የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
275 subscribers
366 photos
3 videos
137 files
97 links
ይህ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣ አዳዲስ ሕጎች የሚጋሩበት፣ ሕግ ነክ ዜናዎችና መረጃዎች የሚተላለፉበት፣ በዳይሬክቶሬቱ የተሰጡ የንቃተ-ሕግ ስልጠናዎች፣ የሕግ መልዕክቶች፣ በራሪ ጽሑፎች እና መሰል ሰነዶች የሚለቀቁበት ነው።
መልካም ቆይታ!
Download Telegram
የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ሕዳር 26 ቀን 2015 ኣ.ም ለ250 የክ/ከተማው የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ። በስልጠናውም የሰብአዊ መብቶች ምንነትና አስፈላጊነት፣ የእግድ አሰጣጥና ተዛማጅ ችግሮች፣ የሊዝ ሕግ እና የአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርአት አስመልክቶ ግንዛቤ ተፈጥሯል። ሰልጣኞችም ስልጠናው ለእለት ተእለት ስራቸው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መሰጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
እነሆ ጥቂት ምስሎች!
ሰላም! እንዴት ከርማችኋል!
ምንም አይነት እውቀት፣ ክህሎት፣ የስራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም እንኳን የመንግስት ሰራተኞች መሆን የማይችሉ ሰዎች እንዳሉ ያውቃሉ?
እንግዲያውስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም በአንቀጽ 14 የመንግሥት ሠራተኛ ሆነው ሊቀጠሩ ስለማይችሉ ሰዎች የደነገገውን ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፤
ሀ) ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሰው፤
ለ) ቅጣቱ ከተፈጸመ፣ በይርጋ ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሠረዘ በኋላ 5 ዓመት ያለፈው ካልሆነ በስተቀር የሙስና፣ የእምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣ የማጭበርበር ወይም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈረደበት ማንኛውም ሰው፤
ሐ) የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ የሌለው ሰው፤
መ) በሕግ በተደነገገው መሠረት ቃለ-መሀላ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው፤
ሠ( ከሥራ ከተሰናበተ ጊዜ ጀምሮ አምስት ዓመት ካልሞላው በስተቀር ከማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በዲስፕሊን ጉድለት ምክንያት ከሥራ የተሰናበተ ሰው፤
የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ ሊቀጠር አይችልም።
በመሆኑም ማንኛውም ሰው በመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ ለማገልገል ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ፥
ሀ) ከኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ምርመራ በስተቀር የጤንነት ማረጋገጫ የሕክምና ምርመራ እና
ለ) ከሙስና፣ ከእምነት ማጉደል፣ ከስርቆት፣ ከማጭበርበር ወይም ከአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከፖሊስ የተሰጠ ማስረጃ
የማቅረብ ግዴታ አለበት።

ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ.ም
ፋሲካ አጌና (የህ/ስ/ም/መ/ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቃቤ-ሕግ)
👍1
በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ጽንሰ ሀሳብ እና ገዢ ህጎቹ
ለሰዉ ልጆች በህግ እዉቅና ካገኙ ሰብአዊ መብቶች አንዱ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብት ነዉ።ይህም መብት በተለያዩ ምክንያቶች ሊገደብ ይችላል። አንዱ ምክንያት ሊሆን የሚችለዉም የሌላን ሀገር ሉአላዊነት ከመጠበቅ አንጻር ነዉ። አንድ ሀገር ምንም ነገር ወደ ሀገሯ እንዲገባም ሆነ እንዳይገባ የምታወጣቸዉ ህጎች ይኖራሉ። አንዱም ህግ ሊሆን የሚችለዉ አንድ ሰዉ ወደ ሀገሯ ለመግባት በቅድሚያ ሊያሙዋላ የሚገባዉ ቀድመ ሁኔታ ነዉ። ይህንም ቅድመ ሁኔታ ሳያሙዋላ ወደዛ ሀገር የገባ እንደሆነ ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዳደረገ ይወሰዳል። በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ዓ.ም አንቀጽ 8 ላይ በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ሲተነተን “ማንኛዉም ሰዉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ወይም ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት በማሰብ ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲገባ፣ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጣ፣ በኢትዮጵያ ግዛት እንዲተላለፍ ያደረገ ወይም ሰዉን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ዝግጅት ያደረገ፣በሂደት ላይ የተገኘ፣ ያገዘ ወይም የተቀበለ” በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ ስለዚህ ይህን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሌላ ሰዉ እንዲፈጽመው እነዚህ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች የፈጸመም ማንኛዉም ሰዉ በወንጀል ሀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል።
በሌላ በኩል ደግሞ ይሀዉ ተመሳሳይ አዋጅ አንቀጽ 3 ላይ በሰው የመነገድ ወንጀልን ሲያብራራ ``ማንኛዉም ሰዉ ሌላዉን ሰዉ በባርነት ወይም በባርነት መሰል ተግባር ፣በአገልጋይነት ወይም እዳ መያዣነት የያዘዉ ፣አካሉን በማዉጣት ወይም በዝሙት አዳሪነት ወይም መሰል የወሲብ ተግባር ብዝበዛ የፈጸመበት፣በግዳጅ ስራ ወይም አገልግሎት፣በልመና፣ በወንጀል ተግባር ፣በግዳጅ ጋብቻ፣ ወይም በማህጸን ኪራይ ያሰማራ ወይም ህጻናትን በጉልበት ስራ የበዘበዘ ወይም እነዚህን መሰል የብዝበዛ ተግባራት የፈጸመ “ ሲል ያስቀምጣል። ከነዚህ ትርጓሜዎች የምንረዳዉ በሰዉ የመነገድ ወንጀል ተጎጂዉን በቀጥታ በመጠቀም የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ደግሞ ተጎጂዉን በማጓጓዝ ድንበር በማሻገር የሚፈጸም ወንጀል ነዉ። በሌላም በኩል በሰዉ መነገድ ወንጀል በአብዛኛው ከተጎጂዉ ፍቃድ ውጪ በሆነ መንገድ የሚፈጸም ወንጀል ሲሆን ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል የተጎጂዉ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህም ወንጀሎች ሲፈጸሙ በተለያየ መንገድ እገዛ ያደረገ ማንኛዉም ሰዉ የራሱ የሆን ቅጣት እንደሚጠብቀዉ ከዚሁ አዋጅ መረዳት ይቻላል።
በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል የሚገዛበትን ህጎች ስንመለከትም
1. በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ዓ.ም
2. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲ የወጣዉ የወንጀል ህግ አዋጅ ቁጥር 414/2016 ዓ.ም ከአንቀጽ 596-አንቀጽ 598 ያሉት
3. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ያሳለፈዉ ዉሳኔ ቁጥር 55/25 በአገራችን አዋጅ ቁጥሮች 736/2004 እና 737/2004 እንደጸደቀዉ የመሳሰሉት ያሉ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩልም እነዚህን ህጎች በስራ ላይ ለማዋል ያወጣቸዉ ደንብና መመሪያዎች አሉ።
1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዎች መነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ተጎጂዎች የቅብብሎሽ ሥርዓት መመሪያ፣
2. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዉ የመነገድ እና ሰዉን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር የትብብር ጥምረትአባላት፡የስራ ቡድኖችን አደረጃጀት እና አሰራር ለመወሰን የወጣ መመሪያ
3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰዎች የመነገድ እና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር ምክር ቤት እና የትብብር ጥምረት ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 126 /2014 ናቸው።
በዚህም መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ በክፍለ ከተማዉና በስሩ ባሉ ወረዳዎች የጥምር ቡድኑ ተመስርቶ ወደ ሰራ የገባበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። የጥምር ቡድኑም ፦
1. የግንዛቤ ፈጠራ፤የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት የስራ ቡድን
2. የተጎጂዎች መልሶ ማቋቋም የስራ ቡድን
3. የወንጀል መከላከል እና የህግ ማስከበር የስራ ቡድን
4. አለም አቀፍ እና ውጪ ግንኙነት ጉዳይ የስራ ቡድን
5. በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል መረጃና አስተዳደር የሥራ ቡድን
6. የጥናትና ምርምር የስራ ቡድን፣
7. እንዲሁም ወደፊት እንደየሁኔታዉ ሊጨመሩ የሚችሉ ቡድኖች ታሳቢ ተደርጎ በመመሪያዉ ተካቱዋል።
በቦ/ክ/ከ/አ/ፍ/ጽ/ቤት/የሕ/ስር/ምክ/መ/ዳይሬክቶት
ዐ/ህግ ዉብአለም መስፍን
ታህሳስ ወር,2015 ዓ.ም