የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ቁም ኑዛዜ ስጦታ

ሟች ከአንድ በላይ የሆኑ ልጆች ወይም ወራሾች ቢኖሩትና ከነዚያ መካከል ለአንደኛው የኑዛዜ ስጦታ ቢያደርግ የሌሎችን ወራሾች ከሟች ውርስ መነቀል አያስከትልም፡፡ ይህንንም የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 913 የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሀሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት አንድ ድርሻ ወይም አንድ ንብረት ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብሎ አይቆጠርም፡፡

በፍ/ብ/ሕ/ቁ ከአንቀጽ 1117 ጀምሮ ያሉት ድንጋጌዎች አግባብነት አላቸው አንቀጽ 1117 አባትና እናት ወይም ሌሎች ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆች ለልጆቻቸው እና ሌሎች ተወላጆች ሀብታቸውን ለመስጠትና ለማከፋፈል እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ ይህ ክፍፍል ሥርዓት አንድን ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል በአንቀጽ 1123 ተደንግጓል፡፡

አንቀጽ 1123/1/ ሲነበብ  “በስጦታ አከፋፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር ወደታች ከሚቆጠሩ ተወላጆች አንዱ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላል”

ሰ/መ/ቁ 32337 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 882፣ 913፣ 2428፣ 2443
የእምነት ማጉደል ወንጀል እና የአደራ ውል ሰ/መ/ቁ.209733 / Daniel Fikadu Law Office?
የእምነት ማጉደል ወንጀል ምን ማለት እንደሆነ እና የወንጀሉማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 675 ስር ተመልክቷል፡፡ በዚሁ አግባብ አንድ ሰው የእምነት ማጉደል ወንጀልፈፅሟል ተብሎ በወንጀል የሚቀጣው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግናን ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰውየሆነውን እና ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይምበከፊል ለራሱ ያደረገ፣ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ወይም ይህንን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት የፈፀመ እንደሆነ እናይህንኑ በእምነት ወይም በአደራ የተቀበለውን ንብረት ወይም ጥሬ ገንዘብ እንዲመልስ ወይም እንዲከፍል ሲጠየቅ ንብረቱያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግሎት ያዋለው ለመሆኑ ማስረዳት ያልቻለ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆን ከዚሁድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 3 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ የእምነት ማጉደል ወንጀል ማቋቋሚያ
83መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ውስጥ አንዱ በአደራ የተቀበሉትን ንብረት እንዲመልስ ሲጠየቅ አለመመለስ እንደሆነ በዚሁ ድንጋጌ ስርበግልፅ ተመልክቷል፡፡
በህገ ወጥነት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለውን ንብረት በአደራፈርመው መቀበላቸው በግራ ቀኙ መካከል ያለው ግኑኝነት የውል የሚያስመስለው ቢሆንም እንዲያስቀምጡ የተሰጣቸውንንብረት ሲጠየቁ አለማቅረብ ንብረቱን የእምነት መጉደል ወንጀል አንጂ የውል ግዴታን አለመፈፀምን የሚመለከት ፍትሐ-ብሄራዊኃላፊነት አይደለም። /በአደራ አሰቀማጩ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።/ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በዳንኤል ፍቃዱ /ጠበቃ/
በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ ፍቺ እና ጉድፈቻ ውሳኔዎች በፍርድ ቤቶች ምዝገባው ነገ ይጀምራል፡፡
**********************************************
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚመዘግባቸው ኩነቶች መካከል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ጉድፍቻ እና ፍቺ በፍርድ ቤቶቹ ከነገ ጀምሮ መመዝገብ ይጀምራል፡፡
ሁለቱ ተቋማት የኩነት ምዝገባን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
ይህንን ተከትሎ በወሳኝ ኩነት ፅንሰ ሀሳብ እና የምዝገባ ስርዓት በሚመለከት በከተማዋ ለሚገኙ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች፣11 ምድብ ችሎት የቤተሰብ እና የጉዲፈቻ ችሎት ዳኞች፣ችሎት አስተባባሪ ሪጅስትራሮች፣ፍርድ ቤቶቹ የሚገኙበት የወረዳ ስራ አስፈፃሚ እና የወረዳው የሲቪል ምዝገባ ስራ አስኪያጅ በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአራዳ እና ቦሌ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች የፌደራልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ ምድብ ችሎት ከጥዋቱ በ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ምዝገባው በይፋ ይጀመራል፡፡
አዲሱ የባንክ ስራ አዋጅ ያካተታቸው ተጨማሪ ድንጋጌዎች የትኞቹ ናቸው?
****

ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የባንክ ስራ አዋጅ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው ይዘት የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበታል። በሶስት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ በረቅቁ ላይ ተካትተው በነበሩ ትርጓሜዎች እና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል። 
ማሻሻያ ከተደረገባቸው ድንጋጌዎች መካከል የባንክ ቅርንጫፎች እና የውጭ ባንኮችን የተመለከቱት ይገኙበታል። የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ የሚሳተፉበትን አካሄድ በሚዘረዝረው የአዋጅ ክፍል ላይ አዲስ አንቀጽ እንዲካተት ተደርጓል። በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ በረቂቁ ላይ ከተቀመጠው በተጨማሪም አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ተካትቷል። 
ከማሻሻያዎቹ እና ከአዳዲስ አንቀጾች ውስጥ በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተጠናቀሩትን፤ ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል፦

ትርጓሜዎች
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት፦ ባለፈው ሰኔ ወር ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ትርጓሜ ሲያብራራ “ወለድ ያለመቀበልን ጨምሮ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት ነው” በሚል ነበር ያስቀመጠው። ይህ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንደ አዲስ እንዲሻሻል ተደርጓል።
በአዲሱ ድንጋጌ “ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት” ማለት “ወለድ ያለመቀበልን ጨምሮ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በወለድ ነጻ ባንኮች እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት መስኮት በሚሰጡ ባንኮች የሚሰጥ እንደሆነ” ተቀምጧል። ይህ ማሻሻያ የተደረገው፤ አገልግሎቱ በወለድ ነጻ ባንኮች እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት መስኮት በሚሰጡ ባንኮች የሚሰጥ መሆኑን “በማያሻማ መልኩ” መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ለፓርላማ በቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተብራርቷል።  
ቋሚ ንብረቶች፦ የአዋጅ ረቂቁ የትርጓሜ ክፍል፤ ቋሚ ንብረቶች “የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶች ሆነው በመመሪያ ይወሰናሉ” በማለት የተሰጠው ትርጓሜም እንደዚሁ ተሻሽሏል። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ “ቋሚ ንብረት” ማለት “ግዙፋዊ ሀልዎት ያለው እና ገቢ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ንብረት እና ዝርዝሩ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ የሚወሰን ነው” የሚል ትርጓሜ ተሰጥቶታል። 
ሀብት እና እዳ ማስተላለፍ፦ የአንድ ባንክን የባንክ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተሰማራ ሌላ ባንክ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ማስተላለፍ የሚመለከተው የ“ሀብት እና እዳ ማስተላለፍ” ትርጓሜ፤ ፋይናንስ ነክ የሆኑ እና ያልሆኑ ሀብቶችን የሚጨምር እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል። በጸደቀው አዋጅ ላይ “ዕዳዎች” በተመሳሳይ መልኩ እንደሚተላለፉ ተደንግጓል።

የባንኮችን ቅርንጫፍ በተመለከተ
የባንክ ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ቅርንጫፍ ለመክፈት መሟላት ያለባቸው “ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች በብሔራዊ ባንክ መመሪያ” እንደሚወሰኑ በአዋጅ ረቂቁ ላይ ተቀምጦ ነበር። በጸደቀው አዋጅ ከዚህ በተጨማሪ የባንክ ቅርንጫፎችን ለመዝጋት መሟላት ያለባቸው “ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች” በብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንዲወሰን ተደርጓል።   
የውጭ ባንክ እንደራሴ ቢሮ በተመለከተ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማንኛውም የውጭ ባንክ እንደራሴ ቢሮ ፈቃድ ለማግኘት ሊያሟላቸው የሚገቡ ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶችን በተመለከተ በመመሪያ እንደሚወስን በረቂቅ አዋጁ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር። በጸደቀው አዋጅ ላይ ባንኩ ከዚህ ስልጣን በተጨማሪ “ቁጥጥር የማድረግ” ኃላፊነትም ተደርቦለታል።   
በአዋጅ ረቂቁ ላይ “ማንኛውም ባንክ ከብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ቅርንጫፍ መክፈት አይችልም” የሚል ድንጋጌ ሰፍሮ ነበር። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ማንኛውም ባንክ ከብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ  “የተከፈተ ቅርንጫፍ መዝጋት አይችልም” የሚል ተጨማሪ ድንጋጌ ታክሎበታል።   

የውጭ ባንኮችን በተመለከተ
የአዋጅ ረቂቁ “ማንኛውም ተቀማጭ ገንዘብ የሚቀበል ወይም የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የውጭ ባንክ ተቀጥላ፤ ተቆጣጣሪው ያወጣቸውን ማንኛውም የጤናማነት መለኪያ መስፈርቶች እንደአግባብነቱ ከሀገር ውስጥ ባንኮች እኩል ማክበር አለበት” ይላል። የውጭ ባንክ ቅርንጫፉ ወይም የውጭ ባንክ ተቀጥላው ከዚህ በተጨማሪ “ሌሎች አግባብነት ያላቸው ተቆጣጣሪ አካላት ያወጡትን ህጎች ማክበር” እንደሚጠበቅበት በጸደቀው አዋጅ ላይ ሰፍሯል። 
ይህ ማሻሻያ የተደረገው “የውጭ ባንኮች የብሔራዊ ባንክን ብቻ ሳይሆን የሌሎች አግባብነት ያላቸውን ተቆጣጣሪ አካላት ህጎችን ከሀገር ውስጥ ባንኮች እኩል አክብረው መስራት እንዳለባቸው ለማመላከት” እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።
የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ ስለሚሳተፉበት ሁኔታ
አዲስ ድንጋጌ፦ የውጭ ዜጎች በተለያዩ ዘዴዎች የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት በባንክ ስራ አዋጅ የተደነገገውን ገደብ በጠበቀ መልኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ፤ በረቂቅ አዋጁ ላይ ያልነበረ አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንዲካተት ተደርጓል። ይህ ድንጋጌ “በውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያዊያን ወይም እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት በሚቆጠር የውጭ ሀገር ዜግነት ባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በጋራ ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት፤ አንድ ባንክ ላይ አክስዮን ሲይዝ፤ ባንኩ ላይ የተደረገው የውጭ ኢንቨስትመንት መጠን የሚሰላው፤ አክስዮን በገዛው ደርጅት ላይ የውጭ ዜጎች ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ መጠን መሰረት በማድረግ ይሆናል” ይላል። 
የተሰረዘ ድንጋጌ፦ “ተቀማጭ የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍን” በተመለከተ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተካትቶ የነበረው ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንዲሰረዝ ተደርጓል። የተሰረዘው ድንጋጌ “ማንኛውም ተቀማጭ የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ መሰማራት የሚፈቀድለት፤ በማበደር፣ የብድር ክፍያዎችን በመቀበል እና ብድር የመስጠት ሂደቱን ለማቀላጠፍ የተከፈቱ የተበዳሪዎች የተቀማጭ ሂሳቦችን በማስተዳደር ላይ ብቻ ነው” የሚል ነበር። 
የውጭ ባንኩ “ብድሮችን እና ሌሎች ፋይናንሶችን ከውጭ ሀገር ምንጮች ሊያገኝ እና በብሔራዊ ባንክ መመሪያ እና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች መሰረት መጀመሪያ ላይ በተመዘገበው አግባብ መልሶ ሊከፍል” እንደሚችልም በዚህ ድንጋጌ ላይ ተካትቶ ነበር። ይህ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ሳይካተት የቀረው“ ማንኛውም የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ስራ በሚሰራበት ወቅት የሚፈቀዱለትን እንቅስቃሴዎች በግልጽ የሚያስቀምጥ መመሪያ ብሔራዊ ባንክ እንደሚያወጣ የተደነገገ” በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ለፓርላማ አባላት የተሰራጨው ማብራሪያ ያስረዳል። 

በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ
በፓርላማ የጸደቀው አዋጅ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ የሚሰማራበትን ሁኔታ የተመለከተ አዲስ አንቀጽ፤ በረቂቁ ከተቀመጡ ድንጋጌዎች በተጨማሪነት እንዲያካትት ተደርጓል። አዲሱ አንቀጽ የተካተተው “በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች በባንክ ሥራ ላይ ስለሚኖራቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ስርዓት በግልጽ በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ” ምክንያት እንደሆነ በማብራሪያው ላይ ተቀምጧል።ይህ አንቀጽ “አግባብነት ባለው ሕግ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ሰው ወይም በእነዚህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተያዘ እና የተቋቋመ
ድርጅት እና እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር የፈለገ፤ በብር የባንክ አክሲዮን ስለሚገዛበት አግባብ ወይም ባንክ ስለሚያቋቁምበት አግባብ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ነው” ይላል። ሆኖም ትውልደ ኢትዮጵያዊው ከዚሁ ኢንቨስትመንት የሚያገኘውን ማንኛውንም ክፍያ ወይም ገቢ “በውጭ ምንዛሬ ከኢትዮጵያ ውጭ ማዛወር እንደማይችል” በአዲሱ አንቀጽ ላይ ተደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Forwarded from Mizan Law / ሚዛን ሎዉ⚖️ (Mesfin assefa)
ከባድ_አካል_ጉዳት_ማድረስ_ወንጀልየወህቁ_555.pdf
963.6 KB
ከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል(የወ/ህ/ቁ.555)
Vs.
ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል (የወ/ህ/ቁ.556)
በአንዋር መሀመድ

ቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ከከባዱ የአካል ጉዳት ማድረስ (Grave wilful injury Vs. Common willful injury) የሚለየው በሚደርሰው አካላዊ ጉዳት መጠን መሆኑን የወንጀል ህግ ድንጋጌዎቹን በማንበብ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ በወንጀል ህጉ ከተቀመጠው የቀላልና ከባድ አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ዝርዝር በራሱ ግልጽ ባለመሆኑ- ለማድረግም ስለማይቻል፡፡ ብዙ ግዜ በባለሙያዎች ዘንድ ቀላሉን ከከባድ አልፎ አልፎም ቀላል የአካል ጉዳት ማድረስን ከእጅ እልፊት ለመለየት ልዩነቶች ይፈጠራሉ፡፡

የወ/ህ/ቁ. 555 ከባድ የአካል ጉዳትን በመዘርዘር ከመተርጎም (Illustrative) የሞከረ ቢሆንም በመጨረሻው ንዑስ አንቀጽ 555(ሐ) ስር “በሌላ መንገድ ከባድ የሆነ ጉዳትን…” የሚል ጥቅል (ሰፊ) ሀረግ ያስቀምጣል፡፡ በዚህም የተሰጠው ትርጉም ለሰዎች ግላዊ ቀላልና ከባድ እይታ ውስጥ መውደቁ አይቀርም፡፡ ቀላል አካል ጉዳት ማድረስን ደግሞ “ከከባዱ ውጭ ..” በማለት አሁንም ለልዩነት በር በሚከፍት መልኩ አስቀምጦታል፡፡

በወንጀል ህግ ላይ በተጻፈ ጽሁፎች ውስጥ ቀላል የአካል ጉዳት ለመባል የቆዳ ውስጠኛ ክፍል መሰንጠቅ ጭምር የሚይዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ (A complete breaking of all layers of the victims’ skin)
ይበልጥ በተብራራ መልኩ ሲቀመጥ ፡- (the continuity of the whole skin must be broken; ….including not merely the outer skin of the body but the skin of an internal cavity….) (ይመልከቱ፤ Dr. Roger Geary,
Forwarded from De Z Habesha
የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ  ጸደቀ 
*

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የፌደራል  ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት  ክፍያን  ለመወሰን  የወጣውን ረቂቅ ደንብ አጽድቋል። 
ደንቡ በጸደቀበት ወቅት  የሕግና  ፍትህ  ጉዳዮች  ቋሚ  ኮሚቴ   ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ  እንደተናገሩት  የዳኝነት አከፋፈል ሥርዓቱን ለማዘመን፣  ሥርዓቱም አጭር፣  ቀልጣፋና   ለከፋዩ  ያመቸ እንዲሆን ለማስቻል ሕጉን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች  እስከ አሁን ድረስ ሲጠቀሙበት የነበረው  የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል የህግ ክፍል ማስታወቂያ ደንብ በ1945 ዓ.ም  የወጣና ማሻሻያ  ሳይደረግበት የቆየ ነው። ከዚህም በተጨማሪ  በደንቡ  ያልተሸፈኑ በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው  ወቅቱን ያገናዘበ  የዳኝነት ክፍያን መወሰኛ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በተጨማሪም  የፌደራል ፍርድ ቤቶች  አሁን ከደረሱበት ወቅታዊ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃና ከሚሰጡት አገልግሎት  አንጻር  ተመጣጣኝ  የሆነ  የዳኝነት  ክፍያ  ለማስከፈል  የሚያስችል ሕግ በማስፈለጉ ደንቡ  ተዘጋጅቷል።
ደንቡ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር  በቂ ውይይት የተደረገበትና የሀገር ውስጥን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባትና የሌሎች ሀገራትንም ልምድ ታይቶ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል ። መረጃዉ የኢትጵያ ፕሬስ  ድርጅት ነዉ፡፡👇👇👇👇
© ዳንኤል ፈቃዱ
ሰሞኑን በፓርላማ የፀደቀው የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ?

➡️ የዘር ፍሬ በመለገስ ልጅ መውለድ እንዲቻል ለመፍቀድ ቀርቦ የነበረው የአዋጅ ድንጋጌ የለበትም።

➡️ በመሣሪያ ላይ የተመሠረተ አተነፋፈስ ማቋረጥ ተፈቅዷል።


" የጤና አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ " ለ3 ወር ያህል ውይይት ሲደረግበት ቆይቶ ከቀናት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ9 ድመጸ ተአቅቦ ፣ 1 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል።

የዘር ፍሬን በመለገስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ልጅ መውለድ እንዲቻል እንዲፈቅድ በረቂቅ ሕጉ ተካቶ የነበረው አንቀጽ እንዲወጣ ተደርጓል።

ለጤና፣ ማኅበራዊና ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ውይይት ሲደረግበት በነበረው ረቂቅ አዋጅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት የሚፈቅደው ድንጋጌ እንዲወጣ ተጠይቆ ነበር።

ድንጋጌው እንዲወጣ ያደረገው " ልጅ እንዲኖረው የፈለገ ምን ይሁን ? " ለሚለው ጥያቄ፣ የጉዲፈቻ ልጅ በበቂ ሁኔታ የሚገኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ተነጋግሮበት በመወሰኑ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" ድንጋጌው ከረቂቁ እንዲወጣ የተደረገው ወላጆች ልጅ ለመውለድ ያላቸውን ፍላጎት ሳይሆን፣ ሕግ አውጪው የሚወለዱ ልጆች የማኅበረሰብ ቀውስ እዳያጋጥማቸው በማሰብ፣ ከእምነትና ከማኅበረሰብ መስተጋብር ጋር የተጣጣመ ሕግ መውጣት እንዳለበት ታስቦ ነው።

በተጨማሪም ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ ድንጋጌ ማውጣት ስለማይፈቀድ ነው።

ለተጋቢ ባለትዳሮች ፍላጎት ሲባል ይህ ሕግ ወጥቶ የሚወለደውን ሕፃን መብት መጋፋት አያስፈልግም።

ይሁን እንጂ የፀደቀው ሕግ በጋብቻ የተጣመሩ ባለትዳሮች ያለ ልገሳ የራሳቸውን የዘር ፍሬ ብቻ በመውሰድ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዷል " ብለዋል።

ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው ረቂቅ ሕግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ በሕጋዊ ጋብቻ የተጣመሩ ወይም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ልጅ መውለድ የማይችሉ መሆናቸው በዘርፉ ባለሙያ ሲረጋገጥ እንደሆነ ይል ነበር፡፡

የምክር ቤት አባላት የዘር ፍሬን በሕጉ ከተፈቀደው ውጪ አሳልፎ የሰጠ አካል ከተገኘ በወንጀል ሕግ ተጠያቂ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ በአዋጁ አንቀጽ 14 በመሣሪያ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡

በዚህ ድንጋጌ በመሣሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ሥርዓትን ማቋረጥ የሚቻለው፣ የልብና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።

አፈጻጸሙ አግባብነት ባላቸው ሶስት ባለሙያዎች ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
#ሪፖርተር
Forwarded from JURIS PODCAST
በፍትሐብሔር ጉዳይ ሕግ ወደ ኋላ ሄዶ ይሰራልን ?

እንደሚታወቀው በወንጀል ጉዳይ አንድ የወንጀል ድርጊት በኢፌድሪ የወንጀል ህግ መሠረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው የወንጀል ሕግ ግን እንደወንጀል ካልተቆጠረና የተፈፀመው ይህ ሕግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ እደማይችል በኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 5(2) ላይ የወንጀል ህግ ወደኃላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑን ይደነግጋል፡፡የኢፌድሪ ህገ-መንግስትም በአንቀፅ 22(1) ላይ ማንኛውም ሰው የወንጀል ክስ ሲቀርብበት የተከሰሰበት ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑ በህግ የተደነገገ ካልሆነ በስተቀር ሊቀጣ አይችልም፡፡ሲል ይደነግጋል፡፡ይህ የወንጀል መርህ ለፍትሐብሔር ተፈፃሚነት ይኖረዋልን ?ይህን አከራካሪ ጭብጥ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 229940 (ባልታተመ) ውሳኔው ላይ ህግ ወደኃላ ተመልሶ አይሰራም በሚል የሚታወቀው መርህ መሰረት ሀሳቡ አንድ ህግ በሥራ ላይ መዋል ያለበት ሕጉ ከፀና በኃላ በተፈጠረ መብትና ግዴታ ወይም ፍሬ ነገር ላይ ተፈፃሚ መሆን እንዳለበት እና ዜጎች በሚያውቁት ህግ መተዳደር አለባቸው የሚለውን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡እንዲሁም አንድ ህግ የሚፀናበትን ጊዜ አስመልክቶ በህግ አውጪው ከተደነገገበት ቀን በፊት ለተፈጠሩት ክስተቶች ወይም መብትና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አይኖረውም የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡የዚህ መርህ ተግባራዊነት የህግ የበላይነት ከሚረጋገጥባቸው መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ስለሆነም በተለይም አንድ መሠረታዊ ህግ(substantive law) ወደ ኃላ ተመልሶ እንዲሰራ ህግ አውጪው በህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካላመለከተ በስተቀር ፍርድ ቤት ወይም ሌላ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል ለያዘው ጉዳይ ተፈፃሚነት ያለውን መሠረታዊ ህግ ሲመርጥ መሠረት ሊያደርግ የሚገባው ወይም መሠረት እንዲያደርግ የሚጠበቅበት ለክርከሩ መነሻ የሆነው ጉዳይ በተፈጠረበት ጊዜ ተፈፃሚ ሲሆን የነበረውን ህግ ሊሆን ይገባል፡፡ሲል በፍትሐብሔር ጉዳይ አንድ ህግ ወደኃላ ሄዶ የሚሰራው በህጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካመላከተ ብቻ ነው ካልሆነ አንድ ህግ ወደኃላ ሄዶ አይሰራም ማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
ፕሌይ ስቶር በመግባት ሌጋልቴክ/LegalTech ብላችሁ በቀላሉ በመፈለግ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ !
አፕሊኬሽኑን ለማውረድ በዚህ ሊንክ ግቡ   👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli

ጠበቆች የሕግ ባለሙያዎች ና ተማሪዎች በዚህ የሕግ ሶፍትዌር
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው አድራሻ መግባትና መመዝገብ ትችላላችሁ
#share  #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግምክር  #የኢትዮጵያ

https://t.me/Ethiopianlegalinsight
Forwarded from አለ ሕግ
#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦

➡ ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

➡ አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

➡  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

➡ ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

➡ ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

➡ አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

➡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

➡ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
#tikvahethiopia
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

✅Website & Social Media⌛
✅Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:✅
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM