የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ከክ/ከተማው የፌደራል ፍትሕ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በወንጀል መከላከል የሕብረተሰቡ ተሳትፎ እና በአካል ጉዳተኞች፣ በሴቶችና በወጣቶች መብቶች ዙርያ ከሲቪክ ማሕበራት ለተወጣጡ የክ/ከተማው ነዋሪዎች ስልጠና ሰጠ!
በስልጠናው ተሳታፊዎች ለፍትሕ አካላት መረጃ በመስጠትና በሌሎች መንገዶች የፍትሕ ሥርዓቱን ማገዝ እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን የሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞች እና ወጣቶች መብቶች ከዐለም አቀፍ፣ አህጉራዊና አገራዊ ሕጎች አንጻር በሕግ ስርጸትና ምክር አቃቤ ሕጎች በሰፊው ተዳሠዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች የተዳሰሱ ጉዳዮችን አስፈላጊነት የሚያጎሉ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በተለይም መጤና ባሕል በራዥ ሆነው በሴቶችና በተማሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከፍትሕ አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት መከላከል የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።
Forwarded from Tibebu S.
⚖በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ የወንጀል  አይነቶች⚖
*
❖#በመርህ_ደረጃ_ወንጀል የመንግስትን እና የህዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ክስ የሚመሰረተው በመንግስት ዐቃቤ ህግ ነው። ሆኖም አንዳንድ የወንጀል አይነቶች በግል ተበዳይ እና በከሳሽ መካከል በሚደረግ እርቅ እንዲያልቁ ሕጉ ይፈቅዳል። በእርቅ ማለቁ   ለሁለቱም ወገኖች ጊዜን፣ ወጪንና ጉልበትን ከመቆጠብ ባሻገር በህብረተሰቡ  ውስጥ ሰላማዊ  የሆነ ማህበራዊ መስተጋብር ትስስርን  ያጎለብታል ።

❖#በወንጀል_ጉዳዮች_ላይ_እርቅ_የሚፈቀደው በአንጻራዊነት ክብደታቸው ዝቅተኛ በሆኑ እና በግለሰቦች መካከል በሚፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ነው። እነዚህ ወንጀሎች በመንግስት ወይም በህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት የማያስከትሉ በመሆኑ ጉዳዩ በግል ስምምነት እንዲያልቅ ይፈቀዳል።

❖#የግል_አቤቱታን_መሰረት_ሲያደርግ: አንዳንድ የወንጀል አይነቶች የሚመሰረቱት በተበዳዩ አካል የግል አቤቱታ ላይ ብቻ ነው። አቤቱታው ከተነሳ በኋላም ቢሆን ተበዳዩ እርቅ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ ክሱ ሊቋረጥ ይችላል።

@በእርቅ ማለቅ የሚችሉበት  የወንጀል አይነቶች የሚከተሉት ናቸው ።እነሱም 

1. የእጅ እልፊት (አንቀጽ-560(1) ፣
2. የዛቻ ወንጀል (አንቀጽ-580) ፣
3. ታስቦ የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ 556(1)፣
4. በቸልተኝነት የሚፈጸም ቀላል የአካል ጉዳት (አንቀጽ-559(3))፣
5. አመንዝራነት (አንቀጽ-652) ፣
6. ስድብና እና ማዋረድ (አንቀጽ-615) ፣
7. የስም ማጥፋት ወንጀል (አንቀጽ-618) ፣
8. በቤተዘመድ ንብረት ላይ የተፈጸመ ንብረት ነክ ወንጀል (አንቀጽ-664)
9. ጋብቻን በተንኮል ወይም በማታለል መፈፀም(አንቀጽ-646)፣
10. ቀለብ የመስጠት ግዴታን ያለመወጣት(አንቀጽ-558)፣
11. በሌላ ሰው ሀብት ያለአግባብ መጠቀም(አንቀጽ-678)፣
12. አግኝቶ መደበቅ(አንቀጽ-679)፣
13. በሰው ንብረት ላይ ሁከት ማድረግ(አንቀጽ-686)፣
14. በሌላ ሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ
(አንቀጽ-689)…ወዘተ ናቸው ።

በወንጀል ጉዳዮች ላይ እርቅ የሚፈፀምበት ሂደት#በጠቅላይ_ዐቃቤ_ህግ_መመሪያ_ቁጥር 22/2010 ጉዳዩ እንዴትእንደሚመራ፣ ተበዳዩ ምን መብቶች እንዳሉት እና እርቅ ሲደረግ ምን አይነት ጥንቃቄዎች መወሰድ እንዳለባት በዝርዝር ተቀምጧል::
#ፍቺ_እና_ንብረት_ክፍፍል |የሰበር ችሎት አስገዳጅ መርሆች

=====================================
​በኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ውስጥ ንብረት ሲከፋፈል የሚተገበሩ ዋና መርሆዎች እነሆ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጣቸው እነዚህ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜዎች ንብረትዎ የግል ወይስ የጋራ መሆኑን ይወስናሉ!

​I. የጋራ እና የግል ሀብት መለያ

1. ቅድመ ጋብቻ ንብረት:- የግል ነው!
በውርስ ወይም በስጦታ በግል ያገኛችሁት ንብረት ሁልጊዜ የግል ነው። (የፌዴራል ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57)

2. የካሳ ንብረት:- ​በልማት ምክንያት በመንግስት የተሰጠ የካሳ ቤት ወይም ገንዘብ፣ ለተሰጠው ተጋቢ የግል ንብረት ሆኖ ይቆያል — የጋራ ውል ከሌለ። (ሰ/መ/ቁ 252723)

​II. ከግል ወደ ጋራነት የሚደረግ ለውጥ

1. ዓቢይ መሻሻል (Major Improvement):- በውርስ የተገኘ ቤት ቢሆንም እንኳ፣ በቤቱ ላይ ከነባር ቤቱ ዋጋ እጥፍ በላይ የሆነ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገ ቤቱ የጋራ ንብረት ነው ተብሎ ሊወሰን ይችላል። (ሰ/መ/ቁ 241998

2. አክሲዮን ዕድገት (Stock Growth):- ​ከጋብቻ በፊት የተገዛ የአክሲዮን ድርሻ በትዳር ውስጥ ያሳየው የዋጋ ዕድገት ወይም ትርፍ የጋራ ሀብት ነው። (ሰ/መ/ቁ 251014)

​III. የሕግ ግምት እና የማስረዳት ሸክም

​1. በአንዱ ስም መመዝገብ (Registration): በትዳር ውስጥ በግብይት የተገኘ ንብረት በአንዱ ስም ቢመዘገብም፣ የግል ንብረትነቱን የማረጋገጥ ሸክም ያለበት ንብረቱ የግል ነው የሚለው ተጋቢ ነው። (ሰ/መ/ቁ 239542)

2. የትዳር ገንዘብ አጠቃቀም :- ገንዘብ የትዳር ጊዜ ውጤት መሆኑ ከተረጋገጠ፣ "ለጋራ ጥቅም አልዋለም" የሚል ወገን ነው ማስረጃ አቅርቦ ሊያረጋግጥ የሚገባው። (ሰ/መ/ቁ 239911 እና 242630)

3. ተለያይቶ መኖር (Separation):- ጋብቻው በሕጋዊ ሥርዓት እስካልፈረሰ ድረስ፣ ተጋቢዎች ተለያይተው ቢኖሩም በዚያ ጊዜ የተፈራ ንብረት የጋራ ንብረት ነው በሚለው ግምት ውስጥ ይጠቃለላል። (ሰ/መ/ቁ 252442)

​IV. የክፍፍል መርሆዎች እና እኩልነት 50/50

​1/ክፍፍል በዓይነት (In Kind) ቀዳሚ ነው!
​ፍርድ ቤቶች ንብረቱ በዓይነት ሊከፋፈል የሚችልበትን ሁኔታ ሳያጣሩ በቀጥታ እንዲሸጥ መወሰን የሕጉን መርህ ይጥሳል። (ሰ/መ/ቁ 242840)

2. የግንባታ ክፍፍል (Improvements) :- በጋራ የተሰሩ ግንባታዎች ክፍፍል ሲደረግ፣ የስር ፍርድ ቤቶች የግንባታውን ግምት ብቻ እንዲወስዱ መወሰን የሕገ መንግሥቱን የእኩልነት መርህ የጣሰ ነው። ንብረቱ ይዞታውን ጨምሮ በእኩል ይካፈላል። (ሰ/መ/ቁ 247067)

​3. ፕሮቪደንት ፈንድ እና አክሲዮን (Provident Fund & Stocks):- ​በትዳር ጊዜ ከተጋቢዎች ገቢ ላይ የሚጠራቀመው ፕሮቪደንት ፈንድ ወይም የአክሲዮን ድርሻ የጋራ ሀብት ተደርጎ በዓይነት እኩል መከፋፈል አለበት። (ሰ/መ/ቁ 243551 እና 190650)

​4. የጋራ ንብረት ላይ መኖር:- አንድ የጋራ ባለሀብት በጋራ ንብረት ላይ በመኖሩ ብቻ ለሌላኛው የቤት ኪራይ እንዲከፍል አይገደድም። (ሰ/መ/ቁ 212598)

​V. የጋብቻ ውል፣ ኑዛዜና ይርጋ

1. የጋብቻ ውል መጽደቂያ (Validation):- ​ከጋብቻ በኋላ የሚደረግ የንብረት ክፍፍል ስምምነት ወይም ውል ማሻሻያ ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት (Sene) መመዝገቡ ብቻውን አይበቃም። በመደበኛ ፍርድ ቤት መጽደቅ አለበት። (ሰ/መ/ቁ 240810)

​3. ስጦታ ይርጋ :- ባል ወይም ሚስት ያለ ሌላኛው ፈቃድ የጋራ ንብረት በስጦታ ሲሰጥ፣ ይህን ውል የመሻር የይርጋ ጊዜ (Statute of Limitations) የቤተሰብ ሕጉ ሁለት ዓመት ሳይሆን፣ የፍትሐብሔር ሕግ የተመለከተው የአስር ዓመት ጊዜ ነው። (ሰ/መ/ቁ 247605)

ምንጭ:- Aberham Yohanes
❤1
📅 የዓለም የአካል ጉዳተኞች ቀን፡- (ሕዳር 24/2018)
📢 መሪ ቃል፡- "አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማኅበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማኅበራዊ እድገት!"
መሪ ቃሉ የሚያስተላልፈው መልዕክት፡-
ይህ መሪ ቃል የሚያተኩረው ሁለንተናዊ ተደራሽነት ለሁሉም የልማት ዘርፎች እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በማስገንዘብ ላይ ነው።
1. የተሻለ እድገት፡- አካል ጉዳተኞችን የሚያካትት ማኅበረሰብ የሰው ኃይሉን ሙሉ አቅም እንዲጠቀም ያስችለዋል። ይህም በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በማኅበራዊ ፈጠራ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
2. የመሰናክሎች መወገድ፡- አካታችነት ማለት የአካል፣ የቴክኖሎጂ፣ የመረጃ እና የአመለካከት መሰናክሎችን ማስወገድ ማለት ሲሆን፣ ማንም ሰው ወደ ኋላ አለመቅረቱን ማረጋገጥ ነው።
3. የሁሉንም ጥቅም ማረጋገጥ፡- አካታች ሥርዓቶች ለአካል ጉዳተኞች ብቻ ሳይሆን ለጊዜያዊ ጉዳተኞች፣ ለአረጋውያንና ለሕጻናትም ጭምር ጠቃሚ ናቸው። ስለዚህ አካታች ማኅበረሰብ መገንባት የሁሉንም ዜጋ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል።
መልዕክታችን፡- "አካል ጉዳተኝነት የችሎታ ማነስ አይደለም፤ ነገር ግን ማኅበራዊ መሰናክል ነው።" አካታች የሆነች ኢትዮጵያን በጋራ በመገንባት፣ ለተሻለ ማኅበራዊ እድገት ድርሻችንን እንወጣ!

#IDPD2025 #የአካልጉዳተኞችቀን #ሁለንተናዊተደራሽነት #ማካተት #ማኅበራዊእድገት
❤2
ሰብዓዊ መብቶች፡ የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ፍላጎቶቻችን!
ዛሬ ታህሳስ 1 (Dec 10, 2025) ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ቀን ነው። ዘንድሮ ቀኑን የምናከብረው "Our Everyday Essentials" (የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ፍላጎቶቻችን) በሚል መሪ ቃል ነው።
በዚህ እርግጠኝነት በጎደለውና ሁለንተናዊ ቀውስ ባለበት ዓለም ውስጥ ሰብዓዊ መብቶች የሰው ልጅ ሁሉ ድል የሚያደርግበት አስተማማኝ መሣሪያ መሆናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል። ሰብዓዊ መብቶች ምናባዊ ሃሳቦች ሳይሆኑ በየቀኑ በሕይወታችን ውስጥ የምንጠቀማቸው መሠረታዊ ነገሮች ናቸው።
ሰብዓዊ መብቶች፦
• አዎንታዊ ናቸው (Positive)፦ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ደስታን፣ ደህንነትንና ነፃነትን ያመጣሉ። በምንናገረው ቃል፣ በምንመገበው ምግብና በምናገኛቸው ዕድሎች ውስጥ ሁሉ አሉ።
• መሠረታዊ ናቸው (Essential)፦ የዘር፣ የጾታ፣ የሃይማኖትና የማንነት ልዩነት ሳይገድባቸው ሁላችንንም የሚያስተሳስሩ የጋራ እሴቶቻችን ናቸው። ዓለም ስትናወጥ ሰላማችንንና የመሳተፍ መብታችንን የሚያረጋግጡልን ምሰሶዎች ናቸው።
• ተደራሽ ናቸው (Attainable)፦ እነዚህ መብቶች የሚጀምሩት በእኛ ነው። በምናደርጋቸው ትንንሽ ምርጫዎች፣ ለሌሎች በሚኖረን አክብሮትና ለፍትሕ በምናደርገው የጋራ ትግል እውን ይሆናሉ።
እነዚህ መሠረታዊ መብቶች በየቀኑ እንዲከበሩና ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ እንዲሆኑ የበኩላችንን እንወጣ! ፍትሕ የሁላችንም የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ፍላጎት ናት!
"ሰብዓዊ መብቶች ለዕለት ተዕለት ሕልውናችን!"
መልካም የሰብዓዊ መብቶች ቀን!
#HumanRightsDay2025 #OurEverydayEssentials #HumanRightsForAll #ፍትሕ #ሰብዓዊመብቶች
❤1
እባክዎ ጥቂት ደቂቃ ወስደው ይህን ቅጽ በመሙላት በቀጣይ የምንሰጣቸውን ሥልጠናዎች ጥራት እንድናሻሽል ይርዱን!
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
https://forms.gle/KwNMsQ6YBzjTcSfV9
እባክዎ ጥቂት ደቂቃ ወስደው ይህን ቅጽ በመሙላት በቀጣይ የምንሰጣቸውን ሥልጠናዎች ጥራት እንድናሻሽል ይርዱን!
ስለየኢትዮጵያ የሕንፃ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 ምን ያህል ያውቃሉ?
አዋጁ እጅግ ሰፊና ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ ሲሆን፣ በተለይ በግንባታ ጥራት፣ በአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት እና በባለሙያዎች ተጠያቂነት ላይ ትኩረት ያደርጋል።
አዋጁን በወፍ በረር ለመቃኘት እንዲመቸን፣ ዋና ዋና ነጥቦቹን በሚከተለው መልኩ ከፍለን አቅርበንላችኋል፡
1. የሕንፃዎች ምደባ (Building Categories)
አዋጁ ሕንፃዎችን በውስብስብነታቸውና በከፍታቸው በ4 ዋና ምድቦች ይከፍላቸዋል፦
• ምድብ 'ሀ'፦ ባለ አንድ ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃዎች (ከ7 ሜትር ያልበለጠ ርቀት ያላቸው)።
• ምድብ 'ለ'፦ ከ2 እስከ 4 ፎቅ ያላቸው የግል ወይም የጋራ መኖሪያዎች።
• ምድብ 'ሐ'፦ ከ5 እስከ 12 ፎቅ ያላቸው ሕንፃዎች።
• ምድብ 'መ'፦ ከ12 ፎቅ በላይ የሆኑ፣ ማንኛውም የሕዝብ መገልገያ፣ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች።
2. የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት (Accessibility)
ይህ አዋጅ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት ይሰጣል።
• ማንኛውም የሕዝብ መገልገያ ሕንፃ "ሁሉን አቀፍ ንድፍ" (Universal Design) መከተል አለበት።
• ነባር ሕንፃዎች እንኳ ሳይቀሩ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ያስገድዳል።
3. የፈቃድና የቁጥጥር ሥርዓት
• የሕንፃ ሹም፦ ግንባታዎችን የሚቆጣጠርና ፈቃድ የሚሰጥ ባለሙያ መመደብን ይደነግጋል።
• የመጠቀሚያ ፈቃድ (Occupancy Permit)፦ በተለይ ለምድብ 'መ' ሕንፃዎች ግንባታው ሲጠናቀቅ ደህንነቱ ተረጋግጦ የመጠቀሚያ ፈቃድ ማግኘት ግዴታ ነው።
• የዲዛይን ዋስትና፦ ከፍተኛ የሕንፃ ዲዛይን ባለሙያዎችና ተቋራጮች ለሚሰሩት ሥራ የኢንሹራንስ ወይም የገንዘብ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶች
አዋጁ ጥብቅ የሆኑ ቅጣቶችን ያስቀምጣል፦
• ያለ ፈቃድ መገንባት ወይም ከዲዛይን ውጭ መሥራት ተጠያቂነትን ያስከትላል።
• ለባለሙያዎች፦ በቸልተኝነት ወይም ሆን ብሎ መረጃ በመደበቅ ጥፋት ለሚያጠፉ ባለሙያዎችና የሕንፃ ሹሞች እስከ 10 እና 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና ከፍተኛ የገንዘብ መቀጮ ተደንግጓል።
• ለአሰሪዎች፦ ደረጃውን ያልጠበቀ ቁሳቁስ መጠቀም ወይም ያለ መጠቀሚያ ፈቃድ ሕንፃውን አገልግሎት ላይ ማዋል ያስቀጣል።
በቀጣይ በአዋጁ ክፍሎች ላይ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ይዘን እንመለሳለን!
👍1
እባክዎ ጥቂት ደቂቃ ወስደው ይህን ቅጽ በመሙላት በቀጣይ የምንሰጣቸውን ሥልጠናዎች ጥራት እንድናሻሽል ይርዱን!
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
https://forms.gle/KwNMsQ6YBzjTcSfV9
እባክዎ ጥቂት ደቂቃ ወስደው ይህን ቅጽ በመሙላት በቀጣይ የምንሰጣቸውን ሥልጠናዎች ጥራት እንድናሻሽል ይርዱን!
የገንዘብ ሚኒስቴር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የግብር ጫና ለመቀነስ በማሰብ፣ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተሞች ዋጋቸው ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች የሆኑ ንብረቶች ከንብረት ግብር ነጻ እንዲሆኑ ወሰነ።

ገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለክልል እና ለከተማ አስተዳደሮች ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት፣ ከግብር ነጻ የሆነው የንብረት ዋጋ ጣሪያ እንደ ከተሞቹ ደረጃ ይለያያል፡-

• በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ - ከአንድ ሚሊዮን ብር በታች፣
• በሌሎች ማዘጋጃ ቤት ባላቸው ከተሞች - ከ250,000 ብር በታች፣ እንዲሁም
• በታዳጊ ከተሞች ከ100,000 ብር በታች ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ግብር አይከፍሉም።

"ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች" ተብለው የተለዩት፣ በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ እንዳሉ በአካባቢው የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊዎች የተረጋገጠላቸው እና ዓመታዊ ገቢያቸው ከሀገራዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ግማሽ  በታች የሆኑ ናቸው።

በፓርላማ የጸደቀውን አዋጅ መሰረት በማድረግ በሚዘጋጀው የክልሎች ህግ፤ ለግብር ስሌት የሚወሰደው የንብረት ዋጋ፣ የንብረቱ ትክክለኛ የገበያ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ብቻ ይሆናል። የግብር መጠኑም (Tax rate) ከ0.1 በመቶ እስከ 10 በመቶ ባለው ክልል ውስጥ የሚወሰን ይሆናል።

በተጨማሪም የሃይማኖት ተቋማት መገልገያዎች፣ የመቃብር ስፍራዎች፣ የህዝብ መንገዶች፣ ፓርኮች፣ ቅርሶች እና ለህዝብ ነጻ የማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ንብረቶች ከዚህ ግብር ነጻ መደረጋቸው በመመሪያው ተካቷል።
=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ይዞታዎች ታክስ እንዲከፈልባቸው የሚያስገድድ ሕግ ተዘጋጀ
የተመዘገበ የባለቤትነት መብት በሌለበት ጊዜ ማንኛውም ታክስ የሚከፈልበትን ንብረት ይዘው የሚገኙና በይዞታው ጥቅም የሚያገኙ፣ የይዞታ ማረጋገጫ ባይኖራቸውም፣ የንብረት ታክስ የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው የሚደነግግ አስገዳጅ ሞዴል ንብረት ታክስ አዋጅ ረቂቅ ተዘጋጀ፡፡
አገራዊ ወጥነት ያለው የንብረት ታክስ መሠረት፣ የታክስ ምጣኔና ታክስ የሚከፈልባቸው ንብረቶች እንዲኖሩ ለማስቻል የሚረዳ የአፈጻጸም ሕግ ክልሎች ሊያወጡ እንደሚገባና ለዚህ መነሻ የሚሆን ሞዴል የንብረት ታክስ ሕግ የፌዴራል መንግሥት ማዘጋጀት ስላለበት፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ከገቢዎችና ከተማና መሠረተ ልማት  ሚኒስቴር ጋር ረቂቁን አዘጋጅቶ ይፋ አድርጓል፡፡
ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተላከው ሞዴል የንብረት ታክስ ሕጉ በሊዝ ይዞታ ስሪት በሚተዳደር ማንኛውም የከተማ ቦታ የመጠቀሚያ መብት፣ ከሊዝ ይዞታ ስሪት ውጪ በሆነ ነባር የቦታ የመጠቀሚያ መብትና ቦታ ላይ በተደረገ ማሻሻያ ወይም በሕንፃ ባለቤትነት ላይ የሚጣልና የሚሰበሰብ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሕጉ መሠረት ታክስ የመክፈል ግዴታ የተጣለበት ማንኛውም ሰው፣ በታክስ ከፋዩ ስም የታክስ ጉዳዮችን እንዲያስፈጽም ውክልና የተሰጠው የታክስ ከፋዩ ተወካይ፣ የሟች የውርስ ንብረትን በሚመለከት ሥልጣን ያለው አስፈጻሚ ወይም አስተዳዳሪ፣ ዕዳ ያለበትን ንብረት በሚመለከት ሥልጣን ያለው ባላደራ፣ ሕንፃውን ወይም ማሻሻያውን የሚያሠራውና የሚቆጣጠረው ኩባንያ፣ የሪል ስቴት የባለቤትነት መብት እስኪያስተላልፍ ወይም የተጠናቀቀውን ሕንፃ ለገዥው በአካል እስኪያስረክብ ድረስ የያዘውን የሚያካትት ይሆናል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የተመዘገበ የባለቤትነት መብት በሌለበት ጊዜ፣ ማንኛውም ታክስ የሚከፈልበትን ንብረት ይዞ የሚገኝ ሰው ወይም በይዞታው ጥቅም እያገኘ ያለ ሰው፣ የይዞታ ማረጋገጫ ባይኖረውም፣ የንብረት ታክስ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት  ተደንግጓል፡፡
ሆኖም የተመዘገበ የባለቤትነት መብት በሌለበት ጊዜ ታክሱን እንዲከፍል መደረጉ ብቻውን በንብረት የመጠቀም ወይም ባለቤትነት መብትን እንደማያስገኝና በሌሎች ሕጎች የሚወሰዱ ዕርምጃዎች እንደማያስቀር፣ በተጨማሪም ንብረቱ በጋራ ባለቤትነት ወይም ይዞታ የተያዘ እንደሆነ ሁሉም የጋራ ባለቤቶች ወይም የጋራ ባለይዞታዎች ለንብረት ታክስ በጋራና በተናጠል ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስፍሯል፡፡
ከታክስ ነፃ የመሆን ወይም ዕፎይታ የማግኘት መብቶች እንደተጠበቁ ሆነው፣ከአንድ ንብረት የገበያ ዋጋ ውስጥ ታክስ የሚከፈልበት የንብረቱ የገበያ ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ መሆኑንና የመሬት አስተዳደር አካሉ በከተሞች፣ በቦታ መጠቀሚያ፣ በሕንፃዎችና በማሻሻያዎች ምድብ፣ ተፈጻሚነት ባለው የግመታ ዘዴና የዋጋ ግሽበት ማሻሻያዎችን መሠረት ያደረገ ወቅታዊ ማሻሻያ ማድረግ እንዳለበት ተገልጿል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በሚያወጣቸው ደረጃዎችና መመርያዎች፣ እንዲሁም የክልሉን የከተሞች ሕግ መሠረት በማድረግ የከተሞች ፈርጅ ምደባና ንዑስ ምደባን እንደሚወስን ተመላክቷል፡፡
የንብረት ታክስ ምጣኔው በመጀመሪያው ዓመት በዝቅተኛ ታክስ ምጣኔ ተጀምሮ በአራት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ጣሪያ ላይ መድረስ በሚያስችል አዳጊ ሒደት ሥራ ላይ እንዲውል እንደሚደረግ፣ የከተማ አስተዳደሮች የታክስ ምጣኔውን በሚያሻሽሉበት ጊዜ የከተማውን ዓመታዊ የካፒታል ወጪ ፍላጎትና የሁሉም ንብረቶች ታክስ የሚከፈልበት ዓመታዊ ዋጋን ከግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡
ዓመታዊ የታክስ ምጣኔው በሚሻሻልበት ጊዜ ከንብረት ጋር ከተያያዙ ገቢዎች በስተቀር፣ ከልዩ ልዩ ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች፣ ከክልሉ መንግሥት የሚገኙ ድጎማዎች፣ የውጭ ዕርዳታና ከሌሎች ምንጮች ከተሞች የሚያገኟቸው ገቢዎች ታሳቢ አይደረጉም ተብሏል፡፡
ዓመታዊ የንብረት ታክስ ምጣኔ ሰንጠረዥ የማፅደቅና የማሻሻል ሥልጣን የተሰጠው ለከተማው ምክር ቤት ሲሆን፣ ምክር ቤት በሌለበት ጊዜ አግባብነት ባለው የክልል ከተማ ሕግ መሠረት ተመሳሳይ ሥልጣን የተሰጠው አካል የማፅደቅና የማሻሻል ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
በከተማ ቦታ መጠቀሚያ መብት ላይ የሚጣለው ታክስ ምጣኔ ታክስ የሚከፈልበት ዋጋ ላይ ከ0.2 በመቶ በታችና ከአንድ በመቶ በማይበልጥ ሁኔታ ተግባራዊ እንደሚደረግ፣ ከተሞች አግባብነት ያላቸውን ሕጎች መሠረት በማድረግ በባዶ ቦታ ላይ ከፍተኛውን የታክስ ተመን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ሰፍሯል፡፡
በሕንፃ ወይም የቦታ ማሻሻያ ላይ የሚጣለው ታክስ ምጣኔ፣ ታክስ የሚከፈልበት ዋጋ ላይ ከ0.1 በመቶ በታችና ከአንድ በመቶ የማይበልጥ መሆኑን፣ ከተሞች ተጠናቀው ጥቅም ላይ ያልዋሉ ሕንፃዎችና የቦታ ማሻሻያዎች ላይ ከፍተኛውን ታክስ ምጣኔ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡
የንብረቱ ጥቅል ዋጋ በከተማ አስተዳደሮች ከአንድ ሚሊዮን ብር፣ በማዘጋጃ ቤት ከተሞች ከሁለት መቶ ሃምሳ ሺሕ ብርና በታዳጊ ከተሞች ከአንድ መቶ ሺሕ ብር ያነሰ፣ ዝቅተኛ ገቢ ላለው አንድ ቤተሰብ በመኖሪያነት የሚያገለግል የከተማ ቦታ፣ ሕንፃና የቦታ ማሻሻያ ከንብረት ታክስ ነፃ ተደርጓል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት ለአምልኮ ተግባርና ለመካነ መቃብር አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች፣ በከተማ ክልል ያሉና ለአንድ ቤተሰብ ፍጆታ ለሚውል የግብርና ሥራ የሚያገለግልና ለኅብረተሰቡ ነፃ የማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች አገልግሎቱን ለመስጠት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች ከታክስ ነፃ ናቸው ተብሏል፡፡
Ethiopian Reporter - ሪፖርተር
እባክዎ ጥቂት ደቂቃ ወስደው ይህን ቅጽ በመሙላት በቀጣይ የምንሰጣቸውን ሥልጠናዎች ጥራት እንድናሻሽል ይርዱን!