የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት በአንቀጽ 2ዐ (6) ይግባኝ ከመሠረታዊ መብቶች አንዱ አድርጎ ያስቀመጠዋል፡፡ እንዲሁም በአንቀጽ 9 (4) ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች የሐገሪቱ ሕግ አካል እንደሆኑ ይገልፃል፡፡
ይግባኝ መቼ እና እንዴት ይቀርባል ?
ይግባኝ የሚጠየቀው በመጀመሪያው ፍርድ ወይም ውሳኔ ቅር የተሰኘ አካል እነደሆነ ተመልክተናል፡፡ ይግባኝ የሚቀርብባቸው አቤቱታዎች በመጨረሻ ፍርድ ወይም ውሣኔ ያላገኙ ጉዳዮች ( Inter-Locutory Issues ) መሆን የለባቸውም፡፡ ባለጉዳዮች የተበጣጠሱ ጉዳዮችን ይዘው ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የሚመጡ ከሆነ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ላይ ጫና ከማሳደሩም በላይ ፍ/ቤቶቹ በሚሰጡት ቁጥር ስፍር የሌለው ትዕዛዝ በስር ፍ/ቤቶች እየተካሄደ ያለን የፍትህ ሥርዓት ሊያውከው ስለሚችል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪInter-Locutory ጉዳዮች ይግባኝ የማይቀርብባቸው ለጊዜው እንጂ ከዋናው ጉዳይ ጋር ተጠቃለው ይግባኝ ሊባልባቸው እንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 32ዐ /3/ ላይ ተመልክቷል፡፡በወንጀል ጉዳይ ይግባኝ የሚል አካል ፍርዱ በተሰጠ በ15 ቀን ውስጥ በፅሁፍ ማስታወቅ እንዳለበት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 187 (1) የተደነገገ ሲሆን ይግባኝ ባዩ የፍርዱ ግልባጭ በደረሰው በ3ዐ ቀን ውስጥ ቅሬታውን ( የይግባኝ ማመልከቻውን ) አዘጋጅቶ መላክ አለበት፡፡
በፍትሐብሔር ጉዳይ ሲሆን ግን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 123 /2/ እንደተመለከተው ፍርዱ በተሰጠ በ6ዐ ቀን ውስጥ ይግባኙ ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት መቅረብ መቻል አለበት፡፡ በሕጉ የተፈቀደው ጊዜ ካለፈ በወንጀልም ሆነ በፍትሃብሔር በቂ ምክንያት በማቅረብ ሲፈቀድ ነው ይግባኝ ሊቀርብ የሚችለው፡፡
በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት መሠረት ይግባኝ መብት ቢሆንም በጊዜ እና በእርከን ሊገደብ እንደሚችል ነው ዳኛ ፀጋይና ዳኛ ሽመክት የሚገለፁት፡፡ በጊዜ የተባለው ከላይ የተገለፀው ሲሆን በእርከን የተገደበው ደግሞ ከአንድ ጊዜ በላይ ይግባኝ ማለት የማይቻልበት ሁኔታ ስላለ ነው፡፡ ይህም ማለት ይግባኙን የተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ካፀናው ወይም ይግባኙን ካልተቀበለው ይግባኝ ባዩ ለበላይ ፍ/ቤት በድጋሚ ይግባኝ የማለት መብት አይኖረውም፡፡ በአጠቃላይ በተለይ በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች አንድ ፍርድ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው እንዲታይላቸው የማድረግ መብት እንዳላቸው ያረጋግጣል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሕገ መንግስታዊ መብት ለሁለተኛ ጊዜ ይግባኝ ማቅረብን የሚያጠቃልል እንዳልሆነ መገንዘብ ያሻል፡፡ይግባኝ ባዩ ያለው አማራጭ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚል እምነት ካለው ወደ ሰበር ሰሚው ፍ/ቤት ብቻ ማቅረብ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ሌላው ተከራካሪ ወገን ቅጣት አንሷል ብሎ የይግባኝ አቤቱታ ካቀረበ እና የበላይ ፍ/ቤት አቤቱታውን ተቀብሎ ቅጣቱን ከጨመረ ተቀጪው በዚሁ ውሣኔ ላይ ብቻ ለአንድ ጊዜ ወደ ቀጣዩ የበላይ ፍ/ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የይግባኝ መብት አንድ እርከን ብቻ ነው የሚለው የይግባኝ ሥርዓት ቁጥሩ ላይበተለያዩ ክልሎች የሚለያይ ቢሆንም አሰራሩ በተመለከተ ተመሳሳይ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ዳኛ ፀጋይ አስማማው ይናገራሉ፡፡
ሁለተኛ ይግባኝ ማለት የሚፈቀደው ውሣኔውን ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ካሻሻለው ብቻ እንደሆነ ነው የሚገልፁት ፡፡አዋጅ ቁጥር 25/88 የሥር ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ወደሚቀጥለው ፍ/ቤት ይግባኝ ከተባለበት ያ ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን ካሻሻለ ሁለተኛ ይግባኝ ማለትን እንደሚፈቅድ ይጠቅሳሉ ፡፡ ይሁን እንጂ በተግባር ሲታይ ሕጉ ግልፅነት የሚጎድለው ቢሆንም ለሁለተኛ ጊዜ ይግባኝ የሚሉ ባለጉዳዮች ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔውን ያሻሻለው ይግባኝ ባዩን በሚጠቅም መልኩ ከሆነ ይኸ ሰው እንደገና ይግባኝ የማለት መብት ሊኖረው እንደማይገባው ነው፡፡
ይግባኝ እና የዳኞች ተጠያቂነት
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 78 ነፃ ፍ/ቤት መቋቋሙንና አንቀጽ 79 ደግሞ ዳኞች ሥራቸውን ያለምንም ጣልቃ ገብነት በነፃነት ማከናወን እንዳለባቸው ይገልፃል፡፡ እንደ ዳኛ ሽመክት አሰፋ አገላለፅ ለተቋሙና ለዳኞች የተሰጠው ነፃነት አለጠያቂ እንዳሻቸው እንዲሆኑ ሳይሆን ከማንም ጣልቃ ገብነት ነፃና ገለልተኛ ሆነው በሕግና በሕግ ብቻ ተገዝተው ትክክለኛና አግባብነት ያለው ዳኝነት እንዲሰጡ ለማስቻል ያለመ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ነፃ ስለተባለ በቻ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ስለዚህ የዳኝነት አካሉ ያለበትን ተጠያቂነት ከሚገለፅባቸው መንገዶች አንዱ ከይግባኝና ከይግባኝ ስርዓት ጋር የተያያዘ መሆኑን በአፅንኦት ያሰምሩበታል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ ወይም ውሳኔ ተመልሶ ማንም የማያያው ከሆነ ዳኛው ሆነ ችሎቱ እንደወደዱ ይሰራሉ ማለት ነው ራሳቸውንም አያርሙም፡፡ ሂደቱ በይግባኝ እንዲታይ የማይፈቅድ ከሆነ ክፍተት ይኖራል፡፡ ስህተቶች ሳይታረሙ ያልፋሉ፡፡ የዚህ ውጤት ፍትህ በማንገስ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ ስርዓት ዳግም የሚመረመርና የሚታይ ከሆነ ደግሞ የሥር ፍ/ቤት የተሳሳተ ውሳኔእየተሻረና እየተሻሻለ እንዲሄድ ስለሚያደርግ የተጠያቂነት መንፈስ እንዲሰርፅ ያግዛል፡፡ የስር ፍ/ቤት ለወደፊት ማረም ያለበትን ያርማል ያስተካክላል፡፡
የዳኝነት አካሉ የተጠያቂነት አሰራር ከዚህም ያለፈ እንደሆነ ነው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ አቶ ሽመክት የሚገልፁት፡፡ “በሕግና በአስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚያስጠይቅ ጉዳይ ካለም ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ያ እንዳለ ሆኖ ግን ዳኝነትን ዳኛው ራሱን እያረመ እንዲሄድ ማድረግ የተጠያቂነት አንዱ መገለጫ ነው፡፡ የዲሲኘሊን ወይም የሥነ-ምግባር ችግር ሲያጋጥም በሌላ መንገድ ተጠያቂ መሆን እንዳለ ሆኖ በይግባኝ በኩል ሥራው ተጠያቂነት ያለው ሥራ እንጂ ነፃ ነው ስለተባለ እንደተፈለገ የሚሰራ ያለመሆኑ ያመለክታል፡፡” በዚህ ጉዳይ ዳኛ ፀጋይም ሓሳቡን ይጋራሉ፡፡የይግባኝ ስርዓት ውሳኔዎች ጥራት እንዲኖራቸውና የስር ፍ/ቤቶች በጥንቃቄ እንዲሰሩ ያደርጋል የሚል እምነት አላቸው፡፡
👍1
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ!

የኢፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 27 ቀን 2016 ባፀደቀው የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 አንቀጽ-11 መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸው፡-

ሀ/ በቪዬና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ኮንቬንሽን ሚሲዮኖች፣ ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እስከሆኑ ድረስ እነዚህ ሚሲዮኖች፣  ዲፕሎማቶች ወይም የኩንሱላር ጽ/ቤቶች ወደ አገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፡
ለ/ በዓለም ዐቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ወደአገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች ፤
ሐ/ በፋይናንስ፣ በቴክኒክ፣ በሰብዓዊ ዕረዳታ ወይም በአስተዳደር ድጋፍ የዓለም አቀፍ ስምምነት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እስከተደረገ ድረስ የውጭ አገር መንግስት ወደ አገር የሚያስገባቸው ዕቃዎች፣
መ/  በጉምሩክ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ እስከተደረገ ድረስ መንገደኛው ይዞት የሚመጣ የግል መገልገያ እቃ፣
ሠ/  ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወስነው እስካልበለጠ ድረስ ተመላሾች ወደ አገር የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣
ረ/ ወደአገር የሚገባ ለግብርና ሥራ ብቻ የሚውል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የተባይ ማጥፊያ፣ የአረም ማጥፊያ ወይም የፈንገስ ማጥፊያ፣
ሰ/  ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ወርቅ፣
ሸ/  የውሃ ማከሚያ፣ አጎበር፣ የህክምና መገልገያ፣ እና የህክምና መሣሪያ፣
ቀ/  በአባሪ-2 ትርጉም የተሰጠው ወደ ሀገር የሚገባ በሐኪም የሚታዘዝ መድኃኒት፣
በ/ በሚኒስትሮች ምክርቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር-517/2014 በተደነገገው መሰረት ኢንቨስተሮች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው ወደአገር የሚያስገቡት እቃ፣
ተ/ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ አገር እንዲገቡ የተፈቀዱ የካፒታል እቃዎች፣
ቸ/ በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ከጉምሩክ ቀረጥና ከማናቸውም ታክስ ነጻ የሆኑ ያልተመደቡ ወደ አገር የሚገቡ እቃዎች፣
ኀ/  አምቡላንስ እና የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎችና መሳሪያዎች ወደ አገር ማስገባት፣ እና
ነ/  ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ሃሳብ መሰረት በጠቅላይ ሚኒሰትር ጽ/ቤት ከታክሱ ነፃ የሚደረጉ እቃዎች
የወንጀል ክስ የማቅረቢያ
  (የይርጋ) ግዜ

👇
★ አንድ ግለሰብ በፈፀመው ድርጊት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው ሕጉ በሚያዘው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ የቀረበበት እንደሆነ ብቻ ነው።

★ ሕጉ ያስቀመጠው የጊዜ ገደብ ካለፈ የወንጀል ክሱ በይርጋ ስለሚታገድ ድርጊቱን ፈፀመ የተባለው ግለሰብ ክስ ቀርቦበት ሊፈረድበት አይችልም ለበለጠ መረጃ  {የወ/መ/ሕ/ቁ. 226}።

★ ሕግ የሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ (የይርጋ ጊዜ) እንደ ወንጀሉ ዓይነት እና ክብደት የሚለያይ ሲሆን ከባድ ወንጀሎች በ25 ዓመት ይርጋ ሲታገዱ፥ ቀላል ወንጀሎች በ3 ዓመት ይርጋ ይታገዳሉ።

★ የሞት ፍርድ ወይም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የሚጠረጠር ሰው በዚህ ወንጀል በ25 ዓመት ግዜ ውስጥ ክስ ካልቀረበበት ከዛ በኋላ ሊጠየቅ አይችልም የወ / መ/ ሕ/ቁ /_226(U)

★ ይህ የተለመደ _ አሰራር _ በስብእና ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።

የሕገ – መንግስቱ አንቀጽ 28 እነዚህን ወንጀሎች በፈፀሙ ሰዎች ላይ የሚቀርብ ክስ በይርጋ እንደማይታገድ በግልጽ ይደነግጋል።

✓ በስብእና ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፦ የሰው ዘር ማጥፋትን፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ መውሰድን፣ በአስገዳጅ ሰውን መሰወርን፣ ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊት መፈፀምን፣ የሚያጠቃልል መሆኑን ይሄው አንቀጽ ይገልጣል። እነዚህ ወንጀሎች የከፋ ሰቆቃን የሚያስከትሉ በመሆናችው ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች የይርጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሕገ መንግስቱ አይፈቅድም፡፡

ሥለዚህ እነዚህን ወንጀሎች የፈጸሙ ሰዎች በሕይወት እስካሉ ድረስ በማንኛውም ግዜ ክስ ሊቀርብባቸው ይችላል።
👍1
በሕግ አስከባሪ አካላት ያለአግባብ ጉዳት የደረሰበት ሰው ምን መፍትሔ አለው? /የሕግ ጉዳይ/

አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ሹም (ፖሊስን ይጨምራል) የሥራ ጥፋት ፈጽሞ በሰው ላይ ጉዳት ካደረሰ መንግሥት ካሳ የመክፈል ግዴታ አለበት።(የፍሕቁ 2126 /2/)። ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ሹም የሚፈጽመው ጥፋት ደግሞ የሥራ ጥፋት ነው ተብሎ ይገመታል።(የፍሕቁ 2127 /3/)። ስለዚህ ፖሊስ ወንጀል ለመፈጸሙ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሳይኖረው ሰው ቢይዝ፣ ፍርድ ቤት ሳይፈቅድለት ከ48 ሰዓት በላይ ሰው በእስር ቢያቆይ፣ ወይም በእስረኞች ላይ ድብደባ ቢፈጽም የሥራ ጥፋት ነው ማለት ነው። ለዚህ የፖሊስ ጥፋት መንግሥት ማለትም የፖሊስ ተቋም ፍትሐብሔራዊ ሀላፊነት ይኖርበታል ማለት ነው። ለተጎጂዎች ካሳ ለመክፈል ይገደዳል። ይህ በተግባር ሲሠራበት ባይታይም ሕጉ የሚለው ይህንን ነው።

በተመሳሳይ ዐቃቤ ሕግም ማስረጃ ወይም ሕግ ሳይኖር ሰው ያለአግባብ ቢከስ የሥራ ጥፋት ነው። ስለዚህ መሥሪያ ቤቱ ካሳ ለመክፈል ይገደዳል። ነገርግን ፖሊስ ካሰባሰበው ማስረጃ አንጻር ዐቃቤሕግ በበቂ ምክንያት ከከሰሰ እና ተከሳሹ ተከላክሎ ቢወጣ በፖሊስም ሆነ ዐቃቤ ሕግ በኩል የተፈጸመ ሙያዊ ጥፋት አለ ለማለት አይቻልም። በተግባር ብዙም ባይሠራበትም ሕጉ ይሄው ነው።

ሌላው ሠራተኛው ወይም ሹሙ የሥራ ሳይሆን የግል ጥፋት የፈጸመ እንደሆነ በፍሕቁ 2126 /3/ መሠረት መንግሥት ከሀላፊነት ነጻ ቢሆንም ሹሙ ወይም ሠራተኛው ግን ለግል ጥፋቱ ከመጠየቅ ከለላ የሚሰጠው ሕግ የለም። ስለዚህ አንደኛ ነገር ሁልጊዜ የተፈጸመው ጥፋት የሥራ ጥፋት ነው ተብሎ ይገመታል። ሁለተኛ ነገር ለተፈጸመው የሥራ ጥፋት መንግሥት ካሳ ይከፍላል። ሦስተኛ ጥፋቱ የሹሙ ወይም የሠራተኛው የግል ጥፋት ሆኖ ቢገኝ እንኳን በግሉ ከመጠየቅ አያመልጥም። በእርግጥ መንግሥት ካሣ የከፈለ እንደሆነ የከፈለውን ካሳ ጥፋቱን ከፈጸመው ፖሊስ ወይም ዐቃቤ ሕግ በግል የመጠየቅ መብት አለው።

አሁን ይሄ በፖሊስና ዐቃቤ ሕግ ላይ ሲተገበር አይሰተዋልም እንጂ ቢተገበር ምን ይጎድለዋል ?

በአጠቃላይ በፖሊስ ወይም በዐቃቤ ሕግ ለሚፈጸሙ ጥፋቶች ጉዳት ካሳ ለመጠየቅና መልካም ስም እንዲሁም የተያዘ ንብረት ለማስመለስ የሚያስችል በቂ ሕግ አለን። የሚያስፈልገው መተግበርና መብትን መጠየቅ ብቻ ነው። ግለሰቦች መብታቸውን በመጠየቃቸው በግል ተጠቂ የማይሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት ላይ ይበልጥ ቢሠራ የተሻለ ነው። የካሳ ሕጉን የፖሊስና ዐቃቤ ሕግ ተጎጂዎች እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሊጠቀሙበት ይችላል በሚለው ላይ ጥናቶችና ውይይቶች ቢደረጉ ውጤታማ ነው።#Tamerat kidanemariam
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በየዓመቱ ከነሐሴ 1 ቀን እስከ መስከረም 30 ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

#በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 ዓ.ም አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀይ 2 ላይ በግልጽ ተቀምጧል::

#በርካቶቻችን ግን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዝግ ይሆናሉ ሲባል ክርችም ተደርጎ እንደሚዘጋ ተቋም አድርገን በስህተት እንረዳለን፤ ለዛም ነው ትላንት በችሎት ገጠመኝ በርካታ ባለጉዳዮች ፍርድ ቤት ሊዘጋ ነውና ኧረ በፍጥነት ዕግድ ስጡን! ፋይል ክፈቱልን! የውሳኔ ግልባጭ ካልተሰጠን... እያሉ ሲጋፉ የተስተዋለው። በዚህ የዕረፍት ወቅት የሚሰሩ ሥራዎች፦

#የዋስትና

#የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች

#አካል ነፃ የማውጣት ክሶች

#በመንግሥትና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት

ሊያደርሱ የሚችሉ ጉዳዮች #የቀለብ ጉዳዮች እና ሌሎች በበቂ ምክንያት በአስቸኳይ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች በተረኛ ችሎት በመደበኛነት ይስተናገዳሉ።

ሌሎች ጉዳዮችስ?

#ትልቁ አለመረዳት እዚህ ጋር ነው፤ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑባቸው ወቅቶች ፋይል መክፈትንና ዕግድ መጠየቅን ሚከለክል ድንጋጌ አልተቀመጠም።

#ያለዎት ጉዳይ ቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ፋይል ቢከፈት ሚፈጠርብዎት የመብት ጥሰት ከሌለ ፋይል ሳይከፍቱ መቆየት ይችላሉ፤ ነገር ግን የለም ፋይል ከፍቼ ቀጠሮው ለቀጣይ ዓመት ይሻገርልኝ ካሉም መብትዎ ነውና የተሳሳተውን አረዳድ ያርሙ።

ልብ ይበሉ👇

በአዲስ አበባ ደረጃ የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እና ማኅበራዊ ፍርድ ቤቶች መደበኛ ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ አይርሱ።
ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ
https://t.me/AboutJustices
❤2
Forwarded from የሕግ ቤት
................👇👇👇👇👇
👉በወንጀልም ሆነ በፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ላይ ለምስክርነት ስንጠራም እነኚህን ጉዳዮች ልብ ማለት እና ሕግ የጣለብንን ግዴታ መወጣት ይጠበቅብናል።

1.መጥሪያን መቀበል

የሚላክልን መጥሪያ ለምን ጉዳይ፣ መቼ እና የት እንደተጠራን ይገልፅልናል። ስለ ጉዳዩ እንኳን ባናውቅ የተላከልንን መጥሪያ አልቀበልም ማለት አይገባም፡፡

ፍርድ ቤቱ መጥሪያ አልቀበልም ማለታችንን ካረጋገጠ ታስረን በግድ እንድንቀርብ ትዕዛዝ ሊያስትላልፍብን ይችላል። ስለዚህ ግልፅ ያልሆነልን ወይም መጥሪያው አይመለከተኝም የምንል ከሆነ መጥሪያውን ተቀብለን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት ቀርበን ማስረዳት ወይም ማጣራቱ ተገቢ ነው።

2.ቀጠሮ ማክበር

ማንኛውም መጥሪያ ከደረሰን በቀጠሮው ቀንና ሰዓት በፍርድ ቤቱ መገኘት አለብን። በፍርድ ቤቱ ስንጠራም በአካል መቅረብ እና መቅረባችንን ማሳወቅ አለብን። ፍርድ ቤቱ ሳያሰናብተንም ችሎቱን ለቅቀን መሄድ አንችልም፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- 👇👇👇👇👇👇👇
https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7390

በጠበቃና የሕግ አማካሪ #0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
Save it/share it‼️
የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች‼️
ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት የትራንስፖርት አበል እና የመጓጓዣ ወጪ ከግብር ነጻ የሚሆነው፡-

1.  በስራ ባህሪው ምክንያት ስራውን ከቦታ ወደቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ ለአንድ ወር ጉዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2,200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የትራንስፖርት አበል በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2,200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

2.  አንድ ተቀጣሪ በስራ ባህሪው ምክንያት በመዘዋወር ለሚሰራው ስራ ለነዳጅ ወጪ የሚከፈለው ጥሬ ገንዘብ ለትራንስፖርት አበል እንደተከፈለ ተቆጥሮ ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደመወዙ ከአንድ አራተኛ(1/4) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና የተቀጣሪው ጠቅላላ የወር ደመወዝ አንድ አራተኛ ከብር 2200 የሚበልጥ ሲሆን ከግብር ነፃ የሚደረገው የነዳጅ ወጪ በማንኛውም ሁኔታ ከብር 2,200 ሊበልጥ አይችልም፡፡

3.  አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራው ቦታ እንዲሁም ከስራው ቦታ ወደ መኖሪያ ቤቱ የሚጓጓዝበት የመስርያ ቤቱ የትራንስፖርት ሰርቪስ ቢቀርብም ባይቀርብም ለዚህ ዓይነቱ የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

4.  አንድ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ስራ ቦታው እንዲሁም ከስራ ቦታው ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመሄድ ለነዳጅ ወጪ በጥሬ ገንዘብ የሚከፈለው የትራንስፖርት አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

5.  አንድ ተቀጣሪ ሥራውን ለማከናወን መደበኛ የሥራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ ውጪ ሲንቀሳቀስ ለመጓጓዣ ወጪ የሚሰጠው ክፍያ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በስራ ላይ ባለው የትራንስፖርት ታሪፍ ወይም በሚያቀርበው ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከከፈለው የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ሊበልጥ አይችልም፡፡

6.  አንድ የውጭ አገር ዜጋ ሥራን ለማከናወን ወደ የኢትዮጵያ ሲመጣ እና የውል ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈጸመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት የአገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ለግል መገልገያ ዕቃዎቹ የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪሎ ግራም ሊበልጥ አይችልም፡፡

7.   አንድ ግብር ከፋይ ከመደበኛ መኖሪያ ቦታቸው ርቀው ሥራቸውን የሚያከናወኑ ሠራተኞች ቤተሰባቸውን ለመጠየቅ የሚያደርጉትን ጉዞ ውጪ የሚሸፍን በሚሆንበት ጊዜ የዚህ ዓይነት ወጪ ከግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈፀመው የቅጥር ውል ውስጥ ቀጣሪው ይህ ግዴታ ያለበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ሆኖም ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ የሚከፈለው ወጪ ከግብር ነፃ የሚደረገው በአንድ የግብር ዓመት ከሁለት የደርሶ መልስ ጉዞ ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
#አዩዘሀበሻ:#ገቢዎች
====================
ትኩስ ያልተሰሙ ዜናዎችን ማግኘት ከፈለጉ ቻናላችንን join አድርጉ+ለሌሎች ጋብዙ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምከንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠየቅ አለበት ?

ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የ ግል ንብረት መጠየቅ ያለበት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ መሆን እንዳለበት የሰበር ውሳኔ በቅፃ 4 በሰ/መ/ቁ ( በሰበር መለያ ቁጥር) 17937 መጋቢት 2,/1999 በሰጠው ውሳኔ አሳውቋል::
ሰበር ለዚህ ውሳኔ መሰረት የሆነው የፍ/ብ/ህ/ቁ 1845 ነው ይህም አንቀፃ መብቶችን የመጠየቂያ ጊዜ 10 አመት መሆናቸውን ይደነግግል


በጠበቃ ህሊና ጌታቸው
#Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo
https://t.me/Ethiopialegalinfo
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE

በኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ላይ የተደረገው ማስተካከያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 13/2016 ዓ.ም መጽደቁ ይታወሳል።

ይህ ተከትሎ  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት የታሪፍ ማሻሻያው ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ የታሪፍ ጭማሪው የደንበኞችን የኃይል የአጠቃቀም መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም፦

የቤት ደንበኞች፤ የንግድ ተቋማት፤ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፤ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚዎች በሚል መከፋፈሉን አስታውቀዋል።

የቤት መብራት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ " እንደ አጠቃቀማቸው አሁን ከሚከፍሉት እና ጭማሪ ከተደረገበት መካከል ያለውን ልዩነት ሲከፍሉ እንደ አጠቃቀማቸው ድጎማ ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

ድጎማው ምን ይመስላል ?

➡ 50kW በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

➡ ከ50kW - 100KW ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

➡ 200kW - 300 Kw ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 4 በመቶ የሚሆነውን ይደጎማሉ፤

➡ 400kW - 500 KW የሚሆነውን ማሻሻያውን ያለምንም ድጎማ ይከፍላሉ

➡ ከ500kW በላይ የሚሆነውን ደግሞ ሌላውን ተጠቃሚ የሚደግፉበት የጎንዮሽ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል።

የአከፋፈሉ ሁኔታ ምን ይመስላል ?

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ ይህ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያው (የተጨመረው 6 ብር) የሚከፈለው በአንድ ጊዜ ሳይሆን በ16 ዙር በሚደረግ የሂሳብ ማስተካከያ [ከመስከረም 1 /2017 ጀምሮ] በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢንጂነር ሽፈራው ይሄንን ሲያስረዱ 50KW የሚጠቀሙ ደንበኞች አሁን የሚከፍሉት 27 ሳንቲም እንደሆነ ገልጸው ከመስከረም ጀምሮ የሚከፍሉት 35 ሳንቲም ይሆናል ብለዋል።

ከአራት ዓመታት በኋላ ደግሞ [በ16 ዙሮች በሚደረግ ማስተካከያ] 1.56 ብር መክፈል ይጀምራሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ያለው ጫና ተጠንቷል ወይ ?

ይህ ጥያቄ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ሲሆን በሰጡት ምላሽ በዚህ ላይ ጥናት መደረጉን ጠቅሰው ይህም #ከአራት_ዓመት በኋላ የሚኖረው ተጽዕኖ 2 በመቶ እንደሆነ አንስተዋል።

" ከአከራይ ተከራይ ጋር ያለው ተጽዕኖም በጣም አነስተኛ ነው፤ የሚያጣላቸው ነገር አይኖርም " ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው ይህ የታሪፍ ማሻሻያው በዋነኛነት የወጣበትን ወጪ ለመሸፈን (A cost reflective tariff) መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።

#ማብራሪያ: ከላይ የተያያዘው ሰንጠረዥ ድጎማ የተደረገበት የሂሳብ ታሪፍ ሲሆን። በዓመት 4 ጊዜ በ4 ዓመት ደግሞ 16 ጊዜ የሚተገበር የሂሳብ ማስተካከያ የያዘ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
10 መሰረታዊ የውል አተረጓጎም ደንቦች
***
በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)
***
ውል ቅኔ መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ለሁሉም ተዋዋይ ወገን እንዲሁም ለሶስተኛ ወገኖች ጭምር ግልፅ በሆነ መንገድ መደረግ አለበት ። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በተለያየ መንገድ የሚደረጉ ውሎች ግልፅነት የጎደላቸው ይሆኑና የግጭት ና ያለሙግባባት መንስኤ ሆነው ለትርጉም አስማሚ ወይም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ይህ ሲሆን ፍርድ ቤቶች ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ መሰረታዊ የሆኑ የውል አተረጓጎም ደንቦች አሉ። እነሱን እጠር አርገን ከተያያዥ የሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉሞች ጋር እንመልከት:
የውል አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች
1. ውሉ ግልፅ ከሆነ ምንም አይነት ትርጉም አያስፈልግም። ( If the contract is clear no need of interpretation ) /፩/
2. የውሉ ትርጉም ውጤት መገኘት ያለበት ከራሱ ከውሉ እንጂ ፣ ውሉ ወይም ግዴታው ከትርጉሙ ሂደት መመንጨት የለበትም። / The interpretation of the contract must come from the contract not the contract from the interpretation./ በሌላ አማርኛ ፍርድ ቤት ውልን በመተርጎም ስም ያልነበረ ውል ወይም ግዴታ ሊፈጥርና ሊሰራ አይችልም።
3. የቅን ልቦና አተረጓጎን ደንብ (1732) :- ማንም ሰው የራሱን መብት በአግባቡ ከመጠቀም አልፎ በሌላው ተዋዋይ ላይ አላስፈላጊ ጉዳት የማድረስ ፍላጎት የለውም የሚል አወንታዊ መነሻ ሃሳብ ( positive premise) አለ። ከዚህ ተቃራኒ የሄነ ሃስብ ይዞ ከቅን ልቦና በተቃራኒ ጉዳት ለማድረስ ያለው ተዋዋይ ወገን ካለ ህግ በመርህ ደረጃ ጥበቃ ያደርግለታል። /፪/
4. በተገቢው መንገድ ያልተብራሩ ሃሳቦችን አተረጓጎም በተመለከተ ለልማዳዊ አሰራሮች እና አፈፃፀሞች በቂ ትኩረት ሊቸረው ይገባል። ውል ከአካባቢው አሰራርና ተቀባይነት ካላቸው ልምዶች አንፃር እየተገናዘበ መተርጎም ይኖርበታል።
5. አሻሚ የሆኑ ቃላት እና ሃረጎችአተረጓጎም፣
" A plain contract means what it says "
ግልፅ የሆነ ውል የውሉ ቃላት በቀጥታ የሚያስተላልፈው ትርጉም ብቻ ነው
በተቃራኒው የውሉ ሃሳብ ግልፅ ካልሆነና አሻሚ ከሆነ ግን የተዋዋዮች ሃሳብ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም ማለት ትርጉም በመስጠት ሂደት ውሉን እንዲተረጉም የቀረበለት አካል ትርጉሙን የሚፈልገው በውሉ ውስጥ ከሚገኙ ቃላት ላይ ብቻ አይደለም ። ውሉ ለድርድር ( ለስምምነት ) በቀረበበት ጊዜ ( Offer and Acceptance ) ፣ እንዲሁም የውሉ ድርድር በሚካሄድበት ጊዜ ፣ ድርድሩ በቀረበበት እና ተቀባይነት ባገኘበት ጊዜ ፣ ከዚያም በፊት የተከናወኑ ቀዳሚ ግንኙነቶች በተደረጉበት ጊዜ የተደረጉ እና የተከናወኑ ጉዳዮች ሁሉ ተገናዝበው ትርጉም ሊሰጣቸው ይገባል።
አሻሚ የሆነው ቃል አጠቃላይ አነጋገር ከሆነ በትርጉም የሚወሰደው የቃሉ የተለመደ ትርጉም ነው።
በቅጡ ተለይቶ ያልታወቀ የውል ፍሬ ነገር ( Object ) ካለ ሁሉንም የውሉን ቃላት አረፍተ ነገሮች አንዱን ከአንዱ በማገናዘብ የመጨረሻ ትርጉም ላይ መድረስ ይቻላል።/፫/
6. ከውሉ ባህርይ ጋር የሚቀራረበው ትርጉም ከማይቀራረበው ይመረጣል።
7. ውሉን ዋጋ ከሚያሳጣው ትርጉም ይልቅ ውጤታማ የሚያደርገው ይመረጣል።/፭/
8. የውሉን ባለመብት ከሚጠቅመው ባለዕዳውን የሚደግፈው ይመረጣል።/፬/
9. ውሉን ካዘጋጀው ወገን ይልቅ ውሉን ላላዘጋጀው የሚጠቅመው ትርጉም ይመረጣል።
10. ያለዋጋ በተደረገ ውል ( Gratuitous contract) በውሉ መብት ካገኘው ሰው ይልቅ ውሉ ግዴታ ለሚጥልበት ሰው የሚጠቅመው ትርጉም ይመረጣል።/፮/ /፯/

ተዛማጅ የሰበር ውሳኔዎች
/፩/ ሠ/መ/ቁ 15662 ( ቅፅ 4) - ውሉ ግልፅ በሆነ ጊዜ ግልፅ ሆኖ ካለው ሃሳብ በመራቅ የተዋዋዮቹ ፍቃድ ምን እንደነበር ዳኞች ለመተርጎም አይችሉም።
/፪/ ሠ/መ/ቁ 25165 (ቅ.7) የቅን ልቦና መከራከሪያን ወደጎን በመተው ውልን ተርጉሞ አንድን ውል ማፍረስ ትክክል አይደለም።
/፫/ ሠ/መ/ቁ 38544 (ቅፅ 10) - ተዋዋዮች ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድመው ወይም ከተዋዋሉ በኋላ የነበሩትን ሁኔታዎች ፣ የፈፀሙትን ተግባራት በማመዛዘንና ሃሳባቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ መሞከር ፣ የውሎችን ቃላቶች አንዱን ከአንዱ ጋር እያዛመዱ መመልከት ለውሉ ጉዳይ አግባብ ያለው ትርጉም ለመስጠት ተገቢ ነውና
/፬/ ሠ/መ/ቁ 41893 (ቅፅ 10) - የስጦታ ውል ሊተረጎም የሚገባው በውሉ ውስጥ የሚገኘውን አንድ ሃረግ ነጥሎ በማውጣት ሳይሆን የውሉን አጠቃላይ ይዘት በመመልከት ነው።

/፭/ ሠ/መ/ቁ 27869 (ቅፅ 5 ) - የቤቱ መለያዎች እና ቦታ ሳይጠቀስ አንድ ቤት ለማክበር በአይነት መዋጮ ቢሄንና ሰውየው ያለው አንድ ቤት ብቻ እንጂ ሌላ ቤት የሌለው ከሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 መሰረት ሲተረጎም በውሉ ላይ የተገለፀው እያዋጣው ያለውን አንድ ቤት እንደሆነ መተርጎም አለበት። ስመ ንብረቱ በማህበሩ ባይመዘገብም በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2878 መሰረት ለ3ተኛ ወገን መቃወሚያ እንዳይሆን ይከለክላል እንጂ መዋጮውን ውጤት አያሳጣውም።
/፮/ ሠ/መ/ቁ 103910 ( ቅፅ 10 ) - በውሉ ውስጥ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም የውሉ ድንጋጌ መተርጎም ያለበት በውሉ አስገዳጅ ( ባለመብት ) የሆለው ወገን በሚጠቅም ሁኔታ ሳይሆን በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1738 መርህ መሰረት በውል ተገዳጅ ለሆነው ሰው ምቹ በሚሆንበት አኳኋን ነውና
/፯/ ሠ/መ/ቁ 107990 (ቅ.17) - በግልፅ የሰፈረ የውል ቃል ባይኖርም ስጦታ ሰጪው በድህነት ላይ ወድቆ እያለ ስጦታ ተቀባይ የምክር ግዴታ ያለበት ሲሆን ስጦታ ተቀባይ ከስጦታ ሰጪ የተቀበለውን የእርሻ መሬት እየተጠቀመ በውለታ ቢስነት ስጦታ ሰጪውን የሚጎዳ ተግባር ፈፅሞ ከተገኘ ስጦታ ሰጪው ውሉ እንዲፈርስለት የመጠየቅ መብት አለው።
👍1
#ጳጉሜ_በህግ_እይታ

የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1858 እና 1859
🏛 ሰ/መ/ቁ. 96458 ቅጽ 16፣ ፍ/ህ/ቁ. 1860(3)
✍️  ይርጋ ማለት የመብት ጥያቄ ጊዜ በማለፉ ቀሪ የሚሆንበት እና በአንፃሩ መብት ላልነበረው የሚያጎናፅፍ ነው፡፡

👉  ጳጉሜ እንደ አስራ ሦስተኛ ወር የማትቆጠር መሆኑ የሚታወቅና የሀገራችን የአንድ አመት ጊዜ 12 ወራቶች ከሆኑ ከዚህ አቆጣጠር ውጭ ያሉት ቀናት በአሰሪና ሰራተኛው መካከል መብትም ሆነ ግዴታ ሊፈጥሩ አይገባም፡፡

👉 ጳጉሜ ሰራተኛው ሥራም ላይ ቢሆኑ የሚሰጣቸው ጥቅም ወይም በመብት ደረጃ የሚጠይቁትም ክፍያ የለም፡፡እንግዲህ እንደወር የማይቆጠረው ‘ጊዜ’ ለቀረበው ከውል መቋረጥ ጋር ተያይዞ የሚነሣውን የክፍያ ጥያቄ ጳጉሜ በይርጋ አቆጣጠር በማስገባት ተሰልቶ የሰራተኛውን መብት ሊያጣብብ አይገባውም።

👉 ህጉ የይርጋ ጊዜውን በወር ወይም ወራት ከወሰነ ጊዜው የሚቆጠረው በጳጉሜ ውስጥ ያሉት ቀናት ታሳቢ ሳይደረጉ ነው፡፡ በፍትሐብሔር ህጉ ቁጥር 1860(3) በተመለከተው የጊዜ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ጳጉሜ እንደወር አይቆጠርም፡፡ ጳጉሜ እንደ አስራ ሦስተኛ ወር የማትቆጠር መሆኑ ከታወቀና የሀገራችን የአንድ አመት ጊዜ 12 ወራቶች ከሆኑ ከዚህ አቆጣጠር ውጭ ያሉት ቀናት በተዋዋይ ወገኖች መካከል መብትም ሆነ ግዴታ ሊፈጥሩ አይገባም፡፡

👉 ጳጉሜ በህግ እይታ ወር አይደለችም ስለዚህ  ወርን መሰረት አድርጎ የሚደረጉ ውሎች፣ ስምምነቶች ፣ ግብይቶች ፣ ወዘተ አይመለከቷትም ( መብትና ግዴታ ልትፈጥር አትችልም) ። ደመወዝ ፣የቤት ኪራይ፣ ብድር ወዘተ ወርን መሰረት አድርገው የተፈፀሙ ነገሮች በጳጉማ በተግባር ላይ አይውሉም ። በተቃራኒው! በቀን(ኖች) እና በሳምንት (ቶች) የተወሰኑ ከሆኑ በጳጉሜም ቢሆን በተግባር ላይ ይውላሉ።
👍1
።።። የዋስ መብት (Bail) ።።።።             
ወንጀል የማህበረሰብን አጠቃላይ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ከመሆኑ አንፃር ማህበረሰቡ ወንጀል ፈጻሚዎች እንዲለዩ እና የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ይፈልጋል፡፡ በአንፃሩ በወንጀል የሚጠረጠሩ ሰዎች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ እስካልተባሉ ድረስ ነፃ ሆነው የመገመት መብት ያላቸው በመሆኑ የማህበረሰቡን ፍላጎት እና የተጠረጠሩ ሰዎችን መብት በአማከለ መልኩ መፍትሄ ይሆን ዘንድ የዋስ መብት የህግ ጥበቃ ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የዋስ መብትን ምንነት፣ የዋስ መብትን በተመለከተ በሀገራችን ያለውን የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም የዋስ መብትን የሚያስነፍጉ ልዩ ሁኔታዎችን በዝርዝር የምንመለከት ይሆናል፡፡
የዋስ መብት ምንነት......👇👇👇👇👇
https://wp.me/pfoz3m-85
https://wp.me/pfoz3m-85
ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረ ሰራተኛ ሰ/መ/ቁጥር 212420
.............................................................................................
አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ- ወጥ ነው።

ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም።

የካሳው መጠን ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ ብቻ ነው።
Source - Abreham Yohannis Law Corner
Forwarded from abyssinialaw.com⚡️ (Attorney Liku Worku)
Federal Supreme Court Cassation Decision Volume 26.pdf
5.3 MB
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 26 የሰበር ውሳኔዎችን አትሟል። ውሳኔዎቹን ከዚህ ያግኙ!
#volume26 #cassationdecision #abyssinialaw

https://www.abyssinialaw.com/decisions/federal-supreme-court-cassation-decisions/federal-supreme-court-cassation-decision-volume-26
የሥራ ውል ያለ ማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው መንገዶች

በ፦ሙሉቀን ሰይድ ሐሰን (የሕግ አማካሪና ጠበቃ)

የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27 ስር ያለ ማስጠንቀቂያ የስራ ውል የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ተጠቅሰዋል፡፡ በዚህም ጽሁፍ በአንቀጽ 27 ስር ከተመለከተቱት ዝርዝር ሁኔታዎች የተወሰኑት በመጥቀስ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ጋር በማገናዘብ አጭር ዳሰሳ ለማደረግ ተሞክሯል፡፡

በዚህ ጽሑፍ፦

1) የሥራ ሰዓት አለማክበር
2) ከሥራ ገበታ መቅረት
3) በስራው ላይ የማታለል ተግባር መፈጸም፡፡
4) ከአቅም በታች መስራት፡፡
5) የሰራተኛው መታሰር
6) የማሰናበቻ ምክንያቶች በጽሁፍ ለሰራተኛው መገለጽ ያለባቸው ስለመሆኑ፡፡
7) የሥራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የ30 ቀን ገደብ ያለው ስለመሆኑ
8) የሥራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ከመቋረጡ በፊት ሰራተኛውን ለ30 ቀናት አግዶ ማቆየት ስለሚቻልበት ሁኔታ፡፡

መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/termination-of-employment-contract-without-notice