ጋብቻን ለመፈጸም በቅድሚያ መሞላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
በሀገራችን የቤተሰብ ሕግ ሶስት ዓይነት የጋብቻ ስርዓቶች እንዳሉ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ እነዚህም፡- 1. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈጸም ጋብቻ፣
2. በሀይማኖት ስርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ እና
3. በባህል ስርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ ናቸው፡፡
ጋብቻ ቢፈጸምም ሶስቱም ዓይነት የጋብቻ መፈጸሚያ ስርዓቶች በቅድሚያ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች መሰረታዊ የሆኑ ናቸው፡፡
1. ፈቃደኝነት (Consent)
የሚጸና ጋብቻ ተፈጸመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ እንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 6 ላይ ተገልጿል፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 34(2) ላይ “ጋብቻ በተጋቢዎቹ ነፃና ሙሉ ፈቃድ ላይ ብቻ ይመሰረታል” ይላል፡፡ ስለዚህ በየትኛውም አይነት ጋብቻ አፈፃፀም ስርዓት ጋብቻ ቢፈጸምም የተጋቢዎቹ ነፃ እና ሙሉ ፈቃደኝነት አስፈላጊ ነው፡፡
2. እድሜ (Age)
ጋብቻ ራሱን የቻለ ኃላፊነት የሚያስከትል በመሆኑ ወደ ጋብቻው የሚቀላቀሉት ተጋቢዎች ይህን ኃላፊነት መቀበል የሚችሉ መሆን አለበት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከጤና አንጻርም ወደ ጋብቻ የሚገቡ ሰዎች እድሜያቸው ብቁ መሆን አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ተጋቢቹ ለጋብቻው ፈቃዳቸውን በነፃ መስጠት መቻል አለባቸው፡፡ በዚህ በተሻሻለው ቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 7(1) ላይ ወንዱም ሆነ ሴቷ አስራ ስምንት አመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈጸም እንደማይችሉ ይገልፃል፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ ይህ እድሜ ሳይሞላ በፍትህ ሚኒስቴሩ ከመደበኛ እድሜ ሁለት ዓመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ ይህ የሚሆነው ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ብቻ ነው፡፡
3. ዝምድና (Affinity and Consagunity)
ከህብረተሰቡ ሞራልና ከጤና ምክንያት የተነሳ ተጋቢዎች የቅርብ ዘመድ (የስጋም ሆነ የጋብቻ ዘመድ) መሆን እንደሌለባቸው እሙን ነው፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 8 እና 9 ላይ ክልከላው በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡
4. በጋብቻ ላይ ጋብቻ (Bigamy)
የፀና ጋብቻ ያለው አንድ ሰው ይህ ጋብቻ ጸንቶ እያለ ሌላ ጋብቻ መፈጸም እንደማይችል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 11 ክልከላ ተጥሎበታል፡፡
5. በብቸኝት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ (Period of Widowhood)
ይሄኛው ክልከላ ወይም ቅድመ ሁኔታ ከላይ ካሉት አራት ቅድመ ሁኔታዎች ለየት ባለ መልኩ በሴቶች ላይ ብቻ የተጣለ ነው፡፡ አንዲት ሴት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ አንድ መቶ ሰማኒያ ቀን ካላለፈ በቀር ሌላ ጋብቻ መፈጸም እንደማትችል ክልከላ ተጥሎባታል፡፡ ነገር ግን ይህ አንድ መቶ ሰማኒያ ቀን ሳይደርስ የወለደች እንደሆን ወይም ጋብቻ የምትፈጽመው ከቀድሞ ባለቤቷ ጋር ከሆነ ወይም እርጉዝ አለመሆኗ በህክምና ከተረጋገጠ ወይም ይህን ጊዜ እንዳትጠብቅ በፍ/ቤት የተወሰነ እንደሆነ ይህን ጊዜ ሳትጠብቅ ጋብቻ ልትፈጽም እንደምትችል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 16 (2) ላይ ተቀምጧል፡፡ ይህ ክልከላ በመሰረታዊነት የተቀመጠው የህፃናትን መብት ለመጠበቅ ነው፡፡ ህፃናት ወላጆቻቸውን የማወቅና ከወላጆቻቸው እንክብካቤ የማግኘት መብት እንዳላቸው በሕገ-መንግስታችንና አለማቀፍ ስምምነቶች ላይ የተቀመጡ እና የተረጋገጠ መብታቸው ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ክልከላ በማድረግ የሕፃናትን መብት ለማስከበር የወላጆቻቸው ማንነት ላይ አከራካሪ ሁኔታ እንዳይፈጠር ነው፡፡
ቸር ሰንብቱ
ፌናን ተጊበሉ
ጥር 14/2013 ዓ.ም

የወንጀል ክስ ማንሳት እና ማስቀጠል የሚቻለዉ መቼ ነዉ?
የክስ ማንሳት የፍሬ ነገር ይዘትና ስነ ሥርዓት በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር በአምስት ንዑስ አንቀጾች ተጠቃሎ ይገኛል፡፡ በይዘቱም፡-
ከከባድ የሰው ግድያ እና ከከባድ ውንብድና ወንጀሎች ውጭ ዐ/ሕግ ከፍርድ በፊት ክስ ማንሳት ይችላል፡፡
ክስ የሚነሳው በዐ/ህጉ ጥያቄ ወይም በሌላ የመንግስት አካል ትዕዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡
ክሱ የሚነሳው በፍ/ቤት ፈቃድ ሲሆን ፍ/ቤቱ ለመከልከልም ሆነ በመፍቀድ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡
በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 113 መሰረት አዲስ ክስ ካልቀረበ ተከሳሹ ለግዜው ይለቀቃል፡፡
የክሱ መነሳት ዐ/ሕግ ክስን ከማንቀሳቀስ አያግደውም፡፡
የሚል ሀሳብ ያለው ነው፡፡
የፍትሕና የሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲቲዩት ባዘጋጀው ረቂቅ የወንጀል ስነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 119 ስር ዐ/ሕግ ከፍርድ ቤት በማንኛውም ጊዜ ክስ ማንሳት የሚችል መሆኑን በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 ስር የተመለከተው የፍርድ ቤት ፈቃድና በተወሰኑ የወንጀል ክሶች ላይ የተደረገው ክልከላ ተነስቷል፡፡ አብሮ በተዘጋጀው የህጉ ሀተታ ዘምክንያትም ጉዳዩን ዐ/ሕግ ካልተከታተለው በውጤት ደረጃ ልዩነት የሌለው በመሆኑ በተወሰኑ ወንጀሎች የተደረገው ክልከላ እና የፍ/ቤት ፈቃድ መጠየቅ አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም በሚል አስፍሯል፡፡
የኢ.ፌ.ድሪ. አስፈጻሚ አካላትን ስልጣን እና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ. 691/2003 የፍትሕ ሚኒስቴርን ስልጣንና ተግባር በዘረዝረው አንቀጽ 16 ስር በንዑስ አንቀጽ 6 “… በቂ ምክንያት ሲኖር በህጉ መሰረት ክሱን ያነሳል…” በሚል ያስቀምጣል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 947/2008 ክስ ማንሳትን አስመልክቶ “… የፌደራል ጠ/ዐ/ሕግ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ጠ/ሚንስትሩን በማማከር ክስ ያነሳል፡፡ የተነሳም ክስ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡” የሚል ድንጋጌ አካቷል፡፡ የፍትሕ ሚኒስቴር በ2003 ባዘጋጀው የኢትየጲያ የወንጀል ፖሊሲ ላይ በገጽ 37 ክስ ማንሳትን አስመልክቶ “… ዐ/ሕግ የመሰረተውን የወንጀል ክስ ክርክር መቀጠል የህዝብና የመንግስት ጥቅምን አያስጠብቅም ብሎ ካመነ ለፍ/ቤቱ በማስታወቅ ክስን ማቋረጥ ይችላል፡፡ … በዐ/ሕግ ጥያቄ የተነሳ ክስ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የተቋረጠውን የክስ ሂደት የሚቀጥል መሆኑ…” በሚል አስቀምጧል፡፡
ከላይ የተመለከቱት ህጎች በጥቅሉ ክስ ማንሳት በመቀጠል ላይ ያለ የክርክር ሂደት ለሰፊና ለተሻለ ጥቅም ሊቋረጥ የሚችልበት ሥርዓት መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ በአንዳንድ የሕግ ስርኣቶች የወንጀል ክስ ለማስጀመር የግድ የጽሁፍ አቤቱታ መቅረብ ያለበት እንደመሆኑ መጠን (Accusatory principle) በፍ/ቤት ተቀባይነት አግኝቶ የተጀመረን ክርክር ዐ/ሕግ ማንሳት አይችልም፡፡ (Principle of immutability) በሌሎች የሕግ ስርዓቶች ክስን ለማንሳት አሳማኝ የሆነ ምክንያት በማቅረብ በፍ/ቤት ፈቃድ (Up on the consent of the court) ሊፈጸም ይችላል፡፡ የወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 122 በሁለቱ የሕግ ስርዓቶች መካከል የተቀመጠ ይመስላል፡፡ በመርህ ደረጃ በፍ/ቤት ፈቃድ በበቂ ምክንያት ክስ ማንሳት የሚቻል ሲሆን በከባድ ወንጀሎች ላይ ግን ክልከላ ተደርጎበታል፡፡
በአጠቃላይ በክስ ማንሳት ወቅት የዐ/ሕግ፤ የመንግስትና የፍ/ቤት ሚና እና ሀላፊነት ምንድን ነው? (ለማስቀጠልም-) ክስ ለማንሳትና ለማስቀጠል ተገቢ ሊሆን የሚችልና ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባ ምክንያት የቱ ነው? የሚሉት ነጥቦች በትኩረት መመርመር የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ህጎች ውስጥ በአንድ በኩል ክስን ለማንሳትና ለማስቀጠል በፍ/ቤት ፍቅድ ስልጣን ላይ ወጥ አቋም ባያንጸባርቁም ክስ ማንሳትና ማስቀጠል በቂ ምክንያት ሊኖረው ወይም የህዝብ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ያሰምሩበታል፡፡ የቀረበው ምክንያት ተገቢ መሆን አለመሆኑን ደግሞ መመርመር የፍ/ቤት ስልጣን ነው፡፡ በሌላ በኩል ፍ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ብይን ሲሰጥ ምክንያቱን ማስቀመጥ አለበት፡፡ ዐ/ሕግ አቤቱታውን ሲያቀርብም ምክንያት ማቅረብ ያለበት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
በዘፈቀደ ክስን ማንሳትና ማስቀጠል ከፍ/ቤት ነጻነት ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ የፍርድ ቤቶች ነጻነት አንድ ጉዳይ በፍ/ቤት ከቀረበ በኋላ ፍ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ባለሙሉ ስልጣን በመሆኑ በእያንዳንዱ ጉዳይ የመወሰን ስልጣንን ይጎናፀፋል፡፡ እንኳንስ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር በፍትሐብሔር ጉዳዮች እንኳ ክስ በፍ/ቤቱ ፈቃድ እና ያለፈቃድ ካነሳ በኋላ ማስቀጠሉ ላይ ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል፡፡ የፍ/ቤቱን ፈቃድ ለማግኘት ምክንያት ማቅረብ የሚያስፈልግ ሲሆን ከፈቃድ ውጭ ክስን ማንሳት ደግሞ ወደ ፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ሌላ አዲስ ክስ ማቅረብ እንዳይችል ያደርገዋል፡፡ (የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 278 – 279) በወንጀል የፍትሕ አስተዳደር ውስጥ በሁሉም መልኩ ሊባል በሚችል መጠን ትኩረትና ጥብቅ ቁጥጥር ያሻል፡፡
የጉዳዩን ጥቅል ይዘት በመመልከት ክስ ለማንሳትም ሆነ የተነሳ ክስ ለማስቀጠል ለህዝብ ጥቅም የተደረጉ መሆናቸውን ፍ/ቤቶች መገምገም አለባቸው፡፡ የክስ ማንሳትና ማስቀጠል ሥርዓት ተገቢ ላልሆነ አላማ እንዳይውል መከልከል አለበት፡፡ በወንጀል የፍትሕ አስተዳደር ላይ የአንድን ሰው የፍትሕ ሥርዓት ግንዛቤ እና እምነት በሚቃረን መልኩ መፈጸም የለበትም፡፡ የህዝብ ጥቅም፤ ፍትሐዊነት ቅንልቦና የሕግ ሥርዓት (ሂደት) (Public interest, Fairness, Good Faith (Bonafide) & Fairness) ታሳቢ ተደርገው የሚፈጸም ሥርዓት ነው፡፡ የማስረጃ ማነስን (Paucity of evidence) የግዜ፤ ገንዘብ እና የውጤታማነት ጉዳዮችን (Time ,money & chance of success) ታሳቢ ተደርጎ ክስ የማይነሳ ሲሆን በነዚሁ ታሳቢነትም አይንቀሳቀስም፡፡
በእኛ ሀገር የሕግ ሥርዓት የህዝብ ጥቅም / በቂ ምክንያት የሚሉት የትኞቹን ምክንያቶች ነው የሚለው በግልጽ በሕግ ወይም በፍርድ ተቀምጠው ባይገኙም በዳበሩ የሕግ ስርዓቶች ውስጥ እነዚህ ምክንያቶች በተለመደ ሁኔታ የትኞቹ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም፡-
ክሶቹ ፖለቲካዊ ወይም ግለሰባዊ በቀልን መሰረት አድርገው ቀርበው ሲገኙ፤ (Political & personal vendetta)
መንግስታዊ እና ህዝባዊ በሆነ ምክንያት ክስን ለመቀጠል የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች አለመኖር፤
በሁኔታዎች መቀያየር ምክንያት በክሱ መቀጠል ህዝብና መንግስትን የሚጎዳ ሆኖ ሲገኙ ናቸው፡፡
በክርክር ቀረቦ በተሰማ አንድ ጉዳይ ዐ/ሕግ የክስ ማንሳት አቤቱታ የቀረበ ሲሆን ምክንያቱም “ተጨማሪ ማጣራት የሚገባን ጉዳይ ስላገኘን” የሚል ነበር፡፡ ፍ/ቤቱም የቀረበውን ምክንያት ሳይመረመር በጥቅሉ ተቀብሎት ክሱ ተቋርጧል፡፡ በሌላ ግዜ በተመሳሳይ ጉዳይ ዐ/ሕግ ክስ እንዲንቀሳቀስ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን የሰጠው ምክንያትም 1ኛው ምስክር ቃሌን አቃናለሁ ያለ በመሆኑ መዝገቡ ይንቀሳቀስ ምስክሮች እንደ አዲስ ይሰሙልኝ በሚል ነው፡፡በመሰረቱ የቀረበው ምክንያት አሳማኝ እና ለህዝብ ጥቅም የተደረገ ስለመሆኑ ከመመርመሩ በፊት ክስ ለማንሳት የቀረበው ምክንያትና ክስ ለማስቀጠል የቀረበው ምክንያት የተለያዩ ናቸው፡፡ በሌላ በ

ኩል በክርክሩ ሂደት ተሰምተው የተመለሱ ምስክሮችን ክስን በማቋረጥ እንደገና ቀርበው እንዲሰሙ ማድረግ የክርክር አመራር ስርኣትን ያልተከተለ እና ህገ ወጥ ነው፡፡በአጠቃላይ የክስ ማንሳትና ማንቀሳቀስ የዐ/ሕግ ያልተሸራረፈ መብት ሳይሆን በሕግ መሰረት በተቋቋሙ ፍ/ቤቶች የሚመራ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡
Mr zee
ምንጭ
የወንጀል ሕግ እና ስነስርዓቱ
በይነ መረብ
Mr zee
ምንጭ
የወንጀል ሕግ እና ስነስርዓቱ
በይነ መረብ
ሥለ ጦር መሣሪያ ሕግ
ማን፣ ምን መታጠቅ ይችላል?
መንግሥት የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የሕዝብን መብትና ደህንነት ለማስከበር የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥርን በተመለከተ አዲስ ሕግ ማውጣት አስፈልጎኛል ብሏል።
ረቂቅ አዋጁም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ታህሳስ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጸድቋል።
"ተቆጣጣሪ ተቋም" ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ውክልና የተሰጠው የክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሥሩ ብሔራዊ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሥራ ክፍል አደራጅቶ አዋጁን ያስፈጽማል።
ለመሆኑ ይህ ሕግ ምን ይላል? ማን፣ ምን፣ እንዴት መታጠቅ ይችላል? ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል?
የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው?
የጦር መሳሪያ ፍቃድ እና ሁኔታ?
ለግለሰብ የሚፈቀደው አንድ አነስተኛ ወይም አንድ ቀላል የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። ለድርጅትም ቢሆን የሚፈቀደው የጦር መሳሪያ አይነት አነስተኛ ወይም ቀላል የጦር መሳሪያ ሲሆን፤ ዝርዝሩ እና የጥይት ብዛት በተቆጣጣሪው ተቋም በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል።
የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተጠየቀበት የጦር መሳሪያ ከዚህ ቀደም በሌላ ሰው ስም ፈቃድ ያልወጣበት እና የጦር መሳሪያው ወንጀል ያልተሰራበት መሆን አለበት።
ፍቃድ የሚሰጥባቸው መስፈርቶች
በተቆጣጣሪ ተቋሙ የሚወጣውን ዕድሜ የሚያሟላ፣ ቋሚ አድራሻ እና መተዳደሪያ ገቢ ያለው
ኢትዮጵያዊ የሆነ ወይም በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር ፍቃድ ያለው
1 ከጦር መሳሪያ አያያዝ ጋር ያሉ ሕጎችን ግዴታዎች መወጣት የሚችል
2 ለጦር መሳሪያ ፍቃድና እድሳት አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍል
3 ከሚኖርበት አካባቢ አስተዳደር መልካም ሥነ ምግባር ያለው ለመሆኑ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤ የሚሉ መስፈርቶች ይገኙበታል።
የተከለከሉ ተግባራት
ሀ በዚህ አዋጅ መሰረት ከተፈቀደለት ሰው ውጪ ማንኛውም ሰው፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ እና መለዋወጫዎች ወይም አብረው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መሳሪያዎችን፣ ወደ ሀገር ማስገባት እና ማስወጣት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ መገልገል፣ መደለል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማስተላለፍ፣ ማዘዋወር . . . ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ይገኙበታል።
የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የማይቻልባቸው ሥፍራዎች
1 ሰላማዊ ሰልፍ ወይም አድማ በሚደረግባቸው ሥፍራዎች
2 በምርጫ ሥፍራዎች
ሆቴል፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ሙዚየሞች እና ተመሳሳይ በሆኑ የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች
3 በትምህርት እና ሃይማኖት ተቋማት ግቢ ውስጥ
3 ሆስፒታል፣ መሥሪያ ቤቶች . . . የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ሥፍራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
መሳሪያ ታጥቀው ከላይ ወደ ተጠቀሱት ሥፍራዎች መግባት ካሰቡ በቅድሚያ የጦር መሳሪያውን ለተቋማቱ የጥበቃ ሰራተኞች ማስረከብ ይኖርብዎታል።
mr zee
ምንጭ
የጦር መሠሪያ አዋጅ

ጤና ይስጥልኝ
ከዚህ ቀደም በ“የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 " ድንጋጌ ላይ በመነሳት በሠራዊቱ ዉስጥ አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞችን በማሳየት በአዋጁ ላይ ስለተቀመጡት የማዕረግ ደረጃዎች እና ስለሚሰጡ ሽልማቶች ጽሑፍ እንደምናቀርብ ቃል በገባነዉ መሠረት፤ አነሆ፡-
መልካም ንባብ፡-
የመከላከያ ሠራዊት በምድር፤ በአየር፤ በባህር ኃይል እና በልዩ ዘመቻዎች ኃይል የሚደራጅ ሆኖ እንደአስፈላጊነትም የስፔስና የሳይበር ኃይሎችን ሊያካትት እንደሚችል የተደነገገዉ ቢኖርም በአዋጁ ላይ የማዕረግ ደረጃዎቻቸዉ ተዘርዝሮ የምናገኘዉ የምድር እና የአየር ኃይልን በመሆኑ ይህንኑ እንደሚከተለዉ እናሰፍረዋለን፡-
የማዕረግ ደረጃዎች
በምድር ኃይል
ሀ) ምክትል አስር አለቃ ቸ) ምክትል መቶ አለቃ
ለ) አስር አለቃ ኀ) መቶ አለቃ
ሐ) ሃምሳ አለቃ ነ) ሻምበል
መ) መጋቢ ሃምሳ አለቃ ኘ) ሻለቃ
ሠ) ሻምበል ባሻ አ) ሌተናል ኮሎኔል
ረ) ሻለቃ መጋቢ ባሻ ከ) ኮሎኔል
ሰ) ሻለቃ ባሻ ኸ)ብርጋዴር ጀነራል
ሸ) ጁኒየር ዋራንት ኦፊሰር ወ)ሜጀር ጀነራል
ቀ) ሲኒየር ዋራንት ሶፊሰር ዐ) ሌተናል ጀነራል
በ) ማስተር ዋራንት ኦፊሰር ዘ) ጀነራል
ተ) ቺፍ ዋራንት ኦፊሰር
በአየር ኃይል
በአየር ኃይል የማዕረግ ደረጃዎች ከጁኒየር ዋራንት ኦፊሰር እስከ ጀነራል ድረስ ያሉት (ከፊደል ሸ እስከ ፊደል ዘ) ተመሳሳይ ሆነዉ ከጀነራል ዋራንት ኦፊሰር በታች ያሉት የአየር ኃይል የማዕረግ ደረጃዎች የሚከተለዉ ይሆናል፡-
ደረጀ ማርቆስ ጥር 2013 ዓ.ም

ሀ) ጁኒየር ኤርክራፍት ማን ሠ) ሲኒየር ቴክኒሺያን
ለ) ሲኒየር ኤርክራፍት ማን ረ) ሊዲንግ ቴክኒሺያን
ሐ) ሊዲንግ ኤርክራፍት ማን ሰ) ማስተር ቴክኒሺያን
መ) ጁኒየር ቴክኒሺያን
ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ሜዳይ ሪቫንና የምሥክር ወረቀትና ከዚሁ ጋርም ልዩ መብት ያለ ሲሆን ይህንኑ እንደሚከተለዉ እንመልከተዉ፡-
ሀ)የአድዋ ድል ሜዳይ
ለ) የአዉደ ዉጊያ ጅግና ሜዳይ አንደኛ ደረጃ
ሐ) የአዉደ ዉጊያ ጅግና ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ
መ) የአዉደ ዉጊያ ጅግና ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ
ሠ) የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ባለዘንባባ
ረ) የትግል ተሳትፎ ሜዳይ ያለ ዘንባባ
ሰ) የላቀ የሥራ ዉጤት ሜዳይ
ሸ) የዉትድርና አገልግሎት ሜዳይ አንደኛ ደረጃ
ቀ) የዉትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሁለተኛ ደረጃ
በ) የዉትድርና አገልግሎት ሜዳይ ሦስተኛ ደረጃ
ተ) ዓለም አቀፍ የሰላም ማስጠበቅ ሜዳይ
ቸ) የአዉደ ዉጊያ ቁስለኛ ሜዳይ
ኘ) የዉትድርና አገልግሎት ሪቫን
ኀ) የዉትድርና አገልግሎት ሪቫን
ነ) የዉጊያ ተሳትፎ የምስክር ወረቀት
ሲሆኑ ከዚህ በላይ በፊደል (ሀ)፤ ከፊደል (ለ) እስከ (መ) የተጠቀሱትና በፊደል (ሰ) የተጠቀሰዉ የገንዘብ ወይም የዓይነት ሽልማትም የሚያስገኙ መሆናቸዉንም ልብ ይሏል፡፡

ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ በዛሬ ጽሁፋችን ስለ ዋስትና ስናነሳ ባለእዳዉን በተመለከተ በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ስለማይወሰዱ ሃብቶች አቅርበናል መልካም ንባብ፡-
ከዉልም ሆነ ከዉል ዉጭ በሚመነጭ ግዴታ የባለዕዳዉ ንብረት ከእርሱ ላይ ገንዘብ ሊጠይቁ ለሚችሉ ባለመብቶች ሁሉ የጋራ መያዣቸዉ ነዉ፡፡ ባለገንዘቦቹ ከባለዕዳዉ ጋር የተለየ ስምምነት ማድረግ ሳያስፈልጋቸዉ ባለገንዘብ በመሆናቸዉ ብቻ የዚህ መብት ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ በባለዕዳዉ ላይ የሚያቀርቡትን ጥያቄ በፍርድ ካረጋገጡ አፈጻጸሙን በንብረቱ ላይ በፍ.ብ.ሕ.ቁ 1988(1) መሠረት ለባለዕዳዉ ግዴታ አፈጻጸም ማረጋገጫ የሚሆነዉ ሊያዝበት አይገባም ተብሎ በሕግ ከተደነገገዉ በቀር የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል፡፡
ህድአት ጥር/2013 ዓ.ም

እነዚህ ባለገንዘቡ መብቱን/ገንዘቡን የማይጠይቅባቸዉ ወይም በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት የማይወሰዱ የባለዕዳዉ ንብረቶች/ሃብቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
• ለፍርድ ባለዕዳዉና ለቤተሰቡ የዕለት አገልግሎት የሚጠቅሙ ልብሶች የምግብ ማብሰያ የሆኑ የቤት ቁሳቁስ የመኝታ አልጋ የአልጋ ልብሶችና የብርድ ልብሶች
• ለዕለት ሞያ ሥራዎቹ አገልገሎት ለንግድ ሥራዉ ማከናወኛ ተገቢ የሆኑ ዕቃዎች
• የፍርድ ባለዕዳዉ ገበሬ ወይም በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ሲሆን በፍርድ ቤቱ አስተያየት ለዚሁ ሥራዉ አገልግሎት በቂ ሆነዉ የሚገመቱ የቀንድ ከብቶች የዘር እሕልና ሌላም ፍጹም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች
• ለራሱና ለቤተሰቡ ለሶስት ወር መተዳደሪያ የሚበቃ ገንዘብና ለዕለት ምግብ ጠቃሚ የሚሆን ሥንቅ
• ለጡረታዉ የሚከፈለዉ ገንዘብና ባል ሚስቱን ከፈታ በኋላ ለወር ቀለቡዋ የሚከፍላት ገንዘብ
• የፍርደ ባዕዳዉ የወር ደመወዝ ሁለት ሶስተኛዉ እጅ
• እንዳይበር እንዳይሸጥና ለዕዳ መክፈያ እንዳይሆን በማናቸዉም ሕግ ላይ የተወሰነ ማናቸዉም ዓይነት ሀብት ወይም ንብረት
ምንጭ የኢትዮጵያ ዉል ሕግ መሰረተ ሀሳቦች/ጥላሁን ተሾመ/
የፍ.ብ.ሕ
የፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ

ዉድ አንባቢያን የጥላቻ ንግግር፤ የሐሰት ወሬ እና የሐሰት መረጃ ይዋል ይደር እንጂ እዉነቱ መዉጣቱ የማይቀርና ይህንን በሚጠየፍ ሕብረተ-ሰብ ዘንድም የማህበራዊ ቅጣትን የሚያስከትል መሆኑ እንዳለ ሆኖ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊትም በሕግም ቅጣት ሊጣልበት ግድ የሚለዉ በመሆኑ " የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ቁጥር 1185/2012" ወጥቶ ሥራ ላይ የዋለና እኔም በዚህ ላይ መጠነኛ ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳ ዘንድ የሚከተለዉን ለማቅረብ ወደድኩ፡-
መልካም ንባብ
የዲሞክራሲ መብቶች ከሆኑት አንዱ ሀሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ ቢሆንም ይህ መብት ግን ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የሚደረግለትን ያህል በአጠቃቀም ረገድ በሌላ ሰዉ ላይ ወይም የጦርነት ቅስቀሳን የሚያነሳሳ የጥላቻ ንግግር ማድረግን ወይም የሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨትን በሕገ-መንግሥቱም ሆነ ከዚህ በላይ በገለጽኩት አዋጅ ቁጥር 1185/2012 የተከለከለና ቅጣት የሚጣልበት መሆኑን ስንገልጽ ከዚህ አንጻር የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፤ በሕትመት ወይም በማሕበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሑፍ ፤ በምስል፤ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት መሆኑንና ይህም የተከለከለ መሆኑን፤
የሐሰት መረጃን ማሰራጨት ማለት ደግሞ የሐሰት መረጃዉን በአደባባይ ስብሰባዎች በብሮድካስት፤ በሕትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በጽሑፍ፤ በምስል፤ በድምጽ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለ መሆኑን እና አነዚህኑ ማለትም ሐሰተኛ መረጃዎች ማሰራጨት እስከ አንድ መቶ ሺህ ብርና እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስራት መቀጮን የሚያስከትል ይሆናል፡፡
ህድአት ጌታቸዉ
የካቲት/2013 ዓ.ም

Election ppt Omi.pptx
450.9 KB
ዳሬክቶሬታችን ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ አንዱ በተለያዩ ሕጎች ዙሪያ ነዋሪው በሕገ መንግስቱና በቻርተሩ የተሰጡትን መብቶችና ነጻነቶች እንዲያውቅና እንዲጠቀም ተገቢውን የሕግ ስልጠና ይሰጣል፡፡በዚህም መሠረት በየካቲት 10 እና 11 ቀን 2013 ዓ.ም የዳሬክቶሬቱ 2 ዐቃቤ ሕጎች በ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ተያያዥ ሕጎች ዙሪያ ለቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 እና 4 ምክር ቤት የሰጠውን ስልጠና በተመለከተ ለእናንተም በርዕሱ ላይ የተነሱትን ነጥቦች ለማጋራት ስለወደድኩኝ ስልጠናው ላይ የተነሱ ነጥቦችንና የተሳታፊዎችን ፎቶ በመጨመር ከታች አስፍሬላችኋለው፡፡
የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቶች በአዋጁ መግቢያ ላይ የተዘረዘሩ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች በመዋሀድ፣ ግንባር በመፍጠር ወይም በመቀናጀት ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ለመደንገግ፣ለፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሥርዓት መስፈን በምርጫ የሚሣተፉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ዕጩዎች ገንቢ አስተዋጽኦ የሚያደርጉበትን ግልፅ አሰራር ለመዘርጋት፣ምርጫዎች በመልካም ሥነ ምግባር የሚመሩ ነጻ፣ ፍትሃዊ ፣ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆኑና እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኙ ለማድረግ በምርጫ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣እጩዎች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የሚመሩባቸውን የሥነ ምግባር መርሆች ለመደንገግእና በምርጫ ሂደት ለሚነሱ አለመግባባቶች አስተዳደራዊ እና የዳኝነት መፍትሔ የሚሰጡ ተቋማትን እና አሰራራቸውን ለመወሰን የሚሉት ይገኙበታል፡፡
የአዋጁ ተፈፃሚነት ወሰኑን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጠቅላላ ምርጫ እንዲሁም እንደ አግባብነቱ የአካባቢ ምርጫ፣ የማሟያ ምርጫ፣ የድጋሚ ምር

…የድጋሚ ምርጫ እና በሕገ መንግሥቱ መሠረት በሚካሄድ ሕዝበ ውሳኔ ላይ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ ለሚመሠርቱ ዜጎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ኃላፊዎች፣ አባላት፣ ወኪሎች እና ተጠሪዎች፣ የፓርቲና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፣ ግንባር ወይም ውህደት ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን በአዋጁ አንቀጽ 3 የተደነገገ ሲሆን የምርጫ ሥርዓትን በተመለከተ በፌደራል ሕገ መንግስታት እና በክልል ሕገመንግስታት የሚል ክፍፍል ቢኖርም የክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫን የሚመለከቱ የክልል ሕጎች በሕገ መንግሥቱና በአዋጁ ከተቀመጡ ምርጫን የተመለከቱ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣሙ መሆን እንዳለባቸው በአንቀጽ 4 ስር ሰፍሯል፡፡
ስለ ምርጫ መርሆዎች፣በኢትዮጵያ ስለሚካሄዱ የምርጫ ዓይነቶች፣ስለ ምርጫ ማስፈጸሚያ አደረጃጀቶች፣ስለ መራጮች እና ዕጩዎች መብትና ገዴታ፣ስለ ምርጫ ዘመቻ፣ስለ የድምፅ ቆጠራና ውጤት አገላለፅ፣በምርጫ ወቅት ስለሚነሱ አቤቱታዎችና መፍትሔዎቻቸው እንዲሁም ደግሞ በምርጫ ሂደት ስለ ተከለከሉ ተግባራትና ቅጣቶች ሌሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ የተደረገባቸው ነጥቦችን ሲሆኑ በሁለቱም ቀን የነበሩት ተሳታፊዎቻችን በጥሞና ያዳመጡንና ስልጠናው ሲያልቅም ያነሷቸው ጥያቄዎች ጥሩ የስልጠና እና የውይይት መድረክ ኢንዲኖር ስላደረገ ተሳታፊዎቻችንን እመሰገንኩኝ የተነሱት ነጥቦችን በተመለከተ ከተዘጋጀው power point ማግኘት ስለሚቻል ከታች power pointውን ስላሰፈርኩላችሁ መልካም ቀን በመመኘት ለዛሬ አበቃው፡፡
ሰናይ ዕለተ አርብ ቀን 12/06/2013 ዓ.ም! (ኦምኒኤል)

ስለንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ሕግ (ክፍል አንድ)
መግቢያ
ሀገራት ከሚከተሉት የኢኮኖሚ ሥርዓት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ወይም የዕዝ ገበያ ኢኮኖሚ ስርዓት በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን ሁለቱንም የገበያ ኢኮኖሚ ባማከለ መልኩ የቅይጥ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓትም ተጠቃሽ እንደሆነ ከተለያዩ ፅሁፎች መረዳት ይቻላል፡፡ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት የንግዱን ህብረተሰብ ከፀረውድድር እና ተገቢ ካልሆኑ የገበያ ተግባራት እንዲሁም ሸማቹን ከሚያሳስቱ የገበያ ሁኔታዎች የሚከላከል ሥርዓት መዘርጋት እና ለነፃ ገበያ ውድድር አመቺነት ያለው ሥርዓት ማስፈን አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ የንግድ እንቅስቃሴዎች ማደግን ተከትሎ የሸማቾችን ጤንነትና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የንግድ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን መስፋፋት ለመግታት እንዲቻልና ተጠቃሚዎች ላወጡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆኑ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት እና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረው የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ታውጇል፡፡ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃን ስናስብ ነጋዴዎች እና ሸማቾች የገበያው ተዋንያን በመሆናቸው በዋናነት በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት ሊኖራቸው የሚገባ መብትና ግዴታዎቻቸውን በቅጡ ሊያውቁት ይገባል፡፡
ስለ ነፃ ገበያ ምንነት
ዓለማችን የምትመራባቸው ሶስት የኢኮኖሚ ሥርዓቶች ሲኖሩ አነሱም፡- የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ፣ የዕዝ ገበያ ኢኮኖሚና የቅይጥ ገበያ ኢኮኖሚ በመባል ይታወቃሉ፡፡ የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት ማለት ገበያው ያለመንግስት ጣልቃ ገብነት እራሱን በራሱ የሚመራበት ስርዓት ማለትም ነጋዴዎች መንግስት በሚያወጣላቸው ዕቅድና መመሪያ ሳይሆን በተጨባጭ በገበያ ላይ ባለ ፍላጎትና አቅርቦት መሰረት መስራት የሚያስችላቸው ስርዓት ነው፡፡ የእዝ ገበያ የኮኖሚ ስርዓት የሚባለው ሀገራችን በደርግ ዘመነ መንግስት ትከተለው የነበረ የኢኮኖሚ ስርዓት ሆኖ ገበያው የሚመራው በፍላጎትና አቅርቦት ኃይሎች ባለ ነፃ መስተጋብር ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ኖሮበት የሚመራ የገበያ ስርዓት ነው፡፡ የቅይጥ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት የሚባለው ደግሞ የነፃ ገበያና የዕዝ ኢኮኖሚ የገበያ ስርዓቶች ድብልቅ ሆኖ ሁለቱም አካላት የየራሳቸው ሚና መጫወት የሚያስችል የገበያ ምህዳር ሲኖር ማለት ነው፡፡
ከአዋጁ መግቢያ መገንዘብ እንደሚቻለው ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትመራው በነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት ነው፡፡ የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት ትከተላለች ማለት ግን የንግዱን ዘርፍ ልቅ መተው ማለት አይደለም፡፡ የሀገር ኢኮኖሚ አደጋ ላይ እንዳይወድቅና ሸማቹ ማህበረሰብ እንዳይጎዳ ቁጥጥርና ወጥ የሆነ ስርዓት ማበጀት ከመንግስት በእጅጉ ይጠበቃል፡፡
ስለሸማቾች ጥበቃ እና ስለንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ስርጭት
የሸማች መብቶች (አንቀጽ 14)
ሸማች ማለት ለማምረት ሥራ ወይም መልሶ ለመሸጥ ሳይሆን ዋጋዉን ራሱ ወይም ሌላ ሰዉ የሚከፍልለት ሆኖ ለራሱ ወይም ለቤተሰቡ ፍጆታ የሚሆን የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚገዛ የተፈጥሮ ሰው ነው (አን. 2(4))፡፡ ማንኛውም ሸማች እንደ ሸማች የተለያዩ መብቶች በአዋጁ መሠረት የተቀመጠ ሲሆን እኚም መብቶች፡- መረጃ ወይም መግለጫ የማግኘት፣ አማርጦ የመግዛት፣ እንዲገዛ ያለመገደድ፣ በአክብሮት የመስተናገድ እና ካሣ እንዲከፍሉት የመጠየቅ ናቸው፡፡
ሀ. መረጃ ወይም መግለጫ የማግኘት መብት፡- ማንኛውም ሸማች ስለሚገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ጥራትና አይነት አስመልክቶ በቂና ትክክለኛ መረጃ ወይም መግለጫ የማግኘት መብት አለው፡፡
ለ. አማርጦ የመግዛት መብት፡- ሸማች መግዛት ወይም መሸመት የሚፈልገው የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህን ለመሸመት የሚፈልጋቸውን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን አማርጦ የመግዛት መብት አለው፡፡
ሐ. እንዲገዛ ያለመገደድ፡- የዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ጥራት ወይም አማራጮችን ጥራት ወይም አማራጮችን በማየቱ ወይም የዋጋ ድርድር በማድረጉ ምክንያት እንዲገዛ ያለመገደድ መብት አለው፡፡
መ. በአክብሮት የመስተናገድ መብት፡- ሸማች ወይም ገዢ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በሚፈልግበት ጊዜ፣ በሚመርጥበት ጊዜ እና በሚገዛበት ጊዜ በትህትናና በአክብሮት የመስተናገድ መብት ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ሸማች በነጋዴው ከሚደርስበት የስድብ፣ የዛቻ፣ የማስፈራራት እና የስም ማጥፋት ተግባር የመጠበቅ መብት አለው፡፡
ሠ. ካሣ እንዲከፍሉት የመጠየቅ መብት፡- ሸማች ወይም ገዢ የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በመግዛቱ ወይም በመጠቀሙ ምክንያት የደረሰበት ጉዳት ካለ፣ ለደረሰበት ጉዳት ካሳ የማግኘት መብት አለው፡፡ ይህን ካሳ የመክፈል ግዴታ ያለባቸው በአምራችነት፣ በአስመጪነት፣ በጅምላ ሻጭነት፣ በችርቻሮ ሻጭነት ወይም በሌላ ማንኛውም ሁኔታ በአቅርቦቱ የተሳተፉ ሰዎች ናቸው፡፡ ሸማቹ ከነዚህ አካላት በተናጠል ወይም በጋራ ካሳ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
ይቀጥላል
ፌናን ተጊበሉ
የካቲት 15/2013 ዓ.ም

በዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ዉስጥ ሦስት የሥልጣን አካለት ያሉና እነዚህም አባላት የየራሳቸዉ የሆነ ሥልጣንና ተግባር ያላቸዉና እርስ በ'ርሳቸዉም አንዱ ሌላዉን ያለአግባብ እንዳያከናዉን የሚቆጣጠሩ (check and balance) ሆነዉ የሚቋቋሙ ሲሆን አነዚህም አካላት፡- ሕግ አዉጪ (ፓርላማ) ፤ ሕግ አስፈጻሚ (ጠቅላይ ሚኒስትሩና የሚኒስትሮች ምክር ቤት) እና ሕግ ተርጓሚ (ዳኝነት) ናቸዉ፡፡
ለዚህ ጽሑፍ የምንመለከተዉ የሕግ ተርጓሚዉንና ዳኝነቱን ከፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና በተለይ አሁንና ወደፊት ልናቀርባቸዉ ስለአሰብነዉ የሰበር ችሎቶች የተደነገገበት አዋጅ ቁጥር 454/1997 የአዋጆቹ መንፈስ የተወሰነ በማቅረብ ለወደፊቱ የሰበር ችሎቱ የሰጣቸዉን አንዳንድ ዉሣኔዎችና በማቅረብ ይሆናል፡፡
መልካም ምንባብ፡-
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78 እና ተከታዮቹ አናቅጽት ነጻ የዳኝነት አካል እንደሚቋቋም በተደነገገዉ መሠረት የፌደራል ፍ/ቤቶች አ/ቁጥር 25/1988 የወጣና ይህዉ አዋጅም በአዋጅ ቁጥር 138/91፤ በአዋጅ ቁጥር 321/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 454/1997 ተሻሽሎ እየተሰራበት የሚገኝ ሲሆን አሁን ከያዝነዉ ጉዳይ አንጻር በአ/ቁጥር 25 እና በአ/ቁጥር 454 ላይ ስለተጠቀሰዉ የሰበር ችሎት ስንመለከት በፍርድ ቤት ታይተዉ የመጨረሻ ዉሣኔ የተሰጠባቸዉና መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለባቸዉን ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሰጠዉ የሕግ ትርጉም በየትኛዉም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ያለዉ ዉሣኔ የሚሰጥ ሲሆን ይህንኑ የአስገዳጅነት ዉሣኔም ፍ/ቤቶች አንደ ሕግ ወስደዉ ዉሣኔ የሚሰጡበት መሆኑን ለግንዛቤ ስንገልጽ ለወደፊቱ ይህዉ የሰበር ሰሚ ችሎት ከሰጣቸዉ ዉሣኔዎች የተወሰኑትን እንደምናቀርብ በመግለጽ ተሰነባበትን፡፡
ደረጀ ማርቆስ
የካቲት 2013

በኢትዮጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 46 መሠረት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
ቤተ ክርስትያኖች፤ መስጊዶች፣ወታደራዊ ካምፖች እና ፖሊስ ጣቢያዎች የመማር ማስተማር ሂደት ተግባር እየተከናወነ በሚገኝበት ወቅት በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ በ2 መቶ ሜትር ርቀት ዙሪያ፤ ህዝብ የዕለት ተለት ግብይት በሚፈፅምባቸው እና በተወሰኑ ቀናት በገጠርም ሆነ በከተማ በይፋ ገበያ እየተካሄደ በሚገኝባቸው ቦታዎች በ2 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤ የመንግሥት ወይም የህዝብ መደበኛ ሥራ በመከናወን ላይ የሚገኙባቸው የመንግሥትና የህዝብ ተቋማት ሥራቸውን በሚያከናውኑበት መደበኛ የሥራ ሰዓት እና ቦታ፣ እንዲሁም ሌላ ህዝባዊ ስብሰባ እየተካሄደ ባለባቸው ቦታዎች እና አካባቢዎች፡፡
ሰናይ ዕለተ ማክሰኞ!(16/06/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)

በኢትዮጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 134 መሠረት ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ማንኛውንም ዓይነት ማስፈራራት ወይም ወከባ የተከለከለ መሆኑን ተቀብሎ የፓርቲው ኃላፊዎች፣ እጩዎች፣ አባላት እና ደጋፊዎች መቼም ቢሆን ማንንም ሰው የሚያስፈራሩ፥ የሚያሸማቅቁና የሚያዋክቡ ድርጊቶችን እንዳይፈጽሙ የሚከለክሉ መመሪያዎች ማውጣት፤አመፅንና አመጽ ቀስቃሽ ድርጊቶችን መቃወምና አባላቱንም ማስተማር፤ በኃላፊዎቹ፣ በእጩዎቹ፣ በአባላቱ ወይም በደጋፊዎቹ የሚፈፀሙ አውዳሚ ወይም ሰላምን የሚያናጉ ድርጊቶችን ወይም ይህን የሚጋብዝ ዛቻን በመቃወም ማስተማር፤የሌላውን ግለሰብ ሆነ ፓርቲ መብት፣ ንብረትና ጥቅሞች ማክበር ያለበት ሲሆን ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የፓርቲው ኃላፊዎች፣ እጩዎች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ለፖለቲካ የድጋፍ ሰልፍ፥ ለስብሰባ፣ የእግር ጉዞ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ ማናቸውንም ባህላዊ ወይም ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች መያዝ ክልክል መሆኑን ማስተማር፤ አለበት፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ በማንኛውም የሁከት ወይም የአመጽ እንቅስቃሴ መሳተፍ ወይም እንዲደረግ መፍቀድ የለበትም፤በህዝብ ወይም በግለሰብ ንብረት ላይ ውድመት እንዳይደርስ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ መከላከል አለበት፤ እንዲሁም ደግሞ ደጋፊዎቹ በአዋጁ ላይ የተደነገጉ ማናቸውንም ክልከላዎች እንዲጥሱ ማነሳሳት የለበትም፡፡
ሰናይ ዕለተ ማክሰኞ!(16/06/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
ሰናይ ዕለተ ማክሰኞ!(16/06/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)