የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የከተማ ቦታ በሊዝ ስለሚፈቀድባቸዉ ሁኔታዎች
• በጨረታ
• በምደባ
በጨረታ፡- በገበያ የዉድድር ሥርዓት በሚወጡ የዉድድር መስፈርቶች መሰረት አሸናፊ ለሚሆነዉ ተጫራች የከተማ መሬት በሊዝ የሚተላለፍበት መንገድ ነዉ
በምደባ፡- በጨረታ ሊስተናገዱ ለማይችሉ ተቋማት የከተማ ቦታ በሊዝ የሚተላለፍበት መንገድ ነዉ፡፡ ከነዚህ ተቋማት መካከል
• ለባለ በጀት የመንግስት መሥሪያ ቤቶቸ ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ቦታዎች፤ በመንግስት ወይም በበበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለሚካሄዱ ማህበራዊ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚዉሉ ቦታዎች፤
• በመንግስት ለሚካሄዱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ፕሮግራሞች እና በመንግስት እየተወሰነ ለሚካሄዱ ለራስ አገዝ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታዎች የሚዉሉ ቦታዎች፤
• ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት የሚዉሉ ቦታዎች፤
• ከመንግስት ጋር በተደረጉ ስምምነቶች ለኤምባሲዎችና ለአለምአቀፍ ድርጅቶች አገልግሎት የሚዉሉ ቦታዎች፤ ልዩ አገራዊ ፋይዳ ላላቸዉ ፕሮጀክቶች የሚዉሉ ቦታዎች ናቸዉ
ህድአት
ጥቅምት/2014 ዓ.ም
ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ስሪት ስለሚቀየሩበት ሁኔታ
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስተር በሚያቀርበዉ ጥናት ላይ ተመስርቶ የሚወሰን ሆኖ ከዉርስ በስተቀር በማንኛዉም መንገድ ለሌላ ሰዉ ከተላለፈ ንብረቱ የተላለፈለት ሰዉ የቦታዉ ባለይዞታ ሊሆን የሚችለዉ በሊዝ ሥሪት መሰረት ይሆናል፡፡ ነባር ይዞታ ወደ ሊዝ በሚቀየርበት ወቅት በከተማዉ ፕላን መሠረት በሚደረግ ሽንሻኖ
• የሚቀነስ ወይም የሚጨመር የከተማ ቦታ ሊኖር ይችላል፡፡
የሚቀነስ ቦታ ሲኖር ከይዞታዉ ላይ ለሚነሣዉ ንብረት ካሣ የሚከፈለዉ ሲሆን
የሚጨመር ይዞታ ሲኖር ደግሞ ለተጨመረዉ ይዞታ በሊዝ ክፍያ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
ህድአት
ጥቅምት/2014 ዓ.ም
ሰላም ውድ የቴሌግራም ተከታታዮቻችን በቅርቡ የወጡ ሁለት አዋጆችን (የሀገር ህልው እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነ አደጋን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወስን የወጣውን አዋጅ ታነባቸው ዘንድ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ
መልካም ምንባብ!
የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

ውድ አንባቢያን በያላችሁበት ሰላም እንድትሆኑ የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡
በዛሬው መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ 74/2014 ከተቋቋሙት ቢሮዎች አንዱ ስለሆነውና በተለይም ከዚህ ቀደም በሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ስር የነበሩ ተግባራትን ወደዚህ ቢሮ የተዛወሩ በመሆኑ እንግልትን ለመቀነስ ይረዳል በሚል ከዚህ እንደሚከተለው አቅርቢያለሁ!!፡፡
በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሥራ ቦታ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል፤ የወል የሥራ ክርክሮች እና የኅብረት ስምምነት ድርድር ልዩነቶች በመግባባት እልባት እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የህብረት ስምምነቶችንና ማሻሻያቸውን ይመዘግባል፤
በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሥራ ቦታ ሰላም እንዲሰፍን የትምህርትና የሥልጠና አገልግሎት ይሰጣል፣ የሙያ ምክር አገልግሎት ስለሚስፋፋበት፣ ክፍት የሥራ መደቦች ስለሚመዘገቡበትና ሥራና ሠራተኛ ስለሚገናኙበት ዘዴ ይቀይሳል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤
አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በከተማው ውስጥ በሥራ ላይ ስለተሰማራውና ሥራ አጥ ስለሆነው የሰው ኃይል፣ ስለሙያ መደብ፣ የከተማውን የስራ ሰምሪት እንዲሁም የሙያ አመዳደብ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ መረጃዎችን ይይዛል፤ የስራ ገበያ መረጃዎች ስርዓት ይዘረጋል፣ ይሰበስባል፣ ያጠናክራል፤ ያሰራጫል፤
በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ህግ በተደነገገው መሰረት በከተማው ውስጥ የሚደራጁ የአሰሪና ሰራተኛ የሙያ ማህበራትን ይመዘግባል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤ ሲፈርሱ ምዝገባውን ይሰርዛል፤
አሰሪዎች የስራ ሁኔታን፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነትንና የስራ አካባቢን ለመጠበቅ የወጡ የስራ ሁኔታ ደረጃዎችና የመከላከያ ዘዴዎች በሥራ ላይ ማዋላቸውን ይቆጣጠራል፤
ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ በህግ መሰረት ይሰጣል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ይሰርዛል፤
በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህግ መሰረት የከተማው አስተዳደር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ያቋቁማል፤ የቦርዱን አባላት ይሰይማል፤ ያሰናብታል፤ ተግባርና ኃላፊነታቸውን ይከታተላል፤
የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን፣ የሥራ ሥምሪት አግልግሎትና የሥራ አፈጻጸም እያጠና ምክር የሚሰጠው የመንግሥት፣ የአሠሪዎች ማህበራትና የሠራተኛ ማህበራት ተወካዮችን ያካተተ ቋሚ የሆነ አማካሪ ቦርድ ሊያቋቁም ይችላል፤
የከተማ ነዋሪው ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጨባጭ ሁኔታ፤ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ የመገናኛ ብዙኃንንና ሌሎች አማራጭ ዘዴዎችን በመጠቀም ቀጣይነት ያለው ከተማ አቀፍ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን ያከናውናል፤
ለሥራ ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ፍላጎት ላላቸው ዜጎች ስለተቀባይ አገር ሁኔታ በሚሰማሩበት የስራ መስክ ሊኖራቸው ስለሚገባ ክህሎት፣ ስለመብታቸውና ኃላፊነታቸው እና ስለመሳሰሉት ጉዳዩች የቅድመ-ስምሪትና የቅድመ ጉዞ ግንዛቤ ማሰደጊያ ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤
ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም "ሥራ" ማለት አግባብ ባለው ሕግ የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የስራ ገበያ መረጃ፣ የሙያ ደህንነት ጤንነትና የሥራ አካባቢ፣ የሠራተኛና የአሰሪዎች ማህበር፣ ማህበራዊ ምክክር ሥርዓት፣ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ እና መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችና ግዴታዎችን አካትቶ የያዘ ነው፡፡

ሲሳይ ሰማኝ
ቸርይግጠመን!!!
በዛሬዉ ዕለት ህዳር 7/2014ዓም የቦሌ ክፍለ ከተማ የህግ ሰርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በሀገር ህልዉና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የወጣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 አስቸከኳይ አዋጁን በተመለከተ ለሕብረተሰቡ በስፋት ተደራሽ ይሆን ዘንድ ሙሉቀን የፈጀ ገለጻ በቦሌ ክ/ከተማ በር አጠገብ በመዉጣት ለህብረተሰቡ ገለጻ በማድረግና አዋጁን በብሮሸር መልክ በማዘጋጀት 6640 (ስድስት ሺ ስድስት መቶ አርባ ) ብሮሸሮችን በመበተን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሎል፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የወጣ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ
ከተማችንን ጽዱና ለኑሮ የተመቸች ከሚያደርጓት ዋነኛ ነገሮች አንዱ የከተማዋን ጽዳት መጠበቅ ሲሆን ለዚህ ደግሞ በጽዳት ስራ ላይ ከተሰማሩት ባለፈ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚመለከት ስለሚሆን ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አሰባሰብ እና አወጋገድን በተመለከተ ከወጡ ሕጎች የተወሰኑትን እንመለከታለን መልካም ንባብ
ደረቅ ቆሻሻ ምን ማለት ነዉ ስንት ዓይነት ደረቅ ቆሻሻ አለ?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸሻለ የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 100/2010 አንቀጽ 1 (7)፤ (8)፤ (9)፤ (10)
የደረቅ ቆሻሻ ተርጓሜ፡- ከመኖሪያ ቤት፤ ከንግድ፤ ከኢንዱስትሪ፤ ከተለያዩ ተቋማት፤ ከጋራዥ፤ ከመንገድ ጽዳት፤ ከግብርና፤ ከእንስሳትና በጠቅላላዉ ከህብረተሰቡ ስራዎች ምክንያት የሚፈጠር ጥቅም የማይሰጥ ወይም የማይፈለግ ተብሎ ሚጣል ጠጣር/ከፊል ጠጣር የሆነ ቁስ ነዉ፡፡
ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻ፡- በየቦታዉ በግልጽ የሚታዩና በሰዎች እንቅስቃሴ ምክንያት ተጠቃሚዎች የሚጥሏቸዉ የሲጋራ ቁርጥራጭ፤ የሶፍት ወረቀት፤ ፌስታል፤ የጫት ገረባ፤ የፍራፍሬ ተረፈ-ምርቶች ትራንስፖርት ቲኬት፤ ሞባይል ካርዶች፤ የማስቲካና ከረሜላ ሽፋኖች፤…… የሚያጠቃልል ነዉ፡፡
ኤልክትሮኒክስ ነክ ቆሻሻዎች፡- እንደገና አገልግሎት ሊሰጡ ወይም ላይሰጡ ሚችሉ ኮምፕዩተሮች፤ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች፤ ማንናዉም የስልክ ቀፎ፤ ቴሌቪዥኖች፤ የማቀዝቀዣ መሳሪያዎች፤ ….. እና የእነዚህ ዕቃዎች የዉስጥና የዉጭ ስብርባሪና የወላለቁ አካላት ማለት ነዉ፡፡
አደገኛ ደረቅ ቆሻሻ፡- የሚፈነዱ፤ በቀላሉ በእሳት የሚቀጣጠሉ፤ መርዛማ ነገሮች፤ ራዲዮአክሪቭ ቁሶች፤ ልዩ ልዩ ኬሚካሎች፤ የደም ንክኪ ያላቸዉ ሆነዉ ከኢንዱስትሪ፤ ከማምረቻ፤ ከጤና ተቋማት እና ከቤተ ሙከራ የሚወጡና በሰዉ፤ በእንስሳ፤ በእጽዋትና በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ማንኛዉም ቆሻሻ ነዉ፡፡

ህድአት ጌታቸዉ
ህዳር/2014 ዓ.ም
የደረቅ ቆሻሻ የጽዳት አገልግሎት በማን ይሰጣል?
በግል፤ በማህበር፤ በሽርክና፤ በዩኒየን (100/2010 2(19)
"የደረቅ ቆሻሻ የጽዳት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት፡- ማለት ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ የመሰብሰብ፤ የመጓጓዝ፤ የማስወገድና የመንገድ ጽዳትና አገልግሎት የሚሰጡ በግል፤ በማህበር፤ በሽርክና፤ በዩኒየን፤ ወዘተ የሚሰሩና የደረቅ ቆሻሻ የጽዳት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ናቸዉ"
የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ማህበራት/ድርጅቶች የቆሻሻ አያያዝ
የተጣሉ ግዴታዎች (100/2010 13)
ማንኛዉም የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ማህበር/ድርጅት የሰበሰበዉን ደረቅ ቆሻሻ
• እስከ ሚጓጓዝ ድረስ ሸፍኖ የማስቀመጥ
• ኤጀንሲዉ በሚያወጣዉ ስታንዳርድ መሰረት የማጓጓዝ/እንዲጓጓዝ የማድረግ
• መጥፎ ሽታ ሊፈጥሩ የሚችሉና ለጤና ስጋት የሆኑትን በልዩ ሁኔታ በፍጥነት ከአካባቢዉ ወደ ማስወገጃ ቦታ እንዲጓጓዙ የማድረግ
• በህግ በተፈቀዱ ጊዚያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን ከግቢዉ ዉጭ እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱና አረንጓዴ በማድረግ ቆሻሻዉ እንዳይበተን የማድረግ
• የጽዳት ኤጀንሲ በሚያወጣዉ የአሰራር ስታንዳርድና መመሪያ መሰረት ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት

ህድአት ጌታቸዉ
ህዳር/2014 ዓ.ም
በመመሪያ ቁጥር 2/2014 መሠረት የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም በአዋጁ እና ሌሎች ሕጎች መሰረት የወንጀል ኃላፊነት ያስከትላል፡-
1. ጊዜያዊ መታወቂያ ለመውሰድ ሀሰተኛ መረጃ መስጠት
2. መስፈርቱን ለማያሟላ ሰው ጊዜያዊ መታወቂያ መስጠት
3. መስፈርቱን የማያሟላ ሰው ጊዜያዊ መታወቂ እንዲሰጠው በማሰብ ማረጋገጫ ደብዳቤ መጻፍ ወይም ምስክር መሆን
4. ከአንድ በላይ ጊዜያዊ መታወቂ ይዞ መገኘት
ኦምኒኤል (ህዳር 13/2014 ዓ.ም)
አግባብ ባለዉ ድንጋጌ አስገዳጅነት የሚረጋገጡና የሚመዘገቡ ሰነዶች ህጋዊ ዉጤትን በተመለከተ
አግባብ ባላቸው ሕግ መሠረት ካልተረጋገጡ እና ካልተመዘገቡ ሕጋዊ ውጤት የማያገኙ ሠነዶችን አስመልክተው ከፍትሐብሔር ሕግ ከተመላከተው አንቀጾች በተጨማሪ ለጠቅላላ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች ባሉት የተለያዩ የፌዴራል አዋጆች እና ደንቦች ላይ ጭምር የተቀመጡ ስለመሆናቸው ለማሳያ ይረዳ ዘንድ እንደሚከተለዉ ተቀምጧል፡፡
1. ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1123/2013 የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ “ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማሕበር ለመቋቋም አባሉ የሚሰጠው መግለጫ ሰነድ ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መደረግ እንዳለበት (በአንቀጽ 536 ንኡስ ቁጥር 1) የሚያመላክት ሲሆን እንዲሁም ይህ ባለ አንድ አባል ያለው ማሕበር ለመቋቋም በቅድመ ሆኔታ ዕጩ ንብረት ጠባቂ አስመልክቶ አባሉ እና ዕጩነቱን ከተቀበለው ንብረት ጠባቂ ጋር የሚያደርጉት ስምምነት በተመሳሳይ ሁኔታ በውል አዋዋይ አካል ፊት ቀርቦ ካልተረጋገጠ ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ ማሕበር ሊመሠረት እንደማይችል (በንግድ ሕጉ አንቀጽ 537(1) አስገዳጅ ድንጋጌ ተቀምጠዋል።
2. በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 474/2012 ዓ.ም
• በትግበራ ላይ የሚገኝ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ለሌላ 3ኛ ወገን በሽያጭ ለማስተላለፍ (በደንቡ አንቀጽ 12) የሚደረግ ስምምነት፣
• በቴክኖሎጂ ተቀባይ እና አቅራቢ መካከል የሚደረግ የቴክኖሎጂ ስምምነት ለመፈጸም (አንቀጽ15/1/ሰ/) እና
• ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘ በአገር ውስጥ ባለሀብቱ እና በውጭ ኢንተርፕራይዝ መካከል የሚደረግ ስምምነቶች (በደንቡ አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 1 (ሰ)
ከላይ የተዘረዘሩ ስምምነቶች እንደ ቅድመ ሁኔታ ሰነድን ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ተረጋግጠው ካልተመዘገቡ በቀር በሕግ ፊት ተቀባይነት እንደማገያኙ አስገዳጅ ድንጋጌ ናቸዉ
3. በተመሳሳይ የንግድና ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ለማስፈጸም በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 392/2009 ዓ.ም በአንቀጽ 37 እና 48 ላይ እንደተቀመጠው
• የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታ በሆልዲንግ ኩባንያው የቡድን አባላት መካከል ኩባንያው ስለመመስረቱ የሚደረግ ስምምነት (አንቀጽ 37 ንዑስ ቁጥር 1 ላይ እንደተቀመጠው) እንዲሁም
• የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት የፍሬንቻይዘሩ (ውል ሰጪ) እና የፍሬንቻይዝ (ውል ተቀባይ) መካከል የተፈጸመ የፍሬንቻይዚንግ ውል ስምምነት (አንቀጽ 48 እንደተመለከተው)
በቅድመ ሁኔታ ሰነድን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ በሕግ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርበው ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ ሕጋዊ ውጤት እንደማይኖራቸው ተደንግጓል።
4. በሌላ በኩል ሠነድን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ በወጣው አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 9(1) እንደተመላከተው ካልተረጋገጠና ካልተመዘገበ ሕጋዊ ውጤት አይኖራቸውም ተብሎ ከተገለጹት መካከል የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ ብቻ ሳይሆን የውክልና መሻሪያ ሰነድም አንዱ ሲሆን የመሻሪያ ሰነድ ወካይን ከመቼ ቀንና ዓ.ም ጀምሮ ከስልጣኑ እንደሻረው እና ከተሻረ ጊዜ ጀምሮ በወካይ ስም አንዳች ሕጋዊ ተግባር እንዳይፈጸም በተሻረው የውክልና ስልጣን እንዳይሰራ አስቀድሞ ለመከላከል የመሻሪያው ሰነድ ስልጣን ባለው አካል ተረጋግጦ መመዝገብ እንዳለበት ተደንግጎ ይገኛል።
ምንጭ፣ Federal Documents Authentication and Registration Agency.
ኦምኒኤል (ህዳር 13/2014 ዓ.ም)