የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
Forwarded from አለ ሕግ
#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦

➡ ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

➡ አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

➡  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

➡ ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

➡ ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

➡ አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

➡ በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

➡ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

➡ ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

➡ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

➡ መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
#tikvahethiopia
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

✅Website & Social Media⌛
✅Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:✅
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Mizan Law / ሚዛን ሎዉ⚖️ (Mesfin assefa Ali)
የህፃናት_መብት_dna_የፌደሬሽን_ምክር_ቤት.pdf
509.5 KB
1. ሕፃናት በፍ/ቤት ለማስረጃነት የሚውል የዘረ መል (DNA) ምርመራ ለማድረግ አይገደዱም፤ ምርመራውን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ብቻውንም እንደ በቂ ማስረጃ ተቆጥሮ "ሕፃኑን DNA ለማስመርመር ፈቃደኛ ያልተሆነው ልጁ የባልዬው ባይሆን ነው" የሚል  የሕግ ግምት [የፍ/ሕ/ቁ. 22ን ልብ ይሏል] በመያዝ ባልዬው የልጁ አባት አይደለም ብሎ መወሰን ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ነው::
2. በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ ልጄ አይደለም በማለት (አባትነትን ለመካድ) የሚቀርብ ክስ በጠባቡ ሊታይ የሚገባና የክስ ማቅረቢያ ጊዜውም ባልዬው የልጁን መወለደ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ ባሉት 180 ቀናት ውስጥ የመሆኑ ይርጋ የሕፃናትን ሕገ መንግሥታዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከሌሎች ይርጋዎች የተለየ ስለሆነ በአንድነት ሊታይ የማይገባ እና ተከራካሪ ወገኖች ባያነሡትም እንኳን ፍ/ቤቶች በራሳቸው አንሥተው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ ነው::
ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 94/13
ግንቦት 30/2013 ዓ.ም
Forwarded from Guyita Guna
የእምነት ማጉደል ወንጀል እና የአደራ ውል ሰ/መ/ቁ.209733 / Daniel Fikadu Law Office?
የእምነት ማጉደል ወንጀል ምን ማለት እንደሆነ እና የወንጀሉማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 675 ስር ተመልክቷል፡፡ በዚሁ አግባብ አንድ ሰው የእምነት ማጉደል ወንጀልፈፅሟል ተብሎ በወንጀል የሚቀጣው ተገቢ ያልሆነ ብልፅግናን ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰውየሆነውን እና ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይምበከፊል ለራሱ ያደረገ፣ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ወይም ይህንን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት የፈፀመ እንደሆነ እናይህንኑ በእምነት ወይም በአደራ የተቀበለውን ንብረት ወይም ጥሬ ገንዘብ እንዲመልስ ወይም እንዲከፍል ሲጠየቅ ንብረቱያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግሎት ያዋለው ለመሆኑ ማስረዳት ያልቻለ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆን ከዚሁድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 3 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ የእምነት ማጉደል ወንጀል ማቋቋሚያ
83መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ውስጥ አንዱ በአደራ የተቀበሉትን ንብረት እንዲመልስ ሲጠየቅ አለመመለስ እንደሆነ በዚሁ ድንጋጌ ስርበግልፅ ተመልክቷል፡፡
በህገ ወጥነት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለውን ንብረት በአደራፈርመው መቀበላቸው በግራ ቀኙ መካከል ያለው ግኑኝነት የውል የሚያስመስለው ቢሆንም እንዲያስቀምጡ የተሰጣቸውንንብረት ሲጠየቁ አለማቅረብ ንብረቱን የእምነት መጉደል ወንጀል አንጂ የውል ግዴታን አለመፈፀምን የሚመለከት ፍትሐ-ብሄራዊኃላፊነት አይደለም።                                           /በአደራ አሰቀማጩ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።/ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በዳንኤል ፍቃዱ /ጠበቃ/
• የቅጣት አላማዎች በጠቅላላ
ቅጣት ሊያሳካ ከተነሳለት አላማ በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የተለያዩ አላማዎችን ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህ አላማዎች በወንጀል ቅጣቶች ውስጥ በተናጥል ወይም በጣምራ ተካተው የሚገኙበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ ቅጣት የሚከተሉት ዓላማዎች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡

1. ቅጣት እንደ በቀል ማስፈፀሚያ (Retribution)
የዚህ የቅጣት ዓላማ አራማጆች ወንጀለኛው ማህበረሰቡ ተው አታድርግ ያለውን ነገር ተላልፎ በማህበረሰቡ ህይወት፣ አካል፣ ጤና፣ ሞራል፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ፋይዳ ላይ ጥቃት ስለፈፀመ ለዚህ ተገቢ ያልሆነ ድርጊቱ የጁን ማግኘት አለበት የሚል መነሻ ያላቸው ሲሆን መሠረቱም የሀሙራቢ አይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ መርሆ ነው፡፡ የዚህ ቅጣት አላማ ተቃዋሚዎች ቅጣት እንደዚህ ከሆነ ለሁሉም ወንጀሎች ተመሳሳይ አቻ ቅጣት ልናገኝላቸው አንችልም ለምሳሌ በሀገር ክደት ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ወንጀለኛ አቻ ቅጣት ምንድ ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እንዲሁም እንዲህ አይነቱ አካሄድ ዓለምን የአይነ ስውራንና የአካል ጉዳተኞች መነሃሪያ ያደርጋታል የሚል መከራከሪያ አላቸው፡፡ ይህ አይነቱ የበቀል አስተሳሰብ በዘመናዊው አለም የጎለበተውን ሰብአዊ መብት የሚቃረን በመሆኑ በአሁኑ ዘመን በአንዳንድ ሀገሮች ካልሆነ በስተቀር እንምብዛም አይገኝም፡፡

2. ቅጣትን እንደ ወንጀል መከላከያ (Deterrence)
በሌላ በኩል ደግሞ የቅጣት ግብ ወደ ፊት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል እንጂ ወንጀለኛውን መበቀል ሊሆን አይገባውም፡፡ የፈሰሰ ውሃ ስለማይታፈስ ወንጀለኛው ላደረገው ነገር የምንቀጣው ላደረገው ነገር እንደ ቅጣት ሳይሆን ወደ ፊት ቅጣት ፈርቶ ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፅሙ ለመከላከል ነው የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ወንጀለኛው ወንጀል እንዲፈፅም ያነሳሳው ምክንያት ከቅጣት ፍርሃቱ ሊበልጥ ስለሚችል እንዲሁም ሰዎች ወንጀል በሚፈፅሙበት ቅፅበት ቅጣት ትዝ ስለማይላቸው ቅጣት ሁል ጊዜ ይህን ግቡን ላይመታ ይችላል የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ በተጨማሪም በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን ወንጀልና የወንጀለኞችን ደጋጋሚነት በማውሳት ቅጣት የማስተማር ግቡን እንዳልተወጣ ያሳያል የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡

3. ቅጣት እንደ ወንጀለኛውን ማግለያና መለያ (Incapacitation)
በዚህኛው አላማ ደግሞ ቅጣት ወንጀለኛውን ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለዘላለሙ (በሞት ቅጣት) ወንጀል ከሚፈፀምበት ማህበረሰብ በማግለል ወይም በመለየት በማህበረሰቡ ላይ ድጋሜ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል ይቻላል የሚሉ ወገኖች ያሉ ሲሆን ወንጀለኛው እስር ቤት በሚሆንበት ጊዜ ማህበረሰቡ ከወንጀል ይገላገላል፤ እንደ ሞት ያሉ ቅጣቶች በሚጣልባቸው ወንጀሎች ደግሞ ወንጀለኛው በድጋሜ ወንጀል የመፈፀም እድል ስለሌለው ማህበረሰቡ ከወንጀለኛው ድጋሚ ጥፋት መታደግ ይቻላል የሚል ነው፡፡ እንደ ሌሎቹ ቅጣት ሁሉ በዚህ የቅጣት አላማ ላይም ትችቶች ያሉ ሲሆን ከሞት ቅጣት ውጭ ባሉ ቅጣቶች ላይ ወንጀለኛው እስር ቤትም ሆኖ እንደ ስርቆት፣ ግብረሰዶም፣ ግድያና የአካል ጉዳትን የመሳሰሉ ወንጀሎችን መፈፀሙ አይቀርም ወይም ከእስር ሲፈታ ጠብቆ መልሶ ወንጀል ሊሰራ ይችላል፣ እንዲያውም በእስር ቤት ቆይታው ወንጀል ተምሮ እንዴት በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ እንደሚፈፅመው፣ እንዴት የመያዝ እንድሉን እንደሚቀንስ ተምሮ ሊወጣ ስለሚችል ይህ የቅጣት አላማ ብዙ ርቀት አያስጉዝም፣ እንዲሁም የቅጣቱ ግብ እስረኛውን በማህበረሰቡ ላይ ይበልጥ በቀለኛ ስለሚያደርገው በወንጀል ተግባሩ የመግፋት ዝንባሌ ሊኖረው ይችላል የሚል ክርክር ያቀርባሉ፡፡

4. ቅጣት ወንጀለኛውን እንደ ማረሚያ (Rehabilitation)
የዚህ ቅጣት ግብ መሠረት አጥፊውን ከመረዳት የሚጀምር ሲሆን ወንጀለኛው ወንጀል ውስጥ የገባው ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች ወንጀል እንዲፈፅም ገፍተውት ስለሆነ እነዚህ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች በማከም ወንጀለኛውን ከድጋሜ ጥፋት ማረም ይቻላል የሚል ነው፡፡ ወንጀለኞች ተወልደውም ይሁን ተሰርተው ወንጀለኛ እንዲሆኑ ያደረገ ሳይኮሎጂካል፣ ባዮሎጂካል፤ ኢኮኖሚካል ወይም አካባቢያዊ አሊያም ማህበራዊ ምክንያት ስለሚኖር ወንጀለኛው ወንጀል ለመፈፀም ያነሳሳውን ምክንያት በመመርመር ምክንያቱ አክሞ በማዳን ወንጀለኛውን ጤነኛ አምራች ወንጀልን የሚጠየፍ ለማህበረሰቡ ርህራሄ የሚያሳይ አድርጎ መመለስ ስለሚቻል የቅጣት ግብ ይህ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ያለው ነው፡፡

• የቅጣት አላማና ግቦች በኢ.ፊ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ
የወንጀል ህጉ አላማና ግቦች በህጉ አንቀፅ 1 እንደዚሁም በመግቢያው ላይ በዝርዝር ተገልፀው ይገኛሉ፡፡ በዚህ መሰረት የወንጀል ሕጉ ዓላማ ስለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎችን፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ ስርዓት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ሲሆን የሕጉ ግብ ደግሞ ወንጀል እንዳይፈፀም ለመከላከል የሚያስችል ስለወንጀሎችና ስለሚያስከትሉት ቅጣት በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ይህ በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀለኞቹ ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ፣ ለሌሎችም ማስተማሪያ እንዲሆኑ፣ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሆነ በወንጀል ህጉ አንቀፅ አንድ ተገልፀዋል፡፡ በዚህ መሰረት የወንጀል ህጉ ከላይ ከተዘረዘሩት የቅጣት አላማና ግቦች ውስጥ በተለይ ችሎታ ማሳጣትን፣ ማስጠንቀቂያ መስጠት እና እርማትን ወይም መልሶ ማቋቋምን አዋህዶና አካቶ ይዟል ለማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የወንጀል ሕጉ የቅጣት ዓላማና ግቦች በሕጉ በጠቅላላም ሆነ ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ ስለቅጣት አወሳሰን በሚደነግጉት አንቀፆች ስር ተንፀባርቆ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ የወንጀል ዓይነቶች ላይ ተፈፃሚ እንዲሆኑ የተደነገጉት የቅጣት አይነቶችና መጠን ተቀባይነት ያላቸውን የቅጣት አላማና ግብ ለማሳካት የተደነገጉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በወንጀል ህጉ ጠቅላላ ክፍል በአንቀፅ 117 የተደነገገው የሞት ፍርድ፣ በአንቀፅ 123 ስር የተደነገገው ከቤተሰባዊ፣ ሙያዊና ተመሳሳይ ከሆኑ መብቶች የመሻር ቅጣት፣ በአንቀፅ 127 ስር የተገለፀው ከወታደራዊ መዓረግና የሥራ ገበታ መቀነስ ወይም ማስለቀቅ እንዲሁም ከአንቀጽ 142-150 የተገለፁት የተለያዩ ፍቃድ የመንጠቅ ቅጣቶች የወንጀል ሕጉ የቅጣት ዓላማ ወንጀል የመፈፀም ችሎታን ማሳጣት እንደሆነ የሚያስረዱ ናቸው፡፡ እንዲሁም በወንጀል ህጉ አንቀፅ 98 ስር እንደተደነገገው የፅኑ እስራት ግብ ተቀጪው እንዲታረምና ወደ ማህበራዊ ኑሮው እንዲመለስ ከማድረግ በተጨማሪ በተለይ ለህብረተሰቡ ደህንነት ጥብቅ ቁጥጥር ሥር እንዲቆይ ማድረግ ነው፡፡
👍1
ህገ-ወጥ የስራ ውል መቋረጥ የሚያስከትለው ውጤት

የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ለተዋዋይ ወገኞች ፈቃድ ብቻ እንዳይተውና ህግ ጣልቃ እንዲገባ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ከስራ ውል መቋረጥ ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው፡፡  ስለዚህም የስራ ውል በዘፈቀደ ሳይሆን በበቂ ምክንያቶች ላይ ተመስርቶ የተቋረጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ሕግ አስፈላጊውን ጥበቃ ያደርጋል፡፡ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያለ የስራ ውል በአሰሪው አነሳሽነት፣በሠራተኛው አነሳሽነት፣በህግ በተደነገገው መሰረት እና በህብረት ስምምነት በተቀመጠው መሰረት ሊቋረጥ የሚችል ሲሆን በህግ ተቀባይነት ያለው የስራ ውል መቋረጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ከአንቀፅ 23 ጀምሮ እና ዝርዝር ምክንያቶቻቸውና ሁኔታዎቻቸው ደግሞ ከዚሁ አንቀጽ ቀጥለው በሚገኙት አንቀጾች ተደንግገዋል፡፡

•  በአሰሪው አነሳሽነት የሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ እንደየ ሁኔታው በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማሰጠንቀቂያ ሊደረግ የሚችል ሆኖ የምክንያቶቹ ዝርዝር እና አፈጻጸሙ ከአንቀጽ 26 እስከ 30 ተደንግገው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሕብረት ስምምነት መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ለማቋረጥ የሚያበቃ ምክንያት ተደርጎ የተወሰደ ጉዳይም በአሰሪው አነሳሽነት ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ሊያቋርጥ የሚችል መሆኑ በአንቀጽ 27/1/ተ/ ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡  የስራ ውል በአሰሪው አነሳሽነት ሊቋረጥ የሚችለው የሰራተኛውን ጠባይ ወይም የሰራተኛው የመስራት ችሎታን ከሚመለከቱ ግልጽ ሁኔታዎች ወይም ከድርጅቱ ድርጅታዊ አቋም ወይም የስራ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት ባላቸው ምክንያቶች ብቻ ነው፡፡

•  በሰራተኛው አነሳሽነት የሚደረጉት ደግሞ ልክ በአሰሪው አነሳሽነት ሊደረግ እንደሚችለው በማስጠንቀቂያ እና ያለማሰጠንቀቂያ ውሉን የሚያቋርጥበት መንገድ  ሲሆን ( ለምሳሌ የስራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ከሚቻልባቸው ምክንያቶች ውስጥ  አሰሪው የሰራተኛውን ክብርና ሞራል የሚነካ ወይም በወንጀል የሚያስቀጣ ሌላ አድራጎት የፈፀመበት እንደሆነ) ሁኔታዎቹና ምክንያቶቹ ከአንቀጽ 31 እስከ 33 ተደንግነው ይገኛሉ፡፡


•  ውሉ በሕግ የሚቋረጥበት ምክንያቶች በአብዛኛው ከሁለቱም ወገን ቁጥጥር ውጭ ያሉ ሲሆን( የሰራተኛው መሞት፣በጡረታ መገለል፣የድርጅቱ መክሰር ወይም መዘጋት ወ.ዘ.ተ  አንቀጽ 24)፤ የስራ ውል ሁለቱም በፈቃደኝነት የሚገቡበት እንደመሆኑ ሁሉ ሁለቱም በፈቃኛነት ከተስማሙ ውሉን ሊያቋርጡ የሚችሉበት ሁኔታም በአንቀጽ 25 ስር ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ከላይ በተገለጹት ቁጥሮች በተደነገጉት ምክንያቶችና ሁኔታዎች የሚፈጸም የስራ ውል መቋረጥ ሕጋዊ የስራ ውል መቋረጥ ሲሆን ከነዚህ ውጭ የሚደረጉ የስራ ውል መቋረጥ በሕገወጥነት የሚፈረጁ ናቸው (አንቀጽ 42 ድረስ በዝርዝር ተቀምጧል)፡፡

ሰራተኛው የስራ ውሉን በህገ ወጥ መንገድ ሲያቋርጥ የሚያስከትለው ውጤት
በሠራተኛው አነሳሽነት የሚፈጸም የስራ ውል መቋረጥ ሕገወጥ ሊሆን የሚችለው ሠራተኛው ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ከሚችልባቸው በአንቀጽ 32 ስር ከተደነገጉት ውጪ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች ሆኖ ነገር ግን ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ማስጠንቀቂያ ለአሰሪው ሳይሰጥ ውሉን ያቋረጠ ከሆነ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የስራ ውሉን ያቋረጠ ሠራተኛ ለአሰሪው አሰሪው ለሱ ከሚከፍለው ቀሪ ክፍያ ውስጥ ከሠላሳ ቀናት ያልበለጠ ክፍያን በካሳ መልክ መክፈል ይኖርበታል (አንቀጽ 45)፡፡

አሰሪው የስራ ውሉን በህገ ወጥ መንገድ ሲያቋርጥ የሚያስከትለው ውጤት
አንድ አሰሪ ሰራተኛውን በህገ-ወጥ መንገድ ከስራ ቢያሰናብት ሰራተኛው ሊያገኛቸው የሚችላቸው መፍትሔዎች ምንድናቸው ወይም ውጤቱ ምን ይሆናል ለሚለው በአዋጁ ክፍል 4 አንቀፅ 43 መሰረት እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ሠራተኛው ወደ ስራ እንዲመለስ አልያም የስራ ስንብት ክፍያን ጨምሮ ካሳ እና ሌሎች ተያያዥ ክፍያዎች ተከፍለውት የስራ ውል መቋረጡ እንዲፀና ሊደረግ ይችላል፡፡ የሰራተኛው ወደ ስራ መመለስ የስራ ከባቢውን የሚረብሽ ከሆነ እና በአሰራው እና በሰራተኛው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሻክር ከሆነ ወደ ስራ ከመመለስ ይልቅ በህጉ የተቀመጡትን ክፍያዎች ፈፅሞ ማሰናበት የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ህጉ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ሁለቱን አማራጮች ያስቀመጠ ሲሆን ይህንንም በማጠናከር የፌ/ጠ/ፍ/ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 18581 ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡
ስለአመክሮ አንዳንድ ነገሮች
አመክሮ ማለት አንድ ታራሚ የእሥራት ጊዜውን ሙሉ በሙሉ ከመፈጸሙ በፊት በገደብ ወይም በሁኔታ ላይ ተመስርቶ ከእስር የሚለቀቅበትና ገደቡን ተላልፎ ሲገኝ እንደ አስፈላጊነቱ ወደነበረበት ማረሚያ ቤት እንዲመለስ የሚደረግበት አሠራር ሲሆን በአመክሮ መለቀቅ ሙሉ በሙሉ ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ሳይሆን ይልቁንም የቀረውን 1/3ኛ ቅጣት ታራሚው በገደብ ወይም ሥልጣን በተሰጠው አካል ክትትል ሥር ሆኖ እንዲፈጽም የሚደረግበት የቅጣት አፈጻጸም ሥርዓት ነው፡፡
በአመክሮ ለመለቀቅ መሟላት ያለባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች
1ኛ፣ በፍርድ ቤት ከተላለፈው ቅጣት 2/3ኛውን መፈጸም፣ የእድሜ ልክ እስራት በሚሆንበት ጊዜ ቢያንስ 20 ዓመት እስር ሲፈጽም፣
2ኛ፣ ከተበዳይ ጋር በተደረገ ስምምነት (እርቅ) ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ሊከፍል የሚገባውን ካሳ መክፈል፣
3ኛ፣ በማረሚያ ቤት ቆይታው በሥራውና በጠባዩ መሻሻል ማሳየትና
4ኛ፣ ተቀጪው “ልማደኛ ደጋጋሚ” አለመሆን ናቸው፡፡
እነዚህና መሰል የህግ ግንዛቢያችንን የሚጨምሩ ጉዳዮችን፣ አዳዲስ የሚወጡ ህጎችን፣ አዳዲስ ህግ-ነክ መረጃዎችን ለማግኘትና ለየትኛውም የህግ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/getuasnakew ሳብስክራይብ የቴሌግራም ግሩፓችንን https://t.me/debgzv174 ደግሞ ጆይን ያድርጉ።
አስተማሪ መልእክቶቻችንን ሼር በማድረግና የቴሌግራም ግሩፓችንንና ቻናላችንን ደግሞ ተደራሽ እንዲሆን ጓደኞቻችሁን አድ በማድረግና በመጋበዝ አጋርነተዎን ያሳዩን፤ ያበረታቱን።
በስልክ ልታገኙን የምትፈልጉ ወዳጆቻችን 0913771324 ላይ መደወል ይቻላል።
ምርጫዎት በአካል ቢሮ መምጣት ከሆነ ደግሞ መገናኛ የካ ክ/ከተማ አጠገብ ከሚገኘው ሰላም ታወር ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፊትለፊት እንገኛለን።
ስለስመዎት አስበው ያውቃሉ?

የፍትሀ ብሔር ህጋችን ስለስም ዘርዘር ያሉ ድንጋጌዎችን ይዟል። አንድ ሰው አንድ የቤተዘመድ እና የአባት ስም ሊኖረው፤ አንድ ወይ ሁለት የግል ስሞች ሊኖሩት እንደሚችል ደንግጓል። የግል ስም አሰጣጥን በሚከተለው መንገድ እንዲሆን ደንግጓል።
1. የአንድን ልጅ የግል ስም የሚመርጠው አባቱ ነው፡፡ አባቱ በሌለ ጊዜ የአባቱ ቤተዘመዶች ይመርጣሉ።
2. ለልጁ ሁለተኛ የግል ስም እናቱ ወይም እርሷ የሌለች እንደሆነ የእናቱ ቤተዘመዶች መርጠው ሊያወጡለት ይችላሉ።
3. የልጁ አባት ያልታወቀ በሆነ ጊዜ ወይም የልጁ አባት ወገን የሆኑ ቤተዘመዶች የሌሉት የሆነ እንደሆነ የልጁ እናት ወይም እርሷ ባትኖር የእናቱ ቤተዘመዶች ለልጁ ሁለት የግል ስም ሊሰጡት ይችላሉ።
4. ከላይ የተጠቀሱት ቤተሰቦች በሌሉበት ወቅት ለልጁ በጣም ቅርብ የሆነ ወደ ላይ የሚቆጠር ወላጅ ወይም የጎን ዝምድና ያለው ሰው የቤተዘመድ እንደራሴ በመሆን የግል ስም ሊያወጡለት ይችላሉ፡፡ በአጋጣሚም በቤተዘመድ እንደራሴዎች እንደራ በመሆን የዝምድና ደረጃ እኩል በሚሆኑበት ጊዜ የልጁን የግል ስም የሚመርጠው በእድሜ ከፍ ያለው ወደላይ የሚቆጠር ወይም የጎን ዝምድና ያለው ሊሆን ይችላል።
5. በመጨረሻም ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በሙሉ የሌሉ እንደሆነ የልጁን የግል ስም የሚያወጣው የክብር መዝገብ ሹም መኮንን በአካባቢው ከሚገኙ ልማዳዊ ስሞች መካከል መርጦ ይሆናል።
ይህንን ካነበቡ በኋላ የርሰዎ ስም እንዴት እንደወጣና ህጉንስ እንዴት እንደተመለከቱት አስተያየተዎትን እንዲሰጡን በክብር ጋብዘነዎታል።
እነዚህና መሰል የህግ ግንዛቢያችንን የሚጨምሩ ጉዳዮችን፣ አዳዲስ የሚወጡ ህጎችን፣ አዳዲስ ህግ-ነክ መረጃዎችን ለማግኘትና ለየትኛውም የህግ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/getuasnakew ሳብስክራይብ የቴሌግራም ግሩፓችንን https://t.me/debgzv174 ደግሞ ጆይን ያድርጉ።
አስተማሪ መልእክቶቻችንን ሼር በማድረግና የቴሌግራም ግሩፓችንንና ቻናላችንን ደግሞ ተደራሽ እንዲሆን ጓደኞቻችሁን አድ በማድረግና በመጋበዝ አጋርነተዎን ያሳዩን፤ ያበረታቱን።
በስልክ ልታገኙን የምትፈልጉ ወዳጆቻችን 0913771324 ላይ መደወል ይቻላል።
ምርጫዎት በአካል ቢሮ መምጣት ከሆነ ደግሞ መገናኛ የካ ክ/ከተማ አጠገብ ከሚገኘው ሰላም ታወር ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፊትለፊት እንገኛለን።
👍1
የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነታቸው ምን ያህል ነው❓ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው❓

አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ።

1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም።

2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤና ነው።

3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው።

4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች ሟሟላት።

የመንደር ውል ሕጋዊ ነው❓

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ።

ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው ❓

አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ።

ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው።

እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው።

ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው❓

በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል።

በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው❓

በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት።

ወደ ጥያቄው ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው❓

እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም :: የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ ሰጥቷል።

በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቍ 21448)

በሌላ በኩል ደግሞ የመንደር ውል በውል አዋዋይ ፊት እስካልተመዘገበ ድረስ ሕግ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቁ 83674)

ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈራረሙ ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል::

ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ❓

አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም።

ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል።

በሁለት ዓይነት ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል።

በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር ከሰረ ማለት አይደል?

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረጉ የሽያጭ ውሎች በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን  በአዋዋይ ወይም ፍርድ ቤት ፊት መከናወን ይገባቸዋል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ; የማረጋገጥ መስፈርት ውሉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዲኖረው ብቻ መከናወን ያለበት ሳይሆን ውሉ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውጤት እንዲኖረውም ጭምር መከናወን ያለበት ነው፡፡
የዜጎች መብት እና የመንግስት ግዴታ በፌደራል አሰተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ

በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት መሰረታዊ የሆነ መብት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመንግስት የአሰራር ፍትሀዊነት እና ግልፅነት ጭምር የሚገለፅ ነው፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 12 የመንግስት አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት እና ማንኛውም ኃላፊና የሕዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ደንግጓል፡፡ በዚህ መነሻነትም የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የወጣ ሲሆን አዋጁ ለዜጎች የተለያዩ መብቶችን የሚሰጥ እና በመንግስት ላይ ደግሞ ግዴታዎችን የሚጥል ነው፡፡ ይህ አዋጅ የወጣበት ምክንያት ይህን ሕገ መንግሰታዊ መርሆ መሰረት በማድረግ የአስተዳደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትሉትን ጣልቃ ገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ የሚገዛ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ የእነዚህ ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና መመሪያ አወጣጥ መርሆችንና ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰው የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትሕን ማስፈን በማስፈለጉ ነው፡፡ በአዋጁ መሰረት ዜጎች አገልግሎት የማግኘት መብት፣ የመሳተፍ መብት፣ ቅሬታ የማቅረብ መብት፣ በፍርድ ቤት ክለሳ የመጠየቅ መብት የሚሉት እና ሌሎች መብቶች አሏቸው፡፡

ምንጭ፡- የፍትህ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ
በፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለዎትን ቅሬታ/አስተያየት በቴክኖሎጂ በመታገዘ ያቅርቡ
********
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለተገልጋዮች ቅሬታ እና አስተያየት ማቅረቢያ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በውስጥ አቅም በማልማት ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ይህን መተግበሪያ ለመጠቀም ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በድምፅ አሊያም በፅሁፍ የሚያሰፍሩበት ሲስተም ሲሆን ወደ ተቋሙ ለአገልግሎት በሚመጡበት ወቅት ተቋሙ ውስጥ በሚገኘው የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮች የአንድ ማዕከል ሬጅስትራር አገልግሎት መስጫ ማዕከል ውስጥ የዳኝነት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ በስራ ክፍሉ በሚገኙ ባለሙያዎች በመታገዝ አሊያም በእጅ ስልኮ በተቋሙ ኢንተርኔት/ዋይፋይ በመጠቀም የተቋሙን QR ኮድ ስካን በማድረግ የዳኝነት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት የሚለውን በመጫን በድምፅ ወይንም በፅሁፍ ቅሬታዎን/አስተያየቶን ያቅርቡ ከሚሉ አማራጮች የሚፈልጉትን በመምረጥ ቅሬታዎን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ቅሬታው/አስተያየቱ የሚቀርበው በድምፅ ከሆነ የድምፅ ምልክቷን በመጫን መልእክቱን ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን በፅሁፍ የሚቀርብ ሲሆን ከተዘረዘሩት አስተያየት መስጫ ነጥቦች (እጅግ ከፍተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ ወይም ዝቅተኛ) አንዱን በመምረጥ አስተያየቶን መስጠት ይችላሉ፡፡

የተገልጋይ ቅሬታም ወደ ሰርቨር ገብቶ ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ ለኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የሚላክ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡

የአጠቃቀሙን ቅደም ተከተል ከስር ባለው ምስል ይመልከቱ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
ዋስትና  የሚቆይበት ጊዜ እና ተግባራዊ አፈጻጸሙ!
***
ዋስ በወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰዉ የተጠረጠረበት የወንጀል ጉዳይ ምርመራ እስኪጠናቀቅ ወይም ክሱ በፍርድ ቤት ታይቶ ዉሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በሚፈለግበት ጊዜ እና ቦታ ለማቅረብ ግዴታ ገብቶ ተጠርጣሪዉ ወይም ተከሳሹ ከእስር እንዲለቀቅ የሚያደርግ መተማመኛ መሆኑን ይገልጸዋል፡፡ በወንጀል ጉዳይ ከዋስትና ጋር በተያያዘ ከሚነሱ ጥያቄዎች ዉስጥ አንድ ዋስትና ለምንያህል ጊዜ፣ እስከመቼ ድረስ ተይዞ ይቆያል የሚለዉ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህ የዋስትና ቆይታ ጊዜ  በወንጀል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በፍትሐ ብሔር ጉዳይም መሰረታዊ የሚባል ነዉ፡፡  በልምድ እንዳየነዉ ከሆነ አንድ ሰዉ ታስሮ በዋስ መፈታቱን፣ ዋስትና አስይዞ መዉጣቱን እንጅ  ያስያዘዉ ዋስትና እስከመቼ ድረስ ተይዞ እንደሚቆይ ጉዳዩ አይደለም፡፡
እስኪ ታስረዉ በዋስ ከተፈቱ ሰዎች ዉስጥ ስንቶቹ ጉዳያቸዉን ተከታትለዉ ዋስትናቸዉን አስመልሰዋል? ዋስትና ገቢ የሚደረግባቸዉ የፍርድ ቤቶች ሞዴል 85 ስንት ያልተመለሰ የዋስትና ገንዘብ እንደያዙ ቀርተዉ ይሆን? ጥናት የሚያስፈልገዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዋስትና በሞዴል 85 የተያዙ ገንዘቦች የብዙ ዓመታት ጥርቅም ያልተወራረደ ሂሳብ ያላቸዉ ናቸዉ ፡፡

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ዋስትና የሚያስይዙ ሰዎች እንኳን በዋስ ወጣሁ እንጅ ገንዘቡን መንግስት ይብለዉ የሚል የራስን መብት የመተዉ ችግር ቢሆንም ቁልፍ ችግሩ ያለዉ ሕግ አተገባበሩ ላይ ነዉ፡፡ ዋስትና የሚሰጥበት እና የሚፈጸምበት ሥርዓት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕጉ እና በሌሎች ልዩ ሕጎች ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በወንጀል ጉዳይ የሚሰጥ ዋስትና የእድሜ ልክ ሳይሆን በጊዜ ተገድቦ የሚሰጥ ነዉ፡፡ በጊዜ የመገደቡም ዋና ዓላማ ከተጠርጣሪዎች እና ከተከሳሾች አፋጣኝ ፍትሕ ከማግኘት መብት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነዉ፡፡  የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕጉ አንቀጽ 71 ዋስትና የሚቆየዉ ፍርድ ቤቱ ለወሰነዉ ጊዜ ብቻ እንደሆነ በአስገዳጅ አስቀምጦታል፡፡ ዋስትናዉ እንዲቆይ በተወሰነበት ጊዜ ጉዳዩ ባያልቅ እንኳን ዋስትናዉ የሚቆይበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሊያራዝመዉ እንደሚችል በድንጋጌዉ ተመላክቷል፡፡
ሕጉ በተግባር ሲታይ ግን አንድ በወንጀል ጉዳይ የሚሰጥ ዋስትና ጊዜ ተቀምጦለት ሲወሰን አይታይም፡፡ ፍርድ ቤቶች አንድን ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ በዋስ እንዲወጣ ሲወስኑ ዋስትናዉ የሚቆይበትን ጊዜ ሲያስቀምጡ አይታይም፡፡ ይህም ፖሊስ እና ዓቃቤ ሕግ አንድን የወንጀል ጉዳይ አፋጥነዉ ወደ ዕልባት እንዳያደርሱ የማድረግ ዉጤት ከማስከተሉ አልፎ  የወንጀል ተጠርጣሪ እና ተከሳሾችም ዋስትና ማስያዛቸዉን እንጅ ዋስትናን ለማስመለስ ጥረት እንዳያደርጉ ምክንያት ሲሆናቸዉ ይታያል፡፡
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ዕለታዊ🔔
፣፣፣፣፣፣፣፣
ወራሽነትን ስለማጣራት?📚
---------------------__-----------~-
በዛሬው ፅሁፍ ውርስ መጣራት ማለት ምን እንደሆነ? ውርስን በማጣራት ሂደት ስለሚፈፀሙ ተግባራት ?አጣሪ እንዴት እንደሚመረጥ ?: የአጣሪው ስራ ምን እንደሆነ እና የአጣሪው ስራ የሚቀርበትን ሁኔታ እንመለከታለን።
📚ውርስን ማጣራት ማለት፦
🔥የውርስን ተቀባይ እነማን እንደሆኑ መወሰን፤
🔥የውርስ ሀብት ምን መሆኑን መወሰን
🔥ለውርሱ የሚከፈለውን ገንዘብ መቀበል ለመክፈል አስገዳጅ የሆነውን ዕዳ መክፈል
🔥ሟች በኑዛዜው ስጦታ ላደረገላቸው ሰዎች የሰጣቸውን መክፈል ነው።የፍሕቁ 944
⚖️📚ውርስ እስከ ተጣራ ድረስ እንደ ተለየ ንብረት ሆኖ ይቆጠራል።ይህም የተለየው ንብረት ለወራሾች እስኪከፋፈል ድረስ ንብረቱ ተለይቶ ይቀመጣል ማለት ነው።እንዲህም ሆኖ ከውርሱ ሀብት ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም ግዜ ለገንዘባቸው ዋስትና መያዣ የሚሆናቸው በመጣራት ላይ ያለው በውርሱ የሚገኘው ንብረት ነው።ይሁንና እነዚህ ገንዘብ ጠያቂዎቹ በወራሾቹ የግል ሀብት ላይ አንዳችም መብት የላቸውም የፍ.ሕ.ቁ 943 ።
📚⚖️ወራሾችና በኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዋች ስለውርሱ ማጣራት ወይም መካፈል ጉዳይ በመካከላቸው በሚደረገው ክርክር ሁሉ አንድ ወይም ብዙ የዘመድ አስታራቂ ዳኞች እንዲያዩት ስምምነት ለማድረግ ይቻላል።
በኑዛዜም ይሁን ያለ ኑዛዜ የሆነን ውርስ አጣሪ ተብለው በተመረጡ በአንድ ወይም በብዙ ሰዎች የሚጣራ ይሆናል።
⚖️📚አንዳንዴ አጣሪ በሕግ የሚመረጥበት ሁኔታ ይኖራል ይህም ያለ ኑዛዜ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ሰውየው ከሞተበት ቀን አንስቶ ያለ አንዳች ፎርማሊቲ የአጣሪነት መብት ይኖራቸዎል በፍ/ሕቁ 947።
📚⚖️እንዲሁም ሟች አንድ ነዛዜ የተወ እንደሆነ ሟቹ በዚሁ ኑዛዜ ውስጥ የኑዛዜ አስፈፃሚ እንዲሆን የመረጠው ሰው የአጣሪነት መብት ይኖረዋልየፍ/ሕ/ቁ 948(1)።
⚖️📚ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች እንዳሉ ሆነው የአጣሪነት ስራ በግለሰቡ ፍቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነው።ማንም ሰው የአጣሪነት ስራዎችን እንዲቀበል አይገደድም የፍ/ሕ/ቁ953።
⚖️📚 አንድ አጣሪ ውርስ እንዲያጣራ ከተደረገ የሚሰራቸው ተግባራት፦🔥ሟች አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግና በመጨረሻው ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዋች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፤
🔥የውርሱን ሀብት ማስተዳደር፤
🔥መከፈያቸው የደረሰውን የውርስ ዕዳዎች መክፈል
🔥ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈል ነው።የፍሕቁ956
በአጠቃላይ የአጣሪው ሥራ የሚቀረው አጣሪው በሕጉ ወይም በኑዛዜ ወይም በዳኞች ውሳኔ መሠረት በአንድ አዲስ አጣሪ የተተካ እንደሆነ ነው።እንዲሁም የአጣሪው ሥራ የሚቀረው አጣሪው ስራውን ፈፅሞ አሠራሩን የሚያመለክት ሂሳብ በሰጠ ጊዜ ነው።የፍ/ሕ/ቁ 956

📚⚖️📚⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️
👇👇👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ከለላ ያላቸው አካላት

🔙 በኢትዮጵያ አሁን ባለው የህግ ማዕቀፍ ካለባቸው ህዝባዊ ሀላፊነት ወይም የሚወክሉትን ህዝብ/ሀገር ጥቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉት ሰዎች ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ ወይም ያለመከሰስ መብታቸው በህግ በቀመጠው አግባብ እስካልተነሳ ድረስ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት በህግ ተሰጧቸዋል።
1ኛ. የምክር ቤት አባላት
2ኛ. ዳኞች
3ኛ. የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት
4ኛ. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
5ኛ. የምርጫ ቦርድ አባላት
6ኛ. ለምርጫ የተመወገቡ እጩዎች
7ኛ. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
ይህ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ከለላ ዋና አላማው እነዚህ አካላትን ከህግ ተጠያቂነት ለማሸሽ ሳይሆን ከአለባቸው ሀላፊነት አንፃር ስራቸውንን ከአስፈፃሚው አካል ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው።
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ክስን ስለማሻሻል

👇በፍ.ስ.ስህ.ቁ. 91. መሰረት አንድ ፍ/ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ማንኛውም ጊዜ ተከራካሪዎች ሲያመለክቱ ወይም በራሱ ጊዜ አቤቱታ እንዲሻሻል ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ ድንጋጌ በጠባቡ ሊተረጎም የሚገባው ነው፡፡ ለምሳሌ በአዲስ  ማስረጃ ለማቅረብ ማሻሻልን ነሚጠቀሙ አሉ፡፡
👇በክስ ማሻሻል ስርዓቱና ዓላማ ቀድሞ ዳኝነት ከተጠየቀበት ጉዳይ ፈጽሞ የተለየ ጥያቄ ለማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ አንቀጽ 91፣342 (መዝ.ቁ 100475(ቅጽ 19)
👇ለአንድ ክስ መሻሻል ወይም ለክርክሩ መለወጥ ቀደም ሲል የቀረብን የክስ ምክንያት በመቀየር ለመሞገት ማቅረብ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራሩ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ነው በሚል ክስ እንዲሻሻል የሚፈቅድበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ የፍ/ስ/ስ/ቁ. 91(1፣2)
👇 በመጀመሪያ በቀረበ የክስ መከላከያ መልስ ያልተካተትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መልስ አንዲሻሻል በሚል ፍ/ቤት በሰጠው ትእዛዝ መነሻነት ተካቶ ሲቀርብ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አንቀጽ 91፣244፣ መዝ.ቁ. 55973(ቅጽ 12)
👇 ከሳሽ ያቀረበው ክስ እና የክሱ ዝርዝር ይዘት የተለያየ ሆኖ የተገኘ ከሆነ ፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በማዘዝ ፤የክርክሩን ሂደት መምራት ያለበት ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91(1) (መዝ.ቁ 122249 (ቅጽ 20).👇👇👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips
❤1
የተጨማሪ አሴት ታክስ ምንነት
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ መሰረቱ ሰፊ የሆነ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ቀጥታ ያልሆነ ታክስ ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ በእቃዎች እና በአገልግሎቶች ላይ በሚደረጉ ተጨማሪ እሴቶች ላይ የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የፍጆታ ታክስ (consumption tax) በሚባለው ታክስ ዓይነት ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ የእቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋ በግብይት ሂደቶች ውስጥ በሚጨምርበት ጊዜ በእያንዳንዱ የግብይት ሂደት በተጨመረው እሴት ልክ የተጨማሪ እሴት ታክስ ይሰላል፡፡ ይህ ታክስ በእያንዳንዱ የግብይት ሂደት ላይ በመከፈሉ በአንድ እቃ ወይም በአንድ አገልግሎት ላይ በተደጋጋሚ እንደሚጣል ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ነገር ግን በግብዓት ላይ የተከፈልን ታክስ በውጤት ላይ ከተሰበሰበ ታክስ በማቀናነስ ታክስ የሚሰላበት ሥርዓት በመሆኑ ተደጋጋሚ ታክስ እንዳይሰበሰብ ያደርጋል፡፡
ታክሱ ከአስመጪዎችና ጥሬ ዕቃ አምራቾች አንስቶ እስከ ችርቻሮ ድረስ በሚደረጉ የማምረትና የማከፋፈል (የማሰራጨት) ሂደቶች በሁሉም ደረጃዎች በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት ላይ ይሰበሰባል፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰበሰበው ወይም የሚቀረጠው ምርት ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወይም የዕቃና የአገልግሎት ግብይት ሲካሄድ ነው፡፡ ይህ ታክስ በፍጆታ ላይ ወይም በተጠቃሚው ወጪ ላይ የተመሰረተ ታክስ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተጠቃሚ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በሚሸምትበት ወቅት ከሚከፍለው ዋጋ በተጨማሪ የተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ በእያንዳንዱ ግይብት ላይ የሚጨመሩ እሴቶችም ተጠቃለው በመጨረሻ ላይ በሚደረገው ግብይት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፈልባቸዋል፡፡
በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሀገራት የታክስ አጣጣል እና አሰባሰብ ሕግጋት ውስጥ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋዮች በመባል የሚታወቁት ለዚህም ታክስ ተመዝጋቢ የሚሆኑት የእቃዎች እና የአገልግሎቶች አቅራቢዎች ናቸው፡፡ በዚሁም መሰረት ዓመታዊ ታክስ የሚከፈልበት ግብይታቸው አንድ ሚለዮን ብር እና ከዚያ በላይ የሆነ ወይም ሊሆን እንደሚችል የሚገመት ሰዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ይሆናሉ፡፡
የመጨረሻ ሸማቾች ከከፈሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ በስተቀር በግብይት ሂደት ውስጥ ይህንን ታክስ ለከፈሉ ሌሎች ሰዎች የከፈሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ ስለዚህም ሸማቾች ከሚከፍሉት ታክስ ውጪ ሌላ የሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደለግበትን ሁኔታ ስንመለከት ነጋዴዎች የሚያቀርቡትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በሚገዙበት ወቅት የከፈሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ እቃዎቹን እና አገልግሎቶቹን በሚሸጡበት ጊዜ ከሚሰበስቡት ታከስ ላይ የሚቀናነስ ይሆናል፡፡
የታክስ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት
የተጨምሪ እሴት ታክስ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያለው የታክስ ዓይነት ሲሆን ይህ የታክስ ዓይነት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ ተግባራዊ የሆነው በ1994 ዓ.ም (አዋጅ ቁጥር 285/1994) ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ወቅት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ አዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 ቁጠባንና ኢንቨስትመንትን የማበረታት ሚና አለው፡፡ የካፒታል ዕቃዎችን ሳይጨምር በዕቃ እና አገልግሎት ፍጆታ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተጣለው በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ረገድ የተደረጉ ለውጦችን በተለይም የኤሌክትሮኒስ ግብይትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ከታክሱ ነፃ የመሆን መብት አተገባበርም ለውጦች ተደርገውበታል።
አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች
ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከወጣ 22 ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ አስከ አሁን ድረስ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በርካታ ለውጦች ተደርገዋል፡፡ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 እነዚህን ለውጦች እንዲያካትት የተደረገበት ሁኔታ ያለ ሲሆን፡-
1. የጉዳዮችን ምክንያታዊነት ፍሰት በተከተለ መልኩ እንዲቀረጽ እና እንዲዋቀር ተደርጓል ፡፡
2. የታክስ መርሆች በግልጽ በሚያሳይ መልኩ ተደረጃቶ የተዘጋጀ አዋጅ መሆኑ፡፡
3. ራሳቸውን ችለው መደንገግ ያለባቸው በተለይ እንደ ግብዓት ዓይነት ታክሶች ራሳቸውን ችለው እንዲደነገጉ ሆኗል፡፡
4. ነባሩ አዋጅ 285/94ን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 79/95 ላይ የተቀመጡ በአዋጁ ላይ የሌሉ ነገሮች በደንቡ ላይ ተካተው የነበሩ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ እነዚህም ከደንቡ ወጥተው በአዋጁ ላይ መደንገግ ስለነበረባቸው እንዲመጡ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ የታክስ ማስታወቅና የታክስ መክፈል ሥርዓት፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ የታክስ ደቢትና ክሬዲት አያያዝ እና መሰል ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡
5. የአዋጁ ተፈፃሚነት ወሰን ሰፋ እንዲል ተደረጎ ተደንግጓል፡፡ በማንኛውም የዕቃ ግዥ ወይም አገልግሎት የተከፈለ ማንኛውም አቅርቦት ላይ፣ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ወይም የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው አገልግሎቶችን ሩቅ ሆነው አገር ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች የሚያቀርቡ ስለሆነ ኢትዮጵያ በምትከተለው የዴስትነሽን (መዳረሻ) መርህ መሰረት አቅርቦቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከሆነ ድረስ ታክስ የሚመለከታቸው እንደሆነ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
6. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የሚታየው ዋጋ፡- የመነሻ ዋጋ የሚለው ትርጉም በግልጽ መደንገጉ እንደ አንድ አዲስ ነገር የሚወሰድ ሲሆን በተጨማሪ እሴት ታክስ ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋ የምንለው፡-
• ማንኛውም ሰው ለአቅረቦቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የከፈለው የገንዘብ መጠን በተለይም ዕቃ አቅርቦት በሚሆንበት ጊዜ የዕቃ አቅርቦቱ መያዣ ዕቃ ካለው የዕቃ መያዣው ተመላሽም ቢሆንም እሱን ታሳቢ ሳያደርግ የዕቃ መያዣውን ጭምር ታሳቢ ተደርጎ የሚከፈለው ዋጋ በተጨማሪ እሴት ታክስ የአቅርቦቱ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
• በአቅርቦቱ ምክንያት የተከፈሉ ሌሎች ማናቸውም የታክስ አይነቶች ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ ሱር ታክስ እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያዎች (ሰርቪስ ቻርጅ) የሚሏቸው ክፍያዎች ካሉ እነሱንም ሁሉ አጠቃሎ ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንደ ዋጋ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
7. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሚሆኑ ምርቶች በተመለከተ፡- የተጨማሪ እሴት ታክስን ነፃ የማድረግ ዓላማ ገቢ መጠኑ ዝቅተኛ የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ጫና ለመቀነስ እና የውጭ ንግድን (ኤክስፖርትን) ለማበረታት ተብሎ የተለያዩ ዘርፎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ሆነው ቀይተዋል፡፡ ነገር ግን የነበረው የታክስ ዓላማ ከታሰበለት ዓላማ ውጭ ሆኖ ብዙዎችን ከታክስ ነፃ አድርጎ ስለነበር ከዚህ ላይ ማሻሻያ ማድረጉ፡፡ በዚህም መሠረት ነፃ ተደርገው ከነበሩት ውስጥ ትክክለኛ ወይም ምክንያታዊ በቂ የሆነ ምክንያት የሌላቸው ወደ ታክሱ እንዲካተቱ አደርጓል፡፡
8. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የማድረግ (የመድሀኒት አቅርቦትን በተመለከተ) ሥልጣን ለገንዘብ ሚኒስቴር ተሰጥቶ የቆየ ሥልጣን ነበር አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተነስቶ የመድኃኒት እና ፈንድ አቅርቦት መሥሪያ ቤት ብቻ ሥልጣኑ ተዘዋውሯል፡፡
9. ነፃ የመሆን መብት በቀጥተኛ ጥቅም ላይ በሚውሉ የመጨረሻ ምርቶች ላይ እንጂ በግባዓቶች ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን በአዋጁ ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረት እነዚህ ባማከለ መልኩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆን ያለባቸው ተብለው የተዘረዘሩ ግብይቶች ምንምን እንደሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 10 እና አባሪ 2 ላይ ተደንግጓል፡፡
10. የማሳወቂያ እና የመክፈያ ጊዜ አንድ ወር መሆኑ፡- ይህም ግብር ከፋዮች በአካል በመገኘት ሳይሆን ቴክኖሎጂ መጠቀምን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
11. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ ያለው መስፈርት ሲሆን በግዴታ የሚመዘገቡት ዓመታዊ የሽያጭ መጠን (threshold) ሁለት ሚሊዮን ብር የሆነ ሲሆን በፈቃደኝነት መመዝገብ የሚችሉበት መስፈርት ደግሞ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን (threshold) አንድ ሚሊዮን በሚል አዋጁ አስቀምጧል፡፡ ከአንድ ሚሊዮን በታች ያሉት የሽያጭ ታክስን (ቲኦቲን) ሰብስበው ለሰብሳቢ መሥሪያ ቤቱ ገቢ እንዲያደርጉ በግልጽ አስቀምጧል፡፡
12. መሠረታዊ ድንጋጌዎችና አስተዳደር ድንጋጌዎችን ለይቷል፡፡ መሠረታዊ ድንጋጌዎችን በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ የደነገገ ሲሆን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አስተዳደር በተመለከተ ተፈፃሚነት እንዲኖረው መደረጉ (አዋጅ ቁጥር 1341 /2016 አንቀጽ 57) ፡፡
13. በኤሌክትሮኒክስ አማካኝነት የአገልግሎት አቅርቦት መከናወን በአዋጁ ሽፋን ማግኘቱ፡- በኤሌክትሮኒስ ዘዴ ግብይት በስፋት እየተካሄደ ነው፡፡ በድኅረ ገጽ፣ የኢንተርኔት ፖርታል፣ ጌት ወይ፣ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግብይት የሚፈፀምበት መደብር፣ የገበያ ቦታ፣ የማከፋፈያ መድረክ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መንገድ አቅራቢው ሩቅ ሆኖ በሩቅ የሚሰጡ አገልግሎቶች ወይም በኤለክትሮኒስ ዘዴ የሚታገዙ ዕቃዎችን በሌላሰው አማካኝነት ለ3ኛ ወገን የሚተላለፉበት ዘዴ በመሆኑ ይኸ ግብይት በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለ ስለሆነ ይህ በአዋጁ ተካቷል፡፡ ምክንቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ግብይቶችን የሚፈጽሙ አካላት አሉ፡፡ እነዚህን ግብይቶች የሚያስፈጽሙ ሌሎች አገበያዮች አሉ፡፡ ምርቱን የሚያቀርቡ ለምሳሌ፡- አማዞን፣ ጎግል ፕሌይ፣ አፕል ስቶር እና የመሳሰሉት እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ግብይት ሊያካሂዱ ስለሚችሉ ታክስ መመዘገብ አለባቸው ( አንቀጽ 2 እና 25)፡፡
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ ግብይቶች
የሚከተሉት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ አቅርቦቶች ናቸው፡፡
 በመኖሪያ ቤትነት ለሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ፣
 ከሁለት ወራት በታች ለሆነ ጊዜ የተከራየን ቤት ሳይጨምር የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣
 ፈቃድ በተሰጠው ባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም ወይም በሌላ ማናቸውም ሰው የሚሰጥ የፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦት (ብድር፣ ክሬዲት ወይም የክሬዲት ዋስትና አገልግሎት መስጠት ወይም መነገድ፤ ዕዳ መሰብሰብን እና ተሰብሳቢ ሒሳብ መሸጥን ሳይጨምር ገንዘብ፣ ተቀማጭ ሒሳብን፤ ቁጠባንና ሌሎች ተመሳሳይ ሒሳቦችን፣ ክፍያዎችን፣ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራትን (የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አግልግሎትን ሳይጨምር)፣ ዕዳን፣ ቼክን ወይም የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የሚመለከቱ ተግባራት፤ የአክስዮን ድርሻ፣ ቦንድ እና ሌሎች የግዴታ ምስክር ወረቀቶች መገበያትና ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ማናቸውም ምርጫ ወይም ዋስትና፤ የኢንቨስትመንት ፈንድ ማስተዳደር፤ የጡረታ ፈንድ፣ ፕሮቪደንት ፈንድ፣ የመድን ፈንድ ማስተላለፍ)፣
 አቅራቢው የትምህርት ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የሚያቀርባቸውን ዋጋቸው ለፕሮግራሙ የሚከፈለው ዋጋ ውስጥ የተካተተ የመማሪያ መፃሕፍት፣ ቁሳቁሶች ወይም መሣሪየዎችን ጨምሮ የትምህርት ፕሮግራሞች አቅርቦት (ዕውቅና የተሰጠው፣ ፕሮግራሙ ዲግሪ ወይም ተመሳሳይ የብቃት ማስረጃ የሚያስገኝ ከሆነ)፣
 ፈቃድ በተሰጠው አገልግሎት ሰጪ የሚከናወን የህፃናት ማቆያ አገልግሎት፣
 የሕክምና አገልግሎት፣
 በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች አቀርቦት፣
 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት፣
 ቅዱሳት መፃሕፍትን ማቅረብን ጨምሮ በእምነት ተቋማት የሚሰጡ ከእምነቱ ወይም ከሃይማኖቱ ሥርዓት ጋር በቀጥታ የተያያዙ አገልግሎቶች፣
 የሕክምና መገልገያ፣ የህክምና መሣሪያ፣ የወባ አጎበር አቅርቦት፣
 ለትርፍ ባልተቋቋሙ ድርጅቶች የሚቀርቡ በእርዳታ የሚሰጡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች
 ለግብርና አገልግሎት ብቻ የሚውል የምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የፀረ ተባይ፣ የፀረ አረም፣ የአፈርን አሲዳማነት ለመከላከል የሚውል ካልሲየም ሃይደሮኦክሳይድ (ውህድ ኖራ) ወይም የፈንገስ መከላከያ ኬሚካሎች፣
 ኢንቨስተሮች ወደ ሀገር የሚያስገቡት ወይም ከሀገር ውስጥ የሚገዙት ዕቃ (በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ በተደነገገው መሠረት )፣
 የኤሌክትሪክ ኃይል (ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን ወርሀዊ ፍጆታ ያልበለጠ) እና የታሸገ ውሃን ሳይጨምር የውሃ አቅርቦት፣
 60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኛ የሆነ ሰው የሚያቀርባቸው ማናቸውም አቅርቦቶች፣
 ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ሀሳብ መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከታክሱ ነፃ የሚደረጉ ዕቃዎች፣
 አምቡላንስ እና የእሳት አዳጋ ተሽከርካሪዎች እና መሣሪያዎች አቅርቦት፡፡
ለዚህም ማብራረያ አባሪ 2 ን ይመለከቷል፡፡
 በተጨማሪ ከታክሱ ነፃ የሆነ ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ በአዋጁ አንቀጽ 11 በተደነገገው መሠረት ሲሆን ከአዋጁ ጋር በተያያዘው አባሪ 3 የተዘረዘሩት ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርገዋል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ታክስ መክፈል ለሀገር ዕድገት እና ለዜጎች ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በሀገራችን ካሉት የታክስ ዓይነቶች ተጨማሪ እሴት ታክስ አንዱ ሲሆን ይህን ታክስ ለመንግስት መክፈል ግዴታ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል፡፡ በተጨማሪም ይህን አውቆ በወቅቱ አለመክፈል ቅጣቶችን ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሚጠበቅበትን በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡
via:- FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
Federal Justice and Law institute
Forwarded from የሕግ ቤት
ደሀ ደንብ
• ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479
ይግባኝ ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ እንዲፈቀድ በቀረበ ጥያቄ ላይ ሊሰጥ የሚችለው ትእዛዝ እንደነገሩ ሁኔታ ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንደኛው ከሣሽ የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችለው የገንዘብ አቅም የሌለው ስለሆነ እንደ ጥያቄው የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከሣሹ ድሃ ያለመሆኑ ስለተረጋገጠ ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈለ በቀር በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ አይችልም የሚለው ነው፡፡
በመጀመሪያው አኳኋን ትእዛዝ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ትእዛዝ መሠረት ፋይሉ ተከፍቶ ክርክሩ የሚቀጥል ነው፡፡ የክርክሩ ውጤት የሚታወቀው ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር ማስረጃ መሠረት ነው፡፡ በመጨረሻው የክርክር ውጤት ተከሣሹ ባይስማማ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ክሱ ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ እንዲከፈት መደረጉ የሕግ ድጋፍ አልነበረውም የሚለውን እንደ አንድ የይግባኝ ምክንያት በማድረግ በውሣኔው ላይ ካለው ቅሬታ ጋር አዳምሮ ማቅረብ ይኖርበታል እንጂ ከሥረ-ነገሩ ፍርድ በፊት የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብት አይኖረውም፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320/3/ የተመለከተው ድንጋጌም በዚህ አኳኋን በሚቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ክልከላ ለማድረግ ነው፡፡
በሌላ በኩል ድሀ ያለመሆንህ ተረጋግጧል፡፡ የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈልክ በቀር ፋይል አይከፈትም ለተባለው ከሣሽ ግን ይህ ዓይነቱ ትእዛዝ የመጨረሻ ነው፡፡ ሌላ የሚጠበቅ የሥረ-ነገር ፍርድ የለውም፡፡ ስለሆነም የዳኝት ገንዘብ ለመክፈል አቅም ሳይኖረኝ ክርክሬና ማስረጃዬ በአግባቡ ሳይታይ አቅም እንዳለኝ ተቆጥሮ የዳኝነት ገንዘብ ክፈል መባሌ ተገቢ አይደለም የሚል ከሆነ የተሰጠው ትእዛዝ የመጨረሻ እንደመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320/1/ መሠረት የይግባኝ አቤትታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 23744 ቅጽ 6፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 320.
በውጭ ሀገር የተሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ስለሚፈፀምበት ስነስርዓት

በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን በአንቀፅ 458 እንደተገለፀው በውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈፀም የሚችለው
1) እንዲፈፀም የተጠየቀውን ፍርድ የወሰነው ፍርድ ቤት የሚገኝበት ሀገር በኢትዮጵያ የተሰጠውን ፍርድም የሚፈፀም መሆኑ ሲረጋገጥ
2) ፍርዱ የተሰጠው በህግ በተቋቋመ ፍ/ቤት መሆኑ ሲረጋገጥ
3) የፍርድ ባለዕዳው ቀርቦ መቃወሚያውን ለማሰማት መብት የተሰጠው መሆኑ ሲረጋገጥ
4) ፍርዱ የመጨረሻ እና ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ ሲታወቅ
5) የፍርዱ መፈፀም ለሕዝብ ሞራልና ፀጥታ ተቃራኒ ያለመሆኑ ሲታወቅ እንደሆነ ነው፡፡
እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በአጠቃላይ መሟላት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በውጭ አገር የተሰጠውን ፍርድ ለማስፈፃም የሚያስችላቸው ሲሆን በተናጥል መሟላት የኢትዮጵያን ፍርድ ቤቶች በውጭ ሀገር የተሰጠውን ፍርድ ለማስፈፀም የሚያስችላቸው አይሆንም፡፡