የማስረጃ ህግ ጽንሰ ሀሳቦች
= ማስረጃ ምንድነዉ ?
ማስረጃ በመመርመር ላይ ያለ ወይም አከራካሪ የሆነ ፍሬ ነገር ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ፍሬ ነገር ሲብራራ ደግሞ ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ማስረጃ ማለት ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ሰዎችም ብዙ ግዜ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡት የዚህን ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር ወይም እዉነት/ሀሰት መሆን እንዲረጋገጥላቸዉ ስለሚፈልጉ ነዉ፡፡ የዳኞችም ስራ ይህ ፍሬ ነገር በማስረጃ መረጋገጡን ማጣራት ነዉ፡፡
= የማስረጃ አይነቶች
1. የቃል ማስረጃ፡- በምስክር አንደበት የሚነገር ወይም የሚሰማ
2. የሰነድ ማስረጃ፡-ወረቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኝና የሚነበብ ወይም ሀሳብ የያዘ ነገር
3. የቁሳዊ/ገላጭ ማስረጃ፡-መጠኑን ፣ዓይነቱን…ወዘተ የሚያሳይ ነዉ፡፡ዳኞች በራሳቸው የስሜት ህዋሳት ተረድተው ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሚቀርብ ዳኞች በአካል የሚመለከቱትን፣ የሚሰሙትን…የሚያመለከት ነው፡፡
4. የሳይንሳዊ ማስረጃ፡-የህክምና ሳይንስን ጨምሮ በሌሎች ሳይንሳዊ ዘዴዎች የተሰበሰበን፣ የተገኘን፣ የታወቀን፣ የተረጋገጠን… ፍሬ ነገር የሚመለከት
5. የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃ፡-በኮምፒውተር፣ በኢንተርኔት ወይም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ውስጥ የሚገኝ የማይጨበጥ/የማይዳሰስ መረጃ ናቸዉ።
= በማስረጃ የሚረጋገጥ እና የማይረጋገጥ ፍሬ ነገር ምን ማለት ነዉ?
የሚረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
1. ከመሰረታዊ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ
2. ከማስረጃ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ ተቀጽላ ወይም ተጓዳኝ ፍሬ ነገሮች፤
3. በጭብጥ ለተያዙ ፍሬ ነገሮች አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች ናቸዉ፡፡
እነዚህንም ፍሬ ነገሮች
በፍሬ ነገር ማረጋገጫ ዓይነቶች-
• በፍርድ ቤት ፊት የሚሰጥ የእምነት ቃል (Formal Admission)፣
• የዳኞች ግንዛቤ መዉሰድ/መያዝ (Judicial Notice)፣
• የህግ ግምት (Presumption)፣
• የመኃላ ቃል (Oath)፣
• ማስረጃ (Evidence) ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
= የማይረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
- በፍ/ቤት ፊት በተከራካሪ ወገን የታመኑ (Formally Admitted Facts)
- በዳኞች ግንዛቤ የሚያዝባቸው (Facts which judges take Judicial Notice)
- በህግ ግምት የሚወሰድባቸው (Presumed Facts) ሆነው ከተገኙ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን ፍሬ ነገሮች ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልግ በነዚህ በቀረቡት ሁኔታዎች ብቻ ማስረዳት ይቻላል፡፡
= አግባብነት ወይም አስፈላጊነት እና ተቀባይነት ያለዉ ማስረጃ ምንነት
አግባብነት፡- አግባብነት ሲባል አንድ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ከሌላ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ጋር ያለውን ተዛመዶ ወይም ትስስር የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት በተከራካሪ ወገን የሚቀርብ ማንኛዉም ማስረጃ ሳይሆን በግራቀኝ ለቀረበዉ ክርክር ተገቢነት ኖሮት ሊያስረዳ የሚችል ማለት ነዉ፡፡
ተቀባይነት፡- ሲባል አንድ ማስረጃ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ ችሎቱ ይቀበለዋል ወይስ አይቀበለዉም የሚለዉን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ችሎትም ማስረጃዉን ሊቀበለዉ ወይም ማስረጃዉን ሊተወዉ የሚችለዉ ደስ ስላለዉ ወይም ስላላለዉ ሳይሆን ማስረጃዉ በህጋዊ ሁኔታ መምጣት አለመምጣት ማጣራት እንዳለበት የሚያሳይ ሃሳብ ነዉ፡፡
= ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ወይም የማን ሸክም ይሆናል?
ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ሲባል መጀመሪያ ማስረጃ ማን ማቅረብ አለበት የሚለዉን ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነዉ፡፡ይህም ከሁለቱ ወገኖች አቤቱታ ይዘትና በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው አንጻር ታይቶ የሚለይ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ነገር እንዳለ የሚከራከር ወገን ይህ ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ቀድሞ የማስረዳት ወይም ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ፍሬነገሩም እንዳለ ተከራካሪዉ ካስረዳ ይህን ማስረጃ በማቅረብ መቀልበስ ወይም መቃወም ያለበት የሌላኛዉ ወገን ድርሻ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ይህም የማስረዳት ሸክም ዞረ ይባላል፡፡
= የማስረጃ አቀራረብ መንገዶች
በመሰረቱ ማስረጃ ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት ከአቤቱታ ወይም ከመልስ ጋር ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ማስረጃዎች በምንፈልገዉ ሰሀት እና በምንጠይቀዉ ሰአት ላናገኛቸዉ እንችላለን፡፡ እነዚህንም ማስረጃዎች በወንጀልም ይሁን በፍትሐብሔር ክርክሮች እንድናቀርብ የምንጠይቅባቸዉ አግባቦች አሉ፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለዉ በማስረጃ ዝርዝራችን ላይ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲቀርቡ በመጠየቅ፣ክስ ከመሰማቱ በፊት በችሎት በማቅረብ፣ እንዲሁም ክርክሩ እየተካሄደ ባለበት ግዜ በበቂ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ ማስረጃዎች ለችሎቱ በማቅረብ ነዉ፡፡
ዉበአለም መስፍን የቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ

👍2
የሙስናፅንስሃሳብ.
1.
አደራን አለመጠበቅ፣ እምነትማጉደል፣
በጉቦ፣በምልጃናበአድሎ፣ሐቅን፣ውሳኔንወይምፍትህንማዛባት፣
2. ለግልወይምለቡድንጥቅምሲባል፣ሥርዓቶችን፣ደንቦችን፣ህጐችንናመርሆዎችንመጣስ ነው፡፡
3.
የመንግስትን ሥራ ሥነ ምግባራዊና ህጋዊ መሠረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ ተመርኩዞ አለመስራት፡፡
4. በመንግስትናበህዝብየተሰጠንሥልጣንናኃላፊነትለግልጥቅም፣ወይምሌላንለመጥቀም ወይም ለመጉዳት ሲባል በስልጣን አለአግባብ መገልገል ነው፡፡
የሙስና ዓይነቶች
ሀ. ዝቅተኛ ሙስና (Petty Corruption)
ከመንግስትናከህዝብአገልግሎትአሰጣጥጋርበተያያዘሲሆንበየደረጃውበሚገኙ፡-
የመንግስትሠራተኞች፣
ባለስልጣኖችና በአገልግሎት ፈላጊ ግለሰቦች የሚፈፀምነው፡፡
ለ.ከፍተኛሙስና (GrandCorruption)
መጠነ ሰፊ የሆነ የመንግስት ሃብትና ንብረት፣በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችና በከፍተኛ የፖለቲካአመራርአካላትበአጭርጊዜውስጥየሚዘረፍበትናየሚመዘበርበትነው፡፡
ምሳሌ፡- የፕሮጀክት ውሎች፣
ባንኮች፣
የገቢ ሰብሳቢዎች
መሰረተ ልማት ላይ የተሰማሩ መ/ቤቶች፣ /ት/ቤት፣ መንገድ፣ ውሃ፣ ቴሌ፣
መብራት፣ ጤና ወዘተ/
ሐ. ፖለቲካዊሙስና
የአንድን ማህበረሰብ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዕሴቶችና ልማዶችን በመጣስ ይፈፀማል፡፡ በአጠቃላይሙስና፡- ልማትእንዲቀጭጭ፣
የአገር ኢኮኖሚ እድገት እንዲገታ፣ ኪሳራና ውድቀት እንዲስፍንና፣ ድህነት እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡

Forwarded from የአ.አ ስርጸት ዐቃቢያን ሕግ መረጃ ልውውጥ (fasika aggena)
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ሕዳር 19 ቀን 2015 ኣ.ም ለ250 የክ/ከተማው የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ። በስልጠናውም የሰብአዊ መብቶች ምንነትና አስፈላጊነት፣ የእግድ አሰጣጥና ተዛማጅ ችግሮች፣ የሊዝ ሕግ እና የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርአት አስመልክቶ ግንዛቤ ተፈጥሯል። ሰልጣኞችም ስልጠናው ለእለት ተእለት ስራቸው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መሰጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
እነሆ ጥቂት ምስሎች!
እነሆ ጥቂት ምስሎች!
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ሕዳር 26 ቀን 2015 ኣ.ም ለ250 የክ/ከተማው የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ። በስልጠናውም የሰብአዊ መብቶች ምንነትና አስፈላጊነት፣ የእግድ አሰጣጥና ተዛማጅ ችግሮች፣ የሊዝ ሕግ እና የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርአት አስመልክቶ ግንዛቤ ተፈጥሯል። ሰልጣኞችም ስልጠናው ለእለት ተእለት ስራቸው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መሰጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
እነሆ ጥቂት ምስሎች!
እነሆ ጥቂት ምስሎች!