📢 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ውጤቶች የደህንነት ፍቃድና ቁጥጥር (አዋጅ ቁጥር 1310/2016)
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች!
ዛሬ፣ የሀገርን ደህንነት ለመጠበቅና የዲጂታል መረጃዎችን ስርቆት ለመከላከል የወጣውን አዲስ አዋጅ ልናስተዋውቅ ወድደናል! ዋና ዋና ነጥቦቹን እንደሚከተለው አጠቃልለን አቅርበናል።
🔍 የትኞቹን ውጤቶች (ምርቶች) ይመለከታል?
የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን ለመጥለፍ፣ ለመስረቅ፣ ለማጥፋት ወይም ለማጭበርበር የሚያገለግሉ ማንኛቸውም የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች፣ ዲዛይኖችና አፕሊኬሽኖች ላይ ቁጥጥር ይደረጋል።
🚫 የተከለከሉና ገደብ የተጣለባቸው ውጤቶች
1. የተከለከሉ፦ ለሀገር ደህንነት ስጋት በመሆናቸው ወደ ሀገር እንዳይገቡ ወይም እንዳይወጡ የተከለከሉ።
2. ገደብ የተጣለባቸው፦ ወደ ሀገር ለማስገባትም ሆነ ለመጠቀም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ልዩ የደህንነት ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው።
✅ የፍቃድ ባለቤቶች ግዴታ
* ፍቃድ ያገኙበትን መሣሪያ ለተፈቀደለት ዓላማ ብቻ መጠቀም።
* መሣሪያው ቢጠፋ፣ ቢሰረቅ ወይም ቢበላሽ በ8 ሰዓት ውስጥ ለአስተዳደሩ (INSA) ማሳወቅ።
* ያለ አስተዳደሩ ፍቃድ መሣሪያውን ለሌላ ሰው አሳልፎ አለመስጠት።
⚖️ ሕገ-ወጥ ድርጊትና ቅጣቱ
* ያለ ፍቃድ የተከለከሉ ወይም ገደብ የተጣለባቸውን መሣሪያዎች ይዞ መገኘት፣ መጠቀም ወይም ማዘዋወር እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራት እና እስከ 100,000 ብር መቀጮ ሊያስቀጣ ይችላል።
* ወንጀሉ በተደራጀ መልኩ የተፈጸመ ከሆነ ቅጣቱ እስከ 10 ዓመት እስራት እና 500,000 ብር ይደርሳል።
ለተጨማሪ መረጃ፦ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ድረ-ገጽን ይጎብኙ።
*ደህንነቱ የተጠበቀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለሀገር ሰላም!*

### 🔍 ስለ ደላሎች ሕጉ ምን ይላል? ⚖️
በኢፌድሪ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 (ምዕራፍ 5) ላይ ስለ ደላሎች የተደነገጉ ወሳኝ ነጥቦችን ለዕውቀትም ሆነ ለጥንቃቄ እንዲረዳ በሚከተለው መልኩ አቅርበነዋል፦
#### 📌 1. ደላላ ማነው? (አንቀጽ 54)
ደላላ ማለት ራሱን የቻለ የሙያ ተግባር አድርጎ፣ ውል የሚዋዋሉ ሰዎችን (ለምሳሌ፦ ሽያጭ፣ ኪራይ፣ ኢንሹራንስ፣ ትራንስፖርት) ፈልጎ የሚያገናኝና የሚያዋውል ሰው ወይም የንግድ ማኅበር ነው።
* ልዩ ነጥብ፦ ደላሎች የሚሠሩት የሥራ ዓይነት ወይም የሚያገናኙዋቸው ሰዎች ማንነት ሳይታይ "ነጋዴ" ተብለው ይጠራሉ።
#### ⚠️ 2. ደላላው ምን ማድረግ አይችልም? (አንቀጽ 54/3)
በውሉ ላይ በግልጽ ካልተቀመጠ በስተቀር፣ ደላላው ተዋዋዮቹን ተክቶ፦
* ገንዘብ መቀበል አይችልም።
* ማንኛውንም ውልን ወደ ተግባር የሚያስገባ እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈቀድለትም።
#### 📢 3. የማሳወቅ ግዴታ (አንቀጽ 55)
ደላላው ተዋዋዮቹ በጉዳዩ ላይ መስማማታቸውንና የውሉን ሁኔታዎች ለሁሉም ወገኖች ወዲያውኑ የማሳወቅ ግዴታ አለበት። ባለጉዳዮቹ ውሉን ካላጸደቁት በስተቀር ውሉ ተፈጻሚ አይሆንም።
#### ⚖️ 4. የደላላው ኃላፊነት (አንቀጽ 56)
ደላላው በሥራው ሂደት በሁለቱም ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ማንኛውም ጉዳት በሕግ ተጠያቂ (ኃላፊ) ይሆናል።
#### 💰 5. የደላላ አበል (ኮሚሽን) አከፋፈል (አንቀጽ 57)
* መቼ ይከፈላል? ደላላው ውሉን ካስጨረሰ ወይም ካዋዋለ በኋላ፣ ውሉ ቢፈጸምም ባይፈጸምም አበል የማግኘት መብት አለው።
* ማን ይከፍላል? ሌላ ስምምነት ከሌለ በስተቀር፣ አበሉን የሚከፍለው የደላላውን አገልግሎት የጠየቀው ወገን ብቻ ነው።
* የአበል መጠን፦ በስምምነት ወይም በልማድ ይወሰናል። ሆኖም መጠኑ ከባድ ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤት የመቀነስ ሥልጣን አለው።
#### 🚫 ደላላው አበል የማይከፈለው መቼ ነው? (አንቀጽ 57/4)
ደላላው የሚከተሉትን ጥፋቶች ከፈጸመ አበል የመጠየቅ መብቱን ያጣል፦
1. የደንበኛውን ጥቅም ጎድቶ ለሌላ (ለሦስተኛ) ወገን ጥቅም ከሠራ።
2. ደንበኛው ሳያውቅ ከሌላኛው ወገን ክፍያ ከተቀበለ።
💡 ማጠቃለያ፦ በደላላ በኩል ማንኛውንም ግብይት ሲፈጽሙ መብትና ግዴታዎን በሚገባ ማወቅዎን ያረጋግጡ!
ለተጨማሪ የሕግ መረጃዎች ቻናላችንን ይከታተሉ! 📲

❤1
አዋጅ ቁጥር 1395/2015 የግብር ማሻሻያ ሕግ ነው። ይህ ሕግ በኢትዮጵያ የግብር ስርዓትን ለማሻሻል ተዘጋጅቷል።”
🎤
“ግብር ማለት ህዝብ ለመንግስት የሚከፍለው ግዴታ ነው። ይህ ገንዘብ ለመንግስት አገልግሎቶች ይጠቅማል።”
🎤 ዓላማ
“የዚህ አዋጅ ዋና ዓላማ ፍትሃዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጥ እና የመንግስት ገቢ ማሻሻል ነው።”
🎤 ዋና ለውጦች
“አዋጁ የግብር ሂደትን ቀላል አድርጓል እና ዲጂታል ስርዓት መጠቀምን አበረታቷል።”
🎤 Slide 5: የግብር አይነቶች
“በዚህ ሕግ ውስጥ የገቢ ግብር፣ የንግድ ግብር እና VAT እንደ ዋና ዋና ግብሮች ይገኛሉ።”
🎤 ግዴታዎች
“ግብር ከፋዮች መመዝገብ፣ ሪፖርት ማቅረብ እና በጊዜ መክፈል ያስፈልጋቸዋል።”
🎤 : መብቶች
“ግብር ከፋዮች መረጃ መጠየቅ፣ ክስ መመስረት እና ፍትሃዊ አገልግሎት መቀበል መብት አላቸው።”
🎤: ቅጣቶች
“ግብር በጊዜ ካልተከፈለ ቅጣት ይኖራል። ሐሰተኛ መረጃ መስጠት ደግሞ ከባድ ቅጣት ያመጣል።”
🎤 : አስፈላጊነት
“ይህ ሕግ የመንግስት ገቢን ያሻሽላል እና የኢኮኖሚ እድገትን ያጠናክራል።”
🎤 መደምደሚያ
“በመጨረሻ፣ አዋጅ 1395/2015 ፍትሃዊ እና ዘመናዊ የግብር ስርዓት ለመፍጠር አስፈላጊ ሕግ ነው። አመሰግናለሁ።”

Forwarded from fasika aggena
📌 በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞች የንቃተ-ሕግ ሥልጠና ተሰጠ
ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦሌ
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽሕፈት ቤት የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት፤ የክፍለ ከተማው አመራሮችና ሠራተኞች ስለ አገራዊ የምርጫ ሥርዓትና ሕግጋት ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ሥልጠና በተሳካ ሁኔታ ሰጠ!
በሥልጠናው ላይ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የሥነ-ምግባር ሕግጋት ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተዳስሰዋል፦
✅ የምርጫ መርሆችና አፈጻጸም፦ ስለ መራጮችና እጩዎች ምዝገባ፣ ስለ ምርጫ ጣቢያዎች አደረጃጀትና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት፤
✅ የሥነ-ምግባር መርሆች፦ የምርጫ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት፣ የተከለከሉ ተግባራትና የሥነ-ምግባር ጥሰቶች ሲያጋጥሙ የሚወሰዱ ሕጋዊ እርምጃዎች፤
✅ አቤቱታና ክርክር አፈታት፦ በምርጫ ሂደት የሚነሱ ቅሬታዎች የሚስተናገዱባቸው ሕጋዊ መንገዶች፤
ሥልጠናው አመራሩና ሠራተኛው በምርጫ ወቅት ሊኖረው የሚገባውን ተቋማዊ ገለልተኝነትና ሙያዊ ሥነ-ምግባር ከማስገንዘብ ባለፈ፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሕግ የበላይነት ያለውን ፋይዳ ያጎላ ሆኖ አልፏል።
ተሳታፊዎችም ከሥልጠናው ባገኙት ግንዛቤ የራሳቸውንም ሆነ የሌሎችን መብት በማክበርና በማስከበር ረገድ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
"የሕግ የበላይነት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ነው!"
የቦሌ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት

ሰበር በቅፅ 28 በሰ/መ/ቁ 150290 በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም
በባንክ የገንዘብ ሐዋላ መላኪያ ወረቀት ሰነድ ገንዘብ መላኩን ከማስረዳት ውጪ በምን ምክንያት ገንዘቡ መላኩን ወይም ገንዘቡ በብድር፣በአደራ የተሰጠ መሆኑን ሊያስረዳ የማይቻል ስለመሆኑ። የፍ/ሕ/ቁጥር 2472፣ 2782/1/2/2802/2 ጠቅሶ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
ተከሳሽ የነበረውም ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ነው!

📌 ወለድ አገድ (Antichresis)፦ ዕዳን በንብረት ፍሬ የመክፈያ የሕግ ጥበብ!
ብዙዎቻችን የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን (Mortgage) እናውቃለን። ንብረታችን በእጃችን ሆኖ፣ ሰነዱን ብቻ ባንክ ወይም ግለሰብ ጋ አስይዘን ብድር እንወስዳለን። ነገር ግን በፍትሐብሔር ሕጋችን (ከቁጥር 3117-3130) የተደነገገውና “ወለድ አገድ” በመባል የሚታወቀው የሕግ ጽንሰ-ሐሳብ ከዚህ ለየት ያለ፣ ሆኖም እጅግ ጠቃሚ አሠራር ነው።
፩. ወለድ አገድ (Antichresis) ምንድን ነው?
ወለድ አገድ ማለት አንድ ባለዕዳ ለተበደረው ገንዘብ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረቱን (ቤት) ለገንዘብ ጠያቂው አስረክቦ የሚሰጥበት የውል ዓይነት ነው። እዚህ ላይ ሌሎች በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚቋቋሙ መያዣዎችና ወለድ አገድ የሚለያዩት ንብረቱ ለባለገንዘቡ ተላልፎ በሚሰጥበት (Possession) እና ፍሬው በሚሰላበት መንገድ ነው።
፪. ወለድ አገድ እንዴት ይቋቋማል?
ወለድ አገድ በባሕርይው ከማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ጋር ስለሚመሳሰል፣ አቋቋሙ በሕግ፣ በፍርድ፣ በውል ወይም በኑዛዜ ሊሆን ይችላል (ቁ. 3041)። ይሁን እንጂ ውሉ ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት፦
• የጽሑፍ ውል፦ ውሉ በጽሑፍ ካልተደረገ ዋጋ የለውም (ቁ. 3045)።
• የገንዘብ መጠን፦ የብድሩ ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር ተለይቶ መጠቀስ አለበት።
• ምዝገባ፦ ውሉ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ (ካዳስተር) ካልተመዘገበ በስተቀር በሕግ ፊት ውጤት አይኖረውም (ቁ. 3052)።
• ማስረከብ፦ ባለዕዳው ንብረቱን ለባለገንዘቡ ካላስረከበ ውሉ እንደ መደበኛ የቤት መያዣ (Mortgage) ነው የሚቆጠረው (ቁ. 3121)።
፫. የባለገንዘቡና የባለዕዳው መብትና ግዴታ
በወለድ አገድ ውል ጊዜ ንብረቱ ለባለገንዘቡ ስለሚሰጥ፣ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት በአከራይና ተከራይ ሕግ መርሆዎች ይመራል (ቁ. 3120)፦
• ትርፉ ለወለድ፦ ንብረቱን የተረከበው ባለገንዘብ ለባለቤቱ ምንም ዓይነት ኪራይ አይከፍልም። ይልቁንም ከቤቱ የሚገኘው ኪራይ የብድሩ ወለድ ተደርጎ ይቆጠራል (ቁ. 3124)።
• የወለድ ጣሪያ፦ ባለገንዘቡ ከንብረቱ ከሚያገኘው ጥቅም በላይ ተጨማሪ ወለድ እንዲከፈለው በውል መስማማት አይችልም። እንዲህ ዓይነት የውል ቃል ካለ ፈራሽ ነው!
• ጥገናና ማደስ፦ ባለገንዘቡ ንብረቱን ይረከባል እንጂ ባለቤቱ (ባለዕዳው) ንብረቱን እንዲያድስለት ወይም እንዲጠግንለት የመጠየቅ መብት የለውም (ቁ. 3123)።
፬. ንብረቱን ስለመውረስ (⚠️ ትልቅ ጥንቃቄ!)
ብዙዎች "ዕዳውን ካልከፈልክ ቤቱን እወርሳለሁ" የሚል ውል ይፈራረማሉ። ነገር ግን በሕጋችን ቁጥር 3060 መሠረት፦
"ዕዳው ሳይከፈል ቢቀር ባለገንዘቡ ንብረቱን በባለቤትነት ይወስዳል" ወይም "ያለ ፍርድ ሥርዓት ይሸጠዋል" የሚል የውል ቃል ፈራሽ ነው!
ባለገንዘቡ ዕዳው ካልተከፈለ ንብረቱን በሐራጅ አሽጦ ገንዘቡን ከመቀበል ውጭ፣ በራሱ ሥልጣን ንብረቱን የግሉ ሊያደርግ አይችልም። ንብረቱን ለዕዳው መክፈያነት በባለቤትነት መውሰድ የሚቻለው ዕዳው የሚከፈልበት ጊዜ ካለፈ በኋላ በሁለቱ ወገኖች በሚደረግ አዲስና ነጻ ስምምነት ብቻ ነው።
፭. ውሉ የሚቀረው (የሚሰረዘው) መቼ ነው? (ቁ. 3110፣ 3128 እና 3130)
• ዕዳው ሙሉ በሙሉ ተከፍሎ ሲያልቅ፤
• ባለገንዘቡ የመያዣ መብቱን በጽሑፍ ሲተወው፤
• ንብረቱ በሐራጅ ተሸጦ ዋጋው ለባለገንዘቦች ሲከፋፈል፤
• የምዝገባው ዘመን (10 ዓመት) አልፎት ካልታደሰ (ቁ. 3058)።
ማጠቃለያ፦
ወለድ አገድ ብድርን ከቤት ኪራይ ጋር አቀናጅቶ ለመጠቀም የሚረዳ ጥንታዊ ግን ጠቃሚ የሕግ መሣሪያ ነው። በተለይ ጥሬ ገንዘብ በሌለበት ሁኔታ ንብረትን ለባለገንዘቡ ሰጥቶ ከወለድ ጫና ለመገላገል ይረዳል። ሆኖም ውሉ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ካልተመዘገበ በስተቀር ለሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ሊሆን እንደማይችል መዘንጋት የለበትም።
⚖️ የሕግ ምክር፦ ማንኛውንም የወለድ አገድ ውል ከመፈረማችሁ በፊት በሕግ ባለሙያ መታየቱንና በውልና ማስረጃ መመዝገቡን አረጋግጡ።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3041 - 3130።
ንቃተ-ሕግን በማሳደግ መብትና ግዴታችንን እንወቅ! ይህን መረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ።

ሴቶችና ሕፃናት በአዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ
በ- ኃይሉ ሐሰና (ጠበቃ)
ባለፈው ዋስትናን በሁኔታ ስለ መከልከል በጻፍነው ላይ ሴቶችና ሕፃናት በአዲሱ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ ውስጥ ልዩ ትኩረት እንዳገኘ ገልጸን ነበር:: እስቲ ከመዘርዘር አንጻር ትንሽ ሰፋ አድርገን እንዳሠው:-
1. በሴቶችና ሕፃናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘን ሰው መርማሪ ፖሊስ በፖሊስ ዋስትና ሊፈታው አይችልም:: አንቀጽ 117(3)::
ማለትም ተጠርጣሪው ወንጀሉን ስለ መፈጸሙም ከነአካቴው ወንጀል ስለመፈጸሙ አጠራጣሪ ቢሆንም ስንኳ ለሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ትኩረት መስጠት ስለሚሻ ፖሊስ የግድ በፍ/ቤት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በማስከፈት የተጠርጣሪው የዋስትና ጉዳዩ በዳኛ እንዲታይ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
2. በሴቶችና ሕፃናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል መጠርጠር/መከሰስ በራሱ በፍ/ቤት ዋስትና ለመከልከል በቂ ምክንያት ነው:: አንቀጽ 139(2/መ)
3. ፍርድ ቤቱ ዋስትና የፈቀደለት ሰው በሴቶችና ሕፃናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል የተጠረጠረ ከሆነ ተጠርጣሪው በመልካም ባሕርይ ለመመራት የእጅ ጠብቅ ዋስ (guarantee of good conduct) እንዲገባ ቅድመ ሁኔታ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 142(7)
4. ዐቃቤ ሕግ በሴቶችና ሕፃናት ላይ በተፈጸመ ወንጀል የወንጀል ክስ ሲያቀርብ በዚያው መዝገብ ዐብሮ ተከሳሽን ወክሎ የፍትሐብሔር (የካሳ) ክስ አጣምሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት:: አንቀጽ 215(2)::
ስለሆነም የተደፈሩ፣ የተጠለፉ፣ ወይም ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶችና ሕፃናት ካሳ ለመጠየቅ በራቸው በፍ/ብሔር ፍ/ቤት የዳኝነት ክፍያ ከፍለው ክስ እያቀረቡ መንከራተት አይኖርባቸውም::
5. ሴትን በመጥለፍ፣ አስገድዶ በመድፈር፣ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እና መሰል በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በማድረግ በተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ በባሕላዊ ሥርዓት አይታይም::
6. ለጥቃት የተጋለጠች ሴት/ሕፃን (የግል ተበዳይ) ምስክር ሲሆኑ የግድ በአካል በችሎት መቅረብ ሳይጠበቅባቸው የምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡበት ሁኔታ [VC, et.] ፍ/ቤቶች ሊያመቻቹ ይገባል: ተብሎ ተደንግጓል፡: አንቀጽ 21(6)
7. እንዲሁም የአስገድዶ መድፈር ወይም ጾታዊ ጥቃት የተፈጸመባት ሴት ወይም ሕፃን የምስክርነት ቃል በምትሰጥበት ጊዜ ዐብሯት ወላጆቿ (አሳዳሪዋ/ሞግዚቷ) እና የማኅበራዊና የሥነ ልቦና ድጋፍ የሚሰጥ ባለሙያ መገኘታቸውን ችሎቱ የማረጋገጥ አለበት:: አንቅጽ 79(3)(ለ)
8. ለመመስከር ያለመገደድ ልዩ መብት ሴቶችና ሕፃናትን አስመልክቶ ተፈጻሚ አይሆንም:: አንቀጽ 254
9. ይም የቤት ውስጥ ጥቃት በትዳር አጋር እና በወላጆችና በልጅ መካከል በሚፈጸምበት ጊዜ ምስክር ማግኘት አስቸጋሪ እንዳይሆን በሚል ነው፡፡
ስለሆነም ሚስት የባል-ሚስት፣ የልጅ-ወላጅ ለመመስከር ያለመገደድ ከለላን በማንሣት ምስክርነት መቃወም አይቻልም::👩🏽⚖️
10. የግል ተበዳይ የሆነች ሴት ወይም የሕፃን ወኪል ያቀረበችውን የግል አቤቱታ (complaint) ለማንሣት በፈለገች ጊዜ ፍ/ቤቱ ዐ/ሕግ አስተያየት እንዲሰጥ የማድረግ ግዴታ አለበት:: አንቀጽ 67/1/
እንደሚታወቀው በግል አቤቱታ ብቻ የሚያስቀጣ ወንጀል የተፈጸመበት የግል ተበዳይ ወይም ወኪሉ ከፍርድ ቤት በማንኛውም ጊዜ ያቀረበውን አቤቱታ በማንሣት በፍ/ቤት እየታየ ያለው መደበኛ ክስ እንዲቀር ማድረግ ይችላል::
ይሁንና በግል አቤቱታ ብቻ የሚያስቀጣው ወንጀል በሕፃናት እና ሴቶች ላይ የተፈጸመ ከሆነ ተጎጂዋ ሴት ወይም የሕጻኑ ወኪል ክሱን ለማንሣት ብትፈልግ/ቢፈልግ ፍ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥበት በማድረግ የግል ተበዳይ ወይም ወኪሉ አቤቱታውን ለማንሣት የወሰነው በነጻ ፈቃዱ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት::
ስለሆነም ዐቃቤ ሕግ የግል አቤቱታውን መነሣት ከተቃወመ ወይም የግል አቤቱታውን ለማንሣት የወሰነችው ጥቃትን በመፍራት እንደሆነ ካረጋገጠ ፍ/ቤቱ የግል አቤቱታ ለማንሣት የቀረበውን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ ክሱ መታየቱ እንዲቀጥል ያዛል::🧑🏾⚖️
11. በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የወንጀል ምርመራና ክስ አመሠራረትን በተመለከተ ፍትሕ ሚኒስቴር ልዩ መመሪያ ያወጣል፡፡ 430(3/ቸ)
*እንግዲህ በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን አስመልክቶ መርማሪ ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ ፍትሕ ሚ/ር የሚያወጣውን ልዩ መመሪያ ተከትለው የመሥራት ግዴታ ይኖርባቸዋል::👴🏽🧓🏾
——— ——— ——— ———
ምንጭ:-ከጠበቃ ሃይሉ ሃሰና
ማህበራዊ ሚዲያ የተወሰደ

👍1
በኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ተገልጋዮች ከአገልግሎት ሰጪው እውቅና እና ፈቃድ ውጭ በራሳቸው በሚዘረጉት የኤሌክትሪክ መስመር ለሚደርሰው ጉዳት አገልግሎት ሰጪው ተቋም ተጠያቂ አይሆንም።
እንደ ኤሌክትሪክ አደጋ ባሉ የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ በፖሊስ የሚደረግ የባለሙያ (Forensic) ምርመራ ከፍተኛ የማስረጃነት ዋጋ (High Probative Value) አለው። ይህንን የባለሙያ ምርመራ ውጤት ያለ በቂ ምክንያት ወደ ጎን በማለት ውሳኔ መስጠት መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው።
አገልግሎት ሰጪው ኃላፊነት የሚኖርበት እሱ ራሱ በዘረጋውና ባለቤት በሆነበት መስመር ላይ ለሚደርስ ጉዳት ብቻ ነው። በተገልጋዮች ጥፋት ለሚደርስ አደጋ ተቋሙ ካሣ የመክፈል ግዴታ የለበትም።
የኤሌክትሪክ ኃይል ባለቤት መሆን ብቻውን ኃላፊነትን አያስከትልም፤ ኃላፊነት ሊኖር የሚችለው ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ጥፋት ከተፈጸመ ብቻ ነው።
ሰ/መ/ቁ.175142 (ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም)

አንድ ተከሳሽ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎለት ክስ የቀረበበት ስለመሆኑ እውቋል የሚል ግምት ሊወሰድ የሚገባው አገር አቀፍ ስርጭት ባለው ጋዜጣ ጥሪ የተደረገለት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ እንጂ በአንድ ክልል ብቻ ተደራሽ በሆነ ጋዜጣ ብቻ ጥሪ መደረጉን መጥሪያ እንዳደረሰው ማረጋገጫ አድርጎ በመውሰድ እና መጥሪያ ደርሶታል የሚል ግምት በመውሰድ ጉዳዩን ተከሳሹ በሌለበት አይቶ ውሳኔ መስጠት በሕገ-መንግሥቱ ለተከሰሱ ሰዎች የተረጋገጠላቸውን መሠረታዊ መብት የሚጥስ ስለመሆኑ ።
@የሰ/መ/ቁ፦ 173967 ቅፅ.24
@የሰ/መ/ቁ፦ 173967 ቅፅ.24
ይህንን ያውቃሉ❓❓
የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በወረዳ ጽሕፈት ቤቶቹ የሚሰጣቸውን የኩነት (የልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ፣ ሞትና ጉዲፈቻ) ማስረጃዎችን የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት ተገልጋዮች ይዘው መቅረብ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችንና ደጋፊ ሰነዶችን እንደሚከተለው ያሳውቃል።
ለእያንዳንዱ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ልዩ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የልደት ሰርተፍኬት ለማረጋገጥ
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ፦ በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የልደት ማስረጃ
አገልግሎቱ የሚሰጠው ከሁለቱ አንዱ ወላጅ በአካል ሲገኝ ነው (የወላጆች የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ያስፈልጋል)።
ምዝገባው በሞግዚትነት ከሆነ የፍርድ ቤት የሞግዚትነት ውሳኔ ሰነድ መቅረብ አለበት።
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ፦ ባለጉዳዩ በአካል መቅረብ አለበት። በአካል መቅረብ ካልቻለ፣ ጉዳዩን የሚገልጽ ልዩ ውክልና ከወካይና ተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
2. የጋብቻ ማስረጃ ለማረጋገጥ
በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የጋብቻ ማስረጃ መያዝ።
ለግልባጭ ወይም ለእርማት አገልግሎት፦ የተጋቢዎች ሁለት ሁለት (2) ጉርድ ፎቶግራፍ።
በውክልና የሚጠየቅ ከሆነ (ለእርማት፣ ዕድሳትና ግልባጭ)፦ ባልና ሚስት ጉዳዩን በግልጽ የሚያሳይ ውክልና፣ የወካዮች እና የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም የታደሰ የመኖሪያ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3. የፍቺ ማስረጃ ለማረጋገጥ
በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የፍቺ ማስረጃ
የህግ አስገዳጅነቱ የተረጋገጠ የፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሰነድ መቅረብ አለበት።
4. የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት ለማረጋገጥ
በወረዳ የተመዘገበ የጉዲፈቻ ሰርተፍኬት እና የፍርድ ቤት ውሳኔ ሰነድ
ጉዲፈቻ አድራጊዎች የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በመያዝ በአካል መቅረብ አለባቸው።
ጉዳዩ በውክልና ከሆነ፣ይህንኑ የሚያስረዳ ልዩ ውክልና መቅረብ አለበት።
5. የሞት ማስረጃ ለማረጋገጥ
በወረዳ ደረጃ የተመዘገበ የሞት ማስረጃ የማረጋገጥ አገልግሎት ለማግኘት
ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው፣ እርሱ ከሌለ የሟች የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፣ እነዚህም ከሌሉ የቅርብ ጎረቤት ወይም ስለሟቹ መሞት የሚያውቅ ማንኛውም ሰው የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት በማቅረብ ማስመዝገብና ማረጋገጥ ይችላል።
ሟች የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆነ ከሆስፒታል የተሰጠ የማሳወቂያ ወረቀት መቅረብ አለበት።
ማሳሰቢያ፡- ለሁሉም ከላይ ለተዘረዘሩት የኩነት አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስፈልግ ደጋፊ ሰነድ
• የታደሰ ብሔራዊ መታወቂያ / የታደሰ ፓስፖርት / የትውልደ ኢትዮጵያ የውጭ ዜግነት መታወቂያ (የቢጫ ካርድ)።
• ከዝቅተኛው አስተዳደር ጽ/ቤት መደበኛ ነዋሪነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ / የስደተኛነት ማስረጃ / የመኖሪያ ፈቃድ።
• ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ባልደረባነቱንና ዜግነቱን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመስሪያ ቤቱ መታወቂያ ጋር / የመከላከያ ሰራዊት ከሆነ የመከላከያ ሰራዊት መታወቂያ መያዝ
• የጠፋ ሰርተፍኬት ግልባጭ ለመውሰድ፦ ከፖሊስ የተሰጠ የጠፋ ሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ ግዴታ ነው።
• ከወረዳ የመጡ ማስረጃዎች፦ ከወረዳው ስለመውጣታቸው የሚገልጽ ማረጋገጫ ደብዳቤ ያስፈልጋቸዋል።
• ከክፍለ ከተማ የመጡ ማስረጃዎች፦ ከሰነዱ በስተጀርባ የማረጋገጫ ማህተም ማረፍ ይኖርበታል።
• ከውጭ ሀገር የሚመጣ ውክልና፦ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በፌደራል ሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ መረጋገጥ አለበት።
=====================

👉 ቃብድ ✍️
ቃብድ ማለት ተዋዋይ ወገኖች ውላቸው እንዲጸናላቸው ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት እና ሽያጩን ለማረጋገጥ አንዱ ወገን ለሌላኛው የሚሰጠው የማስያዣ ገንዘብ ነው።
በኢትዮጵያ የውል ሕግ ሥርዓት ውስጥ ቃብድ ከመደበኛ የውል አፈጻጸም ለየት ያሉ የሕግ ውጤቶች አሉት።
1. የቃብድ የሕግ ውጤት በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885
እንደ ፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1885(1) እና (2) ድንጋጌ፣ በቃብድ የታሰረ የሽያጭ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለየው በሚከተሉት ነጥቦች ነው፦
ተቃራኒ ስምምነት እስካልተደረገ ድረስ፣ ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመተው፣ ቃብድ የተቀበለው ወገን ደግሞ የተቀበለውን ቃብድ እጥፍ አድርጎ በመመለስ ውሉን በፈቃዳቸው ማፍረስ ይችላሉ።
በቃብድ የታሰረ ውል እንደ ሌሎች መደበኛ ውሎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1776 መሠረት በግዴታ እንዲፈጸም በሕግ አይገደድም።
ይልቁንም ተዋዋዮቹ ቃብዱን በመተው ወይም እጥፍ በመመለስ ከውሉ የመውጣት የመውጫ ቀዳዳ ይሰጣቸዋል።
የቅድመ ክፍያ እና የቃብድ ልዩነት
👇👇👇✍️✍️✍️
ተከራካሪዎች የከፈሉት ገንዘብ ቃብድ ሳይሆን ለሽያጭ ዋጋው ማሟያ የተደረገ የቅድመ ክፍያ ከሆነ፣ የቃብድ ሕግ እጥፍ መመለስ ወይም ትቶ መቅረት ተፈጻሚ አይሆንም።
ቃብድ ለተዋዋይ ወገኖች ውሉን የመተው መብት የሚሰጥ ቢሆንም፣ የሚከፈለው ገንዘብ ቃብድ መሆኑንም ወይም የቅድመ ክፍያ መሆኑ በግልጽ መታወቅ አለበት።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
ሚኪያስ መላክ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service

Telegram
አለ ሕግ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
" አከራዮችን በሕግ ያስጠይቃቸዋል " - ቢሮው
አዲስ አበባ ውስጥ ሰኔ 30 የሚያበቃውን የቤት ክራይ ውል ተንተርሶ አከራዮች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ለተከራዮች እያሳወቁ ነው።
አንዳንዶቹ አከራዮሽ " ቤቱን እፈልገዋለሁ ውጡ / ቤቱ ተሽጧል ውጡ " በማለት ቤት ተከራዮች እንዲለቁ ግፊት እያሳደሩ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
ከቤት ኪራይ ጭማሪ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ መቅደስ ወ/ጊዮርጊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምን አሉ ?
" ተከራዮች በህግ የተሰጣቸው መብታቸውን በደምብ መጠቀም ይጠበቅባቸዋል። አከራዮችም መብትና ግዴታቸውን በአግባቡ መጠቀም ይኖርባቸዋል።
ከተማችን ላይ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉ የኪራይ ቤቶችን መዝግበናል ወደ ሲስተም አስገብተን ቋት ውስጥ ነው ያለው።
የት ክ/ከተማ ፣ የት ወረዳ ፣ የትኛው የቤት ቁጥር ፣ ባለስንት መኝታ ቤት በስንት ብር ተከራየ ፣ ማነውስ የተከራየው የሚለው ዳታ አለ እጃችን ላይ።
እውነት ነው አንድ ሰው ግዴታ ያለበት 2 ዓመት አንድን ሰው ሊያከራይ ነው። ግዴታው ሁለት አመት ነው ከዛ በላይ መጨመር ይችላል (ጊዜውን)።
ስለዚህ አከራዩ ' ዋጋ ጨምር ' ማለት አይችልም። ዋጋ መጨመር የሚችለው መንግሥት ነው። በአመት አንድ ጊዜ ሰኔ 30 ላይ በመጣው የዋጋ ጥናት መሰረት ዋጋ መጨመር የሚችለው መንግሥት ነው። ለምሳሌ ፦ አንድ ቤት 1 ሺህ ብር ተከራይቶ ቢሆን 1,100 ብር ማድረግ የሚችለው መንግሥት ነው። የማርኬት አሰስመንት ሰርቶ በምን ያህል መጠን ዋጋ ከፍ እንዳለ አስልቶ የሚጨምረው በፐርሰንት መንግሥት ነው።
2017-2018 በጀት አመት ላይ አምና ዋጋ ተጠና የጨመረ ዋጋ ስላልነበረ በነበረው ነው የሚቀጥለው ብለን አሳውቀን በነበረው ነው የቀጠለው። ዘንድሮም ዋጋ እያጠናን ነው። ስለዚህ የዋጋ ጥናቱ በሚመልሰው መልስ መሰረት ወይ በነበረት ይቀጥላል አሁንም አልያም የጨመረ ዋጋ ካለ በይፋ መንግሥት ያሳውቃል። እስከዛ ድረስ አከራዮች ዋጋ ጨምሩ የማለት መብት የላቸውም ፤ አሰራሩም አይፈቅድላቸውም።
ተከራዮችም መብታቸውን መጠቀም አለባቸው። አከራይ ' ዋጋ ጨምር ' ስላለው ብቻ ዋጋ መጨመር የለበትም። ውላቸው እኛ ጋር አለ። ውላቸው የሚያበቃው ከሰኔ 30 በኋላ ነው። ውላቸው ውስጥ ሆነው ዋጋ መጨመር ስለማይጠበቅባቸው እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም በቅርባቸው ወረዳ አለ ስራ አስፈጻሚ የሚመራው ፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አለ ፣ ክፍለ ከተማም አለ ወረዳው ካልፈታ ክፍለ ከተማ ይፈታል፣ ቢሮ እኛም ጋር አለ። እነዚህ ቦታዎች ላይ እየመጣ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
አከራይ ዋጋ ጨምር ስላለው ብቻ የሚጨምር ተከራይ ካለ መብቱን እየተጠቀመበት አይደለም። መንግሥት በተከራይ እና አከራይ መካከል ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሰፊ ጥረት አድርጓል እያደረገም ነው፤ አሰራርም የተበጀተው ተከራዮች ቢያንስ 2 ዓመት የሆነ ቦታ ተረጋግተው እንዲቀመጡ ነው።
አከራዮችም በተከራዮች በኩል የሚደርስባቸውን ያልተገቡ ነገሮች (ቤቱን ላልተገባ ነገር መጠቀም) መከላከል የመንግሥት ድርሻ ነው።
አከራዮች ተገቢ አይደለም ፤ ' ውጡልኝ ' ከዛ ደግሞ ' ጨምሬ ነው የማከራየው ' የሚባል አሰራር ስለሌለ ይሄ በጥቆማ ቢደረስበት ከክልከላዎቹ ውስጥ አንዱ ስለሆነ በሕግ ያስጠይቃቸዋል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

በስታቲስቲክስ ተግባር የተሰበሰበ የግለሰብ መረጃ በማንኛውም ተቋማት ዘንድ ለምርመራ፣ ለደህንነት፣ ለሕግ ወይም ለአስተዳደራዊ ውሳኔዎች እንዳይውል የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ።
ለልማት ዕቅድና ለፖሊሲ ቀረጻ የሚውሉ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ ለማመንጨት ያስችላል የተባለ የስታቲስቲክስ አዋጅ ተዘጋጅቶ የሚኒስትሮች ምክርቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል።
አዲሱ አዋጅ በዋናነት ያስፈለገው የሀገሪቱን የልማት ዕቅዶች፣ የፖሊሲ ቀረጻዎችና የትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሞችን በተሟላ መረጃ ለመደገፍ ሲሆን፤ከዚህ ባለፈም ከሃያ ዓመታት በላይ ያስቆጠረው ነባሩ ሕግ እንደ ቢግ ዳታ (big data)፣ ጂኦስፓሻልና ዲጂታል የመሳሰሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና የመረጃ ምንጮችን ለማስተናገድ አቅም ማጣቱ ለለውጡ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡
በሌላ በኩል ተቋማዊ ተጠያቂነትን፣ ግልጽነትንና ሙያዊ ነፃነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዋጁ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
ይህም በብሔራዊ ደረጃ የሚታዩ የመረጃ ድግግሞሾችንና እርስ በእርስ የሚጋጩ ዳታዎችን በማስቀረት፣ የኢትዮጵያን የመረጃ አያያዝ ከተባበሩት መንግሥታትና ከአፍሪካ የስታቲስቲክስ ቻርተር መርሖዎች ጋር ለማጣጣም ያለመ ነው፡፡
ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የተሰኘውን ተቋም በድጋሚ በማቋቋም፣ ተቋሙ የራሱ ቦርድና የሥራ አመራር እንዲኖረው ያደርጋል።
ይህ አዲስ መዋቅር ተቋሙ ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆኖ ሙያዊና ሳይንሳዊ ግኝቶችን ብቻ መሠረት አድርጎ እንዲሠራ የሚያስችል መሆኑ በረቂቁ ላይ ተመላክቷል።
ተቋሙ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተጠሪ ቢሆንም፣ በቴክኒካዊና በስታቲስቲካዊ ሥራዎቹ ላይ ግን ሙሉ ነፃነት እንደሚኖረው ተደንግጓል።
በዚህ አዋጅ የስታቲስቲክስ ትርጉም ሰፋ ባለ መልኩ ቀርቧል ከዚህ ቀደም ከሚታወቁት የሕዝብ ቆጠራና የናሙና ጥናቶች በተጨማሪ፣ አዲሱ ረቂቅ እንደ "ቢግ ዳታ" (Big Data)፣ የሳተላይት መረጃዎች (Geospatial Data)፣ የዲጂታል ምንጮችና በሴንሰር የተደገፉ መረጃዎችን እንደ ስታቲስቲክስ ምንጭነት ዕውቅና ሰጥቷቸዋል።
"ብሔራዊ የስታቲስቲክስ ሥርዓት" (National Statistical System) በሚል የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሚሰበስቧቸው መረጃዎች ተቀራራቢና ወጥ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የሥራ ድግግሞሽን ለማስቀረት የተቀናጀ አሠራር እንዲዘረጋ ያዝዛል።
ማንኛውም ተቋም የሚያመነጨው መረጃ በኢትዮጵያ የዳታ ጥራት ቁጥጥር ማዕቀፍ ውስጥ ማለፍ እንደሚኖርበትም ተደንግጓል።
የዜጎች የግል መረጃ ምስጢራዊነት አጠባበቅም በተመለከተም በስታቲስቲክስ ተግባር የተገኘ የግለሰብ ዳታ ለስታቲስቲክስ ዓላማ ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፣ በማንኛውም ሀገራዊ ወይም የዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ ለምርመራ፣ ለደህንነት፣ ለሕግ ወይም ለአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሊውል እንደማይችል ረቂቁ በግልጽ ያሳስባል።
የግለሰቦችን መለያዎች የያዙ ሁሉም የዳታ መሰብሰቢያ ቅጾች ለስታቲስቲክስ ዓላማዎች አስፈላጊነታቸው እንዳበቃ ወዲያውኑ መወገድ አለባቸው፡፡
የግለሰቦችን ማንነት የሚገልጽ መረጃ አሳልፎ መስጠት በረቂቁ መሰረት በወንጀል የሚያስጠይቅ ነው።
ረቂቅ አዋጁ በመረጃ አሰባሰብ ሂደት ላይ ለሚታዩ መሰናክሎች የቅጣት ድንጋጌዎችን ያስቀመጠ ሲሆን ማንኛውም መረጃ እንዲሰጥ የተጠየቀ አካል የተሳሳተ መረጃ ቢሰጥ ወይም ለመተባበር ፈቃደኛ ባይሆን በወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል።
ይህ ረቂቅ አዋጅ ግንቦት 18 የተካሄደው 55ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ፣ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱን መገለጹ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ/ም