Forwarded from Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ (Ayu)
የመንግስት ሰራተኞች የተሻሻለው አዋጅ 1353/2017 ያለደመወዝ የሚሰጥ ልዩ ፈቃድ እና በችሎታ ማነስ ምክንያት ሰራተኛውን ከስራ የማሰናበት ቅደም ተከተል👇👇👇
፩. የመንግሥት ሠራተኛ በበቂ ምክንያት
ደመወዝ የማይከፈልበት ልዩ ፈቃድ እንዲሰጠው ሲጠይቅና የመሥሪያ ቤቱን ጥቅም የማይጎዳ ሲሆን የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ከአንድ ዓመት ለማይበልጥ
ጊዜ ሊፈቅድለት ይችላል፤
፪. የመንግሥት ሠራተኛ በሕዝብ ምርጫ
ለመወዳደር ተወዳዳሪ ሆኖ ሲቀርብ
የምርጫ ቅስቀሳ በሚካሄድበት ወቅት
እና ምርጫው በሚከናወንበት ጊዜ ያለ
ደመወዝ ፈቃድ እንዲሰጠው
ይደረጋል፤
፫. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ቢኖርም የመንግሥት ሠራተኛው
ያለደመወዝ ልዩ ፈቃድ እንዲሰጠው
የጠየቀው የመንግሥት
መሥሪያ ቤትን በሚመለከት የፕሮጀክት ሥራ ላይ በመመደቡ ወይም በትዳር
ጓደኛው ለዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራ
በውጭ ሀገር መመደብ ምክንያት ከሆነ
ልዩ ፈቃዱ የፕሮጀክት ወይም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራው
እስከሚጠናቀቅ ላለው ጊዜ ሊሰጠው
ይችላል፡፡
🎯በችሎታ እና ብቃት ማነስ ምክንያት ከሥራ የማሰናበት አሠራር ሥርዓት ቅደም ተከተል፡-
፩. የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የመንግስት
ሠራተኛ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ
ስድስት ወር በሥራ አፈጻጸም ውጤቱ
የችሎታ ማነስ ከታየበት ምክርና ተገቢው
የአቅም ማጎልበት ሥልጠናዎች ይሰጠዋል፤
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩)
የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
የመንግሥት ሠራተኛ በተመደበበት
ሥራ ላይ የሥራ አፈጻጸም ውጤቱ
በበጀት ዓመት ለሁለት ጊዜ ያህል
ከመካከለኛ ውጤት በታች ካገኘ በዕቅድ
አፈጻጸም የችሎታ ማነስ ምክንያት ከሥራ ይሰናበታል፤
፫. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ከተመደበበት ሥራ ጋር በተያያዘ
በብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሂደት
በስድስት ወር ለሁለት ጊዜ ያህል
ተመዝኖ ከዝቅተኛ ማለፍያ ውጤት
በታች ካገኘ በብቃት ማነስ ምክንያት
ከሥራ ይሰናበታል፤
፬ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩)፣(፪)
እና (፫) መሠረት የመንግሥት ሠራተኛውን ከሥራ ማሰናበት የሚቻለው
አንቀጽ ፵፬ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ዓላማ እና በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፻፵፪ ላይ የጡረታ መብት ተጠብቆ አገልግሎትን
ስለማቋረጥ የተደነገገውን በመከተል
ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡
(አዩዘሀበሻ)
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

❤2
Forwarded from Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ (Ayu)
የመንግስት ሰራተኞች የተሻሻለው አዋጅ 1353/2017 ስለ ቋሚ የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥር ምን ይላል?👇
፩. የሚከተሉት በቋሚ የመንግሥት
ሠራተኛነት ለመቀጠር የሚያስችሉ ምክንያቶች ናቸው፡-
ሀ) ዕድሜ ፲፰ ዓመት እና በላይ፤
፷ ዓመት በታች የሆነ ሰው፤
ለ) ቅጣቱን አጠናቆ ከተሰየመ፣ በይርጋ
ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሠረዘ
በኋላ አምስት ዓመት ያለፈው፣ የሙስና፣የእምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣የማጭበርበር ወይም
የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት
ያልተፈረደበት ማንኛውም ሰው፤
ሐ) የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ያለው ወይም በመንግስት ሠራተኞች የብቃት ምዘና ሥርዓት ዝርጋታ ደንብ በሚወሰነው ጊዜ ገደብ የታደሰ ማስረጃ ያለው ሰው፤ እና
መ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፰ መሠረት ቃለ መሃላ ለመፈጸም ፈቃደኛ
የሆነ ሰው፡፡
፪. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተራ
ፊደል (ለ) እንደተጠበቀ ሆኖ ከማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት
በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፻፴፮ መሠረት
በዲስፕሊን ጉድለት ምክንያት ከሥራ
የተሰናበተ ሰው የባህሪው መሻሻል
ተረጋግጦ ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ
ጀምሮ አምስት ዓመት ከሞላበት ቀን
ጀምሮ በመንግሥት ሠራተኛነት
መቅጠር ይቻላል፤
፫. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተራ ፊደል (ሐ) እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም አመልካች በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ ለማገልገል ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ ከኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ምርመራ በስተቀር
የጤንነት ማረጋገጫ የሕክምና ምርመራ
ከጤና ተቋም እና በዚህ አንቀጽ ንዑስ
አንቀጽ (፩) ተራ ፊደል (ለ) ከተጠቀሱት
ወንጀሎች ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ
ከፖሊስ ተቋም የተሰጠ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
፳፪. የውጭ ሀገር ዜጎች ቅጥር
የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን
በትውልድ ሀገራቸው በተለያዩ መብቶች
ተጠቃሚ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፸/፲፱፺፬ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና የዚሁ አዋጅ አንቀጽ ፴፪ ንዑስ አንቀጽ (፪) እንደተጠበቁ ሆነው ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው በመንግሥት ሠራተኛነት ሊቀጠር አይችልም፡፡

👉የስጦታ ዉል ማለት ሰጪዉ ለሌላ ሰዉ ችሮታ በማድረግ ሃሳብ ከንብረቶቹ አንዱን የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ዉል ስለመሆኑና ስጦታ ማድረግ የሰጪዉ የግል ተግባር ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2427 እና 2434 ይደነግጋል፡:
👉ከዚህ እንደምንገነዘበዉ ስጦታ ዉል የጸና ዉል እንዲሆን እንደማናቸዉም የዉል ጉዳዮች በዉል ህግ የተደነገገዉን መሰረታዊ መስፈርት
አሟልቶ መገኘት ያለበት መሆኑን ነዉ፡:
👉የስጦታ ዉሉ በህግ የተመለከተዉን መሰረታዊ መስፈርት እና ስለስጦታ ዉል የተደነገጉትን ደንቦች አላሟላም በሚል መብትና ጥቅሙ የተነካበት ወገን ዉሉ እንዲፈርስ ሊጠይቅ እንደሚችል ከዉል ህጎች ጠቅላላ ድንጋጌ እና ስለስጦታ ዉሎች ከተደነገገዉ ልዩ ከፍል መገንዘብ ይቻላል።
👉በመሰረቱ አንድ ዉል እንዲፈርስየሚደረገዉ ዉሉ የተቋቋመበት ሁኔታ ከመሰረቱ ግድፈት ሲኖርበት ነዉ።
👉ይኸዉም የተዋዋይ ወገን ለመዋዋል ችሎታ ወይም ፈቃድ ጉድለት ሲኖር ወይም የዉለታዉ ጉዳይ ህግን ወይም ግብረ ገብነት/ሞራል/ የሚጻረር ሲሆን ወይም በህግ የተደነገገዉን ፎርም ሳያሟላ ሲቀር ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
👉ከእነዚህ ምክንያቶች በአንዱ ወይም በሌላ ሁኔታ ዉሉ ጉድለት አለበት በሚል ዉሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የሚችለዉ ወገን ማንነት እንደየምክንያቱ የሚለያይ መሆኑም በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል።
👉ይህ እንደ አጠቃላይ ሆኖ የስጦታዉ ዉል ሊፈርስ የሚችልባቸዉ ልዩ ሁኔታዎች በህጉ አንቀጽ 2437 እስከ 2440 ላይ ተዘርዝረዋል፡፡👉በዚህም መሠረት የስጦታ ዉል ሊፈርስ የሚችለዉ ስጦታዉ በተደረገበት ወቅት ስጦታ አድራጊዉ የአእምሮ ችግር እንዳለበት ታዉቆ በፍርድ ክልከላ የተደረገበት (judicial interdiction) ወይም ስጦታዉ የተደረገዉ ስጦታ ሰጪዉ የፍርድ ክልከላ እንዲደረግበት ለፍርድ ቤት ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ወይም ስጦታዉ ሲደረግ የስጦታ ሰጪዉ አእምሮ ጤነኛ አለመሆኑን የዉሉ ይዘት የሚያሳይ ሲሆን፣ ስጦታዉን ለማድረግ መነሻ
የሆነዉ ምክንያት ከህግ ወይም ከሞራል ተቃራኒ ከሆነ፣ ስጦታዉ ሲደረግ ስጦታ ሰጪዉ
በመንፈስ ጫና (undue influence) ስር መሆኑ ከተረጋገጠ ስለመሆኑ ከድንጋጌዎች ይዘትመገንዘብ ይቻላል፡፡
👉ስለሆነም የስጦታ ዉል እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ የሚያቀርብ ሰዉ ከእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሁኔታ መኖሩን የመግለጽ እና ይህንኑ የማረጋገጥ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
👉የሰ/መ/ቁ.200144 ቀን፡- 02/02/2014ዓ.ም

Forwarded from fasika aggena
fasika aggena
የመሬት_ይዞታ_መብት_ፈጠራ_እና_አገልግሎት_አሰጣጥ_ደንብ_ቁጥር_195_2017.pdf
አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ ለተያዙ ይዞታዎች በደንብ ቁጥር 163/2016 የተሰጠው የ1 ዓመት የአገልግሎት መስጫ ጊዜ መጋቢት 2017 ላይ መጠናቀቁ ይታወቃል። ይህ የማሻሻያ ደንብ ይህን ጊዜ በ2 ዓመት አራዝሞታል።
⚖️ የፍርድ ቤት መጥሪያ በ Telegram (ማህበራዊ ሚዲያ) ሊደርስ ይችላል?
Abrham Yohanes
የሰበር መዝገብ ቁጥር: 213020 ቀን: 🗓 ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም
📰 የጉዳዩ ማጠቃለያ
የጉዳዩ ክርክር የተጀመረው በአሁን ተጠሪ (ወ/ሮ ዓለም ቤዛ የሻው) በአሁን አመልካች (አቶ ዳኛቸው ደመቀ ከበደ) ላይ ባቀረቡት የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል እና የልጅ ቀለብ ጥያቄ ነው። ግራ ቀኙ ለ10 ዓመታት ያህል በጋብቻ ሳይተሳሰሩ አብረው የኖሩ ሲሆን፣ በተፈራው የጋራ ቤት 🏠 ላይ ክፍፍል እና ለልጃቸው ቀለብ 💰 እንዲቆረጥ ተጠይቋል።
የሥር ፍርድ ቤት (የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት) መጥሪያውን ለአመልካች ለማድረስ የተለያዩ ሙከራዎችን (ፖሊስን ማዘዝ 👮♂️፣ በጋዜጣ ጥሪ 📢 ማድረግ) አድርጓል፤ ምክንያቱም ተጠሪ አመልካች አገር ውስጥ እንደሌለ ገልጻለች። ፍርድ ቤቱ አመልካች በጋዜጣ ጥሪ ቀርቦ ባለማግኘቱ በሌለበት ጉዳዩን አይቶ ቤቱን ለጋራ ሀብትነት ወስኖ የልጅ ቀለብ በወር 3,000 ብር እንዲከፍል ወስኗል።
አመልካች (አቶ ዳኛቸው) ከኢትዮጵያ ውጭ (እንግሊዝ 🇬🇧) ነዋሪ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ በአግባቡ ሳይደርሳቸው በሌሉበት የተሰጠው ውሳኔ እንዲነሳላቸው በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 78 መሰረት አቤቱታ አቅርበዋል። ምክንያታቸውም ውሳኔውን ያወቁት ተጠሪ በስልክ 📞 ደውላ በቫይበር 📲 ከላከችላቸው በኋላ መሆኑን እና ከእኔ ጋር በስልክና በቫይቨር እንገናኝ የነበረ ሲሆን፣ ዉሳኔዉን ስልክ ደዉላልኝና በቫይቨር እንደላከችልኝ ሁሉ፣ ክሱን በቫይቨር ወይም በቴሌግራም 💬 ልታሳዉቀኝ እየቻለች የአመልካችን አድራሻ አላዉቀዉም በማለት በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግ ማድረጓ ከቅን ልቦና 😇 ዉጭ በመሆኑ ፍትሕ የመግኘት መብታቸው እንደተነገፈ በአቤቱታቸው ገልጸዋል።
የሥር ፍርድ ቤት የአመልካቹን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ውሳኔውን አፅንቷል። ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል። በመጨረሻም አመልካች ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ❌ ተፈጽሞበታል በማለት ለሰበር ሰሚ ችሎት 🏛 አቤቱታ አቅርበዋል።
📜 የሕግ ትርጉም
ችሎቱ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓትን በሚመለከት በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 94-110 ያሉትን ድንጋጌዎች ተመልክቷል።
• የመጥሪያ አደራረስ ቅደም ተከተል: የመጥሪያ አደራረስ ሂደት አራት የቅደም ተከተል ደረጃዎች እንዳሉት ተንትኗል። እነርሱም፡- ለተከሳሽ ለራሱ ማድረስ፣ መጥሪያውን ሊያደርስ ለሚችል ሰው ማድረስ፣ በፖስታ ✉️ ማድረስ፣ በመጨረሻም ምትክ የመጥሪያ አደራረስ ዘዴን (እንደ ጋዜጣ) መጠቀም ናቸው።
• የፍርድ ቤቱ ግዴታ: ፍርድ ቤት ክስ የቀረበበት ወገን የመከላከልና የመከራከር ሕገ መንግስታዊ መብት 🗣 እንዳይነፈግ፣ ሕጉ በዘረጋው የመጥሪያ አደራረስ ዘዴዎች ቅደም ተከተል መሰረት በተሻለ አማራጭ መጥሪያው እንዲደርስ ጥረት ማድረግ ይገባዋል።
• በጉዳዩ ላይ ያለው ትርጓሜ: የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር በስልክና በቴሌግራም ግንኙነት እንዳላት ለፍርድ ቤቱ ሳታሳውቅ ቀርታ፣ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻው አማራጭ የሆነውን በጋዜጣ የመጥራት ዘዴን ወዲያውኑ መጠቀም ተገቢ አልነበረም። ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጥሪያ ዘዴ (ለምሳሌ ተጠሪ በስልክና በቴሌግራም ግንኙነት መኖሩን አስመልክቶ ማሳወቅ ወይም መጥሪያ በፖስታ ለመላክ መሞከር) ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ሳያደርግ በሌለበት ውሳኔ መስጠቱ ፍትሓዊ ሙግት የመስማት ሂደት እና የመሰማት መብትን የነፈገ ነው ብሏል።
• ችሎቱ በሰ.መ.ቁ. 53113 (ቅጽ 12) ላይ የተላለፈውን አስገዳጅ ውሳኔ ✅ ተፈጻሚነት እንዳለው አረጋግጧል።

#Hemorrhagic_Fever ምንድን ነው❓
ይህ በሽታ በቫይረስ የሚከሰት ከባድ የበሽታ ቡድን ነው ። በሽታው በመሰረቱ የደም መፍሰስን ወይም የደም መርጋትን በሰውነት ውስጥ የሚያመጣ ነው ። በርካታ የሰውነት አካላትን በማጥቃት እና በሰውነት ውስጥ ያሉ የደም ሥሮችን የሚጎዳ ፣ በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጣ በሽታ ነው።
#የበሺታው_መንስኤ እና የቫይረስ ዓይነት
. Ebola and ,Rift Valley Fever (RVF) & Yellow Fever ተብሎ የሚከፈል ሲሆን እንደ #ኢቦላቫይረስ ፣#ደንጉ እና #የለውፊቨር የተባሉ ቫይርሶች የበሺታው መንስኤ ሲሆኑ #በትንኝ ንክሻም የሚመጡ ናቸው ።
በሽታው ስሙ እንደሚያመለክተው በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም እንዲፈስ በማድረግ ለሞት የሚዳርግ ህክምና አልባ አደገኛ በሺታ ነው።
በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደም መድማት እና መፍስሥ ከተከሰተ የበሽታው ከባድ ደረጃ ምልክት ነው።
በሽታው እንዴት ይተላለፋል?
1· ከተያዙ እንስሳት ጋር በመነካካት፡ በእንስሳት (ለምሳሌ አይጥ) ፣ ሽንት፣ ምራቅ ፣ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች በሚነካኩበት ጊዜ።
2· በነፍሳት ንክሻ፡
3· ከሰው ወደ ሰው፡ ከተያዘ ሰው የሚገኘው ደም፣ ምራቅ፣ የሰውነት ፈሳሾች ወይም ሌሎች ክምችቶች በቀጥታ በሚነካኩበት ጊዜ። ይህ ለበሽታው ከባዱ እና ዋነኛው ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ነው።
#የበሽታው_ምልክቶች
ምልክቶቹ በድንገት ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ በተጠቃ ከ 2-21 ቀናት ውስጥ ምልክቶቹ መታየት ይጀምራሉ
መጀመሪያ ላይ የሚታዩ ምልክቶች
ምልክቶቹን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን
የመጀመሪው ቀለል ያሉ ምልክቶች እና የመጨረሻው አደገኛ //አስጊ ደረጃ ላይ ሲደርስ የሚታዩ ናቸው
#የመጀመሪያ_ምልክቶች
· ከፍተኛ የሰውነት ሙቀት (ትኩሳት)
· ድካም እና የመዛል ስሜት
· የጡንቻ፣ የአጥንት ህመም እና ቁርጥማት
· ራስ ምታት
· የጉሮሮ ህመም
#ከባድ_ምልክቶች (በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ)፡
· በቆዳ ስር ደም መውጣት
. ከአፍ፣ አፍንጫ፣ ከዓይን ወይም ከጆሮ ደም መፍሰስ።
· የጭንቅላት አዕምሮ መናጋት ፣ መደንገጥ፣
. ራስን መሳት ኮማ ውስጥ መግባት)
· የኩላሊት እና የጉበት መጎዳት እና ስራ ማቆም
· ከፍተኛ ድካም እና ሾክ/Shock
· የበርካታ አካላት አለመሥራት
እንዴት መከላከል ይቻላል ?
በሽታው በትንኝ ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በመሆኑ #የአልጋ_አጎበርን ነፍሶን ከሞት መታደግ ስለሆነ በአግባቡ ይጠቀሙት ። ከታማሚ ሰው ጋር ያልዎትን ንክክ መከላከል እና
አፋጣኝ አስፈላጊ የህክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጉ ሆኖ ፣በሺታውን ሙሉበሙሉ ማዳን የሚችል ህክምና የለም ፣
መከላከል ብቸኛው ቁልፍ መንገድ ነው !
የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልግዎታል !!
1. እጆችዎን በንፅህና ይታጠቡ፡ በሳሙና እና በንጹህ ውሃ ዘወትር ማጠብ አስፈላጊ ነው።
2. ከሌሎች ሰዎች (ክምችቶች) ራስዎን ይጠብቁ፡ ከሰዎች ደም፣ ምራቅ ወይም ሌሎች ከሰውነት የሚለቀቁ ፈሳሾች ንክኪዎች ራስዎን ይጠብቁ። ይህ ለቤተሰብ አባላት እና በተለይም ለህክምና ባለሙያዎች እጂግ አስፈላጊ ነው።
ብዙ የህክምና/ጤ ና ባለሙያዎች ህይወታቸውን የሚያጡበት ወረርሺኝ ነው።
3. ከእንስሳት ይራቁ፣ አይጦችን እና ሌሎች እንስሳት ከቤትዎ አርቀው ያቆዩ። የሚታወቁ የእንስሳት ክምችቶች ባሉበት ስፍራ ጥንቃቄ አይለይዎት
4.ከ ነፍሳት ይጠበቁ ፣ አጎበር መጠቀም፡
ይህን በሽታ ለመግታት እና ለመቆጣጠር መከላከያ መንገዶቹ ላይ ማተኮሩ ይመከራል።
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ከክ/ከተማው የፌደራል ፍትሕ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በወንጀል መከላከል የሕብረተሰቡ ተሳትፎ እና በአካል ጉዳተኞች፣ በሴቶችና በወጣቶች መብቶች ዙርያ ከሲቪክ ማሕበራት ለተወጣጡ የክ/ከተማው ነዋሪዎች ስልጠና ሰጠ!
በስልጠናው ተሳታፊዎች ለፍትሕ አካላት መረጃ በመስጠትና በሌሎች መንገዶች የፍትሕ ሥርዓቱን ማገዝ እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች እና ወጣቶች መብቶች ከዐለም አቀፍ፣ አህጉራዊና አገራዊ ሕጎች አንጻር በሕግ ስርጸትና ምክር አቃቤ ሕጎች በሰፊው ተዳሠዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች የተዳሰሱ ጉዳዮችን አስፈላጊነት የሚያጎሉ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በተለይም መጤና ባሕል በራዥ ሆነው በሴቶችና በተማሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከፍትሕ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት መከላከል የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።

Forwarded from Tibebu S.
⚖በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል አይነቶች⚖
*
❖#በመርህ_ደረጃ_ወንጀል የመንግስትን እና የህዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ክስ የሚመሰረተው በመንግስት ዐቃቤ ህግ ነው። ሆኖም አንዳንድ የወንጀል አይነቶች በግል ተበዳይ እና በከሳሽ መካከል በሚደረግ እርቅ እንዲያልቁ ሕጉ ይፈቅዳል። በእርቅ ማለቁ ለሁለቱም ወገኖች ጊዜን፣ ወጪንና ጉልበትን ከመቆጠብ ባሻገር በህብረተሰቡ ውስጥ ሰላማዊ የሆነ ማህበራዊ መስተጋብር ትስስርን ያጎለብታል ።
❖#በወንጀል_ጉዳዮች_ላይ_እርቅ_የሚፈቀደው በአንጻራዊነት ክብደታቸው ዝቅተኛ በሆኑ እና በግለሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ነው። እነዚህ ወንጀሎች በመንግስት ወይም በህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት የማያስከትሉ በመሆኑ ጉዳዩ በግል ስምምነት እንዲያልቅ ይፈቀዳል።
❖#የግል_አቤቱታን_መሰረት_ሲያደርግ: አንዳንድ የወንጀል አይነቶች የሚመሰረቱት በተበዳዩ አካል የግል አቤቱታ ላይ ብቻ ነው። አቤቱታው ከተነሳ በኋላም ቢሆን ተበዳዩ እርቅ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ ክሱ ሊቋረጥ ይችላል።
@በእርቅ ማለቅ የሚችሉበት የወንጀል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው ።እነሱም
1. የእጅ እልፊት (አንቀጽ-560(1) ፣
2. የዛቻ ወንጀል (አንቀጽ-580) ፣
3. ታስቦ የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ 556(1)፣
4. በቸልተኝነት የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ-559(3))፣
5. አመንዝራነት (አንቀጽ-652) ፣
6. ስድብና እና ማዋረድ (አንቀጽ-615) ፣
7. የስም ማጥፋት ወንጀል (አንቀጽ-618) ፣
8. በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈጸመ ንብረት ነክ ወንጀል (አንቀጽ-664)
9. ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም(አንቀጽ-646)፣
10. ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት(አንቀጽ-558)፣
11. በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መጠቀም(አንቀጽ-678)፣
12. አግኝቶ መደበቅ(አንቀጽ-679)፣
13. በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ(አንቀጽ-686)፣
14. በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
(አንቀጽ-689)…ወዘተ ናቸው ።
በወንጀል ጉዳዮች ላይ እርቅ የሚፈፀምበት ሂደት#በጠቅላይ_ዐቃቤ_ህግ_መመሪያ_ቁጥር 22/2010 ጉዳዩ እንዴትእንደሚመራ፣ ተበዳዩ ምን መብቶች እንዳሉት እና እርቅ ሲደረግ ምን አይነት ጥንቃቄዎች መወሰድ እንዳለባት በዝርዝር ተቀምጧል::

#ፍቺ_እና_ንብረት_ክፍፍል |የሰበር ችሎት አስገዳጅ መርሆች
=====================================
በኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ውስጥ ንብረት ሲከፋፈል የሚተገበሩ ዋና መርሆዎች እነሆ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጣቸው እነዚህ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜዎች ንብረትዎ የግል ወይስ የጋራ መሆኑን ይወስናሉ!
I. የጋራ እና የግል ሀብት መለያ
1. ቅድመ ጋብቻ ንብረት:- የግል ነው!
በውርስ ወይም በስጦታ በግል ያገኛችሁት ንብረት ሁልጊዜ የግል ነው። (የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57)
2. የካሳ ንብረት:- በልማት ምክንያት በመንግስት የተሰጠ የካሳ ቤት ወይም ገንዘብ፣ ለተሰጠው ተጋቢ የግል ንብረት ሆኖ ይቆያል — የጋራ ውል ከሌለ። (ሰ/መ/ቁ 252723)
II. ከግል ወደ ጋራነት የሚደረግ ለውጥ
1. ዓቢይ መሻሻል (Major Improvement):- በውርስ የተገኘ ቤት ቢሆንም እንኳ፣ በቤቱ ላይ ከነባር ቤቱ ዋጋ እጥፍ በላይ የሆነ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው ተብሎ ሊወሰን ይችላል። (ሰ/መ/ቁ 241998
2. አክሲዮን ዕድገት (Stock Growth):- ከጋብቻ በፊት የተገዛ የአክሲዮን ድርሻ በትዳር ውስጥ ያሳየው የዋጋ ዕድገት ወይም ትርፍ የጋራ ሀብት ነው። (ሰ/መ/ቁ 251014)
III. የሕግ ግምት እና የማስረዳት ሸክም
1. በአንዱ ስም መመዝገብ (Registration): በትዳር ውስጥ በግብይት የተገኘ ንብረት በአንዱ ስም ቢመዘገብም፣ የግል ንብረትነቱን የማረጋገጥ ሸክም ያለበት ንብረቱ የግል ነው የሚለው ተጋቢ ነው። (ሰ/መ/ቁ 239542)
2. የትዳር ገንዘብ አጠቃቀም :- ገንዘብ የትዳር ጊዜ ውጤት መሆኑ ከተረጋገጠ፣ "ለጋራ ጥቅም አልዋለም" የሚል ወገን ነው ማስረጃ አቅርቦ ሊያረጋግጥ የሚገባው። (ሰ/መ/ቁ 239911 እና 242630)
3. ተለያይቶ መኖር (Separation):- ጋብቻው በሕጋዊ ሥርዓት እስካልፈረሰ ድረስ፣ ተጋቢዎች ተለያይተው ቢኖሩም በዚያ ጊዜ የተፈራ ንብረት የጋራ ንብረት ነው በሚለው ግምት ውስጥ ይጠቃለላል። (ሰ/መ/ቁ 252442)
IV. የክፍፍል መርሆዎች እና እኩልነት 50/50
1/ክፍፍል በዓይነት (In Kind) ቀዳሚ ነው!
ፍርድ ቤቶች ንብረቱ በዓይነት ሊከፋፈል የሚችልበትን ሁኔታ ሳያጣሩ በቀጥታ እንዲሸጥ መወሰን የሕጉን መርህ ይጥሳል። (ሰ/መ/ቁ 242840)
2. የግንባታ ክፍፍል (Improvements) :- በጋራ የተሰሩ ግንባታዎች ክፍፍል ሲደረግ፣ የስር ፍርድ ቤቶች የግንባታውን ግምት ብቻ እንዲወስዱ መወሰን የሕገ መንግሥቱን የእኩልነት መርህ የጣሰ ነው። ንብረቱ ይዞታውን ጨምሮ በእኩል ይካፈላል። (ሰ/መ/ቁ 247067)
3. ፕሮቪደንት ፈንድ እና አክሲዮን (Provident Fund & Stocks):- በትዳር ጊዜ ከተጋቢዎች ገቢ ላይ የሚጠራቀመው ፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የአክሲዮን ድርሻ የጋራ ሀብት ተደርጎ በዓይነት እኩል መከፋፈል አለበት። (ሰ/መ/ቁ 243551 እና 190650)
4. የጋራ ንብረት ላይ መኖር:- አንድ የጋራ ባለሀብት በጋራ ንብረት ላይ በመኖሩ ብቻ ለሌላኛው የቤት ኪራይ እንዲከፍል አይገደድም። (ሰ/መ/ቁ 212598)
V. የጋብቻ ውል፣ ኑዛዜና ይርጋ
1. የጋብቻ ውል መጽደቂያ (Validation):- ከጋብቻ በኋላ የሚደረግ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ወይም ውል ማሻሻያ ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት (Sene) መመዝገቡ ብቻውን አይበቃም። በመደበኛ ፍርድ ቤት መጽደቅ አለበት። (ሰ/መ/ቁ 240810)
3. ስጦታ ይርጋ :- ባል ወይም ሚስት ያለ ሌላኛው ፈቃድ የጋራ ንብረት በስጦታ ሲሰጥ፣ ይህን ውል የመሻር የይርጋ ጊዜ (Statute of Limitations) የቤተሰብ ሕጉ ሁለት ዓመት ሳይሆን፣ የፍትሐብሔር ሕግ የተመለከተው የአስር ዓመት ጊዜ ነው። (ሰ/መ/ቁ 247605)
ምንጭ:- Aberham Yohanes

❤1
📅 የዓለም የአካል ጉዳተኞች ቀን፡- (ሕዳር 24/2018)
📢 መሪ ቃል፡- "አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማኅበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማኅበራዊ እድገት!"
መሪ ቃሉ የሚያስተላልፈው መልዕክት፡-
ይህ መሪ ቃል የሚያተኩረው ሁለንተናዊ ተደራሽነት ለሁሉም የልማት ዘርፎች እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በማስገንዘብ ላይ ነው።
1. የተሻለ እድገት፡- አካል ጉዳተኞችን የሚያካትት ማኅበረሰብ የሰው ኃይሉን ሙሉ አቅም እንዲጠቀም ያስችለዋል። ይህም በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በማኅበራዊ ፈጠራ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
2. የመሰናክሎች መወገድ፡- አካታችነት ማለት የአካል፣ የቴክኖሎጂ፣ የመረጃ እና የአመለካከት መሰናክሎችን ማስወገድ ማለት ሲሆን፣ ማንም ሰው ወደ ኋላ አለመቅረቱን ማረጋገጥ ነው።
3. የሁሉንም ጥቅም ማረጋገጥ፡- አካታች ሥርዓቶች ለአካል ጉዳተኞች ብቻ ሳይሆን ለጊዜያዊ ጉዳተኞች፣ ለአረጋውያንና ለሕጻናትም ጭምር ጠቃሚ ናቸው። ስለዚህ አካታች ማኅበረሰብ መገንባት የሁሉንም ዜጋ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል።
መልዕክታችን፡- "አካል ጉዳተኝነት የችሎታ ማነስ አይደለም፤ ነገር ግን ማኅበራዊ መሰናክል ነው።" አካታች የሆነች ኢትዮጵያን በጋራ በመገንባት፣ ለተሻለ ማኅበራዊ እድገት ድርሻችንን እንወጣ!
#IDPD2025 #የአካልጉዳተኞችቀን #ሁለንተናዊተደራሽነት #ማካተት #ማኅበራዊእድገት