አግባብ ባለዉ ድንጋጌ አስገዳጅነት የሚረጋገጡና የሚመዘገቡ ሰነዶች ህጋዊ ዉጤትን በተመለከተ
አግባብ ባላቸው ሕግ መሠረት ካልተረጋገጡ እና ካልተመዘገቡ ሕጋዊ ውጤት የማያገኙ ሠነዶችን አስመልክተው ከፍትሐብሔር ሕግ ከተመላከተው አንቀጾች በተጨማሪ ለጠቅላላ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች ባሉት የተለያዩ የፌዴራል አዋጆች እና ደንቦች ላይ ጭምር የተቀመጡ ስለመሆናቸው ለማሳያ ይረዳ ዘንድ እንደሚከተለዉ ተቀምጧል፡፡
1. ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1123/2013 የኢትዮጵያ ንግድ ሕግ “ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማሕበር ለመቋቋም አባሉ የሚሰጠው መግለጫ ሰነድ ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መደረግ እንዳለበት (በአንቀጽ 536 ንኡስ ቁጥር 1) የሚያመላክት ሲሆን እንዲሁም ይህ ባለ አንድ አባል ያለው ማሕበር ለመቋቋም በቅድመ ሆኔታ ዕጩ ንብረት ጠባቂ አስመልክቶ አባሉ እና ዕጩነቱን ከተቀበለው ንብረት ጠባቂ ጋር የሚያደርጉት ስምምነት በተመሳሳይ ሁኔታ በውል አዋዋይ አካል ፊት ቀርቦ ካልተረጋገጠ ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ ማሕበር ሊመሠረት እንደማይችል (በንግድ ሕጉ አንቀጽ 537(1) አስገዳጅ ድንጋጌ ተቀምጠዋል።
2. በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012 ለማስፈጸም በወጣው ደንብ ቁጥር 474/2012 ዓ.ም
• በትግበራ ላይ የሚገኝ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ለሌላ 3ኛ ወገን በሽያጭ ለማስተላለፍ (በደንቡ አንቀጽ 12) የሚደረግ ስምምነት፣
• በቴክኖሎጂ ተቀባይ እና አቅራቢ መካከል የሚደረግ የቴክኖሎጂ ስምምነት ለመፈጸም (አንቀጽ15/1/ሰ/) እና
• ከውጭ ንግድ ጋር በተያያዘ በአገር ውስጥ ባለሀብቱ እና በውጭ ኢንተርፕራይዝ መካከል የሚደረግ ስምምነቶች (በደንቡ አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 1 (ሰ)
ከላይ የተዘረዘሩ ስምምነቶች እንደ ቅድመ ሁኔታ ሰነድን ለማረጋገጥ እና ለመመዝገብ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ተረጋግጠው ካልተመዘገቡ በቀር በሕግ ፊት ተቀባይነት እንደማገያኙ አስገዳጅ ድንጋጌ ናቸዉ
3. በተመሳሳይ የንግድና ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 ለማስፈጸም በወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 392/2009 ዓ.ም በአንቀጽ 37 እና 48 ላይ እንደተቀመጠው
• የሆልዲንግ ኩባንያ ልዩ የምስክር ወረቀት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታ በሆልዲንግ ኩባንያው የቡድን አባላት መካከል ኩባንያው ስለመመስረቱ የሚደረግ ስምምነት (አንቀጽ 37 ንዑስ ቁጥር 1 ላይ እንደተቀመጠው) እንዲሁም
• የፍሬንቻይዚንግ ልዩ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማግኘት የፍሬንቻይዘሩ (ውል ሰጪ) እና የፍሬንቻይዝ (ውል ተቀባይ) መካከል የተፈጸመ የፍሬንቻይዚንግ ውል ስምምነት (አንቀጽ 48 እንደተመለከተው)
በቅድመ ሁኔታ ሰነድን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ በሕግ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርበው ካልተረጋገጡና ካልተመዘገቡ ሕጋዊ ውጤት እንደማይኖራቸው ተደንግጓል።
4. በሌላ በኩል ሠነድን ለማረጋገጥና ለመመዝገብ በወጣው አዋጅ ቁጥር 922/2008 አንቀጽ 9(1) እንደተመላከተው ካልተረጋገጠና ካልተመዘገበ ሕጋዊ ውጤት አይኖራቸውም ተብሎ ከተገለጹት መካከል የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ ብቻ ሳይሆን የውክልና መሻሪያ ሰነድም አንዱ ሲሆን የመሻሪያ ሰነድ ወካይን ከመቼ ቀንና ዓ.ም ጀምሮ ከስልጣኑ እንደሻረው እና ከተሻረ ጊዜ ጀምሮ በወካይ ስም አንዳች ሕጋዊ ተግባር እንዳይፈጸም በተሻረው የውክልና ስልጣን እንዳይሰራ አስቀድሞ ለመከላከል የመሻሪያው ሰነድ ስልጣን ባለው አካል ተረጋግጦ መመዝገብ እንዳለበት ተደንግጎ ይገኛል።
ምንጭ፣ Federal Documents Authentication and Registration Agency.
ኦምኒኤል (ህዳር 13/2014 ዓ.ም)

የቀጠለ…
የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ ቁጥር 2/2014 ላይ የተሰጠ የአደባባይ ግንዛቤ ማስጨበጫ

የሁከት ይወገድልኝን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ ውሳኔዎችን በተመለከተ
1/ ሰ/መ/ቁ. 80241 ቅጽ 15፣
በፍ/ሕ/ቁ. 1149/1/ መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ መቅረብ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻመ በሆነው ነገር በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረው ነው፡፡ እንዲሁም የይዞታ ክስ የሚቀርበው ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ንብረት በወቅቱ ለመያዝ ምንም ዓይነት መብት በሌለው ሰው ላይ ስለመሆኑም የድንጋጌው መንፈስ ያስረዳል፡፡ የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ አቅራቢ በማስረጃ ማረጋገጥ ያለበት ንብረቱ በይዞታው ስር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የኃይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጢር ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው፡፡ ሁከት ተፈጥሯል የሚባለው ባለይዞታ የሆነው ሰው በይዞታው ስር በሚገኘው ንብረት እንዳይገለገልበት ሌላ ሰው ጣልቃ ገብቶበት መሰናክል ሲፈጥርበት ወይም ረብሻ ሲፈጥርበት ነው፡፡
2/ ሰ/መ/ቁ. 38228 ቅጽ 9
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ ከሳሹ ማስረዳት ያለበት ባለቤትነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዳለው ሳይሆን ክስ ያቀረበበት ንብረት ህጋዊ ባለይዞታ መሆኑ በሌላ አነጋገር ሁከት የተፈጠረበትን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት ሲያዝበት እንደነበር ነው፡፡
3/ ሰ/መ/ቁ. 27506 ቅጽ 6
ሁከት እንዲወገድ በቀረበ ክስ ተከሳሽ የሚያነሳው የባለቤትነት ክርክር እራሱን የቻለ ባለቤትነት የመፋለም ክስ /petitory action/ በሚመለከተው ላይ አቅርቦ ከሚታይ በስተቀር ሁከት ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም ተብሎ ለሚያዘው ጭብጥ ተገቢነት የለውም፡፡
4/ ሰ/መ/ቁ 36645 ቅጽ 9 /በአብላጭ ድምፅ የተሰጠ/
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሲቀርብ በፍርድ ቤት በጭብጥነት ተይዞ መፈታት የሚገባው ጉዳይ ሁከት አለ ወይንስ የለም? የሚለው ነው፡፡
የውሉ ተገቢውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ አለመደረግ ይዞታው በተጨበረበረ መንገድ ስለመያዙ ወይንም በማናቸውም ሕገወጥ ሁኔታ ስለመያዙና ሁከት እንዲወገድለት ክስ ያቀረበው ከሳሽ በይዞታው በእውነት ሊያዝበት እንደማይችል አያረጋግጥም፡፡ በዚህ ረገድ ውሉ ጉድለት አለበት ከተባለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/1808(2) ላይ እንደተመለከተው ውሉ ፈራሽ ነው እንዲባል የክስ ምክንያት ከሚሆን በስተቀር ሁከት ይወገድልኝ ተብሎ በቀረበ ክስ ላይ ሊስተናገድ የሚችል አይሆንም፡፡
ምንጭ፡- ኢትዮ ሕግ
ኦምኒኤል ከበደ (ህዳር 13/2014 ዓ.ም)

ስጦታ በፍትሐብሔር ሕግ
👉 የስጦታ ምንነት
ስጦታ ማለት ሰጪው ተቀባይ ለተባለ ሌላ ሰው ከንብረቶቹ አንዱን ያለ ዋጋ የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው። በመሆኑም ስጦታ በራሱ ውል ነው ማለት ነው።
👉የስጦታ ልዩ ባህሪያት*
በመርህ ደረጃ ስጦት ግላዊ ተግባር ነው ይህም ማለት ሰጪው እራሱ የሚያድረገው ተግባር ነው ማለት ነው። ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን ደግሞ የሚሰጠው ንብረት አይነት እና ለማን እንደሚሰጥ በግልጽ ሊመለከት ይገባል። ስጦታ የሚደረገው የሰጪው ንብረት በሆነው ላይ ብቻ ነው።ስጦታ አድርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት በሕጉ መሠረት ግዴታን አያስከትልም ከዚህም በተጨማሪ ስጦታ ተቀባዩ ስጦታውን እቀበላለሁ በሚል ሀሳቡን መግለፅ ይኖርበታል። ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ እስከ ሁለት አመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም።
👉የስጦታ ሥርዓት ፎርም
ስጦታ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ላይ ወይም በሚይንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ ሊደረግ ይችላል።
*1)በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ *
በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 881 ላይ በተደነገገው መሠረት በግልጽ ኑዛዜ ሥርዓት ፎርም መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ሕጉ ያስረዳል። በሌላ በኩል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ለይ የሚደረገው ስጦታ በፍ/ሕግ አንቀጽ 1723 መሠረት በጽሁፍ ሆኖ በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መሆን አለበት።
*2) በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ*
በሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶች ላይ የሚደረግ ስጦታ በሁለት አይነት መልኩ ሊደረግ ይችላል ይህም እጅ በእጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ በሚደረገው ፎርም ሊሰጥ ይችላሉ።
👉ስጦታ ፈራሽ የሚሆንባቸው ምክንያቶች
በሚንቀሳቀስ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረቶች ላይ የተደረገው ስጦታ በሕጉ በተጠቀሱት በተለያየ ምክንያቶች ፈራሽ ሊሆን የሚችሉባቸው ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነኚህም:-
1ኛ የሰጪው አዕምሮ ትክክል አለመሆን
ሰጪው ስጦታውን በሚያድርግበት ወቅት በአዕምሮ መታወክ(ህመም ምክንያት) በፍርድ የተከለከለ ሲሆን ያደረገው ስጦታ ፈራሽ ሊሆን ይችላል ። የፍ/ሕ አንቀጽ 2437
2ኛ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ሕገ-ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ፈራሽ ነው። የፍ/ሕግ አንቀጽ 2438
3)በመንፈስ መጫን ምክንያት የተደረገውን ስጦታ ዳኞች ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ። የፍ/ሕግ አንቀጽ 2439
4ኛ በ ፍ/ሕግ አንቀጽ 2442 ሥር በሚፈቅደው መሠረት ስጦታው የተደረገው በስህተት ወይም በተንኮል የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል።
5 ስጦታ የተደረገው ክርክር ያለበት ሀብት ላይ ሲሆን ስጦታው ፈራሽ ይሆናል። የፍ/ግ አንቀጽ 2452
ፌናን ተጊበሉ
ሕዳር 14/2014 ዓ.ም

የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት(ባለ ሀብትነት) ምስክር ወረቀት ስላለው ሕጋዊ ውጤት
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ምስክር ወረቀት በአጭሩ ለመግለጽ አንድ ሰው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት
በባለሀብትነት/በባለቤትነት/ ስለመያዙ የሚያስረዳ ማስረጃ ነው። በፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1195(1) ላይ
በግልጽ እንደተደነገገው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በሚመለከት ከአስተዳደር ክፍል የሚሰጠው ምስክር ወረቀት
የንብረቱ ባለሀብት እንደሆነ ግምት ያስወስዳል። ከዚህ ድንጋጌ መረዳት እንደሚቻለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምስክር ወረቀት የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆን ግምት ለመውሰድ የሚረዳ እንጂ የማይስተባበል የመጨረሻ ማስረጃ ተደርጎ የሚወሰድ አለመሆኑን ነው። በሌላ በኩል በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 13 መ/ቁ 67011 ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን አስመልክቶ የሚሰጥ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ተገቢውን ስርዓት እና ደንብ በመከተል የተሰጠ መሆን ያለበት ስለመሆኑ ትርጉም የተሰጠ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ግምት መውሰጃ የሆነው ምስክር ወረቀት ደንብና አሰራርን መሠረት ባላደረገ እንዲሁም ከስልጣን ውጪ የተሰጠና በሕግ ፊት የማይፀና ስለመሆኑ በማናቸውም ማስረጃ ለማረጋገጥ የተቻለ እንደሆነ በተሰጠው የምስክር ወረቀት የተፈጠረውን የሕጉን የህሊና ግምት ማፍረስ የሚቻል ስለመሆኑ ውሳኔ ተሰጥቷል። በተመሳሳይ መልኩ በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 11 መ/ቁ 47139 ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ስመ ሃብት ይዞ መገኘት የንብረቱ ባለቤት አድርጐ የማያስቆጥር ስለመሆኑ ውሳኔ ተሰጥቶበታል።

ኑዛዜ መሻር
• ተናዛዡ ቀድሞ ያደረገውን ኑዛዜ ሽሮታል ሲባል በግልፅና በማያሻማ አኳኋን ሕጋዊ ውጤት ወይም ዋጋ እንዳይኖረው አድርጎታል ማለት ነው፡፡
ኑዛዜ የሟች ጥብቅ የሆነ የግል ጠባይ ያለው እና ራሱ የሚተገብረው ነው፡፡ በመሆኑም የተናዛዡ ሀሳብና ፍላጐት በጥንቃቄ ልንከተለው የሚገባው ነው፡፡ የፍ/ሕ/ቁ. 898(1) ተናዛዡ ኑዛዜዎቹ ዋጋ ያላቸው እንዲሆኑ በሚያስፈልገው ፎርም ዓይነት ግልፅ አድርጎ በማስታወቅ ኑዛዜውን የሻረ እንደሆነ በጠቅላላው አኳኋን የሚሻር ይሆናል ይላል፡፡ በዚሁ ሕግ አንቀፅ 899(1) ተናዛዥ የተናዘዘውን ለመሻር ወይም ለመለወጥ ያለውን ሀሳብ በቂ አድርጎ በመግለፅ ይህንን በኑዛዜው የተመለከተውን ቃል መሻር ይችላል በማለት ተደንግጓል፡፡ ሁለቱም ድንጋጌዎች አንዱ ሌላኛውን በሚያጠናክር መልኩ የተቀመጡ እንጂ የሚቃረኑ አይደለም፡፡
ይህም ሲባል ሁለቱም አንቀፆች ተናዛዡ ያደረገውን ኑዛዜ መሻር ሲፈልግ ሀሳቡን በማያሻማ አኳኋን ግልፅ በሆነ መንገድ መሻር እንደሚችል የሚገልፅ ነው፡፡ ይህም የሚያመለክተው ሟች (ተናዛዡ) ከዚህ ውጭ ሊከተላቸው የሚገባው ሥርዓት መኖሩን አይደለም፡፡ ይልቁንም ተናዛዡ ኑዛዜውን ለመሻር ሊከተላቸው የሚገባውን አማራጮች የሚያመለክት (የሚገልፅ) ነው፡፡ ስለሆነም የኑዛዜ መሻሪያ ሰነዱ ተናዛዥና በቦታው ለነበሩ ምስክሮች የተነበበላቸው ስለመሆኑ የሚያመለክት ቃል በሰነዱ ላይ አለመስፈሩ ኑዛዜው ሕጉ አግባብ እንዳልተሻረ አያስቆጥረውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 96364 ቅጽ 17፣ ፍ/ህ/ቁ. 881፣ 898(1)፣ 899(1)

ጤና ይስጥልኝ
ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ በማየት ከዚህ የሚከተለውን ስለመከላከያ ሠራዊት ከወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1100/2011 መሠረት የሚከተለውን እንበል፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ኢትዮጵያ ለዘመናት ከውጭም ሆነ ከውስጥ የተነሱባትን ጠላት በማንበርከክ ነጻነቷን ጠብቃ ታፍራና ተከብራ የኖረችው እና ያለችው በውድ ልጆቿ ብርቱ ተጋድሎ መሆኑን ይልቁንም በፋሺስት ኢጣሊያ ተመጣጣኝ ያልሆነ የጦር መሣሪያ ኃይልን ተማምኖ የመጣውን መላው ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው በመነሳት ድባቅ በመምታት ለጥቁር ሕዝብ ፋና ወጊ የሆኑበትን እንደዚሁም ኢትዮጵያ በውስጥ የመንግሥት ለውጥ ጊዜ በበርካታ ጉዳዮች ተወጥራ የነበረበትን ጊዜ በመጠቀም የሱማሌውን ተስፋፊ የዚያድበሬን ጦር አይቀጡ በመቅጣት አኩሪ ተግባራትን የፈጸሙ ልጆች እንዳሏት የቅርብ ጊዜ ተጋድሎን እያነሳን ከዚሁ ጋር ከዚህ በላይ በገለጽነው የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 የሠራዊቱ አባል ለሀገር ከሚያበረክተው ከማንም የላቀ አገልግሎት ባይመጣጠንም ለማበረታታት ያህል የቤት መኪና ከቀረጥ ነፃ የመግዛት እና በተወለደበት የክልል ከተማ የመኖሪያ ቤት መስሪያ እንዲያገኝ በመንግስት ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን የተደነገገውን ግንዛቤ እንያዝ ፡፡
መልካም ቀን
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !!
ሕዳር 15ቀን 2014ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 23 ላይ ማንኛውም ሰው በወንጀል ሕግና ሥነ-ሥርዓት መሠረት ተከሶ ጥፋተኛ በሆነበት ወይም በነጻ በተለቀቀበት እንደገና እንደማይከሰስ ወይም እንደማይቀጣ በተደነገገው ላይ የሚከተለውን እንበል ፡፡
መልካም ምንባብ፡-
አንድ ሰው በአንድ ወንጀል ድርጊት ተከሶ የመጨረሻ በሆነ ውሣኔ ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ በተቀጣበት ወይም በነጻ በተለቀቀበት እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም ቢባልም ይህ ማለት ግን ጉዳዩ በአስተዳደር ሕግ (በዲሲፕሊን ክስ ወይም መሰል) ወይም በፍትሐ ብሔር ሕግ አይከሰስም ወይም አይቀጣም ማለት አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
መልካም ቀን
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይባርክ !!
ሕዳር 15 ቀን 2014ዓ.ም

ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን አካል በማቅረብ ፍርድ (ፍትሕ) የማግኘት መብት እንዳለው በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 37 ላይ የተቀመጠ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለፍትሐ-ብሔር ክስ የዳኝነት አከፋፈል ከዚህ የሚከተለውን እንበል፡፡
መልካም ምንባብ፡-
ከዚህ በላይ እንደገለጽነው ማንኛውም ሰው በፍ/ቤት ፍርድ የማግኘት መብት አለው ቢባልም ጉዳዩ የፍትሐ-ብሔር ከሆነ ግን ክሱን የሚያቀርበው ወገን በሚያቀርበው የገንዘብ መጠን ልክ የሚሰላ የዳኝነት ክፍያ ያለበት ቢሆንም ይህ ማለት ግን ግለሰቡ የሚከፍለው ባይኖረው በፍርድ ቤት እንዲታይለት የሚፈልገውን ሳያቀርብ ይቀራል ማለት ሳይሆን ግለሰቡ ድኃ መሆኑን በማስመስከር ጉዳዩን ለፍ/ቤት ሊያቀርብ እንደሚችል ግንዛቤ እንያዝበት፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በ07/03/2014 ዓ.ም በአስቸኳይ አዋጁ እና በጊዜያዊ መታወቂያ መመሪያው ላይ የተጀመረው የአደባባይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ብቻ የተዳሰሱት ቦታዎች 5 ሲሆኑ እነሱም ገርጂ ሮባ፣ጎሮ፣ቦሌ መዳኒዓለም፣ጎላጎል እና ሃያ አራት ናቸው፡፡ በነዚህ ቦታዎች በጊዜያዊ መመሪያው ላይ የተዘጋጀውን 4538 እንዲሁም ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተዘጋጀውን 2642 በራሪ ጽሑፍ ባጠቃላይ 7180 (ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሊሰራጭ ችሏል፡፡
ቸር ያሰማን!
ቸር ያሰማን!
ጤና ይስጥልኝ!!
ዓለማቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በየአመቱ ሕዳር 24 (December 3) በተለያዩ መሪ ቃላት ይከበራል፡፡
በዚህም መሰረት ዘንድሮ በዓለም ለሰላሳኛ በሀገራችን ደግሞ ለሃያዘጠነኛ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ በሱማሌ ክልል ይከበራል፡፡ ይህንን ምክንያት በማድረግ እኔም ስለአካል ጉዳተኞች በወጡ ስምምነቶችና የራሳችን ሕጎች ዙሪያ ተከታታይ መልዕክቶችን በዚህ መገናኛ መስመር አደርሳለሁ፡፡
ለዛሬ ከስራ ስምሪት መብት ጋር በተያያዘ በዓለማቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት የሰፈረውን ቅድሚያ በልቶ ማደር ይቀድማልና አንቀጽ 27 ምን እንደሚል አቀርባለሁ፤ መልካም ምንባብ፡፡
ውድ ተከታያችን በሀገራችን ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በ2013 ዓ.ም ከተገኘው ሪፖርት መረዳት እንደተቻለው ጠቅላላ አካልጉዳተኛ ተቀጣሪዎች 6000 አይሞሉም፤ ለነገሩ የተማሩትም 10000 ስለመሙላታቸው መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡
አንቀጽ 27
1. ተዋዋይ መንግሥታት አካል ጉዳተኞች ከሌሉች ጋር በእኩል ደረጃ ላላቸው የመሥራት መብት ዕውቅና ይሰጣሉ፡፡ ይኸውም በነፃ የተመረጠን ወይም ግልፅ፣ ሁሉንም አካታችና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት ባለው የስራ ገበያና ቅጥር የተገኘንና ተቀባይነት የተሰጠውን ሥራ ሰርቶ መተዳደሪያ የማግኘት መብትን ይጨምራል፡፡ ተዋዋይ መንግሥታት ይልቁንም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በስራ ላይ ለማዋል ይቻል ዘንድ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ በስራ ሂደት የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በሚያካትት መንገድ የሰዎች የመስራት መብት እንዲጠበቅና ተሻሽሎ እውን እንዲሆን የሚያደርጉ ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ፡-
ሀ) ምልመላን፣ ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ቅጥርን፣ በቋሚ ስራ ላይ መቀጠልን፣ የሙያ እድገትን ደህንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የስራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ሁሉ አስመልክቶ በአካል ጉዳት ላይ የተመሰረተ ማናቸውም አይነት አድልዎ እንዳይፈፀም መከላከል!
ለ) ከወከባ መጠበቅንና ለቅሬታዎች የመፍትሄ ምላሽ ማግኘትን ጨምሮ እኩል ዋጋ ላለው ስራ እኩል ዕድልዎችንም ሆነ እኩል ክፍያ የማግኘት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ጤናማ የስራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩል ደረጃ ለአካል ጉዳተኞች ትክክለኛና ምቹ የስራ ሁኔታ የማግኘት መብትን መጠበቅ!
ሐ) አካል ጉዳተኞች ከሌሎች ጋር በእኩል ደረጃ በስራና በሙያ ማኀበራት የመደራጀት መብት እንዳላቸው ማረጋገጥ!
መ) አካል ጉዳተኞች የአጠቃላይ፣ የቴክኒክና ሙያ ነክ የአመራር መርሃ ግብሮች እንዲሁም የምደባ አገልግሎት፣ የሙያዊና ተከታታይነት ያለው ስልጠና ውጤታማ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ማስቻል!
ሠ) ለአካል ጉዳተኞች በሥራ ገበያ ውስጥ የቅጥርና የሙያ እድገት እድሎችን ከፍ ማድረግና እንዲሁም ሥራ ፍለጋ፣ ግኝት፣ ቆይታና የመልሶ ቅጥር ሁኔታዎች ረገድ ድጋፍ ማድረግ!
ረ) በግል ሥራ የመፍጠር ፣ ገቢ በሚያስገኝ ተግባር የመሰማራት፣ የሕብረት ሥራ ማሕበራትን የማሳደግና የራስን ሥራ የመጀመር ዕድሎችን ከፍ ማድረግ!
ሰ) በመንግሥት የሥራ ዘርፎች አካል ጉዳተኞችን በሰራተኝነት መቅጠር!
ሸ) የድጋፍ መርሀ ግብሮችን፣ ማበረታቻዎችንና ሌሎች እርምጃዎች ሊያካትቱ በሚችሉ ተገቢ ፖሊሲዎችና እንቅስቃሴዎች አማካኝነት በግሉ ዘርፍ በኩል የአካል ጉዳተኞችን የስራ ቅጥርና ስምሪት ማሻሻል!
ቀ) በሥራ ቦታ ለአካል ጉዳተኞች ምክንያታዊ ተቀባይነት ያለው ማስተካኪያ የቀረበላቸው መሆኑን ማረጋገጥ!
በ) ክፍት በሆነው የሥራ ገበያ ዘንድ የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ተሞክሮ ግኝት ማሻሻልና
ተ) የአካል ጉዳተኞችን የተለየ ስልጠና፣ ሙያዊ ተሃድሶ፣ ስራ ይዞ መቆየትና ወደ ስራ የመመለስ መርሃ ግብሮችን ማስፋፋት፡፡
ሲሳይ ሰማኝ
ኢትዮጵያ ከፍ ትበል!!!!
ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም

ክቡራን ሰላማችሁ ይብዛ!!
የዓለማቀፉ አካልጉዳተኞች መብቶች ስምምነት ስለተደራሽነቱ የደነገገውንና ሀገራችን በአዋጅ ቁጥር 676/2002 በማጽደቅ የሕጎቿን አካል በማድረግ ለተፈጻሚነቱ ግዴታ የገባችለትን እንደሚከተለው ይድረስልኝ፡!
ተደራሽነት የሚመለከተው አንቀጽ 9 ነው፡፡
አካል ጉዳተኞች ኑሯቸውን በነፃነት እንዲመሩና በየትኛውም የሕይወት መስክ ያልተገደበ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል ተዋዋይ መንግሥታት እነዚሁ ወገኖች ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር ባልተናነሰ ሁኔታ ቁሳዊ አካባቢን የመድረስም ሆነ በመጓጓዣ ዘዴዎች፣ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችንና ስርዓቶችን ጨምሮ በመረጃና መገናኛ አውታሮች እንዲሁም በከተማም ይሁን በገጠር ለሕዝብ ክፍት በተደረጉ ተቋማትና አገልግሎቶች የመጠቀም ዕድል የተመቻቸላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተገቢነት ያላቸውን እርምጃዎች ይወስዳሉ፡፡
በተደራሽነት ላይ የተጋረጡትን መሰናክሎችና ገደቦች መለየትና ማስወገድን የሚያጠቃልሉት እነዚህ እርምጃዎች ከሁሉ በፊት ቀጥሎ በተመለከቱት ላይ ተፈፃሚዎች ይሆናሉ፡፡
ሀ) ሕንፃዎች፣ መንገዶች፣ የመጓጓዣ ዘዴዎችና እንደ ትምህርት ቤቶች፣ የመኖሪያ ሥፍራዎች፣ የሕክምና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶችና የስራ ማከናወኛ ቦታዎች ያሉ የቤት ውስጥና የቤት ውጭ መገልገያ ተቋማት!
ለ) የኤሌክትሮኒክስና የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎቶችን ጨምሮ የመረጃ፣ የመገናኛና ሌሎች አገልግሎቶች፡፡
2. ተዋዋይ መንግስታት በተጨማሪ ከዚህ በታች የተመለከቱትን በስራ ላይ ለማዋል ተገቢ እርምጃዎችን ይወስዳሉ፡፡
ሀ) ለሕዝብ ክፍት የተደረጉ ወይም የተመቻቹ ተቋማትንና አገልግሎቶችን ለመድረስ የሚያስችሉ ዝቅተኛ መስፈርቶችንና መመሪያዎችን ማዘጋጀት፣ በይፋ ማውጣትና ተግባራዊነታቸውን መቆጣጠር!
ለ) ለሕዝብ ክፍት የሆኑ አገልግሎቶችን በማመቻቸትና በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ የግል ድርጅቶች እነዚሁ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች ጭምር ተደራሽነት እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች ሁሉ ግምት ውስጥ ማስገባታቸውን ማረጋገጥ!
ሐ) አካል ጉዳተኞችን በሚገጥሟቸው የተደራሽነት ችግሮች ዙሪያ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ወገኖች ስልጠና መስጠት!
መ) ለሕዝብ ክፍት በሆኑ ሕንፃዎችና ሌሎች መገልገያ ተቋማት ውስጥ በግልጽ የሚታዩ ምልክቶችን፣ ብሬሎችንና በቀላሉ አንብቦ ለመረዳት የሚያስችሉ ቅጾችን ማስቀመጥ ወይም ማቅረብ!
ሠ) የቀጥታ ድጋፍ ዓይነቶችንና መሪዎችን፣ አንባቢያንንም ሆነ በምልክት ቋንቋ አጠቃቀም የሰለጠኑ አስተርጓሚዎችን ጨምሮ ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ሕንፃዎችንና ሌሎች መገልገያ ተቋማትን ተደራሽነት የሚያመቻቹ አማካዮችን ዝግጁ ማድረግ!
ረ) አካል ጉዳተኞች መረጃ የማግኘት ዕድል የተጠበቀላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሌሎች ተገቢነት ያላቸውን የእርዳታና የድጋፍ ዓይነቶችን ማስፋፋት!
ሰ) አካል ጉዳተኞች የመረጃን መረብን ጨምሮ በአዳዲስ የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችና ሥርዓቶች የሚጠቀሙበትን ዕድል ከፍ ማድረግና!
ሸ) ለወደፊቱ በዝቅተኛ ዋጋ ሊቀርቡ የሚችሉበት ዕድል እስኪፈጠር ድረስ ምቹና ተደራሽነት ያላቸውን የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችና ሥርዓቶች ዝግጅት፣ ልማት፣ አመራረትና ሥርጭት ከመነሻው ጀምሮ ማስተዋወቅ
የሚል ዝርዝር ካስቀመጠው በመነሳት ይመስላል ኢትዮጵያም የህንጻ አዋጅ 624/2001በአንቀጽ 36 ማንኛውም ህንጻ ለአካል ጉዳተኞች በተሽከርካሪ ወንበር መንቀሳቀስ በሚያመች መለኩ እንዲገነባ፣ መጸዳጃቤቶችም ለአጠቃቀም በሚያመች መልኩ መሰራት እንዳለባቸው፤
ደንግጋ ትገኛለች፡፡
ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን ለኛ!!!