Forwarded from Hermela Tilahun
Share copy
ሰላም አባላት
መልካም ዜና! በቢሮ ውስጥ ማማከር በስልክ እና በፍርድ ቤት ውክልና በመውሰድ ሲሰጥ የቆየው የነጻ የህግ ምክር አገልግሎት በልዩ ሁኔታ በነጻ የስልክ መስመር ቁጥር መሰጠት ተጀመረ።
አዲስ ነገር፤
በዘጠና አንድ አስር።
ከአንድ ሰአት እስከ አንድ ሰአት፤
በልዩ መስተንግዶ እና ጽናት።
እነሆ ማህበራችን በነጻ የስልክ ጥሪ ነጻ የህግ ምክር አገልግሎት መስጠት ጀመረ! በፍታሐብሄር,ማለትም በቤተሰብ፣ በውል፣ ከውል ውጪ በሚኖር ሀላፊነት፣ በንብረት፣ በውርስ በስራ እና በቅጥር የህግ ጉዳዮች፣ በአስተዳደር፣ በወንጀል እንዲሁም አለም አቀፍ ሕግጋትን በተመለከተ ለማማከር አካል ጉዳተኞች በነጻ የስልክ ጥሪ የሚገለገሉበት ቁጥር ተበሰረ! ዘጠና አንድ አስር ካሉበት ሆነው ይደውሉ ህግን በተመለከተ ያለበዎትን ክፍተት በነጻ ያሟሉ! ጠዋት የማለዳዋን ጀንበር ቀድመን ምሽት የምሽቱን ጀንበር ሸኝተን እርሶን እናገለግላለን። እባክዎን ተገደው በልመና ተግባር ላይ የተሰማሩ አካል ጉዳተኛ ከሆኑ አልያም አካል ጉዳተኞች ተገደው በልመና ላይ ተሰማርተው በሚመለከቱበት ግዜ በዘጠና አንድ አስር በመደወል ያሳውቁ!
ዘጠና አንድ አስር አካል ጉዳተኞች ወደፍትህ የሚፈሱበት ዥረት!
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር

👍1
Forwarded from SAMUEL GIRMA
የታክስ_አስተዳደራዊ_ቅጣት_አነሳስ_መመሪያ_189_2017.pdf
7.3 MB
የታክስ አስተዳደራዊ ቅጣት አነሳስ መመሪያ ቁ.189/2017
ገቢዎች ሚኒስቴር 🇪🇹
🌐 https://SamuelGirma.com
📱 https://fb.me/tebekasamuel
📱 https://t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
👉 @ethiopian_law
👉 @tebeka
DM @samuelgirma
📻 0911190299
TAX
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law
Boost The Channel👇
https://t.me/boost/tebekasamuel
https://t.me/boost/tebekasamuel
ገቢዎች ሚኒስቴር 🇪🇹
DM @samuelgirma
TAX
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law
Boost The Channel
https://t.me/boost/tebekasamuel
https://t.me/boost/tebekasamuel
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
DEMATERIALIZATION OF GOVERNMENT AND NBE SECURITIES.pdf
2.2 MB
DEMATERIALIZATION OF GOVERNMENT AND NBE SECURITIES
DIRECTIVE NO. MFAD/001/2025
DIRECTIVE NO. MFAD/001/2025
Excise Tax Management System Directive No. 1071_2025.pdf
979.9 KB
የኤክሳይዝ ታክስ አስተዳደር ስርአት መመሪያ ቁጥር 1071/2017
DIRECTIVE NO. 1071/2025
DIRECTIVE ON EXCISE TAX MANGEMENT SYSTEM
🇪🇹
🌐 https://SamuelGirma.com
📱 https://fb.me/tebekasamuel
📱 https://t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
👉 @ethiopian_law
👉 @tebeka
DM @samuelgirma
📻 0911190299
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law
DIRECTIVE NO. 1071/2025
DIRECTIVE ON EXCISE TAX MANGEMENT SYSTEM
🇪🇹
🌐 https://SamuelGirma.com
📱 https://fb.me/tebekasamuel
📱 https://t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
👉 @ethiopian_law
👉 @tebeka
DM @samuelgirma
📻 0911190299
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law
የከተማ_መሬት_ይዞታና_መሬት_ነክ_ንብረት_ምዝገባ_የፀደቀ_አዋጅ_ቁጥር_1381_2017_1.pdf
739 KB
የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1381/2017
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1👍1
Forwarded from ሕግ አገልግሎት Legal Service
ንብረት_ማስመለስ_አዋጅ_ቁጥር_13642017_1.pdf
39.2 MB
https://fb.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
👉 @tebekasamuel
👉 @tebeka
Contact @samuelgirma
#Ethiopia 🇪🇹 #samuelgirma
ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
☎️ 0911-190-299
🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
👉 @tebekasamuel
👉 @tebeka
Contact @samuelgirma
#Ethiopia 🇪🇹 #samuelgirma
ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
☎️ 0911-190-299
Forwarded from ሕግ አገልግሎት Legal Service
Civil-and-Family-Registration-Proclamation-No.-1370-2025.pdf
1.5 MB
የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 1370-2017 ዓ-ም
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
የጊዜ ቀጠሮ ወይም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤት ፈቀደ ሲባል ምን ማለት ነው? ከሕግ አኳያ እንዴት ይታያል?
የጊዜ ቀጠሮ ወይም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው? ከሕግ አኳያ እንዴት ይታያል ?
አንድ ተጠርጣሪ በተያዘ በአርባ ስምንት ሰዓት ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤት የመቅርብ መብት እንዳለውና ተጠርጣሪውን ያዘው የፖሊስ አካል ይህንኑ የመፈፀም ግዴት እንዳለበት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 29 በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ስያሜው እንደሚያመለክተው 48 ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤት ለቀረበ ተጠርጣሪ በእስር ቆይቶ ቀጣይ ምርመራ እንዲካሄድበት ተጨማሪ ጊዜ ነው፡፡ምርመራው በ48 ሰዓት ጊዜው ውስጥ መጠናቀቅ ከቻለና የተጠረጠረበት ወንጅል በፖሊስ ዋስ ለመልቀቅ የሚያስችል ከሆነ ተከሳሽ ለተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ፍርድ ቤት መቅርብ አይገባውም፡፡
የወንጀል ምርመራ ሂደት አስፈላጊ የሆነ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ የተጠርጣሪው በእሥር መቆየት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የዋስትና መብቱን በመንፈግ ሳይሆን በማዘግየት ለመርማሪው በፍርድ ቤት የሚፈቀድ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ነው፡፡የጊዜ ቀጠሮ ከዋስትና መብት ጋር ሲገናዘብ በወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በሕግ ከተደነገገዉ ሁኔታ በስተቀር ሊገደብ በማይችል ሁኔታ ያለው መብት ሲሆን የጊዜ ቀጠሮ ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው ለምርመራ ሥራ ማጠናቀቂያ የተጠርጣሪዉ በእሥር መቆየት አስፈላጊ በሚሆንብት የሚፈቀድ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ነው፡፡
ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሰትም ለዚህ ፅንስ ሐሳብ ቦታ በመስጠት የተያዙ ሰዎች አግባብ ባለው ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው የተያዙበትን ምክንያት መረዳት ካልቻሉ የአካል ነፃነታቸው እንዲከበርላቸው የመጠየቅ የማይጣስ መብት እንዳላቸው ቢታወቅም ፍትሕ እንዳይጓደል ሲባል ሁኔታው የሚጠይቅ ከሆነ ምርመራ ለማካሄድ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሲጠየቅ ሊፈቀድ እንደሚችል ደንግጓል፡፡
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 59/2/ “የፖሊሱም ምርመራ ያልተፈፀመ እንደሆነ መርማሪው ፖሊስ ምርመራውን የሚፈፅምበት በቂ ጊዜ እንዲሰጠው ተከሳሹ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ፍርድ ቤቱን ለመጠየቅ ይችላል፡፡” በማለት ተደንግጓል፡፡ ከዚህ ባላይ በተጠቀሰው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥርዓት ቁጥር ንዑስ ቁጥር 3 ለእያንዳንዱ በማረፊያ ቤት ለማቆየት የሚጠይቀው ጊዜ ከ14 ቀን እንደማይበልጥ ደንግጓል፡፡
የጊዜ ቀጠሮ ዋና ዓላማ አንድ ተከሳሽ ወይም ተጠርጣሪ በተከሰሰበት ወይም በተጠረጠረበት ጉዳይ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ በፍርድ ቤት ፈቃድ ተጠርጣሪው በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደርጎ የምርመራ ስራውን ለማጠናቀቅ እንዲያስችለው ማድረግ ነው፡፡ከዚህ እውነታ በመነሳት የጊዜ ቀጠሮ አንድ ተጠርጣሪን አስመልክቶ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ በፍርድ ቤት የሚፈቀድ ምርመራን የማካሄጃ ወይም የማጠናቀቂያ ጊዜ ነው ቢባል መሳሳት አይሆንም፡፡
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 59/3/ መሰረት ለሚቀርብ የተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የሚፈቅደው ለእያንዳንዱ ከ14 ቀን እንደማይበልጥ ተጠቅሷል:: ይሁን እንጂ በሕጉ ድግግሞሹ ለምን ያህል ጊዜ መሆን እንዳለበት ገደብ አልተበጀለትም፡፡
በመጨራሻ መርማሪ ፖሊስ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሰትም ሆነ አገራችን ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ውስጥ የሰፈረውን የነፃነት መብትና በወንጅለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 37/1/…” ማናቸውም የፖሊስ ምርመራ ከሚያስፈልገው ጊዜ በላይ ሳይዘገይ መፈፀም አለበት>> በማለት የተደነገገውን አፅንኦት በመስጠት የምርመራ ሥራን በተፈቀደው የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ለማከናወን ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ፈጣን አግልግሎት መስጠት ይገባል፡፡
👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips

የሰውን ምስል ያለባለቤቱ ፈቃድ ለማስታወቂያ ሥራ በቴሌቭዥን በማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ያዋለ አካል ምስሉን ከባለቤቱ ፍቃድ ውጪ በመጠቀም ለሰራው ማስታወቂያ ተገቢውን ካሳ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 156425 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
❤1👍1
ከዛሬ ከነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው ሁለት ወራት ጊዜ ይቆያሉ ነገር ግን በባህሪያቸዉ አስቸኳይ የሆኑና ጊዜ የማይሰጡ እንዲሁም ለዉሳኔ የደረሱ መዛግብትን መርምሮ ውሣኔ የመስጠት አገልግሎቶች እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሳውቋል።
በክረምቱ ወቅት አገልግሎታቸው የሚቀጥሉ መዝገቦች የትኞቹ ናቸው ?
- ህጻናት ለያዙ ሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመለከት ጉዳዮች፣
- ወጣት ጥፋተኞችን የሚመለከት የይግባኝ ጉዳዮች
- ለወንጀል ምርመራ በቀረበ የጊዜ ቀጠሮና ዋስትናን በሚመለከት በተሰጠ ትዕዛዝ ወይም በውሣኔ ላይ የቀረበ ወይም የሚቀርቡ የይግባኝ ክርክሮች ወይም አቤቱታዎች፣
- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 201 እና በተከታዮቹ በተደነገገው መሰረት የሚቀርብ በአመክሮ መለቀቅን እንዲሁም በአንቀፅ 175 በተደነገገው መሰየምን በሚመለከት የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ክርክሮችን፣
- እግድንና እና መፈቻን በሚመለከት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይነታቸዉ በችሎቱ የሚለዩ መሰል ጉዳዮችን፣
- በፍትሐብሔር ጉዳዮች የቀለብና ተያያዥነት ያላቸዉ የቤተሰብ ጉዳዮች ላይ የሚቀርብ አቤቱታና ክርክር፣ የእግድና እንደ አስፈላጊነቱ አስቸኳይ መፍትሔ የሚፈልጉ አቤቱታዎች ይታያሉ።
በእዚህም መሰረት:-
° የሰበር አጣሪ ችሎቶች በመደበኛ ጊዜ የሚሰራዉን አጣርቶ ዉሳኔ የመስጠት ስራን ከነሐሴ 1ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ በመደበኛ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ።
° ፌደራል ጠቀላይ በተረኛ ችሎት የሚሸፈነው ጊዜ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ከጳጉሜ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ሲሆን በፌዴራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከነሃሴ 01 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ይሆናል።

ሰላም! እባክዎ ጥቂት ደቂቃ ወስደው ይህን መጠይቅ በመሙላት ይተባበሩን።
እናመሰግናለን!
እናመሰግናለን!
👍1
Forwarded from fasika aggena
Google Docs
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት ለሚሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች የሰልጣኞችን ፍላጎት ለመለየት የተዘጋጀ መጠይቅ
ይህ መጠይቅ የቀረበልዎ በቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት የሚሰጣቸው የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች የተሳታፊዎችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ ታልሞ ነው። እባክዎ በበጀት ዓመቱ በዳይሬክቶሬቱ ስልጠና እንዲሰጥዎ የሚፈልጉትን የሕግ ርእስ በመምረጥ ይተባበሩን።
ከሰአትዎ ላይ የምንወስደው 1 ደቂቃ ብቻ ነው። በ4 ክሊኮች ምርጫዎን ሊያሳውቁን ይችላሉ!
ክሊክ1: ሊንኩን ለመክፈት፤
ክሊክ2: የሚሠሩበትን ተቋም ለመምረጥ፤
ክሊክ3: ያሻዎትን ርእስ ለመምረጥ፤
ክሊክ4: ለእኛ ለመላክ፤
የዚህብ ያህል ቀላል ነው!
ክሊክ1: ሊንኩን ለመክፈት፤
ክሊክ2: የሚሠሩበትን ተቋም ለመምረጥ፤
ክሊክ3: ያሻዎትን ርእስ ለመምረጥ፤
ክሊክ4: ለእኛ ለመላክ፤
የዚህብ ያህል ቀላል ነው!
Forwarded from fasika aggena
Google Docs
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት ለሚሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች የሰልጣኞችን ፍላጎት ለመለየት የተዘጋጀ መጠይቅ
ይህ መጠይቅ የቀረበልዎ በቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት የሚሰጣቸው የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች የተሳታፊዎችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ ታልሞ ነው። እባክዎ በበጀት ዓመቱ በዳይሬክቶሬቱ ስልጠና እንዲሰጥዎ የሚፈልጉትን የሕግ ርእስ በመምረጥ ይተባበሩን።
Forwarded from ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ(lawyerhenoktaye) (Henok Taye/ኢትዮ ሕግ)
###የይርጋ መቋረጥ/መቼ ነው ይርጋ አይቆጠርም የሚባለው?
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1852 ድንጋጌ መሠረት ይርጋ በተቋረጠ ጊዜ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ እንደገና አዲስ የይርጋ ዘመን መቁጠር እንደሚጀምር በዚሁ ድንጋጌ በንዑስ ቁጥር /1/ ሥር ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ መረዳት የሚቻለው ይርጋው በተቋረጠ ጊዜ ቀድሞ የነበረው የይርጋ ጊዜ እንደ አዲስ መቁጠር የሚጀምር መሆኑን ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 31185 ቅጽ 6
#በሕግ ተለይቶ የተወሰነ የይርጋ ጊዜ የመቋረጥ እና ያለመቋረጥ ጉዳይ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ ሊነሳ የሚችለው የይርጋውን መቆጠር ያቋርጠዋል የተባለው ምክንያት የተከሰተው የይርጋው ጊዜ ከመሙላቱ በፊት በሆነ ጊዜ እንጂ የይርጋው ጊዜ የሞላ ወይም ያለፈ በሆነ ጊዜ ጭምር አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 90361 ቅጽ 6
ክስ የማቅረብ ውጤት ስልጣን ለሌለው የዳኝነት አካል ክስ ማቅረብ ይርጋን ያቋርጣል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 36730 ቅጽ 9
#ክስ የማቅረብ ውጤት /ሽያጭ ውል/ ይርጋ ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች አንደኛው ባለገንዘቡ መብቱ እንዲታወቅለት በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለባለእዳው አስታውቆ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43992 ቅጽ 10፣ ፍ/ህ/ቁ. 1851(ለ)
ክሱ የቀረበው መብቱን በሚጠይቀው ባለገንዘብ ባይሆንም ባለዕዳው በባለገንዘቡ ላይ ያቀረበው ክስ በይዘቱ የይርጋ መቃወሚያ ከተነሳበት ክስ ጋር ተያያዥነት ካለው ይርጋውን ያቋርጠዋል፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት ገዢ ንብረቱን ለመረከብ (የሽያጭ ውሉ እንዲፈጸምለት) ያቀረበው ክስ ከሽያጭ ውሉ ቀን ጀምሮ ሲቆጠር በይርጋ የሚቋረጥ ቢሆንም ሻጭ ቀደም ብሎ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስለት ክስ ካቀረበ በገዢው ላይ ተፈጻሚ የሚሆነውን የይርጋ ጊዜ ያቋርጠዋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43636 ቅጽ 10
#በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1776 እና በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2892 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ድንጋጌዎች መሠረት የቤት ሽያጭ ውል ይፈጸምልኝ ክስ ሲቀርብ በሕግ የተደነገገው የይርጋ ሕግ የጊዜ ገደብ አልፏል ወይስ አላለፈም? የሚለውን ነጥብ ለመወሰን በመጀመሪያ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2892 ንዑስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ እንደዚሁም ድንጋጌው ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2875 መሠረታዊ መርህና ስለ ሽያጭ እና ጠቅላላ ውል ከተደነገጉ ድንጋጌዎች ጋር ሊኖረው የሚገባውን ተፈፃሚነት መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ሻጭ በውሉ መሠረት ለመፈፀም የማይፈልግ መሆኑን ገዥ ያረጋገጠ መሆኑን ገዥ ውሉ እንዲፈፀምለት ማስጠንቀቂያ መስጠቱንና ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ሻጭ በውሉ መሠረት አለመፈፀሙን በማየት ብቻ ለማረጋገጥ አይችልም፡፡ ሻጭ ገዥ ማስጠንቀቂያ ከሰጠው በኋላም ቢሆን የተለያዩ ችግሮችን እያነሣ በመካከላቸው ያለውን የመተማመንና የቅን ልቦና ግንኙነት ተጠቅሞ ከአንድ ዓመት በላይ ውሉን ሣይፈፅም የሚቆይበት አጋጣሚ ይኖራል፡፡ ስለዚህ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2892 ንዑስ አንቀጽ 3 ይርጋ ተፈፃሚነት የሚኖረው ገዥ ለሻጭ ማስጠንቀቂያ የሰጠበትን ቀን መነሻ በማድረግና ጊዜውን በማስላት ሣይሆን ሻጭ በውሉ መሠረት የመፈፀም ፍላጎት የሌለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ገዥ እንዲያውቀው ያደረገበትን ቀን መነሻ በማድረግ መሆን ይገባዋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 38935 ቅጽ 8
#ሻጭ የውል ይፍረስልኝ ክስ ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ውሉን ለመፈፀም ፍላጎት የሌለው መሆኑን ለገዢ በማያሻማ መንገድ ከማሣወቅ ያለፈ ምክንያትና ውጤት ያለው ተግባር ነው፡፡ ሻጭ ውሉ እንዲፈርስ ሲጠይቅ ውሉ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለማቋቋም የማያስችሉ ጉድለቶች ያሉበት በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች እንደ ሕግ ሆኖ ሊገዙበት የማይገባ መሆኑን የሚያሣዩ የውሉን ሕልውና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና የውል ሕጋዊነት በፍርድ ቤት ተመርምሮ ፈራሽ እንዲባል ወይም እንዲሠረዝ የሚቀርብ ነው፡፡ የውሉ ሕጋዊነትና ሕልውና ጥያቄ ተነስቶበት በፍርድ ቤት በሚመረመርበት ጊዜ ሂደት ገዢ ውሉ ሕጋዊ መሆኑን ከማሣየትና ከማስረዳት አልፎ ውሉ በግዳጅ እንዲፈጽምለት የመጠየቅ ግዴታ አይኖርበትም፡፡
ከዚህ አንፃር ውሉ በፍርድ ቤት ፈራሽ እንዲሆን ወይም እንዲሰረዝለት በውሉ የሚገደድበት ሁኔታ ይቋረጣል፡፡ በሌላ በኩል በክርክሩ ከተረታ ገዢ ሕጋዊ ተፈፃሚነትና አስገዳጅነት ባለው ውሉ ንብረቱን የገዛ መሆኑ ከሻጭ ጋር ባደረገው የውል ሰነድ ብቻ ሣይሆን በፍርድ ቤት ውሣኔ የተረጋገጠለት የፍርድ ባለመብት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ገዢ ፍርድ ቤቱ ሕጋዊነቱንና አስገዳጅነቱን መርምሮ በፍርድ ያረጋገጠውን ውል እንዲፈጽምለት ሻጭን የመጠየቅ መብቱ በፍርድ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 384/ሀ/ በተደነገገው አስር ዓመት ጊዜ ውስጥ እንጂ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2892 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ የሚገደብ አይደለም፡፡ ስለዚህ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2892 ንዑስ አንቀስ 3 የተቀመጠው የጊዜ ገደብ በዚህ ጉዳይ አግባብነት የለውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 39725 ቅጽ 8

የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ 568 እዝባር 2000
አካል ጉዳተኞች፣ የሥራው ጠባይ እስከፈቀደ! ተፈላጊ ችሎታዎችን እስካሟሉ እና በውድድር ውጤት ብልጫ ነጥብ ካገኙ፣ በማንኛውም መሥሪያ ቤት ውስጥ የመቀጠር መብት አላቸው፡፡በውድድር ወቅትም እኩል ወይም ተቀራራቢ ነጥብ ካገኙ፤ ለስራው ወይም ለሥልጠና ቅድሚያ የሚያገኙበት መብት አላቸው!
ቀጣሪዎች ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የሥራ አካባቢንና የሥልጠና እድሎችን ማመቻቸት ግዴታ ነው፡፡ቀጣሪዎች ተስማሚ መሣሪያዎችን የማሟላትና ረዳት ለሚያስፈልጋቸውም ረዳት የመመደብ ግዴታ አለባቸው!
በልዩ ሁኔታ ሴት አካል ጉዳተኞች ያለባቸውን ተደራራቢ ጫና ያገናዘበ ተገቢ የሆነ የማስተካከያ የድጋፍ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
የአካል ጉዳተኞችን የስራ እና የቅጥር መብት በማክበር የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ህይወት እንዲሻሻል የድርሻችንን እንወጣ!
የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ከሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ ባገኘዉ የገንዘብ ድጋፍ
Website: https://elda-eth.com/
Facebook: https://web.facebook.com/p/Ethiopian-Lawyers-With-Disabilities-Association-
Linkdin: [https://www.linkedin.com/company/ethiopian-lawyers-with-disabilities-association/]
Tik tok : https://vm.tiktok.com/ZMSumrLhm/

❤1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA

ከጋብቻ ፍቺ በኋላ የባልና ሚስትን ሀብት ስለማጣራት የፍቺ ውጤት ስለመወሰን
==========================
1.#የባልና ሚስትን ሀብት በስምምነት ስለማጣራት
በዚህ ሕግ ስለካሣ ክፍያ የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው ጋብቻው በዚህ ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የፈረሰ እንደሆነ ባልና ሚስቱ የጋብቻቸው መፍረስ በንብረት በኩል የሚያስከትለውን ውጤት አስመልክተው በሚያደርጉት ስምምነት ወይም በጋብቻ ውላቸው መሠረት ይጣራል፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከተው የጋብቻ ውል ወይም ስምምነት የሌለ ወይም በሕግ ፊት የማይፀና ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የባልና ሚስት ሀብት በሚከተሉት ድንጋጌዎች መሠረት ይጣራል፡፡
2.#የግል ሀብትን መልሶ ስለመውሰድ
ባል ወይም ሚስት የግሉ መሆኑን በማስረዳት የግል ሀብቱ የሆነውን ንብረቱን መልሶ የመውሰድ መብት ይኖረዋል፡፡
ከባልና ሚስቱ አንደኛው የግል ሀብቱ የሆነ ማናቸውም ንብረት ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑንና ከዚሁ ግብይት የተገኘውም ገንዘብ ከጋራ ሀብታቸው ጋር የተቀላቀለ መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ከዚህ ንብረት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ ወይም ንብረት ከጋራ ሀብታቸው በቅድሚያ የማንሳት መብት ይኖረዋል፡፡ ባልና ሚስት የየግል ሀብታቸውን የሚያነሱበት ሁኔታ ሲኖር ሁለቱም በመጨረሻ ከተገኘው የንብረት መጠን እንደየአስተዋጽኦዋቸው ሊደርሳቸው የሚችለውን ያህል የማንሳት መብት ይኖራቸዋል፡፡
3.#ስለካሳ
በዚህ ሕግ መሠረት የጋራ ንብረቱን ወይም የሌላኛውን ተጋቢ ንብረት በብቸኝነት እንዲያስተዳድር ሥልጣን የተሰጠው ተጋቢ ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ በፈፀማቸው ድርጊቶች ምክንያት ወይም ከብልሹ አስተዳደር የተነሳ ወይም የካሳ ጠያቂውን መብት በማታለል ድርጊቱ የጎዳ እንደሆነ፣ ፍርድ ቤቱ በተበዳዩ ጥያቄ ሲቀርብለት ተገቢ የጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ሊያዝ ይችላል፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከተ መሠረት የሚቀርብ የካሳ ጥያቄ ተፈፀመ የተባለው ድርጊት ጋብቻው ከመፍረሱ ከአምስት ዓመት በፊት የሆነ እንደሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
4.#ያለአግባብ ስለመበልጸግ
ባልና ሚስት ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በስተቀር ከባልና ሚስት የአንደኛው የግል ሀብት ከሆነ ንብረት የሌላኛው የግል ሀብት ወይም የጋራ ሀብታቸው ያለአግባብ መበልጸጉን ያስረዳ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ካሳ እንዲከፈለው ሊያዝ ይችላል፡፡
5.#የዕዳ ጠያቂዎችን መብት ስለማክበር
ከባልና ሚስት አንደኛው ወይም ሁለቱም በጋራ በፍርድ የተረጋገጠባቸው ወይም ሁለቱም ያመኑት ዕዳ መኖሩ የታወቀ እንደሆነ ይኸው ዕዳ የባልና ሚስት ሀብት ከመከፋፈሉ በፊት ተቀንሶ የሚከፈል ይሆናል፡፡
6.#የጋራ ሀብትን ስለማከፋፈል
ከዚህ በላይ የተመለከቱትና የባልና ሚስት ሀብትን በስምምነት ስለማከፋፈል የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለሁለቱም እኩል የሚከፋፈል ይሆናል፡፡
7.#የባልና ሚስት ሀብት በዓይነት የሚከፋፈል ስለመሆኑ
በመሠረቱ፣ እያንዳንዱ ተጋቢ ከጋራ ሀብቱ የተወሰነ ንብረት እንዲደርሰው በማድረግ የጋራ ሀብቱ በዓይነት እንዲከፋፈል ይደረጋል፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከተው አኳኋን እኩል ለማከፋፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፣ ልዩነቱ በገንዘብ እንዲካካስ ይደረጋል፡፡ የሀብት ክፍፍሉ በሚደረግበት ጊዜ እያንዳንዱ ተጋቢ ይበልጥ ጠቃሚነት ያላቸውን ንብረቶች እንዲያገኝ ለማድረግ ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡
8.#ለማከፋፈል አዳጋች ስለሆኑ ንብረቶች
ንብረቱ ለክፍፍል የማያመች ወይም ለማከፋፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነና ባልና ሚስቱን ንብረቱ ከሁለቱ ለአንዳቸው እንዲሰጥ ለማስማማት ሳይቻል የቀረ እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን ገንዘብ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል፡፡

Forwarded from Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ (Ayu)
#የመንግስት_ሠራተኞች_የጡረታ_መመሪያ!!!
1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡
2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡
3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡
4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡
5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::
6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡
7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡
8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡
9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡
10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
፫= የጡረታ መለያ ቁጥር
፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡
#አዩዘሀበሻ
======================
💎⬇️⬇️⬇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s