የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
📢 አሰሪና ሰራተኛ: የሙከራ ጊዜ (Probation Period) ዋና ዋና የሰበር ችሎት ውሳኔዎች !
አሠሪዎችና ሠራተኞች ትኩረት! በኢትዮጵያ የሠራተኛ ሕግ የሙከራ ጊዜን በተመለከተ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት የተሰጡ ቁልፍ የሕግ ትርጓሜዎችን ለሁሉም በሚያቀል መልኩ አቅርበናል። መብቶቻችሁንና ግዴታዎቻችሁን እወቁ!
1. የሙከራ ጊዜ ቆይታ እና ስንብት የሚፈቀድበት ጊዜ
•  ⏱️ ከፍተኛው የጊዜ ገደብ:
o  በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት 45 ተከታታይ ቀናት።
o  በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት 60 ተከታታይ ቀናት መብለጥ የለበትም። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 125899, 230567)
•  🗓 የጊዜ አቆጣጠር: የሙከራ ጊዜው ሲጠናቀቅ በቀጣዩ ቀን የስንብት ደብዳቤ መጻፍ የሕጉን መንፈስ አይቃረንም። (የሰበር መ/ቁ. 101890)
•  🤝 በውል የተስማሙበት ጊዜ: ግራ ቀኙ ለምሳሌ ለ"ሁለት ወር" ከተስማሙ፣ ፍርድ ቤት "የሥራ ቀናት" ብቻ ናቸው ብሎ አይተረጉምም፤ ከተጀመረበት ቀን አንስቶ ሁለት ወር ሲያልቅ፣ የሙከራ ጊዜውም ያበቃል። (የሰበር መ/ቁ. 250942)
•  ቀጣይነት: የሙከራ ጊዜው አልቆ ሰራተኛው ስራውን ከቀጠለ፣ ውሉ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ ይቆጠራል። (የሰበር መ/ቁ. 174501)
2. የሙከራ ጊዜ መስፈርቶች
•  📝 የጽሑፍ ውል አስፈላጊነት: የሙከራ ጊዜ ውል ተደርጓል ለማለት በጽሑፍ የተደረገ ውል መቅረብ ግድ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 215599, 225852, 238244)
•  ✅ የስምምነት ማረጋገጫ: ሰራተኛው የሙከራ ጊዜን የሚያመለክት ደብዳቤ መፈረሙ ብቻ በውሉ ላይ ግልጽ ስምምነት ማግኘቱን አያረጋግጥም። አሠሪው በግልጽ አውቆና ተገንዝቦ በፅሑፍ ያሰፈሩት ስምምነት መኖሩን ማረጋገጥ አለበት። (የሰበር መ/ቁ. 140781, 98052)
•  ⚖️ የማስረዳት ሸክም: ሰራተኛውን በሙከራ ጊዜ እንደቀጠረ የሚያቀርበው አሠሪው የማስረዳት ግዴታ አለበት። (የሰበር መ/ቁ. 194058)
3. በሙከራ ጊዜ የሥራ ውል ስለማቋረጥ
•  🧐 የመገምገም ግዴታ: አሠሪው ሰራተኛውን ማሰናበት የሚችለው የሥራ አፈጻጸሙን ገምግሞ ለሥራው ተስማሚ አለመሆኑን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 247252)
•  🚫 ሕገወጥ ስንብት (ያለ ምዘና): ሰራተኛው ገና ስራውን ሳይጀምር ወይም ሳይሰራ/ሳይገመገም በዘፈቀደ ማሰናበት ሕገ-ወጥ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 247252)
•  🔀 "ተስማሚ አለመሆን": "ለሥራው ተስማሚ አለመሆን" የሚለው ሐረግ የሥራ አፈጻጸምን ብቻ ሳይሆን በሥነ ምግባር ረገድ ለሥራ ተስማሚ መሆን አለመሆኑን ጭምር ይመለከታል። (የሰበር መ/ቁ. 170126)
•  💰 ያለመክፈል መብት: ሰራተኛው ብቁ አለመሆኑ ሲረጋገጥ፣ አሠሪው ያለማስጠንቀቂያ፣ የስራ ስንብት ክፍያና ካሳ ሳይከፍል ውሉን ሊያቋርጥ ይችላል። (የሰበር መ/ቁ. 125899)
4. በሕገ ወጥ መንገድ ለተሰናበተ የሙከራ ጊዜ ሠራተኛ የሚሰጥ ካሣ
•  💸 የካሳ መጠን: በሕገ-ወጥ መንገድ ለተሰናበተ የሙከራ ጊዜ ሠራተኛ የሚከፈለው ካሳ ከፍተኛው የሙከራ ጊዜ ጣሪያ (60 ቀን) ድረስ ቢሰራ ኖሮ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝ (ወይም የቀሩት የሙከራ ጊዜ ደመወዝ) ብቻ ይሆናል። (የሰበር መ/ቁ. 212420, 247252)
•  ❌ እገዳ: የሙከራ ጊዜ ሰራተኛ የአገልግሎት ዘመንን ታሳቢ ተደርጎ የሚሰላ የስንብትና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች አይከፈለውም። (የሰበር መ/ቁ. 247252)
5. የሙከራ ጊዜ መጠናቀቅ ህጋዊ ውጤት
•  የቋሚነት ጥያቄ: የሙከራ ጊዜያቸውን የጨረሱ ሰራተኞች "ቋሚ ሰራተኛ እንሁን" የሚለው ጥያቄ የክስ ምክንያት የሌለው (የሕግ መሰረት የሌለው) ነው። (የሰበር መ/ቁ. 236244)
•  🔄 ተደጋሚ ቅጥር: ሰራተኛን ቀድሞ ይሰሩበት ለነበረው ስራ ለሙከራ መቀጠር በሕጉ ያልተፈቀደ ነው። (የሰበር መ/ቁ. 164135)
👍1👏1
Forwarded from fasika aggena
አዲስ አበባ ለአደጋ ስጋት ምላሽ የሚውል "የአደጋ ጊዜ ፈንድ" አቋቋመች
የከተማው ነዋሪ፣ የመንግሥት ሠራተኞችና የንግዱ ማኅበረሰብ ለፈንዱ ገቢ ያደርጋሉ
ጥር 2018 ዐ/ም
(የቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ውስጥ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያቶች የሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን በዘላቂነት ለመመከትና ተጎጂዎችን በአፋጣኝ መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል "የአደጋ ጊዜ ፈንድ" በደንብ ቁጥር 191/2017 አቋቁሟል። ይህ አዲስ ደንብ በተለይም በክፍል 3 እና 4 ላይ ፈንዱ የሚሰበሰብበትን፣ የሚተዳደርበትን እና ተጎጂዎች የሚለዩበትን ጥብቅ ሥርዓት ዘርግቷል።
የፈንዱ ምንጭ እና የገቢ አሰባሰብ (ክፍል 3)
ፈንዱ በከተማው አስተዳደር ስም በሚከፈት ልዩ የባንክ ሂሳብ የሚቀመጥ ሲሆን፣ የአደጋ ጊዜ የሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የመልሶ ግንባታ እና የዘላቂ ማቋቋም ሥራዎችን ለማከናወን የሚውል ነው። ደንቡ የገቢ ምንጮቹን በዝርዝር አስቀምጧል፦
• ከመንግሥት ሠራተኞችና ተሿሚዎች፦ በየወሩ ከተጣራ ደመወዛቸው 0.5% (ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ)።
• ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች፦ ከሥራ ማስኪያጃ በጀታቸው 1% እና 2%።
• ከንግዱ ማኅበረሰብ፦ እንደ ንግድ ደረጃቸው (ሀ፣ ለ፣ ሐ) በየወሩ ከ50 እስከ 200 ብር።
• ከከተማው ነዋሪ፦ በዓመት 60 ብር (በወር 5 ብር) ከውኃ ቢል ጋር ተጨምሮ የሚሰበሰብ።
• ከሃይማኖት ተቋማትና ሲቪክ ማኅበራት፦ እንደቅደም ተከተላቸው፣ በየዓመቱ 12,000 እና 5,000 ብር።
• ከንብረት ሽያጭ፦ በቋሚ ንብረት ግዥና ሽያጭ ወቅት ከሽያጭ ዋጋው ላይ 0.1%።
ፈንዱ "ተዘዋዋሪ" (Revolving) በመሆኑ፣ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋለ ገንዘብ ወደ ከተማው ማዕከላዊ ካዝና ሳይመለስ ለቀጣዩ ዓመት የአደጋ ዝግጁነት ሥራ እንዲውል ይደረጋል።
የመዋጮው ሕጋዊ መሠረት፦ ከሠራተኛው ፈቃድ ባሻገር
"ይህ መዋጮ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው?" ለሚለው ጥያቄ ደንቡና የአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ግልጽ ምላሽ ይሰጣሉ። በአዋጅ ቁጥር 87/2017 አንቀጽ 11(2) መሠረት፣ የሠራተኛ ደመወዝ ሊቆረጥ የሚችልባቸው ሦስት ምክንያቶች ተቀምጠዋል። እነርሱም፡- የሠራተኛው የጽሑፍ ስምምነት፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና "በሕግ በተደነገገው መሠረት" የሚሉ ናቸው።
በመሆኑም በደንብ ቁጥር 191/2017 የተደነገገው ይህ ፈንድ "በሕግ የተደነገገ" በመሆኑ፣ ከመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሚደረገው የ0.5% ቅናሽ ያለ ሠራተኛው የግል ፈቃድ የሚፈጸም የዜግነት ግዴታ ነው። ይሁን እንጂ፣ ማንኛውም ቅነሳ ከሠራተኛው ወርሃዊ ደመወዝ አንድ ሦስተኛ (1/3) መብለጥ እንደሌለበት አዋጁ በገደብ አስቀምጧል።
ተጎጂዎችን የመለየትና የመርዳት ሂደት (ክፍል 4)
ደንቡ ድጋፍ የሚገባቸውን ተጎጂዎች የመለየት ሂደትን ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት አድርጎታል። "የአደጋ ተጎጂ" ተብሎ የተተረጎመው በተፈጥሮ ወይም በሰው ሠራሽ አደጋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም "ሰው" (ግለሰብ ወይም ተቋም) ነው።
• አደጋው ምን መምሰል አለበት?፦ ድጋፍ ለማግኘት አደጋው የግድ "የማኅበረሰብ አደጋ" መሆን የለበትም። ይልቁንም በግለሰብ ወይም በቤተሰብ ደረጃ የደረሰና ተጎጂው በገዛ አቅሙ ሊቋቋመው የማይችል (ከአቅም በላይ) መሆኑ ሲረጋገጥ ዕርዳታ ይፈቀዳል።
• የመረጃ ትክክለኛነት፦ የተጎጂዎች ዝርዝር በወረዳ ተመዝግቦ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ተተችቶና ተረጋግጦ በደብዳቤ ለኮሚሽኑ መላክ አለበት።
• ዲጂታል መረጃ፦ ሁሉም መረጃዎች በሶፍት ኮፒ ተደራጅተው በ"ዳታ ቤዝ" እንዲያዙ ይደረጋል።
• የተጎጂዎች ግዴታ፦ ተጎጂዎች ትክክለኛ መረጃ የመስጠት፣ ዕርዳታ ሲቀበሉ በፊርማ የማረጋገጥና የተሰጠውን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ የማዋል ግዴታ አለባቸው።
የድጋፍ ዓይነቶች
ደንቡ አደጋን ተከትሎ የሚሰጡ ድጋፎችን በሦስት ከፍሏቸዋል፦
1. የዕለት ደራሽ፦ መሰረታዊ ምግብ፣ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁስና የሥነ-ልቦና ማረጋጊያ ድጋፍ።
2. የመልሶ ግንባታ፦ የወደመ ንብረትን መተካት፣ የቤት ጥገና፣ የትምህርትና የሕክምና ወጪዎችን መሸፈን።
3. ዘላቂ ማቋቋም፦ የቤት ኪራይ ድጋፍ (ቤት እስኪገነባ)፣ የሥራ ዕድልና የሥራ መሥሪያ ካፒታል እንዲሁም ለሞት የቀብር ማስፈጸሚያና የቤተሰብ መጽናኛ ድጋፍ።
ይህ ደንብ ከመጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ሲሆን፣ ፈንዱን ለግል ጥቅሙ የሚያውል ወይም አፈጻጸሙን የሚያሰናክል ማንኛውም አካል በወንጀልና በፍትሐብሔር ሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን ደንቡ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።
በመንግስት መ/ቤቶች ውስጥ አንድ ስራተኛ በውክልና ምን ያህል ጊዜ መቆየት ይችላል?

✅ የውክልና ጊዜ መጠን

🔹 1️⃣ መደበኛ የውክልና ጊዜ

👉 እስከ 6 ወር (ስድስት ወር)

* የስራ መደብ ባዶ ሲሆን

* ዋናው ሰራተኛ በፍቃድ፣ በስልጠና፣ በህመም ወይም በሌላ ምክንያት ሲጠፋ

🔹 2️⃣ በልዩ ሁኔታ (በማራዘም)

👉 እስከ 12 ወር (1 ዓመት) ብቻ

በግልፅ ምክንያት ለምሳሌ፦

* በከፍተኛ አመራር / የሰው ኃብት ፈቃድ

* የቋሚ ሹመት ሂደት እየተካሄደ ከሆነ

* ከ1 ዓመት በላይ በውክልና ማቆየት ህጋዊ አይደለም።

⚖️ አስፈላጊ ህጋዊ መርሆዎች፡

ውክልና ፦ ጊዜያዊ ነው፣ ቋሚ መብት አይጠይቅም፡፡

ረጅም ጊዜ በውክልና ማቆየት፦

👉 የሰራተኛ መብት ጥሰት ሊሆን ይችላል

ሰራተኛው በውክልና ላይ እያለ፦

👉 የውክልና ደመወዝ/አበል ሊከፈለው ይገባል (ካለ)

📝 በተግባር ምን ማድረግ ይቻላል?

ከ6–12 ወር በላይ ካቆዩት

* የማብራሪያ ጥያቄ ካልተፈታ

* የአስተዳደር ቅሬታ ማቅረብ ካልተፈታ

* እስከ ፍ/ቤት ድረስ መውሰድ ይቻላል።
አዩዘሀበሻ
======================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
❤1👏1
የመንግስት ዓቃቢያነ ሕግ እና የፍትህ መዛባት፦ ሊታረሙ የሚገባቸው 7 ስር የሰደዱ ችግሮች! ⚖️⚠️

የመንግስት መብትና ጥቅም ለማስከበር ከወረዳ እስከ ክልል የሚገኙ ዓቃቢያነ ሕጎች በትጋት የመከራከር ግዴታ አለባቸው። ነገር ግን፣ በተግባር የሕግ የበላይነትን እና የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጋፉ የሚከተሉት "ጎጂ ልምዶች" በስፋት ይስተዋላሉ፦

1️⃣ "መሸነፍን መፍራት" እና ያለአግባብ መከራከር (Unjustifiable Litigation)
📉 ጉዳዩ በሕግ እንደማያሸንፍ እያወቁ፣ "መንግስት ተሸነፈ" እንዳይባል ብቻ በማሰብ የዜጎችን መብት መርገጥ። ክርክሩ አያዋጣም ብሎ በድፍረት ለበላይ አካል ሪፖርት ከማድረግ ይልቅ፣ ጉዳዩን አላስፈላጊ ይግባኝ በማለት ማራዘም ተገቢ አይደለም።

2️⃣ ተጠያቂነትን ወደ ጎን መተው
👤 አንድ የመንግስት መሥሪያ ቤት ለክስ እንዲዳረግ እና ካሳ እንዲከፍል ያደረገው ግለሰብ/ባለሥልጣን ማን ነው? ተብሎ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ዓቃቤ ሕጉ ግፊት አያደርግም። ይህ ባለሥልጣናት በፈለጉት ጊዜ ሕግ እንዲጥሱ በር ከፋች ሆኗል።

3️⃣ ትክክለኛ ፍትህን ሳይሆን "ውጤትን" ብቻ ማሳደድ
🏆 ዓቃቤ ሕግ የፍትህ አካል እንጂ የግል ጠበቃ አይደለም። ግቡ ፍትህ እንዲሰፍን ማድረግ መሆን ሲገባው፣ መዝገቡ በሽንፈት እንዳይመዘገብ ብቻ በማሰብ የሕግ ክፍተቶችን ተጠቅሞ ፍትህን ማድበስበስ ይታያል።

4️⃣ የሕግ ምክር የመስጠት ክፍተት (Legal Advice Gap)
💡 ተቋማት ስህተት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ዓቃቤ ሕግ ትክክለኛ የሕግ ምክር በመስጠት መከላከል ሲገባው፣ ስህተቱ ተፈጥሮ ክስ ከተመሰረተ በኋላ ብቻ ለመከራከር መሮጥ። ይህ ለሀገር ሀብት ብክነት ትልቅ ምክንያት ነው።

5️⃣ በአፈፃፀም ወቅት "የውኃ ሽታ" መሆን
🏃‍♂️💨 በመንግስት መሥሪያ ቤት ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሲሰጥ፣ ዓቃቤ ሕግ እስከ መጨረሻው ይግባኝ ይከራከራል። ነገር ግን መሥሪያ ቤቱ እንዲፈጽም ሲታዘዝ፣ ዓቃቤ ሕጉ ለሕግ የበላይነት ሲባል መሥሪያ ቤቱ እንዲፈጽም ግፊት ከማድረግ ይልቅ ችሎት ላይ አለመገኘት እና ግዴታውን መዘንጋት።

6️⃣ የሙያ ነፃነት ማጣት (Lack of Independence)
⛓️ አንዳንድ ዓቃቢያነ ሕጎች ከሕግ ይልቅ የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ የሚሰጣቸውን "የፖለቲካ ትዕዛዝ" በማስቀደም የሕግ ባለሙያነታቸውን ይዘነጋሉ። ይህም ሕዝቡ በፍትህ ስርአቱ ላይ እምነት እንዳይኖረው ያደርጋል።

7️⃣ የጥቅም ግጭት እና ሙስና
💰 በአንዳንድ አካባቢዎች ከመንግስት ይልቅ ከተከሳሽ ወገን ጋር በጥቅም በመመሳጠር የመንግስትን መብትና ጥቅም አሳልፎ መስጠት ወይም ደካማ ክርክር ማድረግ ይስተዋላል።

መፍትሔው ምንድን ነው?
✅ ዓቃቤ ሕግ የሕግ የበላይነት ጠባቂ መሆኑን መረዳት።
✅ በመንግስት መሥሪያ ቤት ውስጥ ጥፋት የሚያጠፉ ኃላፊዎች በሪግሬሽን (Recourse action) እንዲጠየቁ ማድረግ።
✅ ዓቃቢያነ ሕጎች በሙያቸው ብቻ የሚመሩበትን ነፃነት ማረጋገጥ።

እናንተስ በየአካባቢያችሁ ባሉ የመንግስት ዓቃቢያነ ሕጎች ላይ ምን ትታዘባላችሁ? ፍትህ እየተሰጠ ነው ወይስ ክርክር ለክርክር? 👇

https://t.me/Shields_Law
❤2👍1
የትራንስፖርት ታሪፍ ይፋ ሆኗል‼️
በ #አዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ‼️
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ሰኞ መጋቢት 7/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ጭማሪው የከተማ አውቶብስ አገልግሎትን ጨምሮ በሚኒባስ፣ በሚዲባስና የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ያካትታል ተብሏል።
ታሪፉ "ነባር" እና "አዲሱ" ተብሎ የተቀመጠው እንደሚከተለው ነው፦

1. የሚኒባስ ታክሲ ታሪፍ

* እስከ 2.5 ኪ.ሜ ፦ ነባር 10 ብር --- አዲሱ 10.00 ብር

* ከ 2.6 እስከ 5 ኪ.ሜ ፦ ነባር 15 ብር --- አዲሱ 20.00 ብር

* ከ 5.1 እስከ 7.5 ኪ.ሜ ፦ ነባር 20 ብር --- አዲሱ 25.00 ብር

* ከ 7.6 እስከ 10 ኪ.ሜ ፦ ነባር 25 ብር --- አዲሱ 35.00 ብር

* ከ 10.1 እስከ 12.5 ኪ.ሜ ፦ ነባር 30 ብር --- አዲሱ 40.00 ብር

* ከ 12.6 እስከ 15 ኪ.ሜ ፦ ነባር 35 ብር --- አዲሱ 45.00 ብር

* ከ 15.1 እስከ 17.5 ኪ.ሜ ፦ ነባር 40 ብር --- አዲሱ 50.00 ብር

* ከ 17.6 እስከ 20 ኪ.ሜ ፦ ነባር 45 ብር --- አዲሱ 55.00 ብር

2. የሚዲ-ባስ (ሀይገርና ቅጥቅጥ) ታሪፍ

* እስከ 8 ኪ.ሜ ፦ ነባር 10 ብር --- አዲሱ 15.00 ብር

* ከ 8.01 እስከ 12 ኪ.ሜ ፦ ነባር 15 ብር --- አዲሱ 20.00 ብር

* ከ 12.01 እስከ 16 ኪ.ሜ ፦ ነባር 20 ብር --- አዲሱ 30.00 ብር

* ከ 16.01 እስከ 20 ኪ.ሜ ፦ ነባር 25 ብር --- አዲሱ 35.00 ብር

* ከ 20.01 እስከ 24 ኪ.ሜ ፦ ነባር 30 ብር --- አዲሱ 40.00 ብር

* ከ 24.01 እስከ 28 ኪ.ሜ ፦ ነባር 35 ብር --- አዲሱ 45.00 ብር

3. የከተማ አውቶቡስ ታሪፍ

* እስከ 7.5 ኪ.ሜ ፦ አዲሱ 10.00 ብር

* ከ 7.6 እስከ 12 ኪ.ሜ ፦ ነባር 10 ብር --- አዲሱ 15.00 ብር

* ከ 12.01 እስከ 17 ኪ.ሜ ፦ ነባር 20 ብር --- አዲሱ 25.00 ብር

* ከ 17.1 እስከ 23 ኪ.ሜ ፦ ነባር 20 ብር --- አዲሱ 30.00 ብር

* ከ 23.01 እስከ 30 ኪ.ሜ ፦ ነባር 30 ብር --- አዲሱ 40.00 ብር

* ከ 30.01 እስከ 45 ኪ.ሜ ፦ ነባር 40 ብር --- አዲሱ 60.00 ብር

* ከ 40.01 እስከ 50 ኪ.ሜ ፦ ነባር 50 ብር --- አዲሱ 70.00 ብር ሆኗል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!
***
የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ በእድሜ (60 ዓመት ሲሞላ) ሲሆን በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ  ሠራተኛው የጡረታ ምዝገባ ማድረግ እንዳለበት ተደንግጓል

1. የምዝገባ ሂደት

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ከተቀጠረ በ60 ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ ምዝገባ ማድረግ አለበት።

2. የጡረታ መዋጮ

● ለሲቪል ሰራተኞች: ከሰራተኛው 7%፣ ከመንግስት 11% ሲሆን፣ በድምሩ 18% ይሆናል።

● ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት: ከሰራተኛው 7%፣ ከመንግስት 25% ሲሆን፣ በድምሩ 32% ነው።

3. ለጡረታ የሚያበቁ ምክንያቶች

● በእድሜ ምክንያት (60 ዓመት ሲሞላ)
● በራስ ፍቃድ
● በጤና ጉድለት
● በስራ ላይ በደረሰ የአካል ጉዳት
● በሞት

4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች

● በእርጅና
● በህመም
● ወደ ውጭ አገር በመሄድ
● በትምህርት ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ
● በእስራት ምክንያት

5. የጡረታ አበል በይርጋ የሚዘጋበት ጊዜ

● የጡረታ ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነ የጡረታ አበል ሳይወሰድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ፣ አይከፈልም። ነገር ግን፣ ከዚያ በኋላ ጥያቄ ካቀረበ፣ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ክፍያው ይቀጥላል።

○ የሟች ጡረታ (ዳራጎት) ሳይጠየቅ ወይም ለ3 ዓመት ሳይወሰድ ከቆየ፣ በይርጋ ይዘጋል።

6. በእድሜ ምክንያት ለሚወጣ ሰራተኛ የጡረታ ስሌት

● የጡረታ አበል የሚሰላው በመጨረሻዎቹ 36 ወራት (3 ዓመት) አማካይ ደመወዝ ላይ ተመስርቶ ነው።

● ከመጀመሪያው የቅጥር ቀን እስከ 10 ዓመት ያለው አገልግሎት በ30% ይባዛል።

● ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት በ1.25% ይባዛል።

○ ለምሳሌ: 28 ዓመት ያገለገለ ሰራተኛ ስሌት፡-

● (10 ዓመት × 30%) + (18 ዓመት × 1.25%) = 30% + 22.5% = 52.5%

● የመጨረሻ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ 5,000 ብር ከሆነ፣ የጡረታ አበሉ 52.5% × 5,000 ብር = 2,625 ብር ይሆናል።

7. የቅጥር ቀንና ወር ሲታጣ
የቅጥር ዘመን ብቻ በህይወት ታሪክ ከተሞላ፣ የጡረታ ቀንና ወር በሚከተለው መልኩ ይያዛል፡-

● በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ይወሰዳል።

● በግሪጎሪያን (እ.ኤ.አ) አቆጣጠር ከሆነ ታህሳስ 31 ተብሎ ይወሰዳል።

8. በራስ ፈቃድ ጡረታ መውጣት

● አንድ ሰራተኛ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን እና የ25 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ሲኖረው በራሱ ፍላጎት ጡረታ መውጣት ይችላል።

● ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት ግን ጡረታ ከሚወጡበት እድሜ 5 ዓመት ቀድመው መውጣት ይችላሉ።

9. የሟች ጡረታ ወራሾች

● የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ወይም የአካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ ከ21 ዓመት በታች መሆን አለባቸው።

● የሟች እናትና አባትም ወራሾች ይሆናሉ።

10. ለጡረታ አበል ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

● የህይወት ታሪክ ቅጽ (ጡ1 እና ጡ2)
● የሙከራ እና የቋሚ ቅጥር ደብዳቤዎች
● የጡረታ መለያ ቁጥር
● የ36 ወራት ደመወዝ መረጃ
● የዝውውር፣ የደረጃ እድገት እና የደመወዝ ለውጥ ደብዳቤዎች
● የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
● የባለጡረታው ወይም የወራሽ ፎቶግራፍ!
👍1
Forwarded from AMAS Advocates LLP (Masresha@Amas Advocates)
የመኪና ሽያጭ ውል በፅሁፍ መደረጉ ብቻ በቂ ነዉ ወይስ ዉሉ ስልጣን ባለዉ አካል መመዝገብ አለበት??
**
የመኪና ሽያጭ ውል በፅሁፍ ተደርጎ ገዥ መኪናዉን በእጁ አድርጎ መያዙ ብቻ የመኪናዉ ህጋዊ ባለቤት አያደርገውም። መኪና ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሆኑ ባለቤትነት ከአንድ ወደ ሌላ ሰዉ ተላልፏል ሊባል የሚችልበት ሁኔታ በህግ በተለይ የተመለከተ እንደሆነ፣ ንብረቱ ተላልፏል ሊባል የሚችለዉ ስለጉዳዩ በሚደነግገዉ ህግ በተመለከተዉ መሠረት መሆኑ ሲረጋገጥ መሆኑን ነዉ።
በዚህ ጉዳይ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 681/2002 አንቀጽ 4 የተሽከርካሪ ባለንብረት የባለንብረት መታወቂያ (ሉብሬ) መያዝ ግዳታ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም ተሽከርካሪን አስመልክቶ በተደረገ ዉል የተሽከርካሪዉ ባለንብረትነት ከሻጩ ወደ ገዥዉ ተላልፏል ወይም ገዥ በዉሉ መሠረት ተረክቧል ማለት የሚቻለዉ ከላይ በተጠቀሰዉ አዋጅ አንቀጽ 6 እና 7 ላይ በተዘረጋዉ ስርዓት መሠረት ገዥዉ መኪናዉን በስሙ ሲያዝመዘግበዉ ነዉ ።
❤1
ስለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምን ያህል ያውቃሉ? እስኪ ስለኮሚሽኑ እነዚህን ጠቃሚ ነጥቦች እናጋራችሁ!
1/ የኮሚሽኑ መቋቋም እና ተጠሪነት
• መቋቋም፦ ኮሚሽኑ የከተማው አስተዳደር መሥሪያ ቤት ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 75/2014 ተቋቁሟል።
• ተጠሪነት፦ የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለከተማው ምክር ቤት ነው።
• ነፃነት፦ ኮሚሽኑ ተግባሩን ሲያከናውን ከማንኛውም ሰው ወይም አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ ነው።
2/ የኮሚሽኑ አቋምና አመራር
• መዋቅር፦ ኮሚሽኑ በከንቲባው አቅራቢነት በምክር ቤት የሚሾሙ ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነሮች እንዲሁም አስፈላጊ የሥራ ክፍሎችና ሠራተኞች ይኖሩታል።
• የሥራ ዘመን፦ የኮሚሽነሩና የምክትል ኮሚሽነሩ የሥራ ዘመን 6 ዓመት ሲሆን፣ ለተጨማሪ አንድ የሥራ ዘመን ብቻ ድጋሚ ሊሾሙ ይችላሉ።
• ከኃላፊነት መነሳት፦ ከፈቃዳቸው ውጭ ከሥራ የሚነሱት በሥነ-ምግባር ጉድለት፣ በችሎታ ማነስ፣ በጤና ችግር ወይም ለጡረታ ሲበቁ ብቻ ሲሆን፣ ይህም በምክር ቤት ተጣርቶ በአብላጫ ድምፅ መፅደቅ አለበት።
3/ የኮሚሽኑ ዓላማዎች
1. ሙስናን የማይታገስ የነቃ ኅብረተሰብ መፍጠር።
2. የሙስና ወንጀልንና ብልሹ አሠራርን መከላከል።
3. ነዋሪው የፀረ-ሙስና ትግል ባለቤት እንዲሆን ማድረግ።
4. ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ማስፈን።
5. ተቋማዊ አቅምን መገንባት።
4/ ዋና ዋና ሥልጣንና ተግባራት
• ፖሊሲና ስትራቴጂ፦ ከተማ አቀፍ የፀረ-ሙስና ፖሊሲ ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም ይተገብራል።
• ሥልጠና፦ ተሿሚዎችና ሠራተኞች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የሥነ-ምግባር ሥልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል።
• ጥናትና ማሻሻያ፦ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን በማጥናት የመፍትሔ ሃሳብ ያቀርባል፤ ተግባራዊ ባላደረጉት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ለሕግ አካል ያቀርባል።
• ቅድመ-መከላከል፦ ሙስና ሊፈጸም መሆኑን ሲጠረጥር ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ጣልቃ በመግባት ያስቆማል።
• የሀብት ምዝገባ፦ የተሿሚዎችንና ሠራተኞችን ሀብት ያስመዘግባል፣ ትክክለኛነቱን ያረጋግጣል፣ መረጃውንም ለሕዝብ ተደራሽ ያደርጋል። ለዚህም ሶፍትዌር ያበለጽጋል።
• የጥቅም ግጭት፦ የጥቅም ግጭትን ለመከላከል ሥርዓት ይዘረጋል።
• ዕውቅናና ሽልማት፦ በፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማ የሆኑ አካላትን ያወዳድራል፣ ይሸልማል።
• ክትትል፦ የሥነ-ምግባር ደንቦችን ያዘጋጃል፣ የፀረ-ሙስና ሕጎች መከበራቸውን ያረጋግጣል።
• ሪፖርት መቀበል፦ ከምርመራና ክስ መሥራች አካላት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ይቀበላል።
5/ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች አደረጃጀት
• ኮሚሽኑ በመሥሪያ ቤቶችና በልማት ድርጅቶች ውስጥ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎችን ያደራጃል።
• እነዚህ ክፍሎች ተጠሪነታቸው ለኮሚሽኑ ነው።
• የእነዚህ ክፍሎች ኃላፊዎችንና ሠራተኞችን የመመደብ፣ የመቅጠርና የማሰናበት ሥልጣን የኮሚሽኑ ነው (ከተቋማቱ ማኔጅመንት ጋር በመመካከር)።
6/ ግንኙነትና ሌሎች ጉዳዮች
• የሥራ ግንኙነት፦ ከፌደራል፣ ከክልልና ከድሬዳዋ አስተዳደር ኮሚሽኖች ጋር የቴክኒክ ድጋፍ፣ የዕቅድና የሪፖርት ልውውጥ ያደርጋል።
• ሕጋዊ ሰውነት፦ ኮሚሽኑ የንብረት ባለቤት መሆን፣ ውል መዋዋል፣ መክሰስና መከሰስ ይችላል።
### 📢 አዲስ የወጣ ደንብ፦ የመንግሥት ሠራተኞች የዲሲፕሊን፣ የቅሬታና የይግባኝ አወሳሰን ሥነ-ሥርዓት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን የዲሲፕሊን አፈጻጸምና የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓት ይበልጥ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ቀልጣፋ ለማድረግ ደንብ ቁጥር 201/2018 አውጥቷል።

የደንቡ ዋና ዋና ነጥቦች

#### 1. የዲሲፕሊን ኮሚቴ አደረጃጀትና አሠራር
* ተቋማዊ አደረጃጀት፦ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት የዲሲፕሊን ምርመራ የሚያካሂድ ኮሚቴ እንዲያቋቁም ተደንግጓል።
* የኮሚቴው አባላት፦ ኮሚቴው በበላይ ኃላፊ የሚመደቡና በሠራተኞች የሚመረጡ 5 አባላትን (ጾታን ያገናዘበ) የያዘ ሆኖ፣ አባላቱ በመልካም ሥነ-ምግባራቸው የተመሰገኑ መሆን አለባቸው።
* የቅጣት ዓይነቶች፦ እንደ ጥፋቱ ክብደት ከቃል ማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከ ሥራ ስንብት ድረስ ያሉ የቅጣት እርምጃዎች የሚወሰዱበትን ሥርዓት በግልጽ ያስቀምጣል።

#### 2. የዲሲፕሊን ምርመራና የክስ አቀራረብ
* የተፋጠነና መደበኛ ምርመራ፦ ቀላል ጥፋቶች በተፋጠነ ሁኔታ፣ ከባድ ጥፋቶች ደግሞ በመደበኛ የምርመራ ሥርዓት እንዲታዩ ይደረጋል።
* የተከሳሽ መብት፦ ማንኛውም ክስ የቀረበበት ሠራተኛ ክሱ እንዲደርሰው፣ መቃወሚያና የመከላከያ መልስ እንዲያቀርብ፣ እንዲሁም ምስክሮችን መስቀለኛ ጥያቄ የመጠየቅ ሙሉ መብቱ የተከበረ ነው።
* የጊዜ ገደብ፦ የዲሲፕሊን ምርመራዎች በአንድ ወር (ተጨማሪ ካስፈለገ በሁለት ወር) ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው የውሳኔ ሐሳብ መቅረብ እንዳለባቸው በማስቀመጥ የጉዳዮችን መጓተት ይከላከላል።

#### 3. ግልጸኝነትና ተጠያቂነት
* የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ለሠራተኛው በጽሑፍ መድረስ ያለባቸው ሲሆን፣ ሠራተኛው በማንኛውም አስተዳደራዊ ውሳኔ ላይ ቅሬታ የማቅረብና ለፍርድ ቤት ይግባኝ የመጠየቅ መብቱ በደንቡ ተረጋግጧል።

---
ዓላማው፦ ፍትሐዊ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አሠራርን በመዘርጋት የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን ነው።

📌 ሙሉ ደንቡን ለማንበብና ስለ መብትና ግዴታዎ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ደንብ ቁጥር 201/2018ን ይመልከቱ።

#አዲስአበባ #የመንግሥትሠራተኞች #ሕግ #ዲሲፕሊን #ደንብ201/2017 #ፍትሕ
📢 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች የደህንነት ፍቃድና ቁጥጥር (አዋጅ ቁጥር 1310/2016)

ውድ የቻናላችን ተከታታዮች!
ዛሬ፣ የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅና የዲጂታል መረጃዎችን ስርቆት ለመከላከል የወጣውን አዲስ አዋጅ ልናስተዋውቅ ወድደናል! ዋና ዋና ነጥቦቹን እንደሚከተለው አጠቃልለን አቅርበናል።

🔍 የትኞቹን ውጤቶች (ምርቶች) ይመለከታል?
የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን ለመጥለፍ፣ ለመስረቅ፣ ለማጥፋት ወይም ለማጭበርበር የሚያገለግሉ ማንኛቸውም የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች፣ ዲዛይኖችና አፕሊኬሽኖች ላይ ቁጥጥር ይደረጋል።

🚫 የተከለከሉና ገደብ የተጣለባቸው ውጤቶች
1. የተከለከሉ፦ ለሀገር ደህንነት ስጋት በመሆናቸው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ወይም እንዳይወጡ የተከለከሉ።
2. ገደብ የተጣለባቸው፦ ወደ ሀገር ለማስገባትም ሆነ ለመጠቀም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ልዩ የደህንነት ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው።

✅ የፍቃድ ባለቤቶች ግዴታ
* ፍቃድ ያገኙበትን መሣሪያ ለተፈቀደለት ዓላማ ብቻ መጠቀም።
* መሣሪያው ቢጠፋ፣ ቢሰረቅ ወይም ቢበላሽ በ8 ሰዓት ውስጥ ለአስተዳደሩ (INSA) ማሳወቅ።
* ያለ አስተዳደሩ ፍቃድ መሣሪያውን ለሌላ ሰው አሳልፎ አለመስጠት።

⚖️ ሕገ-ወጥ ድርጊትና ቅጣቱ
* ያለ ፍቃድ የተከለከሉ ወይም ገደብ የተጣለባቸውን መሣሪያዎች ይዞ መገኘት፣ መጠቀም ወይም ማዘዋወር እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራት እና እስከ 100,000 ብር መቀጮ ሊያስቀጣ ይችላል።
* ወንጀሉ በተደራጀ መልኩ የተፈጸመ ከሆነ ቅጣቱ እስከ 10 ዓመት እስራት እና 500,000 ብር ይደርሳል።

ለተጨማሪ መረጃ፦ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ድረ-ገጽን ይጎብኙ።

*ደህንነቱ የተጠበቀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለሀገር ሰላም!*
### 🔍 ስለ ደላሎች ሕጉ ምን ይላል? ⚖️

በኢፌድሪ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 (ምዕራፍ 5) ላይ ስለ ደላሎች የተደነገጉ ወሳኝ ነጥቦችን ለዕውቀትም ሆነ ለጥንቃቄ እንዲረዳ በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፦

#### 📌 1. ደላላ ማነው? (አንቀጽ 54)
ደላላ ማለት ራሱን የቻለ የሙያ ተግባር አድርጎ፣ ውል የሚዋዋሉ ሰዎችን (ለምሳሌ፦ ሽያጭ፣ ኪራይ፣ ኢንሹራንስ፣ ትራንስፖርት) ፈልጎ የሚያገናኝና የሚያዋውል ሰው ወይም የንግድ ማኅበር ነው።
* ልዩ ነጥብ፦ ደላሎች የሚሠሩት የሥራ ዓይነት ወይም የሚያገናኙዋቸው ሰዎች ማንነት ሳይታይ "ነጋዴ" ተብለው ይጠራሉ።

#### ⚠️ 2. ደላላው ምን ማድረግ አይችልም? (አንቀጽ 54/3)
በውሉ ላይ በግልጽ ካልተቀመጠ በስተቀር፣ ደላላው ተዋዋዮቹን ተክቶ፦
* ገንዘብ መቀበል አይችልም።
* ማንኛውንም ውልን ወደ ተግባር የሚያስገባ እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈቀድለትም።

#### 📢 3. የማሳወቅ ግዴታ (አንቀጽ 55)
ደላላው ተዋዋዮቹ በጉዳዩ ላይ መስማማታቸውንና የውሉን ሁኔታዎች ለሁሉም ወገኖች ወዲያውኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት። ባለጉዳዮቹ ውሉን ካላጸደቁት በስተቀር ውሉ ተፈጻሚ አይሆንም።

#### ⚖️ 4. የደላላው ኃላፊነት (አንቀጽ 56)
ደላላው በሥራው ሂደት በሁለቱም ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ማንኛውም ጉዳት በሕግ ተጠያቂ (ኃላፊ) ይሆናል።

#### 💰 5. የደላላ አበል (ኮሚሽን) አከፋፈል (አንቀጽ 57)

* መቼ ይከፈላል? ደላላው ውሉን ካስጨረሰ ወይም ካዋዋለ በኋላ፣ ውሉ ቢፈጸምም ባይፈጸምም አበል የማግኘት መብት አለው።
* ማን ይከፍላል? ሌላ ስምምነት ከሌለ በስተቀር፣ አበሉን የሚከፍለው የደላላውን አገልግሎት የጠየቀው ወገን ብቻ ነው።
* የአበል መጠን፦ በስምምነት ወይም በልማድ ይወሰናል። ሆኖም መጠኑ ከባድ ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤት የመቀነስ ሥልጣን አለው።

#### 🚫 ደላላው አበል የማይከፈለው መቼ ነው? (አንቀጽ 57/4)
ደላላው የሚከተሉትን ጥፋቶች ከፈጸመ አበል የመጠየቅ መብቱን ያጣል፦
1. የደንበኛውን ጥቅም ጎድቶ ለሌላ (ለሦስተኛ) ወገን ጥቅም ከሠራ።
2. ደንበኛው ሳያውቅ ከሌላኛው ወገን ክፍያ ከተቀበለ።

💡 ማጠቃለያ፦ በደላላ በኩል ማንኛውንም ግብይት ሲፈጽሙ መብትና ግዴታዎን በሚገባ ማወቅዎን ያረጋግጡ!
ለተጨማሪ የሕግ መረጃዎች ቻናላችንን ይከታተሉ! 📲
❤1