በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ርቂቅ መመሪያ ላይ በ 8/3/2015 ዓ.ም ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ባዘጋጀዉ ስብሰባ ላይ በመገኘት የተሰጠ ስልጠና።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በቀን 10/03/2015 ዓ.ም የ 17ኛ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክብረ በአል "ሕብረብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ባከበረበት ወቅት የቦሌ ክ/ከ/የሕ/ስር/ምክ/መስ/ዳ በሕብረ ብሔራዊ ፌደራል ስርአት ምንነት፣ባህርያት እና የኢትዬጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል። በስልጠናውም ከቦሌ ክፍለ ከተማ ሁሉም ወረዳዎች ለተወጣጡ የሕብረተሠብ አካላት ፌደራሊዝም ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ የፌዴራሊዝም አይነቶች፣ አንድ የሚያደርጋቸዉን ባህርያት እንዲሁም ልዩነታቸውን፣ በመጨረሻም ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ስልጠናው ተሠጥቷል። ለሠልጣኞችም ስለፌደራሊዝም ያላቸውን እውቀት በመጨመር ለሠላም አለመኖር ምክንያቱ የእኛ አስተሳሰብ ችግር እንጂ ከስርአቱ አለመሆኑን እንዲገነዘቡት በማሳሰብ ስልጠናው ተጠናቋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም! እንደው ቸር ከርማችኋል?
ትንሽ ስለደመወዝ ልናወጋችሁ ብቅ ብለናል። ቀድሞ ነገር ግን “ደመወዝ” ምንድን ነው?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 በአንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 12 ላይ “ደመወዝ” ለሚለው ቃል የሚከተለውን ትርጓሜ ሰጥቶታል፥
“ደመወዝ” ማለት በአንድ የሥራ ደረጃ ለተመደቡ ሥራዎች የተወሰነ መነሻ ክፍያ ወይም የእርከን ክፍያ ነው”
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በየወሩ መጨረሻ ለሠራተኞቹ ወይም ለሕጋዊ ወኪሎቻቸው የደመወዝ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ ያለበት ሲሆን እኩል ዋጋ ያላቸው ሥራዎች ሁሉ እኩል መነሻ ደመወዝ ይኖራቸዋል።
ይህን ልብ ይበሉ!
የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፥
ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፣
ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት
ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም።
በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በሕግ መሠረት ከሠራተኛ ደመወዝ በየወሩ የሚቆረጠውም ቢሆን ከደመወዙ አንድ ሦስተኛ አይበልጥም።
ህዳር 17 ቀን 2015 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህ/ስ/ም/መ/ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቃቤ-ሕግ)

የፍርድ ቤቶች ስልጣን
የፍርድ ቤቶች አንድን ክርክር አይተዉ አከራክረዉ ለመወሰን ስልጣን አላቸዉ የሚባለዉ በህግ ተወስኖ ሲሰጣቸዉ ነዉ፡፡የፍርድ ቤቶችን ስልጣን ለይተዉ ከቀረቡ ህጎች መካከልም የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013፣ የተሻሻለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ቁጥር 361/1995፣ የኢትዮጵያ ፍትሐብሔር ስነ-ስርአት ሕግ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ የፍርድ ቤቶች ስልጣንም ሲባል ከማህበራዊ ፍርድቤት ተነስቶ እስከ ፌደራል ፍርድ ቤቶች ያሉትን ያካትታል፡፡
የአንድ ፍርድ ቤት ስልጣንም ሊወሰን የሚችለዉ፡-
1. በሚከራከሩበት ንብረት የዋጋ መጠን
2. በተከራካሪ ወገኖች ማንነት
3. የሚከራከሩበት ንብረት የሚገኝበት ቦታ
4. ተከራካሪ ወገኖች የሚገኙበት ቦታ
5. በዉል ጉዳይ ከሆነ ዉሉ የተፈረመበት ቦታ፣ ሊፈጸምበት የታሰበዉ ቦታ በመሳሰሉት
6. በሚከራከሩበት ጉዳይ የግዝፈት መጠን እንዲሁም በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ይወሰናል፡፡
የከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ስልጣንን በተመለከተ
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ ስንመለከት አንቀጽ 4(16) ላይ የወንጀል ጉዳዮችን የሚያይበት ስልጣኑ የተለየ ሲሆን በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዙሪያ አንቀጽ 5(ደ) ስር ተዘርዝረዉ ይገኛሉ፡፡
የተሻሻለዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ቁጥር 361/1995 በሌላ መልኩ ደግሞ በአንቀጽ 41 ላይ የፍትሐብሔር እና ወንጀል ስልጣናቸዉን አስቀምጧል
ይህን ካልን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሉት ፍርድ ቤቶች የመጀመሪያ ደረጃ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ናቸዉ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ለከተማዉ የተሰጠዉን የፍትሐብሔር እና የወንጀል ጉዳዮች አጠቃሎ የሚያይ ሲሆን የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን በይግባኝ ያያል። ነገር ግን በይግባኝ ፍርድ ቤቱ በተሰጠዉ ዉሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን በአገሪቱ ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠን የመጨረሻ ዉሳኔ የማየት ስልጣን ለተሰጠዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ማቅረብ ይቻላል። በመጨረሻም ህገ መንግስታዊ ዉሳኔ ለሚያስፈልጋቸዉ ጉዳዮች የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፍትህ ስርዓቱን የመጨረሻ ዉሳኔ ይሰጣል።
ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስንመጣ ከከተማ ፍርድ ቤቶች የሚለያቸዉ 3 እርከን ስላላቸዉ ነው። የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ናቸዉ። የፍርድ ስልጣናቸዉም በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ላይ ተለይቶ ተቀምጥዋል። አንድ ተከራካሪ ወገንም የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን አቅርቦ ዳኝነት የጠየቀበት ጉዳይ ዉድቅ ቢደረግበት የይግባኝ ቅሬታዉን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ሲሆን የመጀመሪያው ዉሳኔ ከጸና ጉዳዩን ለሰበር ችሎት አቅርቦ የህግ ስህተት ካለ ከማሳረም ዉጪ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን አቅርቦ ለሁለተኛ ግዜ ይግባኝ ማቅረብ አይችልም። ይህም ማለት አንድ ጉዳይ ከአንድ ግዜ በላይ ይግባኝ ሊባልበት አይችልም። የከፍተኛ ፍርድ ቤትም በመጀመሪያ ፍቅደ ስልጣኑ ያየዉን ክርክር ይግባኝ ሊባልበት የሚችለዉ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሆናል።
ዉበአለም መስፍን የቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ

የማስረጃ ህግ ጽንሰ ሀሳቦች
= ማስረጃ ምንድነዉ ?
ማስረጃ በመመርመር ላይ ያለ ወይም አከራካሪ የሆነ ፍሬ ነገር ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ፍሬ ነገር ሲብራራ ደግሞ ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ማስረጃ ማለት ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ሰዎችም ብዙ ግዜ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡት የዚህን ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር ወይም እዉነት/ሀሰት መሆን እንዲረጋገጥላቸዉ ስለሚፈልጉ ነዉ፡፡ የዳኞችም ስራ ይህ ፍሬ ነገር በማስረጃ መረጋገጡን ማጣራት ነዉ፡፡
= የማስረጃ አይነቶች
1. የቃል ማስረጃ፡- በምስክር አንደበት የሚነገር ወይም የሚሰማ
2. የሰነድ ማስረጃ፡-ወረቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኝና የሚነበብ ወይም ሀሳብ የያዘ ነገር
3. የቁሳዊ/ገላጭ ማስረጃ፡-መጠኑን ፣ዓይነቱን…ወዘተ የሚያሳይ ነዉ፡፡ዳኞች በራሳቸው የስሜት ህዋሳት ተረድተው ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሚቀርብ ዳኞች በአካል የሚመለከቱትን፣ የሚሰሙትን…የሚያመለከት ነው፡፡
4. የሳይንሳዊ ማስረጃ፡-የህክምና ሳይንስን ጨምሮ በሌሎች ሳይንሳዊ ዘዴዎች የተሰበሰበን፣ የተገኘን፣ የታወቀን፣ የተረጋገጠን… ፍሬ ነገር የሚመለከት
5. የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃ፡-በኮምፒውተር፣ በኢንተርኔት ወይም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ውስጥ የሚገኝ የማይጨበጥ/የማይዳሰስ መረጃ ናቸዉ።
= በማስረጃ የሚረጋገጥ እና የማይረጋገጥ ፍሬ ነገር ምን ማለት ነዉ?
የሚረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
1. ከመሰረታዊ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ
2. ከማስረጃ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ ተቀጽላ ወይም ተጓዳኝ ፍሬ ነገሮች፤
3. በጭብጥ ለተያዙ ፍሬ ነገሮች አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች ናቸዉ፡፡
እነዚህንም ፍሬ ነገሮች
በፍሬ ነገር ማረጋገጫ ዓይነቶች-
• በፍርድ ቤት ፊት የሚሰጥ የእምነት ቃል (Formal Admission)፣
• የዳኞች ግንዛቤ መዉሰድ/መያዝ (Judicial Notice)፣
• የህግ ግምት (Presumption)፣
• የመኃላ ቃል (Oath)፣
• ማስረጃ (Evidence) ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
= የማይረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
- በፍ/ቤት ፊት በተከራካሪ ወገን የታመኑ (Formally Admitted Facts)
- በዳኞች ግንዛቤ የሚያዝባቸው (Facts which judges take Judicial Notice)
- በህግ ግምት የሚወሰድባቸው (Presumed Facts) ሆነው ከተገኙ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን ፍሬ ነገሮች ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልግ በነዚህ በቀረቡት ሁኔታዎች ብቻ ማስረዳት ይቻላል፡፡
= አግባብነት ወይም አስፈላጊነት እና ተቀባይነት ያለዉ ማስረጃ ምንነት
አግባብነት፡- አግባብነት ሲባል አንድ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ከሌላ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ጋር ያለውን ተዛመዶ ወይም ትስስር የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት በተከራካሪ ወገን የሚቀርብ ማንኛዉም ማስረጃ ሳይሆን በግራቀኝ ለቀረበዉ ክርክር ተገቢነት ኖሮት ሊያስረዳ የሚችል ማለት ነዉ፡፡
ተቀባይነት፡- ሲባል አንድ ማስረጃ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ ችሎቱ ይቀበለዋል ወይስ አይቀበለዉም የሚለዉን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ችሎትም ማስረጃዉን ሊቀበለዉ ወይም ማስረጃዉን ሊተወዉ የሚችለዉ ደስ ስላለዉ ወይም ስላላለዉ ሳይሆን ማስረጃዉ በህጋዊ ሁኔታ መምጣት አለመምጣት ማጣራት እንዳለበት የሚያሳይ ሃሳብ ነዉ፡፡
= ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ወይም የማን ሸክም ይሆናል?
ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ሲባል መጀመሪያ ማስረጃ ማን ማቅረብ አለበት የሚለዉን ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነዉ፡፡ይህም ከሁለቱ ወገኖች አቤቱታ ይዘትና በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው አንጻር ታይቶ የሚለይ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ነገር እንዳለ የሚከራከር ወገን ይህ ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ቀድሞ የማስረዳት ወይም ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ፍሬነገሩም እንዳለ ተከራካሪዉ ካስረዳ ይህን ማስረጃ በማቅረብ መቀልበስ ወይም መቃወም ያለበት የሌላኛዉ ወገን ድርሻ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ይህም የማስረዳት ሸክም ዞረ ይባላል፡፡
= የማስረጃ አቀራረብ መንገዶች
በመሰረቱ ማስረጃ ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት ከአቤቱታ ወይም ከመልስ ጋር ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ማስረጃዎች በምንፈልገዉ ሰሀት እና በምንጠይቀዉ ሰአት ላናገኛቸዉ እንችላለን፡፡ እነዚህንም ማስረጃዎች በወንጀልም ይሁን በፍትሐብሔር ክርክሮች እንድናቀርብ የምንጠይቅባቸዉ አግባቦች አሉ፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለዉ በማስረጃ ዝርዝራችን ላይ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲቀርቡ በመጠየቅ፣ክስ ከመሰማቱ በፊት በችሎት በማቅረብ፣ እንዲሁም ክርክሩ እየተካሄደ ባለበት ግዜ በበቂ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ ማስረጃዎች ለችሎቱ በማቅረብ ነዉ፡፡

👍2
የሙስናፅንስሃሳብ.
1.
አደራን አለመጠበቅ፣ እምነትማጉደል፣
በጉቦ፣በምልጃናበአድሎ፣ሐቅን፣ውሳኔንወይምፍትህንማዛባት፣
2. ለግልወይምለቡድንጥቅምሲባል፣ሥርዓቶችን፣ደንቦችን፣ህጐችንናመርሆዎችንመጣስ ነው፡፡
3.
የመንግስትን ሥራ ሥነ ምግባራዊና ህጋዊ መሠረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ ተመርኩዞ አለመስራት፡፡
4. በመንግስትናበህዝብየተሰጠንሥልጣንናኃላፊነትለግልጥቅም፣ወይምሌላንለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል በስልጣን አለአግባብ መገልገል ነው፡፡
የሙስና ዓይነቶች
ሀ. ዝቅተኛ ሙስና (Petty Corruption)
ከመንግስትናከህዝብአገልግሎትአሰጣጥጋርበተያያዘሲሆንበየደረጃውበሚገኙ፡-
የመንግስትሠራተኞች፣
ባለስልጣኖችና በአገልግሎት ፈላጊ ግለሰቦች የሚፈፀምነው፡፡
ለ.ከፍተኛሙስና (GrandCorruption)
መጠነ ሰፊ የሆነ የመንግስት ሃብትና ንብረት፣በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችና በከፍተኛ የፖለቲካአመራርአካላትበአጭርጊዜውስጥየሚዘረፍበትናየሚመዘበርበትነው፡፡
ምሳሌ፡- የፕሮጀክት ውሎች፣
ባንኮች፣
የገቢ ሰብሳቢዎች
መሰረተ ልማት ላይ የተሰማሩ መ/ቤቶች፣ /ት/ቤት፣ መንገድ፣ ውሃ፣ ቴሌ፣
መብራት፣ ጤና ወዘተ/
ሐ. ፖለቲካዊሙስና
የአንድን ማህበረሰብ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕሴቶችና ልማዶችን በመጣስ ይፈፀማል፡፡ በአጠቃላይሙስና፡- ልማትእንዲቀጭጭ፣
የአገር ኢኮኖሚ እድገት እንዲገታ፣ ኪሳራና ውድቀት እንዲስፍንና፣ ድህነት እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡

Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ሕዳር 19 ቀን 2015 ኣ.ም ለ250 የክ/ከተማው የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ። በስልጠናውም የሰብአዊ መብቶች ምንነትና አስፈላጊነት፣ የእግድ አሰጣጥና ተዛማጅ ችግሮች፣ የሊዝ ሕግ እና የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርአት አስመልክቶ ግንዛቤ ተፈጥሯል። ሰልጣኞችም ስልጠናው ለእለት ተእለት ስራቸው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መሰጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
እነሆ ጥቂት ምስሎች!
እነሆ ጥቂት ምስሎች!