በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 በሽታ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. በቤት ሆኖ የኮቪድ-19 ህክምና ለማግኘት ፍቃደኛ የሆነ፣
2. ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት፣
3. በቤት ውስጥ የቆይታ ጊዜ አጋዥ ወይም ረዳት ያለው እንዲሁም እራሱን መርዳት የሚችል፣
4. የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማግኘት ወይም ማሟላት የሚችል፣
5. በተመሳሳይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሌላ ሰው የግል ንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ ማሸፈኛ ጭንብሎችን ማግኘት የሚችል እንደሆነ፣
6. ኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ማለትም የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ፣ አስም፣ ኤች አይቪ፣ ቲቢ፣ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ካሉባቸው ሰዎች ጋር አብሮ የማይኖር ከሆነ፣
7. የኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከቤት ላለመውጣት ወይም ማናቸውም ጠያቂ ወደቤት እንዳይመጣ ለማድረግ ማረጋገጫ የሚሰጥ ከሆነ፣
8. እራሱን ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ለይቶ ማቆየት የሚያስችል ክፍል ወይም ከቤተሰብ አባላት በ2 ሜትር ርቀት ላይ መቆየት የሚያስችል ክፍል ያለው እንደሆነ፣
9. በጤና ቡድን በቋሚነት ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
መልካም ቀን
ፌናን

ስለ አካል-ጉዳተኞች መብት በአጭሩ:- ክፍል ሁለት
በአንቀጽ 3/ሀ) በግል ምርጫ የመወሰን ነፃነትና ራስን ችሎ የመኖር መብትን ጨምሮ ለተፈጥሯዊ ክብርና ለግለሰብአዊ ልዕልና ዋጋ የመስጠት ግዴታ ተደንግጓል፡፡
ሌላው በስምምነቱ አንቀጽ 2 (ሐ) የተደነገገው መሰረታዊ መርህ አካል-ጉዳተኝነትን መሰረት ያደረገ መድልዎ አልባነት (non-discrimination based on disability) ነው፡፡ በዚህ ንኡስ አንቀጽ መሰረት “በአካል ጉዳት ላይ የተመሠረተ መድልዎ” ማለት በፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊ፣ ባህላዊ፣ በሲቪል ነክ ወይም በሌላ በማናቸውም መስክ ሰብዓዊ መብቶችንና መሠረታዊ ነፃነቶችን ሁሉ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ደረጃ ከመጠቀም ወይም ተግባራዊ ከማድረግ ወይም ለነዚሁ መብቶችና ነፃነቶች እውቅና ከመስጠት የመገደብ ዓላማ ወይም ይህንኑ ዓይነት ውጤት የሚያስከትል ማናቸውም ልዩነት፣ አግልሎት ወይም ተፅዕኖ ነው፡፡ አድራጎቱ ምክንያታዊ ተቀባይነት ያለው ማስተካከያ አለማቅረብን ወይም ይህንኑ መንፈግን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት የመድልዎ ተግባራት ያካትታል፡፡
አካል ጉዳተኞች በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስኮች የመሰማራት፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ጉዳዮቻቸውን የመቆጣጠር እና የማንቀሳቀስ መብት አላቸው፡፡ በስምምነቱ አንቀጽ 12 (5)፡፡ እንደተመለከተው አካል ጉዳተኞች የንብረት ባለቤት የመሆን፣ ንብረትን የመውረስ፣ ፋይናንስ-ነክ ጉዳዮቻቸውን በገዛ ራሳቸው የመቆጣጠርና የባንክ ብድር፣ የወለድአገድና ሌሎች የዱቤ አገልግሎቶችን የማግኘት እኩል መብትና እድል ያላቸውና ንብረታቸውን በዘፈቀደ የማያጡ ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡
ሌላው መሰረታዊ ነጥብ የተደራሽነት መርህ ሲሆን የቁሳዊ አካባቢን፣ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ ስርአቶችን፣ የመሰረተልማት አውታሮችን እና አገልግሎቶችን ምቹና ቅርብ በሆነ መንገድ ማቅረብን ያካትታል፡፡ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያጋጥሙ የአካላዊ፣ የመረጃና የአገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት በአንቀጽ 9 ስር የተደነገገ ሲሆን ባንኮች የሚሰጡትን የወረቀትና የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አካል-ጉዳትን መሰረት ያደረገ አግላይና አድሏዊ አሰራር እየተገበሩ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ቸር ሰንብቱ!!
ፌናን
08/01/2013 ዓ.ም

ሰላም!
አዲስ የታተሙ የኢትዮጵያ የብር ኖቶች ሥራ ላይ ለማዋል በወጣው መመሪያ ቁጥር ከማዳ/2/2013 አንቀጽ 6(4) መሠረት ከብር 5000 በላይ ገንዘብ የሚለወጠው በደንበኛው ስም በተከፈተ የተቀማጭ ሂሳብ በኩል ብቻ እንደሚሆን ተደንጓል።መመሪያዋን እንድታነቧት ከታች አስቀምጬላችኋለው።
ሰናይ 13/1/2013 ዓ.ም!