የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
276 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ላይ ከተካተቱ ነጥቦች መካከል ከተከለከሉ ተግባራት ውስጥ አንዱ ለማንኛውም ማህበራዊ አላማ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና በማናቸውም ቦታ ስብሰባ ማድረግ መከልከሉ ነው።ማህበራዊ አላማ ደንቡ ላይ በተሰጠው ትርጓሜ መሠረት ለሰርግ፣ለለቅሶ፣ክርስትናልደት፣እድር...እና ለመሳሰሉት አላማ ማለት ሲሆን ስብሰባ ማለት ደግሞ ማንኛውንም ተግባር ለመፈጸም፣ለመነጋገር፣ለመወያየት ወይም መሰል ተግባራትን ለማከናወን የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጪ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ በአካል መገኘት ነው።የአንድ ቤተሰብ አባላት ምን ማለት እንደሆነ ደንቡ ባካተታቸው ትርጓሜዎች ውስጥ የለም።እንዲሁም የቤተሰብ ሕጋችን የቤተሰብን ትርጉም ከማስቀመጥ ይልቅ ቤተሰብ የሚመሠረትበትን መንገድ ስለሆነ ያስቀመጠልን የአንድ ቤተስብ አባላት የአለም ጤና ድርጅት በሰጠው ትርጓሜ መሠረት በጋብቻ፣በደም ወይም በጉዲፈቻ የተጣመሩ ሰዎችን(አባት፣እናት፣ወንድም፣እህት)ይመለከታል።
ሰናይ አርብ!
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 እና ይህንኑ አዋጅ ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ዙሪያ ከ21/8/2012 ዓ.ም እስከ 26/8/2012 ዓ.ም ለሶስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ በሰጠበት የተሰራጨውን በራሪ ጽሑፍ ከታች አስቀምጠንላቹሀል።👇
የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ (preliminary objection) ሲባል ምን ማለት ነው?
______________________
ብዙውን ጊዜ በዜና አውታሮች ፍርድ
ቤቱ በነ እገሌ የክስ ሂደት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ለመስማት ቀጠሮ ሰጠ
ሲባል እንሰማለን ለመሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሲባል ምን ማለት ነው?
ለዛሬ በዚሁ አርዕሰት ላይ እናንተን ያስተምራል ያልነውን ጥንቅር ወደናንተ ልናደርስ ወደድን
ተከታተሉን፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ተከሳሹ ስለ ክሱ ማመልከቻ ፎርም ወይም በክስ
ማመልከቻ የተገለፀውን ነገር የሚቃወምበት ስርዓት ነው፡፡የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
አላማ ፍርድ ቤት እና ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክሩ ፍሬ ነገር ሳይገቡ መነሳት ያለባቸውን
ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ በመስጠት ጊዜ መቆጠብ ነው፡፡ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ ውስጥ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊነሳባቸው የሚችሉ ነጥቦች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የክሱን ይዘት በተመለከተ ሊቀርብ ይችላል፡፡ይህም
ማንኛውም የክስ ማመልከቻ ቀንና ዓመተ ምህረት የተፃፈበት እና የተፈረመበት እንዲሁም
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እንዲገልፅ ያስፈልጋል፡፡እነዚህም ተከሳሽ የተከሰሰበት ወንጀል
እንዲሁም የወንጀሉ መሰረታዊ ነገር እና ሁኔታዎች፤ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ እና ስፍራ
ተገቢ በሆነ ጊዜም በደል የደረሰበት ሰው ስም ወይም ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት፣ተከሳሽ
ድርጊቱን በመፈፀም የተላለፈው የህግ አንቀጽ መያዝ አለበት፡፡ክሱ ግልፅ እና የተከሳሽን
የመከላከል መብት የማያጣብብ መሆን አለበት፡፡
በመሆኑም እነዚህ ነገሮች ግልፅ ባልሆኑ እና ባልተሟሉ ጊዜ ተከሳሽ የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ማንሳት ይችላል፡፡ በተጨማሪ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 130/2 ስር የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ የሚያስነሱ ነገሮች ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡
• ተከሳሽ በዚሁ ነገር ክስ በሌላ ፍርድ ቤት ተጀምሮ በቀጠሮ ያለ መሆኑ
• በዚሁ ክስ ከዚህ በፊት ተከሶ ነፃ የወጣ ወይም የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑ
• ክስ የቀረበበት ወንጀል በይርጋ ህግ የታገደ ወይም ምህረት ወይም ይቅርታ የተደረገለት
መሆኑ ከተረጋገጠ፡፡ ይርጋ ማለት አንድ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሞ ክስ ለማቅረብ በ1996
ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማለት ነው፡፡በወንጀል ህግ አንቀጽ
219 ስር እንደተደነገገው የይርጋ ዘመን የሚታሰበው የቅጣት ማከበጃ ወይም ማቅለያ
ሁኔታዎች ግምት ውሰጥ ሳይገቡ በወንጀል ህጉ ልዩ ክፍል የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት
መሰረት በማድረግ ነው፡፡የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው ጥፋተኛው የወንጀል ድርጊቱን
ከፈፀመበት አንስቶ ነው፡፡ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ
ወንጀል ወንጀሉ በተፈፀመ በአስር አመት ውስጥ ክስ መቅረብ አለበት፡፡አስር አመት ካለፈ ግን
ክስ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው፡፡
• ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር በተከሰሰ ጊዜ እና ለብቻው ተነጥሎ ክሱ ባይታይለት የሚጎደው
መሆኑን፣
• ክሱን ለማቅረብ በህጉ መሰረት ፈቃድ ያልተሰጠ መሆኑ ለምሳሌ ተከሳሽ በአለም አቀፍ
ህግ ዲፕሎማቲክ ኢሙኒቲ የማይከሰስ እንደሆነ፣
• በሌላው ችሎት የቀረበው ክስ ሳይፈፀም በዚህ የወንጀል ክስ ሊሰጥ የማይገባ መሆኑ፣
• ለፈፀማቸው ተግባሮች ኀላፊ አለመሆን ፤ለምሳሌ የተከሳሽ አድሜ ከዘጠኝ አመት በታች
ከሆነ፣ በወንጀል ህግ አንቀጽ 48 ላይ እንደተመለከተው ማንም ሰው በእድሜ ፣ በህመም
፣ባልታሰበ የእድገት መዘግየት ወይም ጥልቅ በሆነ የአዕምሮ የመገንዘብ ችሎታ መቃወስ
ወይም የወንጀል ድርጊት በሚፈፅምበት ጊዜ የድርጊቱን አይነት ወይም ውጤት ለመገንዘብ
ወይም በዚህ ግንዛቤ መሰረት ራሱን ለመቆጣጠር በፍፁም ያልቻለ ሲሆን ኢ-ኃላፊ
ስለሚሆን አይቀጣም፡፡
ከላይ የተዘረሩት ነጥቦች ባጋጠሙ ጊዜ ተከሳሽ እራሱ ወይም ጠበቃ ካለው በጠበቃው
አማካኝነት በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ሊያነሳ ይችላል፡፡
ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ሲጠይቀው ተከሳሹ የክሱን ማመልከቻ ወዲያውኑ ካልተቃወመ በቀር
ቆይቶ እንዲህ ያለውን መቃወሚያ ነገሩ በሚሰማበት በሌላ ጊዜ ሊነሳ የሚችለው ፍርድ
ቤቱን የሚፀና ፍርድ ለመስጠት የሚያግደው ከሆነ ብቻ ነው (ወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/
ቁ.130/3)፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ አንድ ጊዜ ተከሶ በተቀጣበት ወንጀል ድጋሚ ሊከሰስ
እንደማይገባ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ባይነሳም በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ
እንደሚችል የሚያሳየንን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ
72304 የሰጠውን ውሳኔ እንደ አብነት ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ጉዳዩ ባጭሩ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ ከተቀጣ
በኃላ ተበዳይ በመሞታቸው ዐቃቤ ህግ ድጋሚ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ክስ
ሲያቀርብ ተከሳሽ እንደ መጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሳያነሳ ቀርቶ በኃላ በተመሳሳይ ወንጀል
ድጋሜ ያለመከሰስ መብት principle of double jeopardy ይነካል ማለቱ ተገቢ
አይደለም ብሎ የተከራከረበት ጉደይ ነው፡፡
ሰበር በውሳኔ ዝርዘሩ ላይ እንዳስቀመጠው “ አንድ ሰው በወንጀል ህግ እና ስነ ስርዓት ተከሶ
የመጨረሻ ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ጥፋተኛ ሆኖ ተቀጥቷል ወይም ነፃ ተለቋል የሚለው
መከራከሪያ በመጀመሪያ የወንጀል ክስ የክስ መቃወሚያ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑ በወ/
መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 130 የተደነገገ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የቀረበው የክስ መቃወሚያና ማስረጃ
በመመርመር ውሳኔ መስጠት ያለበት መሆኑ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 131 ተደንግጓል፡፡
ሆኖም አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተከሶ በመጨረሻ ፍርድ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በተቀጣበት
የወንጀል ድርጊት በድጋሜ ያለመከሰስ ያለመጠየቅ መብት መሰረታዊ እና ህገ መንግስታዊ
መብት በመሆኑ ክርክሩ በሚካሄድበት በማናቸውም ደረጃ ሊነሳ የሚችልና በማስረጃ
ተረጋግጦ በተገኘ ጊዜ ፍርድ ቤቶች ተቀብለው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ መሆኑ በውሳኔው
አስፍሯል፡፡
ከመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጋር ሊምታታ የማይገባው መቃወሚያ በማለት ተከራካሪ
ወገኖች እንደ አስፈላጊነቱ ዐቃቤ ሕግም ይሁን ተከሳሽ በክርክር ወይም ምስክር በሚሰማበት
ጊዜ ጣልቃ የሚገቡበት ስነ ሥርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ ምስክር በሚሰማበት ጊዜ ለምስክሩ በዋና ጥያቄ ላይ መሪ ጥያቄ ቢቀርብ ወይም
ምስክሩ ከተመለከተው ወይም ከሚያውቀው ነገር ባሻገር ግላዊ አስተያየቱን ወይም ግምቱንእንዲሰጥ ቢጠየቅ ወይም ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ቢጠየቅ ተከራካሪ ወገኖች
መቃወሚያ አለኝ ብለው ፍርድ ቤቱን በማስፈቀድ ምስክሩ መልስ እንዳይመልስ ማድረግ
ይችላሉ፡፡
ለዛሬ ካዘጋጀንላችሁ ጥንቅር በጉዳዩ ዙሪያ ዕውቀት እንደጨበጣችሁ ተስፋ
እናደርጋለን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ ተመኝን ሰላም::

ፌናን ተጊበሉ