የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
ጤና ይስጥልኝ ፡-
ግለሰቦችም ይሁኑ አበዳሪ ተቋማት በብድር ዉላቸዉ ላይ ባመለከቱት ወለድ ብቻ እንደሚገደዱ የሚከተለዉን እናቅርብ
መልካም ምንባብ፤
ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ወለድን አስመልክቶ በዉላቸዉ ካመለከቱት ሃሳብ ዉጪ የራሱን ስሌት መሰረት በሚደረግ ዉሳኔ መስጠት እንደማይችል በፍትሐ-ብሔር ሕጉ ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ሐምሌ 2013ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ
ከጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚሀ በፊት የነበረውን የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 እና አዋጁን ለማሻሻል የወጡትን ማሻሻያዎችን በመሻር ተግባር ላይ የዋለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 የፍትሐብሔር የዳኝነት ሥልጣንን በተመለከተ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሚከተሉት የፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ሠልጣን ይኖራቸዋል፡-
1. የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ ጉዳዮች፤
2. የውጭ ሀገርን ፍርድ ወይም ብይን ማስፀም በሚቀርብ አቤቱታ፤
3. ዜግነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ ክርክሮች፣
4. ከመክሰር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች፤
5. ዓለም አቀፍ የዲኘሎማቲክ ሕጎችና ልምዶች እንዲሁም ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የውጭ ሀገር አምባሳደሮች፣ ቆንስላዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ መንግሥታት ወኪሎች ተጠያቂ በሆኑባቸው ወይም/እና ልዩ መብትና ጥበቃ ያላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ሰዎች ተከራካሪ በሆኑበት ጉዳዮች፣
6. የፌደራል መንግሥት አካል ተከራካሪ በሆነበት ጉዳይ
7. የፌደራል መንግሥቱን ንብረቶች በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች፤
8. መደበኛ ነዋሪነታቸው በተለያዩ ክልሎች፣ በክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ፣ በክልል እና በድሬዳዋ ከተማ፣ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚነሱ ጉዳዮች፣
9. የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣኖችና ሠራተኞች በስራቸዉ ወይም በሃላፊነታቸዉ ምክንያት ኃላፊ በሚሆኑባቸው ጉዳዮች፣
10. በፌደራል መንግሥቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮች፣
11. የሚተላፉየገንዘብ ሰነዶች በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች
12. በፈጠራ፣ በድርሰትና ሥነ ጥበብ፣ ቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ባለቤትነት በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች
13. የኢንሹራንስ ውልን በተመለከተ የሚነሱ ክርክሮች፣
14. ተገዶ የመያዝ ሕጋዊነትን ለማጣራት የሚቀርብ አቤቱታ፤
15. ለከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች በቻርተር አዋጅ የተሰጣቸው የፍትሀብሔር ዳኝነት ሥልጣን ማለትም በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መታዎቂያ ወረቀት ህግ መሠረት በሚሰጥ ሰነድ ጋር በተያያዘ፣ ከስም ለውጥ፣ ከመጥፋት፣ የፍርድ ክልከላ፣ የባልነት ሚስትነት የአሳዳሪነት የሞግዚትነት ማስረጃ ይሰጠን ጉዳይ፣ የከተማው አስተዳደር ከሚያስተዳድረው ቤት ጋር በተያያዘ በሚነሳ የይዞታ ወይም የባለቤትነት ወይም ሌላ ማንኛውም ክርክር፣ በከተማው ውስጥ ከሚገኝ እዴድር ጋር በተያያዘ የመዲኘት ሥሌጣናቸው እንዯተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪ በግሇሰቦች መካከሌ የሚደረጉ እስከ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የገንዘብ፣ ውል፣ እና ብድር ክርክሮች የሚመለከቱ ሆኖ ቀሪ በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች የሚነሱ የፍትሀብሔር ክርክሮች በ,ፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚዳኙ ይሆናሉ፤
16. በሌሎች ሕጎች የተጠቀሱ ጉዳዮች፡፡
የክልል ጉዳይ በክልሉ ፍርድ ቤት እየታየ እያለ ወይም ከተወሰነ በኋላ ከላይ በቁጥር 8 እና 13 ሥር የተጠቀሱት ተከራካሪ በማንኛወውም ሁኔታ ወደ ክርክሩ ቢገባ እንኳ ጉዳዩ በክልሉ ፍርድ ቤት መታየቱ ይቀጥላል፡፡
ቸር ያሰማን! (28/11/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
የንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 ከሸማቹ ማህበረሰብ አንጻር የሚከተሉት አላማዎች ይኖሩታል
• ሸማቹን ከሚያስቱ የገበያ ሁኔታዎች ለመከላከል
• የሸማቾችን ጤንነትና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን መስፋፋት መግታት
• ደህንነታቸዉንና ሌጤና ተስማሚ መሆናቸዉን በዘላቂነት ማረጋገጥ
• ተጠቃሚዎች ላወጡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆኑ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነዉ
ህድአት
ነሃሴ/2013 ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ ፡-
በኢትዮጵያ የፍትሐብሔር ሕግ የሟች ዉርስ በኑዛዜ ወይም ያለኑዛዜ ሊተላለፍ እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን ሟቹ ንብረቱን ለተወላጆቹ ወይም ተወላጆቹ ላልሆኑ ሰዎች በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን ስለዚሁ የኑዛዜ አንዳንድ ሁኔታዎች የሚከተለዉን እንበል፤
መልካም ምንባብ፡-
በሕጋችን ሦስት ዐይነት የኑዛዜ ፎርሞች ያሉና ተናዛዡ አለኝ የሚለዉን ንብረት ከሦስቱ ፎርማቶች በአንዱ ለኑዛዜ ተጠቃሚዉ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን ተናዛዡ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ (ልጆች) የሆኑትን “በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥረዉብኛል “ በሚል በቂና ሕጋዊ ባልሆነ ምክንያት ወይም በዝምታ ከዉርሱ መንቀሉም ሆነ ሟቹ ካለዉ ሀብት ላይ እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ ተወላጁ ተነቅሏል ተብሎ ግንዛቤ ሲያዝበት የሚችል በመሆኑ ከዚህ በላይ የተገለጸዉ ከሆነ ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት መሆኑን ከፍ/ብ/ሕጉ ላይ ከተገለጹት ድንጋጌዎች በመነሳት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚዉ ችሎት በሰ/መ/ቁ 58338 በሆነ የአስገዳጅነት ዉሣኔ ሰጥቶበታል ፡፡
ደረጀ ማርቆስ ነሐሴ 6/2013
ጤና ይስጥልኝ ፡-
ማንኛዉም ሰዉ በአንድ የወንጀል ደርጊት ተከሶ የመጨረሻ ዉሳኔ ባገኘበት በድጋሚ ሊቀጣ እንደማይገባ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 23 ላይ የተደነገገዉን ስለአፈጻጸሙ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 2/5 ላይ የተቀመጠዉን እንደሚከተለዉ እናቀርባለን፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ማንም ሰዉ በሕግ መሠረት የመጨረሻ በሆነ ዉሣኔ ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ ከዚህ ቀደም በተቀጣበት ወይም ሌላ ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም በማለት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 2/5 ላይ የተደነገገ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ ተጠቃሚ ነኝ በማለት በድጋሚ ልከሰስ አይገባም በሚል ክርክር ከቀረበ ከዚህ ቀደም ቀርቧል የተባለዉን በድጋሚ (ለሁለተኛ ጊዜ) ክስ ቀርቦበታል ከተባለዉ የወንጀል ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑ ተገናዝቦ መሆን ያለበት ስለመሆኑ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚዉ ችሎት በሰ/መ/ቁ/85237 በሆነ ዉሣኔም የሰጠበት መሆኑን ግንዛቤ ይያዝበት
ደረጀ ማርቆስ ነሐሴ 6/2013
የሸማች መብቶች
• ስለሚገዛዉ ዕቃ ወይም አገልግሎት ጥራትና አይነት በቂና ትክክለኛ መረጃ ወይም መግለጫ የማግኘት
• ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን አማርጦ የመግዛት
• የዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ጥራት ወይም አማራጮችን በማየቱ ወይም የዋጋ ድርድር በማድረጉ ምክንያት እንዲገዛ ያለመገደድ
• በማንኛዉም ነጋዴ በትህትናና በአክብሮት የመስተናገድ እንዲሁም በነጋዴዉ ከሚደርስበት የስድብ፤ የዛቻ፤ የማስፈራራት እና የስም ማጥፋት ተግባር የመጠበቅ እና
• የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በመግዛቱ ወይም በመጠቀሙ ምክንያት ለሰረሰበት ጉዳት የንግድ ዕቃዎቹን ወይም አገልግሎቶቹን ከማቅረብ ጋር ተያይዞ በአምራችነት፤ በአስመጪነት፤ በጅምላ ሻጭነት፤ በችርቻሮ ሻጭነት ወይም በሌላ ማንኛዉም ሁኔታ በአቅርቦቱ የተሳተፉ ሰዎች በተናጠል ወይም በአንድነት ካሣ እንዲከፍሉት ወይም ከዚህ ጋር ተያያዥ መብቶችን የመጠየቅ መብት አለዉ
አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 14
ህድአት
ነሃሴ/2013 ዓ.ም
ከተ.መ.ድ የስደተኞች ኮንቬንሽን እና ከአፍሪካን ኮንቬንሽን ጥምርት ምንባብ እንደምንገነዘበው አንድ ሰው ስደተኛ የሚባለው፡-
በዘሩ፤ በሃይማኖቱ፤ በዜግነቱ፤ በአንድ የህብረተሰብ ቡድን አባል በመሆኑ፤ ወይንም
በፖለቲካ እምነቱ ምክንያት፡ ተጨባጭ ማሳደድ. ወይንም አደጋ ወይንም እንግልት ወይንም ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ በመስጋት ምክንያት ከአገሩ የተሰደደና፤ በነዚህ ክስተቶች ምክንያት የዜግነት አገሩን ጥበቃ ማግኘት ያልቻለ ወይም በዚሁ ስጋት
የተነሳ የዜግነት አገሩን ጥበቃ ያልፈለገ፤ ወይንም ዜግነት የሌለው ሆኖ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ተጨባጭ ማሳደድ፤ አደጋ፤
እንግልት ወይም ስቃይ ይደርስብኛል ብሎ በመስጋት ከዜግነት አገሩ የተሰደደና
ወደቀድሞ መደበኛ መኖሪያው መመለስ ያልቻለ ወይም ያልፈለገ እንደሆነ እንዲሁም ደግሞ
ከላይ ከተቀመጡት ምክንያቶቸ በአማራጭ፤
ከአፍሪካ የመጣ ስደተኛ ከሆነ በውጭ ወረራ ምክንያት፤ በግዛት መያዝ፤ በውጭ አገዛዝ፤
የትውልድ ወይም የዜግነት አገሩን ህዝባዊ ስርአት በከፊልም ሆነ በሙሉ በሚያናጋ ከባድ
ክስተት ምክንያት፤ከትውልድ ወይንም ከዜግነት አገሩ ውጭ ጥገኝነት ለመጠየቅ ሲል መደበኛ መኖሪያ ስፍራውን ለመልቀቅ የተገደደ እንደሆነ ነው፡፡

ሰብአዊ መብት ባህል የሆነባት ኢትዮጵያን እንፍጠር!
ኦምኒኤል (14/12/2013 ዓ.ም)
የስደተኛ መብቶችን በተመለከተ በተ.መ.ድ የስደተኞች ኮንቬንሽንና በስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1110/2011 መሠረት:-
እንደ ስደተኛ የመቆጠር መብት
ተገዶ ያመመለስ መብት (non-refoulment)
ከአገር ያለመውጣት መብት
የጥገኝነት ማመልከቻ ያቀረበ እንደሆነ የይግባኝ መብት እስኪያበቃ ድረስ ኢትዮጵያ
ውስጥ የመቆየት መብት
ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር መብት
በፈቃደኝነት ወደ አገር የመመለስ መብት
የቤተሰብ አንድነት መብት
ስደተኝነትን የሚገልፅ መታወቂያ ወረቀት የማግኘት መብት
የጉዞ ሰነድ የማግኘት መብት
የትምህርት እድል የማግኘት መብት
የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት
የመስራት መብት
የመደራጀት መብት
የመዘዋወር ነፃነት
ንብረት የማፍራትና የማስተላለፍ መብት
ፍትህ የማግኘት መብት
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የማግኘት መብት
የባንክ እና ፋይናንስ አገልግሎት የማግኘት መብት
የቴሌኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የማግኘት መብት እንዲሁም ደግሞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የማግኘት መብት አለው።

ሰብአዊ መብት ባህል የሆነባት ኢትዮጵያን እንፍጠር!
ኦምኒኤል (14/12/2013 ዓ.ም)
በስደተኞች ጉዳይ አዋጃችን መሠረት
የኢትዮጵያ ዜግነት ማግኘት የሚፈልግ ስደተኛ/የውጭ አገር ዜጋ ሊያሟላቸው የሚገቡ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
ለአካለ-መጠን የደረሰና በህግ ችሎታ ያለው መሆን፤
መደበኛ መኖሪያን በኢትዮጵያ መመስረትና እስከ ማመልከቻው ቀን ድረስ ባሉት
አምስት አመታት ቢያንስ ለአራት አመት ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር፤
ካገሪቱ ቋንቋዎች ቢያንስ ባንዱ መግባባት መቻል፤
ራስንና ቤተሰብን ማስተዳደር የሚያስችል ህጋዊ የገቢ ምንጭ ያለው መሆን፤
መልካም ስነ-ምግባር ያለው መሆን፤
በወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ መሆን፤
የቀድሞ ዜግነቱን የተወ/የሚተው መሆኑን ማስረዳት የሚችል፤
የዜግነት ቃለ-መሃላ ለመፈፀም ፈቃደኛ መሆን፤

ሰብአዊ መብት ባህል የሆነባት ኢትዮጵያን እንፍጠር!
ኦምኒኤል (14/12/2013 ዓ.መ)
ቸር ይግጠመን
በቦሌ ክ/ከ/ዐ/ጽ/ቤት የህ/ም/መ/ዳይሬክቶሬት የቴልግራምመልክት የተዘጋጀ ነሐሴ 7/12/2013
በሰላም ይገላገሉ
ውድ የቴሌግራም ተከታታዮቻችን ማንም ሰው ለአቅመ አዳም /ሄዋን/ ደርሶ ስራ ከያዘ፣ ቀጥሎ ማሳካት ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ መውለድ ወይም ዘሩን መተካት ነው፡፡
መውለድ ደግሞ የግል ብቻ ሳይሆን ለሀገር ቀጣይ ተረካቢ ትውልድ የማፍራት ጉዳይ ስላለበት መንግስታትም ለሰራተኞቻቸው ከሚሰጧቸው መብቶች አንዱ የወሊድ ፈቃድ በመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010የወሊድ ፈቃድ በሚል የሚከተለውን ደንግጓል እንደሚከተለው አቅርበነዋልና ለመውለድ ከምታደርጉት ዝግጅት አንዱ ይህንን ማንበብ ይሆን ዘንድ እጋብዛለሁ፡፡
አንቀጽ 42 የወሊድ ፈቃድ
1.ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሰራተኛ፣
ሀ. ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሰረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፣
ለ. ከመውለዷ በፊት እረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት እረፍት ይሰጣታል
2.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1)የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህምም ፈቃድ አይቆጠርም
3.ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሰራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል
4.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) መሰረት ሰራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል
5.ሰራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የምትቆይበት እረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የእረፍት ፈቃዷ ይተካል
6.ሰራተኛዋ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(1) በተደነገገው መሰረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች
7.ማንኛውም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሰራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል
8.የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል
9.ከሶስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል
10.ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የስራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት የነበረውን አዋጅ ስድስትን በአዋጅ ሀምሳስድስት መቀየር ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል፡-
የጽንስ መቋረጥ ላጋጠማቸው ሴቶች የሚሰጠው ፈቃድ፤
የወሊድ ፈቃድን ከ90 ቅድመ ወሊዱን ጨምሮ ወደ 120 ቀናት ያሳደገው፤
እንዲሁም በክፍል 5 አንቀጽ 48/6 የተደነገገው ማንኛውም መስሪያቤት ህጻናት ማቆያ ማቋቋም እንዳለበት የሚደነግጉት ናቸው፡፡

አዘጋጅ ሲሳይ ሰማኝ
ጤና ይስጥልኝ ፡-
በወንጀል ተከሶ የተያዘ ሰው በሕግ መሠረት ካልሆነ በቀር በዋስ የመፈታት መብት ያለው መሆኑን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19 መሠረት የምንረዳ ሲሆን ይህንኑ በዝርዝር እንዲህ እናቅርበው፡፡
መልካም ምንባብ፡-
በወንጀል ተከሶ የተያዘ ሰውን ዋስትና ለመከልከል ፍ/ቤቶች በሕጉ ላይ ክልከላ ያልተደረገበት መሆኑን፣የተከሰሰበትን ክሶች ብዛትና ከባድነት እንደዚሁም ሌላ ዋስትናውን ለመከልከል በቂ ምክንያትን በማንሳት ሲሆን ከጤና አንፃር የሚቀርብ የዋስትና ጥያቄን ፍ/ቤቶች ግምት ውስጥ የሚያስገቡት መሆኑን የሰ/መ/ቁጥር 68407 በሆነ ትርጉም የሰጠበት መሆኑንና ሆኖም ግን የዋስትና መብት እንዲከበርለት ትዕዛዝ ከተሰተጠ በኃላ ፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ወይም በማናቸውም ባለ ጉዳይ አመልካችነት አዲስ ነገር ተከስቷል ብሎ ካመነ ዋስትናው እንዲነሳ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ደረጀ ማርቆስ
ነሐሴ 17 ቀን 2013 ዓ.ም
ጤና ይስጥልኝ ፡-
የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ሕግ እና የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ግለሰቦች(ተከራካሪ ወገኖች ) ጉዳያቸውን በዕርቅና ግልግል እንዲጨረሱ የሚያበረታታና የሚደግፍ ሲሆን በዚህ ረገድ በድንጋጌው ያሉትን ለንባብ በሚያመች መልኩ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ግለሰቦች ባልተግባቡበትና ባልተስማሙበት ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ክርክር በማቅረብ ፍርድ የማግኘት መብት እንዳላቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 37 ላይ እንደተገለጸው ሁሉ ይህንኑ ጉዳያቸውንም በሚመረጡበት ግለሰብም ይሁን በሕግ ሥልጣን የተሰጠውን ተቋም በመምረጥ በዕርቅ ወይም በግልግል ለመጨረስ የሚችሉ ሲሆን ከእነርሱ የሚጠበቀው ጉዳያቸውን በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ ለመጨረስ እንደሚፈልጉ ስምምነት መስጠት ሲሆን ጉዳዮም በፍርድ ሂደት ላይም ሆነ በፍርድ ውሳኔ የተሰጠበት ሲሆን የሚችል ሲሆን ጉዳዮም በዕርቅ ካለቀ የዕርቅ ሰነድ (ውሉ) ለፍ/ቤቱ ቀርቦ ፍ/ቤቱም የቀረበው ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አለመሆኑን በማረጋገጥ ይመዘግበዋል ማለት ነው፡፡

ደረጀ ማርቆስ
ነሐሴ 17 ቀን 2013 ዓ.ም
ማንኛዉም የንግድ ዕቃ ከመደበኛ የግብይት አሰራር ዉጪ ተከማችቷል ወይም ተደብቋል የሚባለዉ፡-
ግምቱ ከነጋዴዉ ካፒታል ሃያ አምስት በመቶ የማያንስ ሲሆን እና የሚከተለቱት ተሟልተዉ ሲገኙ ነዉ፡፡
• ከዉጭ አገር የመጣ የንግድ ዕቃ ሲሆን አስመጪዉ ራሱ ለቀጣይ የምርት ሂደት በጥሬ ዕቃነት ወይም በግብዓትነት የሚጠቀምበት ካልሆነ በስተቀር የገምሩክ ፎርማሊቲ ከተጠናቀቀለት በኋላ በሦስት ወራት ዉስጥ ለሽያጭ ካልቀረበ፤
• በአገር ዉስጥ የተመረተ የንግድ ዕቃ ሲሆን አምረቹ ራሱ ለቀጣይ የምርት ሂደት በጥሬ ዕቃነት ወይም በግብዓትነት የሚጠቀምበት ካልሆነ በስተቀር ከተመረተበት ቀን ጀምሮ በሁለት ወራት ዉስጥ ለሽያጭ ካልቀረበ፤
• በጅምላ ሻጭ ወይም በችርቻሮ ሻጭ የተገዛ የንግድ ዕቃ ሲሆን የጅምላ ሻጩ ወይም የችርቻሮ ቻጩ ንግድ ዕቃዉን ከገዛበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ዉስጥ ለሽያጭ ካላቀረበ ነዉ፡፡
ከላይ ተየመለከቱት ባይሟሉም በማናቸዉም መጓጓዣ ከተፈቀደዉ የስርጭት መስመር ዉጪ ሲጓጓዝ የተገኘ የንግድ እቃ እንደተከማቸ ወይም እንደተደበቀ ይቆጠራል፡፡
አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 24(2)፣(3)
ህድአት
ነሃሴ/2013 ዓ.ም
በንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 14 የተመለከተዉ የሸማች መብቶች አለመጠበቅ ካሳ እንዲከፈለዉ የሚጠቀይቅ ማንኛዉም ሸማች ግብይቱ የተካሄደዉ በአዲስ አበባ ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዉስጥ ሲሆን ለባለሥልጣኑ የዳኝነት ችሎት ወይም ግብይቱ የተካሄደዉ በክልል ዉስጥ ሲሆን ለክልሉ የሸማቾች ጥበቃ ዳኝነት አካል ክስ ማቅረብ ይችላል፡፡
አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 37(3)
ህድአት
ነሃሴ/2013 ዓ.ም