የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from አለ ሕግ
የጋብቻ ምዝገባ-ግለሰባዊ ጥቅሞች

✅ጋብቻ ለመከሰቱ ህጋዊ ማስረጃ በመሆን

✅ጋብቻዉ ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ፣

✅የተጋቢዎቹን ዝምድና እና ግንኙነት ለማረጋገጥ፣

✅የጋብቻ ውጤት ለሆኑት ህፃናት በቤተሰብነት የመጠበቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ፣

✅ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ፣

✅ለቤተሰብ ድጎማ ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ፣

✅ከተጋቢዎች አንዳቸው ቢሞቱ ቋሚው የኢንሹራንስ ጥያቄን ለማቅረብ፣

✅ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆችን አስተዳደግ ለመወሰን፣

✅ወደ ውጪ ሃገር ለመጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፈቃድን ለማቅረብ፣

✅የልጆችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ፣

✅የራስን ልጆች ህጋዊነት ለመመስረት እንዲሁም ከሌላ የተወለዱትን ለማስመዝገብ፣

✅የዜግነት ቅያሬን ለመጠየቅ፣

✅ጋብቻዉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ቦታ በማሳወቅ ህጋዊ መረጃ በመሆን፣

Alternative legal enlightenment/ALE
አማራጭ የሕግ እውቀት🔴

ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
5️⃣መሠረታዊ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ነጥቦች
የኮሪደር ልማቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የስራ ሰአት ቢያንስ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንዲሆን
Forwarded from የሕግ ዜና
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016
የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች

• የአዋጁ አስፈላጊነት
👇👇👇👇👇👇👇
በሀገራችን አሁን ባለው ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እና በዜጎች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንገብጋቢ እና መሰረታዊ የመብት ጉዳይ እንደመሆኑ መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ንረት በአግባቡ መቆጣጠርና ማስተዳደር በማስፈለጉ አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል። በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ያለው እና የአከራዮችን እና ተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ ወጥቷል።

• የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ከአንድ ክፍል ጀምሮ ለመኖሪያ አገልግሎት የተከራየና ገንዘብ የሚከፈልበትን ማንኛውም ቤት ላይ ሲሆን በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡

• ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል

ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በወረዳ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት፡፡ የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። የአከራይ እና ተከራይ ውሉን ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ሁሉም ወረዳዎች ፅ/ቤቱ የማረጋገጥና የመመዝገብ ስራውን ጀምሯል፡፡ ይህ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል አከራይና ተከራይ በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል።
የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል እስከ ሶስት ወር የሚደርስ በውሉ ላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ ያስቀጣል፡፡
ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በፅሁፍ የተደረገ የኪራይ ውል ካልሆነ በስተቀር የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም። እንዲሁም ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል ሲገባ አከራይ ከተከራይ ላይ ሊጠይቅ የሚችለው ቅድሚያ ክፍያ ከ2 ወር የቤቱ የኪራይ ዋጋ ሊበልጥ አይችልም። በዚህ የውል ዘመን ውስጥ ተከራይን ከቤት ማስወጣትም ሆነ በአዋጁ ከሚፈቀደው አግባብ ውጭ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም፡፡

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ

የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል እንጂ አዲስ የሚወጣ የቤት ኪራይ ዋጋ አሁን ላይ የለም።
አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ በአመት አንድ ጊዜ በሰኔ ወር ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ብቻ ነው።
አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል። ነገር ግን አከራይ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤት ያለአገልግሎት ከስድስት ወር በላይ እንዲቀመጥ ካደረገ ቤቱ ቢከራይ ሊከፍል ይችል የነበረውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተሰልቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ


1. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣
2. ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት
3. የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠት ነው።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

1. የቤት ኪራይ በውሉ በተመለከተው የመክፈያ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ከ15 ቀን ካሳለፈ
2. ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣
3. ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣
4. የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ
5. በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈፅም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀምበት ከሆነ፣
6. አስቦ ወይም በቸልተኝነት በቤቱ ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት ከተፈጠረ ተከራይ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ቤቱን እንዲለቅ በህግ ሊገደድ ይችላል።

በውል ምዝገባ ወቅት ስለሚቀርቡ ሰነዶች

ማንኛውም አከራይ እና ተከራይ ለምዝገባ ሲቀርብ ፡-
1. በህግ አግባብ የተዘጋጀ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሰነድ፤
2. የአከራይና ተከራይ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ተመጣጣኝ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ (የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ሕጋዊ ውክልና የሁለት ምስክሮች የታደሰ መታወቂያ ኦሪጅናልና ኮፒ)
3. አከራይ የመኖሪያ ቤቱን ለማከራየት የሚያስችል መብት እንዳለው የሚያሳይ ህጋዊ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
በማንኛውም ምክንያት የተሻሻለ ውል በ30 ቀናት መመዝገብና መረጋገጥ አለበት፡፡

የተከለከሉ ተግባራት እና ጥቆማ የሚቀርብባቸው ጉዳዮች

1. የተመዘገበ ውል ሳይኖር የመኖሪያ ቤት ማከራየት፤
2. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ሳያስመዘግቡ መከራየትና ማከራየት ወይም በአዋጁ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ አሳልፎ ማስመዝገብ፤
3. በተመዘገው ውል ላይ ከተቀመጠው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በላይ ክፍያ መፈጸም
4. በአዋጁ ከተፈቀደው ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ወይም ከ2 ወር በላይ የቅድመ ክፍያ እንዲፈጸም ማስገደድ፤     
5. በአዋጁ ከተፈቀደው ውጪ የቤት ኪራይ ዘመን ውል ማቋረጥ፤
6. በአዋጁ ለአከራይ የተሰጠውን ማበረታቻ ያለአግባብ ለመጠቀም ሀሰተኛ መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረብ፤
7. መኖሪያ ቤቱ ከመኖሪያነት ዓላማ ውጪ አገልግሎት ወይም ለወንጀል መፈጻሚያነት ወይም ለወንጀል ተግባር ላይ እየዋለ ከሆነ፤
8. አዋጁ ከሚፈቅደው ውጪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ከቤት ማስወጣት፤
9. በአዋጁ የተቀመጠውን የማስታወቂያ ወይም የማስጠንቀቂ ጊዜ ሳይሰጥ ውል ማቋረጥ፤
10. በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የሆነ የኤሌክትሮኒክስ መንገድ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ አለመፈጸም፤
11. ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ መኖሪያ ቤት ያለአገልግሎት እንዲቀመጥ ማድረግ፤

ስለ ቁጥጥር

ጽህፈት ቤቱ ቁጥጥር የሚያደርገው ለቁጥጥር በተመደበ ባለሙያ ይሆናል፤ ተቆጣጣሪ ባለሙያው በመንግሥት የሥራ ሰዓት ተቆጣጣሪ መሆኑን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የቁጥጥር ተግባሩን ይፈጽማል፤ የቁጥጥር ሥራ የሚከናወነው በተናጠል በአንድ ባለሙያ ሳይሆን በቡድን ከአንድ በላይ ተቆጣጣሪዎች በመሆን ነው፡፡
#አለሕግ #Alehig
@NegereHig
https://t.me/NegereHig
👍2
የስጦታ ውል አፈፃፀም ሥነሥርዓት
የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብትን የመሰጥ ስጦታ ውል በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ አሠራር ዓይነት ካልተደረገ ፈራሽ እንደሆነ በፍትሃብሄር ሕግ አንቀጽ 2443 ላይ ተመላክቷል፡፡ግልጽ ኑዛዜ የሚደረገው ኑዛዜ ተነዛዡ እየተናገረ ማናቸውም ሌላ ሰው ወይም ተናዛዡ ራ የሚጽፈው ሲሆን ሕጋዊ አፈፃፀም ሥረዓቱም በፍትሃብሄር ሕግ ቁጥር 881 ላይ ተመላክቷል፡፡
የግልጽ ኑዛዛ አደራረግ ሕጋዊ ሥርዓት፡-
1. ኑዛዜው በተናዛዡ እና በአራት ምስክሮች ፊት ተነቦ ይኸው ሥርዓት መፈፀሙ በኑዛዛ ሰነዱ ላይ መጠቀስ አለበት፤
2. ኑዛዜው የተደረገበት ቀን በኑዛዛው ሰነድ ላይ መጠቀስ አለበት፤
3. ተናዛዡ እና አራቱም ምስክሮች ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም የአውራ ጣት ምልክታቸውን በኑዛዛው ሠነድ ላይ ማኖር አለባቸው
የስጦታ ውል በውልና ማስረጃ ያልተደረገ ቢሆንም በፍታብሄር ሕግ ቁጥር 2443 እና 881 መሠረት የግልጽ ኑዛዛ አደራግ ሕጋዊ ሥርዓትን ተከትሎ ከተዘጋጀ በሕግ ፊት የፀና ይሆናል፡፡
በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች

• የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ከአንድ ክፍል ጀምሮ ለመኖሪያ አገልግሎት የተከራየና ገንዘብ የሚከፈልበትን ማንኛውም ቤት ላይ ሲሆን በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡

• ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል

ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በወረዳ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት፡፡ የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። የአከራይ እና ተከራይ ውሉን ከሰኔ 1/2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች ፅ/ቤቱ የማረጋገጥና የመመዝገብ ስራውን ተጀምሯል፡፡ ይህ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል አከራይና ተከራይ በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል እስከ ሶስት ወር የሚደርስ በውሉ ላይ የተጠቀሰውን ገንዘብ ያስቀጣል፡፡

ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በፅሁፍ የተደረገ የኪራይ ውል ካልሆነ በስተቀር የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም። እንዲሁም ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል ሲገባ አከራይ ከተከራይ ላይ ሊጠይቅ የሚችለው ቅድሚያ ክፍያ ከ2 ወር የቤቱ የኪራይ ዋጋ ሊበልጥ አይችልም። በዚህ የውል ዘመን ውስጥ ተከራይን ከቤት ማስወጣትም ሆነ በአዋጁ ከሚፈቀደው አግባብ ውጭ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም፡፡

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ

የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል እንጂ አዲስ የሚወጣ የቤት ኪራይ ዋጋ አሁን ላይ የለም።

አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ቢሮ በአመት አንድ ጊዜ በሰኔ ወር ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ብቻ ነው።

አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል። ነገር ግን አከራይ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤት ያለአገልግሎት ከስድስት ወር በላይ እንዲቀመጥ ካደረገ ቤቱ ቢከራይ ሊከፍል ይችል የነበረውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተሰልቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ

1. የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣
2. ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት
3. የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠት ነው።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

1. የቤት ኪራይ በውሉ በተመለከተው የመክፈያ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ከ15 ቀን ካሳለፈ
2. ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ውል በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ አስገዳጅ ህግ እንደሚቆጠር ግልፅ ነው። ነገር ግን በቅድሚያ የሚደረገው የውል ስምምነት ከህግና ከሞራል የሚፃረር መሆን የለበትም። በዚሁ መሰረት ከውል ጋር በተያያዘ ተዋዋይ የሆነ ወገን ውሉን የፈፀምኩት ተገድጄና ከፍላጐቴ ውጭ ነው በሚል የሚያደርገውን ክርክር ዳኞች (ፍ/ቤቶች) የዚህን ተዋዋይ ወገን እድሜ፣ ጾታ፣ የተዋዋይ ወገኖችን ልዩ ግንኙነት እና አጠቃላይ ተያያዥነት ያላቸው አኳኋኖች ጭምር መሰረት በማድረግ መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1706/1/,1678/ሀ/,1809 ድንጋጌዎች መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 12 ላይ አስገዳጅ ወሳኔ ሰጥቶበታል።
https://t.me/ethiolawtips
❤1
የሞት ፍርድ በኢትዮጵያ እንዴት ይፈጸማል? ምን ያህልስ ተቀባይነት አለው?
***
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሞት ቅጣት እየጨመረ መሆኑን ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ እአአ በ2023 ብቻ 1153 የሞት ቅጣት መመዝገቡን አስታውቋል።
ይህ አሃዝ በ2022 ከነበረው 883 የሞት ፍርድ አንጻር የ31 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለጸው። አምነስቲ በ2015 ብቻ 1634 ከመዘገበ በኋላ 2023 ከፍተኛው የሞት ቅጣት የተላለፈበት ዓመት ሆኗል።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት በኢትዮጵያ ያለውን የሞት ቅጣት ቁጥር በይፋ አላስቀመጠም። ሆኖም አለፍ ገደም እያለ በአገሪቱ በተለያዩ ወቅቶች የሞት ቅጣት መተላለፉ ተዘግቧል።
በኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ በምትገኘው ሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከወራት በፊት ሁለት ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው የእንጀራ እናት ሞት ተፈረዶባታል። ጥፋተኛ ሆና በተገኘችው ግለሰብ ላይ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትነው- ቢቢሲ።
ከሰሞኑ ከአባቱ ጋር በተፈጠረ የጥቅም ግጭት በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ አባቱን፣ እናቱን፣ አጎቱ እና የ9 ዓመት ታናሽ ወንድሙን የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። ውሳኔውን ያሳለፈው የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው - ፋና።
በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ደከ ኦዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እናቱን በቢላዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ የገደለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ውሳኔውን ያሳፈው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው- ፋና።
በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሕግ ክፍል መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር መሐሪ ረዳኢ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሞት ቅጣት የሚጣልባቸው ጉዳዮች “በጣም ውስን” መሆናቸውን ይገልጻሉ።
ጭካኔ እና ነውረኝነት በተሞላበት መንገድ ሆን ተብሎ የሚደረግ ግድያ እና ከአገር ክህደት ጋር በተያያዙ የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ የሞት ቅጣቱ እንደሚወሰን ሕጉን ጠቅሰው ለቢቢሲ አስረድተዋል።
“በተቻለ መጠን አጥብቦ ነው [የሞት ፍርድ ቅጣት] ሕጉ የሚተቀረጸው” የሚሉት የሕግ መምህሩ፣ በዚህ ምክንያትም ተፈጸማኒቱ አነስተኛ ነው።
ሕጉ አጥብቦ ከመቀረጹም በላይ ዳኞችም የሞት ቅጣት ሲያስተላልፉ ተከሳሽ የፍርድ ማቅለያ ምክንያቶችን ማቅረብ በማይችልበት ሁኔታ ነው። የወንጀለኛው ዕድሜም ከ18 ዓመት በላይ መሆን ይጠበቅበታል። “ከዚያ በታች ወንጀል በሚፈጸሙ ላይ [ቅጣቱ] አይጣልም።”
ብዙ ጊዜ የሞት ፍርድ ተላለፈ ተብሎ በመገናኛ ብዙኃን ይነገራል። ጉዳዩ እዚህ ጋር ያበቃ፤ የሞት ፍርዱ የሚፈጸም ቢመስልም ተጨማሪ ሂደቶች ይኖራሉ። ተከሳሽ ይግባኝ በማለት የተለየ ፍርድ ሊያገኝ ይችላል።
ይግባኙ ተቀባይነት አጥቶ ፍርድ ቤቱ የሞት ቅጣቱን ካጸና በኋላም በቀጥታ ወደ ማስፈጸም አይገባም። የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸም በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር መጽደቅ ይኖርበታል።
በቁጥር ብዙ ባይሆኑም በዚህ ሂደት ውስጥ አልፈው የሞት ቅጣት ተፈጻሚ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸውን ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ያስታውሳሉ።

ሆኖም ባለፉት 25 እና 30 ዓመታት ውስጥ የሚታወቁ የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው ጥቂት መሆናቸውን አንስተዋል። በቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ የመግደል ሙከራ አድርገው በተያዙት ከሱዳን የመጡ ናቸው በተባሉ አሸባሪዎች ላይ የሞት ቅጣት እንደተፈረደባቸው አስታውሰዋል።
“ጄኔራል ሃየሎም አርአያን የገደለው ሰው የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደተፈጸመበት አስታውሳለሁ። በተመሳሳይም ክንፈ ገብረመድኅንን [የቀድሞው የደኅንነት ኃላፊ ነበሩትን] የገደለው ሰው የሞት ፈርድ ተወስኖበነት እንደተፈጸመበት፣ የአልሻባብ ታጣቂዎችም ይመስለኛል ድሬዳዋ ወይም ጅግጅጋ በፈጸሙት ጥቃት ተይዘው እንደተፈጸመባቸው አስታውሳለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
በሞት ቅጣቱ ላይ ርዕሰ ብሔሮች ውሳኔ እንዲሰጡበት መደረጉ “የፖለቲካ ጉዳይ ነው” ይላሉ ተባባሪ ፕሮፌሰር መሐሪ።
የሰው ሕይወት ጉዳይ ስለሆነ “ድንጋጌዎችን ብቻ አይቶ ከተወሰነ እና ከተፈጸመ ከባድ ሊሆን ይችላል። . . . ለፍርድ ቤት ብቻ ሊተው አይገባም። ርዕሰ ብሔር የአገር ተወካይ ስለሆኑ እዚያ ድረስ ጸድቆ ነው መወሰን ያለበት ከሚል የመነጨ ይመስለኛል” ብለዋል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ርዕሰ ብሔሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጋቸው የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። በሞት ቅጣት አላምንም የሚል ርዕሰ ብሔር ከመጣ የሞት ቅጣት የተላለፈበት ግለሰብ ውሳኔው ተግባራዊ ሳይደረግበት ሊቀመጥ የሚችልበት ዕድል ይፈጠራል።
“ርዕሰ ብሔሮች በማጽደቁ ላይ እግር የመጎተት ነገር ስላለ አፈጻጸሙ አነስተኛ ነው” የሚሉት የሕግ ምሑሩ፣ “ለምሳሌ ፕሬዝዳንት ግርማ በነበሩበት ጊዜ የራሳቸው ፍልስፍና ስለነበራቸው ብዙም ሲያጸድቁ አልታየም። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅም ያጸደቁበትን [ጊዜ] አላስታወስም። ስለዚህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የርዕሰ ብሔር ውሳኔም ስላለበት . . . ቅጣቱ እየተፈጸመ አይመስለኝም።”
ፍርድ ቤት አንድ ተከሳሽ ሞት ይገባዋል ብሎ ወስኖ ይህን ውሳኔ ሲያሳልፍ ፍርዱን እንዲያጸድቅ ኃላፊነት የተሰጠው አካል [ርዕሰ ብሔር] በተለያየ ምክንያት አላጸድቅም ካለ ፍርደኛው የተጣለበት ቅጣት ተግባራዊ ሳይሆን እንዲቆይ ምክንያት ይሆናል።
“ሥርዓቱ እርስ በርስ የሚጠባበቅበት መንገድ አበጅቷል ተብሎ ነው የሚወሰደው። የሞት ቅጣት ያስፈልጋል የሚል ርዕሰ ብሔር ካለ ከፍርድ ቤት የሚመጣለትን እያጸደቀ እርምጃ ሊያስወስድ ይችላል። ተገቢ አይደለም የሚል ሲመጣ ደግሞ በተቀራኒው መሆኑ አይቀርም” ብለዋል።
ርዕሰ ብሔሩ የሞት ፍርዱ እንዲተገበር በፊርማቸው ካላረጋገጡ ወንጀለኛው ፍርደኛ ሆኖ ይቀመጣል። አንድ ሰው የተፈረደበትን የእስር ጊዜ 2/3ኛውን በማረሚያ ቤት ካሳለፈ በኋላ በሚያሳየው የባህሪ መሻሻል አመክሮ እንዲያገኝ የሚያስችለው የሕግ አግባብ አለ። ባህሪው ለውጥ ከሌለው ግን ሙሉውን የእስራት ጊዜ በማረሚያ ቤት እንዲያሳልፍ ይገደዳል።
ይህ ግን የሞት ቅጣት ለተላለፈበት ሰው አይተገበርም። ፍርደኛው በሞት እንዲቀጣ ርዕሰ ብሔሩ ባይፈርሙ እንኳ ቀሪውን ሕይወቱን በእስር አሳልፎ “አስከሬኑ ከማረሚያ ቤት ይወጣል ማለት ነው።” #BBC Amharic
👍2