የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 28 እና 29 ቀን 2015 ኣ.ም በአ/አ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 እና በዲስፕሊን ክስ አቀራረብና አፈጻጸም ዙሪያ ስልጠና የሰጠ ሲሆን በስልጠናው ከ270 በላይ ለሆኑ የክ/ከተማ፣ የወረዳ እና የት/ቤቶች የዲስፕሊን ኮሚቴ አባላት ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል። እነሆ ከመድረኩ የተወሰዱ ጥቂት ምስሎች!።
በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ርቂቅ መመሪያ ላይ በ 8/3/2015 ዓ.ም ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ባዘጋጀዉ ስብሰባ ላይ በመገኘት የተሰጠ ስልጠና።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በቀን 10/03/2015 ዓ.ም የ 17ኛ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክብረ በአል "ሕብረብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ባከበረበት ወቅት የቦሌ ክ/ከ/የሕ/ስር/ምክ/መስ/ዳ በሕብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርአት ምንነት፣ባህርያት እና የኢትዬጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናውም ከቦሌ ክፍለ ከተማ ሁሉም ወረዳዎች ለተወጣጡ የሕብረተሠብ አካላት ፌደራሊዝም ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ የፌዴራሊዝም አይነቶች፣ አንድ የሚያደርጋቸዉን ባህርያት እንዲሁም ልዩነታቸውን፣ በመጨረሻም ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ስልጠናው ተሠጥቷል። ለሠልጣኞችም ስለፌደራሊዝም ያላቸውን እውቀት በመጨመር ለሠላም አለመኖር ምክንያቱ የእኛ አስተሳሰብ ችግር እንጂ ከስርአቱ አለመሆኑን እንዲገነዘቡት በማሳሰብ ስልጠናው ተጠናቋል።
ሰላም! እንደው ቸር ከርማችኋል?
ትንሽ ስለደመወዝ ልናወጋችሁ ብቅ ብለናል። ቀድሞ ነገር ግን “ደመወዝ” ምንድን ነው?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 በአንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 12 ላይ “ደመወዝ” ለሚለው ቃል የሚከተለውን ትርጓሜ ሰጥቶታል፥
“ደመወዝ” ማለት በአንድ የሥራ ደረጃ ለተመደቡ ሥራዎች የተወሰነ መነሻ ክፍያ ወይም የእርከን ክፍያ ነው”
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በየወሩ መጨረሻ ለሠራተኞቹ ወይም ለሕጋዊ ወኪሎቻቸው የደመወዝ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ ያለበት ሲሆን እኩል ዋጋ ያላቸው ሥራዎች ሁሉ እኩል መነሻ ደመወዝ ይኖራቸዋል።
ይህን ልብ ይበሉ!
የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፥
ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፣
ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት
ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም።
በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በሕግ መሠረት ከሠራተኛ ደመወዝ በየወሩ የሚቆረጠውም ቢሆን ከደመወዙ አንድ ሦስተኛ አይበልጥም።

ህዳር 17 ቀን 2015 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህ/ስ/ም/መ/ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቃቤ-ሕግ)