የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የዜጎች መብት እና የመንግስት ግዴታ በፌደራል አሰተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕግ

በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የዜጎች ፍትህ የማግኘት መብት መሰረታዊ የሆነ መብት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በመንግስት የአሰራር ፍትሀዊነት እና ግልፅነት ጭምር የሚገለፅ ነው፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 12 የመንግስት አሰራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን እንዳለበት እና ማንኛውም ኃላፊና የሕዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ደንግጓል፡፡ በዚህ መነሻነትም የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 የወጣ ሲሆን አዋጁ ለዜጎች የተለያዩ መብቶችን የሚሰጥ እና በመንግስት ላይ ደግሞ ግዴታዎችን የሚጥል ነው፡፡ ይህ አዋጅ የወጣበት ምክንያት ይህን ሕገ መንግሰታዊ መርሆ መሰረት በማድረግ የአስተዳደር ተቋማት በሰዎች መብቶችና ጥቅሞች ላይ የሚያስከትሉትን ጣልቃ ገብነት በሕግ የሚመራና ለሕግ የሚገዛ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ የእነዚህ ተቋማት የውሳኔ አሰጣጥና መመሪያ አወጣጥ መርሆችንና ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም በአስተዳደራዊ ውሳኔዎችና መመሪያዎች ቅር የተሰኘ ሰው የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ሕጋዊነት በፍርድ ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓት በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትሕን ማስፈን በማስፈለጉ ነው፡፡ በአዋጁ መሰረት ዜጎች አገልግሎት የማግኘት መብት፣ የመሳተፍ መብት፣ ቅሬታ የማቅረብ መብት፣ በፍርድ ቤት ክለሳ የመጠየቅ መብት የሚሉት እና ሌሎች መብቶች አሏቸው፡፡

ምንጭ፡- የፍትህ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ
በፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለዎትን ቅሬታ/አስተያየት በቴክኖሎጂ በመታገዘ ያቅርቡ
********
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለተገልጋዮች ቅሬታ እና አስተያየት ማቅረቢያ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በውስጥ አቅም በማልማት ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ይህን መተግበሪያ ለመጠቀም ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በድምፅ አሊያም በፅሁፍ የሚያሰፍሩበት ሲስተም ሲሆን ወደ ተቋሙ ለአገልግሎት በሚመጡበት ወቅት ተቋሙ ውስጥ በሚገኘው የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮች የአንድ ማዕከል ሬጅስትራር አገልግሎት መስጫ ማዕከል ውስጥ የዳኝነት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ በስራ ክፍሉ በሚገኙ ባለሙያዎች በመታገዝ አሊያም በእጅ ስልኮ በተቋሙ ኢንተርኔት/ዋይፋይ በመጠቀም የተቋሙን QR ኮድ ስካን በማድረግ የዳኝነት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት የሚለውን በመጫን በድምፅ ወይንም በፅሁፍ ቅሬታዎን/አስተያየቶን ያቅርቡ ከሚሉ አማራጮች የሚፈልጉትን በመምረጥ ቅሬታዎን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

ቅሬታው/አስተያየቱ የሚቀርበው በድምፅ ከሆነ የድምፅ ምልክቷን በመጫን መልእክቱን ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን በፅሁፍ የሚቀርብ ሲሆን ከተዘረዘሩት አስተያየት መስጫ ነጥቦች (እጅግ ከፍተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ ወይም ዝቅተኛ) አንዱን በመምረጥ አስተያየቶን መስጠት ይችላሉ፡፡

የተገልጋይ ቅሬታም ወደ ሰርቨር ገብቶ ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ ለኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የሚላክ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡

የአጠቃቀሙን ቅደም ተከተል ከስር ባለው ምስል ይመልከቱ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
ዋስትና  የሚቆይበት ጊዜ እና ተግባራዊ አፈጻጸሙ!
***
ዋስ በወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተከሰሰ ሰዉ የተጠረጠረበት የወንጀል ጉዳይ ምርመራ እስኪጠናቀቅ ወይም ክሱ በፍርድ ቤት ታይቶ ዉሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በሚፈለግበት ጊዜ እና ቦታ ለማቅረብ ግዴታ ገብቶ ተጠርጣሪዉ ወይም ተከሳሹ ከእስር እንዲለቀቅ የሚያደርግ መተማመኛ መሆኑን ይገልጸዋል፡፡ በወንጀል ጉዳይ ከዋስትና ጋር በተያያዘ ከሚነሱ ጥያቄዎች ዉስጥ አንድ ዋስትና ለምንያህል ጊዜ፣ እስከመቼ ድረስ ተይዞ ይቆያል የሚለዉ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህ የዋስትና ቆይታ ጊዜ  በወንጀል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በፍትሐ ብሔር ጉዳይም መሰረታዊ የሚባል ነዉ፡፡  በልምድ እንዳየነዉ ከሆነ አንድ ሰዉ ታስሮ በዋስ መፈታቱን፣ ዋስትና አስይዞ መዉጣቱን እንጅ  ያስያዘዉ ዋስትና እስከመቼ ድረስ ተይዞ እንደሚቆይ ጉዳዩ አይደለም፡፡
እስኪ ታስረዉ በዋስ ከተፈቱ ሰዎች ዉስጥ ስንቶቹ ጉዳያቸዉን ተከታትለዉ ዋስትናቸዉን አስመልሰዋል? ዋስትና ገቢ የሚደረግባቸዉ የፍርድ ቤቶች ሞዴል 85 ስንት ያልተመለሰ የዋስትና ገንዘብ እንደያዙ ቀርተዉ ይሆን? ጥናት የሚያስፈልገዉ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዋስትና በሞዴል 85 የተያዙ ገንዘቦች የብዙ ዓመታት ጥርቅም ያልተወራረደ ሂሳብ ያላቸዉ ናቸዉ ፡፡

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ዋስትና የሚያስይዙ ሰዎች እንኳን በዋስ ወጣሁ እንጅ ገንዘቡን መንግስት ይብለዉ የሚል የራስን መብት የመተዉ ችግር ቢሆንም ቁልፍ ችግሩ ያለዉ ሕግ አተገባበሩ ላይ ነዉ፡፡ ዋስትና የሚሰጥበት እና የሚፈጸምበት ሥርዓት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕጉ እና በሌሎች ልዩ ሕጎች ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በወንጀል ጉዳይ የሚሰጥ ዋስትና የእድሜ ልክ ሳይሆን በጊዜ ተገድቦ የሚሰጥ ነዉ፡፡ በጊዜ የመገደቡም ዋና ዓላማ ከተጠርጣሪዎች እና ከተከሳሾች አፋጣኝ ፍትሕ ከማግኘት መብት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነዉ፡፡  የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕጉ አንቀጽ 71 ዋስትና የሚቆየዉ ፍርድ ቤቱ ለወሰነዉ ጊዜ ብቻ እንደሆነ በአስገዳጅ አስቀምጦታል፡፡ ዋስትናዉ እንዲቆይ በተወሰነበት ጊዜ ጉዳዩ ባያልቅ እንኳን ዋስትናዉ የሚቆይበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሊያራዝመዉ እንደሚችል በድንጋጌዉ ተመላክቷል፡፡
ሕጉ በተግባር ሲታይ ግን አንድ በወንጀል ጉዳይ የሚሰጥ ዋስትና ጊዜ ተቀምጦለት ሲወሰን አይታይም፡፡ ፍርድ ቤቶች አንድን ተጠርጣሪ ወይም ተከሳሽ በዋስ እንዲወጣ ሲወስኑ ዋስትናዉ የሚቆይበትን ጊዜ ሲያስቀምጡ አይታይም፡፡ ይህም ፖሊስ እና ዓቃቤ ሕግ አንድን የወንጀል ጉዳይ አፋጥነዉ ወደ ዕልባት እንዳያደርሱ የማድረግ ዉጤት ከማስከተሉ አልፎ  የወንጀል ተጠርጣሪ እና ተከሳሾችም ዋስትና ማስያዛቸዉን እንጅ ዋስትናን ለማስመለስ ጥረት እንዳያደርጉ ምክንያት ሲሆናቸዉ ይታያል፡፡
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ዕለታዊ🔔
፣፣፣፣፣፣፣፣
ወራሽነትን ስለማጣራት?📚
---------------------__-----------~-
በዛሬው ፅሁፍ ውርስ መጣራት ማለት ምን እንደሆነ? ውርስን በማጣራት ሂደት ስለሚፈፀሙ ተግባራት ?አጣሪ እንዴት እንደሚመረጥ ?: የአጣሪው ስራ ምን እንደሆነ እና የአጣሪው ስራ የሚቀርበትን ሁኔታ እንመለከታለን።
📚ውርስን ማጣራት ማለት፦
🔥የውርስን ተቀባይ እነማን እንደሆኑ መወሰን፤
🔥የውርስ ሀብት ምን መሆኑን መወሰን
🔥ለውርሱ የሚከፈለውን ገንዘብ መቀበል ለመክፈል አስገዳጅ የሆነውን ዕዳ መክፈል
🔥ሟች በኑዛዜው ስጦታ ላደረገላቸው ሰዎች የሰጣቸውን መክፈል ነው።የፍሕቁ 944
⚖️📚ውርስ እስከ ተጣራ ድረስ እንደ ተለየ ንብረት ሆኖ ይቆጠራል።ይህም የተለየው ንብረት ለወራሾች እስኪከፋፈል ድረስ ንብረቱ ተለይቶ ይቀመጣል ማለት ነው።እንዲህም ሆኖ ከውርሱ ሀብት ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሊኖሩ ይችላሉ በዚህም ግዜ ለገንዘባቸው ዋስትና መያዣ የሚሆናቸው በመጣራት ላይ ያለው በውርሱ የሚገኘው ንብረት ነው።ይሁንና እነዚህ ገንዘብ ጠያቂዎቹ በወራሾቹ የግል ሀብት ላይ አንዳችም መብት የላቸውም የፍ.ሕ.ቁ 943 ።
📚⚖️ወራሾችና በኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዋች ስለውርሱ ማጣራት ወይም መካፈል ጉዳይ በመካከላቸው በሚደረገው ክርክር ሁሉ አንድ ወይም ብዙ የዘመድ አስታራቂ ዳኞች እንዲያዩት ስምምነት ለማድረግ ይቻላል።
በኑዛዜም ይሁን ያለ ኑዛዜ የሆነን ውርስ አጣሪ ተብለው በተመረጡ በአንድ ወይም በብዙ ሰዎች የሚጣራ ይሆናል።
⚖️📚አንዳንዴ አጣሪ በሕግ የሚመረጥበት ሁኔታ ይኖራል ይህም ያለ ኑዛዜ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ሰውየው ከሞተበት ቀን አንስቶ ያለ አንዳች ፎርማሊቲ የአጣሪነት መብት ይኖራቸዎል በፍ/ሕቁ 947።
📚⚖️እንዲሁም ሟች አንድ ነዛዜ የተወ እንደሆነ ሟቹ በዚሁ ኑዛዜ ውስጥ የኑዛዜ አስፈፃሚ እንዲሆን የመረጠው ሰው የአጣሪነት መብት ይኖረዋልየፍ/ሕ/ቁ 948(1)።
⚖️📚ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች እንዳሉ ሆነው የአጣሪነት ስራ በግለሰቡ ፍቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሠረተ ነው።ማንም ሰው የአጣሪነት ስራዎችን እንዲቀበል አይገደድም የፍ/ሕ/ቁ953።
⚖️📚 አንድ አጣሪ ውርስ እንዲያጣራ ከተደረገ የሚሰራቸው ተግባራት፦🔥ሟች አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግና በመጨረሻው ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዋች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፤
🔥የውርሱን ሀብት ማስተዳደር፤
🔥መከፈያቸው የደረሰውን የውርስ ዕዳዎች መክፈል
🔥ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈል ነው።የፍሕቁ956
በአጠቃላይ የአጣሪው ሥራ የሚቀረው አጣሪው በሕጉ ወይም በኑዛዜ ወይም በዳኞች ውሳኔ መሠረት በአንድ አዲስ አጣሪ የተተካ እንደሆነ ነው።እንዲሁም የአጣሪው ሥራ የሚቀረው አጣሪው ስራውን ፈፅሞ አሠራሩን የሚያመለክት ሂሳብ በሰጠ ጊዜ ነው።የፍ/ሕ/ቁ 956

📚⚖️📚⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️
👇👇👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips
ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ከለላ ያላቸው አካላት

🔙 በኢትዮጵያ አሁን ባለው የህግ ማዕቀፍ ካለባቸው ህዝባዊ ሀላፊነት ወይም የሚወክሉትን ህዝብ/ሀገር ጥቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉት ሰዎች ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፈንጅ ካልተያዙ ወይም ያለመከሰስ መብታቸው በህግ በቀመጠው አግባብ እስካልተነሳ ድረስ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት በህግ ተሰጧቸዋል።
1ኛ. የምክር ቤት አባላት
2ኛ. ዳኞች
3ኛ. የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት
4ኛ. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
5ኛ. የምርጫ ቦርድ አባላት
6ኛ. ለምርጫ የተመወገቡ እጩዎች
7ኛ. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች
ይህ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብት ከለላ ዋና አላማው እነዚህ አካላትን ከህግ ተጠያቂነት ለማሸሽ ሳይሆን ከአለባቸው ሀላፊነት አንፃር ስራቸውንን ከአስፈፃሚው አካል ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው እንዲሰሩ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው።
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
ክስን ስለማሻሻል

👇በፍ.ስ.ስህ.ቁ. 91. መሰረት አንድ ፍ/ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ማንኛውም ጊዜ ተከራካሪዎች ሲያመለክቱ ወይም በራሱ ጊዜ አቤቱታ እንዲሻሻል ሊያዝ ይችላል፡፡ ይህ ድንጋጌ በጠባቡ ሊተረጎም የሚገባው ነው፡፡ ለምሳሌ በአዲስ  ማስረጃ ለማቅረብ ማሻሻልን ነሚጠቀሙ አሉ፡፡
👇በክስ ማሻሻል ስርዓቱና ዓላማ ቀድሞ ዳኝነት ከተጠየቀበት ጉዳይ ፈጽሞ የተለየ ጥያቄ ለማቅረብ የማይችል ስለመሆኑ አንቀጽ 91፣342 (መዝ.ቁ 100475(ቅጽ 19)
👇ለአንድ ክስ መሻሻል ወይም ለክርክሩ መለወጥ ቀደም ሲል የቀረብን የክስ ምክንያት በመቀየር ለመሞገት ማቅረብ ነገሩን ይበልጥ የሚያብራሩ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት የሚረዳ ነው በሚል ክስ እንዲሻሻል የሚፈቅድበት የህግ ምክንያት ስላለመኖሩ የፍ/ስ/ስ/ቁ. 91(1፣2)
👇 በመጀመሪያ በቀረበ የክስ መከላከያ መልስ ያልተካተትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መልስ አንዲሻሻል በሚል ፍ/ቤት በሰጠው ትእዛዝ መነሻነት ተካቶ ሲቀርብ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችልበት የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አንቀጽ 91፣244፣ መዝ.ቁ. 55973(ቅጽ 12)
👇 ከሳሽ ያቀረበው ክስ እና የክሱ ዝርዝር ይዘት የተለያየ ሆኖ የተገኘ ከሆነ ፤ ጉዲዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በማዘዝ ፤የክርክሩን ሂደት መምራት ያለበት ሰለመሆኑ፤ ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91(1) (መዝ.ቁ 122249 (ቅጽ 20).👇👇👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips
❤1
የተጨማሪ አሴት ታክስ ምንነት
የተጨማሪ ዕሴት ታክስ መሰረቱ ሰፊ የሆነ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ቀጥታ ያልሆነ ታክስ ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ በእቃዎች እና በአገልግሎቶች ላይ በሚደረጉ ተጨማሪ እሴቶች ላይ የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የፍጆታ ታክስ (consumption tax) በሚባለው ታክስ ዓይነት ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ የእቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋ በግብይት ሂደቶች ውስጥ በሚጨምርበት ጊዜ በእያንዳንዱ የግብይት ሂደት በተጨመረው እሴት ልክ የተጨማሪ እሴት ታክስ ይሰላል፡፡ ይህ ታክስ በእያንዳንዱ የግብይት ሂደት ላይ በመከፈሉ በአንድ እቃ ወይም በአንድ አገልግሎት ላይ በተደጋጋሚ እንደሚጣል ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ነገር ግን በግብዓት ላይ የተከፈልን ታክስ በውጤት ላይ ከተሰበሰበ ታክስ በማቀናነስ ታክስ የሚሰላበት ሥርዓት በመሆኑ ተደጋጋሚ ታክስ እንዳይሰበሰብ ያደርጋል፡፡
ታክሱ ከአስመጪዎችና ጥሬ ዕቃ አምራቾች አንስቶ እስከ ችርቻሮ ድረስ በሚደረጉ የማምረትና የማከፋፈል (የማሰራጨት) ሂደቶች በሁሉም ደረጃዎች በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት ላይ ይሰበሰባል፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰበሰበው ወይም የሚቀረጠው ምርት ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወይም የዕቃና የአገልግሎት ግብይት ሲካሄድ ነው፡፡ ይህ ታክስ በፍጆታ ላይ ወይም በተጠቃሚው ወጪ ላይ የተመሰረተ ታክስ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተጠቃሚ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በሚሸምትበት ወቅት ከሚከፍለው ዋጋ በተጨማሪ የተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ በእያንዳንዱ ግይብት ላይ የሚጨመሩ እሴቶችም ተጠቃለው በመጨረሻ ላይ በሚደረገው ግብይት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፈልባቸዋል፡፡
በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሀገራት የታክስ አጣጣል እና አሰባሰብ ሕግጋት ውስጥ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋዮች በመባል የሚታወቁት ለዚህም ታክስ ተመዝጋቢ የሚሆኑት የእቃዎች እና የአገልግሎቶች አቅራቢዎች ናቸው፡፡ በዚሁም መሰረት ዓመታዊ ታክስ የሚከፈልበት ግብይታቸው አንድ ሚለዮን ብር እና ከዚያ በላይ የሆነ ወይም ሊሆን እንደሚችል የሚገመት ሰዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች ይሆናሉ፡፡
የመጨረሻ ሸማቾች ከከፈሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ በስተቀር በግብይት ሂደት ውስጥ ይህንን ታክስ ለከፈሉ ሌሎች ሰዎች የከፈሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ ስለዚህም ሸማቾች ከሚከፍሉት ታክስ ውጪ ሌላ የሚከፈል የተጨማሪ እሴት ታክስ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ የሚደለግበትን ሁኔታ ስንመለከት ነጋዴዎች የሚያቀርቡትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በሚገዙበት ወቅት የከፈሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ እቃዎቹን እና አገልግሎቶቹን በሚሸጡበት ጊዜ ከሚሰበስቡት ታከስ ላይ የሚቀናነስ ይሆናል፡፡
የታክስ ሕጉን ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት
የተጨምሪ እሴት ታክስ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ያለው የታክስ ዓይነት ሲሆን ይህ የታክስ ዓይነት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ ተግባራዊ የሆነው በ1994 ዓ.ም (አዋጅ ቁጥር 285/1994) ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ወቅት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ አዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 ቁጠባንና ኢንቨስትመንትን የማበረታት ሚና አለው፡፡ የካፒታል ዕቃዎችን ሳይጨምር በዕቃ እና አገልግሎት ፍጆታ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተጣለው በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ረገድ የተደረጉ ለውጦችን በተለይም የኤሌክትሮኒስ ግብይትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በተጨማሪም ከታክሱ ነፃ የመሆን መብት አተገባበርም ለውጦች ተደርገውበታል።
አዳዲስ የተካተቱ ጉዳዮች
ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከወጣ 22 ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ አስከ አሁን ድረስ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በርካታ ለውጦች ተደርገዋል፡፡ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 እነዚህን ለውጦች እንዲያካትት የተደረገበት ሁኔታ ያለ ሲሆን፡-
1. የጉዳዮችን ምክንያታዊነት ፍሰት በተከተለ መልኩ እንዲቀረጽ እና እንዲዋቀር ተደርጓል ፡፡
2. የታክስ መርሆች በግልጽ በሚያሳይ መልኩ ተደረጃቶ የተዘጋጀ አዋጅ መሆኑ፡፡
3. ራሳቸውን ችለው መደንገግ ያለባቸው በተለይ እንደ ግብዓት ዓይነት ታክሶች ራሳቸውን ችለው እንዲደነገጉ ሆኗል፡፡
4. ነባሩ አዋጅ 285/94ን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 79/95 ላይ የተቀመጡ በአዋጁ ላይ የሌሉ ነገሮች በደንቡ ላይ ተካተው የነበሩ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ እነዚህም ከደንቡ ወጥተው በአዋጁ ላይ መደንገግ ስለነበረባቸው እንዲመጡ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ የታክስ ማስታወቅና የታክስ መክፈል ሥርዓት፣ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣ የታክስ ደቢትና ክሬዲት አያያዝ እና መሰል ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡
5. የአዋጁ ተፈፃሚነት ወሰን ሰፋ እንዲል ተደረጎ ተደንግጓል፡፡ በማንኛውም የዕቃ ግዥ ወይም አገልግሎት የተከፈለ ማንኛውም አቅርቦት ላይ፣ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ወይም የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው አገልግሎቶችን ሩቅ ሆነው አገር ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች የሚያቀርቡ ስለሆነ ኢትዮጵያ በምትከተለው የዴስትነሽን (መዳረሻ) መርህ መሰረት አቅርቦቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከሆነ ድረስ ታክስ የሚመለከታቸው እንደሆነ በአዋጁ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
6. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የሚታየው ዋጋ፡- የመነሻ ዋጋ የሚለው ትርጉም በግልጽ መደንገጉ እንደ አንድ አዲስ ነገር የሚወሰድ ሲሆን በተጨማሪ እሴት ታክስ ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋ የምንለው፡-
• ማንኛውም ሰው ለአቅረቦቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የከፈለው የገንዘብ መጠን በተለይም ዕቃ አቅርቦት በሚሆንበት ጊዜ የዕቃ አቅርቦቱ መያዣ ዕቃ ካለው የዕቃ መያዣው ተመላሽም ቢሆንም እሱን ታሳቢ ሳያደርግ የዕቃ መያዣውን ጭምር ታሳቢ ተደርጎ የሚከፈለው ዋጋ በተጨማሪ እሴት ታክስ የአቅርቦቱ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
• በአቅርቦቱ ምክንያት የተከፈሉ ሌሎች ማናቸውም የታክስ አይነቶች ቀረጥ፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ ሱር ታክስ እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያዎች (ሰርቪስ ቻርጅ) የሚሏቸው ክፍያዎች ካሉ እነሱንም ሁሉ አጠቃሎ ለተጨማሪ እሴት ታክስ እንደ ዋጋ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
7. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሚሆኑ ምርቶች በተመለከተ፡- የተጨማሪ እሴት ታክስን ነፃ የማድረግ ዓላማ ገቢ መጠኑ ዝቅተኛ የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ጫና ለመቀነስ እና የውጭ ንግድን (ኤክስፖርትን) ለማበረታት ተብሎ የተለያዩ ዘርፎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ሆነው ቀይተዋል፡፡ ነገር ግን የነበረው የታክስ ዓላማ ከታሰበለት ዓላማ ውጭ ሆኖ ብዙዎችን ከታክስ ነፃ አድርጎ ስለነበር ከዚህ ላይ ማሻሻያ ማድረጉ፡፡ በዚህም መሠረት ነፃ ተደርገው ከነበሩት ውስጥ ትክክለኛ ወይም ምክንያታዊ በቂ የሆነ ምክንያት የሌላቸው ወደ ታክሱ እንዲካተቱ አደርጓል፡፡
8. ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የማድረግ (የመድሀኒት አቅርቦትን በተመለከተ) ሥልጣን ለገንዘብ ሚኒስቴር ተሰጥቶ የቆየ ሥልጣን ነበር አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተነስቶ የመድኃኒት እና ፈንድ አቅርቦት መሥሪያ ቤት ብቻ ሥልጣኑ ተዘዋውሯል፡፡
9. ነፃ የመሆን መብት በቀጥተኛ ጥቅም ላይ በሚውሉ የመጨረሻ ምርቶች ላይ እንጂ በግባዓቶች ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን በአዋጁ ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሰረት እነዚህ ባማከለ መልኩ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆን ያለባቸው ተብለው የተዘረዘሩ ግብይቶች ምንምን እንደሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 10 እና አባሪ 2 ላይ ተደንግጓል፡፡
10. የማሳወቂያ እና የመክፈያ ጊዜ አንድ ወር መሆኑ፡- ይህም ግብር ከፋዮች በአካል በመገኘት ሳይሆን ቴክኖሎጂ መጠቀምን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
11. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ለመመዝገብ ያለው መስፈርት ሲሆን በግዴታ የሚመዘገቡት ዓመታዊ የሽያጭ መጠን (threshold) ሁለት ሚሊዮን ብር የሆነ ሲሆን በፈቃደኝነት መመዝገብ የሚችሉበት መስፈርት ደግሞ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን (threshold) አንድ ሚሊዮን በሚል አዋጁ አስቀምጧል፡፡ ከአንድ ሚሊዮን በታች ያሉት የሽያጭ ታክስን (ቲኦቲን) ሰብስበው ለሰብሳቢ መሥሪያ ቤቱ ገቢ እንዲያደርጉ በግልጽ አስቀምጧል፡፡
12. መሠረታዊ ድንጋጌዎችና አስተዳደር ድንጋጌዎችን ለይቷል፡፡ መሠረታዊ ድንጋጌዎችን በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ላይ የደነገገ ሲሆን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አስተዳደር በተመለከተ ተፈፃሚነት እንዲኖረው መደረጉ (አዋጅ ቁጥር 1341 /2016 አንቀጽ 57) ፡፡
13. በኤሌክትሮኒክስ አማካኝነት የአገልግሎት አቅርቦት መከናወን በአዋጁ ሽፋን ማግኘቱ፡- በኤሌክትሮኒስ ዘዴ ግብይት በስፋት እየተካሄደ ነው፡፡ በድኅረ ገጽ፣ የኢንተርኔት ፖርታል፣ ጌት ወይ፣ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግብይት የሚፈፀምበት መደብር፣ የገበያ ቦታ፣ የማከፋፈያ መድረክ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መንገድ አቅራቢው ሩቅ ሆኖ በሩቅ የሚሰጡ አገልግሎቶች ወይም በኤለክትሮኒስ ዘዴ የሚታገዙ ዕቃዎችን በሌላሰው አማካኝነት ለ3ኛ ወገን የሚተላለፉበት ዘዴ በመሆኑ ይኸ ግብይት በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለ ስለሆነ ይህ በአዋጁ ተካቷል፡፡ ምክንቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ግብይቶችን የሚፈጽሙ አካላት አሉ፡፡ እነዚህን ግብይቶች የሚያስፈጽሙ ሌሎች አገበያዮች አሉ፡፡ ምርቱን የሚያቀርቡ ለምሳሌ፡- አማዞን፣ ጎግል ፕሌይ፣ አፕል ስቶር እና የመሳሰሉት እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ግብይት ሊያካሂዱ ስለሚችሉ ታክስ መመዘገብ አለባቸው ( አንቀጽ 2 እና 25)፡፡
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ ግብይቶች
የሚከተሉት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ አቅርቦቶች ናቸው፡፡
 በመኖሪያ ቤትነት ለሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ፣
 ከሁለት ወራት በታች ለሆነ ጊዜ የተከራየን ቤት ሳይጨምር የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣
 ፈቃድ በተሰጠው ባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም ወይም በሌላ ማናቸውም ሰው የሚሰጥ የፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦት (ብድር፣ ክሬዲት ወይም የክሬዲት ዋስትና አገልግሎት መስጠት ወይም መነገድ፤ ዕዳ መሰብሰብን እና ተሰብሳቢ ሒሳብ መሸጥን ሳይጨምር ገንዘብ፣ ተቀማጭ ሒሳብን፤ ቁጠባንና ሌሎች ተመሳሳይ ሒሳቦችን፣ ክፍያዎችን፣ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራትን (የፋይናንስ ቴክኖሎጂ አግልግሎትን ሳይጨምር)፣ ዕዳን፣ ቼክን ወይም የሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችን የሚመለከቱ ተግባራት፤ የአክስዮን ድርሻ፣ ቦንድ እና ሌሎች የግዴታ ምስክር ወረቀቶች መገበያትና ከእነዚህ ጋር የተያያዘ ማናቸውም ምርጫ ወይም ዋስትና፤ የኢንቨስትመንት ፈንድ ማስተዳደር፤ የጡረታ ፈንድ፣ ፕሮቪደንት ፈንድ፣ የመድን ፈንድ ማስተላለፍ)፣
 አቅራቢው የትምህርት ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች የሚያቀርባቸውን ዋጋቸው ለፕሮግራሙ የሚከፈለው ዋጋ ውስጥ የተካተተ የመማሪያ መፃሕፍት፣ ቁሳቁሶች ወይም መሣሪየዎችን ጨምሮ የትምህርት ፕሮግራሞች አቅርቦት (ዕውቅና የተሰጠው፣ ፕሮግራሙ ዲግሪ ወይም ተመሳሳይ የብቃት ማስረጃ የሚያስገኝ ከሆነ)፣
 ፈቃድ በተሰጠው አገልግሎት ሰጪ የሚከናወን የህፃናት ማቆያ አገልግሎት፣
 የሕክምና አገልግሎት፣
 በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች አቀርቦት፣
 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት፣
 ቅዱሳት መፃሕፍትን ማቅረብን ጨምሮ በእምነት ተቋማት የሚሰጡ ከእምነቱ ወይም ከሃይማኖቱ ሥርዓት ጋር በቀጥታ የተያያዙ አገልግሎቶች፣
 የሕክምና መገልገያ፣ የህክምና መሣሪያ፣ የወባ አጎበር አቅርቦት፣
 ለትርፍ ባልተቋቋሙ ድርጅቶች የሚቀርቡ በእርዳታ የሚሰጡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች
 ለግብርና አገልግሎት ብቻ የሚውል የምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የፀረ ተባይ፣ የፀረ አረም፣ የአፈርን አሲዳማነት ለመከላከል የሚውል ካልሲየም ሃይደሮኦክሳይድ (ውህድ ኖራ) ወይም የፈንገስ መከላከያ ኬሚካሎች፣
 ኢንቨስተሮች ወደ ሀገር የሚያስገቡት ወይም ከሀገር ውስጥ የሚገዙት ዕቃ (በሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ በተደነገገው መሠረት )፣
 የኤሌክትሪክ ኃይል (ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን ወርሀዊ ፍጆታ ያልበለጠ) እና የታሸገ ውሃን ሳይጨምር የውሃ አቅርቦት፣
 60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኛ የሆነ ሰው የሚያቀርባቸው ማናቸውም አቅርቦቶች፣
 ሚኒስቴሩ በሚያቀርበው ሀሳብ መሠረት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከታክሱ ነፃ የሚደረጉ ዕቃዎች፣
 አምቡላንስ እና የእሳት አዳጋ ተሽከርካሪዎች እና መሣሪያዎች አቅርቦት፡፡
ለዚህም ማብራረያ አባሪ 2 ን ይመለከቷል፡፡
 በተጨማሪ ከታክሱ ነፃ የሆነ ወደ ሀገር የሚገባ ዕቃ በአዋጁ አንቀጽ 11 በተደነገገው መሠረት ሲሆን ከአዋጁ ጋር በተያያዘው አባሪ 3 የተዘረዘሩት ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርገዋል፡፡
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ ታክስ መክፈል ለሀገር ዕድገት እና ለዜጎች ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በሀገራችን ካሉት የታክስ ዓይነቶች ተጨማሪ እሴት ታክስ አንዱ ሲሆን ይህን ታክስ ለመንግስት መክፈል ግዴታ መሆኑን ህብረተሰቡ ሊያውቅ ይገባል፡፡ በተጨማሪም ይህን አውቆ በወቅቱ አለመክፈል ቅጣቶችን ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሚጠበቅበትን በወቅቱ መክፈል አለበት፡፡
via:- FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር
Federal Justice and Law institute
Forwarded from የሕግ ቤት
ደሀ ደንብ
• ዳኝነት ሳይከፈል፣ በነፃ መዝገብ ማስከፈት
ክስ ለማቅረብ የፈለገ ወገን ከፍርዱ ለሚያገኘው የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችል የገንዘብ አቅም የሌለው ከሆነ ክሱን ያለዳኝነት ገንዘብ በደሀ ደንብ መሠረት የማቅረብ መብት እንዳለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 215 ተደንግጓል፡፡ ክሱን የሚያቀርበው ወገን ድሀ በመሆኑ ምክንያት የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል ክሱን አቅርቦ እንዲያሰማ ሊፈቅድለት ይገባል? የሚለው ጉዳይ ሊለይ የሚችልበት ዝርዝር አፈፃፀም ደንቡም ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 እና ተከታዩ ድንጋጌዎች ተመልክቷል፡፡ እነዚህ ደንቦች ተፈፃሚነታቸው ክስ ለማቅረብ በፈለገ የተፈጥሮ ሰውም ሆነ በሕግ ሰውነት ያላቸው ወገኖችም ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሠረት ድሀ ነኝ፤ መብቴን ለማስከበር ያለኝ ፍላጐቴ በዳኝነት ገንዘብ እንቅፋት ምክንያት ሊሰናከል አይገባም፡፡ ስለሆነም በድሀ ደንብ መሠረት ክሱን በነፃ እንዳሰማ ይፈቀድልኝ የሚል ማናቸውም ከሳሽ ድሀ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳሹ የሚገኝበት የገንዘብ አቋም ከተረጋገጠ በኋላ ለክሱ ሊከፈል የሚገባው የዳኝነት ገንዘብ መጠን ከሳሹ ከሚገኝበት የገንዘብ አቋም አኳያ ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 467 መሠረት ድሀ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ሊለይ ይገባል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 79555 ቅጽ 14፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467
አንድ ሰው በፍርድ ሊያልቅ የሚገባው ጉዳይን ፍርድ ቤት ይዞ ሲቀርብ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ መክፈል ያለበት መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 215፣ ከ467 እስከ 479 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያሉ፡፡ የዳኝነት አገልግሎት መክፈል የማይችል ሰው ክስ ለማቅረብ የሚችልበት አግባብ ስለመኖሩም ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ አንድ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመክፈል የማይችል ሰው በደሃ ደንብ ክስ ለማቅረብ የሚችል ሲሆን ለመክፈል አቅም እያለው ክስ ያቀረበ መሆኑ ከተረጋገጠ ግን መዝገቡ እንደሚዘጋ፣ የተዘጋ መዝገብ ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ /ገንዘቡን/ ለመክፈል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ የሚንቀሳቀስለት መሆኑን የሥነ ሥርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መንፈስና ይዘት ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 52942 ቅጽ 12፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215፣ 467-479
ይግባኝ ዳኝነት ሳይከፈል በነፃ ለመክሰስ እንዲፈቀድ በቀረበ ጥያቄ ላይ ሊሰጥ የሚችለው ትእዛዝ እንደነገሩ ሁኔታ ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንደኛው ከሣሽ የዳኝነት ገንዘብ ለመክፈል የሚያስችለው የገንዘብ አቅም የሌለው ስለሆነ እንደ ጥያቄው የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍል በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከሣሹ ድሃ ያለመሆኑ ስለተረጋገጠ ተገቢውን የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈለ በቀር በነፃ ፋይል ከፍቶ ክሱን ለማቅረብ አይችልም የሚለው ነው፡፡
በመጀመሪያው አኳኋን ትእዛዝ በተሰጠ ጊዜ በዚህ ትእዛዝ መሠረት ፋይሉ ተከፍቶ ክርክሩ የሚቀጥል ነው፡፡ የክርክሩ ውጤት የሚታወቀው ግራ ቀኙ በሚያቀርቡት የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር ማስረጃ መሠረት ነው፡፡ በመጨረሻው የክርክር ውጤት ተከሣሹ ባይስማማ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ክሱ ዳኝነት ሳይከፈልበት በነፃ እንዲከፈት መደረጉ የሕግ ድጋፍ አልነበረውም የሚለውን እንደ አንድ የይግባኝ ምክንያት በማድረግ በውሣኔው ላይ ካለው ቅሬታ ጋር አዳምሮ ማቅረብ ይኖርበታል እንጂ ከሥረ-ነገሩ ፍርድ በፊት የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብት አይኖረውም፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320/3/ የተመለከተው ድንጋጌም በዚህ አኳኋን በሚቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ክልከላ ለማድረግ ነው፡፡
በሌላ በኩል ድሀ ያለመሆንህ ተረጋግጧል፡፡ የዳኝነት ገንዘብ ካልከፈልክ በቀር ፋይል አይከፈትም ለተባለው ከሣሽ ግን ይህ ዓይነቱ ትእዛዝ የመጨረሻ ነው፡፡ ሌላ የሚጠበቅ የሥረ-ነገር ፍርድ የለውም፡፡ ስለሆነም የዳኝት ገንዘብ ለመክፈል አቅም ሳይኖረኝ ክርክሬና ማስረጃዬ በአግባቡ ሳይታይ አቅም እንዳለኝ ተቆጥሮ የዳኝነት ገንዘብ ክፈል መባሌ ተገቢ አይደለም የሚል ከሆነ የተሰጠው ትእዛዝ የመጨረሻ እንደመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 320/1/ መሠረት የይግባኝ አቤትታ የማቅረብ መብት አለው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 23744 ቅጽ 6፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 320.
በውጭ ሀገር የተሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ስለሚፈፀምበት ስነስርዓት

በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን በአንቀፅ 458 እንደተገለፀው በውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈፀም የሚችለው
1) እንዲፈፀም የተጠየቀውን ፍርድ የወሰነው ፍርድ ቤት የሚገኝበት ሀገር በኢትዮጵያ የተሰጠውን ፍርድም የሚፈፀም መሆኑ ሲረጋገጥ
2) ፍርዱ የተሰጠው በህግ በተቋቋመ ፍ/ቤት መሆኑ ሲረጋገጥ
3) የፍርድ ባለዕዳው ቀርቦ መቃወሚያውን ለማሰማት መብት የተሰጠው መሆኑ ሲረጋገጥ
4) ፍርዱ የመጨረሻ እና ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ ሲታወቅ
5) የፍርዱ መፈፀም ለሕዝብ ሞራልና ፀጥታ ተቃራኒ ያለመሆኑ ሲታወቅ እንደሆነ ነው፡፡
እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በአጠቃላይ መሟላት የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች በውጭ አገር የተሰጠውን ፍርድ ለማስፈፃም የሚያስችላቸው ሲሆን በተናጥል መሟላት የኢትዮጵያን ፍርድ ቤቶች በውጭ ሀገር የተሰጠውን ፍርድ ለማስፈፀም የሚያስችላቸው አይሆንም፡፡
Value Added Tax Regulation No. 570-2025.pdf
2.3 MB
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ ቁ 570/2017 🇪🇹

Council of Ministers Value Added Tax Regulation No 570/2025

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2024 አንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት የሚከተለውን ደንብ አውጥቷል።

This regulation is issued by the Council of Ministers pursuant to Article 72 Sub-Article (1) of the Value Added Tax Proclamation No1341/2024

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ

📱  https://fb.me/tebekasamuel

🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel

👉 @ethiopian_law
                                        
👉 @tebeka

Contact @samuelgirma
☎️ 0911190299

#Ethiopia 🇪🇹 #samuelgirma

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ


የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁ.1341/2024
👉 t.me/tebekasamuel/2890
👉 t.me/tebekasamuel/2890

Boost 👇
https://t.me/boost/tebekasamuel
https://t.me/boost/tebekasamuel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱ የፅዳት ህግ‼️
ግለሰቦች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ድርጅቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ሜትር የማፅዳት ኃላፊነት የሚጥለው ረቂቅ አዋጅ ውይይት እየተደረገበት መሆኑ ተገለፀ‼️

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከመንግሥትና የግል ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት አድርጓል።

ረቂቅ አዋጁ ግለሰቦች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ድርጅቶች ላይ ደግሞ እስከ 50 ሜትር የማፅዳት ኃላፊነት እንደሚጥልና አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች እንደሚከላከል ተገልጿል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ ረቂቅ አዋጁ አገር የጀመረችውን ፅዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመፍጠር እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ለአሰባሰብ አዳጋች እና አካባቢን በመበከል  ማህበረሰቡን ለተለያዩ የጤና ችግሮች እየዳረጉ ስለሆነ መቆም አለባቸው ብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ፈቲያ አሕመድ ረቂቅ አዋጁ ረዥም ዘመናት ማገልገል እንዲችል በርካታ ባለድርሻዎችን ያካተተ ውይይት በቀጣይነት እንደሚደረግበት ገልጸዋል።

ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጁ መዘጋጀቱን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
#Ethiofm
❤1
ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት

መግቢያ
ጉዳይን ያለ አግባብ ማጓተት በተገልጋዩ ህብረተሰብ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል ባለ ግንኙነት የሚፈጸም ተገቢነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ተገልጋዩ የህብረተሰብ አባል በህግ ክርክሮች እና በአስተዳደር አከላት የሚሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ለማግኘት ወደተለያዩ መንግስታዊ አና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፊት ይቀርባል፡፡ በዚሁ ሁኔታ አገልግሎት ፈልጎ የቀረበው ተገልጋይ እንደ ጉዳዩ ባህሪ በህግ እና አሰራር በተቀመጠ ምክንያታዊ ጊዜ ውስጥ ለጉዳዩ እልባት አግኝቶ መሸኘት አለበት፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ተገልጋዮችን ተገቢ ላልሆነ እንግልት በመዳረግ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን እና ጉልበታቸውን እንዲያባክኑ በማድረግ ለከፋ ምሬት እና ተስፋ መቁረጥ በመዳረግ በመንግስት እና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሻክር ይሆናል፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍም ጉዳይን አለአግባብ ማጓተት ምንነት እና የሚያስከትለውን የህግ ተጠያቂነት በአጭሩ የምንዳስስ ይሆናል፡፡

ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት ምንነት
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ህገመንግስት አንቀጽ 12 ላይ የመንግስት ስራ በግልጽነት እና ተጠያቂነት በሰፈነበት ሁኔታ መከናወን እንዳለበት ያመለክታል፡፡ ይህ መርህ በህግ እና አስተዳደራዊ ውሳኔዎች አሰጣጥ ላይ ተፈጻሚነት አለው። የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተቋቋሙበትን አላማ ለማሳካት የሚያስችሏቸው የገልግት መስጫ ስታንዳርድን የሚያመለክቱ የተለያዩ መመሪያዎች እና የአሰራር ስርአት አላቸው፡። ከነዚህ መካከልም ጉዳዮችን ተቀብለው ውሳኔ የሚሰጡበትን የጊዜ ገደብ የሚያመላክቱ ድንጋጌዎች በአዋጅ በደንብ እና መመሪያዎች የተደነገጉ ናቸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በዜጎች ቻርተር፣ በመሰረታዊ የአሰራር ለውጥ(ቢፒአር) እና ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች እንደየ ጉዳዮቹ ባህሪ እና የውስብስብነት ደረጃ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንድን ጉዳይ ተቀብለው መርምረው እልባት የሚሰጡበትን የጊዜ ገደብ ያመላክታሉ፡፡ እነዚህን በህግ የተዘረጉትን የአሰራር ደረጃ ባለመጠበቅ ጉዳይን ያለ በቂ ምክንያት ሳይወስኑ ወይም ሳይፈጽሙ ማቆየት ጉዳይን ያለአግባብ የማጓተት ትግባር ነው፡፡

በፍትህ አስተዳደር ዘርፍ ያለውን በምናይበት ጊዜ በመርህ ደረጃ የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ የሚቆጠር ነው፡፡ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 20 (1) መሰረት ማንኛውም የተከሰሰ ሰው ክስ ከቀረበበት በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ የመሰማት መብት እንዳለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በዚህም ጉዳያቸው ታይቶ የመጨረሻ ፍርድ ያልተሰጣቸውን ተከሳሾች በተገቢው ጊዜ ፍርድ መስጠት የሚገባ ሲሆን ውሳኔ አስከሚያገኙ በእስር የሚቆዩበትን ጊዜ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ እንደተሰጠ ተደርጎ ሊታይ አይገባውም፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ ንቀጽ 3 መሰረት ማንኛውም በወንጀል ፍርድ ሂደት ውስጥ ያለ ሰው ከጥፋተኝነት ፍርድ በፊት በተከሰሰበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ሊቆጠር እና ሊታይ አይገባውም፡፡ በወንጀል ጉዳይ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት የተከሰሱ ሰዎች መብት ብቻ ሳይሆን ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎችም መብት ነው፡፡ በዚህም በህገመንግስቱ አንቀጽ 19(3) መሰረት በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰአት ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ለመታሰር ያበቃቸውን በቂ ምክንያት የማወቅ መብት አላቸው፡፡ ለመታሰራቸው በቂ ምክንያት የሌለ ከሆነ ፍ/ቤቱ የኣካል ነጻነታቸውን ጠብቆ በነጻነት ሊለቃቸው እንደሚገባ ነገር ግን ልዩ በሆነ ሁኔታ ፍትህ እንዳይጓደል ምርመራ ለማካሄድ አስፈላጊ የሆነውን ተጨማሪ የእስር ማቆያ ጊዜ በጥብቅ መስፈርት ሊፈቅድ ይችላል፡፡

ከዚህም የምንረዳው በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙም ሆነ የተከሰሱ ሰዎች በህገመንግስቱ በተጠበቀላቸው መብት መሰረት ጉዳያቸው ሳይጓተት ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ ውሳኔ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ በፍትሐብሄር ፍትህ አስተዳደርም ፍርድ ቤቶቻችን የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች እንደ ጉዳዩ ውስብስበነት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ አይቶ አከራክሮ ለመወሰን የሚያስችላቸው የፍትሀብሄር ስነስርአት ህግ እና የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 008/2013 ጉዳይን በተወሰነለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ያለማጓተት መወሰን እንደሚገባ አመላካች የአሰራር ስርአቶች ናቸው፡፡

ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት በወንጀል እና በፍትሐብሄር ጉዳይ ብቻ የሚታይ ሳይሆን በማናቸውም አስተዳደራዊ ጉዳዮችም ጭምር ተቀባይነት የሌለው የአሰራር ብልሹነት ነው፡፡ የፌደራል አስተዳደር ስነ ስርአት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 33 ላይ “በተገቢው ጊዜ መወሰን” በሚል ርእስ እንደተደነገገው የአስተዳደር ውሳኔ የሚሰጠዉ ሰዉ የአስተዳደር ውሳኔዉን ሳይዘገይ በተገቢዉ ጊዜ መስጠት እና በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ጥቅሞች በውሳኔው መዘግየት ምክንያት ለጉዳት እንዳይጋለጡ ማድረግ አለበት በማለት በመደንገግ በግልጽ ጉዳይን ያለ አግባብ ማጓተት ህገወጥ እንደሆነ የደነገገ ሲሆን ከውጤት አንጻርም የአስተዳደር ውሳኔው በተገቢው ጊዜ ሳይሰጥ መቅረት የአስተዳደር ውሳኔ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ እንደተሰጠ ውሳኔ ይቆጠራል በማለት አስቀምጦ ይገኛል፡፡ በአገራችን የህግ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው ይሄው የአስተዳደር ስነ ስርአት አዋጅ የአስተዳደር አካላት የተገልጋዮችን መብት በማክበር ጉዳያቸውን ሳያጓትቱ በተገቢው ፍጥነት መወሰን እንዳለባቸው ያመለክታል፡፡ በዚሁ አግባብ አለመወሰንምጥያቄውን ውድቅ እንደማድረግ ይወሰዳል፡፡ ይህ ማለትም ተገልጋዩ ወደሚከተለው አቤቱታ ሰሚ የበላይ የመንግስት አካል ቅሬታውን ማቅረብ እና ምላሽ ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡፡

ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት የሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት
ለጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት ወንጀል ተጋላጭ የሆኑት የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ህዝባዊ የሆኑ የግሉ ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትንም የሚያካትት ነው፡፡ ከዚሁ አኳያ በተገልጋዮች ላይ የሚፈጸም ምክንያታዊ ያልሆነ የጉዳይ ማጓታት ተግባር ከአስተዳደራዊ እና የፍሐብሄር ተጠያቂነት ብቻ ሳይሆን በወንጀልም የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡ በሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም የመንግስት ወይም የህዝባዊ ድርጅት ሰራተኛ በሃላፊነቱ በስራው ምክንያት በቀረበለት ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ጥቅም ለማግኘት ሲል በጉዳዩ ላይ ጥቅም ያለውን ማንኛውንም ሰው ለመጥቀም ወይም ለመጉዳት በማሰብ ከህግ፣ ከመመሪያ ወይም ከተለመደው አሰራር ውጪ ያለበቂ ምክንያት ጉዳዩን ያልወሰነ፣ ያዘገየ ወይም ባለጉዳይን ያጉላላ ሰው እንደ ጉዳዩ ሁኔታ በመቀጮ ወይም በቀላል እስራት ወይም ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ ሰእስራት እና አመስት ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ እንደሚቀጣ ደንግጎ ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው በአዋጁ እንደተደነገገው ጉዳይን ማጓተት ወንጀል የሙስና ወንጀል የሆነበትን መሰረታዊ ምክንያት ነው፡፡ በዚሁም መሰረት የሙስና ወንጀሎች በመሰረታዊነት የሚፈጸሙት የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለአንዱ ወገን በተለያዩ ምክንያቶች በማዳላት ሌላውን ወገን ለመጥቀም በማሰብ ነው። የዚህ ወንጀል ፈጻሚዎች ጉዳይን አለአግባብ የማጓተት ተግባር የሚፈጽሙት ባለጉዳዩ በመመላለስ ምክንያት ከሚደርስበት እንግልት ለማምለጥ ሲል ገንዘብ እንዲከፍላቸው ተጽእኖ ለማሳደር አለያም ባለጉዳዩ ተማሮ ጉዳዩን መከታተሉን እንዲተወው በማድረግ የባለጉዳዩን መብት ለመረጡት ሌላኛው ሰው በማስተላለፍ በዚህም የሚከፈላቸውን ተገቢ ያልሆነ
የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሌላው ልብ ልንለው የሚገባው አጥፊው ጉዳይን ያለአግባብ ማጓተት ፈጽሟል ለማለት የተላለፈው ግልጽ የሆነ በህግ፣ በመመሪያ እና በአሰራር ደንብ የተቀመጠ ምክንያታዊ የውሳኔ መስጫ ጊዜን በመተላለፍ ውሳኔውን በሰአቱ ሳይሰጥ የቀረ መሆኑን በማስረዳት ነው፡፡ በዚህም እንደየሙያና አገልግሎት መስኩ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባው ጉዳይ የሚፈልገውን ምክንያታዊ ጊዜ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ
የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆኑ የህዝባዊ ድርጅቶች ተገልጋዮቻቸውን ሲያስተናግዱ አገልግሎት ወይም ውሳኔ የሚሰጥበት ጉዳይ ያለውን ልዩ ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት በህግ እና በአሰራር ስርአት እንዲሁም የተለመዱ አካባቢያዊ ሀኔታዎችን በማገናዘብ ለተገልጋዮቻቸው በተገቢው ጊዜ ውሳኔ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ያለ በቂ ምክንት ህግ እና አሰራርን በመጣስ ተገልጋዮችን ለማንገላታት እና ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት እንዲሁም አግልግሎት ጠያቂው ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ጉዳይን ያለበቂ ምክንያት ማጓተት በህግ የሚያስጠይቅ እና የሚያስቀጣ የወንጀል ተግባር መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ተገልጋዩ ማህበሰረብ በመንገስትም ይሁን ህዝባዊ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ሲሄድ በህግ እና አሰራር ስርአት የተቀመጡ የአሰራር ደረጃዎችን ተረድቶ በዛ ውስጥ ውሳኔ እንዲያገኝ መጠየቅ እና ይህ በማይሆንበት ጊዜ ጉዳዩን ያለ በቂ ምክንያት የሚያጓትቱ የመንግስት እና ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች እና ሀላፊዎች ላይ የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር መስራት ያስፈልጋል፡፡
ከገቢ ግብር ነፃ የሆነ ገቢ
****************************
የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-
ሀ) ሚኒስትሩ በዚህ ፊደል ተራ በቁጥር (2) ፣ (3) ፣ (4) እና (6) በተመለከቱት ላይ በሚያወጣው መመሪያ የሚያደርገው ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለተቀጣሪው የሚከፈሉ የሚከተሉት ገቢዎች ከገቢ ግብር ነፃ ናቸው፡-
(1) ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
(2) በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
(3) በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤
(4) ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤
(5) የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤
(6) የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤
(7) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤
ለ) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
ሐ) ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመውዝ 15% (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
መ) በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
ሠ) የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤
ረ) በዓለም ዐቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
ስ) በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በተደረገ ስምምነት መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡-
(1) ስምምነቱ የተደረገው ለመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ፤
(2) ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፤
ሽ) በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት፤
ቀ) በተቀባዩ ላይ በደረስ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤
በ) የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጦታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
ተ) በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤
ቸ) ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
ን) ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገናኝ የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
ነ) ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው እና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
ኘ) በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤
አ) ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤
ከ) በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ::
👍1
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
አንድ ሰው አስቦ ወደ ሌላ ሰው ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ ካስተላለፈ በስህተት ወይም ተጭበርብሮ መሆኑን ካላስረዳ ገንዘቡ እንዲመለስ የመጠየቅ መብት የሌለው መሆኑን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
Join👇
https://t.me/ethiolawtips
የወንጀል ህግ መርሆች

መግቢያ

ወንጀል ማለት በህግ አስቀጪነቱ የተደነገገውን ድርጊት በማድረግ ወይም ባለማድረግ የህግ ተጠያቂነት እና ቅጣትን የሚያከትል ድርጊት ነው። የወንጀል ህግ ደግሞ ወንጀል ስለሆኑ ድርጊቶች እና አለማድረጎች እንዲሁም ቅጣታቸውን የሚዘረዝር የህግ አይነት ነው። የወንጀል ህግ የራሱ የሆኑ መርሆች ያሉት ሲሆን በሀገራችንም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እና የወንጀል ህጉ አለማቀፋዊ ባህርይ ያላቸውን መርሆች አካተው የወጡ ናቸው። በዚህ ፅሁፍ በህገ መንግስቱ እና በወንጀል ህጉ የተደነገጉ የወንጀል ህግ መርሆች በአጭሩ እንመለከታለን።

• የወንጀል ህግ መርሆዎች

“መርህ” ማለት የአንድ ነገር ማጠንጠኛ መሰረት ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በቀላሉ የማይለወጥ፣ የማይሸረሸር፣ ሊጣስ የማይገባውና ከተጣሰ ግን ያ በሱ ላይ የተመሰረተው ፍሬ ሀሳብ ህልውናው ሊናጋ ስለሚችል መርሁ ወይም መሪው ሀሳብ በሚገባ ሊጠበቅና ሊያዝ የሚገባው ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ደስታ ተክለ ወልድ በአማርኛ የመዝገበ ቃላት መፅሐፋቸው “መርህን” “የመራ፣ የሚመራ፣ መሪ” በሚል የተረጎሙት። በመሆኑም ህጎች ሲወጡም ሆነ ሲተገበሩ የህግ መርሆችን መሰረት ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል። በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገራችን ተቀባይነት ያላቸው እና በሥራ ላይ እየዋሉ የሚገኙ የወንጀል ህግ መርሆችን እንደሚከተለው እንመለከታለን።

1. የሕጋዊነት መርህ (Principle of Legality)፡- የህጋዊነት መርህ

መሰረታዊ ሀሳብ በህግ ከተደነገገው ውጪ ቅጣት ሊኖር አይችልም የሚል ነው። በመሆኑም ማናቸውም ሰው የተከሰሰበት ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ድርጊቱን መፈፀሙ ወይም አለመፈፀሙ ወንጀል መሆኑን የሚደነግግ ህግ ከሌለ በወንጀል ተጠያቂ ሊሆንና ሊቀጣ አይገባውም የሚል ነው፡፡ አንድን ሰው ሆነ ብሎም ይሁን በቸልተኝነት አንድ ድርጊት ፈፅመሀል ወይም መፈፀም የሚገባህን አልፈፀምክም ብሎ ለመክሰስና በወንጀል እንዲቀጣ ለማድረግ የወንጀል ፈፃሚው ድርጊት ወይም ተዓቅቦ በወንጀልነት የሚፈርጅና የወንጀል ቅጣት የሚደነግግ አስቀድሞ የታወጀ ህግ መኖር አለበት፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ሕገ-ወጥነቱ በህግ ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት እንደወንጀል ሊቆጥረው እና ቅጣትን ሊወስን እንደማይችል በወንጀል ህጉ እንቀፅ 2(2) ስር ተደንግጎ ይገኛል። እንዲሁም ፍርድ ቤቱ በህግ ከተደነገገው በቀር ሌሎች ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን መወሰን አይችልም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ የተመሳሳይነት (analogy) ጉዳይ ሲሆን በህግ ላይ ከተደነገጉት ወንጀሎች ጋር ይመሳሰላል በማለት ወንጀልነቱ በግልፅ ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት እንደወንጀል ሊቆጠር እንደማይችል የወንጀል ህጉ አንቀጽ 2(3) ይደነግጋል።

2. የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑ (Non-Retroactivity of Criminal Law)

በዚህ መርህ መሰረት ህግ ሊተገበር ወይም ሊፈፀም የሚችለው ህጉ ከፀደቀ በኋላ በተፈፀሙ ድርጊቶች ላይ ነው። ይህ ማለት አዲስ ህግ ሲወጣ ህጉ ከመውጣቱ በፊት የተፈፀሙት ድርጊቶች በአዲሱ ህግ ወንጀል መሆናቸው ቢደነገግም ለበፊቱ ድርጊት ተፈፃሚ አይሆንም። አንድ ሕግ የዜጎችን መብትና ግዴታ የሚወስን በመሆኑ ሰዎች ሕጉ እስከሚለወጥ ድረስ ድርጊቶቻቸውን ወይም ግንኙነታቸውን ሕጉ በሚፈቅደው ወሰን ውስጥ ያካሂዳሉ፡፡ አንድን ሁኔታ የሚለውጥ ወይም የሚያሻሻል ሕግ ቢወጣ ሕጉ ተፈፃሚ መሆን ያለበት ቢያንስ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ወደፊት መሆን አለበት፡፡

ይህ መርህ በወንጀል ህግ አንቀፅ 5 እና በህገ መንግስቱ አንቀፅ 22 ስር ተደንግጎ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በአዲሱ ወይም በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ እና በተሻረው የወንጀል ህግ እንደወንጀል የተቆጠረ ድርጊት የተፈፀመው አዲሱ ህግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ፣ ጉዳዩ የሚታየው በተሻረው የወንጀል ህግ መሰረት ነው። ድርጊቱ በአዲሱ ህግ መሰረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው ህግ ግን እንደወንጀል ካልተቆጠረና የተፈፀመው አዲሱ ህግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ አይችልም። እንዲሁም የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈፀመ ወንጀል ሲኖር በአዲሱ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም፤ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ እንደሚቋረጥ በወንጀል ህጉ ተደንግጓል።

የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ሄዶ አይሰራም ሲባል በመሰረታዊ ሕጉ ላይ ሁለት ዓይነት ውጤቶችን ያስከትላል፡፡ አንደኛው አንድ ድርጊት በሚፈፀምበት ጊዜ ድርጊቱ በጊዜው የማያስቀጣ ከነበረ ይኸው ድርጊት ከጊዜ በኋላ በወጣ ሕግ ወንጀል ነው ሊባል አይችልም፡፡ ሁለተኛው ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ወንጀል ቢሆንም እንኳን ወንጀለኛው መቀጣት ያለበት ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ተፈፃሚነት የነበረው የወንጀል ሕግ በደነገገው ጣሪያ መሆን አለበት የሚሉ ናቸው፡፡ ስለዚህም ከድርጊቱ በኋላ የወጣው ሕግ የቅጣት ጣሪያውን ከፍ ቢያደርገው ይህ ቅጣት ሕጉ ከመታወጁ በፊት ለተፈፀመ ወንጀል ተፈፃሚ መሆን የለበትም፡፡ ይሁንና አዲሱ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ከድርጊቱ ኋላ የወጣው ህግ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 22(3) ይደነግጋል። በተጨማሪ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 6 ስር እንደተደነገገው አዲሱ የወንጀል ህግ እንዲፀና ከተደረገ በኋላ አድራጊው ህጉ ከመፅናቱ በፊት ላደረገው ወንጀል ሲፈረድበት፣ ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ በሥራ ላይ ከነበረው ሕግ ይልቅ ይሄኛው ሕግ ቅጣት የሚያቀልለት ሲሆን በአዲሱ ህግ ላይ የተመለከተው ቅጣት ይፈፀምበታል።

3. ለአንድ ጥፋት አንድ ቅጣት መርህ (Principle of Double Jeopardy)

የዚህ መርህ መሰረታዊ ሀሳብ ሰው በአንድ የወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ በተቀጣበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና መከሰስና መቀጣት የለበትም የሚለው ነው፡፡ በዚህ መርህ ላይ አግባብነት ያላቸው የሕገ-መንግስቱና የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 23 “ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነ-ሥርዓት መሰረት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኝነቱ በተረጋገጠበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም” በማለት ሲደነግግ የወንጀል ሕጉም በአንቀፅ 2(5) ስር “ማንም ሰው በሕግ መሰረት የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጦ ከዚህ ቀደም በተቀጣበት ወይም ሌላ ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም” በማለት ደንግጓል፡፡

4. የእኩልነት መርህ (Principle of Equality)
የእኩልነት መብት ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ከሚመነጩ እና ከማይገረሰሱ አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች አንዱ ነው። ሰዎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል ናቸው የሚለው መርህ የመጣውም ከዚሁ የእኩልነት መብት ነው። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 25 ስር እንደተደነገገው ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው፤ በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል። በመሆኑም በዘር፣ በብሄር፣ ብሄረሰብ፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ አመጣጥ፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 4 ይህንን መርህ በተመሳሳይ ሁኔታ ያስቀመጠ ሲሆን
አድራጊዎች መሐከል ልዩነት የሚደረገው ምንጩ የአለም አቀፍ ህግ ወይም ህገ መንግስት ሆኖ በወንጀል ህጉ የተደነገገ መሰረታዊ መብት ሲኖር ወይም የወንጀሉ ከባድነት፣ የጥፋቱ ደረጃ ወይም የአድራጊው ዕድሜ፣ ሁኔታ ወይም ልዩ ግላዊ ጠባዩ ወይም ወንጀሉ በሕብረተሰብ ላይ ያስከተለው አደጋ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ህጉ ሲደነግግ እንደሆነ ያስቀምጣል።

ከላይ ከተዘረዘሩት የወንጀል ህግ መርሆች በተጨማሪ ሁሉም ተጠርጣሪዎች እና ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ንፁህ ሆነው የመገመት (Presumption of innocence)፣ ዝም የማለት መብት (the right to remain silent) እና ሌሎችም የተያዙ እና የተከሰሱ ሰዎች መብቶች በህገ መንግስቱ ተደንግገው ይገኛሉ።

ማጠቃለያ

በህገ መንግስቱም ሆነ በወንጀል ህጉ የተመለከቱ የወንጀል ህግ መርሆች ከላይ የተብራሩት ሲሆኑ ህግ አስከባሪ አካላት የወንጀል ምርመራ እና ክርክር ሥራዎችን ሲያከናውኑ እነዚህን የወንጀል ህጉን መርሆች በጥብቅ መከተል ይጠበቅባቸዋ::
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ