የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ 568 እዝባር 2000

አካል ጉዳተኞች፣ የሥራው ጠባይ እስከፈቀደ! ተፈላጊ ችሎታዎችን እስካሟሉ እና በውድድር ውጤት ብልጫ ነጥብ ካገኙ፣ በማንኛውም መሥሪያ ቤት ውስጥ የመቀጠር መብት አላቸው፡፡በውድድር ወቅትም እኩል ወይም ተቀራራቢ ነጥብ ካገኙ፤ ለስራው ወይም ለሥልጠና ቅድሚያ የሚያገኙበት መብት አላቸው!

ቀጣሪዎች ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የሥራ አካባቢንና የሥልጠና እድሎችን ማመቻቸት ግዴታ ነው፡፡ቀጣሪዎች ተስማሚ መሣሪያዎችን የማሟላትና ረዳት ለሚያስፈልጋቸውም ረዳት የመመደብ ግዴታ አለባቸው!

በልዩ ሁኔታ ሴት አካል ጉዳተኞች ያለባቸውን ተደራራቢ ጫና ያገናዘበ ተገቢ የሆነ የማስተካከያ የድጋፍ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

የአካል ጉዳተኞችን የስራ እና የቅጥር መብት በማክበር የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ህይወት እንዲሻሻል የድርሻችንን እንወጣ!

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ከሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ ባገኘዉ የገንዘብ ድጋፍ

Website: https://elda-eth.com/
Facebook: https://web.facebook.com/p/Ethiopian-Lawyers-With-Disabilities-Association-
Linkdin: [https://www.linkedin.com/company/ethiopian-lawyers-with-disabilities-association/]
Tik tok : https://vm.tiktok.com/ZMSumrLhm/
❤1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ 568 እዝባር 2000

አካል ጉዳተኞች፣ የሥራው ጠባይ እስከፈቀደ! ተፈላጊ ችሎታዎችን እስካሟሉ እና በውድድር ውጤት ብልጫ ነጥብ ካገኙ፣ በማንኛውም መሥሪያ ቤት ውስጥ የመቀጠር መብት አላቸው፡፡በውድድር ወቅትም እኩል ወይም ተቀራራቢ ነጥብ ካገኙ፤ ለስራው ወይም ለሥልጠና ቅድሚያ የሚያገኙበት መብት አላቸው!

ቀጣሪዎች ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የሥራ አካባቢንና የሥልጠና እድሎችን ማመቻቸት ግዴታ ነው፡፡ቀጣሪዎች ተስማሚ መሣሪያዎችን የማሟላትና ረዳት ለሚያስፈልጋቸውም ረዳት የመመደብ ግዴታ አለባቸው!

በልዩ ሁኔታ ሴት አካል ጉዳተኞች ያለባቸውን ተደራራቢ ጫና ያገናዘበ ተገቢ የሆነ የማስተካከያ የድጋፍ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

የአካል ጉዳተኞችን የስራ እና የቅጥር መብት በማክበር የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ህይወት እንዲሻሻል የድርሻችንን እንወጣ!

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ከሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ ባገኘዉ የገንዘብ ድጋፍ

Website: https://elda-eth.com/
Facebook: https://web.facebook.com/p/Ethiopian-Lawyers-With-Disabilities-Association-
Linkdin: [https://www.linkedin.com/company/ethiopian-lawyers-with-disabilities-association/]
Tik tok : https://vm.tiktok.com/ZMSumrLhm/
ከጋብቻ ፍቺ በኋላ የባልና ሚስትን ሀብት ስለማጣራት የፍቺ ውጤት ስለመወሰን
==========================
1.#የባልና ሚስትን ሀብት በስምምነት ስለማጣራት
በዚህ ሕግ ስለካሣ ክፍያ የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው ጋብቻው በዚህ ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የፈረሰ እንደሆነ ባልና ሚስቱ የጋብቻቸው መፍረስ በንብረት በኩል የሚያስከትለውን ውጤት አስመልክተው በሚያደርጉት ስምምነት ወይም በጋብቻ ውላቸው መሠረት ይጣራል፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከተው የጋብቻ ውል ወይም ስምምነት የሌለ ወይም በሕግ ፊት የማይፀና ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የባልና ሚስት ሀብት በሚከተሉት ድንጋጌዎች መሠረት ይጣራል፡፡
2.#የግል ሀብትን መልሶ ስለመውሰድ
ባል ወይም ሚስት የግሉ መሆኑን በማስረዳት የግል ሀብቱ የሆነውን ንብረቱን መልሶ የመውሰድ መብት ይኖረዋል፡፡
ከባልና ሚስቱ አንደኛው የግል ሀብቱ የሆነ ማናቸውም ንብረት ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑንና ከዚሁ ግብይት የተገኘውም ገንዘብ ከጋራ ሀብታቸው ጋር የተቀላቀለ መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ከዚህ ንብረት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ ወይም ንብረት ከጋራ ሀብታቸው በቅድሚያ የማንሳት መብት ይኖረዋል፡፡ ባልና ሚስት የየግል ሀብታቸውን የሚያነሱበት ሁኔታ ሲኖር ሁለቱም በመጨረሻ ከተገኘው የንብረት መጠን እንደየአስተዋጽኦዋቸው ሊደርሳቸው የሚችለውን ያህል የማንሳት መብት ይኖራቸዋል፡፡
3.#ስለካሳ
በዚህ ሕግ መሠረት የጋራ ንብረቱን ወይም የሌላኛውን ተጋቢ ንብረት በብቸኝነት እንዲያስተዳድር ሥልጣን የተሰጠው ተጋቢ ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ በፈፀማቸው ድርጊቶች ምክንያት ወይም ከብልሹ አስተዳደር የተነሳ ወይም የካሳ ጠያቂውን መብት በማታለል ድርጊቱ የጎዳ እንደሆነ፣ ፍርድ ቤቱ በተበዳዩ ጥያቄ ሲቀርብለት ተገቢ የጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ሊያዝ ይችላል፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከተ መሠረት የሚቀርብ የካሳ ጥያቄ ተፈፀመ የተባለው ድርጊት ጋብቻው ከመፍረሱ ከአምስት ዓመት በፊት የሆነ እንደሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
4.#ያለአግባብ ስለመበልጸግ
ባልና ሚስት ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በስተቀር ከባልና ሚስት የአንደኛው የግል ሀብት ከሆነ ንብረት የሌላኛው የግል ሀብት ወይም የጋራ ሀብታቸው ያለአግባብ መበልጸጉን ያስረዳ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ካሳ እንዲከፈለው ሊያዝ ይችላል፡፡
5.#የዕዳ ጠያቂዎችን መብት ስለማክበር
ከባልና ሚስት አንደኛው ወይም ሁለቱም በጋራ በፍርድ የተረጋገጠባቸው ወይም ሁለቱም ያመኑት ዕዳ መኖሩ የታወቀ እንደሆነ ይኸው ዕዳ የባልና ሚስት ሀብት ከመከፋፈሉ በፊት ተቀንሶ የሚከፈል ይሆናል፡፡
6.#የጋራ ሀብትን ስለማከፋፈል
ከዚህ በላይ የተመለከቱትና የባልና ሚስት ሀብትን በስምምነት ስለማከፋፈል የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለሁለቱም እኩል የሚከፋፈል ይሆናል፡፡
7.#የባልና ሚስት ሀብት በዓይነት የሚከፋፈል ስለመሆኑ
በመሠረቱ፣ እያንዳንዱ ተጋቢ ከጋራ ሀብቱ የተወሰነ ንብረት እንዲደርሰው በማድረግ የጋራ ሀብቱ በዓይነት እንዲከፋፈል ይደረጋል፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከተው አኳኋን እኩል ለማከፋፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፣ ልዩነቱ በገንዘብ እንዲካካስ ይደረጋል፡፡ የሀብት ክፍፍሉ በሚደረግበት ጊዜ እያንዳንዱ ተጋቢ ይበልጥ ጠቃሚነት ያላቸውን ንብረቶች እንዲያገኝ ለማድረግ ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡
8.#ለማከፋፈል አዳጋች ስለሆኑ ንብረቶች
ንብረቱ ለክፍፍል የማያመች ወይም ለማከፋፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነና ባልና ሚስቱን ንብረቱ ከሁለቱ ለአንዳቸው እንዲሰጥ ለማስማማት ሳይቻል የቀረ እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን ገንዘብ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል፡፡
#የመንግስት_ሠራተኞች_የጡረታ_መመሪያ!!!
1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡
2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡
3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡
4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡
5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::
6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-

= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-

፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)

፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ

፫= የጡረታ መለያ ቁጥር

፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ

፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ

፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ

፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡
#አዩዘሀበሻ
‎======================
💎⬇️⬇️⬇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
የመንግስት ሰራተኞች የተሻሻለው አዋጅ 1353/2017 ያለደመወዝ የሚሰጥ ልዩ ፈቃድ እና በችሎታ ማነስ ምክንያት ሰራተኛውን ከስራ የማሰናበት ቅደም ተከተል👇👇👇
፩. የመንግሥት ሠራተኛ በበቂ ምክንያት
ደመወዝ የማይከፈልበት ልዩ ፈቃድ እንዲሰጠው ሲጠይቅና የመሥሪያ ቤቱን ጥቅም የማይጎዳ ሲሆን የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ከአንድ ዓመት ለማይበልጥ
ጊዜ ሊፈቅድለት ይችላል፤
፪. የመንግሥት ሠራተኛ በሕዝብ ምርጫ
ለመወዳደር ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ
የምርጫ ቅስቀሳ በሚካሄድበት ወቅት
እና ምርጫው በሚከናወንበት ጊዜ ያለ
ደመወዝ ፈቃድ እንዲሰጠው
ይደረጋል፤
፫. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ቢኖርም የመንግሥት ሠራተኛው
ያለደመወዝ ልዩ ፈቃድ እንዲሰጠው
የጠየቀው የመንግሥት
መሥሪያ ቤትን በሚመለከት የፕሮጀክት ሥራ ላይ በመመደቡ ወይም በትዳር
ጓደኛው ለዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራ
በውጭ ሀገር መመደብ ምክንያት ከሆነ
ልዩ ፈቃዱ የፕሮጀክት ወይም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራው
እስከሚጠናቀቅ ላለው ጊዜ ሊሰጠው
ይችላል፡፡

🎯በችሎታ እና ብቃት ማነስ ምክንያት ከሥራ የማሰናበት አሠራር ሥርዓት ቅደም ተከተል፡-
   ፩. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት
ሠራተኛ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ
ስድስት ወር በሥራ አፈጻጸም ውጤቱ
የችሎታ ማነስ ከታየበት ምክርና ተገቢው
የአቅም ማጎልበት ሥልጠናዎች ይሰጠዋል፤
   ፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩)
የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
የመንግሥት ሠራተኛ በተመደበበት
ሥራ ላይ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱ
በበጀት ዓመት ለሁለት ጊዜ ያህል
ከመካከለኛ ውጤት በታች ካገኘ በዕቅድ
አፈጻጸም የችሎታ ማነስ ምክንያት ከሥራ ይሰናበታል፤
    ፫. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ከተመደበበት ሥራ ጋር በተያያዘ
በብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሂደት
በስድስት ወር ለሁለት ጊዜ ያህል
ተመዝኖ ከዝቅተኛ ማለፍያ ውጤት
በታች ካገኘ በብቃት ማነስ ምክንያት
ከሥራ ይሰናበታል፤
፬ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩)፣(፪)
እና (፫) መሠረት የመንግሥት ሠራተኛውን ከሥራ ማሰናበት የሚቻለው
አንቀጽ ፵፬ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ዓላማ እና በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፻፵፪ ላይ የጡረታ መብት ተጠብቆ አገልግሎትን
ስለማቋረጥ የተደነገገውን በመከተል
ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡
(አዩዘሀበሻ)
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤2
የመንግስት ሰራተኞች የተሻሻለው አዋጅ 1353/2017 ስለ ቋሚ የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥር ምን ይላል?👇
፩.  የሚከተሉት በቋሚ የመንግሥት
ሠራተኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ      ምክንያቶች ናቸው፡-
ሀ) ዕድሜ ፲፰ ዓመት እና በላይ፤  
   ፷ ዓመት በታች የሆነ ሰው፤
ለ) ቅጣቱን አጠናቆ ከተሰየመ፣ በይርጋ
ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሠረዘ
በኋላ አምስት ዓመት ያለፈው፣ የሙስና፣የእምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣የማጭበርበር ወይም
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት
ያልተፈረደበት ማንኛውም ሰው፤ 
ሐ) የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ያለው ወይም በመንግስት  ሠራተኞች የብቃት ምዘና ሥርዓት ዝርጋታ ደንብ በሚወሰነው ጊዜ ገደብ የታደሰ ማስረጃ ያለው ሰው፤ እና
መ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፰ መሠረት ቃለ መሃላ ለመፈጸም ፈቃደኛ
የሆነ ሰው፡፡
፪. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተራ
ፊደል (ለ) እንደተጠበቀ ሆኖ ከማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፻፴፮ መሠረት
በዲስፕሊን ጉድለት ምክንያት ከሥራ
የተሰናበተ ሰው የባህሪው መሻሻል
ተረጋግጦ ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ
ጀምሮ አምስት ዓመት ከሞላበት ቀን
ጀምሮ በመንግሥት ሠራተኛነት
መቅጠር ይቻላል፤
፫. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተራ ፊደል (ሐ) እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም አመልካች በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ ለማገልገል ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ ከኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ምርመራ በስተቀር
የጤንነት ማረጋገጫ የሕክምና ምርመራ
ከጤና ተቋም እና በዚህ አንቀጽ ንዑስ
አንቀጽ (፩) ተራ ፊደል (ለ) ከተጠቀሱት
ወንጀሎች ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ
ከፖሊስ ተቋም የተሰጠ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 
፳፪. የውጭ ሀገር ዜጎች ቅጥር
የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን
በትውልድ ሀገራቸው በተለያዩ መብቶች
ተጠቃሚ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፸/፲፱፺፬ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና የዚሁ አዋጅ አንቀጽ ፴፪ ንዑስ አንቀጽ (፪) እንደተጠበቁ ሆነው ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው በመንግሥት ሠራተኛነት ሊቀጠር አይችልም፡፡
(አዩዘሀበሻ)
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
👉የስጦታ ዉል ማለት ሰጪዉ ለሌላ ሰዉ ችሮታ በማድረግ ሃሳብ ከንብረቶቹ አንዱን የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ዉል ስለመሆኑና ስጦታ ማድረግ የሰጪዉ የግል ተግባር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2427 እና 2434 ይደነግጋል፡:
👉ከዚህ እንደምንገነዘበዉ ስጦታ ዉል የጸና ዉል እንዲሆን እንደማናቸዉም የዉል ጉዳዮች በዉል ህግ የተደነገገዉን መሰረታዊ መስፈርት
አሟልቶ መገኘት ያለበት መሆኑን ነዉ፡:
👉የስጦታ ዉሉ በህግ የተመለከተዉን መሰረታዊ መስፈርት እና ስለስጦታ ዉል የተደነገጉትን ደንቦች አላሟላም በሚል መብትና ጥቅሙ የተነካበት ወገን ዉሉ እንዲፈርስ ሊጠይቅ እንደሚችል ከዉል ህጎች ጠቅላላ ድንጋጌ እና ስለስጦታ ዉሎች ከተደነገገዉ ልዩ ከፍል መገንዘብ ይቻላል።
👉በመሰረቱ አንድ ዉል እንዲፈርስየሚደረገዉ ዉሉ የተቋቋመበት ሁኔታ ከመሰረቱ ግድፈት ሲኖርበት ነዉ።
👉ይኸዉም የተዋዋይ ወገን ለመዋዋል ችሎታ ወይም ፈቃድ ጉድለት ሲኖር ወይም የዉለታዉ ጉዳይ ህግን ወይም ግብረ ገብነት/ሞራል/ የሚጻረር ሲሆን ወይም በህግ የተደነገገዉን ፎርም ሳያሟላ ሲቀር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
👉ከእነዚህ ምክንያቶች በአንዱ ወይም በሌላ ሁኔታ ዉሉ ጉድለት አለበት በሚል ዉሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የሚችለዉ ወገን ማንነት እንደየምክንያቱ የሚለያይ መሆኑም በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል።
👉ይህ እንደ አጠቃላይ ሆኖ የስጦታዉ ዉል ሊፈርስ የሚችልባቸዉ ልዩ ሁኔታዎች በህጉ አንቀጽ 2437 እስከ 2440 ላይ ተዘርዝረዋል፡፡👉በዚህም መሠረት የስጦታ ዉል ሊፈርስ የሚችለዉ ስጦታዉ በተደረገበት ወቅት ስጦታ አድራጊዉ የአእምሮ ችግር እንዳለበት ታዉቆ በፍርድ ክልከላ የተደረገበት (judicial interdiction) ወይም ስጦታዉ የተደረገዉ ስጦታ ሰጪዉ የፍርድ ክልከላ እንዲደረግበት ለፍርድ ቤት ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ወይም ስጦታዉ ሲደረግ የስጦታ ሰጪዉ አእምሮ ጤነኛ አለመሆኑን የዉሉ ይዘት የሚያሳይ ሲሆን፣ ስጦታዉን ለማድረግ መነሻ
የሆነዉ ምክንያት ከህግ ወይም ከሞራል ተቃራኒ ከሆነ፣ ስጦታዉ ሲደረግ ስጦታ ሰጪዉ
በመንፈስ ጫና (undue influence) ስር መሆኑ ከተረጋገጠ ስለመሆኑ ከድንጋጌዎች ይዘትመገንዘብ ይቻላል፡፡
👉ስለሆነም የስጦታ ዉል እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ የሚያቀርብ ሰዉ ከእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሁኔታ መኖሩን የመግለጽ እና ይህንኑ የማረጋገጥ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
 
👉የሰ/መ/ቁ.200144 ቀን፡- 02/02/2014ዓ.ም
Forwarded from fasika aggena
fasika aggena
የመሬት_ይዞታ_መብት_ፈጠራ_እና_አገልግሎት_አሰጣጥ_ደንብ_ቁጥር_195_2017.pdf
አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ ለተያዙ ይዞታዎች በደንብ ቁጥር 163/2016 የተሰጠው የ1 ዓመት የአገልግሎት መስጫ ጊዜ መጋቢት 2017 ላይ መጠናቀቁ ይታወቃል። ይህ የማሻሻያ ደንብ ይህን ጊዜ በ2 ዓመት አራዝሞታል።
⚖️ የፍርድ ቤት መጥሪያ በ Telegram (ማህበራዊ ሚዲያ) ሊደርስ ይችላል?
Abrham Yohanes
የሰበር መዝገብ ቁጥር: 213020 ቀን: 🗓 ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

📰 የጉዳዩ ማጠቃለያ
የጉዳዩ ክርክር የተጀመረው በአሁን ተጠሪ (ወ/ሮ ዓለም ቤዛ የሻው) በአሁን አመልካች (አቶ ዳኛቸው ደመቀ ከበደ) ላይ ባቀረቡት የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል እና የልጅ ቀለብ ጥያቄ ነው። ግራ ቀኙ ለ10 ዓመታት ያህል በጋብቻ ሳይተሳሰሩ አብረው የኖሩ ሲሆን፣ በተፈራው የጋራ ቤት 🏠 ላይ ክፍፍል እና ለልጃቸው ቀለብ 💰 እንዲቆረጥ ተጠይቋል።
የሥር ፍርድ ቤት (የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት) መጥሪያውን ለአመልካች ለማድረስ የተለያዩ ሙከራዎችን (ፖሊስን ማዘዝ 👮‍♂️፣ በጋዜጣ ጥሪ 📢 ማድረግ) አድርጓል፤ ምክንያቱም ተጠሪ አመልካች አገር ውስጥ እንደሌለ ገልጻለች። ፍርድ ቤቱ አመልካች በጋዜጣ ጥሪ ቀርቦ ባለማግኘቱ በሌለበት ጉዳዩን አይቶ ቤቱን ለጋራ ሀብትነት ወስኖ የልጅ ቀለብ በወር 3,000 ብር እንዲከፍል ወስኗል።
አመልካች (አቶ ዳኛቸው) ከኢትዮጵያ ውጭ (እንግሊዝ 🇬🇧) ነዋሪ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ በአግባቡ ሳይደርሳቸው በሌሉበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳላቸው በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 78 መሰረት አቤቱታ አቅርበዋል። ምክንያታቸውም ውሳኔውን ያወቁት ተጠሪ በስልክ 📞 ደውላ በቫይበር 📲 ከላከችላቸው በኋላ መሆኑን እና ከእኔ ጋር በስልክና በቫይቨር እንገናኝ የነበረ ሲሆን፣ ዉሳኔዉን ስልክ ደዉላልኝና በቫይቨር እንደላከችልኝ ሁሉ፣ ክሱን በቫይቨር ወይም በቴሌግራም 💬 ልታሳዉቀኝ እየቻለች የአመልካችን አድራሻ አላዉቀዉም በማለት በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ ማድረጓ ከቅን ልቦና 😇 ዉጭ በመሆኑ ፍትሕ የመግኘት መብታቸው እንደተነገፈ በአቤቱታቸው ገልጸዋል።
የሥር ፍርድ ቤት የአመልካቹን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ውሳኔውን አፅንቷል። ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል። በመጨረሻም አመልካች ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ❌ ተፈጽሞበታል በማለት ለሰበር ሰሚ ችሎት 🏛 አቤቱታ አቅርበዋል።

📜 የሕግ ትርጉም
ችሎቱ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓትን በሚመለከት በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 94-110 ያሉትን ድንጋጌዎች ተመልክቷል።
•  የመጥሪያ አደራረስ ቅደም ተከተል: የመጥሪያ አደራረስ ሂደት አራት የቅደም ተከተል ደረጃዎች እንዳሉት ተንትኗል። እነርሱም፡- ለተከሳሽ ለራሱ ማድረስ፣ መጥሪያውን ሊያደርስ ለሚችል ሰው ማድረስ፣ በፖስታ ✉️ ማድረስ፣ በመጨረሻም ምትክ የመጥሪያ አደራረስ ዘዴን (እንደ ጋዜጣ) መጠቀም ናቸው።

•  የፍርድ ቤቱ ግዴታ: ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበት ወገን የመከላከልና የመከራከር ሕገ መንግስታዊ መብት 🗣 እንዳይነፈግ፣ ሕጉ በዘረጋው የመጥሪያ አደራረስ ዘዴዎች ቅደም ተከተል መሰረት በተሻለ አማራጭ መጥሪያው እንዲደርስ ጥረት ማድረግ ይገባዋል።

•  በጉዳዩ ላይ ያለው ትርጓሜ: የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር በስልክና በቴሌግራም ግንኙነት እንዳላት ለፍርድ ቤቱ ሳታሳውቅ ቀርታ፣ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻው አማራጭ የሆነውን በጋዜጣ የመጥራት ዘዴን ወዲያውኑ መጠቀም ተገቢ አልነበረም። ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጥሪያ ዘዴ (ለምሳሌ ተጠሪ በስልክና በቴሌግራም ግንኙነት መኖሩን አስመልክቶ ማሳወቅ ወይም መጥሪያ በፖስታ ለመላክ መሞከር) ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ሳያደርግ በሌለበት ውሳኔ መስጠቱ ፍትሓዊ ሙግት የመስማት ሂደት እና የመሰማት መብትን የነፈገ ነው ብሏል።

•  ችሎቱ በሰ.መ.ቁ. 53113 (ቅጽ 12) ላይ የተላለፈውን አስገዳጅ ውሳኔ ✅ ተፈጻሚነት እንዳለው አረጋግጧል።
#Hemorrhagic_Fever ምንድን ነው❓
‎ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላትን በማጥቃት እና በሰውነት ውስጥ ያሉ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ፣ በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው።
‎
#‎የበሺታው_መንስኤ እና የቫይረስ ዓይነት

‎. Ebola and ,Rift Valley Fever (RVF) & Yellow Fever  ተብሎ የሚከፈል ሲሆን እንደ #ኢቦላቫይረስ  ፣#ደንጉ እና #የለውፊቨር የተባሉ ቫይርሶች የበሺታው መንስኤ ሲሆኑ #በትንኝ ንክሻም የሚመጡ ናቸው ።
‎
‎ በሽታው ስሙ እንደሚያመለክተው  በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም እንዲፈስ በማድረግ ለሞት የሚዳርግ ህክምና አልባ አደገኛ በሺታ ነው።
‎
‎በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም መድማት እና መፍስሥ ከተከሰተ የበሽታው ከባድ ደረጃ ምልክት ነው።
‎
‎በሽታው እንዴት ይተላለፋል?
‎
‎1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
‎2· በነፍሳት ንክሻ፡
‎3· ከሰው ወደ ሰው፡ ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።
‎
‎#የበሽታው_ምልክቶች
‎
‎ምልክቶቹ በድንገት ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ በተጠቃ ከ 2-21 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ
‎
‎መጀመሪያ ላይ የሚታዩ ምልክቶች
‎ምልክቶቹን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን
‎የመጀመሪው ቀለል ያሉ ምልክቶች እና የመጨረሻው አደገኛ //አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚታዩ ናቸው
‎
‎#የመጀመሪያ_ምልክቶች
‎· ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
‎· ድካም እና የመዛል ስሜት
‎· የጡንቻ፣ የአጥንት ህመም እና ቁርጥማት
‎· ራስ ምታት
‎· የጉሮሮ ህመም
‎
‎#ከባድ_ምልክቶች (በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ)፡
‎
‎· በቆዳ ስር ደም መውጣት 
‎. ከአፍ፣ አፍንጫ፣ ከዓይን ወይም ከጆሮ ደም መፍሰስ።
‎· የጭንቅላት አዕምሮ መናጋት ፣ መደንገጥ፣
‎. ራስን መሳት ኮማ ውስጥ መግባት)
‎· የኩላሊት እና የጉበት መጎዳት እና ስራ ማቆም
‎· ከፍተኛ ድካም እና ሾክ/Shock
‎· የበርካታ አካላት አለመሥራት
‎
‎እንዴት መከላከል ይቻላል ?
‎
‎በሽታው በትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በመሆኑ #የአልጋ_አጎበርን ነፍሶን ከሞት መታደግ ስለሆነ በአግባቡ ይጠቀሙት ። ከታማሚ ሰው ጋር ያልዎትን ንክክ መከላከል እና
‎አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ሆኖ ፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ፣
‎መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !
‎
‎ የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል !!
‎
‎1. እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
‎2. ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣  ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
‎ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
‎3. ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
‎4.ከ ነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር  መጠቀም፡
ይህን በሽታ ለመግታት እና ለመቆጣጠር መከላከያ መንገዶቹ ላይ ማተኮሩ ይመከራል።
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ከክ/ከተማው የፌደራል ፍትሕ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በወንጀል መከላከል የሕብረተሰቡ ተሳትፎ እና በአካል ጉዳተኞች፣ በሴቶችና በወጣቶች መብቶች ዙርያ ከሲቪክ ማሕበራት ለተወጣጡ የክ/ከተማው ነዋሪዎች ስልጠና ሰጠ!
በስልጠናው ተሳታፊዎች ለፍትሕ አካላት መረጃ በመስጠትና በሌሎች መንገዶች የፍትሕ ሥርዓቱን ማገዝ እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች እና ወጣቶች መብቶች ከዐለም አቀፍ፣ አህጉራዊና አገራዊ ሕጎች አንጻር በሕግ ስርጸትና ምክር አቃቤ ሕጎች በሰፊው ተዳሠዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች የተዳሰሱ ጉዳዮችን አስፈላጊነት የሚያጎሉ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በተለይም መጤና ባሕል በራዥ ሆነው በሴቶችና በተማሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከፍትሕ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት መከላከል የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።
Forwarded from Tibebu S.
⚖በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል  አይነቶች⚖
*
❖#በመርህ_ደረጃ_ወንጀል የመንግስትን እና የህዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ክስ የሚመሰረተው በመንግስት ዐቃቤ ህግ ነው። ሆኖም አንዳንድ የወንጀል አይነቶች በግል ተበዳይ እና በከሳሽ መካከል በሚደረግ እርቅ እንዲያልቁ ሕጉ ይፈቅዳል። በእርቅ ማለቁ   ለሁለቱም ወገኖች ጊዜን፣ ወጪንና ጉልበትን ከመቆጠብ ባሻገር በህብረተሰቡ  ውስጥ ሰላማዊ  የሆነ ማህበራዊ መስተጋብር ትስስርን  ያጎለብታል ።

❖#በወንጀል_ጉዳዮች_ላይ_እርቅ_የሚፈቀደው በአንጻራዊነት ክብደታቸው ዝቅተኛ በሆኑ እና በግለሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ነው። እነዚህ ወንጀሎች በመንግስት ወይም በህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት የማያስከትሉ በመሆኑ ጉዳዩ በግል ስምምነት እንዲያልቅ ይፈቀዳል።

❖#የግል_አቤቱታን_መሰረት_ሲያደርግ: አንዳንድ የወንጀል አይነቶች የሚመሰረቱት በተበዳዩ አካል የግል አቤቱታ ላይ ብቻ ነው። አቤቱታው ከተነሳ በኋላም ቢሆን ተበዳዩ እርቅ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ ክሱ ሊቋረጥ ይችላል።

@በእርቅ ማለቅ የሚችሉበት  የወንጀል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው ።እነሱም 

1. የእጅ እልፊት (አንቀጽ-560(1) ፣
2. የዛቻ ወንጀል (አንቀጽ-580) ፣
3. ታስቦ የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ 556(1)፣
4. በቸልተኝነት የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ-559(3))፣
5. አመንዝራነት (አንቀጽ-652) ፣
6. ስድብና እና ማዋረድ (አንቀጽ-615) ፣
7. የስም ማጥፋት ወንጀል (አንቀጽ-618) ፣
8. በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈጸመ ንብረት ነክ ወንጀል (አንቀጽ-664)
9. ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም(አንቀጽ-646)፣
10. ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት(አንቀጽ-558)፣
11. በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መጠቀም(አንቀጽ-678)፣
12. አግኝቶ መደበቅ(አንቀጽ-679)፣
13. በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ(አንቀጽ-686)፣
14. በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
(አንቀጽ-689)…ወዘተ ናቸው ።

በወንጀል ጉዳዮች ላይ እርቅ የሚፈፀምበት ሂደት#በጠቅላይ_ዐቃቤ_ህግ_መመሪያ_ቁጥር 22/2010 ጉዳዩ እንዴትእንደሚመራ፣ ተበዳዩ ምን መብቶች እንዳሉት እና እርቅ ሲደረግ ምን አይነት ጥንቃቄዎች መወሰድ እንዳለባት በዝርዝር ተቀምጧል::