡፡ በአጭሩ የሙያ ስህተት የሚባለው በአንድ የሙያ ዘርፍ የተሠማራ ባለሙያ ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ሊከተላቸው ወይም ሊመራባቸው የሚገባውን የሙያ ደንቦችና መመሪያዎች አውቆ ወይም በቸልተኝነት ሳያከብር መቅረት ወይም የሙያ ደንቦችን ባለማክበሩ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2031 እና 2035 ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም አንድ የሕክምና ባለሙያ የሕክምና ስህተት ፈጽሟል ለማለት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
1. የአካሚና ታካሚ ሕጋዊ ግንኙት መኖሩን ማረጋገጥ
የሕክምና ስህተት አለ ብሎ ክስ ለመመሥረት የአካሚና ታካሚ ሕጋዊ ግንኙነት መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡በሕክምና ባለሙያ እና በታካሚ መካከል ለሚኖረው ግንኙነት መሠረቱ የሕክምና አገልግሎት ውል ነው፡፡ታካሚው ከሕክምና ባለሙያው ወይም ከሕክምና ተቋሙ ጋር የሚኖረው የሕክምና ግንኙነት የሚመሠረተው በውል እንደሚሆን የፍትሐብሔር ሕግ ከቁጥር 2639-2652 ያስረዳል፡፡ በአንድ የመዝናኛ ሥፍራ አንድ ዶክተር በሰጠዎት መድኃኒት ምክንያት ጉዳት ደርሶብኛል ለማለት አይቻልም፡፡ በሕክምና ተቋሙ ካርድ አውጥተው የሕክማ ባለሙያውን አግኝተውት እንደሆነ ግን የአካሚ ታካሚ ሕጋዊ ግንኙነት እንዳለ ማስረጃ ይሆናል፡፡
ይቀጥላል
ፌናን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት፣ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 እንዲሁም ተከታትለው በወጡት ማሻሻያዎች አዋጅ ቁጥር 67/2012 እና አዋጅ ቁጥር 70/2012 ዙሪያ በራሪ ጽሑፍ በማዘጋጀት ከታች አስቀምጬላችኋለው።ለበለጠ መረጃ አዋጆቹም ሊያስፈልጋችሁ ስለሚችል 3ቱንም አዋጆች ከታች ታገኟችኋላችሁ።
ሰናይ 16/2/2013 ዓ.ም!

ጤና ይስጥልኝ፡-
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚያስፈጽማቸውንና በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 ስለተጠቀሱት አምስት የምርጫ ዓይነቶች (የሕዝበ-ውሳኔን ጨምሮ) በባለፈው ጽሑፋችን መጠነኛ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሞከርን ሲሆን በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የምርጫ ማስፈጸሚያ አደረጃጀቶችን የምንመለከት ይሆናል፡፡
ቦርዱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በሁሉም ክልሎችና ከዚያ በታች ባሉ የአስተዳደር እርከኖች በማደራጀት አስፈላጊ የሆኑ የጽ/ቤት ሥራዎችን የሚያሰራ ሲሆን እንደዚሁም የምርጫ ጣቢያዎች በአግባቡ ተግባራቸውን ስለማከናወናቸው የሚቆጣጠርና ከምርጫ ጣቢያ የሚላኩ የምርጫ ውጤቶችን በመደመር አሸናፊዎችን ለይቶ ጊዜያዊ ውጤት ለሕዝብ ይፋ የሚያደርጉ የምርጫ ክልሎችን እንደዚሁም የተሰጠውን የድምጽ ቆጠራ በማካሄድ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤትን የሚያሳውቅና ለሚከሰቱ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥና የማስተካከያ እርምጃ የሚወስዱ እና ታዛቢዎች የሚገኙባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚኖሩ ከተመለከትን ለወደፊቱ ስለምርጫ አፈጻጸም የምንመለከተው ይሆናል፡፡
ደረጀ ማርቆስ
ጥቅምት 17/2013 ዓ.ም