በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች እና ከኑዛዜ ጋር የተያያዙ ይርጋዎች
በ፡ ካሴ መልካም
በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን የሕግ ጉዳዮች ያገኛሉ፡
1ኛ. የውርስ ይርጋ ማቋረጫ ምክንያቶች እና የውርስን የይርጋ ጊዜ የሚያቋርጡ ምክንያቶች
2ኛ. በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች
1. የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ
2. ከሕገ-ወጥ ተግባር ጋር የተገናኘ የኑዛዜ ሁኔታ
3. የውርስ ሐብቱን ስመ-ሐብት በጋራ ያስመዘገበ ወራሽ
4. የወራሽነት ማስረጃ ይሰጠኝ ክስ የይርጋ ጊዜ
5. በጋራ የውርስ ሃብቱን ይዞ መጠቀም
6. ሟች ሳይሞት ንብረቱን በያዘ ሰው ላይ የሚቀረብ ክስ የይርጋ ጊዜ
7. የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በሕጉ የጊዜ ገደብ ያረጋገጠ ከሳሽ
8. በሀሰት የተሰጠን የወራሽነት የምስክር ወረቅ ማሰረዝ
3ኛ. የኑዛዜ ይፍረስልኝ ጥያቄ የይርጋ ጊዜ
1. ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች
2. ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ወራሾች
3. በመንፈስ ጫና የተደረገ ኑዛዜ እንዲፈርስ/እንዲቀነስ የመጠየቂያ የይርጋ ጊዜ
4. በሃይል የተደረገ ኑዛዜን የማፍረሻ የይርጋ ጊዜ
5. ከውርስ የተነቀለ ሰው የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ
6. የሟች የኑዛዜ ወራሽ የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ
ጸሐፊው የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሠረታዊ ሀሳቦች በሚል መጽሐፍ አሳትሞ ለአንባቢ ያበቃ ሲሆን በሕግ የመጀመሪያ ድግሪ እንዲሁም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋና ዳኝነት ከሰባት ዓመት በላይ በማገልገል ይገኛል።
መልካም ንባብ
https://www.abyssinialaw.com/blog/inheritance-matters-not-restricted-by-a-period-of-limitation

Abyssinialaw
በይርጋ የማይታገዱ የውርስ ጉዳዮች እና ከኑዛዜ ጋር የተያያዙ ይርጋዎች
ይህ ፅሑፍ “የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረተ-ሐሳቦች” ከሚለው 3ኛ ዕትም መፅሐፍ በ9ኛ ምዕራፍ ላይ የተከተበ ሲሆን በዚህ መፅሐፍ በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዕትም ምዕራፍ 9 ተብሎ የነበረውን በአዲስ መልክ የውርስ ጉዳይ ይርጋዎችን በማዋቀር በመፅሐፉ ተሰንዷል፡፡ በምዕራፍ 9 ላይ ከተቃኙ ከ20 በላይ የሆኑ...
ሰላም! እባክዎ ሁለት ደቂቃዎች ብቻ ወስደው ይህን ፎርም በመሙላት ይተባበሩን!
https://forms.gle/4Y8hSiUa5WecZv9b6
https://forms.gle/4Y8hSiUa5WecZv9b6
Google Docs
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፍትሕ ጽ/ቤት የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት Bole Sub- City Administration, Justice Office Legal Awareness and Advice…
ይህ መጠይቅ ከሐምሌ 2017 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2018 ዓ/ም በሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በተሰጡ የንቃተ ሕግ ሥልጠናዎች የተሳተፉ ሰልጣኞች በሕግ ግንዛቤያቸውና የዕለት ተዕለት ውሏቸው ላይ የመጣውን ለውጥ ለመገምገም ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ምላሾችዎ ለወደፊት ሥልጠናዎች ጥራት መሻሻል ወሳኝ ናቸው። ምላሽ ለመስጠት የሚወስደው ጊዜ ከ5 ደቂቃ አይበልጥም።
ለጊዜዎ በቅድሚያ እናመሰግናለን!
ለጊዜዎ በቅድሚያ እናመሰግናለን!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ የ2019 ዓ.ም የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ መደበኛ ያልሆኑ አሰራሮችን ለመግታት የ2019 በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ እንዲጸድቅ መወሰኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ ቀደም ሲል በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት የተወሰነ ሲሆን፣ በከተማዋ የተካሄደ ሳይንሳዊ ጥናትንና የነዋሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበ መሆኑ ተገልጿል።
ውሳኔው አከራዮች ወቅታዊውን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ተከራዮች ደግሞ ካልተገባ የዋጋ ጭማሪና መፈናቀል ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል ምዝገባና የውል እድሳት ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች በይፋ መጀመሩ ቢሮው አያይዞ ገልጿል።
ቢሮው አክሎም፣ " ይህ አሰራር በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሃምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ዋጋ ጭማሪውና የውል እደሳቱ መነሻ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ብቻ ነው " - ቢሮው
በ2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ የጸደቀ ሲሆን ሕገ-ወጥ " የመንደር እና የአካባቢ ውሎች " በጥብቅ ተከልክለዋል።
ዋጋ ጭማሪውና የውል እደሳቱ መነሻ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ብቻ መሆኑን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡
በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መተግበር መጀመሩ ተገልጿል።
የተጣሉ ጥብቅ ክልከላዎች ምን ምን ናቸው ?
አዲሱን የውል እድሳት ምዝገባና የተቀመጠውን የዋጋ ጣሪያ ወደ ጎን በመተው የሚፈጸሙ ማናቸውም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ጥብቅ ክልከላ ተጥሏል።
በዚህም መሠረት ፡-
- በቢሮው ከተመዘገበው እና ከሚመዘገበው ውል እንዲሁም ከሚሰጠው አቅጣጫ ውጭ፣ «ልዩ ውል» በሚል የሚፈጸሙ ማናቸውም የመንደር ውሎች፤
- ከሕጋዊ አሰራር ውጭ የሚደረጉ የአካባቢ ውሎች፤
- በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) አካባቢ የሚደረጉ ማናቸውም ዓይነት ሕገ-ወጥ ውሎች ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው።
ማንኛውም አከራይ እና ተከራይ እነዚህን የተከለከሉ ሕገ-ወጥ ውሎች ይዘው ሲገኙ ወይም ከተቀመጠው የ11.5% የዋጋ ጭማሪ ጣሪያ በላይ ፈጽመው ከተገኙ ቢሮው ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስጠንቅቋል።
ሃምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም
#TikvahEthiopiaFamilyAA

" ህጋዊው የውል ማሻሻያ ለ2 ዓመታት ይቆያል " - ቢሮው
በአዲስ አበባ የ2019 በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ዓመታዊ የጭማሪ ጣሪያ 11.5 በመቶ ሆኖ እንዲጸድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ከዚህ ተመን በላይ መጨመር በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊው የውል ማሻሻያም ለ2 ዓመታት ይቆያል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።
ከህጋዊ አሰራር ውጪ የሚደረጉ "የመንደር ውሎች" የተከለከሉ ሲሆን ውል በማያድሱና ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ ቅጣት ይጣላል።
የውል እድሳት ጊዜያቸው አልፎ አከራይም ተከራይም አብረው ኖረው እድሳት ሳይፈጽሙ እስከ 2 ወር ከቆዩ የ1 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይጣልባቸዋል።
ውል ሳያድሱ 3 ወር እና ከዚያ በላይ የቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይከፍላሉ።
አዲስ ተከራይ አስገብተው ውል ያላደሱ እና ያላስመዘገቡ የ1 ወር የቤት ኪራይ ይቀጣሉ።
በጥቆማ ወይም በክትትል ውል ያላደሱ ወይም ያላስመዘገቡ መሆናቸው ከተረጋገጠ ደግሞ ከ1 እስከ 3 ወር የሚደርስ የኪራይ መጠን ቅጣት እንደሚጣልባቸው ቢሮው አሳውቋል።
የቤት ኪራይ የውል እድሳት በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ ጽህፈት ቤቶች ወይም በ"መሶብ" ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ማከናወን ይቻላል ተብሏል።
ሃምሌ 3 ቀን 2018 ዓ/ም

ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት የሚሰጣቸውን የንቃተ ሕግ ሥልጠናዎች አርዕስቶች ለመለየት የቀረበ መጠይቅ ነው። እባክዎ 3 ደቂቃ ወስደው በመሙላት ይተባበሩን!
https://forms.gle/azbVBpwN2qeYHDyu6
https://forms.gle/azbVBpwN2qeYHDyu6
Google Docs
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት ለሚሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች የሰልጣኞችን ፍላጎት ለመለየት የተዘጋጀ መጠይቅ
ይህ መጠይቅ የቀረበልዎ በቦሌ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ2019 በጀት ዓመት የሚሰጣቸው የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች የተሳታፊዎችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ ታልሞ ነው። እባክዎ በበጀት ዓመቱ በዳይሬክቶሬቱ ስልጠና እንዲሰጥዎ የሚፈልጉትን የሕግ ርእስ በመምረጥ ይተባበሩን።
የመጥፋት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ሁኔታዎች እና የሚያስከትላቸው ውጤቶች
መግቢያ
አንድ ሰው ከሚኖርበት ወይም ከሚሰራበት አካባቢ ርቆ፣ የት እንደደረሰ ሳይታወቅ እና በሕይወት የመኖሩ ነገር አጠራጣሪ ሆኖ ሲቀር፤ ጉዳዩ ከግለሰቡ ባለፈ በቤተሰቡ፣ በንብረቱ እና በሕጋዊ ግንኙነቶቹ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ይፈጥራል። ይህንን ቀውስ ለመፍታት እና መብትና ግዴታዎቹን ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ የኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ የመጥፋት ውሳኔ ሥርዓትን ደንግጓል። ይህ ጽሑፍ የመጥፋት ውሳኔን ምንነት፣ የሚሰጥባቸው ሁኔታዎችንና ውሳኔው ስለሚያስከትላቸው ውጤቶች እንዲሁም የመጥፋት ውሳኔ ቀሪ ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች በአጨሩ ይዳስሳል።
የመጥፋት ውሳኔ ምንነት
ታዋቂው ብላክ የሕግ መዝገበ ቃላት በ8ኛ እትሙ መጥፋትን “the state of being away from one’s usual place of residence” (Black’s Law Dictionary, 8th edition) ሲል ይተረጉመዋል። ይህም ወደ አማርኛ ሲተረጎም መጥፋት ማለት ከመደበኛ መኖሪያ ቦታ አለመገኘት የሚል ይሆናል።
በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ ቀጥተኛ የሆነ ትርጉም ባይሰጠውም አንድ ሰው በመደበኛነት ከሚኖርበት ቦታ የተሰወረ እና ከ2 ዓመት ወዲህ ስለመኖሩ ምንም አይነት ፍንጭ ያልሰጠ በመሆኑ ምክንያት የመጥፋት መግለጫ ጥያቄ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ እና ጠፋ የተባለው ሰው በሕይወት ስለመኖሩ አጠራጣሪ ሲሆን እና ይህ ሁኔታም ሞተ የሚያስብል ግምት የሚያስወስድ በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጥፋት ውሳኔ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 154 እና 157 ይዘት መረዳት ይቻላል።
የመጥፋት ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች
አንድ ሰው ስለመጥፋቱ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በፍትሐብሔር ሕጉ ላይ የተቀመጡ ጥብቅ መስፈርቶች መሟላት አለባቸው። ከእነዚህ መስፈርቶች ውስጥ አስገዳጁ ሁኔታ የማስታወቂያ ሥርዓት ሲሆን የማጣራት ሥራ እንደአስፈላጊነቱ ጥቅም ላይ ይውላል።
የማስታወቂያ ሥርዓት
የመጥፋት ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ጠፋ የተባለው ሰው በመደበኛነት ይኖርበት በነበረው ቦታ እና ፍርድ ቤት አስፈላጊ ነው ብሎ በሚገምተው ቦታ የተሻለ ነው በሚለው ዘዴ (ጋዜጣ፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን…ወዘተ) ማስታወቂያ በማውጣት ስለግለሰቡ መረጃ ይሰበስባል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 155)። ይህም ሰውየው በሕይወት ካለ እንዲቀርብ ወይም መረጃ ያለው ሰው እንዲያሳውቅ ያስችላል።
የማጣራት ሥራ
ከማስታወቂያው በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ አስፈላጊ ነው ብሎ ባሰበው ማንኛውም ቦታ ሁሉ ይልቁንም የጠፋው ሰው በመጨረሻ ዋና መኖሪያ አድርጎ ይኖርበት በነበረው ቦታ እና በመጨረሻ ጊዜ መኖሩ በታየበት ቦታ ስለጠፋው ሰው ማጣራት /ምርመራ/ እንዲደረግ ትእዛዝ መስጠት ይችላል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 156)።
የመጥፋት ውሳኔ የተፈጻሚነት ጊዜ
ከላይ የተጠቀሱት ሂደቶችን ተከትሎ የጠፋው ሰው ሞተ የሚያስብል ግምት የሚያስወስድ ሆኖ ሲያገኘው ፍርድ ቤቱ የመጥፋት ውሳኔን ይሰጣል። ይህ በሚሆንበት ጊዜም ፍርድ ቤቱ እንደአካባቢው ጠባይ የጠፋው ሰው ንብረቱን የሚያስተዳድርለት ሰው መወከል አለመወከሉን እንዲሁም ስለግለሰቡ ወሬ ላለመገኘቱ ከልካይ የሆኑ ነገሮችን ፍርድ ቤቱ መመርመር እንዳለበት ሕጉ ይደነግጋል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 157)።
ይሁንና ፍርድ ቤቱ ሲያምንበት የሚሰጠውን ውሳኔ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 158 መሠረት ለ1 ዓመት ያህል ሊያራዝም የሚችል ሲሆን የሠጠው ውሳኔም ከ1 ዓመት በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን ትእዛዝ መስጠት ይችላል።
የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ አቤቱታ የማቅረብ መብት ያላቸው ወገኖች
በፍትሐብሔር ሕጉ የተለያዩ ድንጋጌዎች ሥር እንደተመለከተው ማንኛውም ያገባኛል የሚል አካል የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥለት ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ይችላል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 154(1) ‘…ማንኛውም ባለጉዳይ…’)። ይህ ሲባል ግን ሁሉም ማለት ሳይሆን የሚመለከተው ባለጉዳይ ማለት እንደሆነ ከሌሎች ድንጋጌዎች ንባብ መገንዘብ ይቻላል። ይኸውም ጠፋ የተባለው ሰው ሚስት/ባል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 163/1/፣ ጠፋ የተባለው ሰው የኑዛዜ/ያለኑዛዜ ወራሾች (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 164 እና 167)፣ ከጠፋው ሰው በውል ወይም በሌላ መንገድ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 166) እና ዐቃቤ ሕግ (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 156) የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ አቤቱታ የማቅረብ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ጉዳዩን የማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት
መጥፋትን በተመለከተ የማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ማን ነው? የሚለውን በተመለከተ በፌዴራል ደረጃ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንደሆኑ ቻርተር አዋጆች ደንግገዋል (የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 አንቀጽ 33)። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5(1)(ደ) ይህንን ጉዳይ የመዳኘት ሥልጣን የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንደሆነ ይደነግጋል። ሆኖም ግን በሌሎች ክልሎች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ከመጥፋት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን አላቸው።
የመጥፋት ውሳኔ የሚያስከትላቸው ውጤቶች
የመጥፋት ውሳኔ በጠፋው ሰው መኖር ምክንያት የሚገቡ ግዴታዎች ላይ እና በመሞቱ ምክንያት በሚገኙ መብቶች ላይ ውጤቶችን ያስከትላል። እነዚህም፡-
የጋብቻ መፍረስ /Dissolution of Marriage/
በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 163 እና በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75(ሀ) መሠረት በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ በጠፋው ሰው እና በሕይወት ባለው የትዳር አጋር መካከል የነበረው ጋብቻ ይፈርሳል። ይህም የሚሆነው የመጥፋት ውሳኔ የመጨረሻ በሆነበት ቀን ነው።
የውርስ መከፈት እና የንብረት መተላለፍ
የመጥፋት ውሳኔው እንደሞት ስለሚቆጠር የጠፋው ሰው ውርስ ይከፈታል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 164፣ 165)። ንብረቱ ለሕጋዊ ወራሾቹ ወይም በኑዛዜ ለተጠቀሱ ሰዎች ይተላለፋል። ሆኖም ግን ባለይዞታ የሆነ ሰው የጠፋውን ሰው ልጆች ለማቋቋም ካልሆነ በስተቀር ንብረቱን በስጦታ የማስተላለፍ መብት አይኖራቸውም (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 169)። የጠፋው ሰው በሕይወት የመመለስ ዕድል ግምት ውስጥ ስለሚገባ ወራሾች ንብረቱን ከመረከባቸው በፊት ንብረቱ እንዳይጠፋ ዋስትና እንዲያርቡ ፍርድ ቤት ሊያስገድድ ይችላል (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 168)።
የመጥፋት ውሳኔ ቀሪ ስለሚሆንባቸው ሁኔታዎች
የመጥፋት ውሳኔ በሚከተሉት ምክንያቶች ቀሪ ይሆናል። እነዚህም፡-
• ጠፋ የተባለው ሰው መመለስ፣
• ጠፍቷል የሚል የፍርድ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ በሕይወት ለመኖሩ ማስረጃ ከተገኘ
ወይም
• የመጨረሻ ወሬዎቹ የተሰሙበት ከተባለው ጊዜ በሌላ ጊዜ የሞተ ስለመሆኑ ማስረጃ
የተገኘ እንደሆነ የሚሉት ናቸው (የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 170)።

👏1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት
በየዓመቱ የበጀት ዓመቱ ሲጠናቀቅ የዳኝነት አገልግሎት ክብደትና ውስብስብነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የፌዴራል የመጀመሪያ፣ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ለ2 ወራት በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንን ተከትሎ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆኖ በሚቆይበት የክረምት ወራት በተረኛ ችሎት የሚያስተናግዳቸውን አስቸኳይ ጉዳዮች አሳውቋል።
ፍርድ ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳመለከተው፣ አገልግሎቱ የሚሰጠው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 በተደነገገው መሠረት ነው።
ይህም መሰረታዊ የመብት ጥሰት እንዳይከሰት እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጠባቸው ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁ መሠረት በክረምቱ የተረኛ ችሎት የሚታዩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዝርዝር፦
• አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች እና የልጅ ቀለብ ጥያቄዎች፣
• አካል ነጻ ለማውጣት እና እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀረቡ አቤቱታዎች፣
• የሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸም ጉዳዮች፣
• ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ የሚቀርቡ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች፣
• እንዲሁም ሌሎች መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ አጣዳፊ ጉዳዮች በዳኛው ውሳኔ የሚስተናገዱ ይሆናል።
በወንጀል ጉዳዮች በኩል ደግሞ የሚከተሉት ነጥቦች ተለይተዋል፦
• የዋስትና እና የአምክሮ ጥያቄዎች፣
• እስረኛ ያለባቸው የክስ መዛግብት፣
• የጊዜ ቀጠሮ ጉዳዮች (በአራዳ ምድብ ችሎት)፣
• በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ለመሰየም የሚቀርቡ ጥያቄዎች፣
• ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ የወንጀል ጉዳዮች ይስተናገዳሉ።
ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሆነባቸው በእነዚህ ሁለት ወራት፣ ለዳኞች ተራ ወጥቶ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን፤ የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብም ሆነ ተገልጋዩ ለሥራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
የፌዴሬሽን ም/ቤት የጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎችን ኢ-ሕገመንግሥታዊ ሲል ሻረ
⚫ "በሌላ ሰው መሬት ላይ የተገነባ ቤት የመሬቱን ባለይዞታ ባለቤት አያደርግም"
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች ኢ-ሕገ-መንግሥታዊ ናቸው ሲል ሽሯቸዋል።
በዚህም መሠረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሠራ ሰው የቤቱ ባለቤት ይሆናል" በማለት በመዝገብ ቁጥር 30101 እና 36638 ላይ የሰጣቸውን አስገዳጅ ውሳኔዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግሥቱን የሚቃረኑ ናቸው በማለት ውድቅ አድርጎታል።
የምክር ቤቱ ውሳኔ እንደሚያመላክተው፤ በመንግሥት አካል ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ የመሆን እና በመሬቱ የመጠቀም ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው።
በዚህም መሠረት አንድ ሰው የሌላ ሕጋዊ ባለይዞታ በሆነ መሬት ላይ፥ ባለይዞታው ሳይቃወመው እንኳን ቢገነባ የመሬቱ ባለይዞታነትም ሆነ የቤቱ ሙሉ ባለሃብትነት ወደ ቤቱ ሠሪ አይተላለፍም።
የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 40(7) "በመሬት ላይ ንብረት ያፈራ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል" የሚለው ድንጋጌ የሚሠራው ሕጋዊ የመሬት ባለይዞታነት መብት ላለው አካል እንጂ፣ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ያለ ሕጋዊ መሠረት ንብረት ለገነባ ሰው የቤት ባለቤትነት መብት ለመስጠት እንዳልሆነ ምክር ቤቱ አብራርቷል።
በመሆኑም ባለይዞታው ሳይቃወም በይዞታው ላይ ቤት የሠራ ሰው የሚኖረው ሕገ-መንግሥታዊ መብት፣ ለግንባታው ያወጣውን ወጪ ወይም ግምት ከመሬቱ ባለይዞታ የመጠየቅ መብት ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል።
@tikvahethmagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM